‹‹..ጥሩ ነው ወጣት መሆን፡፡ ገንዘብ ባይኖርህም ጤና ይኖርሃል፡፡ መልክ ባይኖርህም አንጎል ይኖርሃል፡፡ ደስታ ባይኖርህም ንዴት ይኖርሃል፡፡ ፍቅር ባይኖርህም ተስፋ ይኖርሃል፡፡ እውቀት ባይኖርህም ጉራ ይኖርሃል፡፡ መጨቆን ቢበዛብህ ሬቮሊሽን ታነሳለህ፡፡ መኖር ቢያስጠላህ ወይም ቢያቅትህ ራስህን ትገድላለህ፡፡ ሠው ባያውቀውም ቅሉ ታሪክ ይኖርሃል፡፡ ወጣት ነህና፡፡… ››
(ትኩሳት - ስብሐት ገ/እግዚአብሔር)
🤖🤖🤖
የትኩሳቱ ባህራም እጅግ የሚደንቀኝ ባህሪ ነው። ኢራናዊ ሆነ እንጂ ከአማርኛ ስነፅሁፍ ታላላቅ ገፀባሕርያት አንዱ ይሆን ነበር። የምናብ ውጤት ሳይሆን ስጋ የለበሰ፣ ደም የሚዘዋወርበት፣ ልቡ የሚመታ የእውነት የነበረ ሰው መሆኑ ይበልጥ ይደንቀኛል።
©©©
ባህራም ከልቡ ኮምዩኒስት ነው። አሜሪካንና ኢምፔሪያሊዝምን አምርሮ ይጠየፋል። ከስብሃት ጋር የተዋወቁት በአንድ አጋጣሚ ነበር።
ስብሐት ብዙ ግዜ የሚተኛው ጠዋት ነው። ከሰአት እነተመስገን ክፍል ስለሚገቡ ቁልፋቸውን ተቀብሎ ሲፅፍ ይውላል። ማታ? ማታማ የኤክስን ጎዳናዎች ንጉስ ይሆንባቸዋል። ብቻውን በአውራ ጎዳናዎቹ ይዘዋወራል።
ከምሽቱ በአንደኛው እንደተለመደው ሲዘዋወር አንድ ጥግ ላይ አንዱ ኢራናዊ ከሁለት አሜሪካውያን ጋር ትግል ገጥሟል። አበሻነቱ ነሽጦት ጠጠር አንስቶ አነጣጥሮ ወረወረ። አንዱን አሜሪካዊ ግንባሩ ላይ አገኘው። ወዲያው ደንግጠው ሁለቱም ሸሹ።
ኢራናዊውን ያውቀዋል። ከነተመስገን ጋር ብዙ ግዜ ያየዋል። አጠገቡ ሲደርስ ልብሱን እያራገፈ ይስቃል። ያ ኢራናዊ ባህራም ነበር። ባህራም ኢትዮጵያዊ ጓደኞች ነበሩት። ስለዚህ ከስብሃት ጋር በአይን ይተዋወቃሉ። ያን ቀን ለመጀመሪያ ተጨባብጠው ተዋወቁ።
ባህራም በተሰባበረ ፈረንሳይኛ
"ጣልያኖችንም ያባረራችኋቸው በዚሁ ድንጋይ የመወርወር ጥበባችሁ ነው እንዴ?!" ብሎ ይቀልዳል። "እኛም አሜሪካኖችን ከሃገራችን ለማባረር ጥሩ መሳሪያ ሳይሆን አይቀርም" አለ ባህራም እየሳቀ።
ፈረንሳይኛው ብዙ የሰዋሰው ስህተት አለው። ቢሆንም ለመግባቢያ በቂ ነው። በቀልዱ አብረው ከሳቁ በኋላ
"ሰልፍ ዲፌንስ እንደምታውቅ እነ ተመስገን ነግረውኛል። ለምን አልተጠቀምክበትም"
"ምክንያቱም ኮምዩኒስት መሆኔን ይደርሱበታል"
ካለ በኋላ "ሃለላሴ ሙት" አለ በአማርኛ። ሁለቱም ከልባቸው ሳቁ።
በመጨረሻ
"የኢትዮጵያ እና የኢራን ወዳጅነት ለዘለአለም ይኑር"
"Yankee go home" አለ። ከዚያ በኋላ እያፏጩ እየተሳሳቁ ወደ ሲቴ አመሩ።
©©©
ባህራምና ኒኮል የፍቅር ጓደኞች ናቸው። የተገናኙት ፓርቲ ላይ ነው። ኒኮል በየምሽቱ አለመጠን ጠጥታ ካገኘችው መንገደኛ ጋር አብራ የማደር ባህሪ(one night stand) አምጥታ ነበር። በአንዱ ምሽት ሰክራ ከባህራም ጋር ወደቤቱ ሄዱ። ጠዋት ስትነቃ ራሷን ባህራም አልጋ ውስጥ አገኘችው። ጫፏን አልነካትም። ባህራም በግዜ ተነስቶ ቁርስ እያበሰለ ነበር። መንቃቷን ሲያይ በታላቅወንድማዊ የቁጣ ቃና
"በቃ ካገኘሽው ወንድ ጋር ጠጥተሽ ማደር ጀብዱ፣ አዋቂነት ይመስልሻል አይደል" አላት።
"በገዛ ህይወቴ ምንም አያገባህም" አለች እየተቆናጠረች።
"እንዴት አያገባኝም?! እኔም እህት አለኝ እኮ። እህቴ እንዲህ ስትሆን እንዴት አያገባኝም።"
ኒኮልና ባህራም ከዚህ ወዲህ የማይለያዩ ጥንዶች ሆኑ። የሚወራው ግን ሌላ ነው። ይቺ ባለ አመዳም ከንፈር ባህራምን ያማለለችው በገንዘብ ነው። ቤቶቿ ሃብታም ስለሆኑ ብዙ ብር ይልኩላታል እየተባለ ይወራል። ባህራም በድንቅ ስብእናው እንዳማለላት የሚያውቁት ጥቂቶች ናቸው።
©©©
ስብሐት ስለ ባህራም እንዲህ ይላል፦
ባህራም ሰውነቱ በፀጉር የተሸፈነ ነው። ግን ንፁህ ልጅ ነው። ፈረንሳይኛው የተሰባበረ ነው። ቢሆንም ትልቅ ስብእናውን ከማየት አላገደኝም። አያችሁ ሰዎች በሚናገሩበት ግዜ ከመልእክታቸው በቃላት የሚያስተላለፈፉት 20% ብቻ ነው። የቀረውን የምንረዳው ከአካላዊ ገፅታቸው ነው። የባህራም የተሰባበረች ፈረንሳይኛ የምትገልፀው የስብእናው መጠን 20% ነው። ዋናውን የሰውዬውን ስብእና የምትረዳው በፊቱ ገፅታ፣ በእጆቹ እንቅስቃሴ፣ በድምፁ ቃና ነው። ለዚህ ነው ባህራም በፈረንሳይኛ ቢንተባተብም ታላቅ ስብእናውን ስብሐት ከማየት ያላገደው።
©©©
ነገር ግን ይህ የተሰባበረ ፈረንሳይኛ በትምህርት ውጤቱ ላይ ጣጣ አመጣበት። አስተማሪዎቹ ስለ መልሱ ትክክለኛነት እንጂ ስለ ተፈታኙ ስብእና አያገባቸውም። ባህራም በአንዱ ትምሀርት F አመጣ። ወደቀ። አንድ አመት ደገመ። ይህንኑ በተሰባበረው ፈረንሳይኛው ለስብሐት በሚያሳዝን ቃና ይነግረዋል፦
"ፈረንሳዮች በቋንቋቸው ስትመጣ አይወዱም። የማይረባ ሃሳብ በትክክኛ ሰዋሰው ከነገርካቸው ያደንቁሃል ፣ ያጨበጭቡልሃል። ሃሳብህ ምን ትልቅ ቢሆን ፈረንሳይኛህ ከተሰባበረ አይሰሙህም። ተራው ህዝብ እንዲህ ነው። ፐሮፌሰሮቹም እንዲህ ሲሆኑ ግን ይገርምሃል። እኛ በደንብ የምናውቀውን ፅንሰሃሳብ ፈተንሳይኛውን አምጠን እንደምንም 3 ገፅ እንፅፋለን። ፈረንሳዮቹ በቋንቋቸው እየተራቀቁ 6 ወይም 7 ገፅ ይፅፋሉ። ታዲያ ፕሮፌሰሮቹ ሃሳብህን አያዩም። ሰዋሰውን እየመዘኑ ይጥሉሃል። አሁን ተመልሼ የማላገኘው አንድ አመት ባከነብኝ። እኔም፣ ቤተሰቤም፣ ሃገሬም አንድ አመት ተነጠቅን።
©©©
ኤክሳንፕሮቫንስ ውስጥ ከመላው አለም የመጡ ብዙ ተማሪዎች አሉ። ተማሪዎቹ በስኮላርሽፕ የሚማሩ ሲሆን ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ወጪ የሚመሩት ከቤተሰቦቻቸው በሚላክላቸው ገንዘብ ነው። የባህራም ቤተሰቦች ግን ገንዘብ መላክ አቁመዋል። ባህራም እጅግ ተጨንቋል። በመጀመሪያ ለደህንነታቸው። ለጥቆ ለኑሮ የሚያስፈልገውን ገንዘብ የሚያገኘው ከነሱ በመሆኑ። ቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራት ተቆጠሩ። የቤተሰቦቹ ጉዳይ ግን የውሃ ሽታ ሆነ። ለቀናት የሚበላው አጥቶ ተራበ። ክብሩን ረሳ። ቀጥ ብሎ አከራዩ አሮጊት ጋር ሄደ። ርቦኛል አላት። ዳቦና ወተት ሰጠችው። ሆን ብሎ ሰክሮ አብሯት አደረ።
©©©
በአማርኛ ስነፅሁፍ ውስጥ የሚደንቁኝ አራት ስብእናዎች አሉ። የፍቅር እስከ መቃብሩ ጉዱ ካሳ፣ የሰንሰለቱ ስነወርቅ፣ የሀዲሱ ሀዲስ እና አራተኛው የትኩሳቱ ባህራም ናቸው።
🤖🤖🤖
ኒኮል
ኒኮልን የሚከጁሏት ብዙ ናቸው።ባህራም ጓደኛዋ ነው ፣ ጃምሺድና ሉልሰገድ በድብቅ ይተኟታል።። እንደውም ለጃምሺድ እና ልዑልሰገድ ሞት ምክንያት የሆነችው ኒኮል ነች።ስብሐትም በወሬ ብቻ የሚያውቀውን የጭኗ ውስጥ ሙቀት እያለመ በስሜት ይቃጠላል።
ተካ ደግሞ አለ። ሴት መተኛት ያምረውና ኒኮልን ሲያያት ጥሩ ምርጫ ሆና አገኛት―ዘርዛራ ጥርስ፣ አመዳም ቆዳ፣ ባህራም እራሱ የሚተኛት ለገንዘቧ ብሎ መሆን አለበት ሲል አሰበ። አንድ ቀን ቤቷ ሲሄድ ብቻዋን አገኛት።
"ምነው ያለወትሮህ" ብትለው
" ለአንቺ የሚሆን ጨዋታ አለኝ" አላት።
አካሄዱ ሲገባት፣ በትህትና ቤቷን ለቆ እንዲወጣ በሩን አሳየችው። ተካ ግን ዘወትር ሌሎች ሴቶች ላይ እንደለመደው፣ እጇን ጠምዝዞ ፣ ፀጉሯን ጨምድዶ ፣ በጥፊ እያጮለ በሃይል ሊገናኛት ሞከረ። ኒኮል እያለቀሰች ነፍሰጡር መሆኗን ስትነግረው ግን፣ የሱሪውን ዚፕ ቆለፈና፣ ከቤቷ ውልቅ ብሎ ወጣ።
ብዙም ሳይቆይ፣ ባህራም በሌላ ጉዳይ ተናዶ ቤት ሲመጣ፣ ኒኮልን ፀጉሯን ተንጨባሮ ፣ ፊቷ ደም መስሎ ፣ እያለቀሰች አገኛት። ጉዳዩን ከኒኮል አፍ እንደተረዳ፣ ተካን ፍለጋ በፍጥነት ከቤት ወጣ። ኒኮል ደግሞ፣ ባህራም ተካን ካገኘው ይጎድለዋል ብላ ስለፈራች ከኋላ ሱክ ፣ ሱክ እያለች ትከተለዋለች።