Latest Posts from ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 (@bookshelf13) on Telegram

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 Telegram Posts

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"
18,903 Subscribers
2,716 Photos
24 Videos
Last Updated 27.02.2025 06:07

Similar Channels

Jafer Books 📚
27,452 Subscribers
FIDEL POST NEWS
18,369 Subscribers

The latest content shared by ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 on Telegram


— ለሁላችን መልካም ጊዜን እመኛለሁ!

© Assaf Hailu

በኢትዮጵያዊ ሁለ ውስጥ የሞላ፣
______

(ልብ የሚሞላ ቅድስና!)

እኔ ግን የቱንም ያህል ተቃራኒ እውነታ ለትንግርት ቢከመር በዚህች ሀገር ተስፋ አልቆርጥም!

ይቺ ሀገራችን የሆነ የምትኖርበት ምሥጢር አላት። የሆነ ተዓምር አምቃለች። የሆነ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ዝም ብሎ በአየሩ ላይ እየተንሳፈፈ የሚኖር አንዳች ጥልቅ ምሥጢር አለ።

የሆነ በመጨረሻ ከመጨረሻው የከፋ ነገር የሚከልለን ተዓምር አለ። ይሄ ሁሉ ዘመናዊው ዓለም ሄዶ ሄዶ ቢጠፋ፣ ቢጠፋፋ፣ የሆነ እንዲቀርልን የተፈለገ፣ እንድንተርፍበት፣ እንድንጠበቅበት የተፈለገ አንዳች መንፈሳዊነትን የተላበሰ ነገር አለ በኢትዮጵያችን።

ብዙ ጊዜ የማስበው ነገር ነው ይህ። ደሞ የማገኛቸው ድርሳናት ሁሉ ይሄንኑ የሚያጠናክሩልኝ ናቸው። የሆነ ዘመኑን የሚጠብቅ ታላቅ ትንሳዔ አለ በምድራችን።

ትንቢት አይደለም ይህ። ብዙ ጥናቶች፣ ምርምሮች እየደጋገሙ የሚሙጡበት ድምዳሜ ነው። ይመጣሉ፣ ይመረምራሉ፣ መንገዶች ሁሉ ወደኛ ያመራሉ።

ከዚያ ግን ሲመጡ አያገኙትም። ልክ የበረሃ ውሃ በአሸዋ ውስጥ ሠርጎ እንደሚጠፋ፣ የሆነ ቦታ ላይ ሲደርሱ ዳናው ይሰወርባቸዋል። But they can feel it. They know in their hearts that there's something sacred in this land!

There's something continuing from the ancient in the spirits of these people ይሉናል ሲደመድሙ ስለኛ።

የሙሴ ፅላት እኛው ጋር አለ። ቅዱስ ፅዋው እኛው ጋር ነው። ታቦቱ የእሱም አቅጣጫ እኛው ጋር ነው የሚያመላክተው። ግማደ መስቀሉ እሱም አለ በዚህችው ምድራችን ላይ።

የቀደሙት ሁሉ ነገሥታት ባህሩንና ውቅያኖሱን ሁሉ አጥብቀው የሚሸሹ ናቸው። ይህን ነገር ከየትም አላገኘሁትም። ግን ደጋግሜ ራሴን የምጠይቀው ጥያቄ ነው።

ለምንድነው ለሺህ ዓመታት ምስጢራቸውንና ምድራቸውን እየተከላከሉ የቆዩ ቀደምቶቻችን ከጠረፉ እና ከባህሩ ይልቅ ወደ heartlandዱ፣ ወደ መሐል እምብርት ምድራቸው ማፈግፈግን የሚመርጡት? የሆነ የሚያውቁት ምሥጢር መኖር አለበት! እንደዚያ ይመስለኛል ታሪካቸውን ስመለከት።

የሆነ ሊመጣባቸው ያለ መቅሰፍት የታያቸውና የሚያውቁ ነው የሚመስሉት። ደግመው ደጋግመው ወደ ተራሮችና ወደ መሐል እምብርት ውስጥ ወደታነፁ ገዳማት፣ በረሃዎች፣ ሃይቆችና ደሴቶች ሥርቻ ውስጥ መሸሸግን ይመርጣሉ።

የሆነ ወደፊት የሚመጣ የዓለም ጥፋት ያለ እና በዚህች ቅዱስ ምድር ተጠልለው የሚያመልጡ ነው የሚመስለው።

ይህች ምድራችን በመጨረሻው የዓለም ጥፋት የኖህ መርከብ ሆና የሰው ዘር የሚተርፍባት ቅድስት ምድር ትመስለኛለች። There's something mysterious about our whole existence and ways of life!

ለማንኛውም እነዚህ የሙሴን ፅላት አድራሻ ከየዓለሙ ሁሉ ጥግ ሊያፈላልጉ የተነሱ ሁለት በዓለም የታወቁና በኢትዮጵያ ምሥጢራት ጉዳይ ላይ እጅግ ከፍ ያለ ክብር የተቸራቸው ተመራማሪዎች፣ ብዙ ነገሮችን ያስሱ፣ ይፈነቅሉና... በመጨረሻ የሙሴ ፅላት በየዓለሙ ሁሉ አለ ይባላል። ግን በኛ እምነት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፅላት እውነተኛው ፅላት ነው ይላሉ።

ይህን ልንል የቻልነው ደሞ መንፈሱ በሀገሪቱ ሁለመና ሰፍፎ በግልፅ የሚታይ፣ በቀልብህ የሚገባ፣ የሚታወቅህ... ስለሆነ ጭምር ነው ይላሉ።

ወደ አንድ የኢትዮጵያኖች መንፈሳዊ በዓል፣ ወይ ቅዳሴ፣ ወይ አኗኗር፣ ወይ አክሱም፣ ወይ ላሊበላ፣ ወይ የሰዉ ልብስና አኗኗር፣ ወይ ወደ ጎጆ ቤቶቻቸው፣ ወይ ሐይማኖቱ ምንም ይሁን ኢትዮጵያኖችን ልብለህ እያቸው እስቲ? ይላሉ።

በየሰዉ ውስጥ የምታየው በዘመናዊው ምዕራባዊው ዓለም የረከሰ ቁሳዊ ግልሙትና የማይደረመስ አንዳች ዓይነት ከሺህዎች ዓመታት በፊት ብቻ ልታገኘው የምትችለው የተቀደሰ ጥንታዊ ሥሪት አለ በየሰዉ ሁሉ የዕለት ተዕለት ህይወት ላይ ያረበበ።

እውነት ይመስለኛል። ዓለምን ሁሉ እንመስላለን። ዓለምን ሁሉ እንወክላለን። ተቀይጠናል። ከዓለሙ ጋርም፣ እርስ በርሳችንም። ግን እንለያለን። ዓለም ሲጠፋፋ በመጨረሻ በፅላቱ ተዓምር የምንተርፍ እኛ ሳንሆን አንቀርም!

የእጣናቸው ሽታ ራሱ ወደሆነ ጥንታዊ ዓለም ይወስደኛል ይላል አንደኛው ተመራማሪ🙏🏿! ፈገግ አልኩ። አንተ ዕጣን ትላለህ፣ ጥንታዊውን መንፈስ ያልተሸከመ ምን ነገር አለ በምድራችን?

ጠጅ ሣሩና አሪቲውስ? ቄጠማና ሉባንጃውስ? ያገር ልብሱስ? ሹሩባውስ? ተነፋነፍና ጥልፍ ቀሚሱስ? ምጣድና አክንባሏችንስ? ጊርጊራና ማራገቢያዎቹስ? ምድጃና ከሰሉስ? ኩሽናችንስ? ሁሉነገራችንስ?

ከመላው አፍሪካ ተነጥለን፣ በሌሎች ዓለማት ገዢዎች ዋና ጥንታዊ ሥሪታችን እንዲጠፋብን፣ እንዲቋረጥብን ያልተደረግን ብቸኛ ነፃ የአፍሪካ ሕዝቦች ስለሆንን... ሁለነገራችን ጥንታዊውን ነገር ያስታውሳቸዋል። ..

የጥንቱን መንፈስ ይቀሰቅስባቸዋል። እንደነዚህ ሪሰርቸሮች፣ ቀና ልብ ያላቸው ይወዱታል። ይፈልጉታል። በአልባሌ መጠቅለያ ውስጥ የዋለውን የከበረውን ነገራችንን ያዩታል። አኗኗራችን በሆነ የተቀደሰ ጥንታዊ መንፈስ የተባረከ መሆኑንም ይመሠክሩልናል።

ጥያቄው እኛስ ግን ተቀብለነዋል? የሚለው ነው። እኛስ ያንን ጥንታዊውን የተቀደሰውን እኛነታችንን እንደ ትርፍ አንጀትና እንግዴ ልጅ ቆርጠን ለመጣልና ትውልድ በማይደርስበት ሥፍራ ለመቅበር ነው መከራችንን እየበላን ያለነው? ወይስ continuityያችንን ለመጠበቅ?

የፅላቱ ታማኝ ጠባቂዎች ነን? ወይስ አደራ በላዎች? የተቀደሰች ምድራችንን ጥለን የምንፈረጥጥ? ነፍሳችን የምታቀነቅነው ዜማ ምንድነው?

በገና ዋዜማ ሳይቸግረኝ ይሄን የቅዱስ ፅላቱን መፅሐፍ ገልጬ... ተወስጄ ቀረሁ! ስለኛ ያልተፃፈልን ነገር የለም! ያኮራል! ልብን ይነፋል ኢትዮጵያዊ መሆን! ኪስን ባይነፋም ልብን ይነፋል! በእውነት!

ፈጣሪ ኢትዮጵያችንን አብዝቶ ይባርክ!

የትውልዶቻችንን ልብ ይጠብቅ!

መልካም የገና በዓል እመኛለሁ!

አበቃሁ!

🙏🏿❤️

© Assaf Hailu

የሴትልጅ ቁንጅና ምንድነው?
_______

(ውበትና ደም-ግባትስ?)

"ቁንጅና ምንድነው ሰዎች አስረዱኝ
እኔ እሷን ወድጄ ታምሜያለሁኝ...
ውበትና ቁንጅናሺ፣ ይማርካል ለሚያይሺ.."

- ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ

በየዘመኑ "የሴት ልጅ ውበት" የሚባለውን አስተሳሰብና መስፈርት ማን ፈጠረው? "ቆንጆ" ሴት ከቆንጆ ሰው በምን ትለያለች? ሴቶች በ"ሽንጥና ዳሌሽ ሲታዩ..." ዓይነት መስፈርቶች እንዲለኩ የበየነላቸው ማነው?

ወንዶች ሴቶችን የሚስሉበት መንገድ ከስሜት ጋር የተያያዘ ለምን ሆነ? ከወሲባዊ መስህብ አሊያም ከመራባትና ከእናትነት አስተሳሰቦች ውጭ ሊታሰብ የሚችል የሴት ልጅ ሰብዓዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ከየማኅበረሰቡ አንጎል የተነነው በምን ምክንያት ነው?

ውበት ምንድነው? ደርባባነትን ከሴት ልጅ ለምን እንድንጠብቅ ሆንን? በዘመናት ውስጥ የተቸራቸውን ማኅበራዊ ተክለሰብዕናና የተሰጣቸውን ሚና ለመጫወት እምቢ ያሉ ሴቶች ዕጣፈንታ ምንድን ነበር? አሁንስ ምንድነው?

ወንዶች በጥቅሉ ለሴቶች ያለን ዝንባሌ በጎችንና ፍየሎችን ሽንጣቸውን ለክተን፣ ጥርሳቸውን ፈልቅቀን፣ ሸሆናቸውን መትረን ለመግዛት ከምንሄድበት መንገድ ብዙም ያልተለየ ሆኖ የሚገኘው በምን የተነሳ ነው? ተፈጥሯዊ ነው? ወይስ ማኅበራዊ?

የሴቶች ተፈጥሯዊ ሰዋዊ አገልግሎት ምንድነው? ብለን ነው የምናስበው? ለምን?

የሴትን ልጅ አካላት ዕርቃን እያወጡ የተሳሉ አያሌ ክላሲካልና ሞደርን የጥበብ ሥራዎች (ሥዕሎች፣ ቅርፃቅርፆች፣ ስነፅሑፎች፣ ሙዚቃዎች፣ ወዘተ.) ለምን በየዓለሙ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ሆኑ?

የሰውልጅ ሴትን ልጅ ከsensual pleasure ውጭ ለማሰብ ያልቻለበት አብይ ምክንያቱ ምንድነው? ሴቶችስ ራሳቸውን ከመኳኳልና ከማጊያጌጥ፣ ሽንጥና ዳሌያቸውን ከማጉላት፣ ፀጉራቸውን ከመሾረብና በአልባሳት ከመሸለም ውጭ ያለውን ጥልቅ የራስ ማንነታቸውን ለመፈለግ ብዙ ዝንባሌ የማያሳዩት ለምንድነው?

በሴትነት ውስጥ ከማኅበራዊው መስፈሪያ ሚዛን የማፈንገጥ ዋጋው ምን ያህል ነው? ይህች ዓለም የማን ዓለም ነች?

እውን It's a man's man's world እንደሚባለው.. ዓለማችን የወንዶች ብቻ ዓለም ነች? ከሆነች ሴቶች የተነጠቀ ሙሉ የሰውነት ክብራቸውንና ዋጋቸውን ለማስመለስ ምን ያድርጉ?

የፆታ አስተሳሰባችን በምን በምን ነገሮቻችን ውስጥ ሥር እንደሰደደ፣ እስከ ምን ከፍታ እንዳሻቀበና እንዴትስ ተብሎ እንደተድበሰበሰና እንደተሸነገለ ልብ ብለን አስተውለነዋል?

ሴትነት ምንድነው? ወንድነትስ? ውበትስ? የሴት ልጅ ውበት ምንድነው? ሴትን ልጅ ያለ ጭንና ባቷ ለማሰብ ፈቃደኝነቱ ያለው ወንድ ከመቶ ስንት ፐርሰንት ነው? ራሷን ከቀሚሷ ውጭ አድርጋ ማሰብ የምትችልስ ሴት ከመቶ መሐል ስንት ትገኛለች?

የነዳጅ ዘይትን የሚተኩ በርከት ያሉ የኃይል አማራጭ ቴክኖሎጂ ተገኝተዋል በዘመናዊዋ ዓለማችን። ግን የዔለም ኢንዱስትሪ ሁሉ ከነዳጅ ጋር የተያያዘ ነው። ዲዛይኑ፣ ሸቀጡ፣ ንግዱ፣ ኢኮኖሚው፣ ቴክኖሎጂው፣ መኪናው፣ መርከቡ፣ አውሮፕላኑ... ሁሉ ከነዳጅ ጋር የተሳሰረ ነው። በዚህ የተነሳ ዓለም የሚያውቀውንና ህልውናውን የመሠረተበትን ኋላቀሩን ነዳጅ ዘይት መተው አይፈልግም። የሴት ልጅ ውበትስ ተመሣሣይ ነገር ይኖረው ይሆን?

በዓለም ሁሉ "የሴቶችን ውበት" መሠረት አድርገው የሚመረቱ ምርቶች፣ ዲዛይኖች፣ ፅሑፎች፣ ሳይንሶች፣ ፊልሞች፣ ኢንደስትሪዎችና ማኅበራዊ አወቃቀሮች... ባንዴ ተንደው እውነተኛ የሴቶችን ሙሉ ሰውነትና ክብር ወዳረጋገጠ ዘመናዊ አስተሳሰብ መሻገር ይችላሉ? የሚቻል ነው? ሴቶች ቂጥና ፊታቸው እየታየ የሚመዘኑበት ዘመን እስኪያበቃስ ስንት ዓመት ይፈጃል?

ይህ የናዖሚ ዎልፍ መፅሐፍ ላለፉት 3ሺህ ዓመታት የተቀነቀኑ የስነውበት ፍልስፍናዎችን፣ ሳይንሶችንና አስተሳሰቦችን እጅግ ጥልቅ በሆነ መንገድ ይቃኛል። አጥብቆ ይሄሳል። እና የውበትን ትርጉም እንድንፈትሽ ያስገድዳል።

ሴቶች ከወንዶች የውበት መስፈርት ራሳቸውን ማላቀቅ አለባቸው፣ ነፃ መውጣት አለባቸው ትለናለች።

በምጥን ፈገግታዋና በመርገፍ ቀሚሷ ዓለምን የምታማልለው ሞናሊዛ የኋላቀሩ ዘመን ማስረጃ ሆና ተቀድዳ የምትጣልበት፣ የፒካሶና የሌሎች በዓለም የተደነቁ የእርቃን ሴቶች ሥዕሎችና ኃውልቶች ተጠራርገው ወደ ቆሻሻ ቅርጫት የሚጣሉበት፣ የሴት ልጅን ሉዓላዊነት ያከበረ፣ ኮርማዊውን የወንዶች ዓለም የገረሰሰ፣ አዲስ የሴቶች ነፃነት ዘመን መበሠር አለበት ትላለች።

ከዚህ በፊት "ዘ ሴክስ ኦፍ ቲንግስ" የሚል አስገራሚ መሠል ይዘት ያለው በአንዲት ጀርመናዊት-እንግሊዛዊት ሪሰርቸር ዶክተር የተፃፈ አንድ ዳጎስ ያለ መፅሐፍ አግኝቼ ስገረምና የያዝኳቸውን ሁሉ የሴትልጅ አስተሳሰቦች ስሞግት ቆይቼ ነበር።

ይህን መፅሐፍ ካነበብኩ በኋላ ደግሞ ብርቱካን ከንፈርሽ፣ ብርንዶ ትንፋሽሽ፣ የዘንባባ ማር ይመስላል ፍቅርሽ፣ ፅጌረዳ ስላንቺ ልጎዳ፣ ሐር ይመስላል ፀጉርሽ፣ ሎሚ ተረከዝሽ፣ ስልታዊ ውዝዋዜሽ፣ ዓይናፋርነትሽ፣ ችቦ አይሞላም ወገብሽ፣ ካንቺ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት፣ እና አንቺን ያለውን በቴስታ ጥርሱን🤩... የመሣሰሉትን የምወዳቸውን የሙዚቃ ስንኞች ከአዕምሮዬ ለማጥፋት ምን ዓይነት ላጲስ መጠቀም እንዳለብኝ በማሰላሰል ላይ ነኝ🤓!!!

ይህች ደራሲና ተመራማሪ፣ ሶስተኛው የፌሚኒዝም አብዮት ተብሎ የሚጠራውን አስተሳሰብ ያፈለቀችና ለዓለም ያስተዋወቀች ጉምቱ ምሁር ስለመሆኗ ከተለያዩ ዜና መወድሶች ለመረዳት ችዬአለሁ።

ለማንኛውም ሃሳቦቿ የያዝካቸውን የሴት ልጅ ውበት ኮተቶች ሁሉ ያስጥሉሃል። ግን ፍራቻዬ ያለንን አስጥላን... በምትኩ የምትሰጠን ውበት ምን ዓይነት እንደሆነ ደራሲዋም ራሷ በትክክል ያወቀችው አልመሠለኝም።

ሽንጥና ዳሌሽ ሲታዩን ትተን... ወደ ምን እንሻገር? ውብ የምንላትን ሴት ከየት እናግኛት? ከስንደዶ አፍንጫና ከማር ከንፈር ውጭ ያለችዋ ቆንጆ ሴት ማነች? ከወዴትስ ትገኛለች? እውን አለችስ ወይ በዓለም ላይ? ሴቶቹ ራሳቸውስ ይቀበሏታል?

ደራሲዋ የምትሰብከን ሴቶች ከሙክትነትና ከጌጥነት አሊያም ከስሜት ማስተንፈሻነት የወረደ የወንዶች አስተሳሰብ ነፃ የሚወጡባት ዓለምስ እውን በዚህ የቅርብ ዘመን ትውልድ እውን ሆና እናያት ይሆን? ...

የወንዶች አሽኮርማሚነት፣ እና የሴቶች ተሽኮርማሚነት አብቅቶ፣ ማንም ማንንም የማያሽኮረምምባትን ዓለም የምናየው መቼ ነው? መቼ ነው ያቺ የፍፃሜ (ዋንጫ) ቀን መምጫዋ? ምን ምልክትስ እንጠብቅ?

ወንድሜ (እና እህቴ🤩)... በበኩሌ ጥይቴን ጨርሼያለሁ!

በዚሁ ባበቃስ?

መልካም ጊዜ!

🙏🏿❤️

© Assaf Hailu

ያደጉ አገሮች ግንባታውን እንደአካባቢው ሁኔታ ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ እንዲቋቋም አድርገው ይሰራሉ፡፡ ሁኔታውን ስለሚያውቁት ይዘጋጃሉ፡፡ እንደኛ እያደጉ ባሉ ደሃ ሃገራት በአደጋው ዙሪያ የግንዛቤ እጥረት ስለሚኖር እና አደጋውን ሊቋቋም የሚችል ግንባታ ስለማይደረግ ክስተቱ ቢፈጠር ባለማወቅ እና ባለመዘጋጀት ብቻ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት መገመት አይከብድም፡፡

በሀገራችን ዘመናዊ ትምህርት ከ100 አመታት በላይ ታሪክ አስቆጥሯል፡፡ ስለዚህ በሎጂክ እና በሳይንስ ማመን አለብን፡፡ አብዛኛው ከተሞቻችን የተመሰረቱት ስምጥ ሸለቆን ተከትለው ነው፡፡ እነዚህ ከተሞች አዲስ አበባን ጨምሮ በስምጥ ሸለቆ ዳርቻዎች መሆናቸው በጥንት ቢታወቅ ኖሮ ለዋና ከተማነት ተመራጭ አይሆኑም ነበር፡፡

ብዙ ኢኮኖሚ የሚፈስበት ግንባታ በደንብ መጠናት አለበት፡፡ በተለይ መሠረቱ የሚወጣበትን ቦታ በጥልቀት መመርመር በሚያስችል መሳሪያ በመታገዝ ቅድመ ጥናት መደረግ አለበት፡፡ አንድ ከተማ ከመከተሙ በፊት መምረጥ ይቻላል፡፡ የኋላ ታሪኮችን ስናይ አንድ ከተማ ታስቦበት አይቆረቆርም፡፡ በ1906 በኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ተፈጥሮ በመሳሪያ የተመዘገበው ትልቁ የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 6.8 ሲሆን በወቅቱ በነበረው መረጃ አዳሚ ቱሉ የተባለችው ከተማ አካባቢ እንደተነሳ ይነገራል፡፡ ከዛ በኋላ በተደረገውም ምርምር ከወደ ምስራቃዊ ፕላቶ አካባቢ እንደተነሳ ያሳያል፡፡ በዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከአዳሚ ቱሉ የተነሳው ንዝረት የእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያንን ደውል ማንም ሳይነካው እንዲደውል አድርጓል፡፡ ከዚህ መረዳት የምንችለው እንዲህ ዓይነት ክስተት የመፈጠር እድሉ መኖሩን ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ቅርብ ርቀት ላይ 6.8 በሬክተር ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ ተነስቷል፡፡

በክፍል ሦሥት ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንውሰድ የሚለውን እንመለከታለን፡፡

© ሰርቫይቫል 101/Survival 101

==መሬት ለምን ይንቀጠቀጣል? በስምጥ ሸለቆውና ዳርቻው ያለን ልብ እንበል==
(ክፍል ሁለት)

ሁኔታው በኢትዮጵያ ውስጥ በማንኛውም ሰዓት ሊፈጠር ይችላል፤ በተለይ የስምጥ ሸለቆን ታከው የሚገኙ ከተሞች፤ ይህ መረጃ አስፈላጊ በመሆኑ ለሌሎችም ያካፍሉ፤ ያዳርሱ፡፡...

==የመሬት መንቀጥቀጥ በምስራቅ አፍሪካና በኢትዮጵያ==

አብዛኛውን ጊዜ ዶ/ር አታላይ አየለ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጂዮ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስ አስትሮኖሚ ተቋም የመሬት መንቀጥቀጥ ባለሙያ የስጋት አስተያየታቸውን በሬድዮ ሲሰጡ እንሰማለን፤ እስኪ ለዛሬ ስጋታቸውን እንጋራ፡፡ ከክፍል አንድ የቀጠለ...

በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ለሚፈጠረው መሬት መንቀጥቀጥ መንስኤው ምንድን ነው? ካልን ከመሬት ከርስ በተለያየ መጠን እና ሁኔታ ወደላይ የሚወጣ ቅልጥ አለት አለ፡፡ ይህ የተለያየ መጠን ያለው ቅልጥ አለት ወደላይ ለመውጣት በሚያደርገው ግፊት የሚፈጠረው ውጥረት የመሬት መንቀጥቀጦችን ይፈጥራል፡፡ እሳተ ገሞራዎችም ይፈነዳሉ፡፡ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ክስተቱ እየተደጋገመ ሲሄድ የመሬት ቅርፊተ አካል(Crust) እየተደረመሰና እየሳሳ በመሄድ ለስምጥ ሸለቆ መፈጠር ምክንያት ይሆናል፡፡ የቀይ ባህር፣ የኤደን ባህርሰላጤና የምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆዎች የዚህ አይነት ተፈጥሮ ሲኖራቸው የሚገናኙትም አፋር ውስጥ ነው፡፡ መገናኛ ቦታውም የአፋር ሦስትዮሽ መገናኛ (Triple Junction) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ በሳይንሱ የቀይባህርና የኤደን ባህረሰላጤ ስምጥ ሸለቆዎች ከዛሬ 30 ሚልዮን ዓመት በፊት አልነበሩም ይባላል፡፡ የየመን ምዕራባዊ ክፍል እና የሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ክፍል የገጠመ ነበር፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊያጠቃቸው ይችላሉ ተብለው የተለዩ አካባቢዎች አሉ ወይ? ብለን ብንጠይቅ አብዛኞቹ የሃገራችን ከተሞች አዲስ አበባን ጨምሮ ከስምጥ ሸለቆ የራቁ አይደሉም፡፡ ምናልባት በሃገራችን ምዕራባዊ ክፍል ባህርዳር፣ ጎንደር እና ወለጋ አካባቢ ደህና ይሆናል፡፡ እንዲሁም በምስራቃዊው የሃገራችን ክፍል ጎባና ሮቤ ሊድኑ ይችላሉ፡፡ ከነዚህ ውጪ ሌላው ከመሬት መንቀጥቀጥ እይታ ውጪ አይደለም፡፡ መቀሌን ብንወስድ የስምጥ ሸለቆ ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡ ወደታች ብንወርድ ወልድያ እና ደሴ ከስምጥ ሸለቆ ጫፍ አይርቁም፡፡ ድሬዳዋና ሃረር ያሉበት ሁኔታ ብዙም ባይርቅም የተሻለ ነው፡፡ ጥፋት ሊደርስ የሚችል የመሬት መንጥቀጥ ያለው በምዕራባዊ ዳርቻ ነው፡፡ አሁን በማደግ ላይ ያሉት ከተሞች አዳማ፣ ሻሸመኔ እና ሃዋሳ ስምጥ ሸለቆ ውሥጥ ናቸው፡፡ የሚገኙት በጣም አሳሳቢ በሚባል ቦታ ላይ ነው፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ እና እሳተ ገሞራ በጣም የተቆራኙ ናቸው፡፡ ነገር ግን ሊፈነዳ የሚችል እሳተ ገሞራን ክትትል ከተደረገበት አስቀድሞ ማወቅ ይቻላል፡፡ በአካባቢው አየር(ጋዝ) እና አመድ መሰል ብናኝ ቅንጣጦች የሚስተዋሉ ከሆነ እንደ ጥቆማ ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም የሚፈጠረውን ንዝረት በማጥናት ሊፈነዳ የሚችልበትን ወቅት መገምገም ይቻላል፡፡ ባይፈነዳ እንኳን ለጥንቃቄ ዝግጅት ይደረጋል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥን ከተመለከትን ባልታሰበ ሰዓት ሊፈጠር የሚችል እውነታ ነው፡፡ በመሆኑም መጠኑን ፣ ጊዜውን እና ቦታውን ለመተንበይ በጣም ከባድ ነው፡፡

መቸም ከጃፓኖች የመጠቀና ያደገ አገር የለም፡፡ በብዛት፣ በዓይነት እና በጥራት ድንቅ የሚባሉ ሳይንቲስቶች አሏቸው፡፡ የበርካታ ቴክኖሎጂዎች ባለቤትም ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በ2011 ዓ.ም ወደ 2 ሺህ የሚደርሱ ዜጎቻቸውን በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በተፈጠረው የሱናሚ አደጋ አጥተዋል፡፡ ይህ ጉዳት የደረሰው መተንበይ ባለመቻላቸው ነው፡፡ ነገር ግን በየትኛውም አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊፈጠር እንደሚችል ስላወቁ የሚሰሩዋቸውን ፎቆች ደረጃቸውን የጠበቁ በማድረግ እና ህዝባቸውን በማስተማር ሊደርስ የሚችለውን መጠነ ሰፊ ጥፋት ይቀንሳሉ፡፡ ብዙውን ግዜ አደጋን ለመቋቋም መፍትሔው ህዝብን ማስተማር በመሆኑ ጃፓኖች ችግሩን ህዝባቸው እንዲያውቅ አድርገዋል፡፡ ከት/ቤት ጀምሮ እያንዳንዱ የጃፓን ህፃን የአካባቢውን ሁኔታ እንዲውቅ ይደረጋል፡፡ ይህን ሁሉ አድርገው እንኳን አደጋውን መተንበይ ሳይችሉ ቀርተው ብዙ ሰዎች ይሞታሉ፤ ይባስ ብሎ የ2011 መሬት መንቀጥቀጥ ሱናሚ በማስከተሉ፣ የሱናሚው ሞገድ ደግሞ የኒዮክለር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ማቀዝቀዣ ስላበላሸው ተደራራቢ የተፈጥሮ አደጋ ተፈጥሯል፡፡

ታዲያ ይህ ሁሉ ከሆነ ስለመሬት መንቀጥቀጥ ማጥናት ጥቅሙ ምንድን ነው? ብለን ልንጠይቅ እንችላለን፡፡ የዚህ ጥናት ዋና ጥቅሙ አደጋውን ማስቀረት እንደማይሆን የሚታወቅ ነው፡፡ ዋናው ነገር የት የት አካባቢ ሊከሰት እንደደሚችል፣በምን ያህል መጠን እና እንዴት እንደሚፈጠር መንስኤውን ለማወቅ ይረዳል፡፡ ይህ ሁኔታ ከታወቀ ደግሞ የጥንቃቄ ስራዎች እንዲሰሩ ያደርጋል፡፡ ይህንን ሁኔታ ለማየት ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን በሃይቲ እና በቺሊ የተፈጠረውን የመሬት መንቀጥቀጥ መመልከት ነው፡፡ የሃይቲው በሬክተር መጠን መለኪያ 7፣ የቺሊው ደግሞ 8.8 የተመዘገቡ ነበሩ፡፡ ቺሊዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ሊያጠቃቸው እንደሚችል ቀድመው በጥናት ስላወቁ አቅማቸው በሚፈቅድላቸው የቴክኖሎጂ እና ኢኮኖሚ መጠን ጥንቃቄ ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ ህንፃዎች፣ ድልድዮች እና መንገዶች ሲሰሩም ምን አይነት ደረጃ መጠቀም እንዳለባቸው ስላወቁ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊከሰት ይችላል ተብሎ የተለዩ ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎችንም የጥንቃቄ መልዕክት በማሰራጭት ሰዎች አካባቢውን እንዲለቁ አድርገዋል፡፡ በተቃራኒው የሃይቲ መንግስት እና ህዝብ ግን ምንም አይነት ግንዛቤ ስላልነበራቸው በተፈጠረው አደጋ ምክንያት በችግር እስካሁን ተዘፍቀው በድንኳን ይኖራሉ፡፡ አደጋው በ2010፣ ከ220,000 በላይ ሰዎችን ጨርሶ ከ300,000 በላይ ሰዎችን ደግሞ አቁስሏል፤ ክስተቱ ሃገሪቱን አውድሟት ነው ያለፈው፡፡ ግንዛቤ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ማህበረሰቡ፣ መንግስት እና ባለሃብቶች ስለችግሩ ቀድመው ቢረዱና ቢያውቁ፣ ትምህርት ቢሰጣቸው ኖሮ እንደዚህ የከፋ አደጋ ጥሎ ባልሄደ ነበር፡፡

ወደ አገራችን ስንመለስ አሁን በአዲስ አበባ ውስጥ እየተገነቡ የሚገኙ ህንፃዎች ሊፈጠሩ የሚችሉ አደጋዎችን ከግምት ውስጥ ያስገቡ ናቸው ለማለት አያስደፍርም፡፡ ምክንያቱም አስገዳጅ ህግ ያለ አይመስልም፡፡ የትኞቹ ህንጻዎች ወይም ድልድዮች አደጋውን ይቋቋማሉ፣ አይቋቋሙም የሚለውን ችግሩ መጥቶ ሲታይ ካልሆነ በስተቀር ማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ በከተማው ውሥጥ ብዙ ህንፃዎች ይገኛሉ፡፡ ትምህርት ቤቶች፣ የጋራ መኖሪያ ህንፃዎች እና ሌሎችም ህንፃዎች የኮለን ስፋታቸው እና እርዝመታቸው ሲታይ ንዝረት ቢመጣ ምን ይሆናል የሚለውን ስናስብ የሚያስፈራ ነው፡፡

በ1910 ዓ.ም ታንዛኒያ በሬክተር ስኬል 7.4 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ አጋጥሟት ነበር፡፡ በዚሁ ሳምንትም በታንዛኒያ በሬክተር ስኬል 5.7 ያስመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ 17 ሰዎችን እንደገደለ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ በ1990 በደቡብ ሱዳን 7.2፣ በ2006 በሞዛምቢክ እና በአካባቢው 7.0 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ አደጋ ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ ባለፉት መቶ ዓመታት የተከሰተ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ኋላ ከሄድን የመሳሪያው ቴክኖሎጂ ሳይመጣ የተከሰቱ የእግዜር ቁጣ ተብለው የተመዘገቡ ብዙ ክስተቶች ነበሩ፡፡ ታሪኮቹን በቤተክርስቲያን ድርሳናት ማግኘት ይቻላል፡፡

==መሬት ለምን ይንቀጠቀጣል?==

(ክፍል አንድ)
ሁኔታው በኢትዮጵያ ውስጥ በማንኛውም ሰዓት ሊፈጠር ይችላል፤ በተለይ የስምጥ ሸለቆን ታከው የሚገኙ ከተሞች፤ ይህ መረጃ አስፈላጊ በመሆኑ ለሌሎችም ያካፍሉ፤ ያዳርሱ፡፡

==የመሬት ውስጣዊ አወቃቀር==
መሬት ሙሉ በሙሉ በጠጣር ቁስ የተሞላች አይደለችም፡፡ መሬት የተዋቀረችው ከሦሥት ዋና ዋና ንብርብር ንጣፎች ነው፡፡ እነርሱም፡- ቅርፊተ አካል(Crust)፣ የምድር ማዕከል ንጣፍ(Mantle) እና ውስጠ እምብርት(Core) ናቸው፡፡ (አወቃቀሩ በስዕላቂ መግለጫ ውስጥ ይገኛል ተመልከቱት፡፡)

• ቅርፊተ አካል(Crust)፡- ይህ ስስ የሆነ የመሬት የላይኛው ንጣፍ ነው፡፡ እኛ የምንንቀሳቀስበትን የመሬት ወለል ይወክላል፡፡

• የቀለጠ አለት(Mantle)፡- ይህ በመሬት ቅርፊተ አካል እና በመሬት ውስጠ እምብረት መከካከል ቀልጦ የሚዋልል የቀለጠ አለት ነው፡፡

• ውስጠ እምብርት(Core)፡- ይህ የመሬት ውስጠ እምብርት ክፍል ሲሆን ስሪቱም ብረት ነው፡፡

==የመሬት ውስጠ እምብርት ምን ያክል ሞቃት ነው?==
የዚህን ጥያቄ መልስ ማንኛውም ተመራማሪ በእርግጠኝነት ይህን ያክል ነው ብሎ አይናገርም፤ ነገር ግን የውስጡ ክፍሎች በጣም ሞቃት እንደሆኑ የሚመሰክሩ ማስረጃዎች በመሬት ገፅታዎች ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ሁኔታም በእሳተ ገሞራዎች ፍንዳታ እና ቀልጠው በሚፈሱ አለቶች መልክ ማየት ይቻላል፡፡

==መሬት መንቀጥቀጥ==
የመሬት ዉጫዊው ክፍል በተለያዩ ቅርፊት መሰል አካላት(plates) የተሸፈነ ነዉ፡፡ የነዚህ ቅርፊት መሰል አካላት ዉፍረት በአማካይ ከ(20-60) ኪ.ሜትር ወደ መሬት ስር ይዘልቃል፡፡ እነዚህ ቅርፊት መሰል አካላት በመካከላቸዉ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የኃይል መጠራቀም ይፈጥራል፡፡ የኃይል መጠራቀሙም እየጨመረ ይሄድና የአለቱ አካል ሊሸከመዉ ከሚችለዉ አቅም በላይ ሲሆን ይደረመሳል፡፡ ይህ በከፍተኛ ጫና ታፍኖ የነበረ ኃይል በድንገት ሲያፈነግጥ የሚወጣዉ ከፍተኛ ኃይል በመሬት የላይኛዉ ቅርፊት አካል ላይ በሞገድ መልክ በፍጥነት ይሰራጫል፡፡ የዚህን ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተፈጠረ ወይም ተከሰተ እንላለን፡፡ የነዚህ ቅርፊት መሰል አካላት እንቅስቃሴ ሁኔታ እና መጠን እንደየአካባቢዉ ይለያያል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ ጥናት ሴስሞሎጂ (Seismology) ይባላል፡፡ ቃሉም የግሪክ (Seismos) ሲሆን ትርጉሙም መንቀጥቀጥ ማለት ነዉ፡፡

እነዚህ ቅርፊት አካሎች(Plates) አንዱ ከሌላዉ የሚለይበት እጅግ በጣም ረዥም የሆነ ስንጥቅ ይገኛል፡፡ ይህ ስንጥቅ የተለያዩ መዛነፎችን ይፈጥራል፡፡ ይህ አጠቃላይ ስንጥቅም የዝንፈት መስመር(fault line) ይባላል፡፡ በዝንፈት መስመር የሚለያዩ ቅርፊተ አካሎች(Plates) እጅግ ግዙፍ እንደመሆናቸዉ መጠን አንደኛዉ በሌላኛዉ ላይ ተፅዕኖ ማድረሳቸው የማይቀር ነዉ፡፡ በመሆኑም እነኚህ የተለያዩ ቅርፊተ አካሎች እርስ በርሳቸዉ በተቃራኒ አቅጣጫ አንዱ ከሌላኛዉ ሊሸሽ ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ቅርፊተ አካሎቹ እርስ በርሳቸዉ ተደጋግፈዉ የሚኖሩበትን መንገድ ስለሚያመክን በከፍተኛ ጫና ምክንያት አለቶቹ ተያይዘዉ እንዲደረመሱ ሲያደረግ ታምቆ የቆየዉ ኃይል በማፈንገጥ የሚለቀዉ ኃይል ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ይፈጥራል፡፡ ከዚህ ማዕከላዊ ቦታ የሚነሳዉ ከፍተኛ ሞገድ በሁሉም አቅጣጫ በመሰራጨት እረጃጅም ስንጥቅ መስመሮችን እየሠራ በመቀጠል የላይኛዉን የመሬት ንጣፍ ገፅታ ያመሰቃቅላል፡፡

ከተፈጥሮአዊ ምክንያቶች በተለየ ሁኔታ የሰዉ ልጅ አንዳንድ እቅስቃሴዎችም የመሬት መንቀጥቀጥ ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፡- የተለያዩ መርዛማ ዝቃጮችን ለማስወገድ ተብለዉ የሚቆፈሩ ጥልቅ ጉድጓዶች፣ ዉሃ ለማከማቸት ተብለዉ የሚቆፈሩ ጥልቅ ጉድጓዶች፣ በመሬት ዉስጥ ለዉስጥ ለኒዩክለር ጦር መሳሪያ ሙከራዎች የሚቆፈሩ መተላለፊያዎች፤ ሰዉ ሰራሽ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ የእነዚህ ድርጊቶች መስፋፋት ከተፈጥሮአዊዉ የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ተፅእኖ በመፍጠር የመሬት መንቀጥቀጥ ሊያስከትል ይችላል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያስከትለዉ ዉድመት አደጋዉ የደረሰበት አካባቢ ያለዉ የመሬት አቀማመጥ፣ መንቀጥቀጡ የሚቆይበት ጊዜ እና መንቀጥቀጡ የሸፈነዉ ክልል ይወስነዋል፡፡ ህንፃዎች የተሠሩበት የንድፍ ዓይነት እና ለግንባታ ጥቅም ላይ የዋለዉ የቁስ ዓይነትም የአደጋዉን አስከፊነት ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ ይችላል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ ማስተዋል ከምንችለዉ በጣም ዝቅተኛ የንዝረት መጠን አንስቶ እስከ ብዙ ሺህ ኪ.ሜትሮች የሚደርስ የሞገድ ነዉጥ ሊፈጥር የሚችል ነዉ፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ላይኛዉ ቅርፊተ አካል ላይ የሚገኙትን ህንፃዎች ፣ድልድዮች እና ግድቦች እንዲፈርሱ በማድረግ በአጭር ጊዜ ዉስጥ እጅግ በጣም ከባድ የሆነ ጥፋት ሊያደርስ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከባህር ወይም ከዉቂያኖስ ከፍተኛ የሆነ የዉሃ ሞገድ ሱናሚ(Tsunami) በማስነሳት እና ወደ የብስ በማምጣት ለመገመት የሚያዳግት ጥፋትን ያደርሳል፡፡ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ተተክለዉ የሚገኙ መሳሪያዎችም የመሬት መንቀጥቀጦችን ከተለያዩ ቦታዎች ላይ በየቀኑ ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡ በእርግጥ ከእነዚህ ዉስጥ አደጋ የመፍጠር አቅም ያላቸዉ በጣም ጥቂቶች ናቸዉ፡፡

ባለፉት 500 ዓመታት በዓለማችን ላይ ብዙ ሚሊዮን ሰዎች ሕይወታቸዉን በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት አጥተዋል፡፡ የብዙ አገራት የመሠረተ ልማት አዉታሮች እና ንብረቶች እንዳልነበር ሆነዉ አልፈዋል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥን ቀድሞ መተንበይ በጣም አዳጋች ቢሆንም በቂ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ፡-ለምሳሌ ስለ አደጋዉ ትምህርት በመስጠት፣ የአደጋ ጊዜ እቅዶችን በማዉጣት እና በማሰልጠን ፣ጠንካራ እና ተጣጣፊ(ከሁኔታዉ ጋር የሚስማማ) ንድፍ ለህንፃዎችም ሆነ ለሌሎች መሠረተ ልማቶች በመጠቀም ሊደርስ የሚችለዉን አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይቻላል፡፡

==ዝርግ ንጣፎች እንዴት ይንቀሳቀሳሉ?==
ዝርግ ንጣፎች የጎንዮሽ በተቃራኒ አቅጣጫ ሊፋጩ ወይም በተቃራኒ አቅጣጫ ተቀራርበው ሊገፋፉ ወይም በተቃራኒ አቅጣጫ ሊራራቁ ወይም በተቃራኒ አቅጣጫ በቁመታቸው ሊፋጩ ይችላሉ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ እነኝህ ንጣፎች የሚገናኙበት ቦታ መረጋጋት የተሳነው እና ብዙ ክንውኖች ያሉበት ቦታ ነው፡፡ ለምሳሌ በስዕል እንደምትመለከቱት ሁለት የተለያዩ ዝርግ ንጣፎች በተቃራኒ አቅጣጫ ቢራራቁ በሁለቱ ዝርግ ንጣፎች ታፍኖ የነበረው የቀለጠ አለት በከፍተኛ ኃይል መገንፈሉ የማይቀር ነው፡፡ ያም ካልሆነ ደግሞ በሁለቱ ዝርግ ንጣፎች በተቃራኒ አቅጣጫ መራራቅ ምክንያት(የአብዛኞቹ ስምጥ ሸለቆዎች የተፈጠሩበት መንገድ) የሚፈጠረው የአለቶች መናድ ከፍተኛ ንዝረቶች በመፍጠር መሬትን ማንቀጥቀጡ የማይቀር ነው፡፡(ስዕላዊ መግለጫዎችን ይመልከቱ)

በዝንፈት መስመር(የቅርፊተ አካሎች መዋሰኛ) ላይ በእንቅስቃሴዎቹ ምክንያት የሚፈጠረው ከፍተኛ ጫና የሚፈጥረው የኃይል መጠራቀም አለቱ መሸከም ከሚችለው አቅም በላይ ሲሆን የሚከሰተው የአለቶች መሰባበር እና መደርመስ በሁሉም አቅጣጫ ሞገዱ በመሰራጨት እና ከፍተኛ ንዝረት በመፍጠር የመሬት መንቀጥቀጥን ያስከትላል፣ የመሬት ገፅታም ምስቅልቅሉ ይወጣል፡፡

==የመሬት መንቀጥቀጥ ልኬት==
የመሬት መንቀጥቀጥ ልኬት የሬክተር ስኬልን(Recter scale) በመጠቀም ይከናወናል፡፡ ዘዴው የሚጠቀመው የሂሳብ ቀመሮችን በመሆኑ በጣም ልከኛ ነው፡፡ ትልቅ ቁጥር ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያመለክተው ትልቅ ጥፋትን ነው፡፡ በስዕል ውስጥ ያለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ፡፡

አንድ የሬክተር ስኬል ቁጥር ከቀዳሚው ቁጥር በአስር እጥፍ ኃያል ነው፡፡ ይህንን የመሬት መንቀጥቀጥ የሚለካው መሳሪያ ሳይስሞግራፍ(Seismograph) ይባላል፡፡ ከተለያዩ ቦታዎች የሚወሰዱትን የሬክተር ስኬል(Recter scale) መረጃዎች በንፅፅር በማየት የመሬት መንቀጥቀጡ ከየት አካባቢ እንደጀመረ ለመለየት ይረዳል፡፡

በክፍል ሁለት የመሬት መንቀጥቀጥ በምስራቅ አፍሪካ እንዲሁም በኢትዮጵያ ምን ይመስላል? ሁኔታው ያሰጋናል ወይ? የሚለውን እንመለከታለን፡፡ ወደፊት በክፍል ሦሥት ደግሞ ሁኔታው ሲፈጠር ምን አይነት ፈጣን እንርምጃ እንውሰድ የሚለውን እናያለን፡፡

© ሰርቫይቫል 101/Survival 101

“የት ነው የምትማሪው? ... ኦ ማይ ጋድ! ከንፈርሽ ደሞ ሲያምር ...”
መልስ ጥበቃ እየሳቀ ያየኛል። የትምህርት ቤቴ ስም ድምፀቱ ከድህነቴ በላይ የሻከረ ነበር። “አብዮት ቅርስ” ብዬ ብነግረው ይህ ስስ ልጅ ተቆርሶ ቢወድቅስ? ሰበበኛ። የጎረቤታችንን የስልክ ቁጥር ስሰጠው እሱ ደግሞ የገዛ ቤታቸውን ስልክ ቁጥር ነገረኝ። በዓይኑ ድሪያ ተጠምቄ ተለያየን።

ካወቅኩት ወራቶች አልፈዋል፤ ነገር ግን በሁለት አማልክት መካከል ሕሊናዬ ይታመስ ስለነበር ከስልክ በቀር ላገኘው ፈቃደኛ አልነበርኩም። አንድ ቅዳሜ "ጭማቂ ልጋብዝሽ!" የሚለው ውትወታውን ያለምንም ማንገራገር ተቀበልኩ። ያን ሰሞን አውራ ጣቴ ላይ ኃይለኛ ጥፍረ-መጥመጥ ይዞኝ፣ እስከሚያስነክሰኝ ድረስ ታምሜ ነበር። ሕመሙ በጣም ከባድ ስለነበር ሐኪም እንዳይነካኝ በመፍራት ሰበብ ስለቆየሁ ቁስሉ መግሎ፣ አመርቅዞ ነበር። አውራ ጣቴን በፕላስተር ጠቅልዬ፣ ክፍት ጫማ እያደረግኩ ዛሬ ነገ እያልኩ ቤተሰቤን አሻፈረኝ አልታከምም ባልኩ ሰዓት ነበር እንዳልካቸው የደወለው።

ሦስት ወር ሙሉ ሲደውል ገፍቼው ያን ቀን በቀጭኗ ሽቦ ስናወራ አተነፋፈሱ፣ የድምፁ ልስላሴ እና በአጠቃላይ አራዳነቱ ከአባዬ አምላክ ጋር ተመሳሰለብኝ። እንዳልካቸውን መሳም ቅድስና እንደሆነ ዓይነት ስሜት ተሰማኝ።

“ከግዮን ሆቴል ወረድ ብሎ ክርስቲያን የሚባል ጭማቂ ቤት አለ። ትወጂዋለሽ!” ሲለኝ በጥፍረ-መጥምጥ እየተሰቃየሁ እንደሆነ ሳልነግረው የመሳምን ተስፋ በጉያዬ አቅፌ ላገኘው ተስማማሁ።
ያን ቀን ከሰዓት፣ አበባ ጣል ጣል ያለባት ውኃ ሰማያዊ የበጋ ቀሚሴን አጥልቄ፣ ጥፍረ-መጥምጤን የሚደብቅ ከፊቱ ወንፊት ያለው ሰንደል ጫማ ተጫማሁ። የእንጀራ አባቴ አምላክ ጸጉሬ ትከሻዬ ላይ ተዘርግፎ፣ ሽቶ ተነስንሼ፣ ያቺ አጭር ዣንጥላ ቅድ ቀሚሴ ንፋስ እያውለበለባት፣ በሥቃይ እያነከስኩ ቢያየኝ ለመሳምና ለመፈቀር እየከፈልኩ የነበረው መስዋዕትነት ያኮራው ይሆን? ቀጠሮአችን ቦታ እስክደርስ ድረስ በደንብ አነክስ ነበር። በኋላ ግን እንዳልካቸው አጠገቤ ደርሶ አቅፎ ሲጠመጠምብኝ “ለጥፍረመጥምጥም ጊዜ አለው፣ ለመሳምም ጊዜ አለው” የሚል የድፍረት መፈክር በውስጤ ተስተጋባ።

ክርስቲያን ጭማቂ ቤት ለፍቅረኛሞች የተሠራ ነው። ጥንዶች የሚቀመጡበት ወንበሮች በሌላ እንዳይታዩ በኮምበርሳቶ ታጥረዋል። እንደተቀመጥን ሁለታችንም የማንጎ ጭማቂ አዘዘን። ነጣ ያለ ጅንስ ጃኬት ነጣ ካለ ጅንስ ሱሪ አዳቅሎ ለብሷል። ጃኬቱን ሲያወልቅ የቲሸርቱ ንጣት አስገረመኝ። እኛ የጨርቆስ ልጆች ነጭ ልብስን የምናውቀው የተገዛ ቀን ነው። ታጥቦ የተሰጣ ዕለት በጢሳጢስና በአዋራ ስለሚታጠን ከዛን ቀን ጀምሮ ነጫጭ ልብሶቻችን ዘላለማዊ ቡላነትን ይይዛሉ። ይሄ ልጅ፣ ልስመው ጥቂት ደቂቃዎች የቀረኝ፣ ቅምጥል የሀብታም ልጅ፣ ጥርሱ ነጭ፣ ቲሸርቱ ነጭ፣ የጣቴን የመረቀዘ መግላም ቁስል ከንፈሬ አሸንፎ አጠገቡ መቀመጤን ቢያውቅ በደንብ ይስመኝ ይሆን?

አራዳ ነው። ይችልበታል። መጀመሪያ እጆቼን በተራ በተራ ሳማቸውና ጸጉሬን ከግንባሬ ላይ በጣቶቹ ገፋ አድርጎ በቀኝ ጆሮዬ ጀርባ ሽጉጥ አደረገለኝ። በስመአብ የእጁ ልስላሴ። ገና ሳይስመኝ ልቤ ከደረቴ ተስፈንጠራ ልትወጣ ደረሰች።

“ኦ! ... ዚ! ... ጆሮ ጌጥሽ በጣም ያምራል። ሲልቨር ነው?” ብሎ በጣቶቹ የቀኝ ጆሮዬን በስሱ ይዳስሰው ጀመር። ኧረ በጌታ! መልሱ እኮ ቀላል ነበር። “አዎ ሲልቨር ነው” ሆኖ ሳለ መልሱ፤ አፌ ግን ተሳሰረ። "ዚ!" ብሎ የሚጠራኝ አንድ እሱ ብቻ ነው። ከንፈሮቹን ወደ ጆሮዬ በጣም አስጠግቶ በሹክሹክታ “አንድ ነገር ልጠይቅሽ?” ብሎ በከናፍርቱ ጆሮዬን ይዳብስ ጀመር። የእስትንፋሱ ወላፈን ነፍሴን ሲያሞቃት ይሰማኛል። ሳይስመኝ ቀለጥኩ እንዴ? አፌ ተሳስሯል። በውስጤ ግን “አንድ ጥያቄ ብቻ? ኧረ ለምን ሁለት መቶ ጥያቄ አትጠይቀም? እንዲያውም ለአምስት ሚሊዮን ጥያቄ ጊዜ አለኝ።” የእናቴን አምላክ ረገምኩት። እንዲህ ያለውን ፍሰሃ ያስመለጠኝን።

“የኔ ልዕልት! ... ተስመሽ ታውቂያለሽ? የኔ ፀሐይ! ... ይህ ዕንቡጥ ከንፈርሽ ተስሞ ያውቃል?” ትንፋሼ ተቆራረጠ። እያቃሰትኩ ዋሸው። “አዎ”። አሁንም ጆሮዬን እየሳመ “ማን አባቱ ነው የሳመብኝ? ማን ይባላል?” ብሎ ጠየቀኝ። ተርበትብቼ ሳላስበው ከባድ ስም ጠራሁ። “ዕቁባይ!” አልኩት። ውስጤ ከመጠን ያለፈ ይንቀጠቀጥ ጀመር። ፊቱን ወደ ፊቴ አዙሮ በሁለት ለስላሳ እጆቹ ጉንጮቼን አሙቆ አንገቱን ዘንበል አደርጎ ከንፈሬን በከናፍርቱ ዳሰስ አደረገና “ዕቁባይ እንደዚህ ነው የሳመሽ?” እያለ አቀለጠኝ። 'ነፍሴ ገላዬን ተሰናብታ በረረች ወይ?' እስክል ድረስ ሳመኝ ። 'ሴይንት ጆሴፍ ትምህርት ቤት እንደ ሒሳብና ኬሚስትሪ መሳሳምም ያስተምሯቸዋል እንዴ?' ብዬ እስከምደነቅ ድረስ በሚያሳብድ አሳሳም ዋጠኝ። እያረፈ እያረፈ በከናፍርቱ አዳረሰኝ። ዓይኔን ሁሉ ሳመኝ። ቀለጥኩ። ከልቡና ከልቤ ትርታ የሚፈልቀው የፍቅር ቅኝት እያስፈነጠዘ በወሲብ ስሜት አጠመቀኝ። 'ይሄ መለኮታዊ ነው' አልኩ። አሁን የእናቴንም የእንጀራ አባቴንም አምላክ አመሰገንሁ። 'ይህ የብዙ አምላኮች ውጤት ነው' አልኩ። ከንፈር ለከንፈር ተቆላልፎ ሰማይ መብረር። በውስጤ ሦስት ጊዜ “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” አልኩ። የሕንድ አማልክት ሁሉ አልቀሩኝም። ለሺቫ፣ ለቪሽኑ፣ ለብራህማ ለሁሉም ምስጋናዬን አቀረብኩ። ደሞ አሳሳሙን ያጀበበት አጠራሩ ሰባተኛው ሰማይ የሚወስድ ዓይነት ነበር። “የኔ አበባ፣ የኔ ጽጌሬዳ፣ የኔ ልዕልት ... እንጆሪ ነሽ!” ይለኝና ይስመኛል። ከንፈሬን ዳሰስ፣ ነከስ፣ ላላ፣ ጠበቅ፣ ምጥምጥ።  “ዓይኖችሽ ውስጥ ልሰደድ የኔ አልማዝ?” ይለኝና ጸጉሬን እያመሰ አንገቴ ሥር ይስመኛል፣ ይልሰኛል፣ ይነክሰኛል። ዓይኖቼን ይስማል። በአምሳሉ የፈጠረው ካላስተማረው እንዲህ ያለውን አፈቃቀር ከየት ተማረው? እኔስ ከንፈሩን ተቀብዬ በከንፈሬ ስፈትለው ከየት ያየሁትን ነው? እጆቹን ወደ ጡቶቼ መርቼ በውስጤ እዲጨምቃቸው ስማጸነው አመራሩን እግዚያር ካልጠቆመኝ ከየት አባቴ አመጣሁት? ጣቶቹ ጡቶቼ ቅንፍ ላይ ሲደንሱ ያሰማሁት የሲቃ ድምፅ ማን ፈጠረው? ያን ዕለት እርጥበት እንደ ጎርፍ ቢወስድ ተጥለቅልቄ አባይ ወንዝን እቀላቀል ነበር። መላልኤል የኖረውን 895 ዓመት፣ እኔ ዘርትሁን ከወጣቱ እንዳልክ ከንፈር ውስጥ በአንድ ቀን ኖርኩት።

ነገር ግን እግዚያር እንዲህ ዓይነት ደስታ፣ ያለ ሕመም ስለማይሰጥ ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ ሲሆን ተጠራጥሬ ነበር። ወደ ቤቴ መሄጃዬ ሲቃረብ አሳሳሙም መንገብገብ የበዛበት ነበርና ስሜት ውስጥ ሆኖ ሲወራጭ ሳያስበው የጣቴን ቁስል ረገጠው። ሕመሜ በጣም ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ የሲቃ ድምፅ አውጥቼ ቲሸርቱን በሁለት እጆቼ ጨምድጄ ያዝኩት። አያያዜ ዓመፅ ነበረው። ያመረቆዘ የጥፍረ-መጥምጥ ቁስል ማንም ላይ አይድረስ። ፍስሃዬን ባንድ እርግጫ ሲያተንነው ሳላስበው ከውስጤ አውሬ ወጣ መሰል ክፉኛ ደነገጠ። ልደፍረው መስሎት ይሆን? ወይ ምን ይታወቃል ጋኔን የሰፈረብኝ መስሎትም ሊሆን ይችላል። ቲሸርቱን የያዙትን እጆቼን ቀስ ብሎ አላቀቀና በሕመሜ ምክንያት ያቀረሩ ዓይኖቼን እያየ “እንደዚህማ መፍጠን የለብንም። ገና ልጅ ነሽ። መረጋጋት አለብሽ! ደሞ ለምን ታለቅሻለሽ? ” ብሎ ሲጠይቀኝ መቸም 'የጣቴን መግል አፈነዳኸው!' አልለው። በዝግታ “እሺ” ብዬ በሕመም አንገቴን አቀረቀርኩ። ሊሸኘኝ ስንነሳ ፊቱ ላይ ውዥንብር አነበብኩበት። መራመድ እንደ ምጥ እያሰቃየኝ ወደ ታክሲ ከመግባቴ በፊት የሆነ በላስቲክ የተጠቀለለ ስጦታ ሰጠኝ። ቻዎ ስንባባል

ከንፈሬን ትቶ ጉንጬን ሳመኝ።

እንዳልካቸውን ከዛ በኋላ አግንቼው አላውቅም። ያን ዕለት ማታ የሰጠኝን ስጦታ ሳየው CORN FLAKES የሚል የተጻፈበት ካርቶን ነበር። በወተት የሚበላ የሀብታሞች ቁርስ ነው አሉ። እንዲህ ያለው ቁርስ በሰፈሬ ጨርቆስ፣ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ከጨነቀ ሱቅ አጠገብ በምኖርባት ጭቃ ቤታችን ውስጥ ቀምሰን አናውቅም። በነጋታው ሆስፒታል እስክወሰድ ድረስ ሕመሙ ቢያሳብደኝም የእንዳልካቸውን ከንፈር በመቅመሴ የእናቴንና የአባባን አምላክ ከማመስገን ባሻገር የቻይኖቹን ዩኋንግን፣ ኑዋን እና ፓንጉን ሳመሰግን አደርኩ።

“ዘርትሁንም እንዳልክን ሳመች፣ እሱም ልዕልቴ ብሎ ጠራት፣ 895 ዓመት የመሳም ያህል ብዙ ብዙ ብዙ ሳማት፣ ልጅቱም ስለዚህ አሳሳም ጻፈች፣ ብዙም ዓመት ኖረች--” ዘፍጥረት 5፡33

© ትግስት ሳሙኤል

መኃልየ መኃልይ ዘመሳሳም 5፡33

በሃይማኖት በተከፋፈለ ቤት ውስጥ ነበር ያደግኩት። ፓስተሯ እናቴ ከጋብቻ በፊት ምንም ዓይነት ግንኙነት የማይፈቅድ አምላክ ነበር የምታመልከው። በሷ አምላክ መስተዳድር ውስጥ፣ በእርሱ አምሳል የተፈጠሩ በከንፈሩ አምሳል ከንፈር የለገሳቸው እኔን መሰል ኮረዳ ወይዛዝርት ለዘላለም ለማግባት ካልፈለግን ወይ ደግሞ ለማግባት ካልታደልን ለዘላለም ሳንሳም እንሞታለን። እንደዚ የሚመስል ነገር አያስደንቅም?

እናቴ በጥንቃቄ አስልታ የደረሰችበት ነገር መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ዓመት ውስጥ አንብቦ ለመጨረስ በቀን ሦስት ምዕራፍ መነበብ እንዳለበት ነው። በእርሷ ጣራ ሥር የሚኖር ማንኛውም ልጅ ይህንን የንባብ መስፈርት የመከተል ግዴታ ነበረበት። አምላኳ ከሚፈቅደው የሚከለክለው ስለሚበዛ በውስጤ በጣም እበሳጭ ነበር። ጥሩነቱ መጽሐፍ ቅዱሱን ይዘን ከተቀመጥን ማንበብ አለማንበባችንን አየዞረች ለማጣራት ጉልበቱም ሆነ ጊዜውም አልነበራትም። ግን ድንገት ነሽጧት በተለይ እኔን ከያዘችኝ ሁሌም ገና ዘፍጥረት ላይ ነኝ። “በየሱስ ስም! ... ዘርትሁን! ... ምንድነው? ... በዘፍጥረት ነው የተለከፍሽው?” ብላ ለመበሳጨት ሰትዳዳ “እየከለስኩት ነው” እላታለሁ። ይሄን መልሴን ሁሌም ታምነዋለች።

አውነቱን ለመናገር በልጅነት ሕይወቴ ሙሉ፣ ሁልጊዜ ደግሜ ደጋግሜ ሳይጎረብጠኝ የማነበው ዘፍጥረት ምዕራፍ አምስትን ብቻ ነበር። እናቴ "ንባብ ... ጥቅስ ... መንፈሳዊነት ..." ብላ ካምባረቀች፣ ፊት ለፊቷ እንድታየኝ ሆኜ እቀመጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱሴን እገልጥና የተለመደችዋን ዘፍጥረት ምዕራፍ አምስትን እያነበብኩ ስለአምላኳ አሰላስላለሁ። ምዕራፉ “አምላክ እረኛዬ ነው!” ፣ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው!” ምናምን አይልም። ዘፍጥረት ምዕራፍ አምስት ሲዖል፣ ገሃነም፣ ኃጢአት፣ ጽድቅ፣ ንሰሃ፣ ዝሙት፣ የገንዘብ ፍቅር፣ የውኃ ጥፋት፣ በድንጋይ መወገር፣ ሰዶምና ገሞራ፣ የጭን ገረድ፣ የእግዚያር መልአክ የግብጽ የበኩር ልጆችን ገደለ፣ ሰይጣን፣ ሌጌዎን ... ምናምን ምናምን አይልም። ሠላሳ ሁለት ቁጥሮች ያሉት ይህ ሙሉው የዘፍጥረት ምዕራፍ የተቀደሰ ምዕራፍ ነው። “እንትና ይህን ያህል ዓመት ኖረ፤ ከዚያም እንትናን ወለደ። ከዚያም ሞተ” ይላል።

“ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። ስለዚህ ቃይናን በአጠቃላይ 910 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። መላልኤል 65 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ያሬድን ወለደ። መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ 830 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። ስለዚህ መላልኤል በአጠቃላይ 895 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ።”

ባጭሩ ለኔ ይህ የሕይወት መንገድ ነው። ማፍቀር፣ መፈቃቀር፣ መውለድ፣ መወለድ፣ መራባት፣ መኖርና መሞት። መላልኤል ሳይስምና ሳይሳም 895 ዓመት አልኖረም። ሲጀመር ለመራባት መተቃቀፍና መሳሳም መሠረታዊ ነገሮች ናቸው። አንድ ሰው መካን መሆኑ አንኳ መታወቅ የሚችለው በመሳሳም እና በመታቀፍ ሂደት ውስጥ ካለፈ በኋላ ነው። መራባት የማይችልም ይሳማል ለማለት ያህል። የእናቴ አምላክ “ከጋብቻ በፊት ክልክል ነው!” የሚለው ነገሩ ይጎረብጠኛል አንጂ መራባትን ይወዳል። ያ ማለት ደሞ መሳሳምንም ይወዳል እንደ ማለት አይደል? እናቴ ግን ከአምላኳ በላይ ትጨክን ነበር ልበል? ባጭሩ የወንድ ጓደኛ መያዝ አይፈቀድልኝም ነበር። በእናቴና በአምላኳ ሕግ መሠረት መሳሳም ክልክል ነው እንደ ማለት ነበር። አልተዋጠልኝም። ዘፍጥረት አምሰት “መሳሳም ሕይወት ነው” ይል የለ እንዴ?

የተከለከለ ነገር ደሞ እያደር ይስባል። ጠዋትና ማታ ስለመሳም ማሰብ ጀመርሁ። አግዚያር ስንት የሚያሳስበው ነገር እያለ የኔ የዘርትሁን ከንፈር ከጋብቻ በፊት ተሳመ አልተሳመ ጉዳዩ ነው እንዴ? በከንፈራቸው የሚክዱት ሐሰተኛ ነቢያቶች በፈሉበት ዘመን የኔ ከንፈር መሳም በአምሳሉ መሠራቴን ያሳያል እንጂ ኃጢአት ሊሆን አይችልም ብዬ ወሰንሁ።

ወደ አሳደገኝ እንጀራ አባቴ ሃይማኖት ስንመጣ አምላኩ ሕይወት የገባው አራዳ ሽማግሌ ይመስለኛል። ተሰብስበን ፊልም ስናይ ገጸ-ባሕርያቶቹ ድንገት መሳሳም ከጀመሩ አባባ እንደ እናቴ ቲቪውን ለማጥፋት ሪሞት አያሯሩጥም። እንዲያውም የመሳሳሙ ክፍል እያዘገመ ቢያዝናናው ደስታው ነው። እናቴ ስትነጫነጭ “ምናለበት ተያቸው ይዩ!” ይላትና የደስታው ተካፋይ ያደርገናል። እንዲያውም አንዳንዴ የእንጀራ አባቴ አምላክ ነጭ በነጭ የለበሰ፣ ጢሙና ጸጉሩ የሸበተ ሶፋችን ላይ ተቀምጦ የሚጣቀስ አዛውንት ይመስለኛል። ደሞ እየሳቀ የሚጠቅሰው እኔን ነው። “ሂጂ እንዳልካቸውን ሳሚው!” ዓይነት አጠቃቀስ። “የኔ ኮረዳ አንቺም ሰው እኮ ነሽ” ዓይነት አጠቃቀስ። “ይህን ዕንቡጥ ከንፈርሽን የፈጠርኩልሽ እኮ እንድትሳሚ ነው” ዓይነት አጠቃቀስ። ሳያቋርጥ ፈገግ ብሎ እያየኝ የመፍቀድ ዓይነት አጠቃቀስ ይጠቅሰኛል። ይህን ደግ አምላክ በሐሳቤ ሳየው ተንደርድረሽ እቀፊው እቀፊው ይለኝ ነበር። በውስጤ እግዚያር ሰው ሰው ሲሸት እንዴት ደስ ይላል እያልኩ ቀስ በቀስ የእንጀራ አባቴን አምላክ መረጥኩ።

ይህንን ውሳኔ ባደረግኩ ሰሞን ከሦስት ወር በፊት የተዋወቅኩት እንዳልካቸው ሲደውልና ሳወራው የሚሰማኝ የኃጢአተኛነት ስሜት እየቀነሰ ሄደ። ትውውቃችን ደስ የሚል ግን በጥድፊያ፣ በሹክሹክታ፣ በመሳሳቅ እና በመሳቀቅ የታጀበ ነበር። ኦሎምፒያ ጋር ያለው ቤተማርያም ክሊኒክ ውስጥ በስፔሻሊስት ሐኪም ለመታየት የገባችው እናቴን ፈዝዤ እየጠበቅኩ ሳለ ይህ ለግላጋ ወጣት ጃኬቱን እንዳቀፈ አጠገቤ ቁጭ እለ። መጠበቂያ ክፍል ውስጥ በጣት የምንቆጠር ሰዎች ነበርን። ተክለፍልፎ መጥቶ እኔ ዘንድ ቁጭ ማለቱ አስገረመኝ። ጥቂት ደቂቃዎች እንኳ ሳያርፍ "ጠይም ቆንጆ ይታመማል እንዴ?" ብሎ በፈገግታ ቃኘኝ። አፈርኩና አንገቴን ሰበርኩ።

“አይዞሽ እናትሽ ናቸው አብረሃት ሁን ያሉኝ”። ወቸጉድ! እናቴ ይሄን ልታደርግ እንደ ማትችለው ሳይታለም የተፈታ ነው። ግራ እንደ ገባኝ አውቆ ማብራራቱን ቀጠለ። “እናትሽን የሚያክማቸው ዶክተር ወንድሜ ነው። ዛሬ ምሳ ሊጋብዘኝ ተቃጥረን ቢሮው ውስጥ እያወራን እያለ እናትሽ ሊታከሙ ሲገቡ እንግዳ ማረፊያ ጠብቀኝ አለኝ። ከዛ አራዳዋ እናትሽ እንዲያውም ልጄ ብቻዋን ናት አብረሃት ጠብቅ አይሉኝ መሰለሽ። ሊያጣብሱን ይሆን እንዴ?” አለና ከትከት ብሎ ሳቀ። ቀለል ያለ ደስ የሚል የሞጃ ልጅ። ልክ እንደ ሴት ጥርት ያለ ጭንቀት የማይችል። ፊቱ ያሳሳል። በሻካረው የጨርቆስ እጆቼ ጉንጮቹን ብዳብሰው ከረከረኝ ብሎ ያለቅስ ይሆን? በውስጤ ሳቅኩ።

“እንዳልካቸው እባላለሁ! ስምሽ ማነው?” ብሎ ጠየቀኝ። 'ዘርትሁን' ብዬ ሙሉውን ስሜን መናገር የጨርቆስ ልጅ መሆኔን የሚያሳብቅብኝ ስለመሰለኝ ብዙም ሳላንገራግር “ዘሪት” አልኩት።

“ኦ! ከዛሬ ጀምሮ 'ዚ' ብዬ ነው የምጠራሽ!” አለና “ልገምት ልገምት 12ተኛ ክፍል ነሽ አይደል?” ብሎ ጠይቆኝ፤ መልሴን ሳይጠብቅ የሴይንት ጆሴፍ ተማሪ አንደነበረና አሁን አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ፍረሽማን አንደሆነ አጫወተኝ። ከአሁን አሁን ፓስተሯ እናቴ መጣች አልመጣች እያልኩ በሰቀቀን እና በደስታ አወራው ጀመር።