Latest Posts from ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 (@bookshelf13) on Telegram

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 Telegram Posts

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"
18,903 Subscribers
2,716 Photos
24 Videos
Last Updated 27.02.2025 06:07

Similar Channels

Dr. Eyob Mamo
79,375 Subscribers

The latest content shared by ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 on Telegram


የFintopio አሰራር እና ዳይመንድ እንዴት እንደምትወጣ ቪድዮውን ይመልከቱ።
© 433 - Crypto

የተከፈለበት ማስታወቂያ!

Fintopio ይባላል። በየሰዓቱ ለ10 ደቂቃ ምትቆየዋን አስትሮይድ ቀስ እያሉ ታብ ታብ በማድረግ 💎 (ዳይመንዷን) ማውጣት ነው። ቀላል ነው። ለምሳሌ ጠዋት 1 ሰዓት ሲል መጥታ ለ10 ደቂቃ ትቆያለች። በቀጣይ ምትመጣው ቀጣይ 2 ሰዓት ሲል ለ10 ደቂቃ ነው። ስለዚህ በየሰዓቱ እየጠበቁ በጥንቃቄ ታብ ማድረግ ግድ ይላል።

ኤርድሮፑ የሚያሸልሙ ሳምንታዊ እና ወርሃዊ ውድድሮች አሉት። ሳምንታዊው ምንም ኢንቪቴሽን ሳያስፈልገው ራሳችን በምንሰራው ማይን ብቻ የሚያሸልም ነው። ይሄም ጓደኛ ለመጋበዝ አዳጋች ለሚሆንባቸው የበዪ ተመልካች እንዳይሆኑ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በዚህ ውድድር ከ1 እስከ 10 ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች እንደየደረጃቸው ከ1.5k እስከ 40k ብር ይሸለማሉ።
እዚህ ላይ 1ኛ=333$
                2ኛ=222$
                3ኛ=111$ እያለ እስከ 10ኛው ድረስ ሽልማቱ ይቀጥላል ማለት ነው።

በአንጻሩ ወርሃዊው ውድድር ላይ አንደኛው: ኢንቫይት አድርገን በምናገኛቸው ሪፍራሎች ከሚሰሩት ላይ ከያንዳንዱ 10% ለኛ ተደምሮ እንወዳደራለን። እዚህ ጠንክረን ሰው ካስገባን እና እነሱ ተግተው ሚሰሩ ከሆነ እኛ ተጠቃሚ እንሆናለን። ስለዚህ ይሄን ውድድር ለማሸነፍ የምንጋብዛቸው የሰው መጠን እና ውጤታቸው ይወስናል። ሁለተኛው ደግሞ እንደሳምንታዊው ውድድር ካለምንም ሪፍራል ቦነስ በኛ ልፋት ብቻ የሚያሸልመን ይሆናል። ከ1 እስከ 50 ለሚወጡ አሸናፊዎች ከ6k እስከ 400k እንደየደረጃቸው ይሸለማሉ።
እዚህ ላይ 1ኛ=3,333$
                2ኛ=2,222$
                3ኛ=1,111$ እያለ እስከ 50ኛው ድረስ ሽልማቱ ይቀጥላል።

በነገራችን ሽልማቱ ትክክለኛ ነው። የተረጋገጠ ነው። ይከፍላል። ሰርች አድርጋችሁ ማጣራት ይቻላል። ሳምንታዊው እና ወርሃዊው ውድድር ዛሬ ተጀምሯል። ሳምንታዊው ቀጣይ አርብ ሌሊት ያበቃል። ወርሐሃዊው ከ30 ቀን በኋላ። አዲስ ስትሆኑ task ውስጥ ገብታችሁ fintopio ዋሌት በመክፈት 100k 💰እና ደግሞ ቴሌግራም ዋለታችሁን ሊንክ በማድረግ ብቻ 200k 💰 በጥቅሉ 300k 💰 በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ። አሰራሩን በቪዲዮ። የበለጠ መረጃ ከፈለጋችሁ 👉 @nehmeya13 ያናግሩኝ። ጌሙን ለመጀመር…

👇👇👇

https://fintop.io/TVKHVFf5

አሚታብ ማለት ለህንዳውያን ምን ማለት እንደሆነ ታውቁታላችሁ ፡ አሁን አሁን እንኳን የጤናው ነገር አሪፍ ነው ። በአንድ ወቅት ግን አለፍ አለፍ እያለ ህመም ብጤ ይሰማው ነበር ።
....
እና አንዳንዴ ህመሙ ባስ ብሎበት ሆስፒታል መግባቱ ከተሰማ. . የሆስፒታሉ ዙሪያ ፡ መንገዱ ሁሉ እዛው ውለው ፡ በሚያመሹ የአሚታብ አድናቂዎች ይሞላል ።
...
አሚታብ እንግዲህ ይህ ነው ። እና ሰሞኑን በአንድ የቲቪ ሾው ላይ ሲናገር. .. ትንሽ ዘና ለማለት ወደ ለንደን ሄጄ ነበር አለ. ..
....
እና አሚታብ በለንደን ቆይታው ፡ አንዳንድ ነገሮችን ሊሸማምት ወደ ገበያ ይወጣል ።
....
ከዛም ብራንድ የሆኑ ውድ ልብሶችን ወደሚሸጥ መደብር ገብቶ ልብሶችን ክራቫቶችን ሲያይ ከቆየ በኋላ አንዱን ውድ ክራቫት መርጦ ፡ ለሚሸጠው ሰው ያሳየውና ፡ ይህንን ፈልጌ ነበር ። ፓክ አርግልኝ አለው ።
....
የመደብሩ ሻጭ አሚታብ ጠቅልልኝ ያለውን ከራቫት እያሳየው " ይህንን ነው ? " ብሎ ደግሞ ጠየቀው
አዎ እሱን ነው ጠቅልለው ሲለው ልጁ ..... ይሄ ህንድ ከረባቱ ርካሽ መስሎታል እንዴ ? በሚል አይነት አስተሳሰብና አነጋገር. ..

" አይ እሱ ይወደድብሀል ሌላ ምረጥ " አለው

አሚታብ ጠየቀ ፡ ስንት ነው ዋጋው
" 120 ፓውንድ "

Ok እንደዛ ከሆነ ....... ይህንን ጨምረህ የተለያየ ከለር አድርግና አስር ከረባት ጠቅልልልኝ በማለት ሂሳቡን ከፍሎ ፡ ከረባቱን ይዞ ወጣ ።
....
እና አሚታብ ንግግሩን ሲያጠቃልል ፡ በርግጥ ልጁ ማን እንደሆንኩ ላያውቅ ይችላል ። ሆኖም ሀብት ወይም ዝና ... ኖራችሁ ... አልኖራችሁ. .. ብቻ. . ማንም ብትሆኑ ........

ሰወች ዝቅ አድርገው እንዲያዩዋችሁ በፍፁም እድል አትስጡ ! ሲል መክሯል ።

( የአሚታብ የቅዳሜ መልእክት ነው ። መልካም ቅዳሜ )

© Wasihune Tesfaye

አጨዋወቱ…
© 433 Crypto

https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startApp=ref_1067310339&startapp=ref_1067310339&utm_medium=web_share_copy

የተከፈለበት ማስታወቂያ!

ከዓለማችን በDigital Currency ግዙፉ የሆነው BINANCE የራሱን Airdrop ትናንት ይፋ አድርጓል። ወደፊት ትልቅ ፕሮጀክት እንደሚሆን ካሁኑ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እና አመኔታን አግኝቷል፤ ምክንያቱም Binance Exchange ነው። ቀድሞ መጀመር ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው። አንደኛ እስከሚያበቃበት ዕለት ድረስ ብዙ ኮይን ትሰበስባላችሁ። ሁለተኛ የሚሰጠው ጊፍት እና ሪዋርድ መጀመሪያ ላይ ዳጎስ ያለ ነው። እናም እላችኋለሁ ይሄን ጨዋታ በትዕግስት እስከመጨረሻው ሳትሰለችሁ ተጫወተቱ ምክንያቱም ባይናንስ በጣም ሚታመን ነው። ለመጀመር…

👇👇👇

https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startApp=ref_1067310339&startapp=ref_1067310339&utm_medium=web_share_copy

ለማንኛውም በግሌ ከጠየቅከኝ፣ ሰው ለፈጣሪው ጊዜ እንደሚሰጠው፣ ለመፅሐፍም፣ ለማንበብም የተወሰነ ጊዜውን መስጠት አለበት ባይ ነኝ። ለነፍሱ ሲል።

ግን "ማንበብ ምሉዕ ሰው ያደርጋል"፣ ወይም "የለም አያደርግም ያነበቡትንኮ አየናቸው.." ወደሚለው አተካሮ ውስጥ መግባት አልፈልግም።

በእርግጠኝነት ግን፣ ቢያንስ፣ ሌላው ሁሉ ቢቀር፣ ማንበብ (ከተቻለ) ጥሩ ጊዜ ማሳለፊያ ነው። ዋጋዎቹን ሳትፈራ (ደፈር ብለህ) ሞክረው። ከመፅሐፎቹ የተሻለ እንደምታስብ ማረጋገጫ ይሆንህም ይሆናል። ማን ያውቃል? ግን ማንበብን አትሽሸው። አንብብ።

በገፆች በኩል ከሰው ጋር ተነጋገር። በመፅሐፍት ዓለምህን አብዛው። ሰው የተፈጠረው አንድ ሆኖ ሳይሆን ብዙ ሆኖ እንደሆነ ተረድተህ ሙት። ሰው ጊዜና ዘመን እንደማይወስነው በመፃሕፍቱ በኩል አስመስክረህ እለፍ።

ስለ ዛሬ ሺህ ዓመቱ ነገር አንብቦ መረዳት የሚችለው የሰው ልጅ ብቻ ነው። ይህን በሁሉም ዘመን፣ በሁሉም ሥፍራ የመገኘት (የOmnipresence) ለሰው ልጅ ብቻ የተሰጠ አምላካዊ ፀጋ፣ በመፅሐፍት በኩል ተላበሰውና ሙት።

የምመሰክረው ይሄም አለ፣ ይሄንንስ አይተኸዋል ወይ? ነው። እንጂ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፣ አያደርግም አይደለም። አንብብና ሞክረው። መጉደልም፣ መሙላትም አለ። ካልጎደልክ አትሞላም ወዳጄ። ራስህ ሞክረውና መስክር። አንተ ምናለብህ? መች ደላኝ? ካልክም መብትህ ነው። ግን ስንት አሪፍ አሪፍ ነገር ቀረብህ! እልሃለሁ!🙂🤓🙏🙏

አንባቢን አመስግኜ አበቃሁ።
መልካም ጊዜ።

© Assaf Hailu

የመፅሐፍ ዋጋ ስንት ነው?
______

በማንበብ ብዙ ነገር ይገኛል አዎ። ግን ስታነብ ደግሞ ብዙ ነገርም ያመልጥሃል። የምታነብበትን ጊዜ ሌላ ነገር ልትሠራበት ትችል ነበር። ይህን አስበኸው ታውቃለህ?

ማንበብ ልክ እንደ ፍቅር የጊዜ ፀር ነው። ጊዜህን እነድትሰጠው ይፈልጋል። መላ አትኩሮትህን እንድትሰጠው ይሻል። ችለህ 10 ገፅ ለማንበብ እንኳ፣ በጣም ትዕግሥተኛ ሰው መሆን መቻል አለብህ።

ደሞ ከራስህ egoistic ዓለም የወጣህ ሰውም መሆን አለብህ። ዓለም ስላንተ ብቻ አያወራም። እንዲያውም 99.9 ፐርሰንቱ የዓለም ህዝብ ከነመፈጠርህም አያውቅህም።

ግን ሁሉም ሰው የሚናገረው የየራሱ ታሪክ አለው። የየራሱ ገጠመኝ አለው። የየራሱ ትዝብት አለው። የየራሱ ዓለምን ያሳለፈበትና የሚረዳበት መነፅር አለው። ሁሉም ሰው የሆነ የሚናገረው ነገር አለ።

ሲበዛ ናርሲሲስት፣ ሲበዛ በራስህ ጩኸትና በራስህ ነገር ብቻ የተጠመድክ ሰው ከሆንክ፣ ዓለምህን በራስህና በራስህ ዛቢያ ላይ ብቻ ወስነህ የምትሽከረከር ሰው ከሆንክ፣ መፅሐፍ አንባቢ ልትሆን አትችልም። ምክንያቱም መፅሐፍ ሰዎች ስለሌሎች ሰዎችና ነገሮች የሚናገሩትን መስማት ይጠይቃል።

ሰዎች ስላንተ ሳይሆን ስለራሳቸው የፃፉትን ለመስማት ጆሮህን ማሠልጠን አለብህ። ሌሎች ስለራሳቸው ወይም ስለመሰጧቸው ነገሮች ሲናገሩ ለመስማት እጅግ ከፍ ያለ ትዕግሥት ሊኖርህ ይገባል።

በራስህ ላይ ብቻ የተጠመድክ ሰው ከሆንክ፣ በፍፁም አንባቢ ልትሆን አትችልም። ተገደህ ለትምህርት ወይም ለሌላ ፈተናህ ልታነብ ትችላለህ፣ አንባቢ ግን ልትሆን አትችልም። አንባቢነት ልክ እንደ ፍቅር ግንኙነት ነው ብዬሃለሁ። በፈቃደኝነት የምታደርገው። ያለፈቃድህም ከሆነ፣ ተወስውሰህ የምትገባበት ነው።

ለመፅሐፍ የሚከፈለውም ትልቁ ዋጋም ይኸው ነው። ለሌላ የምታውለውን ጊዜ መስጠት። ሌሎች ሰዎች የሚሉትን ለመስማት ፈቃደኝነት። የበዛ ትዕግሥት። ከራስ ያለፈ ሰፋ ያለ ሌሎችን ለመረዳት የጓጓ መንፈስ ይፈልጋል። ቀልብህን መስጠት ይፈልጋል።

ማንበብ ረዥም attention spanም ይፈልጋል። ችለህ 3 ገፅ ታነብባለህ? ችለህ 13 ገፅስ ታነብባለህ? 130 ገፅስ? 1,300 ገፅስ? አየህ? ማንበብ ልክ ዳምፔል (ክብደት) እንደማንሳት ነው። በትንሽ በትንሹ ራስህን እያለማመድክ፣ ዳጎስ ወዳለው፣ የበለጠ ክብደት ወዳለው ንባብ የምትሸጋገርበት በልምምድ የሚዳብር ችሎታ ነው።

ማንበብ ደግሞ ከራስህ አመለካከት፣ ካለህበት ሥፍራና፣ ከምታነብበት ጊዜ ወጣ ብለህ፣ በፀሐፊው ቦታ ራስህን ማስቀመጥንም ይጠይቃል። እሱ ባየበት መነፅር ለማየት መፍቀድን ወይም መቻልን ይጠይቃል።

ፀሐፊው ያየውን እያየህ፣ ያሰበውን እያሰብክ ለማንበብ፣ በቀን ውስጥ ለተወሰኑ ሰዓቶች ራስህን መሆንህን ማቆም፣ ወይም ራስን መርሳትን ይጠይቃል። ከራስህ ቤት ወጥተህ፣ በፀሐፊው ቤት፣ በፀሐፊው ሰፈር፣ በፀሐፊው ምናብ ውስጥ ለመቆየት መቻል አለብህ።

ደሞ በንባብ የሚገለፁት ሃሳቦችና ታሪኮች ብዙ ጊዜ በቃላት ብቻ የሚነገሩህ ናቸው። ደጋፊ ምስል፣ ወይም ደጋፊ ቪዲዮ፣ ወይ አጃቢ ድምፅ የላቸውም። በቃላት የፃፉልህን እያነበብክ፣ ሁሉንም ነገር በጭንቅላትህ ማውጠንጠን፣ በምናብህ መሣል ይኖርብሃል።

ቃላቱን ከመፅሐፍ እያነበብክ፣ ልክ በሚተረከው ቦታ ላይ እንዳለህ አድርገህ ምስሎቹን በአንጎልህ መከሰት መቻል አለብህ። አለዚያ ከገፅ ወደ ገፅ ለመሻገር እጅግ አሰልቺ ይሆንብሃል።

እኔ ለምሣሌ፣ የሙሶሊኒ ልጅ ኤዳ፣ ስለ ፋሺስቷ ዘመን ሮማ ቅልጥ ያሉ የሀብታምና የባለሥልጣናት ልጆች የተጫጫሰ ህይወት ስትፅፍልኝ፣ ያገኙትንና ያመለጣቸውን፣ ያስቡና ያደርጉ የነበረውን፣ ሰዎቹንና ቤቶቹን፣ መንገዶቹን ስታወራልኝ... በመፅሐፉ ቃላት ውስጥ ገብቼ በጭንቅላቴ እንደ ፊልም እያሰብኩ ነው የማነበው። ስለዚህ አያሰለቸኝም።

ራሴ በአካል ወደ ጣልያን ሄጄ፣ መካከላቸው ተቀምጬ፣ አብሬ ካርታ እየተጫወትኩ፣ ውስኪ እየቀዳሁ፣ ቀሚስ እያወለቅኩ፣ ሲጋራ እያንቦለቦልኩ፣ በመካከላቸው ኤዳ ባለችበት ቦታ ሁሉ እንደ ተደራቢ ነፍስ ሆኜ አየዋለሁ በሃሳቤ ሁሉንም። ልክ ራሴ በመቶ ዓመት ወደ ኋላ ሄጄ ያየሁት ሁሉ ይመስለኛል። ማንበብ ከፍ ያለ ሃሳባዊነትን፣ ወይም ምናባዊነትን፣ ህልመኛነትን ይጠይቃል የምለውም ከነዚህ ተነስቼ ነው።

ማንበብ ቀላል ነው። ለተወሰነች ሰዓትም ቢሆን ግን፣ ከራስህ ዓለም ፈቀቅ ብለህ፣ ብዙ ነገሮችህን ለፀሐፊውና ለሚነገግርህ ርዕሰ-ጉዳይ መስጠት መቻልን ይጠይቃል። ትልቁ ለአንባቢነት የሚከፈለውም ዋጋ ይህን የመሣሰለው ነው። እንጂ የመፅሐፍ ዋጋ ማለት፣ መፅሐፉን ለመግዛት ከኪስህ የምታወጣት ብር አይደለችም። በፍፁም!

አስበኸዋል? ቁጭ ብለህ የምታነብበትን ጊዜ፣ ብዙ ወርቃማ ነገሮችንምኮ ለመሥራት ልታውለው ትችል ነበር። ከከበረ ጊዜህ ቆርሰህ፣ ከዕድሜህ ላይ ሰውተህ፣ ለምትወዳቸው ሰዎችና ነገሮች ሁሉ ልትሰጠው የሚገባህን ወይም የምትፈልገውን ጊዜ ነው ለመፅሐፉ የምትሰጠው።

ይሄ ዋጋ ትልቁ ለንባብ የምትከፍለው ዋጋ ነው። ይሄንን ትልቅ ዋጋ ለመክፈል የሚችሉትም ጥቂቶች ብቻ ስለሆኑ ነው፣ ሁሉም ሰው አንባቢ ሆኖ የማታገኘው።

ማንበብህ የሚያሳየው፣ ከመፃሕፍቱ ለምታገኛቸው ታሪኮች፣ ባለታሪኮችና ዕውቀቶች ትልቅ ዋጋ መስጠትህን ነው። እና ለዚያም ትልቅ ዋጋ ለሰጠኸው ነገር፣ ከራስህ ጊዜና ገንዘብ አጉድለህ፣ ከራስህ ሃሳብና ቀልብ ሸርፈህ፣ ከራስህ የኑሮ ልፋትና ትግል መሐል የተወሰነች ፋታ ሰጥተህ፣ መፅሐፍን ያክል ሁለመናህን የሚጠይቅን ነገር ማንበብ መቻል ትልቅ self-sacrifice ይጠይቃል።

በህይወትህ ሊገጥምህ የሚችለው ትልቁ ክፍያ፣ ትልቁ ሥጦታ፣ ትልቁ ምፅዋት፣ ትልቁ መስዋዕትነትም ነው መፅሐፍትን ለማንበቢያ የምታውለው ጊዜና ኃይል።

ሳስበው ብዙው ሰው ይህን ይረዳው ይሆን? እላለሁ። አንዳንዴም ብዙ መፅሐፍ ማንበብ አልወድም የሚሉኝን ሰዎች ጠለብዬ ሳጤን ሳጤን፣ አባባላቸው በሌላ አነጋገር፣ እነዚህን ሁሉ ነገሮቼን ለአንድ ለማይናገር፣ ለማይጋገር መፅሐፍ አሳልፌ ለመስጠት ዝግጁ አይደለሁም። መች ደላኝ እኔ?! የሚሉ ሆነው አገኛቸዋለሁ።

በማያነቡ ሰዎች አልፈርድባቸውም። በማንበቤም አልመፃደቅም። ምናልባትም ከማንበብ የተሻሉ ሚሊዮን ነገሮች አሉ በዓለም ላይ። የምርጫና የዝንባሌ ጉዳይ ነው። የነገሮች መመቻቸትና አለመመቻቸት ጉዳይ ነው። ሌላ ተዓምር የለውም።

አንድ ነገር ግን በእርግጠኝነት እናገራለሁ። ማንበብ ፈልጎ፣ ለማንበቢያ የሚሆን ጥቂት ጊዜውን ሰጥቶ፣ በፈቃዱ የመጣ ሰው፣ በፍፁም፣ በምንም ተዓምር አንድ የተለየ ነገር፣ ወይም አንድ ተጨማሪ ነገር ሳይይዝ አይመለስም።

"Every time I turn a page, there's some kind of knowledge." የሚሉትም ለዚህ ነው። አንድ ገፅ ለመግለፅ ፈቃደኝነቱ ካለህ፣ በእርግጠኝነት አንድ ዕውቀት ይጠብቅሃል።

ግን በአራቱም ግድግዳ ላይ የራስህን ፎቶ ለጥፈህ፣ በሞባይልህ ላይ የራስህን ፎቶ ስክሪን-ሴቨር አድርገህ፣ ራስህን ስታመልክ ውለህ የምታድር ሰው ከሆንክ ንባለአንተ አይሆንም።

የራስህን ጨላ፣ የራስህን ጣሪያ፣ የራስህን እንጀራ፣ የራስህን ሚስትና የራስህን ልጅ ብቻ እያሰብክ፣ እየተብሰከሰክህ 24 ሰዓትህን የምታጠፋ "ኃላፊነት የሚሰማው ሰው" ከሆንክም፣ አንዲት ገፅ ለመግለጥ ጊዜ ከሌለህም፣ ወዳጄ ንባብ ላንተ አልተፈጠረም። ብዙ አሪፍ ነገርም አምልጦሃል። እልሃለሁ። አፌን ሞልቼ🙂😃!

የተከፈለበት ማስታወቂያ

ከብዙ ጊዜ ጥበቃ እና መታከት እንዲሁም ግራ መጋባት በኋላ Hamster Kombat ዋጋ ሊወጣለት (list) 9 ቀናት ቀርቶታል። ብዙ ሰው የደከመት፣ የለፋበት ብሎም ተስፋም የጣለበት token ነው፤ እንዲሁም ብዙ ሰው ተስፋ ቆርጦ የተወውም ነው፤ ሐምስተር። በተስፋ ለጠበቁት ውጤቱ ምን እንደሚሆን በቅርቡ በጋራ የምናየው ይሆናል። ነገር ግን ይሄን በCryptocurrency ታሪክ ከፍተኛ ግምት የተሰጠውን ኤርድሮፕ ያልጀመራችሁ በቂ ጊዜ አላችሁ። Daily Combo እና Cypher ብቻ እየወሰዳችሁ PPH (Profit per hour) ካሳደጋችሁ ባለችው ጥቂት ጊዜ ከስጦታው መቋደስ ትችላላችሁ።
መልካም ዕድል። ለመጀመር…

👇👇👇

https://t.me/hAmster_kombat_bot/start?startapp=kentId1067310339