ረመዳን በአምልኮ በስነ ምግባርና በሱሉክ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ጥሩ Environment የሚፈጥር አምላካዊ የስልጠና ማዕከል ነው ። ብዙዎቻችን በረመዳን ባንፈልግ እንኳን እንቀየራለን ቢዓው በግድ የመስጂድ ሰው ያደርግሀል ግን እንዲህ አይነት ለውጥ የግርግር ለውጥ በመሆኑ ከረመዳን ጋ አብሮ ይተንናል ። ለአንድ ወር pause ያደረከውን ወንጀል ረመዳን ሲወጣ play ብለህ ትቀጥለዋለህ ።
ግን የለውጥ ፍላጎታችን ከውስጥ ከሆነ የምር ወደ አላህ ለመቅረብ ፍላጎቱ ካለን ከዚህ ወር የተሻለ ምንም እድል አይመጣም ። አላህ ምን ያህል ነገሮችን እንዳመቻቸ ምታውቁት ጉጉታችንን ሊጨምር የጀነትን በሮች ክፍት እንዲሆኑ ያደርጋል ፣ ማህርታውን ሊያሳየን የጀሂም በሮችን ይዘጋል ፣ ሸይጧንና የጂን አመፀኞችን ዘወር ያደርግልናል፣ ነፍሳችን በረሀብ ተቆፍዷል ። የለውጥ እንቅፋቶች ሁሉ ይወገዱልናል ፣ ተጣሪውም ‹አንተ ኸይርን ፈላጊው ሆይ ና ወደ ኸይሩ ፣ አንተ ሸርን ፈላጊው ሆይ ከወንጀልህ ታቀብ› እያለ ይጣራል ። ይሄ ሁሉ እድል ተመቻችቶለት ወደ አላህ መቅረብ ያልቻለ ከአላህ እዝነት መራቅ በርግጥም ይገባዋል ።
So, ፕሮግራም እናውጣ ላወጣነው ፕሮግራምም Committed እንሁን 'የዘንድሮ ረመዳን ከአላህ ጋ በህይወቴ ላይ ትልቅ ለውጥ የማመጠበት ይሆናል › እንበልና ፆሙን እንጀምረው ።