ዳሩል አርቀም የበጎ አድራጎት ማህበር ከ ስለኔ የሴቶች አቅም ግንባታና የበጎ አድራጎት ድርጅት የረመዳን ኢፍጣር ግብዐቶች ድጋፍ ተበረከተለት!!!!!!!
በየካ ክ/ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖች የረመዳን አስቤዛ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘዉ ዳሩል አርቀም የበጎ አድራጎት ማህበር ለ 75 ሰዎች የሚሆን ግምቱ 300,000 ብር የሚጠጋ ሙሉ አስቤዛ ከ ስለኔ የሴቶች አቅም ግንባታታና በጎ አድራጎት ድርጅት ተበርክቶለታል።
ድጋፉ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለዉን የመደጋገፍ ባህል ይበልጥ ያጠናከረ ሲሆን በምናደርጋቸዉ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ሁሌም ከጎናችን በመሆን የሚታወቅ ተቋም በመሆኑ እጅግ ደስተኞች ነን ።
ምስጋና :- ለስለኔ የሴቶች አቅም ግንባታና በጎ አድራጎት ድርጅት ቦርድ ሀላፊ ወ/ሮ መካነ ሰላም ሙሀመድ
-ድጋፉን በማሳለጥ ሁሌም አብራን ያለችዉ እህት ራቢአ ሙሀመድ