Canal ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠ @betgubae no Telegram

✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠
በዚህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰንበት ትምህርት ቤት የሚሰጠውን ተከታታይ ትምህርት በጉባኤ ተገኝተው መማር ላልቻሉ በሃገር ውስጥም ከሃገራችንም ውጪ ለሚኖሩ ምዕመናን መማማሪያ የተከፈተ ነው።
t.me/betgubae

የፌስቡክ ኣድራሻዬንም ይጎብኙ https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71
8,188 Inscritos
915 Fotos
12 Vídeos
Última Atualização 06.03.2025 02:30

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ጉባኤ እርምጃ እና ቁሳቁስ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ጉባኤ በኢትዮጵያ እና ከዚያ በተወሰነ ዓለም ውስጥ የተቀነበረ ፈጣሪ እና ቤተ ክርስቲን ቤተ መቅደስ ነው። በዚህ ቤተ ጉባኤ ውስጥ የካህን ዝርዝር ይኖራል፣ የዕውቀት ዜማዎች መንግሥታዊ ዝግጅት እና በሰንበት ትምህርት ላይ ቀሪዎች ይኖራሉ። ይህ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ጉባኤ ገንዘብ ውስጥ እንዳለ የትብብር አእምሮ እና ዝግጅት ይወዳዳዳሉ። ይህ ቤተ ጉባኤ በኦርቶዶክስ የሚኖሩ ጅምላ መስክ እና ውድድር መረጃ ይወዳዳዳል።

የጉባኤ ቤተ ጉባኤ ውስጥ ምን ነው የሚኖር አለኝ?

በዚህ ቤተ ጉባኤ ውስጥ የካህን ዝርዝርና የሕዝብ አእምሮ ይገኛሉ። ይህ የሕዝብ ትምህርት ይሆናል እና ይህ ቤተ ጉባኤ እንዳለ የዕውቀት ዝርዝር። ሁሉም ተሳታፊ ይኖራሉ።

ቤተ ጉባኤ ውስጥ የሚኖሩት ተሳታፊ ሕዝብ እና ካህን ይወዳዳዳሉ። ይህ ከእንግዲህ ውስጥ ይመስክ ይታወናል።

ምን ይገኘው አዳዲስ ምዕመናው ወይም ጥያቄ?

የጉባኤ ቤተ ጉባኤ እንዳለ በዚህ ውስጥ የማዋሌ እና የምዕመና ስራዎች ይገኛሉ። ይህ ሌላ የሚኖር በንዴት ወይም ወይም ወይም ግጥም ይሆናል። እዚህ የሚኖሩት ይመለከታሉ አለው!

ይህ የምዕመና የምዕመና ቤተ ጉባኤ ውስጥ የሚኖሩ ውስጥ ይኖራሉ። ይህ አእምሮ ይደርሳል ወይም ክርስትና ጋር በቂ ይሆናል።

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ጉባኤ ምን እንደ ዝግጅት አለ?

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከባይስ ተወላጅ የተምህርቶ ወይም ወይም ወይም ወይም ወይም ምንም ይገኛሉ። ይህ ገንዘብ ወይም ወዮብ እንቅስቃሴ በዚሁ ይወለዳል።

ቤተ ጉባኤ ውስጥ በአንዳንዱ ዘመን ይኖሩ ይተኝዋሉ። ይህ የዕውቀታቸው ይወዳዳዳል።

ከምርጫ ወይም ከትምህርት አስተዋይ ይወርዳል?

እነንቅስቃሴ ናው ግን ከዚህ ውስጥ በኢትዮጵያ ይኖሩ። ግንቦት ድግም ይወዳዲረች ይመለከታል።

ይኖር በምርጫ ወይም ይገኙ ይሆናል። ይህ በእስያዊ መላ ዝርሩ ይወዳዳዳል።

ይህ ኢትዮጵያ የምዕመና ሰላም ነው?

ይህ ዝንቱባ በኢትዮጵያ ይወዳዳዳል። በዚህ ውስጥ የተወሰነ ምዕመና ዝርዝር ይወዳዳዳል።

ይገኙ ይሁን ይህ መኖሪያው አለኝ። ይህ ትምህርት ወለዱ ይወዳዳዳል።

Canal ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠ no Telegram

የቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የሆነችው ትምህርት ቤት ለሃገረ ኦርቶዶክስ ቤቶች በመከፍት ሃገራችንን ለተከታተው የቤተ ጉባኤ ተዋህዶ ማለት ነው። የቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርት ቤት በጉባኤ ላይ ገንዘብ እንዲሆን ገንዘብና ሐሳብ እንዳይጠናቀል ለነሐስኩሽሞን፣ ድምፅ፣ ቋሚ እና ህምሳ መልኩነትን መማር ያስፈልጋል። ተጨማሪ የትምህርት ምሽት አስገራሚነታችንን ይገልፀዋል። በትክክለኛው አጠቃላይ ዋና ትንሽ ለማድረግ ከሚፈልጉት የፌስቡክ የኢልኩክባል አድራሻ ተመልከቱ። ለተጨማሪ መረጃ እና መመዝገብ ለአስተሳሰብ ይህንን ይመልከቱ: t.me/betgubae

Últimas Postagens de ✠ቤተ ጉባኤ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ✠

Post image

#ቅድስት

የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሣምንት ቅድስት ይባላል።
- የተለየች ፤ የተባረከች ፤ የከበረች፣ ንጽሕት ማለት ነው::

ለምን ቅድስት ተባለ?

-> «ጾምን ቀድሰ ጉባኤውን አውጁ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤተ ሰብስቡ፡፡»
(ት.ኢዩኤል 1፥14) ብሎ በነቢዩ ኢዮኤል አፍ የተናገረ ቅዱስ እግዚአብሔር የጾማት ጾም ስለሆነች (የጌታችን ጾም ከቅድስት ጀምሮ በመሆኑ) ቅድስት ትባላለች።

-> እንዲሁም የዲያብሎስን ፈተና ድል ለመንሳት በቅድስት ከተማ በሰሎሞን ቤተ መቅደስ ጫፍ የቆመባት ዕለት በመሆኗ (ማቴ 4፥5/ ዮሐ 10፥22-23 ) ሰው ሁሉ ጾምን ጾሞ እንደ ፈጣሪው ፈተናን ድል ነሥቶ ቅድስና እና ክብርን ያገኛልና ቅድስት ተብላለች።


--> ቅድስት ዕለተ ሰንበት
«እግዚአብሔር ሰባተኛይቱን ቀን ባረካት ቀደሳት» (ዘፍ 2÷3፣ ዘጸ 20፥8) ሰዎች ፍጥረት ያልተፈጠረባት ዕለት ብለው እንዳይንቋት እንዳያቃልሏት እረፍተ ሥጋ እረፈተ ነፍስ የተገኘባት ዕለት ስለሆነች ቀደሳት አለ፡፡ ቅዱስ ያሬድም " ሰንበትየ ቅድስትየ ዕንተ አዕረፍኩ እምኩሉ ግብርየ ይቤ እግዚኣብሔር " ብሉአል:: በዚህ እሁድ (ሳምንት ) ቀደሳት፣ አከበራት፣ ከፍ ከፍ አደረጋት :- የተባለች ሰንበትን የምትታሰብበት የሰንበትንም ቅድስና የሚመለከቱ መዝሙሮች የሚቀርብበት ሳምንት በመሆኑ ቅድስት ተብሏል።


-> መዝሙር ዘቅድስት ፦
ግነዩ ለእግዚአብሔር

-> ምንባባተ ቅድስት ዘቅዳሌ ፦
- 1ኛተሰሎ.4፥1-13
- 1ኛ.ጴጥ.1÷13-ፍም
- የሐዋ.10፥17-30
- ማቴ 6፥16-25 (4፥1-11)

-> ምስባክ ዘቅድስት፦
" እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ አሚን ወሰናይት ቅድሜሁ ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ "
ትርጉም፦ " እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ፥ ምስጋና ውበት በፊቱ ፥ ቅድስትነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው ። " (መዝ 95፥5)

-> ቅዳሴ ዘቅደስት፦
- ኤጲፋንዮስ

✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ)

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://www.youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw/about (የዩቱብ አድራሻ)

01 Mar, 16:48
1,567
Post image

✥✥✥ 0ቢይ ጾም እና ስያሜዎቹ ✥✥✥

➛ ይህ ጾም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ በገዳም ገብቶ 40 ቀንና 40 ሌሊት የጾመው ጾም ሲሆን በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል ፡፡


፩- 0ቢይ ጾም፡- 0ቢይ ማለት ታላቅ ማለት እንደሆነ ሁሉ ይህ ጾም " ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኰቴቱ " "ዐቢይ እግዚአብሔር ወዐቢይ ኀይሉ " የተባለ ጌታ የጾመው ጾም በመሆኑ (መዝ 47፥1 / መዝ 146፥5)

-> ከጾሞች ሁሉ ታላቅ በረከትን የምናገኝበት በመሆኑ

-> በቀኑም ብዛት ከሌሎቹ አጽዋማት ይበልጣልና

-> ርዕሰ ኃጣውዕ (ታላላቅ ኃጢአቶች) ድል የተነሱበት ጾም በመሆኑ ታላቅ የሚለውን ስያሜ ይዟል ፡፡


፪- የሁዳዴ ጾም፡- ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥራ ሁሉ ሁዳዴ ስለሚባል ፥ የጥንት ዘመን ገባሮች ለባለርስቱ የሚያርሱት መሬት ( ሁዳድ ) ይባል እንደነበር ይህም ጾም ሠራኤ ሕግ ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ምዕመናንም ይንን እያሰቡ ከልሒቅ እስከ ደቂቅ ( ከትንሽ እስከ ትልቅ ) የሚጾሙት ስለሆነ ጾመ ሁዳዴ ተብሏል ፡፡ (ት. አሞ 7፥1)

፫- የካሣ ጾም፡- የቀድሞዎቹ ሰዎች አትብሉ የተባሉትን በመብላታቸው ከገነት ለመባረር ለውርደት ለሞት ለሲዖል ባርነት ተዳርገዋል ፡፡ ዳግማዊ አዳም የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ በመብል ምክንያት ድቀት አግኝቶት ረሃብ ሥጋ ረሃበ ነፍስ ደርሶበት የነበረው ቀዳማዊ አዳምና ልጆቹ በፈቃዱ በጾመው ጾም ረሃበ ሥጋችንን ረሃበ ነፍሳችንን ሊያርቅልን ስለጾመው የካሣ ጾም ይባላል ፡፡

፬- የድል ጾም፡- አዳምና ሔዋን ከዚህ ዓለም ርቃ በምትገኝ በገነት ሳሉ በምክረ ከይሲ ተታለሉና ድል ሆኑ ፡፡ ተስፋ አበውን ሊፈጽም የመጣ ክርስቶስም ዲያብሎስን ድል ያደርግልን ዘንድ ተጠምቆ ሳይውል ሳያድር ከዚህ ዓለም ርቆ ወደ ገዳም በመሔድና ከሰው ተለይቶ 40 ቀንና 40 ሌሊት በመጾም ዲያብሎስን ፣ ፈቃደ ሥጋችንን ድል የምናደርግበት ኃይል አጎናጽፎን ፣ ሦስቱን የኃጢአት ራስ የተባሉት ድል የተነሱበት ዲያብሎስ ያፈረበት ስለሆነ የድል ጾም ይባላል ፡፡ (ማቴ 4)


፭- የመሸጋገሪያ ጾም፡- ነቢዩ ሙሴ 40 ቀንና 40 ሌሊት በሲና ተራራ ጾሞ እሥራኤል ዘሥጋን ከሕገ ልቡና ወደ ሕገ ኦሪት ያሸጋገረ ሲሆን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እሥራኤል ዘነፍስ የተባልነውን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል 40 ቀንና ሌሊት በመጾም ያሸጋገረን በመሆኑ የመሸጋገሪ ጾም ተብሎ ይጠራል ፡፡

✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ 

https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ)

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://www.youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw/about (የዩቱብ አድራሻ)

25 Feb, 02:18
2,577
Post image

✥ ዘወረደ ✥

-> የ0ቢይ ጾም የመጀመሪያው እሁድ (ሳምንት ) ዘወረደ ይባላል።

->ጌታችን እኛን ለማዳን ከሰማይ መውረዱን የሚነገርበት ሳምንት በመሆኑ ዘወረደ ተብሏል።

-> ከሰማይ ወረደ ማለት እርሱ የሌለበት ኖሮ ካለበት ወደዚህ መጣ ማለት አይደለም እርሱስ ጽርሐ አርያም ምጥቀቱ በርባኖስ ጥልቀቱ ፥ አድማስ ናጌብ ስፋቱ ተብሎ የማይነገርበት በዓለም ሙሉዕ ነውና ዓለማትን ቢወስን እንጂ ዓለማት እርሱን አይወስኑትም ።

-> የፀሐይ ብርሃን ከክበቡ ሳይለይ ከ0ይናችን ብሌን ጋር እንደሚዋሓድ ወልደም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በምልዓቱ መወሰን ሳይኖርበት በሥጋ ማርያም መገለጹን ሰው መሆኑን ያስረዳል ::

-> ከሰማይ ወረደ ሲባል ስንሰማ መረዳት የሚገባን

1- "ሰማይ" ያለው ዕበዩን፣ ክብሩን ፣ ልዕልናውን ፣ ጌትነቱን፣ መንግሥቱን ፣ ርቀቱን .... ነው :: ስለዚህ ከሰማይ ወረደ ማለት የባሪያውን መልክ ይዞ ሰው መሆኑን ለመግለጽ ነው። (ፊል 2፥6-8)

-> ሰው ሆኖ መፈጠር ታላቅ ክብር ነው ለአምላክ ግን ሰው መሆኑ ተዋርዶ ነውና ይልቁንም እኛን ለማዳን በለበሰው ሥጋ መራብ መጠማቱ ፣ መገረፍ መታመሙ ... እንኳን ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ይቅርና ከመላእክት እንኳን ያነሰበት ነው መላእክት በባህሪያቸው መራብ መጠማት፣ መታመም የለባቸውምና " ከመላእክት እንኳን አሳነስከው " ያለውም ስለዚህ ነው ። (መዝ 8፥5 / ዕብ 2፥7)

-> ይህ ማለት ግን ወልድ ሰው መሆኑ አምላክነቱን አጥቶ በዚህም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አነሰ ማለት አይደለም ጌታችንም "አብ ይበልጠኛል" ያለው በለበሰው ሥጋ ባገኘው መራብ መጠማት አነሰ ለማለት ነው አብ እና መንፈስ ቅዱስ ሰው ሆነው መራብ መጠማት ... ያላገኛቸው መሆኑን ለመግለጽ ነው። (ዮሐ.14፥28)

2- መጣ ወረደ መባሉ የሰው ልጅ በበደሉ ምክንያት ከአምላክ ምን ያህል ርቆ ኮብልሎ እንደነበር ተረዳ ስለዚህ የጠፋን እኛን ለመፈለግ የራቅነውን ወደርሱ ለማቅረብ መጥቷልና ዘወረደ ተባለ። (ሉቃ 15 )

3- የፍጥረት ጥንቱ መጸነሱ ነው ፥ የጌታችን ጥንቱ ግን ከማርያም ከተጸነሰ ወዲህ አይደለምና ዘወረደ የሚለው የጌታንን ቅድምናውን ያስረዳል።
-> ፎጢኖስ የተባለ መናፍቅ የወልድ ሕልውና ከማርያም ከተወለደ ወዲህ ነው (ለፌ እም ማርያም ) የሚል ነበር በቅዱስ መጽሐፍ ግን ስለ ወልድ ሕልውና ከማርያም በፊት ጥንት በማይነገርበት መጀመሪያ መሆኑን ያስረዱናል እነዚህ ማስረጃ ያድርጉ👇
- ዮሐ 1፥1 " በመጀመሪያ ቃል ነበረ.. "
- ዮሐ 8 " እውነት እውነት እላችዃለኹ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለኹ "
- ዮሐ 17 " አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ባንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ። "

-> ቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓውን ሲጀምር " ሃሌ ሃሌ ሉያ ዘወረደ እም ላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሃዩ በቃሉ /
ከሰማየ ሰማያት የወረደ አይሁድ የሰቀሉት ሁሉን በቃሉ እንደሚያድን አይሁድ ያላወቁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው " በማለት ሰው ሆኖ በአይሁድ ተዋርዶ ያገኘው መሆኑን የዚህን ሳምንት ጠቅላላ ሀሣብ ይገልጻል።

የዘወረደ የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)

ሃሌ ሉያ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት በፍርሃት ወተኃሠዩ ሎቱ በረዓድ፤ /መዝ.፪፥፲፩/
እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ፤ ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕጻዲሁ በስብሐት እመንዎ፤ /መዝ.፺፫፥፫-፭/
እስመ … ንጹም ጾመ ወናፈቅር ቢጸነ ፥ ወንትፋቀር በበይናቲነ፤ እስመ … አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት፤/ማቴ.፲፪፥፰/
እስመ … ምሕረተ ወፍትሐ አሀሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጹሐ፤ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ፨

ትርጕም፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ተገዙለት፤ ለእርሱ መገዛትም ደስ ያሰኛችሁ፡፡ እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘለዓለም፣ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነው፡፡ እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያው በጎች ነን፡፡ ወደ ደጁ በመገዛት፤ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ ጾምን እንጹም፤ ጓደኞቻችንን እናፍቅር፤ እርስ በርሳችንም እንፋቀር፡፡ ሰንበት ስለሰው ተሠርታለችና፤ ሰንበትን እናክብር፡፡ እውነትንም እንሥራ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ፤ እዘምራለሁ፤ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ፡፡

የዘወረደ ምስባክ
(መዝ. 2፥11 ) " ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ። አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐፅ እግዚአብሔር።
ትርጉም፦ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ። ጥበብን አጽኑአት ፤ እግዚአብሔር እንዳይቆጣ። "

-> የዘወረደ ምንባብ 1 (ዕብ.13÷7-17)
-> የዘወረደ ምንባብ 2 (ያዕ.4÷6-ፍጻ.)
-> የዘወረደ ምንባብ 3 (ሐዋ.25÷13-ፍጻ.)

የዘወረደ ቅዳሴ

-> ቅዳሴ ዘእግዚእነ (ነአኩተከ )

✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ 

https://t.me/+VBt2ld_HeykCaELL (ቴሌግራም ቻናል )

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://www.youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw/about (የዩቱብ አድራሻ)

23 Feb, 17:45
2,975
Post image

" የሴቲቱ ዘር ራስ ራስህን ይቀጠቅጥሃል " ተብሎ ለአዳም የተገባው ኪዳን የተፈጸመባት መሆንዋን ለማጠየቅ እርሱን "የሴት ዘር " እርስዋንም "ሴት" ተብላለች። ይህም የአዳም የምህረት ኪዳን የተፈጸመባት በመሆኑዋ ኪዳነ ምህረት ትባላለች።

✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

https://t.me/+Vd4rG3DjWHFlDGCo (ቴሌግራም ግሩፕ)

https://m.facebook.com/mekuria.tesfaye.71

https://www.youtube.com/channel/UC8v52_jNY156sxZtplafDtw/about (የዩቱብ አድራሻ)

23 Feb, 07:16
2,142