✍✍አስተማሪ መጣጥፍ📚📚 @astemarimetatf Channel on Telegram

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

@astemarimetatf


አስተማሪ መጣጥፍ (Amharic)

አስተማሪ መጣጥፍ የገንዘብ ምርጥ እና አማራ መፅሀፍ መስሪያዎችን የበለጠ መጀመሪያ ነው። እዚህ መጣጥፉ በአቶጨውር ወልደ ሚኒስትሪ የቀፋውን መግለጫ የሞሃመንስ ስብ ማስመታት እና ለማሳተፍ ያለው ዝግጅት ይደረጋል። አዚያ መጣጥፍያን የቀረቡት መገናኛ መግለጫዎች እና ሌሎች ተጠቃሚዎች በሚዲያ እንድናደርገው በማቅረብ ሌሎችን ይዘናል። እናም ዝርዝሩ የገንዘብ መጣጥፉን የምርምር ስብ ለመግባት እና ለመንገድ እዚህ መሰብሰብ ያለው የአለም ልዩ በቅናት ይሆናል።

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

08 Dec, 09:42


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 20 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

11 May, 17:12


ግሩም አባባሎች

1.አሸናፊ ለመሆን አንድም ሰዉ እንኳ በማይተማመንብህ ወቅት በራስህ ማመን አለብህ።
- ሹገር ሬይ ሮቢንሰን

2.የራስህን የህይወት እቅድ ዲዛይን ካላደረግክ ዕጣ ፈንታህ የሚሆነው በሌሎች እቅድ ውስጥ መኖር/መውደቅ ይሆናል።
- ጂም ሮን

3.ጨለማን ጨለማ አይገልጠውም፣ ብርሃን እንጂ፤ ጥላቻንም ጥላቻ አይፍቀውም፣ ጥላቻን ማጥፋት የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው።
- ማርቲን ሉተር ኪንግ

4.የስኬትን ቀመር (ፎርሙላ) ልሰጥህ አልችልም፤ ነገር ግን የዉድቀት ቀመር ልሰጥህ እችላለሁ፤ ያም ሁሉንም ሰዉ ለማስደሰት መሞከር ነዉ።
- ሀርበርት ስዎፕ

5.የማይገለን የህይወት ፈተና፣ ጠንካራ ያደርገናል።
- ፍሬደሪክ ኒቼ

6.በዓለም ላይ ራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር፤ ያን ካደረክ ራስህን እየሰደብክ ነው ።
- አለን ስትራክ

7.ስለ አንድ ሰው ባህሪ ማወቅ ከፈለግክ ስልጣን ስጠው።
- አብርሃም ሊንከን

8.ሌሎች ሰዎች ምን ያህል በጣም ጥቂት ጊዜ (ከስንት አንዴ) ስለአንተ እንደሚያስቡ ብታውቅ ኖሮ፤ ሌሎች ስለ እኔ ምን ያስባሉ ብለህ አትጨነቅም ነበር። - ኤልኖር ሮዝቬልት

9.እራስን ሁን፣ የሚሰማህንም ተናገር፣ ምክንያቱም እራስህን በመሆንህ ቅር ለሚላቸው ሰዎች ቦታ/ደንታ መስጠት የለብህም፤ የሚበጁህ ሰዎች ደግሞ እራስህን በመሆንህ ቅር አይሰኙምና። - ዶ/ር ሱስ

10.ቅን አሳቢ ሰው ጽጌረዳ አበባው ላይ ሲያተኩር ጨለምተኛ ሰው ግን ጽጌረዳውን በመዘንጋት እሾሁ ላይ ያተኩራል።
- ካህሊል ጂብራን

11.ሳንቲም ብዙ ድምፅ ያሰማል፤ ገንዘብ ግን ምንም አያሰማም፤ ስለዚህ ዋጋህ ሲጨምር ወሬህን እየቀነስክ ና!
-ሼክስፒር

12.ለቀላል ህይወት አትፀልይ፤ ሆኖም አስቸጋሪውን ለመቋቋም ጥንካሬ እንዲኖርህ ፀልይ። - ብሩስ ሊ

13.ሌላን ሰው ለመሆን መፈለግ የራስን ማንነትን ማባከን ነው።
- ኩርት ኮቤይን

14.የዚህች አለም ታሪክ ማለት በራሳቸዉ የሚያምኑ የጥቂት ግለሰቦች ታሪክ ማለት ነዉ።
- ስዋሚ ቪቬካናንዳ

15.የወደፊቱን ለመተንበይ የተሻለው ዘዴ፤ ወደፊትን መፍጠር ነው።
- አለን ኬይ

#Share


Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

11 May, 17:12


ጉዞው የፍጻሜውን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስታውስ!

“ለአንድ ጉዞ ግብና ፍጻሜ የመኖሩ ጉዳይ አስፈላጊ ነው፡፡ በመጨረሻው ላይ ግን የጉዞው ጉዳይ ነው አስፈላጊው ነገር” -
Ursula K. LeGuin

አንዳንድ ሰዎች ህልማቸውን እውን ለማድረግ የሚሄዱበት ጎዳና ለድካም፣ ለህመምና ለቆሰለ ስሜት አሳልፎ ሲሰጣቸው ይታያሉ። በእንደዚህ አይነት መልኩ ማንነቱን ለጉዳት ያጋለጠ ሰው ህልሙ ጋር ቢደርስ ትርጉሙ ምንድን ነው? ህልሙ ጋር ሲደርስ በስኬቱ ለመደሰት የሚያበቃ ጤንነቱም እንኳን አይኖረውም፡፡ ሰዎች ገንዘብ የማግኘትን ህልም ይዘው ያሰቡትን ገንዘብ ለማግኘት ጤንነታቸውን ሲያጡ ክስረቱ ሁለት ነው። አንዱ ክስረት ያገኙትን ገንዘብ ጤንነታቸውን ለመመለስ እንደገና ማጥፋታቸው ነው፡፡ ሁለተኛው ክስረት ደግሞ ገንዘብ የማግኘት ህልም ጋር የደረሰው ሰው ገንዘቡን እንደፈለገው ለማድረግ የሚያበቃ የስሜትም ሆነ የአካል ጤንነት ማጣቱ ነው፡፡

ለአንዳንድ ሰዎች ሕይወት ማለት አንድ የሚደረስበት ግብ ነው፡፡ ሕይወት ግን የሚደረስበት ግብ አይደለም፤ ሕይወት የየእለት ሂደት ነው፡፡ ምንም እንኳ ይህ ሂደት በመጨረሻው አንድ ደረጃ ላይ ቢያደርሰንም፣ የሕይወት ዋናው ክፍል ያለው ወደዚያ ጥግ ለመድረስ የምናደርገው ጉዞ ነው፡፡ አላማ ላይ በመድረስ ምክንያት ሰዎች ትዳርን፣ ልጆችን፣ ቤተሰብን ሲበትኑ ማየት አሳዛኝ ነው፡፡

አንድን በንግዱ ስኬታማ ለመሆን ብዙ የለፋ፣ የተጨቃጨቀና በብዙ የስሜት ውጣ ውረድ ያለፈን ሰው አስብ፡፡ ንግዱን ለማጧጧፍ ሲሯሯጥ ለትዳሩና ለልጆቹ ያለውን ጊዜ ሰርቆበት ከቤተሰቡ ጋር ብዙም ጤናማ ግንኙነት የለውም፡፡ ከወዳጆቹ ጋር በገንዘብ ምክንያት ተለያይቷል፣ የተለያዩ ከስሜት ቀውስ የተነሳ የሚመጡ በሽታዎች አግኝተውታል፣ ስሜቱ ተጎድቷል ...። በመጨረሻ ግን ንግዱ ተሳካለትና ገንዘብን አካበተ። ሰብሰብ ብሎ ሲያስበው ግን ጤንነቱን አጥቷል፣ ቤተሰቡ ፈራርሷል፣ ወዳጆቹ ተለይተውታል ... የክስረት ሁሉ ክስረት!


ይህንን አስታውስ፡- ትርፍና ኪሳራ ሁል ጊዜ ከገንዘብ ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ መፍትሄው ምን መሰለህ፣ ወደህልም የምትሄድበትን ጉዞ ህልሙን የማግኘትህን ያህል አስፈላጊ ነውና ተደሰትበት፡፡

🙏 መልካም ምሽት!!

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

11 May, 17:12


ሌላኛው የምርጫ ገጽታ

ነገሩን ብትፈልገውም ሆነ ሳትፈልገው በሕይወትህ እንዲቆይ የተውከው ነገር እንደመረጥከው ይቆጠራል፡፡ ሁለት አይነት ምርጫዎች አሉ፡-“ንቁ” ምርጫ እና “ፍዝ” ምርጫ

“ንቁ” ምርጫ ማለት አንድን ነገር መፈለጋችንን ወይም አለመፈለጋችንን በንግግራችን ወይም በተግባራችን በመግለጥና እርምጃ በመውሰድ ስንመርጠው ነው፡፡

“ፍዝ” ምርጫ ማለት አንድን ነገር መፈለጋችንን ወይም አለመፈለጋችንን ሳንገልጽ ሁኔታውን ዝም ስንለውና በዝምታችን ስንመርጠው ነው፡፡

አንድን ነገር ምንም እንኳን እንደማንፈልገው ብናውቅና አንዳንዴም ብንናገርም በዚያ ነገር ላይ ንቁ ምርጫ አደርገን የማቆም ወይም የመለየትን እርምጃ እስካልወሰድን ድረስ የ“ፍዝ” ምርጫን መንገድ ተከትለን ሁኔታውን እንደመረጥነው ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ በሕይወትህ በፍጹም የማያዛልቅና እጅግ ጤና-ቢስ ወይም መርዛማ የሆነ ጓደኝነት ካለህ ከዚያ ሰው ለመለየት ተገቢውን ነገር ተናግረህ ወይም የሚገባህን እርምጃ ወስደህ ስትለይ ይህ ምርጫ ንቁ ምርጫ ይባላል፡፡ የዚያን ሰው ግን ኙነት አደገኛነት ብታውቅም ዝም ካልከው ግን በፍዝ ምርጫ መርህ መሰረት ጓደኝነቱን መርጠኸዋል፡፡ ዛሬ “ንቁ” ምርጫ ማድረግ የሚገቡህን ነገሮች በመለየት አስፈላጊውን እርምጃ ውሰድ!

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

11 May, 17:12


ከመስመሩ በላይና በታች

በኑሮ ላይ የተሰመረ ሃሳባዊ መስመር አለ። ጥቂቶች ከመስመሩ በላይ ሲኖሩ ብዙሃኑ ግን ከመስመሩ በታችን ይኖራሉ።

ይህ መስመር የአስተሳሰብ መስመር ነው። ከመስመሩ በታች ለመኖር እጅግ ቀላል ነው፤ ቀላል የሆነው ምቹ ሆኖ ሳይሆን ጥረት እና ልፋት ስለማይኖርበት ነው። እራስን ለማሻሻልም ሆነ እራስን ለማነጽ ምንም አይነት ሙከራ የማይደረግበት፤ የጨለምተኝነት ጭጋግ የወረሰው ስፍራ ነው። ከመስመሩ በታች የሚኖሩ ሰዎች ትናንታቸው ከዛሬ ዛሬያቸው ከነገ ለውጥ የለውም። የሰው ልጅ ዛሬም እንደትናንት ካሰበ እንዴት የተለየ ዛሬ ሊኖረው ይችላል?

ብዙ ጊዜ በህይወታችን ለውጥ ለማምጣት እንፈልግና ጥረታችን ሁሉ ከንቱ ሲሆንብን ኑሮ ልክ እንደ ክብ መንገድ ዞሮ ዞሮ የሚያመመጣን የቆምንበት ቦታ ይመስለናል። ነገር ግን ለውጥ ማምጣት የሚሳነን፤ እራስን መለወጥ ስለማይቻል ሳይሆን፤ አስተሳሰባችን ዛሬም እንደትናንት ስለሆነ ነው። ከመስመሩ በታች የሚኖሩ ሰዎች አስተሳሰባቸውን ለመቀየር ፤በህይወት ላይ ያላቸውን አመለካከት ለመለወጥ ጥረት አያደርጉም ምክንያቱም ቀላል አይደለምና።

አሉታዊ አስተሳሰቦችን ማሰብ በጣም ቀላል ነው፤ በኑሮዋችን ላይ የሚያመጡትን ተጽዕኖ ተቋቁሞ መኖሩ ግን በፍጹም ግን ቀላል አይደለም።

ከመሰመሩ በላይ የሚኖር ሰው አስተሳሰቡ የእጣ ፋንታ ጉዳይ ሳይሆን የምርጫ ጉዳይ እንደሆነ የሚያምን ሰው ነው ። ከመስመሩ በላይ መኖር ቀላል አይደለም ነገር ግን ህይወት የምትጋርጥብንን  ፈተና ለማለፍ ግን መነገዱን ቀላል ያደርገዋል። አወንታዊ አስተሳሰብን በእለት ተለት ኑሮ ላይ ለመተግበር ቀላል አይደለም።

ምክንያቱም ብዙ ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች ስላሉ። ብዙ ሰዎች አንድ መጽሃፍ አንብበው እስከዛሬ የገነቡትን የህይወት ልምድ ለመቀየር ይጥራሉ። ምንም እንኳን ለጠቢብ አንድ ቃል በቂው ነው ቢባልም፤ ባህሪን እና ልምድን በቀላሉ አሽቀንጥሮ መጣል ግን ለብዙዎቻችን ይከብዳል። ለዚህ ነው ብዙ ሰዎች የለውጥን ጎዳና ይጀምሩና ለውጡን በአንድ ጀንበር ሲያጡት ተስፋ ቆርጠው ተደብቀው ወደነበሩበት ጉድጓድ መልሰው የሚገቡት።

እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን አንድ ወሳኝ ነገር አለ። አንድ ሰው አንዴ 100 ኩንታል ስለተሸከመ በአንድ ቀን ጡንቻ አያወጣም። ጡንቻ ለማውጣት አልያም ደህና የሰውነት አቋምን ለማይዝ ያ ሰው ለብዙ ጊዜ ያለማቋረጥ እንቅስቃሴ ማድረግና እራሱን ያለመታከት መጠበቅ ይኖርበታል። አይምሮም ከዚህ አይለይም፤ ጤነኛ አይምሮን ለመያዝ የዘወትር ክትትል ያስፈልጋል።

አይምሮዋችን እያወቅንም ሆነ ሳናውቅ በምናከማቻቸው መረጃዎች የሚመራ ነው። በተለይ ሳናውቅ (subconsciously) እንደዘበት የምናጠራቅማቸው መረጃዎች፤ ልምድ ይሆኑብና አሁን ያለንን  ማንነት እንዴት እንደያዝነው ሳናውቅ በደመነፍስ እንኖራለን።

ደስ የሚለው እውነታ ግን በማንኛውም የህይወት መስመር ላይ ብንሆንም ወደምንፈልገው መንገድ ለመሄድ እድሉ አለን። የሁሉም ነገር ቁልፉ ግን አስተሳሰባችን ነው። አስቡት ማንኛቸውም  ነገሮች አለማችን ላይ እውን ሆነው ከመከሰታቸው በፊት በቅድሚያ አይምሮ ውስጥ መጸነስ አለባቸው። ይህም አሁን እውን ሆኖ የምናየው  እያንዳንዱ ነገር በመጀመሪያ ሃሳብ ነበር ወደሚለው መደምደሚያ ያደርሰናል። ስለዚህ አስተሳሰብ የምንም ነገር ፈጣሪ ነው ማለት ነው። ታዲያ ይህንን ትልቅ ሃይል ለመልካም ፈጠራ ብንጠቀምበትስ? ያኔ ከመስመሩ በላይ መኖር እንጀምራለን። ከመስመሩ በላይ ነጻነት፤ ደስታ እና ፍቅር እንዲሁም ተስፋ በበቂ ይኖራሉ። በቅጡ የማይመራ አስተሳሰብ ግን፤ ከመስመሩ በታች ያለነጻነት ያለተስፋ በእጣ ፋንታ ገመድ አስሮ ያኖረናል።

ሰው_ሁን_ከሰውም_ሰው_ሁን

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

11 May, 17:11


ስለ ጓደኝነት

“ጓደኛችሁ የመሻታችሁ ሁሉ ምላሽ ነው። በፍቅር ዘርታችሁ፣ በምስጋና የምታጭዱበት ማሳችሁ ነው።”
ካህሊል ጂብራን

“ጓደኝነት በዝግታ የሚበቅል ተክል ነው። ከማበቡም በፊት በከበባድ ችግሮች ውስጥ ማለፍ እና እነርሱንም መቋቋም አለበት።”
ሳሙኤል ኦልሪጅ

"መልካም እና አስተዋይ ጓደኛ የህይወት ስንቅ ነዉ።"
ያልታወቀ

"ዕጣፈንታ ዘመዶችህን ይመርጥልሃል፡፡ አንተ ግን ጓደኞችህን ትመርጣለህ፡፡"
ጃኪውስ ዴሊሌ

“ከፍቅርም በበለጠ ጓደኝነት ሕይወት ላይ ትልቅ ምልክት ያስቀምጣል። ፍቅር ወደ ልክፍት እና ባለቤትነት የመቀየር አደጋ አለው። ጓደኝነት ግን ማጋራት ብቻ ነው። ማካፈል።”
ኢሌ ቪይዘ

“ያለ ልበ-ሙሉነት ጓደኝነት ፈፅሞ ሊኖር አይችልም። ያለሃቀኝነት ደግሞ ልበ-ሙሉነት በጭራሽ ሊኖር አይችልም።”
ሳሙኤል ጆንሰን

"የምግባር ልዕልና ብቻ ነው ጓደኝነትን የሚፈጥረውም ጠብቆ የሚያቆየውም። ለፍላጐቶች መጣጣም ፣ ለዘላቂነት እና ለታማኝነት መሠረቱም እርሱ ብቻ ነው።”
ሲሴሮ

"እውነተኛ ጓደኛነት የሚለካው በጓደኞች ብዛት ሳይሆን በውድነታቸው ነው።”
ቤን ጆንሰን

"የሚያልቅ ጓደኝነት ሲጀመርም እውነተኛ አልነበረም ማለት ነው።”
ቅዱስ ጀሮሜ

"እስኪ ደስታ ለሚፈጥሩልን ሰዎች አመስጋኝ እንሁን። እነርሱ የነብሳችንን የአትክልት ስፍራ እንዲያብብ ፣ እንዲለመልም የሚንከባከቡ ድንቅ አትክልተኞች ናቸው።”
ማርሰል ፕራውስት

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

11 May, 17:11


ግትርነት ውስጥ ምህረት የለም!!

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ60 ዓ.ዓ የኖረው ጠቢቡ #ሲሴሮ ስለቁጣ ሲናገር ፦ << በንግሥና ዙፋን ተቀምጦ በቁጣ ቀንበር ስር እንደሚሰቃይ ንጉስ የሚያሳዝን የለም።>> ይላል፡፡

ንጉስ ግኔስ ፒሶ ፦ ቁጡ ፣ ግትር እና ማስተዋል የጎደለው ንጉስ ነበር ። #ፒሶ :: አንድ ቀን አንድ ወታደር ለአሰሳ ከወጣበት ሲመለስ አብሮት የወጣውን የመቶ አለቃ ትቶት ብቻውን ይመለሳል ። ይህን የሰማው #ንጉስ ፒሶ ወታደሩ እንዲገደል ትእዛዝ ሰጠ ። ለሞት ፍርዱም ምክንያት ፦ " ወታደሩ መቶ አለቃውን ገድሎት ሊሆን ይችላል ፤ ባይገድለውም ደግሞ አለቃው ትቶ መምጣቱ በራሱ ብቻ ያስገድለዋል " የሚል ነበር ።
ሞት የተፈረደበትን ወታደር የሚገድል ሌላ ወታደር ታዘዘና ወደ አንድ ከፍታ ይዞት ይወጣና ሰይፉን መምዘዝ ሲጀምር። መቶ አለቃው ድንገት ከተፍ ይላል ። ገዳዩ እና ተገዳዩ በዚህ ደስ ተሰኝተው ከመቶ አለቃው ጋር ሦስቱም ወደ ቤተ መንግስቱ ይመጣሉ ። ይህን ጊዜ በቤተ መንግስቱ ደስታ ይሆናል ። ነገር ግን #ፒሶ ሶስቱን ወታደሮች በአንድ ላይ ሲመለከት በቁጣ ነደደ ። ወዲያው ሦስቱም እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጠ።

የፒሶ ምክንያት ደግሞ ፦ <<የመጀመሪያው እንዲሞት እስቀድሜ ስለፈረድኩበት ይሞታል ፣ ሁለተኛው ወታደሩን እንዲገድል ትእዛዝ ከሰጠሁት በኃላ ትእዛዜን ባለመፈፀሙ ይሞታል ፣ ሦስተኛው የመቶ አለቃ ደግሞ ለወታደሩ መሞት ምክንያት ስለሆነ እሱም ይሞታል>> በማለት ፈረደ ።

#ግትርነት_ውስጥ_ምህረት_የለም!!!

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

11 May, 17:11


የጽሞና ጊዜ

አንድ ነጋዴ በመጋዘኑ ውስጥ ስራ ላይ እያለ በጣም የሚወደው የእጅ ሰዓቱ ይጠፋበታል፡፡ በመጋዝኑ ውሰጥ እየተመላለሰም በፍለጋ ቢወድቅ ቢነሳ ሊያገኘው ባለመቻሉ እውጭ ጨዋታ ላይ ያሉት ልጆች እንዲያግዙት፤ ሰዓቱን ላገኘለት ልጅም ሽልማት እንደሚሰጣቸው ነግሮ አሰማራቸው፡፡

ልጆቹም ሽልማት እንዳለው ባወቁ ጊዜ በፍጥነት እየተራኮቱ ወደ መጋዝኑ በመግባት ሁሉን ቦታ በአንድ ጊዜ አዳረሱት፡፡ ነገር ግን ሰዓቱን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ መጋዘኑ ውስጥ ያለውን እቃ ቢያነሱ ቢጥሉት ማግኘት አልቻሉም፡፡ ነጋዴው ልጆቹ እንዳላገኙት ባወቀ ጊዜ ተስፋ በመቁረጥ የሰዓቱን ፍለጋ ሊያቆም ሲል አንድ ትንሽ ልጅ ጠጋ ብሎ አንድ እድል እንዲሰጡት ጠያቃቸው፡፡ ነጋዴውም እስኪ ይሞክር በሚል ስሜት ፍቃደኛ ሆኑለት፡፡ ከቆይታ በኋላ ትንሹ ልጅ ሰዓቱን እጁ ላይ አንጠልጥሎ ተመለሰ፡፡

ነጋዴውም በሰዓቱ መገኘት እጅግ ደስ እያለው ሌሎቹ ልጆች ማግኘት ያልቻሉትን እንዴት ሊያገኘው እንደቻለ ተደንቆ ጠየቀው ትንሹ ልጅም “እኔ ምንም አላደረኩም ፡፡ ያደረኩት ነገር ከመጋዘኑ መሀከል ላይ በጸጥታ በመቆም ማዳመጥ ነበር፡፡ በፀጥታው ውስጥም የሰዓቱ መቁጠሪያ የሆኑት ዘንጎች ሲዞሩ የሚፈጥሩት ጠቅ…ጠቅ የሚለው ድምጽ ተሰማኝ ይህን አቅጣጫ ተከትዬ ስመለከት ሰዓቱን አየሁት” አላቸው፡፡

ግብረ ገባዊ ትምህርቱ በጽሞና ውስጥ የሆነ አዕምሮ ነገሮችን ለይቶ መረዳት ይችላል፡፡ አርቆ ለማሰብም ፋታ ያገኛል፡፡ ስለሆነም ኳኳታ በበዛበት ዓለም (መጋዝኑ በሸቀጥ እንደተጨናነቀው ሁሉ) ካለን ሰዓት ውሰጥ የተወሰኑትን ደቂቃዎች ለጽሞና ማዋል ከእራስ ጋር ለመነጋገርና መድረስ ወደምንፈልግበት የሕይወት ዓላማ አቅጣጫችንን ለማስተካከል ይረዳናል፡፡

ሰላም ያለው አእምሮ ትክክለኛ እሴት ይገነባል
ትክክለኛ እሴት ትክክለኛ አስተሳሰብ ይፈጥራል
ትክክለኛ የሆነ አስተሳሰብ ትክክለኛ የሆነ ድርጊትን ይወልዳል
ትክክለኛ የሆነ ድርጊት ሁሌም በጥሩ ፍሬ ይደመደማልና

🙏መልካም አዳር

ምንጭ፡- silence

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

11 May, 17:11


ስህተትን የመደጋገም አጉል ተጽእኖ
(“ራስን ማሸነፍ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

“ስህተት የሚሰራ ሰው፣ ሰው ይባላል፣ ስህተትን የሚደጋግም ግን ሞኝ ይባላል” የሚለውን አባባል ከዚህ በፊት እንደሰማኸው እገምታለሁ፡፡ አንድን ስህተት ከሰራ በኋላ አመዛዝኖና ሁኔታውን ፈትኖ በሚታረም ሰውና ያንኑ ስህተት በሚደጋግም ሰው መካከል ደግሞ ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ ስህተትን የሚደጋግም ሰው ከዚያው ጋር ራሱን ለብዙ መዘዞች ያጋልጣል፡፡ ይህንን እውነታ ግን ሁሉም ሰው አይቀበለውም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ስህተት እንዲሰሩ ምክንያት የሆነባቸውን ሰውና ሁኔታ ስለወቀሱ ወይም ስላሳበቡ ከመዘዝ የሚያመልጡ ይመስላቸዋል፡፡ አንድን መርዝ እንድንጠጣ አንድ ሰው ስላታለለንና ያንንም ሰው ስለወቀስነው ከመርዙ ሰበብ እንደማናመልጥ ሁሉ ከማንኛውም ተደጋጋሚ ስህተት አጉል ውጤትም ሰዎችን ስለወቀስን ሊቀርልን አይችልም፡፡

የማይድን ቁስል
ተመሳሳይ ስህተትን መስራት ማለት ከተመሳሳይ ችግር ጋር መኖር ማለት ነው፡፡ ተመሳሳይ ችግር የሚያመጣብን መዘዝ ተመሳሳይ ቦታ ላይ የማቁሰል ሁኔታ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ያንኑ ስህተት ሰርተን ከደረሰብን ሁኔታ በሚገባ ሳናገግም ያንኑ ስህተት በመድገም ተመሳሳይ ጉዳት ሲደርስብን ዝለት ይከተላል፡፡ በእንደዚህ ሁኔታ ለረጅም ጊዜ የሚከርም ሰው የኋላ ኃላ መዘዙን ማየት ይጀምራል፡፡ ሕይወት ከአንዱ ቁስል ወደ ሌላኛው ቁስል በመሸጋገር ለማገገም የምንመኝባት መስክ መሆን የለባትም፡፡ በምትኩ፣ ከስህተት በመማርና ስህተቱን ባለመድገም ከአንዱ ድል ወደ ሌላኛው ድል በመሸጋገር ለተሻለ ነገር የምንሰራባት መስክ ልትሆን ይገባል፡፡

የራስ-በራስ ንቀት
አንድ ሰው የመጨረሻ ዝቅተኛ ደረጃ ወረደ የሚባለው በራሱ ላይ ያለው ግምት በጣም ሲወርድና ራሱን መናቅ ሲጀምር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ከሚከሰትባቸው ምክንያቶች አንዱ ደግሞ አንድን ስህተት ማረም እንዳለበት እያወቀ፣ ደግሞ ደጋግሞ በዚያው ስህተት የመገኘት ሁኔታ ነው፡፡ በስህተትና በጸጸት ዑደት (አዙሪት) ውስጥ የሚኖር ሰው ቀስ በቀስ ራሱን እንደ ሰነፍ፣ መሻሻል እንደማይችልና ሌሎች ሰዎች ማድረግ የቻሉትን ቀላል ነገር እሱ ግን እንዳቃተው ማሰብ ይጀምራል፡፡ ይህ ራስን የመናቅ ሁኔታ ለወደፊቱ የሚኖረውንም የመሻሻል ፍላጎት ስለሚነካበት ወደሌላ የግድ-የለሽነት ስህተት ይመራዋል፡፡

“የእድል ሰለባ” አመለካከት
በዙሪያህ የሚገኙ ሰዎች ስህተታቸውን በማረምና ራሳቸውን በማሻሻል በሚያስገርም ፍጥነት ሲያልፉ እያየህ ራስህን ስትመለከተው ደግሞ ባለህበት እንደረገጥክ ሲሰማህ በአመለካከትህ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ማስከተሉ አይቀርም፡፡ ለጥሩ ነገር እንዳልታደልክና ምንም ያህል ብትጣጣር የአንተ እድል አሁን ያለህበት ሁኔታ እንደሆነ ከማሰብ ውጪ ምንም ምርጫ እንዳይኖርህ ትገፋፋለህ፡፡ “ፈጣሪ ጨከነብኝ”፣ “ማንም ሰው ለእኔ ግድ የለውም”፣ “እድለ-ቢስ ነኝ” እና የመሳሰሉት አመለካከቶችና አባባሎች እንዲሁ አይመጡም፡፡ አእምሮን ተጠቅሞ በማሰብ፣ የተግባርንና የውጤትን ግንኙነት መገንዘብ ካልቻልክ ሁኔታዎችን ከእድል ሰለባነት ጋር ማገናኘትህ አይቀርም፡፡

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

11 May, 17:11


ግሩም አባባሎች

1."የሴቶች ዋነኛ ችግር ወንዶች ስለሴቶች የሚኖራቸውን ፅንሰ ሃሳብ አሟልተው ለመገኘት ሁልጊዜም መጣራቸው ነው።"
ላውረንስ

2.‹‹ፍ/ቤት በተወሰኑ ዳኞች የተገነባ ሲሆን የዳኝነቱን ሥራ የተሻለ ጠበቃ ላለው ሰው መፍረድ ብቻ ነው”
ሮበርት ፍሮስት

3." የራስን ስሜት መቆጣጠር አለመቻል አቅጣጫ ጠቋሚ በሌለው መርከብ እንደመጓዝ ነው። "
ማህተመ ጋንዲ

4."ተኩላዎች ዳኞች ሆነው በተሰየሙበት ችሎት የበጎች ቀጣይ እጣፋንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም።"
ይዲሽ

5.‹‹ሐብታሞችን ድሃ በማድረግ ድሆችን ሃብታም ማድረግ አይቻልም፡፡››
ዊንስተን ቸርችል

6."ሃሳባቸውን መለወጥ የማይችሉ ሰዎች፣ ምንም ነገር ሊለውጡ አይችሉም፡፡"
 ጆርጅ በርናርድ ሾው

7." ብልህ ሰው አንድ ቃል ሰምቶ ሁለት
ይረዳል።"
አይሁዶች

8.‹‹ ብዙ ጊዜ ብቻህን መሆን ካልቻልክ ከሌሎች ጋር ያለህ ግንኙነት ሁሉ የውሸት ነው፡፡ ይሄ ብቸኝነትህን ለመሸወድ የምታደርገው እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፡፡ ››
ኦሾ

9.‹‹መሻሻል ማለት መለወጥ ማለት ነው፡፡ ፍፁም መሆን ማለት ደግሞ ሁልጊዜ መለወጥ ማለት ነው፡፡››
ዊንስተን ቸርችል

10."በዕውቀት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት የላቀ ትርፍ ያስገኛል፡፡"
    ቤንጃሚን ፍራንክሊን

11."በአቋሙ የፀና ሰው ከሆንክ አቋምህን ሊያስቀይሱ ከሚጥሩ ሰዎች ጋር ኣንገት ለአንገት ተናንቀህ የክብር ሞት ትሞታለህ፡፡በተቃራኒው አቋም የሌለው ወለዋይ ከሆንክ ደግሞ በጌቶችህ መዳፍ ሥር ወድቀህ በየቀኑ የቁም ሞት ትሞታለህ"
ባልዛክ

12. ‹‹ጨለምተኛ ሠው በየትኛውም አጋጣሚዎቹ ችግሮች ይታዩታል፤ መልካም አሳቢ ግን በችግሮች ውስጥ መልካም አጋጣሚን ያማትራል፡፡››
ዊንሰተን ቸርችል

#ሼር አድርጉ

አቅራቢ-አቤል
Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

11 May, 17:11


አንድ ቀን ሁሉም ሰራተኞች ወደ ቢሮ ሲደርሱ እንድ ጎላ ተደርጎ የተፃፈ ማስታወቂያ ተለጥፎ አዩ ፡፡ “በዚህ ኩባንያ ውስጥ እድገትዎን የሚያደናቅፈው ሰው በትላንትናው ዕለት ከዚህ አለም በሞት ስለተለየ በመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ተዘጋጅቷልና መጥተው ይሰናበቱት ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን" የሚል

መጀመሪያ ላይ ሁሉም በሞተው የሥራ ባልደረባ ሐዘን ገብቷቸው ነበር ፣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን የባልደረቦቹን እና የድርጅቱን እድገት የሚያደናቅፍ ያ ሰው ማን እንደሆነ ለማወቅ መጓጓት ጀመሩ፡፡
በአዳራሹ ውስጥ በርካታ ሰው ስለነበር ደንብ አስከባሪ ጥበቃ በክፍሉ ውስጥ ያለውን ሕዝብ እንዲቆጣጠሩ ትእዛዝ ተሰጣቸው። አዳራሽ ውስጥ ያለው ሰው እየጨመረ በመጣ ቁጥር የሟቹን ነገር ተረስቶ እድገታቸውን ያስተጓጎለው ሰው በሞሞቱ ደስታ ይሰማቸው ነበር፡፡ ብዙዎቹም እያጉረመሩሙ መደሰታቸውን ይገልጻሉ፡፡ ሰዎች ወደ ሬሳ ሳጥኑ በቀረቡ ቁጥር ደስታቸው እየጨመረ መጣ፡፡ በዛው መጠን ማን እንደሆነ የማወቅ ጉጉታቸው አየለ፡፡ “እድገቴን የሚያደናቅፈው ይህ ሰው ማነው? እንኳንም ሞተ! አሁን ቶሎ አድጋለው” ብለው የሚያስቡ በርካቶች ነበሩ፡፡ አስተናባሪዎች፤ ሰራተኞች አንድ በአንድ ወደ የሬሳ ሳጥኑ እንዲጠጉ እና ወደ ውስጥ እንዲያዩ አደረጉ፡፡ ሳጥኑ ውስ ያለውን ነገር ሲመለከቱ ግን በሙሉ ድንገት ዝም አሉ። በሬሳ ሳጥኑ ውስጥ የጠበቁት ሬሳ አልነበረም። በምትኩ የራሳቸውን ምስል መልሶ የሚያሳያቸው መስታዎት ነበር የተቀመጠው።
ከመስተዋቱ አጠገብ “በእድገትዎ ላይ ገደብ የማድረግ ችሎታ ያለው አንድ ሰው ብቻ ነው ፡፡ እርሱም ራስዎ ነዎት” የሚል መልእክትም በጉልህ ይታያል። ያኔ ሁሉም ሰው ወደ ልቡ ተመልሶ ስራውን በአግባቡ ይሰራ ጀመር...
***
በህይወታችን ውስጥ ለውጥ ሊያመጡ የምንችለው ራሳችን ብቻ ነን፡፡ በደስታ እና በስኬታችንም ላይ ተጽዕኖ ልናሳርፍ የምንችለው እኛው ነን። ለእኛ ከእኛ በቀር ረዳት ከየት ሊመጣል ይችላል።

አለቃችን ስለተቀየረ ፣ ጓደኞች ስለለወጥን፣ መስሪያ ቤት ስለቀየርን፣ ሕይወታችን ላይ ለውጥ አይመጣም። ራሳችንን በለወጥን ጊዜ ግን ሁሉም ለውጥ ይከሰታል።

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

27 Feb, 21:15


የመኖር ጥበብ!!

💚የመኖርን ጥበብ በእጅጉ የሚሻ አንድ ሰው ወደ አንድ ታላቅ ጠቢብ ዘንድ ይሄዳል። ግራ መጋባት የሚታይበት ይህ ሰው ጠቢቡ ጋር እንደ ደረሰ የጥያቄ መዕት ያወርድበታል። ጠቢቡም ሰው ሁሉንም ጥያቄ በጥሞና ይሰማ ነበር። " የመኖርን ጥበብ አውቅ ዘንድ ካንተ ዘንድ መጣው። ቢቻልህስ ንገረኝ።" አለው።

💛ጠቢቡም ሰው እንዲ ሲል መለሰለት። "በ አንድ ወቅት ሰው ሁሉ የሚገረምበት አንድ ትልቅ ከመስታወት የተሰራ ትልቅ ቤት ነበር። ሁሉም ጥበብን የሚሻ የሚሄድበትና ጥበብን የሚማርበት። እናልህ ሁለት ሰዎች ይሄን ሰምተው ወደዛ ቤት ይሄዳሉ። ሁለቱም እጅግ የተለያዩ ናቸው። አንዱ ደስተኛ ተጫዋች ቅለል ያለ ህይወት የሚመራ ሲሆን ሁለተኛው በአንፃሩ ንዴታምና ብስጩ፥ ህይወትንም መክበድ የሌለባትን ያህል አክብዶ የሚያይ ነበር።

❤️ወደ መስታወት ቤት ሲደርሱ ደስተኛው ሰው ቀድሞ ገባ። ወደ ቤቱም ሲገባ በጣም ተማረከበት። ፊታቸው እጅግ የበራ፥ ህይወትን በእጅጉ የሚያጣጥሙ አይላፍ ህዝብ ተመለከተ። ከበፊቱም በላይ እጅግ ተደስቶም ከመስታዎት ቤቱ ወጣ። ውጪ ቆሞ ላለው ለሌለኛው ሰውም ያየውን ነገረው።

💚እጅግ ብስጪ ንዴታሙ ሰውም ወደ መስታዎት ቤቱ ገባ። ያጋጠመውም ነገር ከበፊቱ እጅግ የተለየ ነበር። አእላፍ ደስታ የራቃቸውንም ሰዎች ተመለከተ። ቤቱን ከመውደድ ይልቅ ጥላቻ ሞላበት። እጅግ በተበሳጨ ቁጥር ቤቱ ውስጥ ያሉትም አእላፍ ሰዎች ብስጭታቸው ይጨምር ነበር። እሱ የሚያደርገው እያንዳንዱን ነገር እነርሱ በእጥፍ ይመልሱለት ነበር።" አለ ጠቢቡ ሰው።

💛ቀጥሎም "አየህ ሁለቱ ሰዎች ያዩት ነገር ሌላ ነገር ሳይሆን የራሳቸውን ምስል ነው። መስታወቱ የራሳቸውን ምስል መልሶ እያሳያቸው ነበር። እዚም ምድር ላይ የተለየ የመኖር ጥበብ የለም። አንተ የሆንከውን አከባቢህ ይሆንልሀል። ደስታን ከሰጠኸው እጥፍ አርጎ ይመልስልሃል። ፍቅር ከሰጠኸው አትርፍርፎ ላንተም ይሰጥሀል። ጥበቃ ካረክለት እርሱም መልሶ ይንከባከብሃል። ደግ ስትሆንለት ደግነት ታገኛለህ።

❤️ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደሚባለው ሰው በ አሉታዊ ሀሳብ ተብትቦ ደግ ነገርን ከሰው ይጠብቃል። እየገደለ መኖርን ይፈልጋል። እያደማ መዳንን ይሽል። እየሱስ ይሄን ባንድ አርፍተ ነገር " የዘራኸውን ታጭዳለህ። " በማለት ገልፆታል። "ሊደረግልህ የምትፈልገውን አንተ ለሰው አድርግ ይላል።" ደግሞም እንዲህ ይባላል " አለም ላይ ማየት የምትፈልገውን ነገር አንተ ደግሞ እርሱን አርግ።"

💚አዎ ሰው ነገሮችን ሁለት ጎን እንዳላቸው ሳያቅ ይኖርና በመጨረሻም ይጎዳል። አሸናፊነትን እንጂ በሌላ ጎን ያለውን ሽንፈትን አይረዳውም። ህይወትና ሞት ፥ ደስታና ሀዘን ፤ መግደልና መሞት ፥ መውደድና ጥላቻ...... ወዘት የአንድ ነገር ሁለት ጎኖች ናቸው። አንዱን ብቻ ስንረዳ የእውነትን ግማሽ ተረዳን ማለት ነው። ሁለቱንም ስንረዳ ግን ሁሉም ይገባናል። ሀዘንን ለመሸሽ በሌሎች ሀዘንን አናመጣም። መውደድን ለማቆየት ሌሎችን አንጠላም።

💛ነገር ግን ተቃራኒ የሌለው አንድ ነገር አለ። እርሱም በ እ/ር ተመስሏል። ይህ ተቃራኒ የሌለው አቻም ያልተገኘለት ነገር ፍቅር ነው። ፍቅር ጊዜን ጠብቆ የማይከዳ የተፈጥሮ ሀብት ነው። ገፅ በረከት ስጣታም ነው። ፍቅር ስንሰጥ ሁሉንም በሁሉ ውስጥ እናገኛለን።

❤️ለዚህ የመኖር ጥበብ በጥቅሉ ያለ ቅድመ ሁኔታ ማፍቀር ነው። የሰው ልጅ ደጋግሞ ከመስማቱ ያልተገበረው ነገር ግን የሰለቸው ቃል። ሰው ተቃራኒ ያለውን ፍቅር ይዞ ይጎዳል። ፍቅር ይበለው እንጂ ይሄ በፍቅር ስም የሚነግድ ሌላ አይነት ስሜት ነው። ግዜን ጠብቆ ወደ ጥላቻ የሚሄድ ፍቅር ፍፁም ፍቅር አይባልም ። ፍፁሙን ፍቅር እሻ"!!!


#share
Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

27 Feb, 21:04


እያንዳንዱን ችግር እንደ መሰላል ከተወጣጣህበት ከስኬት ጫፍ ትደርሳለህ!!

በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጉድ ወስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣም መጮህ ጀመረች፡፡ ባለቤቱም እሷን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ አደረገ አልተሳካለትም ፤ አህያዋ አርጅታለችና ጉድጓድ ውስጥ ሊቀብራት አሰበ።

ጎረቤቶቹንም ጠራና ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመረ፡፡ አህያዋ ይህንን ስተመለከት እየቀበራት መሆኑን ተረዳችና እጅጉን አዘነች፡፡

ይሁን እንጂ አፈር በተደፋባት ቁጥር አህያዋ አንድ ነገር ታደርግ ነበር። አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ነበር። በተደጋጋሚ ከዚያም በተደፋው አፈር ላይ መቆም ትጀምራለች። በሒደት ውስጥ በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች በመጨረሻም ከጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መውጣት ቻለች፡፡ በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ስዎች ሁሉ በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡

ውድ አንባቢያን እንደሚታወቀው የአህያዋ ታሪክ ሁላችንንም ይመለከተናል። የሚጫንብን አፈር ደግሞ በየጊዜው የሚያጋጥሙንና ዝም ብንላቸው በመጨረሻ ሊቀብሩን የሚችሉ ችግሮች ወይም መሠናክሎች ናቸው፡፡ አፈሩን የሚጭኑት ሰዎች በዙሪያችን ያሉ ሰዎች፣ ነገሮች፣ በህይወታችን ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩብን አዳዲስ ለውጦች እንዲሁም የራሳችን አፍራሽ ስሜቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ጉድጓዱ ደግሞ አሁን ያለንበት ግራ የተጋባንበት! ተስፋ ቢስ የሆንበት፡ መላ ያጣንበት ህይወት ወይም ገጠመኝ ሊሆን ይችላል፡፡

በእርግጥም እኛ ሰዎች በጤናችን! በኢኮኖሚ ህይወታችን፤ በትዳርና ፍቅር ህይወታችን በተለያየ አጋጣሚ ልክ እንደ አህያዋ ጉድጓድ ውስጥ የመግባት ዕድላችን ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ጠንካሮች እንደ ጠንካራዋ አህያ ከገቡበት ጉድጓድ ውስጥ መውጣት ሲችሉ አንዳንዶቹ በዚያው ተቀብረው ቀርተዋል፡፡

ውድ አንባቢያን በህይወታችን ውስጥ ያለው አማራጭ! ወደ ላይ መውጣት አልያም ደግሞ ወደ ታች ወርዶ ከጥልቅ ጉዳጓድ ውስጥ ተቀብሮ መቅረት ብቻ ነው! በየጊዜው ሊገጥመን የሚችለውን ችግር ልክ እንደ አህያዋ የሚጫንባትን አፈር እየረገጠች ወደ ላይ ከፍ እንዳለችው ሁሉ አንተም/አንቺም በየጊዜው የሚገጥማችሁን ችግሮች እንደ ድጋፍ እየተጠቀማችሁ በጥንካሬ ወደ ላይ መነሳት ያስፈልጋል፡፡ ከጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ለመውጣት የምንችለው ለመውጣት የምናደርገውን ጥረት ባለማቆም ብቻ ነው።
በመሆኑም ምንጊዜም በጠንካራ ውስጣዊ ቁርጠኝነትና እምነት ችግሮችን እንደ መወጣጫ ደረጃ በመጠቀም ከታች ወደ ላይ ተጓዙ ለማለት እወዳለሁ።

#share
Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

27 Feb, 20:30


አዋዋልህ ሕይወትህን ይወስናል!!

አዋዋልህ የህይወትህ መገለጫ ነው፡፡ አንዲቷን ቀን የምታሳልፍበት መንገድ የዘመናት ሕይወትህን ይወስናል፡፡ ዛሬ የምትሠራው ነገር የወደፊት ሕይወትህን ይፈጥራል፡፡ የምትናገራቸው ቃላት፣ የምታፈልቀው ሐሳብ፣ የምትመገበው ምግብ እንዲሁም የምትወስዳቸው እርምጃዎች እጣ ፈንታህን ይወስናሉ፣ ማንነትህንና ሕይወትህን ይቀርፃሉ፡፡ ትናንሽ ውሳኔዎች በጊዜ ሂደት ግዙፍ ውጤት ያስከትላሉ። ‹‹ትርጉም አልባ» እለት የሚባል ነገር የለም፡፡

እያንዳንዳችን ለታላቅነት የሚያበቃ ጥሪ አለን፡፡ እያንዳንዳችን በውስጣችን ታላቅ ኃይል አለ፡፡ እያንዳንዳችን በዙሪያችን በሚገኙ ሰዎች፣ ሁናቴዎችና ነገሮች ላይ ተጽእኖ ማድረግ እንችላለን። በውስጣችን የሚገኘውን ይህን ኃይል ለማጎልበት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ ይበልጥ ተግባራዊ ስናደርገው የበለጠ ይጎለብታል፤ ብርቱ ይሆናል። ይሄን ኃይል ይበልጥ ስትጠቀምበት ይበልጥ ልበ-ሙሉ፤ በራስህ የምትተማመን ትሆናለህ፡፡

ከእኛ መካከል ይበልጥ ስኬታማ የሆኑት ሰዎች ከተቀረነው የተለየ ስጦታ ያላቸው አይደሉም፡፡ ወደ ታላቁ ሕይወት ሲጓዙ በየእለቱ ጥቂት ደረጃዎችን በትክክለኛው አቅጣጫ የሚራመዱ ናቸው፡፡ . ቀናት ወደ ሳምንታት፣ ሳምንታት ወደ ወራት ይሸጋገራሉ. . . ሳይታወቃቸው የተለየ» ተብሎ ከሚታወቅ ሥፍራ ይደርሳሉ፡፡

✍️ሮቢን ሻርማ

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

27 Feb, 20:30


አደጋን ተጋፈጥ

ከብዙ ሰዎች የበለጠ ውድቀት ይገጥመኛል፡፡ በንግድ ሥራዬ ውድቀት ግጥሞኛል፡፡ በማህበራዊ ግንኙነት ውድቀት ገጥሞኛል፡፡ በሕይወቴ ብዙ ጊዜ ውድቀት ይገጥመኛል፡፡ ይህ ለምን እንደተከሰተ በመገረም አስባለሁ፡፡ በውድቀቴ እማረር ነበር፡፡ አሁን ግን ገብቶኛል፡፡ ውድቀት ከታላቅ ደረጃ ለመድረስ የሚከፈል ዋጋ ነው፡፡ ውድቀት የታላቅ ስኬት መሠረታዊ ግብአት ነው፡፡ አዲስ ነገር በመፍጠር ጠቢብ የሆነው ዴቪድ ኬሊ ይህን ብሏል፡- «ቶሎ ውደቅና ፈጥነህ ተነሥ››.. ከምቾት ቀጠናህ ሳትወጣና በተጠና መልኩ አደጋን ካልተጋፈጥህ ልታሸንፍ አትችልም፡፡

ብዙዎቻችን የምንኖረው የደህንነት ስሜት በሚፈጥርልን በሚታወቅ «ወደብ› ላይ ሆነን ነው። ለሃያ ዓመታት አንድ ዓይነት ምግብ ስንመገብ ኖረናል፣ ለሀያ ዓመታት በአንድ ሥፍራ ተወስነን ኖረናል፤ ለሀያ ዓመታት በአንድ መንገድ ተመላልሰናል፣ ለሀያ ዓመታት አንድ ዓይነት አስተሳሰብ አንጸባርቀናል። በዚህ መልኩ አስደሳች ሕይወት ለመምራት አይቻልም፡፡ እስከዛሬ ስትሰራ የኖርከውን መሥራት ከቀጠልክ እስከዛሬ ስታገኝ የቆየኸውን ማግኘትህን ትቀጥላለህ፡፡ አይንስታይን እብደትን የገለጸው «ተመሳሳይ ነገር እየሰሩ የተለየ ውጤት መጠበቅ» በማለት ነው። እውነተኛ ሐሴትን ልትጎናጸፍ የምትችለው አደጋን ተጋፍጠህ ወደ ታላቁ ባሕር ቀዝፈህ ስትገባ እንጂ ከወደብ ላይ ተወስነህ ስትቆም እይደለም፡፡

ውድቀት ደረጃህን ከፍ የማድረግ ሂደት አካል ነው። በምድሪቱ ላይ የሚገኙ ግዙፍ ስኬታማ ተቋማት ስኬትማ ከመሆናቸው በፊት ብዙ ውድቀትን አስተናግደዋል፡፡ በጣም ስኬታማ ሰዎች ከተራ ሰዎች ይበልጥ ውድቀት
አስተናግደዋል። ለእኔ፣ ውድቀት ለመሞከር ና ለመድፈር አለመቻል ነው። እውነተኛ አደጋ ያለው አደጋ አልባ ሕይወት በመምራት ነው፡፡ ማርክ ትዌይን ትዝብቱን እንዲህ ሲል አስፍሯል፡- ‹ከሀያ ዓመታት በኋላ ከሠራሃቸው ይልቅ ባልሰራሃቸው ነገሮች ትበሳጫለህ›› ስለዚህ፣ ከዛሬ ጀምር፡፡

✍️ሮቢን ሻርማ

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

27 Feb, 20:30


🌍ምድር ትንሽ ነች

በግዙፍ ፍጥረተ-ዓለም ውስጥ በሚገኝ ትንሽ ፕላኔት ላይ ነው የምንኖረው፡፡ ታወቀው የፊዚክስ ሊቅ ስቴፈን ሐውኪንግ እንዳለው ከአንድ መቶ ቢሊየን ጋላክሲዎች መካከል በአንደኛው ኮከብ ውጭ በሚገኝ በጣም አነስተኛ በሆነ ፕላኔት ላይ ነን፡፡

እኔና አንተ ከዚህ ካለነው ቢሊየኖች ውስጥ አንዱ ነን፡፡ በየእለቱ የሚገጥሙን ችግሮች ያን ያህል በጣም ግዙፍ ናቸውን? እይታን በጥቂቱም ቢሆን መለወጥ ሕይወትን ቀላል ያደርጋል፡፡
ፈተና ሲገጥመኝ ለራሴ ይህን ጥያቄ አቀርባለሁ፡- «ይህ ነገር ከዛሬ አንድ ዓመት በኋላም ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ይገኛልን? የማይገኝ ካልሆነ በፍጥነት አልፌው እጓዛለሁ። ከባልደረቦችህ ወይም ለቤተሰቦችህ እንድታነሳ የምመክርህ ሌላኛው ጥያቄ ደግሞ ይህ ነው፡- «በዚህ ምክንያት ሕይወት ትቆማለችን?›› ካልቆመች ነገሮች በቀላሉ ይሰክናሉ፤ የሰከነ አእምሮ ሁሌም ያሸንፋል።

ከባድ አደጋ አድርገን የምንቆጥራቸው ችግሮች ብዙውን ጊዜ ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከታቸው በረከት ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ በሕይወቴ የምድር ፍፃሜ መቃረቡን እንዳስብ ያደረጉኝ ከባድ ችግሮች ገጥመውኛል። ነገር ግን ጊዜ ሲያልፍ እነዚያ ችግሮች ሕይወቴን የተሻለ በደስታ የተሞላ ያደረጉልኝ ሆነዋል፡፡ ለአንተም ይኸው እውነት እንደሚሆን እምነቴ ነው። ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ በመልካም ነገር ላይ እተኩር፡፡ ከበፊቱ ይበልጥ ሳቅ፣ፈገግታ ከፊትህ አይለይህ፡፡ ሕይወት አጭር ነች ዓለም ትንሽ ነች ነገር ግን በጣም ሰፊም ነች፡፡

✍️ሮቢን ሻርማ

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

27 Feb, 20:30


ውበት እና ህይወት እንደተመልካቹ ነው።

ከ150 ዓመት በፊት ነው፤ አንድ የእንግሊዝ የጫማ ፋብሪካ፤ አፍሪካ ውስጥ የጫማ ፋብሪካ ማቋቋም ይፈልግና የአዋጪነት ገበያ ጥናት ለማድረግ፤ ሁለት የሽያጭ ሠራተኞቹን በየፊናቸው የገበያ ጥናት እንዲያደርጉ ወደ ጥንታዊቷ አፍሪካ ይልካቸዋል፡፡ ሠራተኞቹ በቦታው እንደደረሱ ጥናታቸውን ለማድረግ፣ በየከተሞቹ በሚዘዋወሩበት ጊዜ ሁለቱም ያዩትን ማመን ይቸግራቸዋል። የሚያዩት ሰው ሁሉ የሚንቀሳቀሰው በባዶ እግሩ ነው፡፡ ቢያዩ ቢያዩ፤ አንድም ጫማ ያጠለቀ ሰው የለም፡፡ ሠራተኞቹም በየግላቸው ሪፖርታቸውን አጠናቅረው ወደ ሀገራችው በመመለስ ሪፖርቱን ያቀርባሉ፡፡

#የመጀመሪያው የሽያጭ ሠራተኛ ሪፖርትና ድምዳሜ፡- ሀገሬው በሙሉ ባዶ እግሩን ስለሚሄድ ፤ ጫማ ብናመርት ከእኛ ጫማ የሚገዛ አንድም ሰው ስለማናገኝ፤ ፋብሪካ መክፈቱ አያዋጣንም በማለት ሪፖርቱን ያቀርባል።

#ሁለተኛው የሽያጭ ሠራተኛ ሪፖርትና ድምዳሜ፡- ሀገሬው በሙሉ ባዶ እግሩን ስለሚሄድ ፤ ጫማ ብናመርት ከእኛ ጫማ የሚገዛ ብዙ ሰው ስለምናገኝ፤ ሰፊ የገበያ ዕድል አለ፡፡ በመሆኑም ፋብሪካ መክፈቱ በከፍተኛ ደረጃ አዋጭ ነው በማለት ሪፖርቱን ያቀርባል፡፡

ሁለት የተለያዩ ሰዎች፣ በአንድ ተመሳሳይ ሁኔታ ላይ መልካም አጋጣሚዎችን በመረዳት ረገድ እንዴት ሁለት የተለያዩ ድምዳሜዎች ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ግን ምን ይሆን? ከበርካታ ምክንያቶች መካከል አንዱና ዋናው የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዊንስተን ቸርችል አባባል ለዚህ ጥያቄ መልስ ሳይሆን ይቀራል ትላላችሁ? “A Pessimist sees the difficulty in every Opportunity፡ An Optimist sees the opportunity in every difficulty” ፤ ማለትም ቀና አሳቢዎች በችግር ውስጥ ለስኬት የሚያበቃ መልካም አጋጣሚዎችን ያያሉ። ነገር ግን ጨለምተኞች ደግሞ በመልካም አጋጣሚዎች ውስጥም የሚታያቸው ነገር ችግር ነው” እንደ ማለት ነው፡፡ ቁም ነገሩ በጎ አመለካከት በመያዝ፤ መልካም አጋጣሚዎችን በውል አጢኖ መጠቀሙ ላይ ነው፡፡

በህይወታችን ውስጥ አንድን ነገር የምናይበት መንገድ የነገሩን ውጤት ይወስናል። አንድ አጋጣሚ ለአንድ ሰው መጥፎ ሊሆን የሚችለው የአጋጣሚውን መጥፎ አቅጣጫ ለመመልከት በማተኮሩ ነው። በተፈጠረው ክስተት ውስጥ “ ምን ጥሩ አጋጣሚ ወይም ዕድል ሊኖር ይችላል?” ብሎ ቢጠይቅ አዕምሯችን ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመፈለግ ትኩረቱን የሚያደርገው በክስተቱ ጠቃሚ ትሩፋቶች ላይ ይሆናል። “ጠይቁ ይሰጣችኃል!” እንዳለው ክርስቶስም እንዲሆንልን የምንፈልገውን ጥያቄ በመጠየቅ አዕምሯችን በዚያ ነገር ላይ እንዲያተኩርና መልስ እንዲፈልግ እናደርገዋለን፡፡በኳንተም ፊዚክስ እሳቤም አንድን ነገር አትኩረን የተመለከትንበት መንገድ ውጤቱን ይወስነዋል፡፡ ስለዚህ የነገሮችን ውጤት የሚወስነው ለማተኮር የፈለግንበት መንገድ ነው።

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

27 Feb, 20:30


“የማትጠቀምበት ነገር ሁሉ ያንተ አይደለም!”

ሽማግሌው ሲጠባበቁት የነበረው አውቶብስ ስለመጣላቸው ለመሳፈር ተጠግተዋል፡፡ እግራቸውን አንስተው ወደ ውስጥ ሲገቡ በአጋጣሚ የአንድ እግር ጫማቸው ተንሸራቶ ውጭ ይቀራል፡፡ መልሰው ጫማቸውን ማግኘት ሳይችሉ አውቶብሱ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ሽማግሌው ምንም አይነት የብስጭት ቃላት ሳያሰሙ የቀሪ እግራቸውን ጫማ ያወልቁና በመስኮት በኩል አሾልከው ወደ ውጭ ይጥሉታል፡፡ የሽማግሌውን ድርጊት ውስጥ ሁኖ ይመለከት የነበረ ወጣት ተሳፋሪ ለሽማግሌው እንዲህ ሲል ጥያቄውን አቀረበላቸው፡፡ “አባት ሲያደርጉ የነበሩትን ነገር እያየሁ ነበር፡፡ ለምንድን ነው ቀሪውን ጫማ የወረወሩት?” አላቸው፡፡ ሽማግሌውም ወዲያውኑ እንዲህ ሲሉ መለሱለት “እየውልህ ልጄ ሾልኮ የቀረውን ጫማ ሊጠቀሙበት የሚችሉት ይሄኛውም አብሮ ሲኖር ነው፡፡ እናም ለማንኛውም ያገኘው አካል ጥቅም እነዲሰጠው ወይም ዋጋ እንዲኖረው ስል ነው ይሄኛውን ጨምሬ መወርወሬ” አሉት፡፡ በዚህም ድርጊታቸው ሽማግሌው ወጣቱን ጥሩ አድርገው የሕይዎትን ፍልስፍና አስተማሩት፡፡

⚜️ንብረታችን ብለን የምንይዛቸው ነገሮች ጥቅም እስከሰጡን ብቻ እንጅ ለእኛ አስፈላጊነት የሚኖራቸው አለኝ ለማለት ነው ወይም የባለንብረትነቱን ስም (ባለቤትነትን) በመሻት ብቻ ይዘን መቀመጥ የለብንም ሲሉት ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ያ ቁስ አካል ለሌላኛው ወገን ከፍተኛ ጥቅም መስጠት ሲችል እንዲሁ በከንቱ እኛ ጋ ዝም ብሎ ተቀምጦ ከሆነ እርባና የለውም፡፡ ደራሲ እንዳለጌታ እንዳለው “የማትጠቀምበት ነገር ሁሉ ያንተ አይደለም!”


Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

27 Feb, 20:02


«እምቢ» ማለትን ተማር

ጠቃሚ ላልሆነ ነገር ይሁንታህን በምትገልጽ ጊዜ ሁሉ ጠቃሚ ለሆነ ነገር እምቢተኛ ትሆናለህ፡፡ ‹‹እሺ›› ብቻ ከአፋቸው የሚወጣ ሰዎች ታላቅ የሆነ ነገር ሊፈጽሙ አይችሉም፡፡ ‹‹እምቢ!›› ማለት ታላቅ እሴት ነው፡፡

ለሀሜተኛ ሰው ፊት አትስጥ፡፡ በሥራ ቦታ አሉታዊ መንፈስና ጨለምተኛነት እንዲሰፍን ከሚፈልግ ባልደረባ ጋር አትወዳጅ። በሕልሞችህ ከሚሳላቅና ራስህን እንድትጠራጠር ከሚያደርግህ ዘመድህ ራቅ፡፡ የሥራ ጊዜህን ከሚያጣብቡ የማህበራዊ ሕይወት ግዴታዎች ተቆጠብ፡፡

ለሁሉም ሰው ሁሉንም ነገር ልትሆን አትችልም፡፡ ከእኛ መካከል ምርጥ የሆኑት ይህን ያውቁታል፡፡ ለምን ቅድሚያ መስጠት እንዳለብህ እወቅ፡።ግቦችህን እወቅ፡፡ ሕይወትህን በአግባቡ ለመምራት በመጪዎቹ ሳምንታት፣ ወራትና ዓመታት ምን ማድረግ እንደሚኖርብህ በሚገባ እወቅ፡፡ ከዚያ ውጭ ለሆነው ለተቀረው ነገር ሁሉ ‹‹እምቢ!» በል። እርግጥ ነው በእምቢተኛነትህ በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ቅሬታ ሊሰማቸው ይችላል። ነገር ግን ሕይወትህን ለመምራት የምትርጠው ለሌሎች ፈቃድ ተገዢ ሆነህ ነውን ወይስ የራስህን እውነትና ሕልም ተከትለህ?

✍️ሮቢን ሻርማ

Join: @astemarimetatf

አስተማሪ መጣጥፍ📚📚

18 Feb, 04:09


ውሃ በተሞላ ድስት ውስጥ አንዲት እንቁራሪት ብንጨምርና ከዚያም ውሃውን ማፍላት ብንጀምር ፤ ውሃው እየፈላ በሄደ ቁጥር እንቁራሪቷም የሰውነት ሙቀቷን ማስተካከል ትጀምራለች ፡፡

☞ የውሃው ሙቀት ከፍተኛ እየሆነ ሲሄድ እሷም የሰውነቷን ሙቀት በዛው ልክ ማስተካከሉን ትቀጥላለች ፡፡ የውሃው ሙቀት ጨምሮ የመፍላት ነጥብ (boiling point) ላይ ሲደርስ ግን ማስተካከል የማትችልበት ደረጃ ስለደረሰ እሯሷን ለማዳን ከድስቱ ዘላ ለመውጣት ትፈልጋለች ትሞክራለች ፤ ግን ዘላ መውጣት አቅም አይኖራትም አትችልም ፡፡ ምክንያቱም ያላትን አቅም ሁሉ ሙቀቷን በማስተካከል የውሃውን ቃጠሎ ለመከላከልና ለመላመድ ባደረገችው ተጋድሎ ጨርሳዋለችና ፤ ወዲያው ትሞታለች ፡፡

እንቁራሪቷን ምን ገደላት ? አብዛኞቻቸችን የፈላ ውሃ እንል ይሆናል ፤ እውነታው ግን ይህ አይደለም ፡፡ እንቁራሪቷን የገደላት የፈላው ውሃ ሳይሆን መች መዝለል እንዳለባት የመወሰን አቅም ማጣቷ ነው ፡፡

አብዛኞቻችን ከሰዎችም ይሁን ከነገሮች ጋር ያለንን ነገር ለማስተካከልና ለመላመድ እንሞክር ይሆናል ፤ ግን እስከ መቼ ማስተካከል እንዳለብንና መች መወሰን እንዳለብን ማወቅ ይሳነናል ፡፡ አንዳንዴ ነገሮችን የለመድናቸውና ለኛ የማይጎዱ መስለው ይታዩናል ፤ በመጨረሻው ቅፅበት ግን እንዳልለመድናቸው ቢገባንም ማምለጥና መውጣት የማይቻለን ሰአት ይሆናል ፡፡ በጥፋት/ወንጀል/ መንገድ ውስጥም ስንሆን እንዲሁ ነው ፤ ትንሹን ወንጀል እንለምደዋለን የሚጎዳን አይመስለንም፤ ደስታ ውስጥ ያለን ይመስለናል ፤ ደስታው ሙቀት ይፈጥርልናል፡፡ ሙቀቱ ወደ እሳት የተቀየረ ጊዜ ግን ??

ከሙቀቱ መውጣት ካልቻልን ከእሳት እንደማንወጣ እውን ነው!
ሙሉ አቅም ባለን ጊዜ እንዝለል!!!

#ሼር አድርጉ

Join: @astemarimetatf