ስነ-ፅሁፍ @amharicfiction Channel on Telegram

ስነ-ፅሁፍ

@amharicfiction


"በእዉቀት መንገድ ላይ መታገስ ያልቻለ እድሜ ልኩን በመሀይምነት ይኖራል"
@Alfatih121

ስነ-ፅሁፍ (Amharic)

የስነ-ፅሁፍ ታሪክ ቤት በአማርኛ በጣም መጣልንት። ይህ ታሪክ ቤት በኮንትክሽል እስከዚህ ጊዜ ተገኝታ መጣልንት። ይህ ታሪክ ቤት በዓለሜ እና በዝናብ መጣልንት። ከሰማይ በአንደኛው ምንጭ እስከዚህ ጊዜ ተገኝታ መጣልንት። ስነ-ፅሁፍ ታሪክ ቤት ከሚከተለው እምነት ጋር በደንብ ምሳሌ መጣልንት። ትኩሳት በሙሉ አና በአማራ ትኩሳት ነው አልፒክስ ጥረት እና ሐምታቸውን እንማኤላቯያና መፅሃፍ እና የክርስቲያን ቅዱስ ናቸው። በሥርዓተ እና በሰይፈ ምስል መጣልንት።

ስነ-ፅሁፍ

30 Aug, 19:59


«ገነትን ግባ» ተባለ፡፡ (እርሱም) አለ፡- «ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ፡፡ ● ጌታዬ ለእኔ ምሕረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መኾኑን፡፡»
ነግቶ ለእናቱ ለሰሚራና ለአህመድ እስከማሳውቃቸው ጨነቀኝ። ኪፋያዬን አቀፍኩ። ተመልሼ ወደ እንቅልፍ ሰመመን ጠለቅኩ። ሰሚርን ሲል ሰማሁት! «የባሪያዎቹን ፀፀት ተቀባይ የሆነው ጌታ ምስጋና ይገባው።»

ተፈፀመ።
.
.
.
https://t.me/amharicfiction

ስነ-ፅሁፍ

30 Aug, 19:59


በብዛት የህፃናት መዝሙሮች

ናቸው። እንደወለደች ጠርጥሬ ነበር። የፈረደባት እህቷ ጋር በዚያራ ሰበብ ደወልኩ። እንደለመደባት ሳልጠይቃት መለሰችልኝ። ወልዳለች። ኑሮዋም ዱባይ ሆኗል።
ዛሬ ከስራ መልስ ወደ ቤት ስገባ ቤቴ ውስጥ የቲላዋ ድምፅ እየተስተጋባ ነው። ወደ ፎቅ ስወጣ ድምፁ የሴት መሆኑን ለየሁ። መኝታ ቤቴን ከኪፋያ ውጪ ማንም ስለማይረግጠው እሷ እንደሆነች ገባኝ። አፏ በጣም ይጣፍጣል። ስገባ ቁምሳጥኑ ፊት ቆማ ልብሶቼን እያስተካከለች በቃሏ ትቀራለች። የምትቀራውን ምዕራፍ በጣም እወደዋለሁ። የዩሱፍ ምዕራፍ ነበር። በሩ ጋር ስደርስ ቀጣዩን የቁርዓን አንቀፅ አነበበች።
«وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
ነፍሴንም (ከስሕተት) አላጠራም፡፡ ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» (አለ)፡፡»
«ድገሚው ....»
«ደገመችው!»
አቀራሯ ልብን ይሰረስራል። አልጋው ላይ ተቀምጬ ማልቀስ ጀመርኩ። እያለቀስኩ መሆኑን ስታይ ዝም አለች። እንድትቀጥል ጠየቅኳት። እየቀራች አቅፋ ታባብለኝ ጀመር። የተቀባችው ሽቶ ጠረኑ ደስ ይላል። አቀራሯን መሳም ፈልጌ ይሁን ባላውቅም ከንፈሯን በከንፈሬ ከደንኩት። ፊቷ ቀላ። ዝም አለች። ደነገጥኩ።
«ሀፊዝ ነሽ እንዴ?»
«ሲያስተዋውቁን ነግረውህ ነበር።»
«አልሰማኋቸውም።»
«ጠዋት ጠዋት የት እንደምታደርሰኝስ ታውቃለህ?»
«አላውቅም!»
«ለምን ቸልተኛ መሆንን መረጥክ?»
«ተሰብሬ ይሆን?»
«የበለጠ መሰበር ትፈልጋለህ?»
«አልፈልግም?»
«እኔ አዝኜብህ ድንገት ብሞትስ?»
«አዝነሽብኛል?»
«ባሌ እንድትሆን እንጂ የተጋባነው እንደ አባቴ ለመንከባከብ ከሆነማ አባት እኮ አለኝ።»
«ምን ላድርግልሽ?»
«ፈገግ በልልኝ! እንደድሮው ተጫዋች ሁን!»
«ድሮ ታውቂኛለሽ?»
«ባባ ከጋሼ ጋር ጓደኛ አይደል። አዎ! ሳታገባ በፊት ቤታችሁ እመጣ ነበር!»
«ይሆናል።»
«ያኔ በጣም ተጫዋች ነበርክ። ደስ ትለኝ ነበር።»
«ይገርማል።»
«ስታገባ አልቅሼ ነበር። ልጅ ነበርኩ ያኔ .... 19 ዓመት ቢሆነኝ ነው።»
«ለምን?»
«ደስ ትለኝ ነበር!»
«የምርሽን ነው?»
«አዎ አሁን ደግሞ በጣም እወድሀለሁ።» ሳመችኝ። 500 ዋት ትራንስፎርመር መያዝ በሉት። ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ።
«ጠዋት ጠዋት የት ነው የማደርስሽ?»
«መድረሳ ነው። ሂፍዝ አስቀራለሁ።»
አዛን አለ። ግንባሬን ስማኝ ተነሳች። መስጂድ ሄድኩ። ቤት እስክመለስ ድረስ ናፈቀኝ። ሳትደሰትብኝ የምትሞት መስሎኝ ፈራሁ። አዲስ ስሜት ነው። ከኢሻ በኋላ አበባ እና ብዙ ቸኮሌት ገዝቼ ገባሁ። እንደሁልጊዜው ቤቱን ድምቅ አድርጋ እየጠበቀችኝ ነበር። ስገባ እጄ ላይ የነበረውን አይታ ማልቀስ ጀመረች።
«ምን ሆንሽ?»
«ወላሂ አውቅ ነበር!»
«ምኑን?»
«አላህ ልብህን ወደኔ እንደሚያዘነብልልኝ! ኪፋያህ እንደምሆን!»
«ትዕግስትሽ ግን ይገርማል።»
«ዱዓ የማይቀይረው ነገር እንደሌለ ስለማውቅ!»
«ከፈይተኒ ኪፋያቲ!»
አበባውን ተቀበለችኝና ወደ መኝታ ቤት ገባች። ቴሌቭዥኑን ከፈትኩት። ዩትዩብ ከፈትኩ። አይኔን ወደ መኝታ ቤቱ ስመልስ ልቤ ትርክክ አለ። ኪፋያ! ሰውነቷ ብርሀን ይረጫል። ታፋዋ ላይ የቀረ የመኝታ ልብስ ለብሳ ወደኔ ተጠጋች። ከቴሌቭዥኑ የፈሪሀን ኢሜይል ዘግቼ ወጣሁ። ድጋሚ ስለሷ ላልከታተል Sign out አልኩት። ታፋዬ ላይ ተቀመጠች።
«አላህ ምን እንደሚል ታውቃለህ?»
«ምን ይላል?»
ውቡ ድምጿ መስረቅረቅ ጀመረ።
«وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡»
«እናስ?»
«እናማ እርካብኝ .... የአላህን አስደናቂ ተዓምር አስተንትንብኝ። ሀላልህ አይደለሁ።» ሳመችኝ።
ከአፌ ዚክር ወጣ።
«بِسْمِ اللَّـهِ، اللَّهُمَّ جَنِّـبْنَا الشَّيْطَانَ، وَجَنِّبِ الشَّيْطَانَ مَا رَزَقْتَنَا
በአላህ ስም፣ አሏህ ሆይ ሸይጧንን ከልለን፤ የምትለግሰንንም ከሸይጧን ከልልን።»
ከዚህ በኋላ የሆነውን መናገሩ የላጤን ሆድ ያስብሳል። ባለትዳርን ላልታቀደ ልጅ ያነሳሳል። መች ወደ መኝታ ክፍል እንደገባን አላውቅም። ጀለቢያ ከሱሪ አንፃር በቀላሉ እንደሚወልቅ ገብቶኛል። የሆነው ሆነ። እቅፍ አድርጌያት አሸለብኩ።
ለሊት ላይ በላብ እንደተጠመቅኩ ድንገት «አላህ! አላህ!» እያልኩ ከእንቅልፌ ባነንኩ። ኪፋያ አቅፋኝ መቅራት ጀመረች።
እንደተረጋጋሁ አቀፍኳት።
«ምን ሆንክ?» አለችኝ።
«ሰሚሬን አየሁት።»
«ማሻአላህ። በመልካም አየኸው?»
«በሁላችንም ምኞት ላይ!»
«ንገረኛ!»
«ጀነት ውስጥ አየሁት።»
«አላሁአክበር! ምን አለህ?»
«እየደጋገመ እንዲህ ይል ነበር።
بِمَا غَفَرَ لِي رَبِّي وَجَعَلَنِي مِنَ الْمُكْرَمِينَ
ጌታዬ ለእኔ ምሕረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መኾኑን፡፡»
«ያ ራህማን!» ማልቀስ ጀመረች።
«ሰው የሚያውቅህ በመልካም አይደለም። ጌታህ እንዴት ማረህ አልኩት።»
«እና ምን አለህ?»
«ወደ አላህ ሳልመለስ የተኛሁበት ምሽት .... ከወንጀሌ ለማምለጥ ያላለቀስኩበት ለሊት የለም። ቀን እወነጅለዋለሁ። ማታ አለቅሳለሁ። ሀጢዓትን በሰራሁ ጊዜ መልካም ነገርን አስከትላለሁ። ድብቅ ሰደቃን አበዛለሁ። ለሙስሊም ወንድም እህቶቼ የተቻለኝን መልካም አደርጋለሁ። የአልቃሾችን እንባ አብሳለሁ። ደካሞችን እከላከላለሁ። አላህ ፀፀቴን ወደደው። እዝነቱ የሰፋው ጌታዬ ማረኝ። አለኝ።»
ኪፋያ መንሰቅሰቅ ጀመረች።
«ዛሬ ደስታዬ ነው .... ምን ያስለቅስሻል?»
«ፉአዴ .... ሰሚር እያነበበው ከነበረው የቁርዓን አያ በፊት ያለውን አንቀፅ ታውቀዋለህ?»
«ምንድነው?» እያለቀሰች መቅራት ጀመረች።
«قِيلَ ادْخُلِ الْجَنَّةَ ۖ قَالَ يَا لَيْتَ قَوْمِي يَعْلَمُونَ
«ገነትን ግባ» ተባለ፡፡ (እርሱም) አለ፡- «ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ፡፡»
ማልቀስ ጀመርኩ። ሰሚሬም ጀነት መግባቱን ዱንያ ያለነው እንድናውቅ ፈለገ። በዱንያ እያለ የጀሀነም ነው ብለው የተጠቋቆሙበት እጆች መሳሳታቸውን እንዲረዱ ተመኘ። ጌታውም አደረገለት። የጌታውን ምህረት ተጎናፅፎ ጀነት ገባ። ጀነት መግባቱንም አወቅን። «እስኪ አንቀፆቹን እየደጋገምሽ አንብቢልኝ።» አልኳት። እየደጋገመች ማንበብ ጀመረች።
«قِيلَ ادْخُلِ الْجَنَّةَ ۖ قَالَ يَا لَيْتَ قَوْمِي يَعْلَمُونَ● بِمَا غَفَرَ لِي رَبِّي وَجَعَلَنِي مِنَ الْمُكْرَمِينَ

ስነ-ፅሁፍ

30 Aug, 19:59


Fuad Muna (Fuya):
የልብ ነገር
ክፍል ሀያአምስት
(ፉአድ ሙና)
***

ይኼ ክፉ
ከሀጢዓት ሀጢዓት፣ የምናውቀው ሰው፣
የፈረድንበት
ጀሀነም እንኳን፣ በጣሙን ሲያንሰው፣

ይሀ ሚስኪን ሰው
ለእናቱ ልጅ፣ ለወዳጅ ጋሻ፣
መቼ ታውቂና
አላህ በእሱ ላይ፣ ምንድን እንደሻ።

መጀን ጌታዬ!

***
ዛሬ ከሰሚር ሞት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከማላውቃት ሴት ፊት ልቀመጥ ነው። ፈጣኑ ፉአድ .... ጨዋታ አዋቂው እኔ .... እንደ ቀድሞ የመዋዕለ ህፃናት ተማሪ በቤተሰቦቼ ተይዤ ወደ ቀጠሮው ቦታ እየሄድኩ ነው። የልብ መሰበር ምላስን ጣዕም ያሳጣል። ከንፈርን ፈገግታ ያስረሳል። ፊትን ጋግርታም ያደርጋል። ሰው እንዴት መሳቅ ተራራ ይሆንበታል። መኖር ውሀ ውሀ ብሎኛል። ራስን ማጥፋት ይሉት ውርደት ውስጥ ራሴን አልጥል ነገር ጌታዬ ከዱኒያ ወደ ጀሀነም ማምለጥ መትረፍ እንዳልሆነ አስተምሮኛል። አሁን ካለሁበት ህይወት የምወደው ወደ ጀመዓ ሰላት መመለሴን እና አዘውትሬ ቁርዓን ማንበቤን ብቻ ነው። ወደ አላህ የሚመልሱን ስብራቶች የእዝነት ደውሎች ናቸው። ብዙ ጊዜ የሰሚር ጉዳይ ሰላም ይነሳኛል። ክፍለሀገር ላይ ለአንድ ቀበሌ ውሀ የሚያስጠቅም ጥልቅ የከርሰ ምድር ውሀ በስሙ አውጥቼያለሁ። ለጓደኛ የሚደረገው ይህ ይመስለኛል። በየወሩ በስሙ ሰደቃ እንዳወጣሁ ነው። አንዳንዴ ብቻዬን ስሆን ሰሚር እንዴት በሞቱ አፋፍ ሸሀዳ ገራለት ብዬ እገረማለሁ። እኔም ሆንኩ አህመድ የምናውቀው በሴት አውልነቱ ነው። አላህ ምኑን ወደደለት? በእርግጥ በሰላቱ አይደራደርም። እኔም ወደ ጀመዓ ሰላት እንድመለስ ብዙ ያገዘኝ ሰሚር ነው። ግን የሴት አውልነቱን ያህል ያላወቅነው የአላህን ውዴታ ያሰጠው ስራ እንዳለ ሁሌም ይሰማኛል። ነገሩ ሞት ሆነ እንጂ ደብዳቤ ልከን በጠየቅነው ነበር። ሰሚር ሸሀዳ ብሎ ባይሞት ሰው የምሆን አይመስለኝም። መፅናኛዬ ሸሀዳ ብሎ መሞቱ ነው። የአላህ ጥሪ ሲመጣ መቅረት የሚባል ነገር የለም። ሰሚር እኔ ቤት አምሽቶ በእግሩ ሄዶ አያውቅም። ሁሌም እንዳደረስኩት ነበር። የአላህ ውሳኔ መጣና ቤትህ ልደር እያለኝ ላለማስቸገር ብዬ እምቢ አልኩት። ልሸኝህ ስለው እምቢ አለ። አላህ የፈለገ ቀን እንዲህ ነው። በነብዩሏሂ ሱለይማን (ዐሰ) ጊዜ የሞት መልዓክ ወደ ሱለይማን (ዐሰ) ለሰላምታ በሰው ተመስሎ ጎራ አለ። ተቀምጦ አንድ ሰውን በግርምት ይመለከተዋል። ትንሽ ቆይቶ ሱለይማንን ተሰናብቶ ወጣ። የሞት መልዓክ አፍጥጦበት የነበረው ግለሰብም «ማነው አሁን የመጣው ሰው? አተኩሮ ሲያየኝ ነበር።» ብሎ ጠየቃቸው። ሱለይማን (ዐሰ) «የሞት መልዓክ ነው።» ሲሉ መለሱለት። ግለሰቡ ተርበተበተ። ሱለይማንን አላህ በሰጣቸው ጥበብ ከዚህ አካባቢ እንዲያርቁት ጠየቃቸው። ሱለይማንም ነፋስን አዘው በሺህ የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን አርቀው ህንድ ላይ አሳረፉት። በቀጣዩ ቀን የሞት መልዓክ ሱለይማን (ዐሰ) ጋር ጎራ አለ። እርሳቸውም «ትናንት አንድ እንግዳዬን አስበረገግክብኝ!» አሉት። የሞት መልዓክም «እኔ ሰውየውን የተመለከትኩት ተገርሜ ነው። አላህ ግለሰቡን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ህንድ ላይ ነብሱን እንድይዝ አዞኝ ነበር። በሰዓቱ አንተ ጋር ሳገኘው ይኼን ሁሉ ርቀት በሰዓት ውስጥ በምን ተጉዞ ህንድ ይደርሳል ብዬ ተገርሜ ነው። ህንድ ስሄድ ግን ቁጭ ብሎ ሲጠባበቀኝ አገኘሁት።» አላቸው። ልክ እንደዚህ ማምለጫ ያልነው ወደ ሞት ውሳኔያችን የምንሄድበት ድልድይ ሊሆን ይችላል። አላህ የወሰነ ጊዜ ውሳኔውን የሚቀይረው የለም።
የህይወት ጣዕም ከጠፋኝ ሁለት ዓመታት አልፈዋል። የስነ–ልቦና ችግር ገጥሞሀል ብለው ስንቱ ሳይካትሪስት ጋር ወሰዱኝ። ንቅንቅ የለም። የሚጠይቁኝን እመልሳለሁ ግን የሚነግሩኝን አልሰማም።

የቀጠሮው ቦታ አንድ ታዋቂ የሙስሊም ሬስቶራንት ነበር። ወደ ሬስቶራንቱ ስገባ ምንጣፍ ላይ ከተቀመጠ አንድ ቤተሰብ ውጪ ማንም የለም። አባቴ ጫጫታ እንደጠላሁ ያውቃል። በስስት እያየኝ «ይኸው እንዳይረብሽህ አዘግተነዋል እሺ!» አለኝ። በእነዚህ የስብራት ጊዜያት ቤተሰቦቼ ከጎኔ አልጠፉም። ሲሳካልን የትም ብንጠፋ፣ በጀሌ ብንከበብ፤ ክንፋችን ሲመታ በቤተሰብ እቅፍ ውስጥ ነን። ወደ ውስጥ እንደገባን ውስጥ የነበረው ቤተሰብ ከተቀመጠበት ተነስቶ ተቀበለን። አባት፣ እናት፣ አጎቶች፣ አክስቶች፣ አስር የሚጠጉ ወጣቶች ..... ስገምት ወንድም፣ እህት እና የአጎት አክስት ልጆች ይሆናሉ። በልቤ ሰርጉ ዛሬ ነው እንዴ? እላለሁ። ለትውውቅ ይኼ ሁሉ ቤተሰብ ምን ይሰራል? ወይስ አባቴ ከተስማማ አይቀር በዚሁ ልዳረው ብሎ ነው። አልፈርድበትም። የምወስናቸው ውሳኔዎች የማይጠበቁ ናቸው። ሀሳቤን ሳልቀይርበት እንደጋለ ብረት እየቀጠቀጠኝ ነው። ትንሽ ስጠጋ የማውቀውን ፊት አየሁ። የልጅቷን አባት አውቃቸዋለሁ። ከአባቴ ጋር ተቃቀፉ .... ተሳሳሙ። ነጭ ጀለቢያ ከባለ ቀይ ነጩ ጥምጣም ጋር ለብሻለሁ። የምወደው ኡስታዝ የለም እንጂ አህመድን መስያለሁ። አባትየውን ሰላም አልኳቸው።
«ማሻ አላህ በጣም አምሮብሀል .... የኔ ልጅ!» አሉኝ። ደረቅ ፈገግታ አሳየኋቸው። ፊት ለፊት ተቀመጥን። ብዙ ነገር አወሩ። እየሰማኋቸው አልነበረም። ሴቶቹ ፊታቸው በሂጃባቸው ተሸፍኗል። አባቴ ልጅቷን እንዳያት ፊቷ እንዲከፈት ለአባቷ ነገረው። እስከዚህ ሰዓት ድረስ ከተቀመጡት ሴቶች መሀል ሙሽራዋ የቷ እንደሆነች አለየሁም። አባቷ ፊቷን እንድትከፍተው ጠየቃት። ጥቁር አባያ በአረንጓዴ ሂጃብ ለብሳለች። አረንጓዴውን ሂጃብ ከፊቷ ላይ አንሸራተተችው። ታምራለች። ግን ልቤ ምንም አልመሰለውም። ለመውለድ እንጂ ለማፍቀር አላገባም። ማፍቀሬን ጨርሻለሁ። ምግብ ቀርቦ ሌሎቹ ከኛ ራቅ ብለው መብላት ጀመሩ። እኔና ልጅቷ አንድ ላይ ማዕድ እንድንቋደስ ተደረገ።
«ኪፋያ እባላለሁ ....»  ፈገግተኛ ነች።
«ፉአድ እባላለሁ .... ፉአድ ሙና!» ፊቴ እንደተቋጠረ ነው።
ልጅቷ የምትጠቀማቸው አወራሮች እኔ ስላለሁበት ሁኔታ በደንብ የተነገራት ትመስላለች። እኔ እስክጠይቃት አትጠብቅም። ታወራለች። ቀለል ብላ ትጫወታለች።
«እጅ እግር አለኝ .... ሌላ ምን ትፈልጋለህ?»
«በእጅ እግር የሚወለድ ከሆነ በቂ ነው።»
ሳቋን ለቀቀችው። ሁሉም ዞረው አዩን። እኔ ፊቴን እንደጣልኩት ነው።
«ዛሬ ለመተያየት አይደል የተገናኘነው .... እንዴት አየኸኝ?»
«በቂ ነው።»
«ጉረኛ!» ዝም አልኳት።
«አንቺ እንዴት አየሽኝ አትለኝም?»
«እሺ ንገሪኝ!»
ጉንጮቿን አየር ሞላቻቸው። ፈገግ አልኩ። በልተን እንደጨረስን አባቶቻችን ተጠግተው ውሳኔያችንን ጠየቁን። እኔ መስማማቴን ገለፅኩ። እሷ ፈገግ ብላ ዝም አለች።

***
አህመድና ሰሚራ እንዲሁ አውፍ ተባብለዋል። ከዚህ በፊት የነበራትን ህይወት አያውቅም። እንግዲህ ከጌታዋና ከእኔ በቀርም የሚያውቅ የለም። ከሰሚር ሞት በኋላ ራሷን በደንብ አሸንፋለች። እኔም የቀድሞ ቤቴ ታድሶ ከአዲስ ሚስት እና ማንነት ጋር ተመልሼያለሁ። ኮስታራ እና ጨዋታ የማያውቅ ፉአድ ሆኛለሁ። ካገባሁ ወደ ሶስት ወራት ከግማሽ ተቆጥረዋል። ሚስትየዋ ቻይ ናት። መስጂድ ሄጄ እመለሳለሁ። ለምትጠይቀኝ ጥያቄ መልስ እሰጣለሁ። አላናግራትም። እስካሁን ድረስ ጫፏን አልነካኋትም። መኪና መንዳት አትችልም። መንጃፈቃድ እየተማረች ነው። ተምራ እስክትጨርስ መሄድ የምትፈልግበት ቦታ ሲኖር ትደውላለች። አደርሳታለሁ። በቻልኩት መጠን እንዳልበድላት እጠነቀቃለሁ። እንደቀድሞው አንሶላ መጋፈፍን ግን ልቤ እሺ ሊለኝ አልቻለም። በየምሽቱ ከመስጂድ ስመለስ ቴሌቭዥኑን ከፍቼ ፈሪሀ የምታያቸውን ቪዲዮዎች እከታተላለሁ። አሁን አሁን

ስነ-ፅሁፍ

29 Aug, 10:38


የማያስቀው ፉአድ! ብቸኝነት

የሚወድ ፉአድ! ከአህመድ ውጪ የማገኘው ወዳጅ የለም። መስጂድ እሄዳለሁ። ሰግጄ ለሰሚር ዱዓ አደርጋለሁ። ለሰሚር ዱዓ ሳላደርግ የመሸ ቀን አላስታውስም። ሰሚር የተገደለበትን ደጃፍ መርገጥ ቀፎኛል። ቤቴን አከራይቼ ሌላ ቤት ተከራይቼ እየኖርኩ ነው። ምሳ ለመብላት ወደ አህመድ ቤት ነዳን።
«ፉዬ .... » ሰሚራ ልጇን አቅፋ በፈገግታ ተቀበለችኝ።
«ማሻአላህ ሀሩኔ እያደገ ነው።» አህመድ ልጁን በሚወደው ኡስታዝ ስም ሰይሞታል።
«አልሀምዱሊላህ!» አህመድ ልጁን ተቀብሎ ወደ ላይ እየወረወረ ያጫውተዋል።
ምሳ በልተን እንደተቀመጥን የፈረደበት ጭቅጭቅ ተጀመረ።
«ፉዬ በአላህ ለምንድነው የማታገባው?» የሰሚራ የሁልጊዜ ንዝንዝ ነው።
«ከዚህ በኋላ ሴት?»
«ምን ችግር አለው?»
«ደከመኝ! ሰለቸኝ!»
«ልጅ ስትወልድ እኮ አዲስ ህይወት ነው። የህመምህ ማስታገሻ ይሆንሀል።»
ሁሌም ባለመስማማት ተስማምተን እንለያያለን። ሴት የሚባል አስጠልቶኛል። ቤት፣ ስራ፣ መስጂድ፣ ዚያራ ቤተሰብ ጋር፣ ከዚያ አህመድ ጋር፣ ከዚያ ሰሚር ቀብር ጋር .... አንድ አይነት ህይወት!

አመሻሹን ወደ ቤት ስገባ አባትና እናቴ ሙሉ ቤተሰቡን ይዘው እኔው ቤት ናቸው። ቤቱ ደምቋል።
«ኧረ ድንገተኛ ወረራ!» ሳቅኩኝ።
አርደው ሰደቃ እያወጡ ነው። ቀድመው የተዘጋጁበት እንደሆነ ገባኝ። የዚህች ወረራ አላማ ምን እንደሆነ አልጠፋኝም። ገብቼ ትንሽ እንደቆየሁ ወሬው ተጀመረ።
አባቴ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመ።
«ፉአዴ የምወድህ ልጄ ነህ። በህይወቴ እንዳንተ ያኮራኝ ልጅ የለም። እኔም እናትህም ወደ ሞት እየተጠጋን ነው። ፍሬህን ማየት እንፈልጋለን። ዛሬ ቤተሰብ የሰበሰብነው አንተን ለመለመን ነው።»
«እኔ የማገባት ሴት የለችም!»
«እኛ አዘጋጅተናል!»
«ማለት?»
«የጥሩ ቤተሰብ ልጅ የሆነች ሴት አዘጋጅተናል። አንተ የምትወዳት አይነት ናት። አግባትና ውለድልን!»
«እሺ!»
«እሺ?» እሺ በማለቴ ተደናግጠዋል።
«አዎ እሺ! ይኼን አይደል የፈለጋችሁት?»
«አዎ! አላህ እሺ ይበልህ!»
ዱዓው ቀለጠ። በልቤ አንዳችም የሴት ፍላጎት የለም። ግን ልጅ ለመውለድ ያህል ዝም ብሎ መኖር አያቅተኝም። እነሱም እንደ ሰሚር ሳያመልጡኝ ባስደስታቸው ይሻላል።
በቀጣዩ ቀን አባቴ ልጅቷን ሊያስተዋውቀኝ ቀጠሮ አስያዘኝ። ሀሳቤን እንዳልቀይርበት የፈራ ይመስላል።

ይቀጥላል!
.
.
.
https://t.me/amharicfiction

ስነ-ፅሁፍ

29 Aug, 10:38


Fuad Muna (Fuya):
የልብ ነገር
ክፍል ሀያአራት
(ፉአድ ሙና)
***

መች ትመጪያለሽ
ማክሰኞ ማክሰኞ፣
የሞትሽስ እንደሁ
ወይ ሞኞ ወይ ሞኞ!

መች ትመጣለህ
አሁን አሁን፣
አንተስ አውቀሀል
ቀኑን ቀኑን!

***
የህይወት ቀጠሮ በኛ እጅ አይደለም። ለሀጢዓት የተቃጠርንበት ሰዓት የእስትንፋሳችን ማብቂያ ሊሆን ይችላል። እናውቃለን ግን እናምፃለን። ለአላህ ቻይነት ምስጋና የተገባ ይሁን። በምድር ላይ ከሚያስደንቁ ነገራት መሀል የሰው ልጅ በአላህ ቁጣ ላይ ያለው ቸልተኝነት ነው። አንድ ክንፉ የተመታ አሞራ ሆነናል። የፍራቻ ክንፋችንን አጥፈን በክጃሎት ክንፋችን ብቻ እየቀዘፍን ነው። የዚህ ውጤቱ ቁልቁል መደፋት መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። አላህ በልቦች መዘንጋት ላይ የግርምት ጥያቄን ይጠይቃል።
«أَفَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَىٰ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا بَيَاتًا وَهُمْ نَائِمُونَ
የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የተኙ ኾነው ቅጣታችን ሌሊት ሊመጣባቸው አይፈሩምን?
أَوَأَمِنَ أَهْلُ الْقُرَىٰ أَن يَأْتِيَهُم بَأْسُنَا ضُحًى وَهُمْ يَلْعَبُونَ
የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የሚጫወቱ ኾነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፋድ ሊመጣባቸው አይፈሩምን?
أَفَأَمِنُوا مَكْرَ اللَّهِ ۚ فَلَا يَأْمَنُ مَكْرَ اللَّهِ إِلَّا الْقَوْمُ الْخَاسِرُونَ
የአላህንም ማዘናጋት አይፈሩምን የአላህንም ማዘናጋት ከከሳሪዎች ሕዝቦች በስተቀር የሚተማመን የለም፡፡»
አዎን ዘንግተናል። አሁንን መኖር ከብዶናል። የአላህ ለሆኑ ጉዳዮች ሁሉ ቀጠሯችን በኋላ እና ነገ ነው። ለአመፅ እና ለዱንያ ሽኩቻ አሁንን ምርጫችን አድርገናል። የጌታህ ውሳኔ በመጣ ቀን ግን የጉልበተኞች ጡንቻ፣ የባለፀጎች ሀብት፣ የእውቀት ባልተቤቶች እውቀት፣ የባለስልጣኖች ስልጣን ወደ ኋላ አይመልሰውም። በባሮቹ ጉዳይ ላይ ከቁጣው እዝነቱ የሚቀድመው ጌታ አላህ ምስጋና የተገባው ይሁን።

መኪናዬ እየከነፈች ነው። የሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ የመኪናዬን ጥሩምባ እያንባረቅኩ ገባሁ። ዘበኛዎቹ መተላለፊያ ላይ የነበረ ተንቀሳቃሽ አልጋ እየገፉ መጡ። ነርሶቹ እየተጯጯሁ ደረሱባቸው። ሰሚርን አልጋው ላይ አስተኝተን ለነርሶቹ አስረከብን። እጆቼ ይንቀጠቀጣሉ። በዚህ ልክ ለደም ቀርቤ አላውቅም። ነርሶቹ ሰሚሬን ወደ ድንገተኛ ክፍል ይዘውት ገቡ። እኛ እንድንከተላቸው አልተፈቀደልንም። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ወደ ቀዶ ህክምና ክፍል ተወሰደ። ወደ ሜዲካል ዳይሬክሩ ቢሮ ሄድኩ። እንባዬን እና የልብሴን በደም መጨማለቅ ሲያይ ደነገጠ።
«አንተ ነህ ሀላፊው?»
«አዎ .... ምን ልታዘዝ?»
«ወንድሜ ብዙ ቦታ ተወግቶ እናንተጋ ይዘነው መጥተናል። የቻላችሁትን አድርጉልን። የገንዘብ ጉዳይ ቅንጣት እንዳያሳስባችሁ።»
«አዎ አሁን ነግረውኝ ነበር። አትጨነቅ የምንችለውን እናደርጋለን። ሙያዊ ግዴታችን ነው።» ቀለል አድርጎ መለሰልኝ።
ገንዘቤ ምንም ሊያደርግልኝ እንዳልቻለ ተሰማኝ። ሁሉም ዶክተሮች ሌላ ስራቸውን ትተው በሰሚር ዙሪያ ቢሰባሰቡ ደስ ይለኝ ነበር። ለዶክተሮቹ ግን ይህ ክስተት እንደኔ በህይወት ዘመን አንድ ጊዜ የሚያጋጥማቸው አይደለም። በየቀኑ የሚያስተናግዱት ጉዳይ ነው። ሰሚር ለእነሱ አንድ በሽተኛ ነው። በየቀኑ በጌታው ውሳኔ ነብሱ የምትያዝ ብዙ ሰው ያገኛሉ። አጀሉ ያልደረሰውን አክመው ያድናሉ። የተጠራውን ቀለል አድርገው ኤክስ አደረገ ይላሉ። ለእኔ እንጂ ለእነሱ የሰሚር መወጋጋት ተራ የሆስፒታል ክስተት ነው። ለሊቱን ሙሉ ከጎረቤቶቼ ጋር ሆስፒታል ፈጠን አደርን። ሲነጋ አህመድ ጋር ደውዬ የሆነውን አሳወቅኩት።
አህመድ «እናቱ እኮ ሲደውሉ ነበር ያደሩት ስልኬ ሳይለንት ነበር!» አለኝ። እንዲያሳውቃቸው ተነጋገርን። ሰላሳ በማይሞሉ ደቂቃዎች ውስጥ አህመድ የሰሚርን ቤተሰቦች ይዞ ደረሰ። ሆስፒታሉ ለቅሶ ቤት መሰለ። እናቱ ማመን አልቻሉም። ልናረጋጋቸው የቻልነውን ያህል ጣርን። የእኔ እና የጎረቤቶቼ ልብስ በደም መጠመቅ ይረብሻል። ሀኪሞቹ ልብስ እንድንቀይር ነገሩን። ጎረቤቶቼን ይዤ ወደ ቤት ተመለስኩ። ቤቴ በር ላይ የሰሚር ደም እንደፈሰሰ ደርቆ አለ። ገብቼ ገላዬን ታጠብኩ። ልብሴን ቀይሬና ሆስፒታል ላሉት የሚሆን ምግብ አሰርቼ መኪናዬ ላይ ካስጫንኩ በኋላ ወደ ሆስፒታል ከነፍኩ። ሰሚር ወደ ICU እንዲገባ ተደርጓል። ሁሉም ወደ ስራቸው እንዲሄዱ አሳምኜ እኔ ብቻ ከእናቱ ጋር ቀረሁ። ሰሚርን ለማየት አልተፈቀደልንም። አህመድ ስራውን አስተካክሎ ወዲያው ተመለሰ። እናቱ ቤት ሄደው እንዲያርፉ ብንለምናቸውም አልተቀበሉንም። እንግዳ መቀበያ ክፍል ቁጭ ብለን እያወጋን ዶክተሩ በአይኑ ሲፈልገኝ አየሁት። እጄን ሳውለበልብለት እንድመጣ ምልክት አሳየኝ። ተከተልኩት። ዶክተሩ እኔን ብቻ ወደ ICU አስገባኝ። ሰሚር በስሱ አይኑ ተከፍቷል። ከአጠገቡ ተቀመጥኩ። ፈገግ ለማለት ሞከረ። እንባዬ መጣ። መናገር እየቸገረው አንደበቱን አላቀቀ።
«ፉዬ ...»
«ወዬ ሰሚሬ»
«አውፍ በለኝ እሺ!»
«ለአላህ ብዬ አውፍ ብያለሁ። አንተም በለኝ።»
«አህሜ አለ?»
«አዎ!» በፊቱ እንድጠራው ነገረኝ።
በተመሳሳይ አውፍ እንዲለው ጠየቀው። ይቅር ተባባሉ። እናቱ እንድትገባ አደረገ። እናቱ ስትገባ የቀረነው እንድንወጣ ነገረን። ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ከእናቱ ጋር አወሩ። ዶክተሩ ለረዥም ሰዓት ሲጠባበቁ የነበሩትን ፖሊሶች ቃል እንዲቀበሉ ፈቀደላቸው። አንድ ሴት ላይ እየደረሰ የነበረን ዘረፋ አስቆማለሁ ብሎ ሳያስበው ከኋላ ባላያቸው ሰዎች መወጋቱን እና ወግተውት ሲሄዱ ወደኔ መደወሉን ተናገረ። የደመነፍሱን ወደ ቤቴ ተንደርድሮ በሬ ላይ ወደቀ። ፖሊሶቹ ብዙ ጥያቄ ጠይቀው አዎ እና አይ እያለ መልሶላቸው ወጡ። የእኔን ቃል ቀድመው ተቀብለዋል። ዶክተሩ ሁላችንም ከወጣን ከአንድ ሰዓት በኋላ መልሶ ጠራኝ። ስገባ ሰሚር ትንሽ ከቅድሙ ደክሟል። ሰሚራ ጋር እንድደውል ነገረኝ። ደወልኩላት። እኛን እንደጠየቀን እሷንም ይቅርታ ጠየቀ። ይቅር ተባባሉ።
በቀጣዩ ቀን ሀኪሙ ለብቻዬ ቢሮው ወስዶ ብዙ ከመከረኝ በኋላ መጨረሻ ላይ «He is not going to make it!» አለ።
«ስትል?»
«የፈጣሪን intervention ባናውቅም ዛሬ ወይም ነገ ኤክስ ያደርጋል!»
«እያወራ አይደል?»
«ሰው ሊሞት ሲል የመናዘዝ ተዓምራዊ የሆነ አቅም አለው።»
የቢሮው በር ተከፈተ። ሌላ ዶክተር ገባ። ዶክተሩን እያየው  «Your patient ኤክስ አድርጓል!» አለ።
ወደ ICU ክፍል ተንደረደርኩ። ሀኪሙ ከኋላ ሲከተለኝ ይሰማኛል። ስገባ አህመድ ከጎኑ ተቀምጦ እንባውን ያፈሳል። ሰሚር አይኖቹ የሚከተሉት ነገር ያለ ይመስል ወደላይ ፈጠዋል። ዶክተሩ አይኖቹን ከደናቸው። ጣቱ ላይ የሸሀዳ ምልክት ይታያል።
«ፉአድ ....» አህሜ እያለቀሰ ተጠጋኝ። ደንዝዣለሁ።
«ሲሞት እኮ ሸሀዳ አለ።»
ተቃቅፈን ተላቀስን።

***

ቀናት የተለየ አቆጣጠር አግኝተዋል። ሰሚር ከመሞቱ በፊት እና በኋላ በሚል ተተክተዋል። ሰሚር ከሞተ ሁለት አመታት አለፉ። ከአህመድ ጋር ኮልፌ የሙስሊም መቃብር ሰሚሬን ለመዘየር ተገኝተናል። የሰሚር ቀብር ቀስ በቀስ እያረጀ ነው። ከቀብሩ ፊት ቆሜ ፈገግታው ትዝ ይለኛል። ቀልዶቹ ይታወሱኛል። ብዙ ጊዜ ሰሚርን ለመዘየር ስመጣ ለአህመድ ሰርግ እሱ መርጦልኝ የለበስኩትን ጀለቢያ እለብሳለሁ። ዱዓ አድርገንለት ትንሽ እየተራመድን ቦታውን ከተመለከትን በኋላ ወደ መኪናችን ተመለስን። ከሰሚር ሞት በኋላ ሌላ ፉአድ ሆኛለሁ። ምንም

ስነ-ፅሁፍ

28 Aug, 06:45


«የሆነ ጊዜ አህሜን ያገባሁት ለፀፀት እንዲረዳኝ ነው ብለሽን ነበራ!»
«አዎ ነበር። ግን አህሜ ከአንደኛ ፎቅ ቀጥታ አስረኛ ፎቅ ማለት ነው። ያለምንም ደረጃ ... ያለምንም ሊፍት! ህይወቴ ማስመሰል ሆነ! እንዳሰብኩት የወንጀል ሸክሜን ማራገፍ አልቻልኩም።»
«እና ሁላችንም የማንፈልገው ህይወት ውስጥ ነን?»
«አዎ የማንፈልገው ግን ማምለጥ ያልቻልነው ህይወት!»
ዛሬ ሰሚራ ይዛት የመጣችዋ ልጅ ፈገግ ስትል አየኋት። ደስ ትላለች። ጠቀስኳት። ወደ መኝታ ክፍል ገባን። አሁን ስለተውበት ባወራሁበት አፍ ሳምኳት። ብዙ ብዙ!

አመሻሹ ሲቃረብ ሰሚራ ጥርሷን ፍቃ ሜካፗን አስተካከለች። ስትቅም የነበረች አትመስልም። እንኳን አህሜ እኔ እንኳን አልጠረጥርም። ለመሄድ እየተነሳች «ቅድም ያልከኝ ትዝ አለህ?»
«የቱ የተውበቱ?»
«አዎ!»
«እሱን ስትጠይቀን መወንጀል ደብሮህ አልደግመውም ብለህ ነበር አይደል?»
«አዎ!»
«ከዚያ መልሰህ ልጅቷን ይዘሀት ገባህ!»
«አዎ!»
«አየህ የልብ ነገር እንዲህ ነው። በሰከንድ ሺህ ጊዜ ይገለባበጣል። ከሁሉም ትልቁ ስህተት የመጀመሪያው ነው። መጀመሪያ ወንጀልን ማወቅ፣ መጀመሪያ ወንጀልን መድፈር፣ መጀመሪያ ወንጀል መጀመር! ከዚያ በኋላ ወንጀል normal ይሆናል። ልብህ አይደነግጥም። ሰውነትህም አይንቀጠቀጥም።»
«ስለዚህ ነገር ግን በጣም ታውቂያለሽ!»
«ራሴን በደንብ ስለምከታተል ነው። የልቤን መገለባበጥ ምናምን!»
«ቸከሷ ከኔ ጋር ትደር?»
«ትቅርብህ አትሆንህም። ቤትህንማ እኛ ሳንኖር በሴት አታስደፍር!» ፊትለፊቷ እንዲህ ስትለኝ ድፍረቷ አስደነቀኝ።
ሰሚሮ «ስማ የጥንት የጠዋቷ ዛሬ ምን የሚል ሙዚቃ እየሰማች ነው?» ብሎ ቲቪውን ከፈተው።
ስክሪኑ ላይ የሰርግ ሙዚቃዎች ተደረደሩ። ተጠንቀቅ የተባልን ወታደሮች መሰልን። ፀጥ ረጭ። ደነገጥኩ ግን ልቤ ደንዝዟል። እንደከዚህ ቀደሙ አላስበረገገኝም። ልቤ በጊዜ ሂደት ተስፋ ቆርጦባት ነበር።
ሁሉንም ሸኘኋቸው። ሰሚር ብቻ ቀረ። እንባ እንባ አለኝ። እንደተፋጠጥን ከምሽቱ 3:00 ሆነ። ሰሚርን ለማድረስ የመኪናዬን ቁልፍ ከመኝታ ቤት ይዤ ተመለስኩ።
«ፉዬ ዛሬ እዚህ ልደር .... ደብሮሀል!»
«አብሽር ሰሚሬ! አብሽር ተነስ!»
«በቃ እዚሁ ሁን እኔ ራሴ እሄዳለሁ።»
«ችግር የለውም ልሸኝህ!»
«አያስፈልግም ዛሬ እኔ እሄዳለሁ። እደውልልሀለሁ ስገባ!»
«አቅፎኝ ወጣ። ከግቢያችን እስኪርቅ የግቢው በር ጋር ቆሜ አየሁት።
ወደቤት ተመልሼ ቀበጧ ነጋዴ ጋር ደወልኩ።
«የቀድሞው የቀድሞው .... »
«ቀውሷ ....»
«ሰምተህ ነዋ!»
«ምኑን?»
«ፌሪ ልታገባ እንደሆነ!»
ሳልጠይቃት የፈለግኩትን መረጃ አረጋገጥኩ።
«አዎ ጥሩ ሰው ነው?»
«አዎ በጣም ጥሩ ሰው ነው።»
«ደስ ይላል።»
«ደበረህ አይደል?»
«ላገባት የምፈልጋት ሴት ሌላ ስታገባ መቼስ .....» መጨረስ ደከመኝ።
«አይዞህ እንግዲህ ፉዬ move ለማድረግ ሞክር!»
ይህቺ move ማድረግ የምትባልን ቃል ማን እንዳደላቸው አላውቅም። ለነገሩ ቡጢና ምክር ለሰጪው ቀላል ነው። ፌሪዬን በጣም እንደምወዳት የተረዳሁት ኢክራም የምትባል ሴት ከትዝታዬ ስትፋቅ ነው። ሳልፈልግም ቢሆን ሰሚር ዘመዷን ስለጠበሰ መረጃዎች ይሰጠኛል። ጥሩ ህይወት እየመራች ነው።
«እሺ አደርጋለሁ ....» ተሰናብቼያት ተንሰቀሰቅኩ።
ስልኬ ላይ ሰሞኑን ደጋግሜ የምሰማውን ሙዚቃ ከፈትኩ። የሙዚቃው እያንዳንዱ ስንኝ ሆድ ያስብሳል።
«ኧረ አስታራቂስ የለም ወይ?
ሀይ የሚለን ሰው፣ ገላጋይ፣
ቀናት አለፉ፣ ተኮራርፈን፣
ምን ነክቷቸው ነው? የሚል አጥተን!»
ቤተሰቦቼ እንኳን ልጅ ይወልድልናል በሚል ተስፋ ከፈሪሀ ጋር እንድንታረቅ ለማድረግ ከመሞከር ተቆጥበዋል። አዲስ ሚስት እያመጡልኝ ሰበብ እየደረደርኩ መመለስ ይዣለሁ። አብነት ሆዴን ማንቦጭቦጩን ቀጠለ።
«አኩርፈሽኝ ስውል፣ ጭር ሲል ቤቱ፣
ደስ አይለኝም፣ ደስ አይለኝም!
ከሰቀቀን ካልዳንኩ፣ ካምናው ከትናንቱ፣
ደስ አይለኝም፣ ደስ አይለኝም!
ዝምታ ሲውጠኝ፣ ምን እንደምል ሳጣ፣
ደስ አይለኝም፣ ደስ አይለኝም!
አንቺን አገኝ ብዬ፣ እኔ ራሴን ሳጣ!
ደስ አይለኝም፣ ደስ አይለኝም!
አፅናንተሽኝ አይዞህ ብለሽ፣
ሆዴን ባዶ አስቀርተሽ፣
እንደገና፣ እንደገና!
ለአንገት የሚከብደው ራስ፣
እንደሌለ አንቺ እያወቅሽ።
እንደገና፣ እንደገና!
ፍቅር የተራበው ልቤን፣
በእቅፎችሽ አስጠልዬ፣
እንደገና፣ እንደገና!
እንደልጅነት ትዝታ፣
እንደ አዲስ በአንቺ በቅዬ፣
እንደገና እንደገና!»
ሰሚር ደወለ። ቤት መግባቱን ሊነግረኝ እንደሆነ ስለገባኝ ዘጋሁበት። በሙዚቃው ተመስጬ አለቅሳለሁ።
«አልቆምም ሸንጎ፣ እኔስ ችዬ፣
አልሄድ ጨክኜ፣ አይ እዳዬ፣
ለማን ልተውሽ፣ ብዬሽ በርቺ፣
ዘመደ ብዙ፣ አይደለሽም አንቺ።
ገላጋይ የለም፣ አስታራቂ፣
አንተም አንቺም ተይ፣ ሚል አዋቂ።
እሳት የሚያበርድ፣ የሚያጠፋ፣
አንድ የልብ ወዳጅ፣ እንዴት ሸምጋይ ይጥፋ!»
ሰሚር በድጋሚ ደወለ። አላነሳሁም። የግቢው በር ሲጋጭ ሰማሁ። ዘበኛው በሩን ከፈተ። የዘበኛው ጩኸት ይሰማኛል። ከቁምሳጥኔ ካዝና ውስጥ መሳሪያዬን አውጥቼ እየተንደረደርኩ ወደ ውጪ ወጣሁ። በሩ ላይ ሰሚር ተዘርሯል። አሁን አብሮኝ ሲስቅ የነበረው ሰሚር በደም ተጠምቋል። ተጠግቼ ተመለከትኩት። የተለያየ ቦታ ላይ ተወጋግቷል። ወደ ቤት ሮጥኩኝ። የመኪናዬን ቁልፍ ይዤ ተመለስኩ። ሰው መሰብሰብ ጀምሯል። መኪናዬ ውስጥ ሰሚርን ጭነን ወደ ሆስፒታል ከነፍን። ከፊቱ ሳቅ የማይጠፋው ሰሚር .... በደም ተጠምቋል። እንባዬ ለጉድ ይንዠቀዠቃል።

ይቀጥላል!
.
.
.
https://t.me/amharicfiction

ስነ-ፅሁፍ

28 Aug, 06:45


Fuad Muna (Fuya):
የልብ ነገር
ክፍል ሀያሶስት
(ፉአድ ሙና)
***

አለ ኧረ አለ
የጥርሱ ፀዳል፣ እስከነሀሴ፣
አይከስምም ከቶ
ለሌላ የኖረ፣ ሚስኪን መነኩሴ።

በነብሱ ስቃይ
በልቡ ቁስል፣ ሰርቶልኝ ሳቄን፣
አብርቶልኛል
የኮሰመነ፣ ጨለማ ቀኔን።

አለ ኧረ አለ!!

***
በህይወታችን ያልተጋበዙ ብዙ ቀጠሮዎች አሉ። በፈጣሪ መዝገብ የተከተቡ ከእኛ እውቀት ግን የራቁ ቀጠሮዎች! የወደፊቱን ባወቅነው መጥፎ የሚባል ባልነካን ነበር። ግን አናውቅም። ስለእያንዳንዷ ትንፋሻችን ማረጋገጫ አልተሰጠንም። ወንጀለኛ የመመለሻውን ቀን አያውቅም። ፃዲቁ የመበላሻውን ጊዜ አይገምትም። መለያየት እና መገናኘት ሁሉ በጊዜ ሰሌዳ የተቀመሩ የአላህ ውሳኔዎች ናቸው። የተውበት ጊዜን አለማወቅ ግን ያማል። መች ነው ወደ አላህ የምንመለሰው? መቼ ነው ካለንበት የወንጀል አረንቋ የምንወጣው? ስለቀጣይዋ ትንፋሽ ማረጋገጫ የሌለን እኛ ነገ ተውበት አደርጋለሁ እንላለን። በቀጣዩ ረመዳን ስንል እናቅዳለን። እቅዳችን ከመድረሱ በፊት አጀል ይሉት ጦረኛ እጅ ከወርች አስሮ ጌትዬው ፊት ቢዶለንስ? አይመስለንም። መሞትን ረስተናል። የምንሞት አንመስልም። ነገ ተውበት አደርጋለሁ ስንል አላህ ተውበት ማድረግን ባይፈቅድልኝስ ብለን አንሰጋም። አላህን ቆሞ ተመልካች አድርገን አስበነዋል። ደስ ሲለን ትተነው ምንሄድ ሲሻን የምንመለስበት ቋሚ አድርገን ዘንግተነዋል። አላህ ይቆጣል። አላህ የመቆጣት ባህሪ አለው። ከደረጃችን ዝቅ ሊያደርገን .... ከተውበት ማግኔት ሊያስተጣጣን ይችላል። ግን አልመሰለንም። እኛም በወንጀላችን ዘውትረናል .... መልዓክቱም ከመፃፍ አልደከሙም። እንደዥዋዥዌም ያደርገናል። አሁን ጌትዬን አሁን ስሜትን ከዛ ጌትዬን ወዲያው ስሜትን ..... ተመሳሳይ የመወዛወዝ ሂደት ውስጥ ያለን አለን። ከፊሎቻችን በራሳችን ላይ ስልጣን አጥተናል። አላህን አናምፅም ብለን ወስነን ግን ደግሞ በስሜታችን አስገዳጅነት እየወደቅን ነው። አይዞን! ለመቆም እንሞክር ደግመን እንደምንወድቅ ብናውቅም እንሞክር ..... እኛ ለመነሳት መሞከር እስካልሰለቸን ድረስ አላህ ጥሎ አይጥለንም። ጉዞ ወደ አላህ .... አሁን ያለምንም ሰበብ! ደግመን ከወደቅን አይዞን ደግመን እንነሳለን!

ሁለታችንም ስልካችንን ደንግጠን እየተመለከትን ነው።
«ስማ እስኪ አንተ አንሳው!»
የአህመድን ጥሪ ምላሽ ሳልሰጥ ተውኩት። ሰሚር ስልኩን አንስቶ ስፒከር ላይ አደረገው።
«ሰሚር ...ዬ!» ድምጿ ገዳይ ነው።
«ወዬ ... »
«ቤት ገባህ?»
«አዎ! አንቺስ?»
«አልገባሁም ‘ባክህ! ምን አስቀይሜህ ነው ግን?»
«ኧረ ምንም!»
«ለምንድነው አልነካሽም የምትለው? ረዥም ጊዜ ሆነን እኮ!» 
«እውነቱን ልንገርሽ?»
«አዎ! ንገረኝ!»
«ስላገባሽ ነው! ጓደኛዬን ስላገባሽ!»
ፀጥ አለች።
«ገባሻ? ግን ለምንድነው ጓደኛዬን ያገባሽው? እናውቃለን እኮ! እህትሽ ስልክ ላይ ፎቶሽን አይተነው ነበር።»
«በቃ ሌላ ጊዜ እናወራለን።» ስልኩን ዘጋችው።
እኔና ሰሚር ዝም እንዳልን መተያየት ጀመርን።
«እስኪ አህመድ ጋር ደውል!»
ደወልኩ። ትንሽ እንደጠራ ተነሳ።
«ወዬ አህሜ!»
«ቅድም እኮ ባንተ ቤት ሳልፍ መኪናህ ስትገባ አይቼያት!»
ሰሚር ይዟት ሲገባ አይቷት እንደሆነ ገባኝ።
«እና እንዴት ጎራ አላልክም?»
«ሰሚራ ቤተሰቦቿ ጋር ስለሆነች ላመጣት እየሄድኩ ነበር። ያው በስልክም ቢሆን ልዘይርህ ብዬ ነው ሀቢቢ!»
«ሽኩረን ሀቢቢ! አመሰግናለሁ።»
ስልኩን ዘግቼ እየተቀመጥኩ በረዥሙ ተነፈስኩ።
«ስማ ሰሚር ይህቺን ልጅ ቅጠራት ምክንያቷን ማወቅ እፈልጋለሁ።»

***

ጊዜ ስለት ነው ይቋረጣል። መልካም ስራ
ጠንካራ ልብስ ነው። በጊዜ ከመቆረጥ ይታደጋል። ጊዜ እየከታተፈኝ ወራት አለፉ። ስለፈሪሀ ለማወቅ ያለኝ እድል ስለምትሰማው ሙዚቃ እና ስለምትሄድባቸው ሀገራት ብቻ ሆነ። ቀበጥ እህቷ ጋር እየደወልኩ የት እንደሆነች እጠይቃታለሁ። የምታውቀውን ትነግረኛለች። ለፌሪዬ በእህቷ በተደጋጋሚ መልዕክት ባስልክም እንዳልሰማ ሆናለች። ኢሜይል በተደጋጋሚ ላኩላት .... በየቀኑ ለመንኳት .... ግን አትመልስም። 
ድባቴ ውስጥ ገባሁ። የማላውቀው እኔን ወለድኩ። የድብርቴ ሁሉ መርሻ ደግሞ ሰሚር ሆነ። ሲለው መስጂድ ይዞኝ ይሄዳል። ቀስ በቀስ ከመስጂድ ስንመለስ ሺሻ ላይ መጣድ ጀመርን። እነሱ ጫት ይቅማሉ። እኔ አይደላኝም። ሺሻ አጭሼ የማላውቀው ልጅ በሰሚር ዊስዋስ ቤቴ ሺሻ አስገባሁ። እንደድሮው ውጪ ውጪ ማለት ትቻለሁ። የኔ ቤት መሰብሰቢያችን ሆኗል። ግማሽ አመት በዚህ መልኩ አለፈ። ተመሳሳይ ፉአድ ..... ተመሳሳይ ሰሚር! ተመሳሳይ ሰሚራ!
ሰሚራ እጇን እየዘረጋች «እስኪ ስጠኝ ሺሻውን!» አለችኝ። ሰጠኋት።
ሰሚራ አሁን የሰሚር ወዳጅ ብቻ አይደለችም። የእኔም ቤተኛ ሆናለች። አህመድ ታማኝ ሚስት እንዳለው እያሰበ በሰላም ይኖራል። አለማወቅ አንዳንዴ ሰላም አለው።
«ስሚ አህመድን ግን እንዲህ በየቀኑ ምን እያልሽው ነው የምትወጪው?»
«ስራ እንደጀመርኩ ነው የሚያውቀው! በጥያቄ አያስጨንቀኝም በጣም ረሀ የሆነ ሰው ነው።»
«አላረገዝሽም?»
«ከማን?» ሳቀች።
«ከማን ይሆናል ከሁለት አንዳቸው ናቸዋ!»
«እኔ አልነካኋትም ሰውዬ!» ሰሚር ራሱን ተከላከለ።
«ከአህሜ ጋር ለአንድ አመት ላለማርገዝ ምናምን ተስማምተናል። ለሁለት አመት እንዲሆን እየወተወትኩት ነው።»
«እሱ ሼኪ አይደል እንዴ?»
«ሴት ስትፈትለው ጥጥ እንጂ ሼይኽ የለማ!» ትስቃለች።
ሰሚራ ከየት እንደምትሰበስባቸው ባላውቅም አንዳንዴ ሴቶች ይዛ ትመጣለች። አብረውን ያጬሳሉ። አንዳንዴም አብረውን ይተኛሉ። ወደ አላህ መመለስ ፈልጌ ነበር። ግን አላህ መንገዱን የዘጋብኝ መሰለኝ።
በህይወቴ የተረዳሁት ራሳችንን በወንጀል በምናሳድፈው ልክ ከእዝነቱ እንደምንገፋ ነው። ተውበት ሲደላን በአንዴ የምናገኘው የመመለሻ ቁልፍ ይመስለኝ ነበር። ወደ አላህ ለመመለስ የአላህ መገጠምን ይሻል። በወንጀል መጥረቢያ ያነካከትነው ጠንካራው እግራችን በተውበት ምንጣፍ ላይ ለመቆም ይጠናዋል። ይውሸለሸላል። ይብረከረካል። በልማዱ ተስቦ ወደ ኋላ ይመለሳል። ወንጀል በሰራሁ ቁጥር ይፀፅተኛል። የሰራሁት ሁሉ ያስጠላኛል። ላልደግመው ለራሴ ቃል እገባለሁ። ግን ደግሞ ጠዋቱኑ እደግመዋለሁ። ማን እንደሚነዳኝ .... ምን እንደሚመራኝ ግራ ገብቶኛል።
«ስሙማ ግን ወንጀል በሰራችሁ ቁጥር normal ናችሁ? አይሸክካችሁም?»
ሁሉም ተያይተው ተሳሳቁ።
ሰሚራ «ሸይኹ ማንነትሽ activate እያደረገ ነው¡» አለች።
«የምሬን ነው መልሱልኝ!»
ሰሚር አየኝና «ብዙ ጊዜ ማታ ማታ አለቅሳለሁ! ከዚያ ጠዋት ማታ በማልቀሴ ራሱ እስቃለሁ።» አለ።
«እኔ በቃ» አለች ሰሚራ «እኔ በቃ ስጠፋባችሁ ሼይኹ ማንነቴ activate ሆነ ማለት ነው። አህሜን እየካደምኩ መኖር አስባለሁ። ድጋሚ ላላገኛችሁ ለራሴ ቃል እገባለሁ።»
«እና ለምን ታገኚናለሽ?»
«አትፍጠና ልነግርህ አይደል! ከዚያ በነጋታው አቅም አጣለሁ። የምናደርገውን አስበዋለሁ። ሰላሳ ጊዜ አመንትቼ ሰሚር ጋር እደውላለሁ። ሰሚርን ሳወራው ፀፀቴ ሁሉ ይበናል። ልቤ እስካገኘው ይጣደፍብኛል።»

ስነ-ፅሁፍ

27 Aug, 17:21


«ፉአድ ሙና ነኝ።»
ጠብ እርግፍ አለችልኝ። እህቷ ነበረች። ተሰናብቼያት ዘጋሁት። ለምን ስልኩን እንደያዘችው እንኳን አልጠየቅኳትም። ወደ ቀበጧ ነጋዴ ደወልኩ። ወደ ታናሽየዋ!
«ድመቴን ገዝተህልኝ እንዳይሆን ..... » ተፍለቀለቀች።
«አዎ ነገ ምናምን ይደርሰኛል። ይዤልሽ እመጣለሁ።»
«እና እንዴት ነህ?»
«አለሁልሽ! ሚስቴ እንዴት ናት?»
«የምናባህ ሚስት ፈተሀት የለ እንዴ? ያልነገረችኝ መስሎህ ነዋ?»
«እሺ የቀድሞ ሚስቴስ?»
«አሁን ልክ ነው! ደህና ናት ከማጂላን ጋር ሳትጋባ አትቀርም!»
«በሀገርኛ ሲተረጎም?»
«ሀገር ለሀገር እየዞረች ነው።»
«ለመዝናናት ነው?»
«ኧረ International expert ሆናልሀለች።»
«ውይ ደስ ይላል በጣም! ስልኳን ስደውል እኮ ትልቋ አነሳችው።»
«አዎ ሰገጤው ነው የያዘው¡» ተሳሳቅን። ለታላቋ የሰጠቻት የኮድ ስም ነው።
«እና አሁን የት ሀገር ናት?»
«ዛሬ ማድሪድ መሰለችኝ .... ትንሽ ቆይቶ ሌላ ሀገር መሄዷ አይቀርም። ወያላ በላት!» ትስቃለች።
«በምንድነው የምትደዋወሉት?»
«ዋትሳፗ ይሰራል ..... በሱ ነው! ናፈቀችህ እንዴ?»
«በጣም! የምር በጣም! እኔ እዚህ መስላኝ ነበር እኮ!»
«የጣልከው ቦታ ማን ቁጭ ይላል ብለህ ነው?»
«ነገረኛ ሆነሻል! የምር ላገባት እፈልጋለሁ!»
«እንደገና .... ፍቅር እንደገና .... እንደገና ....መውደድ እንደገና .... እንደገና ..... አይገኝምና! ሲል አልሰማኸውም ማህሙድን?» አዜመችው!
«አንቺ አትለምኚልኝም?»
«እኔ እወድሀለሁ ፉዬ! ብትጋቡ ደስ ይለኛል። ግን ጀለስ ሳያከር አልቀረም። ይቅርታ ብሎህ ምናምን ገግመህበት አልነበር።»
«ማን ፋዘር ነው?»
«አዎ .... ብቻ እሷ ከፈለገች ግን እንቢ አይላትም። አንተ እሷ ላይ ወጥር! እሷ ከተስማማች ባባን በደካመ ጎኑ መግባት ትችላለህ።»
«ምንድነው ደካማ ጎኑ?»
«ሽማግሌ ሰብስበህ .... ሰንጋ ጭነህ .... ጫት ደግሞ በዛ አድርገህ ይዘህ መምጣት ነው! እና አንድ 20 እሽግ ቸኮሌት!»
«ቸኮሌቱ ላንቺ መሆኑ ነው?» ሳቅኩኝ።
«አዋ ኮሚሽኔ!»
«እሺ በቃ!»
«ሀዬ ይቅናህ!»
ተሰነባበትን። ወደ ዋትሳፕ አካውንቴ ገባሁ። ፌሪ ቦልካኛለች። ደነገጥኩ። ፌሪ እኔን? ለምን አስፈለገ መቦለክ? መልሼ ወደ እህቷ ደወልኩ።
«እሺ ሰውየው!»
«ስሚ ብሎክ አድርጋኛለች።»
«ብሎክሽን አጠጣችሻ¡» ሳቋን ለቀቀችው።
«እስኪ ካንቺ ጋር ያወራነውን ንገሪያት! ደውይልኝ ብሏል በያት።»
«እንዳያሳስብህ ..... ባይሆን ድመቴን ይዘህልኝ ና!»
ተሰነባበትን።

ትናንት እንደፈለጋችሁ ታገኙት የነበረን ሰው .... ከእቅፋችሁ የማይጠፋን ጠረን .... ተለመነኝ ሲላችሁ የነበረን ነብስ .... ከጊዜ በኋላ ማግኘት ሰማይን የመንካት ያህል ሊርቅ ይችላል። አጠገባችን ያሉ ሰዎችን እናክብራቸው .... የሚገባቸውን ክብር እንስጣቸው .... እንንከባከባቸው። አንጉዳቸው! ነገ ከስህተታችን ስንመለስ እንደምናስበው በእጆቻችን ርቀት ልክ ላይኖሩ ይችላሉ። ፌሪ ማለት እኮ የኔ ጌታ የምትለኝ ሴት .... አለቃዬ ብላ ራሷን ያወረደችልኝ ፍቅሬ ነበረች። አንተ ካልክ ይሁን የምትል ውድ ነበረች። ዛሬ ብሎክ? ይገባኛል። ግን ለምን? የምጨቃጨቅ ሰው አልነበርኩም። መፋታት ማለት መጣላት አይደለም ተባብለን ነበር። በእርግጥ ሴቶች የሚሉትና የሚያደርጉት አንድ አይደለም። ተጎድታ ነበር። አሁን ሚስቴ የነበረችውን ሴት ድምጿን እንኳን መስማት አልቻልኩም። ድንገት ቴሌቭዥኑ ትዝ አለኝ። ከፈትኩት። ከዩቲዩብ ላይ ኢሜይል አድራሻዋን ወስጄ ፃፍኩላት። ምንም ምላሽ የለም። ዘግይታ ካየችው ትመልስልኝ ይሆናል ብዬ ተፅናናሁ። ዩትዩቡ በእሷ ኢሜይል አድራሻ ስለሆነ የምትሰማቸውን ሙዚቃዎች ያሳየኛል። ለመጨረሻ ጊዜ የሰማችውን ሙዚቃ ከፈትኩት። ማዲንጎ ነበር። ድሮ ይኼን ሰውዬ ስታዳምጠው ሰምቼ አላውቅም።
«ካምናው ካልተማርኩኝ ተመልሼ፣
እኔም፣ ዛሬም ከደገመኝ፣
እርምን አላውቅ ብዬ፣ እንደገና፣
አዬ ሰው ማመን፣ ካመመኝ፣
አሀ ሞኙ ልቤ፣ አሀ ያልታደለ፣
አሀ ምን ሊፈይድ፣ አሀ ተታለለ?»
ክው ብዬ ቀረሁ! ስለኔ ያስገጠመቻቸው ስንኞች መሰሉኝ። ጆሮዬን ቀስሬ ግጥሙን መስማት ጀመርኩ።
«የካብኩት ተናደ፣ ባለማወቅ፣
ስገነባው ፈርሶ፣
ባፀዳው፣ ቆሸሸ እንደገና፣
የፀዳው ደፍርሶ!
ወርቅ አይደለ ነገር፣ አይጣራ፣
በእሳት አልፈትሸው፣
የቸገረ ነገር፣ ግራ ገባኝ፣
በምን ይለያል ሰው!»
እንባዬ አይኔን ሞላ። ሺህ ጊዜ አፅድታኝ፤ ሺህ ጊዜ ቆሽሼያለሁ።
«ቀድሞ አለመጠንቀቅ፣
ጥንቱን አለመፍራት፣
ኃይለኛ ዱላ ነው ያረፈብኝ፣
ማገገሜን እንጃ፣ ምን ተሻለኝ?»
ከዚህ በላይ መስማት ከበደኝ። ዘጋሁት። የምትሰማቸው ሙዚቃዎች እንኳን እኔ ስለፈጠርኩባት ቁስል መሆናቸው ከፋኝ። እያስታወሰችኝ እንደሆነ ሳስብ ደስም አለኝ። እያነቡ እስክስታ አይነት ስሜት አለው። ሳላስበው እንባዬ ከአይኔ መውረድ ጀመረ። ናፈቀችኝ። ቤቱ ውስጥ ያለው እቃ በሙሉ ከእሷ ጋር ምን ስንሆንበት እንደነበር አፍ አውጥቶ አወራኝ። ብዙ ወጪ የወጣበት እኔና ኢክራም ያዘዝነው አልጋ መጋዘን ተቆልፎበታል።

ከምሽቱ 2:00 ሲል ሰሚር መጣ። ወደ ቤት ሲገባ እንዲጨብጠኝ እጄን ዘረጋሁለት። ፊቱ ላይ ድንጋጤ አለ። ክው ብሏል። እጁን ወደ ኋላ እየደበቀኝ በትከሻው ብቻ ገጨኝ። ጣቶቹ እንደቀፈፉት ገባኝ። ወይኔ ሰሚር!
«ሂድና ሻወር ቤት ታጠበው!» ሳቅኩኝ።
ከሻወር ቤት ጣቶቹን እያሸተተ መጣ።
«አንተ የእጅ መታጠቢያው ሳሙና ጠረኑ በጣም ደስ ይላል።»
«መሪዬን በእሱ እጅህ አልያዝከውማ?»
«አልነካሁትም .... በፎጣ ነው የያዝኩት¡»
ክው ብዬ ቆምኩ!
«ሰሚራ ጋር አልነበር እንዴ የሄድከው?»
«ነበር!»
«እና?»
«አብረን እንሂድ እያልኩህ!»
«ሆነ?»
«አይ የፒያኖ ሰዓት ብቻ!»
«ያምሀል እንዴ? የአህመድ ሚስት እኮ ናት!»
«የደረሰብኝን ዊስዋስ አላየህም!»
«ምንስ ብታደርግህ? ሰሚራን?»
«በፒያኖ ያለፈው ስንት ታግያት ነው። ይኼ እንዳይሆን ነው ና ያልኩህ!»
«ከዚህ በኋላ አጠገቧ እንዳትደርስ!»
«ድረስስ ብትለኝ?»
«አሁን አህመድ ፊት በምን ድፍረት ትቆማለህ?»
«እሱ እኔ ፊት በድፍረት ቆሞ አይደል?»
«ልጅቷ ምንድነው ፍላጎቷ?»
«ሁለት ማንነት ነው ያላት! ጥሩ ሴትነት ሲሰማት አርፋ ከባሏ ጋር ትቀመጣለች። ባለጌው እሷነቷ ሲቀሰቀስ እኔ ጋር ትደውላለች።»
«ሴት ማለፍ አትችልማ?»
«አህመድ ነው እኮ ፋውል የገባው! እኔ አይደለሁም!»
«ብትነግረውስ እሷ?»
«ማገጥኩ ብላ?»
የሁለታችንም ስልክ እኩል ጠራ።
«ማነው?»
«ሰሚራ! አንተስ ጋ ማነው?»
«አህመድ!»
ግራ ተጋብተን ስልካችን ላይ አፈጠጥን!

ይቀጥላል!
.
.
.
.
https://t.me/amharicfiction

ስነ-ፅሁፍ

27 Aug, 17:21


Fuad Muna (Fuya):
የልብ ነገር
ክፍል ሀያሁለት
(ፉአድ ሙና)
***

ሳብ ሳበውና
የገፋኸውን፣ በእሳት በአለንጋ፣
እንደለመድከው
ለሊቱን ሙሉ፣ ስታለቅስ አንጋ!

አልቅስ አልቅሰው
አይወጣለትም፣ የወዳጅ ልቡ፣
አያስኮንንም
የገፋኸውን፣ ዞሮ ማሰቡ።

***
ሁሉም ምዕራፍ መደምደሚያ አለው። ለእነሱ ብለን አላህን ያስቀየምንላቸው ሰዎች ጥለውን ይሄዳሉ። ኢክራም ቤተሰቧን ላለማስቀየም ስትል ተወችኝ። አልተቀየምኳትም። ይኼ የአላህ ሱና ነው። የአላህን አጥር ዘለን የቀነጠስነው እሸት ጊዜ ጠብቆ ያንቀናል። አትተወኝም ብዬ ስተማመንባት የነበረችው ሴት .... ኢክራም እንኳን አልዋጥ አለች። ሚስቴን የተውኩላት እንስት .... እንደቀልድ ቻው አለችኝ። ልቤን በዚህ ልክ እሷ ላይ ማንጠልጠል አልነበረብኝም። የደስታዬን ቁልፍ ጠቅልዬ እጇ ላይ ጥዬው ነበር። ሰው ናትና ደስታዬን ይዛው ሄደች። ተደገፍኳት .... ሸሸችኝ። አሁን ከተራራ ላይ እየተንከባለለ እንዳለ ሰው አይነት ስሜት ይሰማኛል። ምናልባት ጌታዬ በፈሪሀ እጅ ከመሰበር ይታደገኝ ይሆናል። ሲደላን ትዝ የማይለን አላህ .... የመከራችን አዝማች ነው። ጭራሽ አማክረነው ያመፅነው ይመስል «ግን ለምን?» ብለን እናማርረዋለን። ለእሱ ፍቅር በልባችን ውስጥ የተከለለው ቦታ ላይ የፍጡር ፍቅር ሞላንበት። ልባችን ውስጥ ለእሱ የሚሆን ፍቅር ስለጠፋ ስናምፀው ቅንጣት ታህል አልከበደንም። ለወደድነው ሰው ደስታ የጌታችንን ትዕዛዝ ተረማመድንበት። ያለ አንዳች የፍርሀት ስሜት ‘ረጋገጥነው!

የአላህ ፍቅር የሌለበት ልብ እንዴት ደስተኛ ሊሆን ይቻለዋል? ኢብኑልቀይም «ያለምንም ጥርጥር በአለም ላይ ትልቁ የእርካታ ምንጭ አላህን የማወቅና የማፍቀር ደስታ ነው። አላህን ማወቅና ማፍቀር በዚህች አለም ላይ አንድ ሰው ሊያስተናግደው የሚችለው የደስታ ጫፍ ነው። በተቃራኒው ሌላው አለማዊ ነገር የሚሰጠው ደስታ ከባህር ላይ እንደምትወሰድ ጠብታ ያህል ያነሰ ነው። እጅጉን አስደሳች የህይወት ጎን አላህን መውደድ ሲሆን በጀነት ውስጥ ትልቁ የደስታ ጣራ ደግሞ አላህን ማየት ነው።» ይላሉ። በእርግጥ በወንጀል የሚሸመትን ደስታ ፀፀት ይከተለዋል። በሰዓቱ አስደሳች ቢመስልም ካለፈ በኋላ ለዘላቂ ቁጭት ይሰጣል። ሲልም እንደኔ ቤተሰብ ያስበትናል። ከሚወዷት ሚስት ያፋታል። አላህም በእርሱ ፍቅር ላይ ማጋራትን አስመልክቶ እንዲህ ይላል።
«وَمِنَ النَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ اللَّهِ أَندَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ اللَّهِ ۖ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ ۗ
ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡»
ለአላህ የምንፈጥራቸው ባላንጣዎች የተጠረቡ ሀውልቶች ብቻ አይደሉም። በአላህ መሻት እና በነብሳችን መውደድ መሀል ያስበለጥናቸው የስሜት ጣዖቶቻችን ናቸው። ልማዳችንን ጣዖታችን አድርገን ቀርፀናል። በስሜታችን እየተሸነፍን የአላህን ፍቅር ገፍተን ለወንጀል ጣዖታችን ሰግደናል። አሰጋገዱ ግንባር መድፋት አይደለም። የአላህን ክልከላ መጣስ ነው። የምር ባመንን ግን ከስሜታችን የጌታችን ፍቅር በቀደመብን .... ዝሙትን ያህል ወንጀል ላይ ከመውደቅ አላህን ያስቆጣዋል ብለን በተሰበሰብን .... ነበር። አላህን አላፈቀርነውም። የደህንነት ካሜራ አይነት ቦታ የሰጠነው ይመስላል። የሚያይ ግን የማይቆጣ አድርገን ተረድተነዋል። ከአላህ ፍቅር ጎድለን ነብስ የሌለው ተንቀሳቃሽ በድን ሆነናል።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ። «ሶስት መልካም ባህሪዎች አሉ። እነሱን የተላበሰ የኢማንን ጥፍጥና ያገኛል። እነሱም አላህና መልዕክተኛውን ከእነርሱ ውጪ ካሉ ነገሮች ሁሉ አብልጦ መውደድ፣ ሰውን ለአላህ ብቻ ብሎ መውደድ፣ አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ከመራው በኋላ ወደ ክህደት መመለስን እሳት ላይ መወርወርን ከሚጠላው በላይ መጥላት ናቸው።» አላህን ስለመውደድ ሲነሳ አራተኛዋ ሴት ሳትነሳ አታልፍም። ራቢዓተል አደዊያ .... የኢራቋ እንስት .... የበስራዋ ፍሬ .... የቤተሰቦቿ አራተኛ ልጅ .... የቲሟ ህፃን .... ባርያዋ ወልይ .... መንፈሳዊዋ ሴት .... አፍቃሪዋ! በሂጅራ አቆጣጠር አንድ መቶ ላይ ተወለደች። የአስር አመት ህፃን ሆና እናት እና አባቷን ወደ ቀጣዩ አለም ሸኘች። በባሪያነቷም በጨዋነቷም ጊዜ የጌታዋ አፍቃሪ ነበረች። በአንድ ወቅት «አላህን ትወጂዋለሽ?» ተብላ ተጠየቀች። «አዎን እንዴታ!» ስትል መለሰች። «ይህ ማለት ሰይጣንን ትጠይዋለሽ ማለት ነው?» ጠያቂዎቹ ቀጠሉ። ራቢያም «ለአላህ ያለኝ ፍቅር ሸይጧንን የመጥላት ድርጊት ውስጥ ከመሳተፍ ይከለክለኛል።» ስትል መለሰች። የራሷ የሆኑ በርካታ ጥበባዊ የአምልኮ ስንኞች ተመዝግበውላታል። ከእርሱ ውስጥ ቀዳሚው «ጌታዬ ሆይ! አንተን የምገዛህ የጀሀነም እሳትን ፍራቻ እንደሁ .... በጀሀነም ለብልበኝ። አምልኮዬ ጀነትህን በመከጀል እንደሆን ከጀነትህ አቅበኝ። ግን አንተን የምገዛህ ስላንተ ብቻ ብዬ ከሆነ ዘላለማዊ ውበትህን አትከልክለኝ።» ይል ነበር።

ቀበጧ ሴት .... ውቧ ንግስት .... ባለሂጃቧ ፍቅሬ ..... ቻው አለችኝ። ቻው! ከሰሚር ጋር ከአዳራሹ እንደወጣን ወደ ፈሪሀ ደወልኩ። አልተነሳም። ብትኮራብኝም ሲያንሰኝ ነው። ለፈፀምኩባት ክህደት አስራ ብትገርፈኝ አይበዛብኝም። ወደ መኪናችን ተመለስን።
«ስማ ፉዬ!»
ወደሱ ዞርኩ።
«ዛሬ ከሰሚራ ጋር ቀጠሮ ነበረን።»
«ማናት ያቺ?» ወደ መኪናችን አንዲት የሰርገኛ ልብስ የለበሰች እንስት እጇን እያወዛወዘች እየመጣች ነበር። ዞር ብሎ አያት።
«የሪዞርቱ ፍሬ ናት!»
ከመኪናው ወርዶ አወራት። ወይ ሰሚር! ወደ መኪናው እየተመለሰ «የኢክራም ዘመድ እኮ ናት!» አለኝ።
«ምንድነው የምትልህ?»
«አመሰግናለሁ ነዋ!»
«ለምኑ?»
«አንተን ይዤህ ስለመጣሁ?»
«እኔ አይደለሁ እንዴ ይዤህ የመጣሁት?»
«እሱ አንተን የመሰለህ ነው። ኢክራም እንዳትቀር የማድረግ ሀላፊነቱን ለእኔ ሰጥታኝ ነበር። በነገራችን ላይ ይህቺን ቃጭል እየደወልኳት ነው።»
«አንተ የማትደውለው አለ እንዴ .... ተንከሲስ!»
«በቃ አሁን ፈሪሀን መልሰህ አግባት!»
«ከሰሚራ ጋር ቀጠሮ .... እያልከኝ ነበር።»
«አዎ አብረን እንሂድ ልልህ ነበር?»
«ለምን?»
«በቃ ዛሬ ለምን አህመድን እንዳገባችው እንጠይቃት!»
«አስፈላጊ ነው?»
«አዎ በቃ ይለይለት!»
«ዛሬ ደክሞኛል። ወይ አንተ ጠይቃትና ትነግረኛለህ።» ቤት ገብቼ ፈሪሀን እስካወራት ቸኩያለሁ። ቤት እንደደረስን መኪናዬን ይዞ ወጣ።
ልብሴን አወላልቄ ፈሪሀ ጋር መቀጥቀጥ ጀመርኩ። ስልኩ ተነሳ።
«ፌሪ ....»
«ማነህ?» የሌላ ሴት ድምፅ ነበር።
«ፌሪ የለችም?»
«ውይ የለችም። ስልኳን እኔ ነኝ የምይዘው!»
«አንቺ ማነሽ?»
«ደውለህ ማነሽ?»
«የሰው ስልክ ነው የያዝሽው .... ለዚያ ነው።»
«አንተ ማነህ?»

ስነ-ፅሁፍ

24 Aug, 19:03


ምንድነው የተፈጠረው? ወይኔ ድንጋጤዬ! ሀዘን ሲከብድ እንዲህ ነው። የተባለ ያልተባለውን እየደባለቀ ልብን ሰላም ይነሳል። የፌሪ ታናሽ እህት ናት። ቀበጧ ነጋዴ! የቤታቸው ታናሽ እሷ ናት። ከእኔ ጋር በጣም ቅርብ ነን። ይህ ድንጋጤ የተፈጠረው ፌሪዬን ምን ያህል እንደምወዳት ሊያስታውሰኝ ይሆን? እንኳንም ሆነ! እንኳን አለቀስኩ። የለቅሶዋን ከፊል ተጋራኋት።
ወደ ውሳኔዬ ልሂድ! ወደ ፌሪዬ! ወደ ፍቅሬ! ለመደወል ስልኬን አነሳሁ። ግን ደግሞ ኢክራምን መክዳት እንዳይሆንብኝ ሰርጓ እስኪያልፍ ድረስ መጠበቅ አለብኝ።

ሰሚር ከእጄ ላይ ካርዱን ተቀብሎ ተመለከተው።
ካርዱን ከትከሻዬ ጋር እያጋጨ «እንሄዳለን!» አለ።
«ወዴት?»
«ወደ ሰርጉ ነዋ!»
«የምርህን ነው?»
«ጠሪ አክባሪ ነው¡»
«አትቀልድ!»
«ሌላው ቢቀር ኢክራምን እናያታለን።»
ተስማማን። ሰርጉ ቅዳሜ ቀን ነበር። ቀኑ ሲደርስ ሙሽራ መስለን ወደ ሸራተን ነዳን። ስንገባ ከጋሽ በርጊቾ ጋር ተገጣጠምን። ምንም ያልተፈጠረ ይመስል አክብሮ ሰላም አለኝ። ቦታችንን ይዘን እንደተቀመጥን ሙሽሮች መግባት ጀመሩ። በጣም ግራ ገባኝ። እኔና ሰሚር መተያየት ጀመርን። ሰውየው ሱፉን አሳጥሯል። የኢክራም ፊት ላይ የሀዘን ድባብ አይታይም። ፈገግ ብላ ታወራዋለች። ስልጥኛ ዘፈን ተበርግዷል። እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች፣ ህፃናት ሁሉ እየዘለሉ ነው። ኢክራምና ሙሽራውም በሚዜዎቻቸው ተከበው ይነጥራሉ። እንደሁሉም ዘር ስልጤም በራሱ ዘፈን መጨፈርን ሀላል ያደርገዋል። ዘፈን መስሎ የሚሰማቸው አማርኛ ዘፈን ይመስለኛል። ለነገሩ እኛም ትግሬዎቹ ብንብስ እንጂ አንሻልም። አለመጨፈር በትግሬ ሰርግ የሚታሰብ አይመስለኝም። ባይሆን ዘፈኑ በሙሉ ትግርኛ መሆን አለበት። ዘረኝነቱም ተመሳሳይ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ከጥቂት ብሔሮች ውጪ አብዛኛው ዘረኛ ነው። በተለይ ደግሞ ሀብታም ቤተሰብ ሲሆን ዘረኝነቱ ይከብዳል። ጎላ ብለው ከወጡት ብሔሮች መካከል አደሬ በዘረኝነት የወርቅ ሜዳሊያውን የሚወስድ ይመስለኛል። ትግሬ የብር፣ ስልጤ ደግሞ የነሀስ ሜዳልያ! ልጆች ከተዋደዱ በኋላ አይሆንም ብሎ መከልከል ማለት በሀራሙ እንዳሻችሁ እንደማለት ነው። አብዛኛው በእነዚህ ዘር ያሉ ወጣቶች የራሳቸውን ዘር የሚያገቡት ከሌላ ዘር ፍቅረኛቸው ጋር በእንባ እየተለያዩ ነው። ቤተሰቦች እነሱ ጋር ያለውን ዘረኝነት ወደ ልጆቻችን ካላጋባን ብለው ግብግብ የገጠሙ ይመስላል። እርስበርስ ብንከባበርና ስልጣኔው ኖሮን ነብያችን ቆሻሻ ካሉት ድርጊት ብንርቅ ሸጋ ነበር። አላህ ዘር የሰጠን እንድንተዋወቅበት እንጂ እንድንለያይበት አይደለም። ይህን ስል ግን በሁሉም ብሔሮች ውስጥ አላህ የባረካቸው ከዘረኝነት ቆሻሻ የፀዱ ቤተሰቦች የሉም ማለት አይደለም። በጠራናቸው ዘሮች ውስጥ ብዙም ባይሆኑ ከሌላ ዘር ጋር የተዛመዱ አይጠፉም።

ኬክ ተቆረሰ! ፅዋ ተነሳ! ኢክራም አየችኝ .... ፈገግ አለችና በእጇ ቻው አለችኝ። ቻው ፉአድ .... ቻው! አስተናጋጁ ከሙሽሪቷ የተላከ ነው ብሎ ወረቀት ሰጠኝ። ከፈትኩት። በኮምፒዩተር የተፃፈ ነው። አዘጋጅታው የመጣችው መሆኑን ተረዳሁ።
«ጥሪዬን ተቀብለህ ስለመጣህ ደስ ብሎኛል። ላደረግክልኝ ሁሉ አመሰግንሀለሁ። በህይወቴ ቤተሰቤን አስደስቼ አላውቅም። ካስደሰታቸው .... ካንተ ጋር ያለኝን ግንኙነት አቁሜ ያሉትን እያገባሁላቸው ነው። እንደከዳሁህ አይሰማህ። ወደ ፈሪሀ ሂድ። ትዳርህ እሷ ናት። የሰው ሀቅ መንጠቅ ይብቃኝ! የራሴን ሀቅ ልሞክር! እወድሀለሁ አልልህም! ምክንያቱም በደንብ ታውቀዋለህ። ቻው! ፉዬ ቻው!» ከፅሁፉ ስር የከንፈሯ ምልክት በሊፒስቲኳ ታትሟል።
ቀና ስል ተያየን። እጇን አየር ላይ ሳመችና በስንብት አወዛወዘችልኝ። እኔም እጄን ስሜ አወዛወዝኩ። ቻው የትልቁ ወንጀሌ መጀመሪያ! የትልቁ ወንጀልሽ መጀመሪያ .... ይወድሻል .... ቻው!
ከሰርጉ እንደወጣን ያለምንም ማንገራገር ወደ ፈሪሀ ደወልኩ። ወደ መጀመሪያዋ ፍቅሬ .... ሁሉን ወደ ጀመርኩባት የፍቅር አድባር! ከዚያ ሁሉ መገፋት በኋላ እሺ ብላ ትቀበለኝ ይሆን? ልቤ በጣም እየመታ ነው።

ይቀጥላል!
.
.
.
.
https://t.me/amharicfiction

ስነ-ፅሁፍ

24 Aug, 19:03


Fuad Muna (Fuya):
የልብ ነገር
ክፍል ሀያአንድ
(ፉአድ ሙና)
***

ቁረጥ ቁረጠው
የወጠረህን፣ ያንን መንጠቆ፣
ይሄዳል እንጂ
መዳረሻውን፣ ልብህ መች አውቆ?

በጥስ በጥሰው
ተንሳፈፍበት፣ በሰራኸው ሀይቅ፣
አትሙት እንጂ
የምታዘንበው፣ እንባ እንደው አያልቅ!

***
በሰው ልጅ ህይወት ከባዱና መራራው ፅዋ ሞት ነው። ሟች ከስራው ጋር ይገናኛል። አፍቃሪ ልቦች ይደማሉ። አንዳንዴ የማይብራራ ስሜት ...  የማያሳዩት ቁስል አለ። ተመልካች የማይረዳው ስቃይ .... ለተመልካች የሚቀል ስብራት .... ከባድ ህመም! አንድ ቤተሰብ ውስጥ ልጅ ሲሞት ወዳጅ ዘመድ ቤተሰቦቹን ለቅሶ ይደርሷቸዋል። ያፅኗኗቸዋል። የሟች ጓደኞችም ቤተሰቦቹን ለቅሶ ይደርሳሉ። ከእነሱ መካከል ግን ከቤተሰቦቹ እኩል  .... አንዳንዴም በላይ ሀዘን የሚሰባብረው ሰው አለ። ማንም ለቅሶ የማይደርሰው ሚስኪን! ሁላችንም ለልባችን የቀረቡ ውዶች አሉን። ለቅሶ ተቀምጠን ሰው አይደርሰን ነገር ወላጆቻቸው አይደለንም። ወዳጆቻችንም ስብራታችንን አይገምቱትም። ጓደኛን የመነጠቅ ህመም ከባድ ነው። የፍቅር ስሜት ሲሆን ይብሳል። የቀድሞ ባለቤታችሁ ስትሆን ያቃጥላል። በትዳር አብረውት የነበሩት ሰው ቢፋቱም የሚከፈት የትዝታ ዶሴ ይኖረዋል። ከፈሪሀ ጋር የተጋመድነው ማንነት አለ። ለፈሪሀ ያለኝ ጥልቅ ፍቅር .... ድጋሚ ዕድል ብትሰጠኝ እያልኩ እያሰብኩ ነበር። ድንጋጤ ልቤን መታው። ፈሪሀ ትሞታለች እንዴ? ፈሪሀን የመሰለች ውብ የፍቅር ሰው በሞት ትጠረጋለች? በቃ እንደዚሁ? ሳንነጋገር? እወዳት እኮ ነበር። ከወደድካት ለምን ፈታሀት የሚለኝ ገፊ እስካይረዳው ድረስ አፈቅራታለሁ። ከፈጣሪ ጋር ግብግብ መግጠም አማረኝ። ለምን? እኔ ይኼን ያህል ምን በደልኩ? ፈሪሀዬ፣ የኔ አፍቃሪ፣ የኔ ተናናሽ፣ የኔ ቆንጆ .... ለምን? ለምን ሞትሽ? ለምን? የኔ አይነቱ ከሀዲ ቢሞት አይሻልም ወይ? የኔ ንፁህ? ምን ባጠፋሽ? በምን ሀጢዓትሽ ፍቅሬ? ለምን?
አናጣቸውም ብለን የምናስባቸውን ሰዎች ምን ያህል እንደምንወዳቸው የሚገለጥልን ስናጣቸው ነው። ሲኖሩ የሚገባቸውን ክብር እንነፍጋቸዋለን። ስናጣቸው እንጮሀለን .... ልባችንን በለቅሶ እናደማለን። መጀመሪያ ይህን ያህል እንደምንወዳቸው ምን ጋረደብን? ምን ሸፈነን? ፌሪዬ ለመጨረሻ ቀን ስትሰናበተኝ የነበረበት ሁኔታ አይኔ ላይ ድቅን አለ። እቅፌ ውስጥ ነበረች። ስማኛለች። ከሄደች በኋላም እየሮጠች ተመልሳ ስማኛለች። ፍቅር ፍቅር ትሸት ነበር። ለነጋችን ስትል ራሷን ዝቅ አድርጋ ለምናኛለች። ደደብ ነበርኩ። ደደብ! የምፈልገውን እንኳን የማላውቅ ደነዝ!

ሞት ሰው አይመርጥም። ቀጫጫ በለው ወፍራም፣ ህፃን ይሁን ሽማግሌ፣ ባለትዳር አይል ላጤ፣ ወዳጅ አይለይ ጠላት፣ ወንድ አይፈራ ሴት፣ አዋቂ አያከብር መሀይም፣ ኸይረኛ አይከብደው ሸረኛ፣ አፍቃሪ አይተው ተፈቃሪ .... ኪታቡ ላይ ያለችዋን ቀንና ሰዓት እያየ ሩሁን ከአካሉ ይለያል። አንዳንዴ ህይወት ግራ ሲገባን ሞትን እንመኛለን። መልዕክተኛው (ሰዐወ) ደግሞ «ከእናንተ ውስጥ ማንም ቢሆን ሞትን አይመኝ። መልካም ሰሪ እንደሆን መልካምን ይጨምራል፤ መጥፎን አድራጊ ከሆነ ደግሞ ወደ ጌታው ሊመለስ ይችላል።» ይላሉ። የፈሪሀን ሞት እንደሰማሁ መሞት አምሮኝ ነበር። በደግ ጊዜ የቀራሁት ሀዲስ ጭንቅላቴ ላይ ተመላለሰ። «ከእናንተ ውስጥ አንደኛችሁ ባገኘው መከራ ምክንያት ሞትን አይመኝ። ይልቁንስ «ጌታዬ ሆይ! መኖር ለኔ የተሻለ እንደሁ አኑረኝ። መሞት የሚበጀኝ እንደሁ ውሰደኝ።» ብሎ ዱዓ ያድርግ።» እስልምና ለሁሉም ነገር አጥር አለው። ለሁሉም መድረሻ መንገድ አበጅቷል። አሁን እኔ በምን መልካም ስራዬ መሞትን እመኛለሁ? ሲል አኑረህ ተውበቴን ተቀበለኝ ብዬ ማልቀስ ይገባኝ ነበር። ግን ድንጋጤዬ የማያሳስበኝ ነገር አልነበረም። ውዱ ነብያችን (ሰዐወ) «ጥፍጥናን ቆራጭ የሆነችውን ማስታወስን አብዙ!» ሲሉ አስተምረዋል። ይህቺ ጥፍጥና ቆራጭ ሞት ናት። ዱንያ ላይ ከፈሪሀ በላይ የሚጣፍጥ ምን አለ? ምንም! የኔ ጥፍጥና ፈሪሀ ነበረች። ተቆረጠች። በዘነጋሁት ጥፍጥና ቆራጭ ወደመች። ሞትን የሚፈራት የእኔ አይነት አመፀኛ ነው። ጌታውን ሲያምፅ .... ድንበሩን ሲወዘውዝ የከረመ አመፀኛ! ነብያችን (ሰዐወ) «አላህ (ልቅና ይገባውና) ባሪያዬ እኔን መገናኘትን ከወደደ እኔ እሱን መገናኘትን እወዳለሁ። እኔን መገናኘት ከጠላ እኔም እሱን መገናኘት እጠላለሁ! ይላል።» ዱኒያ ላይ ስንኖር አላህን መገናኘትን ልንወድ የምንችለው ከወንጀል ራሳችንን ከጠበቅንና መልካም ስራን ካዘወተርን ይመስለኛል። እንደኔ ዝሙት ውስጥ የወደቀች ልብ አላህን መገናኘት እወዳለሁ የምትልበት ድፍረት አይኖራትም። ሞት ሳይደርስብኝ ወደ አላህ ልመለስ ትል ይሆናል። በእርግጥ ሞትን የሚወድ የለም። ይህን ሀዲስ ነብያችን (ሰዐወ) በተናገሩበት ጊዜ «ሞትን መጥላት አላህን መገናኘት መጥላት ነው? ሁላችንም ሞትን እንጠላለን።» ሲሉ ጠየቋቸው። ነብዩ (ሰዐወ) «ይኼ በሚሞት ጊዜ ነው። በአላህ እዝነት እና በምህረቱ በተበሰረ ጊዜ አላህን ለመገናኘት ይጓጓል፤ አላህም እሱን ለመገናኘት ይጓጓል።  በአላህ ቅጣት በተበሰረ ጊዜ አላህን መገናኘትን ይጠላል፤ አላህም እሱን መገናኘትን ይጠላል።» ሲሉ መለሱ። ፈሪሀዬ በምን ተበስራ ይሆን? በአላህ እዝነት ወይስ ቅጣት? እኔስ በምን እበሰር ይሆን? ጌታዬ ሆይ መጨረሻዬን አሳምርልኝ። የፈሪሀን መዳረሻም አስውብልኝ።

«ሞተች ... ፉ ሞተች!» እንዳለችኝ ደርቄ ቀረሁ። ስልኬ ከእጄ አመለጠኝ። ትንሽ ቆይቶ ስልኩ መልሶ ተደወለ። አነሳሁት።
«በመኪና ገጯት።»
«በመኪና ገጯት።»
«በመኪና ገጯት።»
ጆሮዬ ላይ እየተደጋገመ ተስተጋባ። ወይኔ የእኔ ፍቅር ..... አለሜ! የማውራት አቅም አልነበረኝም። ዝም ብዬ አደምጣለሁ።
«ከቤት እንደወጣች በበራችን የሚያልፍ መኪና ገጭቷት ጠፋ!»
«የኔን ውብ ገደሏት!»
«የኔን ፀባይኛ ገደሉብኝ!»
«አጫዋቼን ጨፈለቋት!»
ታለቅሳለች። አሳዘነችኝ። እንባዬን ዋጥ አድርጌ «አይዞሽ በቃ .... አይዞሽ!» አልኳት።
ማልቀሷን ቀጠለች።
«ሀኪም ቤት ሳትደርስ ነው የሞተችው? አልወሰዳችኋትም?» ጠየቅኳት።
«ምኗን እወስደዋለሁ? የጭነት መኪና እኮ ነው። ጭፍልቅ እኮ ነው ያደረጋት! ሙሉ አካሏን አደቀቀው .... አላህ ያድቅቀው!»
«አብሽሪ!»
«ያንተ ስጦታ ነበረችኮ! ወይኔ ድመቴ!»
«ድመት?»
«አዎ አንተ ከአዲስአበባ ያመጣህልኝ!»
ደገምኩት! «ድመት?»
«አዎ ፉ አንተ የገዛህልኝ ድመቴ!»
ኡፍፍፍ! ተነፈስኩ። ቆሌሽ ይገፈፍ አይባል ነገር! ልቤ ወደ ቦታው ተመለሰ። ከመቀመጫዬ ተነስቼ የምስጋና ሱጁድ ወረድኩ። ተመስገን። ፈሪሀዬን እንኳንም ክፉ ያልነካት።
«ሌላ አትገዛልኝም?»
«ኧረ እገዛልሻለሁ። እንዳታስቢ ..... እገዛልሻለሁ።»
«ከቤት እኮ እንዳትወጣ ሰራተኛዋን አስጠንቅቄያት ነበር። አትሰማም ደንቆሮ ነገር ናት ሰራተኛዋ!»
«አብሽሪ ባለፈው የገዛሁበት ቦታ ቆንጆ እሷን የምትመስል እፈልግልሻለሁ። ስሄድ በቪዲዮ አስመርጥሻለሁ።»

ስነ-ፅሁፍ

23 Aug, 20:46


«አሰላሙአለይኩም ጋሽ በርጊቾ!»
«ወአለይኩሙሰላም ልጅ ፉአድ!»
ሰላምታ ተለዋውጠን አላስፈላጊ ነገሮች ጠፋህ ተጠፋፋን ምናምን ከተባባልን በኋላ ወደ ገደለው ገባሁ።
«ኢክራም ደህና ናት?»
«አዎ ደህና ናት!»
«አውርታችሁ ነበር አይደል ስለትዳሩ?»
«አዎን! ተወያይተን ነበር።» ድምፃቸው ድክም ብሏል።
«ዛሬ አጣኋት እንደምታገኘኝ ነግራኝ ነበር። ስልኳም አይሰራም።»
«ገብቶኛል። አዎ ጠለፋ ምናምን ያለችህን እንኳን ዝም ብዬ እሷን ለማረጋጋት የተስማማሁት ነበር። እኔ ብትጋቡ ደስ ይለኛል። ግን ቤተሰቦቼና ወላጆቼ አልወደዱትም።»
«እሺ ለምንድነው ስልኳ የተዘጋው?»
«ካንተ ጋር እንዳትገናኝ ስልኳን ቀምተዋታል። ቤት ተቆልፎባታል። ትዳር ካንተ ጋር የሚሆን አይደለም ልጅ ፉአድ!»
«በዘር ስለምለያችሁ?»
«አዎ ፉአድ! ግን ዘርህ ብቻ አይደለም። አንተ አግብተህም ፈተሀል። የፈታህ ሰው መሆንህን አልወደዱትም። እኔ አይደለሁም አትቀየመኝ።»
«አባቷ እርስዎ ነዎት! እድራለሁ ካሉ የሚከለክልዎ የለም።»
«ስለማታውቅ ነው። እኔ እንዳልድር እርግማን አስቀምጠውብኛል። ባለፈው ተሰብስበው ልጁን ለትግሬው ከዳረ ብለው እርግማን አስቀምጠውብኛል። የቤተሰብ እርግማን ከባድ ነው በባህላችን! ይገባሀል መቼስ!»
«ዘረኛ ናችሁ! በጣም ቆሻሻ ዘረኛ ናችሁ!» ድምፄ በአንዴ ከእርጋታ ወደማልቆጣጠረው ፍንዳታ ተቀየረ።
«ተረጋጋ ልጅ ፉአድ! ተረጋጋ!»
«እኔ ደግሞ አሳያችኋለሁ! ትከሻ ከሆነ በደንብ እንለካካለን ችግር የለውም! አልቅሰህ ትድርልኛለህ! አልቅሰህ!»
ስልኩን ጆሮው ላይ ጠረቀምኩት። ስልኩን ዘግቼ ጉልበቴን አቅፌ አለቀስኩ። ለምን? ምናለ መንገዱን ባይዘጉብን? በሀራም ስንት ድንበር የተላለፍኳትን ሴት በሀላል ስጠይቅ እንዴት እከለከላለሁ? ዝሙትን ፈቅዶ ጋብቻን መከልከል ደግሞ ምን የሚሉት ባህል ነው?

ኢክራም ተዓምር ፈጥራ ትደውልልኛለች ብዬ አስቤ ነበር። ቀናት አለፉ። የቻልኩትን ያህል ሞከርኩ። ከሰሚር እና አህመድ ጋር ቤታቸው ድረስ በመሄድ ለመግባት ታገልን። ትልቅ ግርግር ከመፍጠር የዘለለ ምንም አላተረፍንም። ጭራሽ ልጃችንን ሊጠልፍ ሞከረ ብለው ከሰሱኝ። ደግነቱ የተከሰስኩበት ጣቢያ ሀላፊ ወዳጄ ነበር። ክሱን ውድቅ አደረገው። በተቃራኒው ልጃቸውን በማፈን ከሰስናቸው። የብርበራ ፈቃድ ወጥቶ ወደ ቤታቸው ፖሊሶች ሄዱ። ግን ኢክራምን አላገኘናትም አሉ። ገንዘብ ተሰጥቷቸው መሆኑ ግልፅ ነበር። የጣቢያው አዛዥ ራሱ እንዲሄድ ተስማማን። እሱ ሲሄድም የለችም። ሲመስለኝ ወደ ሌላ ቦታ ወስደው ደብቀዋታል። ሁለት ወር ሙሉ የኢክራምን ድምፅ ሳልሰማ አሳለፍኩ። ከወንጀል እወጣለሁ ብዬ ወደሌላ ወንጀል መግባት ጀመርኩ። ተስፋ ቆረጥኩ። የኢክራም ሱቅ ሁሌ ይከፈታል። ታናሽ እህቷን አያታለሁ። እንደሷ ቆንጆ ናት።
ሰሚር «ስማ ፉዬ ....» አለ።
ፊቴን ወደሱ መለስኩ። የአህመድ ቤት በር ላይ መኪና ውስጥ ተቀምጠናል።
«ፉዬ ይኼ ነገር ከረረ በጣም!»
«ምኑ?»
«የኢክራም ጉዳይ!»
«እና?»
«ከቤተሰቦቿ ጋር መጋደል እኮ ነው የቀረህ! ብታሸንፋቸው እንኳን አባቷ አይድርልህም! ቃዲ ጋር ሄደህ ዳረህ ብንል እንኳን ምን አይነት ህይወት ልትኖሩ ነው?»
«አልገባኝም!»
«ከቤተሰቧ ጋር እንደዚህ ተጣልተህ እንዴት ነው አማች የምትሆነው?»
«እና ምን ላድርግ?»
«ቢከብድም .... ተዋት! ትዳር ቤተሰብ ሳይኖርበት አይሆንም። ተዋት! መሰልዋን ይዳሯት!»
«ክህደት አይደል!»
«አይደለም! ከዚህ በላይ ምንም ማድረግ አትችልም። የቻልከውን አድርገሀል። ማንም የማይደፍረውን ደፍረህላታል። ከወደድካት ተዋት። ከመሰሏ ጋር ጤነኛ ህይወት ይኑራት። ነፃነትዋን ታግኝ። ባንተ ምክንያት እስረኛ አትሁን።»
«ድምጿን እንኳን ብሰማው .... ቻው እንኳን ብንባባል!»
«ቢሆን ጥሩ ነበር ግን move ማድረግ አለብህ።»
«እጠብቃታለሁ።»
«አትጠብቃት! አትመጣም። የሁለታችሁ ትዳር አይሆንም። ቤተሰብ አይፈቅደውም። አሁን ግን ፈሪሀን  .... »
«ፈሪሀን ምን?»
«ተወው በቃ!»
«ጨርሰው!»
«ፈሪሀን አግኛት እስኪ!»
«ለምን?»
«እሷ ትወድሀለች። ቤተሰቦቿም ይድሩልሀል። በቃ ከኢክራም ጋር ላለመማገጥ አልነበር ኢክራምን የምታገባው? ይኼው እብዳቸውን አስረውልሀል። አሁን ፈሪሀን ብታገባ ከማንም ጋር አትማግጥም።»
«አንተ ፈሪሀን አግባ አልክ?»
«አዎ አግባት! ትወዳት የለ።»
የእኔን ወሬ በእንጥልጥሉ ትተን ወደአህሜ ወሬ ተሻገርን።
«ስማ አገኘሀት እንዴ ሰሚራን?»
«አዎ አገኘኋት!»
«ምን አለችህ?»
«ምንም አልተቀየረችም። ምንም እንዳልተፈጠረ ነው የምታወራኝ።»
«ሌላ ነገር አላደረጋችሁማ?»
«ኧረ ወደዛ ሰው አጣሁ እንዴ?»
«ምን ለብሳ መጣች?»
«እንደሁልጊዜው!»
«ይህቺማ ያማታል።»
«ቀላል!»

ሰሚርን አህመድ ጋር ጥዬ ወደ ቢሮዬ ነዳሁ። ፀሀፊዬ ጠረጴዛዬ ላይ የሚያምር ፖስታ እያስቀመጠች «ይኼ ተቀምጦልሀል!» አለችኝ። ወንበሬ ላይ እንደተቀመጥኩ ፖስታውን ከፈትኩት። የሰርግ ጥሪ ወረቀት ነበር። ለአቶ ፉአድ ሙና ከባለቤትዎ ጋር ይላል። እያነበብኩ ደርቄ ቀረሁ። «የልጃችን ኢክራም በርጊቾ እና የኑረዲን ሁሴን የሰርግ ስነ–ስርዓት .... » የተጠቀሰው ቀን ከሳምንት በኋላ ነው። በርጊቾ የዚህን ያህል እልህ ይጋባኛል ብዬ አላሰብኩም። ሸራተን ሚስትህን ስድር መጥተህ ታደም ብሎ ካርድ ላከልኝ። ሰርጌን ይበጠብጣል ብሎ አለመፍራቱ ገረመኝ። እንባ እንባ አለኝ። ከጎኔ የሚሆን የሌለ ያህል ተሰማኝ። እንባዬ ፈሰሰ። እጄ ይንቀጠቀጣል። ካርዱን እንደያዝኩት ስልኬ ጠራ። የፈሪሀ እህት ነበረች። አነሳሁት።
«ሄሎው .... » ድምጼን ለማስተካከል ሞከርኩ።
«ፉ ....» ታለቅሳለች።
«ወዬ ምነው ድምፅሽ?»
«ሞተች ..... ፉ ሞተች!» ተንሰቀሰቀች።

ይቀጥላል!
.

ስነ-ፅሁፍ

23 Aug, 20:46


Fuad Muna (Fuya):
የልብ ነገር
ክፍል ሀያ
(ፉአድ ሙና)
***
በለው አናቱን
ይድረቅ ይኮስምን፣ ይውጋው መከራ፣
አትዘንለት
ፀጋ ንጠቀው፣ ተራ በተራ!

ገፍቷል ይገፋ
ይሰበር ልቡ፣ ይድረሰው እጣ፣
መሸሻ እስኪያጣ
በእጁ ስራ፣ ዳዒም ይቀጣ።

***
ደረስኩ ሲሉ መውደቅ .... አገኘሁ ሲሉ መንጠፍ .... ከበርኩ ሲሉ መርገፍ .... አወቅኩ ሲሉ መታለፍ .... ኡፍፍፍ .... ልብን ያደክማል። ለአላህ ነግሬው ነበር! አመፅኩህ .... ድንበርህ ላይ ተረማመድኩ .... ስህተት ነው አመንኩ .... መረጋጋትን ፈለግኩ .... ኢክራሜን ማረፊያዬ አድርግልኝ .... የሀራም በሮቼን ጠርቅምልኝ ..... የኸይር በሮቼን ክፈትልኝ .... ለምኜው ነበር። አላህ ደግሞ የለማኞችን ልመና የሚቀበል ጌታ ነው። ለምኑኝ እቀበላችኋለሁ ያለን አምላክ ነው። ለምን ጉዳዮቼ ይወሳሰቡብኛል? ለምን? ሁሉም ነገር እኮ በቁጥጥሬ ስር ያለ መስሎኝ ነበር። ፈሪሀን ስፈታት ከኢክራም ጋር መቆሸሽ ስለሰለቸኝ .... በየቀኑ ልቤን በኃጢያት ክምር ማጥቆር እጅ እጅ ስላለኝ .... ሂድ ሂድላት የሚለኝን ሴት አግብቼ ከወንጀል ለመላቀቅ .... ለዚያ ነበር። ሁሉም ነገር በቁጥጥሬ ስር እንዳለ ተሰምቶኝ ነበር። ፈሪሀን መፍታት .... ኢክራምን ማግባት .... ወደ አላህ መመለስ .... የድሮውን ፉአድ መሆን! አለቀ! ሁሉንም አቅጄው ነበር። አላህ ወደሱ ከመመለስ እቅዴ ጋር ምን ቅሬታ አለው? ለምን ያወሳስብብኛል? ወደሱ የምመለስበትን ቀን ለምን ያራዝምብኛል? ለምን? የእኔ አላህ ከሌሎች አላህ ይለያል እንዴ? አላህ በእኔ ወደሱ ለመመለስ መፈለግ ለምን አልተደሰተም? ጌታዬ ማለት .... ያ በበረሀ ስንቁን ሁሉ የጫነባት ግመል በተኛበት የጠፋችው ሰው .... በረሀውን ቢያስስ አጥቷት የጠፋችኝ ቦታ ሄጄ ልሙት ብሎ እንደተመለሰው .... ሲመለስ እንቅልፍ አሸልቦት ሲነቃ ግመሏን ከጎኑ ከነስንቋ ቆማ እንዳገኛት .... አዎን እሱ ሰው በመመለሷ የደስታን ጣሪያ እንደተደሰተው .... አላህ በባሪያው ወደ እርሱ መመለስ ከዚህ ሰውዬ በላይ ይደሰታል። እና ለምን ወደሱ መመለሴን ያዘገይብኛል? የእኔ ወንጀል ከእሱ መማር ይገዝፋል?  የእኔ አመፅ የአላህን እዝነት ያሸንፋል? ለምን?

ከዘመናት በአንዱ ዲናር አል አያር የተባለ ግለሰብ ይህችን ምድር ረግጧል። ዲናር በእጅጉ አላህን ፈሪ ከነበረች እናት የተወለደ ነው። ምን ያደርጋል? የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነውና ዲናር የለየለት አመፀኛ ሆነ። እናቱ በገባ በወጣ ቁጥር «ዲናር ሆይ አላህን ፍራ! ዲናር ሆይ ወደ አላህ ተመለስ!» እያለች ትገስፀዋለች። ነብዩሏሂ ኑህ አለይሂ ሰላም «ጥሪዬ ሽሽትን እንጂ አልጨመረላቸውም!» ብለው ወደጌታቸው ስሞታ እንዳቀረቡት፤ የእናቱ ተግሳፅ መጥመምን እንጂ አልጨመረለትም። እልል ያለ አመፀኛ ሆነ። ታዲያ አንድ ቀን በቀብር ቦታ ሲያልፍ አንድ አጥንት ተመለከተ። ሲያነሳው አጥንቱ እጁ ላይ ተፈርፍሮ ዱቄት ሆነ። ዲናር በጣም ተደናገጠ። ነገ እኔም እንደዚህ አፈር እሆናለሁ ሲል ተከዘ። የሰራቸው ወንጀሎች አይኑ ላይ ተደቀኑበት። ወደሰማይ እያየ «ጌታዬ ሆይ! እኔ በሙሉ ልቤ ወዳንተ ተመልሼያለሁ። መመለሴን ተቀበለኝ ... ማረኝም!» ሲል ዱዓ አደረገ። ዲናር ወደ እናቱ ተመልሶ «እናቴ ሆይ! አምልጦ የነበረ ባሪያውን ጌታው ሲይዘው ምን ያደርገዋል?» ሲል ጠየቃት። እናትየውም «ሻካራ ልብስን ያለብሰዋል፣ ርካሽ ቀለብን ይመግበዋል፣ መልሶ እንዳይጠፋም እጅና እግሩን በሰንሰለት ያስረዋል።» ስትል መለሰችለት። ዲናርም «ስለዚህ እናቴ ሆይ! ሻካራ የሆነ ሱፍን፣ የገብስ ዳቦን እና ሁለት ሰንሰለቶችን እፈልጋለሁ። እናቴ ሆይ በጠፋ ባሪያ ላይ የሚደረገውን አድርጊብኝ። አላህ ይህን መዋረዴን አይቶ እንዲምረኝ እከጅላለሁ።» አለ። እናቱ ከመስማማት ውጪ አማራጭ አልነበራትም። ዲናር ሁሌም ሲመሽ እየተንሰቀሰቀ ማልቀስ ይጀምራል። «ወዮልህ ዲናር! ጀሀነምን የሚቋቋም አቅም አለህ ወይ! እንዴት ደፋር ብትሆን ነው አላህን የሚያስቆጣ ህይወትን የመራኸው? ወዮልህ ዲናር! ወዮልህ!» ምሽቱ እስኪነጋ ድረስ ይንሰቀሰቃል።  በዚህ ሁኔታ ውስጥ ዘወተረ። ሰውነቱ እየተለወጠ እና እየገረጣ፣ አካሉም እየኮሰመነ መጣ። እናቱ በጣም ሀዘን ተሰማት። «ልጄ ሆይ እባክህ ለነብስህ እዘንላት! ትንሽ ዕረፍት አድርግ!» ስትል ተማፀነችው። እሱም «ተይኝ እናቴ ትንሽ ልታሰር! እኔ አንቺ እና ሌሎች ወደ ጀነት ስትሄዱ እኔ ደግሞ ከጀሀነም ሰዎች ጋር ጀሀነም ስወርድ ይታየኛል። ለረዥሙ ሀገር ምቾት ዛሬን ተይኝ ዕረፍት ልጣ! ነገ አላህ ፊት የምንቆምበት ረዥም ቀን አለ። ወደ አረንጓዴዋ ጀነት ወይስ ወደ ስቃይ ማማ .... ወዴት እንደምወድቅ አላውቅም!» ሲል መልሶላት በለቅሶው ፀና። በአንድ ምሽት ዲናር ቁርዓንን እያነበበ ሳለ ሁለት አናቅፅ ጋር ደረሰ። አንቀፆቹ የሚከተሉት ነበሩ።
«فَوَرَبِّكَ لَنَسْأَلَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ عَمَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ
በጌታህም እንምላለን፡፡ ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን፤ ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ፡፡»
ዲናር የአንቀፁን ትርጉም እና አንድምታ እያሰላሰለ ራሱን ሳተ። እናቱ የተቻላትን አድርጋ ለማትረፍ ሞከረች። ሙከራዋ አልሆን ሲላት እንደሞተ አሰበች። ፊቱን እያየች «ልጄ ሆይ! አንተ የልቤ ሀሴት! የት ይሆን ድጋሚ የምንገናኘው?» ስትል ተከዘች። ዲናር አላህ የፃፈለት ትንፋሽ አላለቀም ነበር። ያለችውን ሰምቷል። በደከመ ድምፅ «እናቴ ሆይ! የቂያም ቀን ሜዳው ላይ ከተሰበሰበው ሰው መሀል ካጣሽኝ፤ የጀሀነም ጠባቂ የሆነውን ማሊክን ስለኔ ጠይቂው!» ሲል መልሰ። ሩሁ አካሉን ተለየች። ወደ ፈራው ጌታው ሄደ። እናቱ ሬሳውን አጥባ ከከፈነችውና ለቀብር ካዘጋጀችው በኋላ «ሰዎች ሆይ! የጀሀነም ፍራቻ ወደገደለችው ሰው የጀናዛ ሰላት ኑ!» ስትል ተጣራች። በዚያን ዘመን ለሱ ስግደት የተሰበሰውን ያህል ሰው ተሰብስቦም ሆነ፤ ለእርሱ ለቅሶ የፈሰሰውን እንባ ያህል ፈስሶ አያውቅም ይባላል። የተቀበረ ቀን ምሽቱን የዲናር ጓደኛ ዲናርን በህልሙ ተመለከተው። ዲናር አረንጓዴ ካባ ለብሶ ጀነት ውስጥ ይንጎማለላል። እየደጋገመ አንዲት የቁርዓን አንቀፅንም ያነባል።
«فَوَرَبِّكَ لَنَسْأَلَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ عَمَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ
በጌታህም እንምላለን፡፡ ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን፤ ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ፡፡»
ዲናር ለጓደኛው «በአላህ ክብር እና ልቅና ይሁንብኝ! አላህ ስለስራዬ ጠየቀኝ! አዘነልኝ።  ይቅርታ አደረገልኝ። ወንጀሌንም ሰረየልኝ። ይህን መልካም ብስራት ለእናቴ ንገርልኝ!» አለው። እና አላህ አዛኝና መሀሪ አይደለምን? አላህ አተ–ተዋብ አይደለምን? የተመላሾችን መመለስ የሚቀበል ጌታ አይደለምን?  እና ዲናርን የማረው አላህ እኔን እንዴት አይምረኝም? ይምረኛል። ይመራኛል። እስኪ ልታገስ!

ስልኬን አንስቼ ወደ አቶ በርጊቾ ደወልኩ። ስልካቸው ይጠራል ግን አይነሳም። ደግሜ ደወልኩ። ተነሳ።

ስነ-ፅሁፍ

23 Aug, 17:40


«አሰላሙአለይኩም ሙሽሮች!»
«ወአለይኩሙሰላም!» በሚስረቀረቅ ድምፅ መለሰች።
«አህመድ የለም እንዴ?» ሰሚር ጠየቀ።
«የለም እቃ ሊገዛ ወጥቶ ነው። ይመጣል .... ግቡ ተቀመጡ።»
የያዙት ሩም ሳሎን አለው። ሳሎኑ ላይ ተቀምጠን አህመድ ጋር ደወልኩ።
«ስልኩ እኮ እዚህ ነው።» የሚጠራውን ስልክ ይዛው መጣች።
«እና እንዴት ነው ሙሽርነት?» ሰሚር ጠየቀ።
«አልሀምዱሊላህ ደስ ይላል። እናንተም አግቡና ጥሩን ኧረ! በጣም ደስ ይላል።»
አስመሳይ ሁላ! በልቤ እስቃለሁ። በሩ መልሶ ተንኳኳ። ሰሚር ከፈተው። አህመድ በደስታ አቀፈን። ተቀምጠን ስናወጋ ቆየን።
ሰሚር  እየሳቀ «እና ከፈትከው?» አለ።
«አዎ ባክህ ትንሽ አሳመምኳት መሰለኝ! ግን ብዙም አላስቸገረችም .... አልሀምዱሊላህ!» አህሜ ጀግንነት ተሰምቶታል።
«እና አንሶላውን ቀየሩላችሁ?» ሰሚር ይጠይቃል። የዚህ ጥያቄ ቅኔ አልጠፋኝም።
«አዎ ደም ነክቶት ስለነበር ቀየሩት። ደስ ብሎኛል ግን በጣም!»
«ለምን?»
«ሳላያት አግብቼ .... ቁንጅናዋ ደስ ሲል! ደግሞ ስርዓትዋ ቢስሚላህ!»
«የምን ስርዓት?»
«ማታ ደክሞኝ ፈጅር ነበር ለመነሳት ያሰብኩት። በለሊት ተነስታ ለይል ካልቆምን ብላ ቀስቅሳኝ ብቻ ምን ልበልህ ደስስስ አለኝ።»
«ስንት ሰዓት ተኛችሁ?»
«ሶስት ሰዓት ነዋ!»
ሰሚራ ጠርታው አህመድ ወደ መኝታ ክፍል ገባ።
«ስማ ማታ ሶስት ሰዓት ያለመደባትን አስተኝቷት እንቅልፍ እምቢ ሲላት ቀስቅሳው እኮ ነው።» ይስቃል።
«ኧረ ዝም በል!»
«ቤት ከገባሁ በኋላ ቻት እያደረግን ነበር ባክህ!»
«ከማን ጋር?»
«ከሷ ጋር!»
«እንዴት?»
«አህሜን አስተኝታው ነዋ። ጀለስ መች እንቅልፍ አላትና! የቃጢራ ሰው ናትኮ!»
«እንዴት አወራችህ ማለቴ እንዳገባች ነገረችህ?»
«ኧረ ወፍ! እንደውም መች ነው የምንገናኘው ስትለኝ ነበር።»
«እና መች ተባባላችሁ?»
«ወዳጄ ሰርግ ላይ ስለሆንኩ ስጨርስ አመቻችቼ እነግርሻለሁ አልኳት!» ሳቄን መቆጣጠር አልቻልኩም .... ለቀቅኩት። የሰሚር እብደት በየቀኑ ያስቀኝ ይዟል።
አህሜ መጥቶ ትንሽ ከተጫወትን በኋላ ተሰናብተናቸው ወጣን።
«ስማ .... » አልኩ። «ስማ አህሜ በጣም ደስ ብሎታል። ይህን ሚስጥር ለራሳችን ይዘነው መቆየት አለብን።»
«አዎ አሁንማ በደንብ ይከትክታት ተወው .... የሰርጉን ወጪ ያስመልስ¡»
«የምሬን ነው ከነገርነው ይኼ ደስታው ጠፋ ማለት ነው።»
«ልጅቷን ቢያውቃት ኖሮ ከሷ ልጅ መውለድ የሚፈልግ ይመስልሀል? ልጅ ከወለደችለት በኋላ ቢያውቅስ ሰው የሚያደርገን ይመስልሀል?»
«እሱም አለ ለካ!»
«የልጅቷን አላማ እናረጋግጥ .... እኔ ጋር ብዙ ሰነድ አላት። አህሜ ላይ እቆምራለሁ ካለች አየር ላይ እንስባቸዋለን።»
«ግራ ይገባል። እስኪ እናያለን ....» በረዥሙ ተነፈስኩ።

ወደቤት እንደገባሁ ኢክራምን ይዤ አህሜ ወዳረፈበት ሆቴል ለመሄድ አሰብኩ። የኒካህ ወረቀት እንደሚጠይቁ ትዝ ሲለኝ በአቅራቢያው ያለ ሆቴል ካለ ብዬ ስልኬ ላይ ማሰስ ጀመርኩ። ኢክሩዬ ስራዋን አስተካክላ እና ለአባቷ ተናግራ እንደምትመጣ ስለተነጋገርን ቤት ቀድማኝ ትደርሳለች ብዬ አስቤ ነበር። ግን አልደረሰችም። ስራ በዝቶባት እንደሚሆን ጠርጥሬያለሁ። ልብሴን እየቀየርኩ ወደ ኢክራም ደወልኩ። ኦፕሬተሯ «ቴሌፎኑ ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም።» ትላለች። ደጋግሜ ደወልኩ .... ስልኳ ተዘግቷል። ኢክራምን ሳውቃት ስልኳ ተዘግቶ አያውቅም።
የጭንቀት ስሜት ስለተጫነኝ ወደ ቢሮዋ ነዳሁ። ቢሮዋ ዝግ ነው። ወደ ቤት ተመልሼ ደጋግሜ ሞከርኩ። ሰዓቱ ከምሽቱ ሶስት ተኩል ሆነ። ያለኝ አማራጭ ወደ አባቷ መደወል ነበር። 

ይቀጥላል!
.
.
.
https://t.me/amharicfiction

ስነ-ፅሁፍ

23 Aug, 17:40


Fuad Muna (Fuya):
የልብ ነገር
ክፍል አስራዘጠኝ
(ፉአድ ሙና)
***

በቃኝ ልረፈው
ላምልጥ ከአመፅ፣ ይብቃኝ ስደቱ፣
አይደክመኝም ወይ፣ ልቁሰል በስንቱ?

አዎ ታከተኝ
መሮጥ ይደክማል፣ መርገጥ እዚያቹ፣
ሌላ አልሻም
ዳሩኝ አለሜን፣ አሚን ብላችሁ።

***
ከአላህ ባህሪዎች ውስጥ አስ–ሰታር የሚለው ይገንብኛል። ዱንያ እና ዱንያ የያዘቻቸውን ኒዕማዎች በአንድ በኩል፤ የአላህን ሲትር በሌላው አድርጋችሁ ብታስመዝኑኝ እኔ የሲትርን ፀጋ እመርጣለሁ። ሲትር ደግሞ ምንድነው የሚል አልፎ ሂያጅን የአላህን የሲትር ፀጋ በእኔ ህይወት ውስጥ እጠቁመዋለሁ። አላህ ባሪያዎቹን እየተከታተለ የሚያዋርድ ጌታ አይደለም። በተቃራኒው ውርደታቸውን ይከልላል። ይሸሽጋቸዋል። እስኪፀፀቱ ሸሽጎ፤ ሲፀፀቱ ደግሞ ይምራቸዋል። እኔና ኢክራም የወደቅንበትን ስህተት ከእኔ አልፎ ሌላው ቢያውቅ ምን የሚለኝ ይመስላችኋል? እኔው የነገርኳችሁ እናንተ እንኳን ምን አላችሁ? ቆሻሻ አላችሁኝ? ርካሽ! በገደልነው? አስጠላኋችሁ አይደል? አዎ! ምናልባት እንዲህ ያላችሁኝ እናንተ አላህ የከለለው ከእኔ የገዘፈ ወንጀል ሳትሰሩ ቀርታችሁ አይደለም። ብዙ ወንጀል ውስጥ ተዘፍቃችኋል። ሰው እንዲያውቀው የማትፈልጉት ብዙ ጉድ አለ። ግን የእናንተ በሲትር ፀጋ ውስጥ ነው። ከጌታችሁ ውጪ ማንም አያውቀውም። አንዳንዴ በቤተሰብ ስብሰባ ውስጥ ተቀምጬ ሁሉም የእኔን ንግግር አፋቸውን ከፍተው ሲሰሙ ሳይ ..... አልሀምዱሊላህ ያ ሳቲር እላለሁ ..... መስሪያ ቤት ሰራተኞቼ ጠብ እርግፍ እያሉ ሲታዘዙኝና እንደ አርዓያቸው ሲመለከቱኝ ሳይ ..... ለከልሀምድ ያ ሰታር እላለሁ .... በሁሉም የህይወት እንቅስቃሴዎቼ ላይ በሰዎች ዘንድ ያለኝን ተቀባይነት ሳስብ .... እንኳንም የደባቂው የከላዩ ጌታዬ ባርያ ሆንኩ ብዬ እደሰታለሁ። እየታመፀ የሚሸሽግ፣ እየታመፀ የሚረዝቅ ጌታ አላህ ነው። ሰው በቻለው አቅም ትንሹን እንከን ተራራ አሳክሎ እንደአውሬ ሊስላችሁ ይፈልጋል። አላህ ግን ለሰው አሳልፎ አይሰጣችሁም። ነውራችሁን ደብቆ ወደሱ ስትመለሱ ምህረቱን ያጎናፅፋችኋል።

በነብዩሏሂ ሙሳ አለይሂ ሰላም ጊዜ ዝናብ ይጠፋል። የእስራኤል ልጆችም ወደ ሙሳ በመምጣት «አንተ ጌታህን የምታናግር ነብይ ሆይ! እኛ በድርቅ ተጠቃን! ጌታህን ዝናብ እንዲያዘንብ ለምንልን!» ሲሉ ጠየቁ። ሙሳም ህዝቡን ሰብስበው ወደ በረሀ ወጡ። ከሰባ ሺህ በላይ ህዝብ ተሰበሰበ። ሙሳ አላህን መለመን እና ይቅርታ መጠየቅ ጀመሩ። ሆኖም ግን እንኳን ሊዘንብ ፀሀዩ ይበልጡኑ ከረረ። ሙሳ በመገረም ለምን ፀሀዩ እንደከረረ ጌታቸውን ጠየቁ። አላህም ለአርባ አመታት ሲያምፀው የኖረ ባርያ በመካከላቸው እንዳለና እሱ ካልወጣ ዝናቡ እንደማይዘንብ ይነግራቸዋል። ሙሳም የተነገራቸውን ተናገሩ። አላህም ድምፃቸው ለሁሉም እንዲሰማ አደረገ። ይህ ወንጀለኛ ባርያ ወደ ቀኝ ወደ ግራ ቢመለከት የሚወጣ ሰው አጣ። ነገሩ የእርሱው ጉድ መሆኑ ገባው። ለአርባ አመታት የሰራውን ያውቃል። ቢወጣ ራሱን ማወረድ ሆነበት። እንዳልሰማ አይሆን ነገር በእሱ ወንጀል ምክንያት ሀገሩ በድርቅ ተመቷል። እናም ወደ አላህ ከልቡ ዱዓ ማድረግ ጀመረ። የሰራሁትን ክፋት አውቃለሁ፣ ወዳንተ ተመልሻለሁና ማረኝ አለ። ወዲያው ሰማዩ በደመና ተሞላ ዝናቡም እንደጉድ መዝነብ ጀመረ። ነብዩላሂ ሙሳ እጅጉን ተገረሙ። አላህንም «ማንም ሰው ከመካከላችን ሳይወጣ እንዴት አዘነብከው?» ሲሉ ጠየቁት። አላህም «አሁንም ያዘነብኩት አርባ አመት ባመፀኝ ባሪያዬ ምክንያት ነው። ባሪያዬኮ ወደኔ በፀፀት ተመለሰ።» ሲል መለሰላቸው። ነብዩላሂ ሙሳ ይህንን ሰው ለማየት ጓጉ። ጌታቸውንም «ጌታዬ ማነው እስኪ ልየው!» ሲሉ ጠየቁ። አላህም «ሙሳ ሆይ አርባ አመታትን ሲያምፀኝ ያላጋለጥኩትን ባርያዬን ዛሬ ወደኔ በፀፀት ሲመለስ የማጋልጠው ይመስልሀል?» ሲል መለሰላቸው። የአላህ ሸሻጊነት እና ከላይነት እዚህ ድረስ ነው።

የሙሳን ታሪክ ያስታወስኩት በሰሚራ ምክንያት ነው። በሙተነቂቧ ሰሚራ! አህመድ ሀይማኖተኛ ሴት አገኘሁ ባለላት ሰሚራ ምክንያት! ሰሚራን ሰሚር እና እኔ እናውቃታለን። በተመሳሳይ ሜዳ ተገናኝተናል። የእርሷን ኒቃብ ያየ ሰው ምን ብሎ ያስባታል? መልዓክ ትመስለዋለች አይደል? እንደእውነታው ከሆነ ግን ሸይጧን ራሱ ይደነቅባታል። ወንጀል ውስጥ በደንብ ተዘፍቃለች። እሺ ደግሞ ወደ ፈሪሀ እንመለስ .... ያቺ ሰፊ ሱሪ የምትለብሰው ..... ፀጉሯን በከፊል የምትከፍተው .... ፈሪሀ! ሰው ሲያያት ምን ትመስላለች? ጨዋ ያልሆነች? ግን ጨዋነት በልኳ የተሰራ .... ህጓን ለባሏ የሰጠች ሴት ናት .... ፈሪሀ! ዲኗ ላይ ጠንካራ ባትባልም ወንጀል ራሱ ምን እንደሆነ አታውቅም። ሙተነቂቧን ሰሚራ እና ባለሱሪዋን ፈሪሀ ብናቀርብላችሁና ከሁለቱ ጨዋ ማን ይመስላችኋል ብንል ማንን ትመርጣላችሁ? አብላጫው ኒቃብ የለበሰችውን ይመርጣል። ግን የተሳሳተ ምርጫ ነው። የሰው ስብዕና በልብሱ አይለካም። ልጅ ሳለሁ ኒቃብ እና ጅልባብ የሚለብሱ ሴቶች በሙሉ መልዓክት ይመስሉኝ ነበር። ግን አይደሉም። አድገን ተማርነው .... አይደሉም። ከመካከላቸው ሱሪ ከሚለብሱት እኩል ወንበዴ የሆኑ ሴቶች አሏቸው። ኒቃብን ተሳደበ የሚለኝ ማንበብ የተሳነው ልበ–እውር እንዳይመቸው ሀሳቤን ለመሰረተ ትምህርት ተማሪዎች በሚገባ ቋንቋ ልተንትነው። ሰውነትን በአግባቡ መሸፈን የአላህ ትዕዛዝ ነው። ሊደረግም ይገባል። ጥያቄው ሰውነትን በመሸፈን ማን ይበልጣል ከሆነ ሁሉም ሰው ኒቃብ እና ጅልባብ የለበሱትን በማያሻማ መልኩ መምረጥ ይችላል። አሁን ጉዳዩ የልብ ነገር ነው። ወንጀል .... የአላህን ድንበር መተላለፍ! ኒቃብ ለብሰው አላህን ከመወንጀል ዝንጉ የሆኑ አሉ። ልክ እንደዛው ሱሪ ለብሰው የአላህን ድንበር ከመተላለፍ ዝንጉ የሆኑ እልፍ ናቸው። ግን ደግሞ ለብሰዋልና ፃድቅ ናቸው፣ ኢማን እና ኢልም ሞልቷቸዋል ብለህ ስትጠብቅ የወንጀል ቃኢዳ የሚያቀሩህ ኒቃቢስት እና ጅልባቢስት ሴቶች ተበራክተዋል። ልብሱን መደበቂያ ያደረጉ አረሞች እየበዙ ነው። በዚህ ምክንያት ሁሉንም መፈረጅ አግባብ አይደለም። ግን ሰውን በለበሰው ልብስ መመዘን አቁሙ! ሱሪ ከምትለብሰዋ እና ኒቃብ ከምትለብሰው አላህን የሚፈራውን የሚያውቀው አላህ ነው። ልብሱ ሰርተፍኬት አይደለም። የአላህ ሲትር ባይኖር ልብሱ ከላያቸው እየተገነጠለ የሚበንባቸው ሴቶች ቁጥር ቀላል ባልሆነ ነበር።  ሁሌም ጌታችሁን ስለ ሸሻጊነቱ አመስግኑት።

ከስራ እንደወጣሁ ከሰሚር ጋር ተገናኘሁ።
እንዳየኝ «አንተ ግን ባለጌ ነህ የምር!» አለኝ።
«ደግሞ ምን አጠፋሁ?»
«ትናንት የዳርከውን ልጅ ምን ሆነ ብለህ አታይም?»
«እና ልንሄድ አይደል?»
«በጠዋት ነበራ መሄድ የነበረብን! አሁን አስራአንድ ሰዓት አለፈ እኮ!»
«አሪፍ ሰዓት ነው ባክህ! ወይስ አህሜ ባነነ አልባነነም የሚለው አንገበገበህ?»
«ተወው ባክህ መጀመሪያ አላማከረኝ ምን አገባኝ!»
ወደ አህሜ የጫጉላ ሆቴል ነዳን። ትልቅ ሆቴል ነው። ወደ ክፍሉ ስንደርስ መጥሪያ አጮህን። በሩ ተከፈተ። ሰሚራ ነበረች። ሰፋ ያለ አባያ ለብሳ ፊቷን በሂጃብ ሸፍናዋለች።

ስነ-ፅሁፍ

22 Aug, 19:38


«ፉዬ .... ተነሳህ?»
አይኖቼን ገልጬ በመዳፌ ጠረግኩ። አልጋዬ ላይ አንፀባራቂ ውበት ተቀምጧል። የምወደው ነብስ! የኢክራም!
«ኢኩዬ .... » ሳብ አድርጌ አቀፍኳት።
«ረፈደ እኮ .... ስልክህም ዝግ ሆነብኝ።»
«ሰርግ ላይ ከተጠለፈ ብለሽ ነው?»
ሳቀች። ከአልጋው ላይ ተነሳሁ። ግንባሯን ስሜ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባሁ።
«ስማ ቶሎ ታጥበህ ውጣ ..... የምናወራው ነገር አለ እሺ!»
ታጥቤ ስጨርስ መርጣ አዘጋጅታልኝ የነበረውን ልብስ ለበስኩ። ቁርስ እየበላን በጠዋት አክንፎ ያመጣትን ወሬ ጀመረች።
«ፉዬ .... »
«ወዬ .... »
«ትናንት ስፅፍልህ የነበሩትን ሚሴጆች አየሀቸው እንዴ?»
«አላየኋቸውም። ደከመኝ እኮ ትናንት!»
«ገብቶኛል። ስልክ ሳታነሳ ስትቀር እንደደከመህ ገብቶኛል።»
«ምን ነበር የላክሽልኝ?»
«ትናንት እኛ ቤት የቤተሰብ ስብሰባ ነበር። ስልህ በእኔ እና ባንተ ጉዳይ ማለት ነው።»
«ብሔሬን ስትጠይቂኝ ገምቼያለሁ።»
«ስላንተ እኔ የማውቀውን ያህል ለአባቴ አስረዳሁ። አባቴ ደግሞ ስለምትተዋወቁም ለተሰበሰቡት የቻለውን ያህል ስላንተ ተናገረ። ሁሉ ነገርህን ወደውት ነበር። ግን በብሔርህ ደስተኛ አይደሉም!»
«በቃ እንደዚያ ከሆነ ወሳኝ ኹነት የሚሰራ ሰው አውቃለሁ። ስልጤ አስብለዋለኋ!» ሳቅን።
«ትቀልዳለህ አይደል!»
«እሺ ይኸው ልኮሳተር .... እንዴት ብሔሬ ደስ አይላቸውም?!»
«ከዚህ በፊት አጎቴ ቤት ትግሬ አማች መጥቶ ነበር። ይመስለኛል አልወደዱትም። አስቀይሟቸዋል። አፋትተዋቸዋል እንደውም! እና ድጋሚ የምናፋታው ትዳር ውስጥ ልጃችንን አንከትም አሉ። አባቴ እንደሚያውቅህና ጥሩ ሰው እንደሆንክ ተሟገተ። ግን አያቶቼም አጎቶቼም እምቢ አሉ።»
«እንዲህ እንደሙዚቃ አለስልሰሽ የምትነግሪኝ የትዳራችንን መከልከል ነው?»
«እነሱ ከለከሉ አልከለከሉ! እኔና አንተን ከመጋባት ማንም አያግደንም!»
«ምን ማለት ነው?»
«አባዬ ይወድሀል። እሱን ኒካህ ብቻ እንዲያስርልን ጠይቄዋለሁ። አያቶቼ ከተደረገ በኋላ ይረሱታል።»
«ምን ማለት ነው?»
«ይዘኸኝ ጥፋ! አባቴን በድብቅ እንጠራውና ተጠልፋለች ስማችን ከሚጠፋ ኒካህ ይታሰር ብሎ እንዲነግራቸው እናደርጋለን። ያው ካሳ ምናምን ትከፍላለህ!»
«እኮ ከተማ አድጌ በዚህ ዘመን ሴት ልጥለፍ?»
«አትጠልፈኝም እኮ እናስመስላለን እንጂ!»
«እሺ ካልሽ ምን አደርጋለሁ። እና መች ነው የምትጠለፊው?» ሳቅኩኝ።
«ልብስ ይዤ ልምጣ ቤት ልሂድና! ከዚያ የሆነ ቦታ ትደብቀኛለህ!»
ባላምንበትም ተስማማን። ስራ ቦታ ሄዳ ማስተካከል ያለባትን ጉዳዮች እንደጨረሰች ቤት ሄዳ ልብሷን እንደምታመጣ ነግራኛለች። ቁርስ በልተን ሁለታችንም ወደ ስራችን ሄድን።
ዙሪያ ጥምጥሙ ደብሮኛል። ለምን ግን? 

ይቀጥላል ....
.
.
.
https://t.me/amharicfiction

ስነ-ፅሁፍ

22 Aug, 19:38


Fuad Muna (Fuya):
የልብ ነገር
ክፍል አስራስምንት
(ፉአድ ሙና)
***

ቻው ቻው
ቻው ብዬሻለሁ፣ ልቤ ተሰብሮ፣
ጥልፍልፍ ያዘን፣ ከመኖር አብሮ።

ቻው ቻው
የልቤ አስኳል፣ የፍቅር ስሙ፣
እንደገፋሁሽ፣ ሌሎች አይስሙ።

ቻው!

***
ጠንካራ እና ቁጡ የሚመስሉ ሰዎች በብዙው እንደሚመስሉት አይደሉም። በህይወታቸው ስስ በመሆናቸው ያሳለፉትን ስብራት ላለመድገም ጠንካራ እና ቁጡ በሚመስል ገፀ–ባህሪ የተደበቁ ሚስኪኖች ናቸው። እኔም ድጋሚ «ላለመውደቅ» የተዋረደልኝን የፈሪሀን ንግስና ዙፋን ገፋሁ። ጠንካራ እመስል ነበር። ግን ውስጤ ደምቷል። ውስጤ አንብቷል። ሰሚር «ጠንካራ ሆነሀል!» አለኝ። ጥንካሬ ራስን መበደል ነው? እኔንጃ! ቀፋፊ ውሳኔ በህይወቴ ላይ የወሰንኩ መስሎኛል። ውስጤን ኢክራምን ስታገኝ እንዳልተፈጠረ ትረሳዋለህ እያልኩ እያባበልኩት ነው። ድጋሚ ዥዋዥዌ መጫወት አልፈለግኩም። እስኪ ደግሞ የውሳኔዬን ገፈት ልቅመስ! ማንም ላይ የማላላክከውን የውሳኔዬን ውጤት ልኑር! ሁሉም የሚመስለውን አለመሆኑ ይገርመኛል። ጠንካራነት ማለት የተደበቀ ልፍስፍስነት ማለት ነው። በሁሉም የህይወት ዘርፍ ከሰው የምንሸፍነው ማንነት አለን። የምንመስለው ግን ያልሆንነው ..... የሆንነው ግን የማንመስለው ብዙ እኛነት አለን። በሰዎች ላለመፈረድ በራሳችን ላይ የምናሰምራቸው ሰቅጣጭ መስመሮች አሉ። ሲጢጢጥ የሚል ድምፅ ያላቸው .... በዙሪያቸው ደም የሚያወጡ መስመሮች! መጥፎ ብቻ ናቸው ለማለትም አያስደፍሩም! የልባችን ነገሮች .... የልባችን መሻቶች ናቸው!

የውበት ሙዳዬን .... የፍቅርን ሀሌታ .... ስሜ ተሰናበትኩ .... አዳማ በማታ .... ተነዳ መኪናው .... ጉዞው ተጣደፈ .... የሰሚር ንግግር ከጆሬዬ አረፈ። ፐ ገጠምኩ። ለታመመ ሰው ቃላትም ያዝናሉ። ግጥም የማይችል አፍቃሪ እንኳን ግጥም የሚገራለት ቃላት ስለስብራቱ ቢያዝኑለት ነው። አሊያም ለእኛነታችን እጅጉን የምንቀርበው ባዘንን እና በተሰበርን ወቅት ይመስለኛል። የተሰበረ ልብ በእርግጥ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለጌታውም ይቀርባል። እይታዬን ወደ መንገዱ እንዳደረግኩ ሰሚርን ጠየቅኩት።
«ሰሚራ ምን?»
«ሰሚራ የአህመድ ሚስት!»
«አወቅኳት! ምንድነው ያረጋገጥከው?»
«ሚስቱ መሆኗን!»
«ይኼን ቀልድ ለመቀለድ ነው እስካሁን ልቤን የሰቀልከው?»
ሳቀ። ስቆ ትንሽ እንደቆየ በረዥሙ ተነፈሰ።
«እህቷ ከጎኔ ተቀምጣ ነበር የዋልነው!»
«በነገራችን ላይ የፈሪሀ ጓደኛ ናት!»
«ገብቶኛል። እህትየው ስልኳን መኪናው ውስጥ አስቀምጣው ወርዳ ነበር።»
«እና .... »
«እናማ .... የስልኳ wallpaper የራሷ እና የእህቷ ፎቶ ነው።»
«እሺ .... »
«ስልህ ሰሚራ ያለኒቃብ ማለት ነው።»
«እና .... »
«እናማ ሰሚራን በደንብ አውቃታለሁ። አንተ ራሱ ታውቃታለህ።»
«ያለ ኒቃብ?»
«አዎ .... ኒቃብ አትለብስም! እህቷን ራሱ ጠየቅኳት!»
«ምን ብለህ?»
«መች ነው የለበሰችው ብዬ ነዋ! ለእነሱ ራሱ እንግዳ እንደሆነባቸው ነገረችኝ። እስከቅርብ ጊዜ ድረስ እንደማትለብስ ነው የሚያውቁት!»
«ማሻአላህ! አህመድ በዚህ ያህል ተፅዕኖ መፍጠሩ ደስ ይላል።»
«አይደል .... »
ሰሚር ዝም አለ። ዝምምምምምም! ከሰላሳ ደቂቃ በላይ ዝም አልን።
የሰሚርን ታፋ ቸብ እያደረግኩ «ተጫወት እንጂ ሀቢቢ!» አልኩት።
«ፉዬ ቃል ትገባለህ? ሚስጥር ታደርገዋለህ?»
«ምኑን?»
«አሁን የምነግርህን!»
«እሺ ንገረኝ!»
«ሰሚራን አውቃታለሁ! ማለት የሆነ ጊዜ አብሬያት አሳልፌያለሁ ማለቴ ነው።»
«ግልፅ አድርገው!»
«ሀዋሳ አብረን የሄድን ጊዜ አስታወስክ?»
«ከኢክራም ጋር?»
«አዎ ከእኔ ጋር የነበረችውን ልጅ አስታወስካት?»
«አዎ! በደንብ አስታውሳታለሁ። አብራችሁ ስትዋኙ ምናምን!»
«የአህመድ ሚስት ሆና የመጣችው እሷ ናት!»
«ምን? እንዴት? ካንተ ጋር መች አቆማችሁ?»
«ከእኔ ጋር ፍቅረኛ አይደለንም። የሆነ ስትፈልግ ተደዋውለህ ፈታ የምትለው ሰው የለም? እንደዚያ ነበርን!»
«ለመጨረሻ ጊዜ መች አገኘሀት?»
«የዛሬ ሳምንት! ታምናለህ? የዛሬ ሳምንት!»
«ኒቃብ ለብሳ ነበር?»
«አትቀልድ ‘ባክህ!»
«ካንተ ጋር ፍቅረኛ ካልሆናችሁ ግን ኖርማል ነው አይደል! ስልህ የኒቃቡ ነገር ነው እንጂ!»
«ምኑ ነው ኖርማል?»
«አህመድን ማግባቷ!»
«አውቀህ ነዋ!»
«ማለት?»
«ከእኔ ጋር ፈታ ማለት ስልህ በምን እንደሆነ አይጠፋህም!»
«ድንግል አይደለችም?»
«ድንግል የሚባለው ሰፈር ራሱ አይደለችም። እኔ ሳውቃት ጀምሮ አልነበረችም። ከእኔ ጋር ደግሞ ብዙ ጊዜ ሆኗል። ደግሞ ሀዋሳ እንኳን ካስታወስክ አንተ ከኢክሩ ጋር .... እኔ ከእሷ ጋር ነበር የምናድረው!»
«ወይኔ አህሜ ....»
ትንሽ በዝምታ ተዋጥን። የሰሚር ቤት በር ፊትለፊት መኪናዋን አቁመን ማውራት ጀመርን።
«እና አህሜ ድንግል አለመሆኗን አውቆ እየተጣሉ ይሆናላ እስካሁን!» አልኩት።
«መቼም አያውቅም!»
«እንዴት?»
«እንኳን እሱ አንተ ራሱ የምታውቅባት አይመስለኝም።»
«አልገባኝም!»
«ልጅቷ በጣም Player ናት! ታስመስልለታለች! ደሙንም በሆነ መልኩ fake ታደርገዋለች። አህሜ ደግሞ የአላህ ሰው ነው። አልሀምዱሊላህ አገኘሁት ይላል።»
«ለምን ግን አህመድን?»
«የገመትኩት ነገር አለ። ግን ደግሞ አሁን እሱን አልነግርህም።»
«እና አፋችንን እንዝጋ? ወይስ እንንገረው?»
«መጀመሪያ ፍላጎቷን እንወቅ! የእውነት ወዳው ከሆነ አላህ የሰተረውን እኛ ምንም አያገባንም! አላማዋ ሌላ ከሆነ ግን እርግጠኛ ስንሆን እንነግረዋለን።»
«አይ ሰሚሬ .... በቃ ሴቶቹን ሰሚር የነካቸውና ያልነካቸው ብለን በሁለት እንክፈል? ከባድ ሰው ነህ¡»

ከሰሚር ጋር ተለያይተን ወደ ቤት ገባሁ። ስልኬ ላይ የተጠራቀሙ የኢክሩ ያልተነሱ ጥሪዎች እና ያልተመለሱ መልዕክቶች ሞልተዋል። የኢክሩን ጥሪ ለመመለስ ሳመነታ ፈሪሀ ደወለችልኝ።
«ፋሚዬ .... »
«ፌሪዬ .... »
«ሰላም ገባችሁ?»
«አዎ ሰላም ገብተናል። አንቺስ ድካሙ እንዴት አድርጎሻል?»
«ደህና ነኝ። አብረን ስለዋልን በጣም ደስ ብሎኛል።»
«እኔም ፌሪዬ ....»
«በል በቃ ደክሞሀል አልያዝህ! ደህና እደርልኝ!»
«ደህና እደሪልኝ!»
«እምጷ!» ሳመችኝ። ድምፁ ከጀነት ይመስላል።
«እምጷ!» ተገድጄ ሳምኳት። ስልኩ ተዘጋ።
ፈሪሀ በጣም ጥሩ እየሆነችልኝ ያለችበት ምክንያት አልገባህ ብሎኛል። እልኸኛዋ ፈሪሀ ስወስን እንደዚህ ለስላሳ መሆኗ በጣም ገርሞኛል። ምናልባት ማዘናጊያም ይሆናል። ከኢክራም ያገኘውን ለስላሳነት ብሰጠው ይመለሳል ብላ አስባ ይሆናል።
የኢክራምን ስልክ ለመመለስ አሰብኩኝ ግን ደከመኝ። ካወራን ለረዥም ደቂቃ ማውራት ይኖርብናል። ጠዋት ባወራት የሚሻል ስለመሰለኝ እንደደከመኝና ጠዋት እንደምደውል የሚገልፅ መልዕክት ላኩላት። ስልኬን ዘግቼ ቻርጅ ሰካሁትና ተኛሁ። በጣም ደክሞኝ ነበር። በቀጣዩ ቀን ጠዋት ራሴ የለመደው አለንጋ ጣት ፀጉሬን ሲዳብሰው ከእንቅልፌ ባነንኩ። አፍንጫዬ የሽቶ ጠርሙስ ውስጥ የተነከረ መሰለኝ። ውብ ጠረን። ለስላሳ ድምፅ!

ስነ-ፅሁፍ

21 Aug, 16:02


ይህ ጥያቄ ጥያቄ ሆኖ ባልቀጠለ

ነበር። አስመሳይ በዝቷል። 

የመኪናችንን ወንበር አስተካክለን የሙሽራውን መኪና መከተል ጀመርን። ዙሪያ ጥምጥም ተሽከርክረን አህሜ ቤት ደረስን። በአንድ ቀን የተሰናዳ ድግስ አይመስልም። የእናት እጅ ይባረክ። የሴቶቻችንን መዳፍ ቁርጥማት ይሽሸው! ብፌው በአይነት በአይነቱ ተደርድሯል። ሰው መች እንደተጠራ ባላውቅም ጢም ብሏል። ሙሽሪት እና ሙሽራውን አጅበን ወንዶችም ሴቶችም ወደተያዘልን ቦታ ተበተንን። ሰሚሬ ከአጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ።
«ስማ ፉዬ .... »
«እሺ አንበሳው .... ዛሬ መቸስ ሴቱ በእጅህ ነው¡»
«‘ባክህ ባለተከታይ ብቻ ነው ያለው!»
«የቅድሞቹስ?»
«አንዷ ብቻ ናት ሌሎቹ አግብተዋል።»
«አንድ ይበቃሀል¡»
«ትንሽ ግራ ያጋባኝ ነገር ተፈጥሮ እኮ .... ልንገርህ አልንገርህ ብዬ እያሰብኩ ነው።»
«ምንድነው?»
«ቆይ እስኪ ላረጋግጠው በደንብ እና በኋላ እነግርሀለሁ።»
«በቃ ልብ ሰቀልክ?»
«ኧረ ሰቀላ አይደለም ..... ብቻ በኋላ እነግርሀለሁ።  ባይሆን ከፈሪሀ ጋር ምንሼ ሮማንስ?»
«ዝም ብለን ነው ባክህ!»
«እኔ ደግሞ ድጋሚ ዥዋዥዌ አምሮሽ ከሆነ ብዬ¡» ሳቀ።
ሰሚር ተነስቶ ሄደ። ተበላ ተጠጣ። ሙሽራዎቹን አጅበን ወደተያዘላቸው ሆቴል በጊዜ አደረስናቸው። አህሜን ሜዳውም ፈረሱም ያው አላህ ይሁንህ ብለን ከሩሙ ወጣን። ሰዓቱ 1:00 ሆኗል። ሌላ ሰርግ ቢሆን ሙሽራ አራት ሰዓት ድረስ ክፍሉ ባልገባ ነበር። ልጁ ብዙ ነገር ስለማይመቸው ዝም ብለን ከምንፋጠጥ ከአዲሷ አሻንጉሊቱ ጋር ይፋጠጥ ብለን በጊዜ አሰናበትነው። 
ከሩሙ ወጥተን የቀሩትን የሷን አጃቢዎች ወደየቤታቸው መበተን ጀመርን። ስራውን የሚሰራው ሰሚር ነው። የፈሪሀን መኪና በሴት ሞልቶ በየፌርማታው ያራግፋል። ፈሪሀ ከጎኔ ተቀምጣለች። አዳማ እኔ ላደርሳት ተስማምተናል። ሴቶቹን አራግፎ ሲጨርስ ወደ አዳማ ነዳን። እኔና ፈሪሀ አንድ ላይ፤ ሰሚር ደግሞ የፈሪሀን መኪና ይዞ ከኋላ ይከተለናል። አዳማ ገባን። ወደ ሰፈሯ እንደደረስን ቆምን።
«ፋሚዬ ....»
«ወዬ ውዴ ....»
«አመሰግናለሁ እሺ!»
«ለምኑ?»
«ስለሸኘኸኝ ነዋ!»
«ግዴታዬ ነው!»
«ለምን?»
«ስለምወድሽ!»
«በቃ አትመልሰኝም አይደል?»
«አዎ ፈሪሀዬ ነገርኩሽ አይደል!»
«ውሳኔህን አከብራለሁ። We will keep in touch.»
እቅፍ አደረግኳት። እቅፍ .... እቅፍቅፍ! ከንፈሬን ሳመችኝ። ደገመችኝ። ተቃቅፈን። ተሳስመን ..... ደግሞ በብዙ ተላቅሰን .... ብዙ ሶፍት ሰጥቻት .... ወረደች።
ተመልሳ እየሮጠች መጥታ ሳመችኝ። ትከሻዬን በጥፍሮቿ ጭምቅ አደረገችኝ።
«ደህና ሁንልኝ እሺ!»
«ደህና ሁኚ!»
በህይወቴ እንደዚህ ጠንክሬ አላውቅም። ውስጤ እያለቀሰ ነው። ፊቴ ግን ጥሩ ትወና ተወነ። የመኪናዋን ቁልፍ ሰሚር ሰጥቷት ወደኔ መኪና መጣ። ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ጀመርን።
ሰሚሮ «ተገላገልና?» አለ።
«ኧረ ቢስሚላህ ተገላገልን ይገልፀዋል እንዴ! እሱ እዛ ይታገል እኛ እንተኛ!»
«ይታገል ስትል አስታወስከኝ። ቅድም የሆነ ነገር እነግርሀለሁ አላልኩህም?»
«ላረጋግጥ ያልከው?»
«አዎ አረጋገጥኩ እኮ!»
«በጣም ግራ የሚገባ ነገር ተፈጥሯል።»
«ምንድነው?»
«ሰሚራ!»

ይቀጥላል ....
.
.
.
https://t.me/amharicfiction

ስነ-ፅሁፍ

21 Aug, 16:02


Fuad Muna (Fuya):
የልብ ነገር
ክፍል አስራሰባት
(ፉአድ ሙና)
***

ሰጥቼህ ነበር
ከክብር መንበሬ፣ መሬት ወርጄ፣
የሀሜት ዱላን፣ እኔው ጋርጄ።

ለምኜህ ነበር
የወደቅንለት፣ ይቃናል ብዬ፣
ሰይሜ አንተን፣ ብዬህ ጌታዬ!
በል ደጉን ምረጥ!

***
አማራጭ መሀል መውደቅ ከባድ ነው። የመጎተት ስሜት አለው። አለፍን ያልናቸውን ፈተናዎች በድጋሚ መፈተን ይረብሻል። ፈሪሀን አልፌያታለሁ .... የፈሪሀን መዝገብ ዘግቼያለሁ ብዬ አስቤ ነበር። ግን እንኳን ላልፋት እግሬ ካለበት እንዳልተወሰወሰ ተረዳሁ። እንደናፈቅኳት እንኳን የገባኝ በራቀችኝ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ደግሜ አይኗን ሳይ ነው። ልቤን የተሰማውን ስሜት ብገልፀው በዳናው የተራመደ እንጂ አይረዳውም። የምትወዱት ሰው የላብ ጠረን እንኳን ምን ያህል ይናፍቃል መሰላችሁ። ፈሪሀን ሳያት የአዕምሮዬ የትዝታ በር ተበረደ።  ፈገግታዋ፣ ንጭንጯ፣ አልሸነፍ ባይነቷ፣ ተለማማጭነቷ፣ አፍቃሪነቷ፣ የእቅፏ ሙቀት እንኳን ሳይቀር ትዝ አለኝ። እወዳታለሁ። ናፍቆት ከባድ ነው። በጣም የለመዳችሁትን መናፈቅ ደግሞ በእጥፉ ያማል! የፈሪሀ ድምፅ ጭንቅላቴ ላይ ያቃጭላል። ግን ደግሞ ከራሴ ጋር የገባሁትን ቃል ማክበር አለብኝ። መወላወል ያስከፈለኝን ዋጋ ደግሜ መክፈል አልፈልግም። መወሰን ከባድ ነው። መወሰን ያስርባል።

የፈሪሀ ውብ ጣቶች ከንፈሮቼ ላይ ናቸው። እየሳምኳቸውም ይመስለኛል። እንዳልናገር ተይዤባቸው ነበር። እጇን ከከንፈሬ ላይ አንሸራተተችው። በደንብ መተንፈስ ጀመርኩ።
«እና ፋሚዬ?» ውብ አይኖቿ ተቁለጨለጩብኝ።
ዝም አልኩ። በህይወቴ ጭንቅላቴ በዚህ ፍጥነት ያሰበበትን ቀን አላስታውስም። ነርቮቼ እስኪወጠሩ አሰብኩ። ራሴን ያመመኝም መሰለኝ።
«ፌሪዬ ... »
«ወዬ ... »
«እወድሻለሁ። በጣም እወድሻለሁ።»
ፊቷ ፍካት ለበሰ። እጄን ሳመችው። እጄን ወደ መሪዬ እየመለስኩ ቀጠልኩኝ።
«ግን ፌሪዬ .... »
«ወዬ? ምን የኔ ጌታ?»
አንደበቴ ተሳሰረብኝ። ከንፈሮቼ ቀጥዬ በማወራው ጉዳይ ላይ ያልተስማሙ ይመስል አልተባበር አሉኝ። ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ።
«እወድሻለሁ ግን አልመልስሽም ፌሪዬ! አዲስ ህይወት መገንባት እፈልጋለሁ። አንቺም አዲሰ  ህይወት መስርቺ!»
«የመጨረሻ ውሳኔህ ነው?» አይኗ በእንባ ሞልቷል።
«አዎ ውዴ ..... ከጥልቅ መውደድ ጋር .... መለየትን መርጫለሁ።»
በዝምታ ቆየን።
«ችግር የለውም። እንግዲህ እጣፈንታችንን መከተል ነው።» በሶፍት አይኖቿን አደራረቀች።
ስልክ ተደወለልኝ። የመኪናዬ ስክሪን ላይ «E❤️» የሚል ስም ወጣ። ፌሪ ፈገግ ለማለት እየሞከረች «አንሳው ከፈለግክ!» አለች።
መልሼ እደውላለሁ ከሚል የፅሁፍ መልዕክት ጋር ስልኩን ዘጋሁት።
«ለምን አላነሳኸውም?»
«ምናልባት እኔና አንቺ ዛሬ የምንገናኘንበት የመጨረሻ ቀን ቢሆንስ?»
«እና?»
«ልሸርፈው አልፈልግም። ካንቺ ጋር መሆን እፈልጋለሁ።»
«ወደ ፊት አንገናኝም?»
«ኧረ እንገናኛለን ምን ችግር አለው?»
ፈገግ አለች። ከአይኗ እንባ ፈሰሰ። ሶፍት አቀበልኳት። እየወጉ ፋሻ እንደመስጠት አይነት ስሜት አለው። የህመሟ መንስኤ እየሆኑ ሀኪሟም ለመምሰል መጣር .... የሚጋጭ ይመስለኛል።
«ካገባሀት ግን ባል ሁንላት። ወደ ሌላ ሴት በፍፁም አትሂድ። ከአካል በፊት ልብ ይሄዳል። ልብህን ያዘው!»
«ልትገያት አልነበር?» ምክሯ ገረመኝ።
«አዎ ግን አልተሳካም። እሷ አሸንፋለች። እንደ ጥሩ ተሸናፊ ላንተ ህይወት ስለማስብ የሚጠቅምህን ልምከርህ ብዬ ነው። ለእሷ አስቤ አይደለም።»
ዝም ብለን ቆየን።
«ፋሚዬ?»
«ወዬ?»
«አንዴ ለመጨረሻ ጊዜ ልቀፍህ? እስኪ እቀፈኝ!»
የመኪናዬን ወንበር ወደ ኋላ አንሸራተትኩት። እሷም ተመሳሳዩን አደረገች። ድሮ መኪና ውስጥ ሆነን ሳቅፋት እንደምታደርገው ጫማዋን አወለቀች። እግሮቿን ወንበሯ ላይ ሰቅላ ደረቴ ውስጥ መሸገች። እቅፍ አደረግኳት። እቅፍ .... ጭምቅ .... ወደ ውስጤ አልከታት ነገር! የልብ ምቴ ይሰማኛል። እያለቀሰች ነው። እንባ እንባ አለኝ።  ወይኔ ፌሪዬ! በየመሀሉ ከእቅፌ እያወጣሁ እንባዋን እጠርጋለሁ። ለሚያየን ሰው የምንጋባ እንጂ የምንፋታ ጥንዶች አንመስልም።

ሰሚር ወደኔ መኪና ሲመጣ አየሁ። ፌሪዬን በእጄ ፀጉሯን ዳብሼ ከደረቴ አስነሳኋት።
የፈሪሀን ያለቀሰ ፊት አይቶ «አጉል ሰዓት መጣሁ እንዴ?» አላት።
«ኧረ ችግር የለውም!»
«ሰዎቹ እኮ አሳደሩን በናትህ!»
«ምግቡ አልደርስ ብሎ ይሆናል።»
«እሱማ እንደዚያ ነበር! አሁን ግን ተዘጋጅተዋል። ደውለውልኝ ነበር።»
«እና እንንቀሳቀስ?»
«አይደለም ሆቴል የት ቡክ እናድርግለት ለአህሜ? ድምፅ እስኪያስጠፋ ሆቴል ቢቆይ አይሻልም?» ሳቅን።
«እሱማ ሆቴል ቢያድር ይሻላል። ቤቱም ደግሞ ግርግር ስላለ አይሆንም!»
«ችግሩ ምን መሰለህ? መጠጥ ያለበት ቦታ አላድርም አለ። ከተማው ላይ መጠጥ የሌለበት ደህና ሆቴል ታውቃለህ?»
«እሱ መጠጡ ጋር ምን አደረሰው? አርፎ ሩሙ አይተኛም?»
«ህንፃው ውስጥ አንድ የመጠጥ ብርጭቆ ካለ አላድርም አለኝ።»
«የወስላ ሆቴል መፈለግ ነዋ!»
ፌሪዬ ስልኳ ላይ የአንድ ሆቴል አድራሻ እያሳየችው «ይኼ ሆቴል በጣም ምርጥ ነው። መስጂድ ሁሉ አለው። በጣም ሀላል ነው። ያለ ኒካህ ወረቀት አያስገቡም። ወረቀቱን ይያዙት የቅድሙን!»
«ፈሪሀ የመፍትሔ ሰው!» ሰሚር እየሳቀ ስልኳን ያያል!
«በዚህ ቁጥር ደውለህ በሚቆይበት ቀን ያህል book አድርግለት።»
«አመሰግናለሁ። በቃ አሁንማ ጭንቀት ቀለለ።» ብሎ እየፈጠነ ወደ ሙሽራዎቹ መኪና ሄደ። ፌሪዬ ተመልሳ ደረቴ ላይ ተጋደመች።

አዲስ አበባ ግን ትገርመኛለች። በርካታ ሙስሊም ባለሀብቶች ያሉባት ከተማ ናት። የሙስሊም ሆቴሎች ግን በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ሙስሊሙ ከተዝናኖት ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች ሳይወድ በግድ ከእምነቱ ጋር የሚጣረሱ ድርጊቶች የሚፈፀሙባቸው ሆቴሎችን ለመጠቀም ይገደዳል። ወንዱ እንኳን ብዙም አይከብደውም። ሴቶች ግን በጣም ያሳዝናሉ። መዝናናት ከፈለጉ አፈንጋጭ መሆን አለባቸው። ካልሆነ ተመልካች ከመሆን የዘለለ ድርጊት መፈፀም አይችሉም። አዲስ አበባን የምታክል ከተማ ለሴቶች ብቻ የሚሆን የዋና ገንዳ የላትም። መዋኘት የፈለገች ሙስሊም ሴት ያላት ምርጫ ተራቁታ ከወንድ ጋር መዋኘት፣ «የሙስሊም ሴቶች የዋና ልብስ» ለብሳ ሁሉም በከፊል ቅርጿን እያያት መዋኘት ወይም አለመዋኘት የሚሉ ናቸው። ሀይማኖታቸው እጅጉን ግድ የሚሰጣቸው ሴቶች ምርጫ ደግሞ አለመዋኘት የሚለው ነው። ስለዚህ በመመልከት ብቻ ለመዝናናት ይገደዳሉ። የሴቶቻችንን ችግሮች ለመቅረፍ በጣም ዳተኛ እንደሆንን ይሰማኛል። መስጂድ እንኳን ሲገነባ የሴቶች መስጂድ «ከማይኖር እንደምንም» በሚል መሪ ቃል የሚገነባ ይመስላል። ከጥቂት መስጂዶች በስተቀር የሴቶች መስጂድ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የተሰራ ነው። መሟላት የሚችሉ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ለማሟላት እንኳን ኮሚቴዎች ዳተኝነት አለባቸው። የሙስሊም በሚል ስም ሌላው የሚታወቀው የሙስሊም ምግብ ቤት ነው። ስማቸው የሙስሊም ምግብ ቤት ሆኖ ኒቃቢስት ሴቶች ለመመገብ ሲመጡ ፊታቸውን በነፃነት ከፍተው እንዲመገቡ የሚጋርዱ ምግብ ቤቶች በጣም ጥቂት ናቸው። ሴቶቹ ግራ ቀኝ አይተው ይጎርሳሉ። ምግብ ቤት ኒቃቢስት ሴት ሳይ በጣም አዝናለሁ። አንድ ምግብ ቤት ብቻ በር የሚመስል ተጣጣፊ መከለያ ለኒቃቢስቶች አዘጋጅቶ ተመልክቼ ተደስቼያለሁ። ለራሱ ጉዳይ ትኩረት መስጠት ያልቻለ ማህበረሰብ ባልቀራው ኪታብ ተከፋፍሎ ሲቧቀስ ይውላል። ስለሚስቱ እና ስለልጆቹ የሚጨነቅ ማህበረሰብ ቢኖር

ስነ-ፅሁፍ

20 Aug, 14:59


«ምንድነው?»
«ቤት ጠይቂ ብለውኝ ነው!»
«እሺ ጠይቂኛ!»
«ብሔርህ ምንድነው?»
«አዲስአበቤ!»
«አትቀልድ ባክህ! ቤት እኮ ማን ነው? ከማን ነው የሚለውን ንገሪን አሉ .... ባባ ብዙውን ተናገረ ግን ብሔርህን አያውቀውም።»
«ምን ያስፈልጋል አሁን እሱ!»
«ለአያቶቼ ያው ለፎርማሊቲ ነገር ነው!»
«ትግሬ ነኝ።»
«እሺ ፉዬ እነግራቸዋለሁ።»
«መልካም!»
«ስማማ! አንተስ ቤት ተናግረሀል?»
«እኔ ቤት አሁን ትውለድ እንጂ .... የዱር እንስሳም ባገባ ሀጃቸው አይመስለኝም¡» ተሳሳቅን።
ስልኩን ዘግቼ ማሰብ ጀመርኩ። የወንድ ልጅ ልብ ሰርከሰኛ ነው። አላህ የፈጠረውን በደንብ ያውቃል። እስከ አራት ሚስት ብሎ ገደበው። ባይገደብ ከዚያም በላይ የሚሄድ ይመስለኛል። አራት አግብቶ የሚማግጥ ሰው ሊኖር ይችላል። ሁለት ሚስት የማግባትን ጉዳይ ሴቶቻችን ተቀብለውት ቢሆን፤ ቤቴ ሳይፈርስ ሁለት ውብ ጎጆ በሰራሁ ነበር። ይህን አማራጭ ደግሞ ሁለቱም ሴቶቼ አይወዱትም።

የሴቶቹ ቤት መሰናዶ ተጠናቀቀ። የአህመድ ሚስት ነጭ ኒቃቧን ለብሳ የቤተሰቦቿን እግር ሳመች። ቤተሰቦቿ አለቀሱ። ብዙ የሴት መንጋ ለማጀብ ተከተለን። ሰሚር መኪና ያላገኙ ሴቶችን በየመኪናው እያስገባ ነው። ከእነሱ ውስጥ ቆንጆዋን ወደኛ መኪና ይዞ ለመምጣት አስቦ እንጂ ማስተናገድ ወዶለት አለመሆኑ አልጠፋኝም። መሪው ላይ ተኝቼ የመኪናዬ መስታወት ተንኳኳ። ቀና ስል ፈሪሀ ቆማለች። መስታወቱን አወረድኩት።
«መኪና አልያዙም ብዙዎቹ .... የእኔን ሰጥቻቸዋለሁ። ካንተ ጋር ብሄድ ሚስትህ ይደብራታል?»
«ግቢ ባክሽ .... ክፍት ነው በሩ!»
ገብታ ከጎኔ ተቀመጠች። እጄ ይንቀጠቀጣል።
«መኪናሽን ግን አላየኋትም!»
«አዎ የሲስተርን ነው የያዝኩት .... ያውልህ!»
«ቆንጆ መኪና ነው።»
«ማታ ወደ አዳማ መንዳቴ አይቀርም! ስለሚመሽ ከከተማ ለመውጣት የሷ ይሻላል።»
«መኪና ከፈለግሽ .... እኔ ጋር ነበር አይደል!»
«ተው አንጀቴን አትብላው።» ሳቀች። ያ ሳቅ! አስታወሳችሁት? ኡፍፍፍ ተለበለብኩ። በሳቋ ውስጥ የተደበቀውን ስብራት አላህ ያውቃል።
«የምሬን ነው። ተፋታን ማለት ተጣላን ማለት አይደለም።»
«እኔም እንደዛ እንዳይሆን ነው አብረን እንሂድ ያልኩህ።»
«አሪፍ አደረግሽ!»
ሰሚር ሶስት ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች ይዞ መጣ። እኔና ፈሪሀ ተያይተን ተሳሳቅን። ፈሪሀ መስታወቱን አውርዳ «ሂድ እዚያኛው መኪና ውስጥ አስገባቸው! ከፈለግክም አንተ ንዳው! አንተ ትሻላለህ ከእነሱ!»
«በቃ ዛሬ ቀኑ አማረለት!» ሳቅኩኝ።
«ሶስት ሴት ሁሉ ምን ያደርግላችኋል?» ትስቃለች።
«ከደሙ ንፁህ ነኝ!»
«እሱን ተወው!»
የሙሽራው መኪና መውጣት ጀመረ። ተከተልኩት።
«በነገራችን ላይ ሳልነግርህ .... ጀለቢያው አምሮብሀል በጣም!»
«ከአይኖችሽ ነው።»
«ድጋሚ ልታሰምጠኝ ነው?»
«ትሰምጫለሽ?»
ሳቀች። ሳቋ የእውነት አልነበረም። ህመም ነበረው። መልሼ አላገባት ነገር የኢክራም ጉዳይ ብዙ ሄዷል። ወስኛለሁ። ጉዞ ከኢክራም ጋር ብያለሁ። አንድ ጉድጓድ ውስጥ ሁለቴ ላለመነደፍ ከራሴ ጋር ተማምያለሁ። የናፈቀችኝ አብራኝ ስላልሆነች ነው።
«ሳልጠይቅሽ .... »
«ምኑን?»
«ከሰሚራ ጋር ምን አዛመዳችሁ?»
«ከእሷ ጋር ሳይሆን ከታላቅ እህቷ ጋር ጓደኞች ነን። መኪናዬን ሰጥቼያት የመጣሁት ለሷ ነው።»
«ሰሚር ሊጠብሳት ነዋ!»
«አግብታለች ኧረ! አራት ወልዳለች።»
«ሰሚር ይምራል ብለሽ ነው¡» ሳቅኩኝ።
ዝም አለች። ዝም አልኩኝ። ዝም ብለን ቆየን።
«ብወልድልህ ግን አትፈታኝም ነበር አይደል?»
«ለምን እፈታሻለሁ?»
«እና አሁን ለምን እድሉን አትሰጠኝም?» ኮስተር ብላ ጠየቀችኝ።
ድንገተኛ ጥያቄ ነበር።
«የሁለተኛ ሚስት ጉዳይ መስሎኝ ያጣላን!»
«ፋሚዬ!»
«ወዬ!»
«እንዳላገባህ እኮ .... አውቃለሁ!»
«ኧረ?»
«አዎ!»
«ማነው ያለሽ?»
«የት ነው ቤቷ እሺ?»
«ፒያሳ!»
«ፒያሳ የቱ ጋ?»
«እኔንጃ!»
«ቦሌ ነው ቤቷ አይደል? የቤተሰቦቿ? ኢክራም ነው ስሟ! ኢክራም በርጊቾ!»
«እንዴት አወቅሽው?»
«ፋሚዬ ሴቶች ነን እኮ .... እናጣራለን። የገባችበት ገብቼ አጣርቻለሁ። ከተለያየን በኋላ ፕሮፖዝ አደረግካት አይደል ቢሾፍቱ?»
ደነዘዝኩ። ቃላት አናውቅህም አሉኝ!
«ለምን ፋሚዬ? ለምን? በቃ ሁሉንም ስህተት ይቅር ልበልህ! እንደአዲስ Move እናድርግ! አዲስ ቤት መገንባት ቀላል አይደለም። እናስተካክለው የኛን! ንገረኝ የማትወደውን ላስተካክልልህ! Please የኔ ጌታ!»
ዝም አልኩኝ። እነአህመድ ቤት ምግብ ገና እየተሰራ ስለሆነ ብዙ መዞር አለብን። ፎቶ መነሳት በሚል ሰዓቱን አንገድለው ነገር ሰውየው አይመቸውም። ከተማው ላይ እንደ እብድ መሽከርከራችንን ቀጠልን። አንድ መናፈሻ ዳር መኪናዎቻችንን አቆምን። ሰው ወርዶ ፎቶ መነሳት ጀመረ። ሙሽራዎቹ መኪናው ውስጥ ተቀምጠዋል። እኔና ፈሪሀም አልወረድንም።
«ግን ትወደኝ ነበር?» መብረቅ የሆነ ጥያቄ!
«እንኳን ያኔ .... አሁንም በጣም እወድሻለሁ!»
«በቃ ተሳስተናል እንበል። እንመን! የትኛውም ትዳር ያለ ጥፋት አልቆመም እኮ!»
«ለኢክራም እኮ ቀለበት አሰርኩ።  አሁን ባላገባት ልቧን መስበር ነው የሚሆነው!»
«ለእቃቃ ቀለበት? የኔስ ልብ? አላሳዝንህም? አትወደኝም? እንደጥፋትህ እኮ ለማኝ እኔ አልነበርኩም መሆን የነበረብኝ! ግን ልሸነፍ፣ ጎጇችን አይፍረስ ብዬ ነው።»
«የማውቀው እንደምወድሽ ብቻ ነው።»
«መልሰኝ! እሷን ደግሞ ተዋት!»
«ቀለበት እኮ .... »
«እንዳትጨርሰው!» አፌን በእጇ ሸፈነችው። የእጇ ጠረን ደስ ይላል። ቀርባኛለች የሰውነት ጠረኗ ትዝታዬን እየጫረው ነው።
«የመጨረሻ እድል እና የመጨረሻ ጥያቄ! አሁኑኑ መልሰኝ እኔን! መልሼሻለሁ ማለት ብቻ ነው የሚጠበቅብህ! በአንድ ቃል ሚስትህ እሆናለሁ። ካልሆነ ግን በህይወትህ መቼም ደግመህ አታገኘኝም! አሁኑኑ ወስን! ከዚህ በላይ ራሴን ማዋረድ ይደክመኛል።»
ከባድ ጥያቄ ነበር።

ይቀጥላል ....
.
.
.
.
https://t.me/amharicfiction