Alif Geopolitics

@alif_geopolitics


🇪🇹 🌍 በሀገራችን ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ እና በሙስሊሙ ዓለም የሚኖሩ አዳዲስ ክስተቶች ከታማኝ ምንጮች የሚቀርቡበት ገፅ ነው ✍️

Alif Geopolitics

23 Oct, 06:09


♻️🔻🇮🇱☦️ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር በታህሳስ ወር በጋዛ ከተገደለው የእስራኤል ወታደር ዴቪድ ቦግዳኖቭስኪ መቃብር ላይ የተቀመጠውን የመስቀል ምልክት ለማስወገድ ከቤተሰቦቹ ጋር እየተደራደረ ነው። 

ይህ ፖሊሲ የእስራኤል ጦር የአይሁድ ኃይማኖታዊ አለቆች ባሳለፉት ውሳኔ ላይ የተመሰረተ ሲሆን, እሱም 'የአይሁዳዊያን መቃብር ላይ መስቀል መደረጉ ቅድስናቸውን ይጎዳል' የሚል ውሳኔ በመተላለፉ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Geopolitics

16 Oct, 17:21


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 በሂዝቦላህ እና በእስራኤል ወራሪ ጦር መካከል በአይታ አልሻዕብ - ራሚያ - ኻውዛህ ትሪያንግል ውስጥ በቀጠለው ውጊያ በትንሹ 10 የእስራኤል ጦር ሄሊኮፕተሮች የሞቱ እና የቆሰሉ የጽዮናውያን ወታደሮችን ከማዕከላዊ ሊባኖስ-ፍልስጤም ድንበር ላይ እያስወጡ ነው።

ውጊያው በአካባቢው በከባድ መሳሪያ ተኩስ እንዲሁም ለእስራኤል ጦር ከለላ ለመስጠት በሚሞክሩ የጽዮናዊያኑ ሄሊኮፕተሮች እንቅስቃሴ ታጅቦ የቀጠለ ሲሆን ወደ ሃይፋ እና "ቴል አቪቭ" ሆስፒታሎች እየተጓጓዙ ከሚገኙት ተጎጂ የእስራኤል ወራሪ ጦር አባላት የሞቱ ወታደሮችም መኖራቸው ተረጋግጧል።

በተያዘው ሃይፋ የሚገኘው ራምባም ሆስፒታል በራሚያ - አይታ አል-ሻዕብ - ኸውዛህ ትሪያንግል ውስጥ የሂዝቦላህ የደፈጣ ጥቃትን ተከትሎ 8 ሄሊኮፕተሮች ተጎጂ አሸባሪ ወታደሮችን ይዘው እዚያ ካረፉ በኋላ የጅምላ ጉዳት መድረሱን በማወጅ ተጨማሪ የህክምና ባለሙያዎች እንዲለኩለት ጠይቋል።

በደቡባዊ ሊባኖስ በቀጠለው ውጊያ ከደቂቃዎች በፊት ሂዝቦላህ በፈፀመው ጥቃት ቢያንስ 44 ጽዮናዊያን ወታደሮች መገደላቸው እና መቁሰላቸው የተረጋገጠ ሲሆን  ወደ ሃይፋ ራምባም ሆስፒታል እና ወደ ቤኔልሰን ሆስፒታል ተወስደዋል።

እንደ እስራኤል ሚዲያዎች ዘገባ ከሆነ ውጊያው የቀጠለ በመሆኑ የተጎጂ ወታደሮች ቁጥር ሊጨምር የሚችል ሲሆን በወራሪው ጦር ውስጥ ቢያንስ 5 ወታደሮች እስካሁን መሞታቸው ተረጋግጧል።

#ዘመቻ_ኸይበር

@Alif_Online_Official

Alif Geopolitics

16 Oct, 16:26


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ከደቂቃዎች በኋላ #ሰበር ዜና ይኖራል👀

@Alif_Online_Official

Alif Geopolitics

05 Oct, 11:54


♻️🔻🇵🇸🇮🇱 ስሙ እንዲገለጽ ያልፈለገ የእስራኤል ባለስልጣን ለቻናል 13:-

የህያ ሲንዋር በህይወት አለ አሁንም በድብቅ “በእስራኤል” ላይ ጦርነት እያካሄደ ነው።

ሲንዋር ያለማቋረጥ በእንቅስቃሴ ላይ ነው እና የመልእክት መላላኪያ ፕሮግራሞቹን ዲጂታል ወዳልሆነ ግንኙነት ቀይሯል።

@Alif_Online_Official

Alif Geopolitics

05 Oct, 07:21


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 #ሰበር

የሂዝቦላህ ልዩ ተዋጊዎች የሬድዋን ፎርስ ባልተጠበቀ ሁኔታ ወደ ጽዮናዊያኑ ኪርያት ሸሞና ሰፈራ ገብተው የአገዛዙን ጦር ተዋግተዋል ሲል የፍልስጤሙ ሳማ የዜና አገልግሎት አርብ ማምሻውን ዘግቧል።

በዚህም በርካታ የጽዮናውያን ወታደራዊ ኃይሎች መማረካቸውን እንዲሁም የተወሰኑት ደግሞ መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን አረጋግጫለሁ ሲል የመገናኛ ብዙሃኑ ዘግቧል።

የእብራይስጡ ቻናል 12 በበኩሉ በተያዙት ሰሜናዊ የፍልስጤም ግዛቶች በገሊላ አካባቢ በሂዝቦላህ ከፍተኛ ጥቃት እንደተሰነዘረ አስታውቋል።

#ዘመቻ_ኸይበር

@Alif_Online_Official

Alif Geopolitics

28 Sep, 11:41


♻️🔻🇱🇧🟡🟢 ሀሰን ነስረላህ መገደሉን ሂዝቦላህ ይፋ አድርጓል።

@Alif_Online_Official

Alif Geopolitics

27 Sep, 06:08


♻️🔻🇾🇪🇮🇱 የመን ቴል አቪቭ ላይ ጥቃት ፈፅማለች!

የየመን ጦር በድንበር ተሻጋሪ ባለስቲክ ሚሳኤል "ቴል አቪቭ" ላይ በፈፀመው ጥቃት በሌሊቱ ከ2 ሚሊየን በላይ ሰፋሪዎች ከቤታቸው ወጥተው ወደ መጠለያ እንዲገቡ አድርጓል።

በርካታ ሰፋሪዎች ከያሉበት ወጥተው መሀል መንገድ ላይ ያድነናል ባሉት ነገር ስር ተደብቀው አድረዋል።

የየመን ጦር ሃይሎች ስለጥቃቱ በሚቀጥሉት ሰዓታት ይፋዊ መግለጫ ይሰጣል።

እስካሁን ባለው መረጃ የመኖች ጥቃቱን የፈፀሙት በሃይፐርሶኒክ ባለስቲክ ሚሳኤል ነው። በቴል አቪቭ ውስጥ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅም ተሰምቷል።

የእስራኤል ጦር ሬድዮ ከየመን የተተኮሰ ሚሳኤል ወደ ማዕከላዊ "እስራኤል" ከደረሰ በኋላ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰፋሪዎች ወደ መጠለያው ገብተዋል ብሏል።

ሚሳኤሉ ወደ ማዕከላዊ እስራኤል መግባቱን ተከትሎ በቤን ጉሪዮን አየር ማረፊያ የሚደረገው እንቅስቃሴ ቆሟል።

የመኖች አንድ ድሮን ሲጠቀሙ ማንም ሳያከሽፈው እስራኤል ገብቶ ከባድ ጉዳት አድርሷል አሁንም አንድ ሚሳኤል ተኩሰው ማክሸፍ አለመቻሉን ተከትሎ የእስራኤሉ ሚዲያ ቻናል 14 በደቡብ ክልል ያለው የአየር መከላከያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጣም ደካማ ነው ይህም አሳሳቢ ጉዳይ ነው ብሏል።

የጽዮናውያኑ መገናኛ ብዙሃን በጥቃቱ 17 እስራኤላውያን ላይ ጉዳት መድረሱን ዘግበዋል።

በተጨማሪም የጽዮናውያኑ ሚዲያ በቴል አቪቭ የ18 አመት ሰፋሪ የሳይረን ድምጽ ሲሰማ ወደመጠለያ ሲሮጥ በመኪና መገጨቱን ገልፀዋል።

እንዲሁም የሀገሪቱ አምቡላንስ አገልግሎት በቴላቪቭ ጥቃቱን ለማስጠንቀቅ በነበረው የሳይረን ድምጽ ብዛት በጭንቀት 18 ሰዎች ራሳቸውን ስተው ሆስፒታል ገብተዋል ብሏል።

@Alif_Online_Official

Alif Geopolitics

26 Sep, 11:41


♻️🔻🇱🇧🇮🇱🇫🇷🇺🇸 ዕብራይስጥ ቻናል 14:- በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በአሜሪካ እና በፈረንሳይ የተኩስ አቁም ሃሳብ ቢቀርብም ሒዝቦላህ በአቋሙ ጸንቷል እና ጋዛን ያላካተተ ማንኛውንም የተኩስ አቁም ስምምነት ለመፈረም ፈቃደኛ እንዳልሆነ አሳውቋል።

@Alif_Online_Official

Alif Geopolitics

26 Sep, 09:38


♻️🔻🇪🇹 ከራስ ገዝነት ወደ ሙስሊም ጠልነት!

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ካምፓስ (5 ኪሎ) ትላንት ተማሪዎችን ሰብስበው ኦረንቴሽን በሚሰጡበት ሰዓት ኒቃብና ተመሳሳይ ኢስላማዊ አለባበስ መልበስ እንደማይችሉ ነግረዋቸዋል። የራሳቸውን ሃሳብ ከተናገሩ በኋላ ተማሪዎች ሃሳብ ለመናገር እጅ ሲያወጡ ባልሰማና ባላዬ ድምፃቸውን አፍነው አልፈዋል። ኒቃብ የለበሰ ተማሪ ግቢ መግባትም ሆነ ካፌና ላይብረሪ መጠቀም እንደማይችል መናገራቸውን የግቢው ሙስሊም ተማሪዎች ተናግረዋል።

የሚመለከታቸው የመጅሊስና ሙስሊሙን የወከሉ የመንግስት ባለስልጣናት በመከራ ያገኟትን የስልጣን እድል በማጣጣም ተጠምደው እንወክልዋለን ያሉትን ህዝብ ረስተውታል ጭራሽ መንግሥት የሙስሊሙን መብት የሚጥስ ውሳኔ እንዲወስን ምክንያት እየሆኑ ነው።

አንዳንዶቹ ያለእውቀት ሌሎቹ ደግሞ ለመወደድ ብለው ሚዲያ ፊት የሚንሸራተቱት ነገር በሙስሊሙ ህዝብ እጣ ፋንታ ላይ ጉልህ ጉዳት እያመጣ ነው። እነዚህ ሰዎች ወይ ውግንናቸውን ለመረጣቸው ህዝብ ሊያደርጉ ወይም ዝም ሊሉ ይገባል።

እንደ ፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ ያሉ ምክንያታዊ ሰዎች የመሩት ተቋም አሁን በጨለማ የሚጓዙ መሃይማን እየመሩት እንደሆነ ቢታወቅም ፀሀይ እና ጨረቃ የማምለክ መብት በተሰጠበት ሀገር ሙስሊም ኢስላማዊ ግዴታውን እንዳይወጣ መከልከል አያዛልቅም።

@Alif_Online_Official

Alif Geopolitics

25 Sep, 19:00


♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)ﷻ (ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ ፣ ...»
ቁርኣን[ 3:104 ]

አድ በማረግ ተሳተፋ ጀዛኩሙላህ 🙏

Alif Geopolitics

22 Sep, 07:19


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ከሰአታት በፊት ሂዝቦላህ እስራኤል በሊባኖስ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እንደመነሻ የምትጠቀምበት ራማት ዴቪድ ኤር ቤዝ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ኢላማ ያደረገ ጥቃት የፈፀመ ሲሆን የእስራኤል 3ኛውን ትልቅ ከተማ ሀይፋን ለመጀመሪያ ጊዜ ኢላማ አድርጓል እንዲሁም የእስራኤል ወታደራዊ የኢንዱስትሪ አካባቢን በፋዲ-1 እና ፋዲ-2 ሮኬቶች መትቷል።

በደርዘን የሚቆጠሩ ጉዳዮች ተመዝግበዋል 10 ሰዎች መጎዳታቸው ሲረጋገጥ አንድ እስራኤላዊ ሞቷል።

ምንም እንኳን ሂዝቦላህ 60 ኪሎ ሜትር በላይ ወደ እስራኤል ዘልቆ በመግባት ጥቃት ቢፈፅምም እነዚህ በቤይሩት ለደረሱት ጥቃቶች 'ምላሽ' አይደሉም, እነዚህ ሂዝቦላህ የጥቃት ይዘቱን እያሰፋ መሄዱን ብቻ ማሳያ ናቸው።

ሃይፋ እና አካባቢው ከ120 በላይ በሚሆኑ የሂዝቦላህ ሮኬቶች ሲጠቁ በሰሜን ብቸኛው የአየር ማረፊያ ጣቢያ ነው "ራማት ዴቪድ" አየር ኃይል ሁለት ጊዜ እንዲሁም ራፋኤል የጦር መሳሪያ ኩባንያ እና የ"ክራዮት" መኖሪያ አካባቢ ላይ ከባድ ጥቃት ተፈፅሟል።

የጽዮናውያኑ መገናኛ ብዙሃንም ከኢራቅ ሁለት እና ከየመን አንድ ባለስቲክ ሚሳኤል በተመሳሳይ ሰአት መወንጨፉንም ዘግበዋል።

@Alif_Online_Official