Latest Posts from Abdurahim Ahmed (@abdure99) on Telegram

Abdurahim Ahmed Telegram Posts

Abdurahim Ahmed
11,736 Subscribers
546 Photos
84 Videos
Last Updated 01.03.2025 10:46

Similar Channels

TIKVAH-ETHIOPIA
1,531,820 Subscribers
Sαlαh Responds ⛉
10,223 Subscribers

The latest content shared by Abdurahim Ahmed on Telegram


"..ሀሩን ሚዲያ በደስታችንም ሆነ በሃዘናችንም ጊዜ ቀድሞ የሚገኝ የሙስሊሙ ልሳን ነው"

ሼይኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ

#one_ummah_one_goal

"..ሀሩን ሚድያን ከምወደው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ በተቻለው አቅም ሚዛናዊነቱን ጠብቆ እየሰራ የሚገኝ መሆኑ ነው። ሀሩን ሚድያ አሁን ላይ በዋናነት የህዝበ ሙስሊሙ ድምጽ ቢሆንም በሒደት አድማሱን እያሰፋ የመላ ኢትዮጵያውያን ከዚያም አልፎ የአለም ህዝብ ድምጽ እንደሚሆን አምናለው.."

- ካፕቴን በህሩዲን አብዱ ስለሀሩን ሚድያ ከተናገሩት

#one_ummah_one_goal

https://youtu.be/PsNHDSVpXiQ?si=IUG8ONzIGfQjqJAu

ድምፅ ለተነፈጉ ድምፅ ያገኙ ዘንድ፣ የተበደሉ ፍትህ የተዛባባቸው ፍትህ ያገኙ ዘንድ፣ የተራቡ ይበሉ ዘንድ፣ የተጠሙ እንዲጠጡ፣ የታረዙ ይለብሱ ዘንድ ሰበብ በመሆን እነሆ አመታት ተሻግረን ዛሬ ላይ ደርሰናል።

በእስካሁኑ ጉዟችን፦
◾️ በሁለት ዩቲዩብ ቻናል ከ748 ሺህ በላይ ተከታዮች

◾️ በሁለት የዩቲዩብ ቻናል 8201 ቪዲዮችን በማድረስ ከ107 ሚሊዮን በላይ እይታዎች

◾️ በፌስቡክ ገፃችን ከ493 ሺ በላይ ተከታዮች

◾️ ከ10 ሺህ በላይ የፅሁፍ ዜናዎች

ማህበረሰባችንን ቀና ለማድረግ ከትላንት በበለጠ አቅምና ተደራሽነት ለመከወን የታቀደ ብሩህ ወደፊት..!

#አንድ_ኡማ_አንድ_ግብ
#One_ummah_One_goal

© ሀሩን ሚዲያ

linked in ላይ የቀጥታ ስርጭት events በማዘጋጀት በተለያየ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ሰዎችን በመጋበዝ ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት፣የተሻለ ትብብር እና ኔትወርክ መፍጠር የምንችልበትን መንገድ አስቤ የጀመርኩ ቢሆንም ላይቭ ኢቨንት ለማዘጋጀት 500 connection እና 15 ሺ ፎሎወር የሚያስፈልግ መሆኑን ለመረዳት ችያለሁ ። በናንተ በኩል ያየሁት ተነሳሽነት ትልቅ መነሳሳት ፈጥሮብኛል ። እናም ይህ ቁጥር እንዲሞላ የlinked in አካውንቴን ፖስት ሼር በማድረግ እንድታስተዋውቅልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ ።

https://www.linkedin.com/in/abdurahim-ahmed-3458a72a1/

Exciting News! 🎉

After a period of inactivity, I’ve revitalized my LinkedIn profile to actively connect and engage with professionals across various industries. I’m eager to share insights, collaborate on innovative projects, and expand my professional network.

I’m also thrilled to announce that I’ll be hosting live conversations and programs on LinkedIn, covering a range of topics and featuring diverse professionals. These sessions aim to foster meaningful discussions and knowledge sharing.

If we’re not already connected on LinkedIn, let’s change that! Click the link below to visit my profile and send a connection request. Together, we can explore new opportunities and foster meaningful professional relationships.

https://www.linkedin.com/in/abdurahim-ahmed-3458a72a1?utm_source=share&utm_campaign=share_via&utm_content=profile&utm_medium=ios_app

Looking forward to connecting with you!

#ProfessionalNetworking #LinkedInLive #CareerGrowth

የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ጋር በፋጢማ ቢንት ሙባረክ ተማሪዎች ጉዳይ ደውለን አነጋግረናል ሃሩን ሚዲያ
https://youtu.be/lzUZiBtyQ7I

የደረሰኝ መልእክት እንቅልፍ የሚነሳ እና የሚረብሽ ነበር። አቅመ ደካማ የሆኑ አይነ ስውራን፦

''በይፋ ሶላት ተከልክለናል፤ መስገድ አልቻልንም። እየተደብቅን ነው ለመስገድ የምንሞክረው። መጅሊሱም በዚህ ጉዳይ ላይ መፍትሄ እንድናገኝ አላደረገም። ጓደኞቻችንም ትምህርት ቤቱን ትተው ወጥተዋል። እኛም ከዛሬ ነገ ይስተካከላል በሚል በትግል በለቅሶ ነው ያለነው። እስካሁን መፍትሄ አላገኝንም። በአዳሪ ት/ቤት እየተማርን ሶላት ተከልክለን ዝም በማለታችሁ ነገ አላህ ፊት እንጠይቃችኋለን'' የሚል ነበር፣ መልዕክቱ በለቅሶ የታጀበና እንቅልፍ የሚነሳ ነበር።

ይህ መልዕክት ከደረሰኝ ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ ፕሮግራሞችን ከባልደረቦቼ ጋር እያደርስናችሁ ነው። ነገር ግን በሚያሳዝን መልኩ የነሱን አጀንዳ ጉዳዩ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ቀርቶ መረጃውን እንኳን በማዳረስ የሚያግዝ የለም። ያለንበት ተጨባጭ እጅግ የሚያስደንግጥ ነው።
ማየት የተሳናቸው ወገኖቻችንን ጉዳይ ችላ በማለታችን እንደ ዑማ ያለንበትን ቁልቁለት ቁልጭ አድርጎም የሚያሳይ ነው።

በፋጢማ ቢንት ሙባረክ ወይም በቀየሩት ስሙ በብርሃን የአይነ-ስውራን ት/ቤት የሚማሩ ሙስሊሞች በሶላታቸው ተፈትነው ፈትነውናል። ተመዝነንም ቀለናል። ለማንኛውም ነገ አላህ ፊት የምንጠየቀው እንደ ግል ነውና በአቅማችን ልክ ቅንጣት ወደኃላ ሳንል ወደፊት ጉዟችን እንቀጥላለን! በጌታችን ፍቃድ በዳዮችንም እንቅልፍ እንነሳለን! ያለንበት ሁኔታ ግን እጅግ ያሳዝናል። ለዚህ ቁልቁለት እንዴት ነበር የፈጠንነው..?!

45 የበደል ቀናት
"..የሌሎችም እጣፈንታ ይህ ከመሆኑ በፊት ድረሱላቸው.."
ተማሪ ጀማል በፋጢማ ቢንት ሙባረክ የአይነ ስውራን ት/ቤት ለመማር ሲመጣ ትልቅ ስንቅን አንግቦ ነበር። የአይነ ስውራን ት/ቤት እምብዛም በሌለበት የሀገራችን ሁኔታ ውስጥ መሠል ት/ቤት ማግኘት ከእድልም በላይ ነበር።
ህልሙ ሁሉ እንደተጨናገፈ ለመረዳት ግን 45 የመከራ ቀናት በቂ ነበሩ። ከሶላት ክልከላ እስከ ሀይማኖት ጫና ድረስ ቢደራረብበት ት/ቤቱን ለቆ ለመውጣት ተገደደ። በት/ቤቱ ውስጥ ያሳለፋቸውን የሰቆቃ ቀናት በዚህ ፕሮግራም ውስጥ ዘርዝሮ ተናግሯቸዋል። ከጋዜጠኛ አብዱረሒም አህመድ ጋር ያደረጉትን ይህንን ቆይታ ዛሬ ምሽት 3:00 ጀምሮ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።
ይጠብቁን...

''ሱረቱል አበሰ'' የቁርኣን ምእራፍ የወረደው አይነ-ስውር በሆነው አብደላ ኢብን ኡሙ መኽቱም ምክኒያት ነው። ዛሬ ማየት የተሳናቸው ወገኖቻችን መሃል ከተማ ላይ በአዳሪ ት/ቤት ሶላት እንዳይሰግዱ ሲከለከሉ ለነሱ ያሳየነው ቸልተኝነት ለኛ ማስተማሪያ ነው።
ረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም የቁረይሽ መሪዎች ሒዳያ ቢያገኙ ለዲኑ ይጠቅማል ብለው አስበው አይነ-ስውር የሆነው አብደላ ኢብን መኽቱምን ችላ ብለዋል ተብለው የተገሰጹበት ምዕራፍ ነው።

እስኪ አንቀጹን ተመልከቱት፧

ሱረቱ ዐበሰ

عَبَسَ وَتَوَلَّىٰٓ
ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡
أَن جَآءَهُ ٱلۡأَعۡمَىٰ
ዕውሩ ስለ መጣው፡፡
وَمَا يُدۡرِيكَ لَعَلَّهُۥ يَزَّكَّىٰٓ
ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡

أَوۡ يَذَّكَّرُ فَتَنفَعَهُ ٱلذِّكۡرَىٰٓ
ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡

أَمَّا مَنِ ٱسۡتَغۡنَىٰ
የተብቃቃው ሰውማ፤
فَأَنتَ لَهُۥ تَصَدَّىٰ
አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡
وَمَا عَلَيۡكَ أَلَّا يَزَّكَّىٰ
ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡