Ethio 251 Media

@ethio251media


ETHIO 251 is an independent media offering you News, Political Analysis and Information feeds. መረጃ ለማድረስ :- @Ethio251MediaInfo

Ethio 251 Media

22 Oct, 16:20


https://youtube.com/live/lO5ASsQKQE0?feature=share

Ethio 251 Media

22 Oct, 14:12


የንፁሀን ጭፍጨፋው ዓለም ዓቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ ጥሪ ቀረበ።

"በጎጃም ቀጠና የንጹሃን ጭፍጨፋ አሁንም እንደቀጠለ ነው፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን ጉዳይ በትኩረት እንዲመለከተው ማሳሰብ እንፈልጋለን" አርበኛ ዝናቡ ልንገረው

በንፁሃን ላይ የሚደርስ የጭፍጨፋ ወንጀል አሳሳቢ መሆኑን የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ለኢትዮ 251 ሚዲያ በላከው መረጃ ገለጸ።

"በጎጃም ቀጠና ድጎ ፅዮን ቢቡኝ ወረዳ ወይንውሃ ከተማ የገባው የጠላት 72ኛ ክፍለጦር ህዝቡን በጅምላ እየሰበሰበ እየረሸነ ይገኛል፤ አርሶ አደሮችን እያገተ መሳሪያ አላችሁ አምጡ እያለ በሰውነታቸው ላይ ኮሸኮሽ እያንጠፈጠፈ የሌላቸውን ሰዎች ክላሽ ገዝተው እንዲያስገቡ በማድረግ ገዝተው ካስገቡ በኋላም እየተረሸኑ ይገኛሉ" ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

የወይን ውሃ ከተማ ነዋሪም ከተማውን ለቀው እየተሰደዱ ይገኛል። ይህ ሕዝብ በየቀኑ በጅምላ ከሚጨፈጨፍ ከፋኖ ጋር ተሰልፎ እንዲዋጋ እና ከሞት ራሱን እንዲያድን ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ጥሪ አቅርቧል።

በቢቡኝ ዙሪያ ብቻ ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም እስካሁን 30 የሚሆኑ ንፁሃን በአብይ አህመድ ተላላኪ ሰራዊት ተገድለዋል ያለው ዋና አዛዡ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው፤ ጎጃም ውስጥ እየተፈፀመ ያለው የንፁሃን ጭፍጨፋም የከፋ ሆኖ አግኝተነዋል ሲል ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

22 Oct, 13:50


ሰበር ዜና

የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ ኃይል አምባ ጊዮርጊስ ላይ ድባቅ ተመታ!

በአርበኛ ሀብቴ ወልዴ የሚመራው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር ቴዎድሮስ ብርጌድ አሳምነው ሻለቃ፤ በፋኖ ወርቁ ዘገዬ እየተመራ አምባ ጊዮርጊስ ከተማ ዘልቆ በመግባት በርካታ ጀብዱዎችን መፈፀሙን ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ኢትዮ 251 ሚዲያ አረጋግጣለች።

አምባ ጊዮርጊስ ላይ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ውጊያ የጠላት ኃይል ከፍተኛ ኪሳራ ሲደርስበት አማራ በመሆናቸው ብቻ የታሰሩ ንጹሃንን እስር ቤቱን በመስበር ማስፈታት መቻሉን ኢትዮ 251 ሚዲያ አረጋግጣለች።

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር ቴዎድሮስ ብርጌድ አሳምነው ሻለቃ የጠላትን ኃይል ድባቅ የመታችው ሲሆን ከተማ ላይ የነበረው የብልጽግና ሰራዊት የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው እየፈረጠጠ ካምፕ መግባቱን የጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር አመራሮች ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጸዋል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

22 Oct, 13:09


በመንዝና ግሼ አውራጃ ባሉ ወረዳዎች፣ ቀበሌዎች፣ጎጦችና መንደሮች << ህዝባዊ አስተዳደር>> ማደራጀቱን እንደቀጠለ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ገለፀ።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ነፃ ባወጣቸው ቀጠናዎች ብልፅግናን አደረጃጀት እያፈረሰ፣ አማራዊ ቅርፅ ያለው ጊዜያዊ ህዝባዊ አስተዳደር መመስረት መቀጠሉንም ገልጿል።

በተለይ ህዝቡ ባሉት የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት እንዲገለገል፣ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲያዳብር እንዲሁም ለፋኖ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ በነፃነት ለነፃነቱ  እንዲዋጋ በሰፊው እየተሰራም ይገኛል ሲል የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ገልጿል። 

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነፃነት አንደበት!

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

22 Oct, 11:30


"የአማራ ዲያስፖራ ዓለም አቀፍ ጉባዔ  በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የጉባዔው ዋና ሰብሳቢ አምባሳደር ብርሃነመስቀል ነጋ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገለፁ።

በጉባኤው ላይ በዓለም ያሉ ከሰላሳ በላይ የአማራ ማህበራት፣ ምሁራንና በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ የሚሳተፉ ተመራጮች መገኘታቸው ታውቋል።

እንደ አምባሳደር ብርሃነመስቀል ነጋ  ከአትዮ 251 ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታም በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የምንሰራቸውን ዝርዝር ስራዎች በመግለጫ ይፋ እናደርጋለን ሲሉም ገልፀዋል።

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

22 Oct, 10:48


አርበኛ ፋኖ ሞላ ደስዬ የጥቅምት ሰማዕት በሚል በትግል ጓዶቹ ታስቦ ውሏል።

አርበኛ ፋኖ መምህር ሞላ ደስየ የተሰዋህለትን አላማ ከግብ ለማድረስ የመጨረሻው ትንቅንቅ ላይ ነን:: ቃልህን ጠብቀን በድል ዋዜማ ላይ እንገኛለን! ለድልም እንበቃለን ሲሉም የትግል ጓዶቹ አርበኛውን አስበውት ውለዋል።

ከትግል ጓደቹ ለኢትዮ 251 ሚዲያ የደረሰውን የመታሰቢያ መልዕክት ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር አቅርቦታል።

ክብር ዉድ ህይወታቸዉን ገብረው ለዛሬ ላደረሱን ሰማእቶቻችን!

https://t.me/ethio251media
  

Ethio 251 Media

22 Oct, 10:21


በጎንደር ቀጠና ጠላት ብልፅግና በልዩ ትኩረት ኢላማ አድርጎ ጥፋት በሚፈፅምባቸው አዲስ ዘመንና እብናት ለተከታታይ ቀናት በተደረገ ተጋድሎ በጎንደር ዕዝ ከፍተኛ ድል ተመዝግቧል።

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ መልካሙ ጣሴ በግንባር ተጋድሎና ድሎች ዙሪያ ከኢትዮ 251 ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ተከታተሉት...

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

22 Oct, 09:59


ዘመቻ ፲ አለቃ በሃይሉ በስኬት እየተጠናቀቀ እንደሚገኝና በደብረብርሃን ዙሪያ እና በሃገረማርያም ንፋስ አምባ በተባለ ቀበሌ ከፍተኛ ተጋድሎ መፈፀሙን የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ገለፀ።

በተለይ ደብረብርሃን ዙሪያ በተደረገው ተጋድሎ በጋራ ድል የተመዘገበበት እንደሆነም ተገልጿል።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ንጋቱ ይታፈሩ ከኢትዮ 251 ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ተከታተሉት....

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

22 Oct, 09:42


በደራና ቀጠና እንዲሁም በደብረብርሃን ዙሪያ ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ እንደሚገኝ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ገለፀ።

በተለይ በደብረብርሃን ዙሪያ በተደረገው ተጋድሎ በጋራ ድል የተመዘገበበት መሆኑም ተገልፆል።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ምክትል የህዝብ ግንኙነት ክፍል ፋኖ ስንታየሁ ደመቀ ከኢትዮ 251 ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ተከታተሉት...

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

22 Oct, 09:11


ሰበር ዜና!

ወልደያ ከተማ ላይ የአገዛዙ ሰራዊት በደፈጣ ተመታ!

ወልድያ ዙሪያ አሳምነው ክፍለጦር እያደረገ ያለው ተጋድሎ የቀጠለ ሲሆን ባህር ዳር መውጫ አፍሪኬር አካባቢ ጠላት ኬላ የሚያደርግበት ቦታ ላይ ደፈጣ በማድረግ የጠላት ኃይል ድባቅ መመታቱን የአማራ ፋኖ በወሎ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ አበበ ፈንታው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገለጸ።

የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ ወታደር በደረሰበት ጥቃት ጠላት አምስት ሙትና ስድስት ቁስለኛ ያነሳ ሲሆን በወልድያና በሳንቃ በኩል ሁለት ዙ23 በማምጣት በዘፈቀደ እየተኮሰ ሲሆን ቃሊም መግቢያ አቦ ቤተ-ክርቲያን አካባቢ ሁለት እናቶችን በከባድ ሁኔታ ማቁሰሉን ገልጾ፤ አንደኛዋ እናታችን ወዲያውኑ ማረፋቸውን ፋኖ አበበ ፈንታው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

አገዛዙ አሁን ላይ ወደመጣበት የሸሸ ሲሆን ወልድያ ከተማ ተረጋግቶ መቀመጥና ስራ መስራት ስላልቻለ ራያ አላማጣ ያስቀመጠዉን ተጠባባቂ ቀይ ቆብ ለባሽ ፈርጣጭ ሰራዊቱን ዛሬ ያስገባ መሆኑን አረጋግጠናል፤ ቢሆንም ግን የሚያመጣው ለውጥ ስለማይኖር ተጋድሎዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የሕዝብ ግንኙነቱ ፋኖ አበበ ፈንታው ለጣቢያችን አስታውቋል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

22 Oct, 09:02


የትግሉ ምዕራፍ እያደገ የፋኖ ስልጠናዎችና አዳዲስ ምሩቃኖችም ወደ ትግል እየተቀላቀሉ መሆናቸው ተገልጿል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም የበላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር የደባይ ጮቄ ብርጌድ አዳዲስ ምልምል ፋኖዎችን ማስመረቁን ለኢትዮ 251 ሚያ ባደረሰው መረጃ አሳውቋል።

ተከታተሉት...

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

22 Oct, 08:42


ታላቅ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ!
በ16 ከተሞች!

Ethio 251 Media

22 Oct, 08:42


በስንቅም በትጥቅም እየተደራጀ የሚገኘው የአማራ ፋኖ አዳዲስ ምልምል ኮማንዶ ፋኖዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም የተፈራ ዳምጤ ክፍለ ጦር ስር የሚገኘው የመብረቁ ተፈራ ብርጌድ ለ2ኛ ዙር የኮማንዶ ሃይሎችን ማስመረቁንም ለኢትዮ 251 ሚዲያ ባደረሰው መረጃ አስታውቋል።

ተከታተሉት....

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

22 Oct, 08:28


በጎጃም ቀጠና ያሉ ተጋድሎዎችና የአገዛዙ ስምሪትን በተመለከተ የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ዮሃንስ አለማየሁ ከኢትዮ 251 ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ተከታተሉት.....

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

22 Oct, 08:14


ከደብረማርቆስ ተነስቶ ወደ ረቡዕ ገበያ ሲንቀሳቀስ የነበረ የጠላት ሃይል በስናን አባጅሜ ብርጌድ የደፈጣ እርምጃ ተወስዶበታል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ክፍለጦር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ መምህር ታደገ ይሁኔ የግንባር ተጋድሎዎችን በተመለከተ ከኢትዮ 251 ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርጓል።

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

21 Oct, 18:02


★የድል ዜና

''ዘመቻ ፲ አለቃ በሀይሉ ሙሉጌታ''

በ ፲ አለቃ በሀይሉ ሙሉጌታ ተሰይሞ በሶስት የፋኖ ብርጌዶች እየተደረገ ባለው ዘመቻና የተጠናከረ ክንድ የተወቀጠው የመከላከያ ሰራዊት አንድ አይሱዙ ሙትና ቁስለኛ ተሸክሞ ፈረጠጠ::

በሀገረማርያም ከሰም ወረዳ ጥቅምት 11/2017 ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በሦስት የውጊያ ግንባሮች ለተከታታይ ሶስት ሰዓታት በቆየ እልህ አስጨራሽ ውጊያ ጀግናው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር በጀግና ብርጌዶቹ ታላቅ ጀብዱን ፈፅሟል።

በከሰም ክፍለጦር ስር ከሚገኙት ከሀይለማርያም ማሞ ፣ከተስፋ ገብረስላሴ እና ከአስማረ ዳኘ ብርጌዶች የተውጣጡ ሻለቆች በአገዛዙ አጠራር በሸዋ ሀገረማርያም ከሰም ወረዳ ንፋስ አምባ፣መስኖ በር እና ሞዬ በተባሉ አቅጣጫዎች ከጠላት ጋር ባደረጉት መደበኛ ውጊያ የአማራን ህዝብ አጥፋ ተብሎ የተላከው የመከላከያ ሰራዊትና ባንዳው የአማራ ሚሊሻ እንደ ጌሾ ከተወቀጠ በኋላ አንድ አይሱዙ ሙትና ቁስለኛቸውን ተሸክመው ወደ መጡበት ከተማ ፈርጥጠው ለአዛዦቻቸው የመርዶ ነጋሪታቸውን ጎስመዋል።

በድርጊቱ የተበሳጨው የአገዛዙ ወታደር ሙትና ቁስለኛውን ተሸክሞ ሲፈረጥጥ በጎች በመጠበቅ ላይ ያለን አንድ የ70 ዓመት አዛውንት ተኩሰው ገድለውታል። የዉጊያውን ዝርዝር ሁኔታ በስልክ ያደረሱት የሃይለማርያም ማሞ ብርጌድ ዋና አዛዥ ደመላሽ መንግስቴ ጠላት ያለውን ሁሉ ከባድ መሳሪያ ማለትም ዙ-23 ፣ሞርተርና ዲሽቃ ተሸክሞ ፋኖን ለመግጠም ቢሞክርም በሶስቱም የፋኖ ብርጌዶች የወንድማማች ብርቱ ክንድ የአገዛዙ ሰራዊት ተገርፎ መመለሱን አብራርተዋል።

ድል ለአማራ ፋኖ
ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል

https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

21 Oct, 16:32


https://youtube.com/live/YoJ2ANjzCJc?feature=share

Ethio 251 Media

21 Oct, 16:13


የድል ዜና
/
የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር የስናን አባ ጅሜ እና የንጉስ ተክለሐይማኖት ብርጌድ ባደረጉት የደፈጣ ውጊያ ጠላት እንደ ቅጠል ሲረግፍ ውሏል።

ገና በጡሀቱ ከደብረ ማርቆስ ተነስቶ ወደ ረቡ ገበያ ስንቅ ለማቀበል ሲንቀሳቀስ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ የንጉስ ተክለ ሐይማኖት ብርጌድ የፋኖ አባላት በደፈጣ አስደንብረውት ይወጣሉ።
በዚህ የተደናበረው እና በፍራቻ የተዋጠው ፈርጣጭ የአብይ አህመድ ወንበዴ ቡድን እንደገና ሐይሉን አጠናክሮ ከደብረ ማርቆስ ባለ ጎማውን መድፍ፣ዙ23 እና ሞርታር ብሎም ድሽቃውን ጠምዶ ከደብረ ማርቆስ አስፍቶ ወደ ረቡ ገበያ ወጣ።

ረቡ ገበያ ላይ መሽጎ ስንቅ መቀበል አልችል ብሎ ራብ የሚያነጉደውና ህዝቡን እያስገደደ የእለት ጉርሱን የሚደፍነው የጠላት ኃይል ደግሞ ሞርታሩንና ድሽቃውን ጠምዶ ከከተማው ወጥቶ ስንቁን ለመቀበል ጉዞ ጀመረ።

ይህን ሁሉ ግሳንግስ የሚስበው በጡሀቱ አንድ ቲም የንጉስ ተክለ ሐይማኖት ብርጌድ በተተኮሰበት ጥይት ተደናብሮ በልመታ ነው ፍራቻ ነው።
ዳሩ ግን በነበልባሉ ሺ አለቃ ባለው ጊዜ ወንዴ የሚመራው የስናን አባ ጅሜ ብሮጌድ የፋኖ አባላት ሁለቱን ሻለቃ ግራና ቀኝ ደፈጣ አስይዞ ይጠብቀው ኖሯል።
ያልታሰበ ዱብዳ እንራታላይ ጠላት አለ ብሎ ሲጠብቅ የነበረ የአብይ ሽፍታ ቡድን ከረቡ ገበያ በቅሮብ እርቀት ሁለቱ ስንቅ ተቀባይና አቀባይ ሳይገናኙ መንገድ ላይ ያላሰበው ዱብዳ ወረደበት።

የፋኖ ጥይት እንደ ዶፍ ዝናብ ይወርድበት ጀመር።የአብይ ፈርጣጭ ቡድን በየቀኑ ከተወሸቀበት ከተማ ወይም አስፓልት በወጣ ቁጥር ሬሳ እየጫነ መፈርጠጥ ልማዱ ነውና ዛሬም እንደ ትናንቱ ቁጥር ስፍር የሌለው ሬሳና ቁስለኛውን ሬሽን ጭኖበት በመጣው መኪና ጭኖ ተመልሷል።

ይህን ሁሉ ጀብዱ የሚፈፅሙት ሲጥሉ እንጅ ሲዋጉ ለአይን ጥቅሻ የማይታዩት የስናን አባ ጅሜ ብርጌድ የነበልባልና የፋሲካው ሻለቃ የፋኖ አባላት ናቸው።
ከጡሀቱ አራት ሰዓት የጀመረው የደፈጣ ውጊያ ወደ መደበኛ ውጊያ ተሸጋግሮ እስከ እኩለ ቀን ሰባት ሰዓት ድረስ ጠላትን ሲያደባዩት መዋላቸውን የብርጌዱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መለሰ ለክፍለ ጦራችን ቃል አቀባይ አርበኛ መ/ር ታደገ (ሸርብ) ገልጧል።
ድል ቁርሱ የሆነው የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ዛሬም በብርጌዶቹ የእለት ተእለት ተጋድሎ ታሪክ በአምዱ እያስመዘገበ ይገኛል።

አማራነት ዘላለማዊነት
አዲስ አብዮት
አዲስ ድል
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በክንዳችንና በአንደበታችን እንፈጥራለን።

የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ መ/ር ታደገ ይሁኔ(ሸርብ)


https://t.me/ethio251media

Ethio 251 Media

21 Oct, 14:38


"የአማራ ዲያስፖራ ዓለም አቀፍ ገባዔ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል" የአማራ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ሰብሳቢ

October 19 እና October 20 በዋሽንግተን ዲሲና ከተለያዩ አገራት በዙም ስብሰባ የተሳተፉበትና የተካሄደውን የአማራ ዲያስፖራ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የጉባዔው ዋና ሰብሳቢ አምባሳደር ብርሃነመስቀል ነጋ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጸዋል።

በዚህ ጉባኤ ላይ በዓለም ያሉ ከሰላሳ በላይ የአማራ ማህበራት፣ በአሜሪካ የሚገኙ ከተለያዬ ስቴት የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው አማራዎች፣ ምሁራን፣ የሚዲያ አባላት፣ በመጭው የአሜሪካ ምርጫ የሚወዳደሩ ተመራጭ አካላት ተሳትፈው ውሳኔና የትግል አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን አምባሳደር ብርሃነመስቀል ነጋ ለጣቢያችን ገልጸዋል።

አምባሳደር ብርሃነመስቀል ነጋ፤ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት የምንሰራቸውን ዝርዝር ስራዎች በመግለጫ ይፋ እናደርጋለን ብለዋል።

ዝርዝር መረጃዎች አሉት "በ251 ዛሬ" ዝግጅታችን ይጠብቁን።

ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!

https://t.me/ethio251media