Ethiopian Lecturers Voice

@euasas


Ethiopian Lecturers Voice

21 Oct, 18:51


👏

Ethiopian Lecturers Voice

19 Oct, 19:30


አዲሱን ደመወዝ ጭማሪ ለመቃወም ከጥቅምት 22/2017 ዓ.ም በኦሮሚያ የሚደረገው የስራ ማቆም አድማ በመላ ሀገሪቱ እንዲተገበር የመምህራን ኔትወርክ ቤተሰቦች ገለፁ።

#ሼር
https://www.facebook.com/100059826090948/posts/pfbid0bdGooanDiZaCGiiXtjsdyS5Q6DtHsQBuj9oGn5rAHD74Vn2yyrJnVzEATrqQUPuFl/

Ethiopian Lecturers Voice

18 Oct, 17:04


ሰላም ዉድ የ አሶሳ university መምህራን አርዳታችሁ ያስፈልገኛል አኔ ንግስት የ አሶሳ university መምህርት ምግብ አና ቡና ስለጀምርኩ መታችሁ ጎብኙኝ ሲል አጠይቃለሁ
አድራሻ ሳርበቶች ቶቶ ጎን
Please come and visit us

Ethiopian Lecturers Voice

06 Oct, 20:25


INBOX #2

ተማራዎች ከመግባታቸው በፊት በመምህራን ማህበር በኩል በየጊቢው  ሰብሰብ ብሎ መመካከር ጥሩ ይመስለኛል። ሀሳብ የሚወለደው በመድረክ ወይም በመነጋገር ነው። አንድ ጊዜ ከተጀመረ ግለቱ እየጨመረ ይሄዳል።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የተዘጋብንን የምንከፍትበት ዋናው ቁልፍ አንድ መሆን ነው።
አንድ መሆን ማለት ስርዓቱ  በተለየ መንገድ የተማረውን ማህበረሰብ intentionally ወደሗላ እየጎተተ እና እያዳከመ ሸምተን እንዳንበላ ከገበያ ውጪ እያደረገን መሆኑን መቀበል ነው። ይህን አልቀበልም የሚል ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር Quickly መሬት ላይ ያለውን Review ማድረግ ነው። ከዚህ ውጪ አውቆ የሚያላግጠውን በሌሎቻችን ላይ የደረሰብን ችግርና መሳቀቅ እግዚአብሔር  ይስጥህ ብሎ በመርገም ጥሎ ማለፍ ነው።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
በችግራችን ረግጠኞች ከሆንን በሗላ የመፈትሔ አማራጮችን በቅደም ተከተል ማስቀመጥና ለመተግበር ቆራጥ መሆን ነው። እዚህ ላይ ፍርሃትና መንቀጥቀጥ አያስፈልግም ምክንያቱም ሀሉም በአንድነት የመፍትሔ አማራጮችን ወደመተግበር እንጂ ፊቱን ወደሗላ የሚያዞርና የሚከዳ አይኖርምና።
ተጠየቅ ከመጣም ያው ሀሉም መጠ፞የ፞ቅ ነው ተለይቶ የሚጠ፞የ፞ቅ የለም።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ስርዓቱ ትምህርትን Strategically እየገደለው ነው። ትምህርት ሲሞት ተውልድ ይሞታል። ተውልድ ከሞተ አሁን በአንዳንድ አካባቢዎች ከምናየው እጅግ የከፈፋና እንደዱር አራዊት ሰው የሰውን ስጋ እየበላ ወደመኖር ያድጋል። ይህ ግነት አይደለም አይናችን እያየው ያለ ነው።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
Saintific law ብቻውን ይመራናል ብለን ይኼው ከጉረኗቸው እንደተበተኑ በጎች ተለያይተን ያገኘን ሁሉ በጉረሯችን ላይ ቆመብን።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
መፍትሄው በእጃችን ነው። መጠቀምና አለመጠቀም ምርጫው የራሳችን ነው።
።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
እያላዘኑ መኖር ደባሪ ነው!!‼️

Ethiopian Lecturers Voice

06 Oct, 20:23


Inbox

መምህር  ጠንካራ አንድነት የለውም  ከገቢዎች እና ጉምሩክ መማር ይጠበቅብናል  መንንግስት ጨመርኩ ካለው ውጭ የቤት 18500 በር፣ የሙያ 8000 ብር ፣ የመሸጋገሪያ 3000 ብር  እና የነዳጅ እና የስልክ የሚል 4000ብር እንደምረው አዳሜ መምህር  ደሞዝ እንዳይመስልህ ከዲፖሎማ እስከ  ዲግሪ ደሞዙ ብቻ ከ17000_35000 ከነሐሴ ወር 2016 ጀምሮ  በድምሩ ትንሹ የዲፖሎማ ደሞዝ 17,000 ብር ሲሆን ዲግሪው ደግሞ እስከ 60,000 ብር ድረስ በየደረጃው  እንደሚከፈላቸው ደብዳቤ ደርሷቸዋል  ወይኔ የዩኒቨርስቲ አስተማሪ  ለምን ሰቃይ ጎበዝ ሆንን የሚያሰኝ ነው  ፕሮፌሰር ያልተጣራ 20,000 ብር   ያገኛሉ   መምህሩን  ያንተ ሙህርነት ጉብዝና ምን ያደርጋል ኑሯችሁ ከእኛ በ300% ያነሰ  ማለት ጀምረዋል ጎበዝ ሆነህ አንተ አንች የዩኒቨረስቲ አስተማሪ ከሆናችሁት እኛ ዲግሪና ዲፕሎማ የገዛነው እንሻላለን  ሲሉ ተሳልቀዋል ባስቸኳይ የስራ ማቆም አድማ ካልተጠራ ..
@EUASAs

Ethiopian Lecturers Voice

05 Oct, 18:03


ምን ታስባላችሁ ?
1. https://www.facebook.com/HakimEthio
2. https://www.facebook.com/Teachersnetwork1
3. https://www.facebook.com/profile.php?id=100077487704652

እነዚህ በጣም ብዙ ተከታይ ያልቸው የሰራተኞች ድምጽ ናቸው። በቴሌግራም እኛ ከምናደርገው ትግል የእነሱ አንድ ፖስት ብዙ ሰው ጋር ተደራሽ ይሆናል። ምናልባት ሌሎች ብዙ ተከታይ ያላቸው የሰራተኞች ገጾችን ማስተባበር እና አጀንዳወች በጋራ ተቀርጸው የመብት ትግል ቢደረግ ለዉጥ ይመጣል።

ምን ታስባላችሁ?
@EUASAs

Ethiopian Lecturers Voice

30 Sep, 08:46


“አንሶላችን ከተቀየረ 8 ዓመት ሞላው”

ሙዝ በዳቦ እየበሉ 'ፒኤችዲ' የሚማሩ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰቆቃ
!

አስተማሪን? በጫማው ትለየዋለሁ እኮ። አንድን ጫማ ለብዙ ዓመታት ነው የምንጫማው። ብዙ ሲረገጥ የአቀማመጥ ሚዛኑን ያጣል።“እኛ ግቢ ብትመጣ ትደነግጣለህ። የብዙ መመህር ጫማ ተንሻፎ ነው ያለው። ድምጽ አውጥቶ ‘ጣሉኝ!’ ነው እያለ ያለው። እንዴት ትጥለዋለህ? ግማሽ ደመወዝህ ደህና ጫማ እንደማይገዛ እያወቅክ? “ታች ግቢ ለምሳሌ ኮመን ኮርስ የምንሰጣቸው የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች አሉ። 5 ዓመት ገደማ ዩኒቨርስቲ ይቆያሉ። እና ሸፋፋዋን ጫማህን ያውቋታል። ጃኬትህን ያውቋታል። ገደድ- ሸፈፍ እያልክ ስትመጣ ከርቀት ይለዩሃል። በጫማህ ባይለዩህ፣ በጃኬትህ ይለዩሃል። ደግሞ ይቀልዱብሃል። ባይቀልዱብህም እንደሚቀልዱብህ ታስባለህ። በአጠገባቸው ስታልፍ ትሸማቀቃለህ። ይህ ነገር ስሜትህን ይጎዳዋል።

“አስበው! አንድ የኢንጂነሪንግ ተማሪ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በኬሚካልም ይሁን በመካኒካል ኢንዱስትሪ እስኪመረቅ ድረስ አንተ መምህሩ ጫማ መቀየር አለመቻልህ...አያምም?
“በአጭሩ ቅድም ‘ኑሯችን ጫማችንን ነው የሚመስለው’ ያልኩህ ለዚያ ነው።”

አንዳንድ የሰቆቃ እና የሰቀቀን ታሪኮች

ይህ ጥናታዊ ዘገባ የዩኒቨርስቲ መምህራን ላይ ያጠነጥናል፤ ከእነርሱም ውስጥ ፒኤችዲ የሚማሩት ላይ ያተኩራል። መምህራኑ የበለጠ በተማሩ ቁጥር የበለጠ እየተራቡ እንደሆነ ያወሳሉ። ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በተለይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዲሠሩ ከተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች የተመደቡ መምህራን ለቅሷቸው የእናቱን ሞት ያረዱት ሰው ያህል ነው። “በተመጣጠነ ምግብ እጦት የተነሳ እየቀነጨርን ነው” ብለው ያማርራሉ።

ቢቢሲ በርከት ያሉ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ለወራት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ቆይቷል። ከጉዳዩ ስፋት የተነሳ የብዙዎቹ ኑሮ በአምስት መምህራን ታሪክ ውስጥ ጨምቆ ማስቀመጡ የተሻለ መንገድ ሆኖ አግኝቶታል። ‘ዕጩ ዶክተሮቹ’ የሰቆቃ ሕይወታቸው በቤተሰባቸው ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ሐፍረት ለማስቀረት፣ በተማሪዎቻቸውም ላይ አሉታዊ ስሜት ለማስወገድ ማንነታቸው በፊደል ተወክሏል።

“ቀንም ማታም ቀጭን ሽሮ ነው የምበላው”

“ልጆቼንና ባለቤቴን ገጠር ትቻቸው ነው የመጣሁት።አዲስ አበባ ባመጣቸው የት ያድራሉ? ምንስ ይበላሉ? እኔ ራሴ የማድረው ዶርም ውስጥ ለአራት ተዳብዬ ነው። በስተርጅና እንዲህ እኖራለሁ አላልኩም ነበር። ለዚህ 1500 ብር እከፍላለሁ። ሦስት ልጆች አሉኝ። በየወሩ ለቤተሰብ 7ሺህ እልክላቸዋለሁ። እጄ ላይ ስንት ቀረ? 1ሺህ ቀረችኝ። አንድ ሰው በ1ሺህ ብር አንድ ወር እንዴት ነፍሱን ያቆያል? ሌላም ወጪ አለብኝ። የልጆች የትምህርት ቤት ክፍያ። 2ሺህ ብር ነው። ከየት አምጥቼ ልክፈል? ከዚያም ከዚህም ተበዳድሬ እከፍላለሁ። የሚያቃዠኝ ልጆቼ ቢታመሙስ የሚለው ነው። እንቅልፌን አጣለሁ። እግዜር ረድቶን እስከዛሬ አልታመሙም። በቃ በየወሩ ጸሎቴ ልጆቼ እንዳይታመሙ ብቻ ነው። ምን ይውጠኛል? በምኔ አሳክማቸዋለሁ?
አንዳንዴ ችግር ሲጠናብኝ ወንድሜ አለ፤ በወር በወር እንዲደጉመኝ እለምነዋለሁ። አይጨክንብኝም። በወር 4ሺህ ብር አካባቢ ይቆርጥልኛል። እሱ ባይኖር ምን ይውጠኛል? ይህን ሁሉ ዓመት ተምሬ ራሴን አለመቻሌ ግን የእግር እሳት ይሆንብኛል።

ስለ ልጆቼ ልንገርህ?

የአስተማሪ ልጅ መዝናናት አያውቅም። ልብስ አይቀይርም። ልጆቼ ልብሳቸው ሰውነታቸው ላይ ያልቃል። ባደጉ ቁጥር እደነግጣለሁ። ሱሪው ያጥራቸዋላ። ልብስ መግዛት ሊኖርብኝ ነው። አባት ልጁ ሲያድግ መደንገጥ አለበት? እኔ ግን እደነግጣለሁ። ምንም ማድረግ አልችልም። ከየት አምጥቼ ነው ልብስ የምገዛላቸው? አስተማሪ ነኝ። ሙስና አልሠራ። እዚህ አገር ሙስና ካልሠራህ መኖር ትችላለህ እንዴ? ተወኝ በናትህ። ፒኤችዲ በአብዛኛው 4 ዓመት ነው የሚወስደው። በ6 ዓመት ያልጨረሱ አሉ። አእምሯቸው የተነካ አሉ። ‘ያበዱ’ መአት ልጆች አውቃለሁ። እንዴት ትማራለህ በዚህ ጭንቅ? ከአራት ኪሎ - 6ኪሎ ዞር ዞር በል። ብቻውን የሚያወራ ሰው አታጣም። የፒኤችዲ ተማሪ ነው።”

“ጓደኞቼን ካየሁ መንገድ እቀይራለሁ”

“ስለ ጓደኞቼ ልንገርህ? ድሮ አብረውኝ የተማሩ ጓደኞቼ ብዙዎቹ ባንክ ይሠራሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ናቸው። ይናፍቁኛል - እናፍቃቸዋለሁ። ግን በፍጹም አላገኛቸውም። ከርቀት ካየኋቸው ራሱ መንገድ እቀይራለሁ። ለምን በለኛ? ልጋብዝህ ሲሉኝ ይሰማኛል። ግብዣውን ብፈልገውም ወደ ኋላ መቅረቴ ያንገበግበኛል። አሁን አንድ ጓደኛዬ አለ። የውጭ ድርጅት ውስጥ ነው የሚሠራው። 2500 ዶላር ገደማ ያገኛል። ኑሮው ያስቀናኛል። ከአንዳንዶቹ ጋር መንገድ ካገናኘን፣ ‘ተው እንጂ! አትራቀን፤ እናግዝሃለን’ ይሉኛል። እሸማቀቃለሁ። ‘ምነው አሞህ ነበር እንዴ?’ ይሉኛል። ‘ራስህንማ እንደዚህ አትጣል’ ይሉኛል። ብዙ ሰው ጀዝቦ ቀርቷል እኮ። እኔ እግዜር ረድቶኝ እጅ አልሰጥ ብዬ እንጂ ብዙ ልጆች እኮ አእምሯቸው ተነክቶ መንገድ ወድቀዋል። ቀልዴን መሰለህ? ይሄ ይገርምሃል እንዴ? ፍቺ የፈጸሙ አሉ። ትዳራቸው የፈረሰ አውቃለሁ፤ በጭንቅ። ሱስ ውስጥ የወደቁ አሉ። ያበደ አስተማሪ 2 እና 3 በየዩኒቨርሰቲው አታጣም። ቀልዴን መሰለህ? እኔ ራሴ አንዳንዴ እያበድኩ ይመስለኛል። ቤተሰቤ ይደውላሉ። ባለቤቴ በጣም ስትቸገር ትደውላለች። ‘እስከመቼ ነው በዚህ ድህነት የምታኖረን? ለምንድን ነው ትምህርቱን ትተህ ሥራ የማትፈልግ?’ ትለኛለች። እኔም ነገሩን አስቤበት ነበር። ነገር ግን በማስተማር ላይ ነው ዕድሜዬን የፈጀሁት። እንዴት ነው አሁን ድንገት ልምድ ሳይኖረኝ ኤንጂኦ እና ባንክ የሚቀጥረኝ? ማን አስተማሪን ይቀጥራል ደግሞ? የመረጥነው መንገድ በጣም ጎዳን - ወንድሜ። ከዜሮ መነሳት ይከብዳል።
እንደነገርኩህ ጓደኞቼ አሉ። በጥሩ ጊዜ ኤንጂኦ የገቡ። በትምህርት ብዙም ያልገፉ። ጂፕላስ- 2 ቤት የገነቡ። እኔ በዚህ ዕድሜዬ ፒኤችዲ እየሠራሁ ዶርም ውስጥ ከ4 ሰው ጋር ተዳብዬ እኖራለሁ።

“እናቴ ደውላ አለቀሰች”
“አንሶላችን ከተቀየረ 8 ዓመት ሞላው”
“ምናለ ጎበዝ ተማሪ ባልነበርኩ” እላለሁ“ባለቤቴ ናት ሱሪ የገዛችልኝ”
“የድሃ ድሃ ነን”

“ከሰው አልጨመርም። አብዝቼ እተክዛለሁ። ፊደል ያልቆጠረ ብዙ የማውቀው ሰው ቤት ንብረት አለው። የተሻለ ሕይወት ይመራል። እኔ ለምን ተማርኩ እላለሁ - አንዳንዴ። እንደሱ አይባልም - አውቃለሁ። ግን ምን ላድርግ? ወደ አእምሮዬ የሚመጣውን ነው የምነግርህ።

“አእምሮዬ ልክ አይደለም”
“የፒኤችዲ ትምህርቱ ያን ያህል ከባድ አይደለም። ግን ቀልባችን ተበተነ። በትምህርቴ ላይ ማተኮር ተቸገርኩ። በዚህ የተነሳ መቀጠል አልቻልኩም።
እንዴት አይሰማኝም ታዲያ?”
#ቢቢሲ #BBC

@EUASAS
https://t.me/EUASAs/1576 [Special thanks to excellent members. https://t.me/EUASAs/1576]

Don't afraid to share it!
https://www.bbc.com/amharic/articles/cpv2k0d714ro

Ethiopian Lecturers Voice

29 Sep, 12:50


ከ22 ብር ወደ 100 ብር - የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት ዋጋ ተመን

በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት ዋጋ ተመን ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሐምሌ መግለፁ ይታወቃል። ይሁን እንጂ የ2017 ትምህርት ዘመን መጀመርንም ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ቀድሞ በነበረው የበጀት አሰራር ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ ይገኛሉ።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የሰጡት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ፣ የተሻሻለው አዲስ የበጀት አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ብለዋል። "ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አንድ አይነት የሜኑ በጀት ይሁን ወይስ በየአካባቢው የሚገኘውን ሀብት መሠረት ያደረገ በጀት ይሁን" በሚለው ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ የተሻሻለው አዲስ የሜኑ አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በዚህም የአንድ ተማሪ የቀን ወጪ ከ100 ብር በላይ እንደሚሆን ገልፀዋል። ዩኒቨርሲቲዎች በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት በቂ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከተለያዩ በጀቶች በማዛወር በቀን እስከ 80 ብር በመመደብ ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ እንደሚገኙ ይገልፃሉ፡፡ የዋጋ ትመናው ጊዜውን ያላገናዘበ በመሆኑ ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ የተለያዩ አካላት ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ ጥናቶች "እስከ ነሐሴ 2016 ዓ.ም ድረስ ሥራዎች ተጠናቀው በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ የቀን ዋጋ ተመን ይፋ ይደረጋል" ብለው እንደነበር አይዘነጋም፡፡


@EUASAs

Ethiopian Lecturers Voice

24 Sep, 11:58


MoE? Where are you?

Ethiopian Lecturers Voice

24 Sep, 11:58


MoE? Where are you?

Ethiopian Lecturers Voice

20 Sep, 14:24


መምህርነት የሙያዎች ሁሉ አባት!!
****
መምህራን ትውልዱን ከአለማወቅ ወደ ማወቅ ከጨለማ ወደ ብርሐን የሚመሩ የእውቀት አባቶች ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ  መምህራን የአለም የእውቀት ብርሐን ሲባሉ እናዳምጣለን!! እውነትም መምህራን የአለም የእውቀት ብርሐን ናቸው፡፡
ዛሬ በሳይንስና ቴክኖሎጅ የበለጸጉት ሀገራት የእድገት ሚስጢር ትምህርት ላይ ትኩረት አድርገው መስራታቸው እንደሆነ ታወቆ ያደረ ሀቅ ነው፡፡ ትምህርት ማለት የሰው ሀብትን ዘመናዊ በሆነ መንገድ ማልማት ነው፡፡ በሰው ሀብት ልማት ሂደቱ ዋናው ተዋናይ ደግሞ መምህራን ናቸው፡፡  መምህራን  በትምህርት ስርዓት ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ቁልፍ ተዋናዮች ናቸው፡፡ የተማሪዎችን ትምህርት እና እድገት ላይ በተለያዩ  መንገዶች  ተጽእኖ ያሳድራሉ፡፡ በዓለምም ሆነ በአገራችን ትልልቅ ቦታ ላይ የደረሱ ተመራማሪዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣….በትምህርት ዓለም ያለፉ በሙሉ በመምህራን ተኮትኩተው ያደጉና የተመከሩ ሳይንስን ከተግባር ጋር አዋህደው እንዲያውቁ የታገዙ ናቸው፡፡ በመሆኑም መምህርነት የተከበረና የተወደደ ሙያ እንደመሆኑ መጠን ለሙያዉና ለሙያ አባቶች ክብርና ድጋፍ ማድረግ የሁሉም አካል እንዲሆን ሁላችንም መስራት ይጠይቀናል፡፡ ምክንያቱም፡-
* መምህራን የመማር አመቻቾች ናቸው፡፡ መምህራን አሳታፊ እና interactive ትምህርቶችን በመፍጠር የተማሪዎችን  የመማር ሂደት የሚመሩ ናቸው። መምህራን ተማሪዎች ውስብስብ ፅንሰ ሀሳቦችን እንዲረዱ እና ሂሳዊ አስተሳሰብን(Critical thinking)እንዲያዳብሩ  ያበረታቷቸዋል፤ ይረዷቸዋል።
* መምህራን አማካሪዎች እና አርአያዎች ናቸው፡- መምህራን እንደ አማካሪ ሆነው ለተማሪዎች ድጋፍ ያደርጋሉ ፡፡ ለተማሪዎች ማበረታቻ ይሰጣሉ፡፡ተማሪዎች ሊከተሏቸው የሚገቧቸውን  ባህሪያትን፣ አመለካከቶችን እና እሴቶችን ሞዴል ሆነው ያሳያሉ ይመክራሉ፡፡
* መምህራን የሂደት ገምጋሚዎች ናቸው፡፡ መምህራን የተማሪውን ግንዛቤ በግምገማ ይለያሉ፤ በዚህም ተማሪዎች እንዲሻሻሉ የሚያግዝ አስተያየት ይሰጣሉ። መምህራን የግለሰቦችን ፍላጎቶች ለማሟላት ለውጥ ተኮር መመሪያዎችን ይከተላሉ፡፡ በሂደቱ የሚያጋጥሙ እንቅፋቶችን ይቀርፋሉ፡፡ ሁልጊዜም ለለውጥ ይዘጋጃሉ፡፡
* መምህራን የስርዓተ ትምህርት ዲዛይነሮች ናቸው፡፡ መምህራን ብዙውን ጊዜ ሥርዓተ ትምህርቱን በመንደፍ፣ ቁሳቁሶችን በመምረጥ እና የተማሪዎቻቸውን ፍላጎት ለማሟላት ይዘቶችን መርጠው ለተማሪዎች በሚመጥን መንገድ ያቀርባሉ
*መምህራን ለተማሪዎቻቸው ተሟጋቾች ናቸው፡፡ መምህራን የተማሪዎቻቸውን ፍላጎት በትምህርታዊም ሆነ በግል ለማሟላት ያለእረፍት ይሰራሉ። ሁሉም ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ የሚሆኑበትን መንገድና አካባቢ ለመፍጠር ይተጋሉ። አማራጭ መፍትሔዎችንም ይፈልጋሉ፡፡
*መምህራን ለተማሪዎች መማር ተባባሪዎች ናቸው፡፡ መምህራን የትምህርት ስራን ለማጎልበት ከስራ ባልደረቦቻቸው ፣ ከወላጆች እና ማህበረሰቡ ጋር በቅርበት ይሰራሉ። ይህም በመሆኑ ትምህርት ቤቱን ከማህበረሰቡ ጋር በማቆራኘት ለመማር ማስተማሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡
*መምህራን የዕድሜ ልክ ተማሪዎች ናቸው፡፡ መምህራን ችሎታቸውን እና እውቀታቸውን ያለማቋረጥ ለማዘመን አንባቢዎች ናቸው፡፡ ይህ ባህሪያቸው ተማሪዎቻቸው  ከክፍል ትምህርት በዘለለ  ለትምህርት ከፍተኛ ዋጋ እንዲሰጡ ያነሳሳቸዋል።
በአጠቃላይ መምህራን የትምህርትን ገጽታ በመቅረጽ ረገድ አጋዥ ናቸው። የመምህራን  ተጽእኖ ከአካዳሚክ ስኬት በላይ የተማሪዎችን  የግል እድገት በማጎልበት እና ተማሪዎችን ለወደፊት ፈተናዎች በማዘጋጀት ረገድ የሚፈጥሩት ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ለትውልዱ መማር ያላቸውን ሚና ተረድተን ሁላችንም መምህራንን ማክበርና መንከባከብ ይገባናል፡፡

                                
ለመምህራን ክብር እንስጥ!!
AEB
@EUASAs

Ethiopian Lecturers Voice

19 Sep, 07:40


https://addisfortune.news/wage-reform-fails-to-soothe-the-civil-service/

Ethiopian Lecturers Voice

13 Sep, 18:00


ከምሁራዊ ፁሑፍና ሀሳብ ወርቅና ሰም በማለያየት  እየኖርክ ያለኸው   መ/ር    የማይታማን ሰበር  ዜና  ስሙ
የንግድ ባንክ ታይቶና ተሰምቶ  የማይታወቅ  ከዚህ ፊት  ሐምሌ 1/2011 ቀጥሎ  በ2013 ከተደረገው  ደመወዝ ጭማሪ አሁን ላይ በአይነትና በመጠን ለየት ባለ መልኩ  ለ3ኛ  ጊዜያት  ተሰርቶ በቦርድ   ፅድቆ   ለዩኒቨርስቲ መ/ራን ጠል አህመድ ሸዴ ቀርቧለት   የገነነ   ነው ይስተካከል በማለት ክርክር ላይ ይገኛሉ ።

ይህ ጭማሪ በተደጋጋሚ አንዴም ለእኛው ሳይደረግ የተለቀቀው ዋናው ም/ት-

1. ከሙት የምሁር  ካንሰር ከሆነው ከሲቪል  ሰርቢስ ኮሚሽን ተገንጥለው ተቋማቸውን በቦርድ ስለተዳደሩ

2. ሠራተኛቹ የተናበበ በጥቅማቸው ላይ አተኩረው በጋራ በመታገላቸው

3. እኛ በፍራቻ ባህር ዋና ውስጥ በመሆናችን እየተደቆስን እንገኛለን ።

4. መ/ራን ከአንድነት ይልቅ መለያየትን መሠረት በማድረግ ፣  በሰፈር፣ በብሔር፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ በእምነት  የተከፋፈለ በመሆኑ የምድርን የኑሮ ምፃዕትና ሰቆቃ እየኖረ ይገኛል።

አይን የሚያየውን፣ ልቦና የሚያስበውን ፣ ህሊና የሚናፍቀውን ሳያሟላ ኑሮውን እየኖረ ይገኛል።

መፍትሔው


ደመወዝን ማስጨመር ብቻ ዘላቂ መፍትሔ ሳይሆን ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጥገኝነት በመውጣት የመ/ራን ኮሚሽን ማቋቋም  መቻል ነው።

Ethiopian Lecturers Voice

10 Sep, 07:27


Our 2017, please .......

Ethiopian Lecturers Voice

08 Sep, 20:21


https://t.me/EUASAs/1659

Ethiopian Lecturers Voice

08 Sep, 19:53


ይህ የደሞዝ አማራጭ በሚንስትሮች ምክር ቤት መጽደቅ ይኖርበታል። ያኛውን አንቀበለዉም።

ይሄን ለመጠየቅ አትፍራ ! ሁሉም ካድሬ ይህን ደሞዝ ማግኘት ይፈልጋል። የሰራተኛዉን ትግል ይደግፋል። ይህ ደሞዝ እስኬል በሁሉም ዘንድ መስረጽ ይኖርበታል። ሼር

ሃሳብ ስጡበት

https://t.me/boost/EUASAs
https://t.me/boost/EUASAs
https://t.me/boost/EUASAs

Ethiopian Lecturers Voice

08 Sep, 19:52


Live stream finished (1 hour)

Ethiopian Lecturers Voice

08 Sep, 17:58


Open Meeting, አወያይ ሆኖ መምራት ትችላላችሁ። መምህር የመምራት አቅም በማንኛዉም ሁኔታ አለው። inbox @MessageELAbot to lead

Ethiopian Lecturers Voice

08 Sep, 17:56


Live stream started