ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

@historicalheromedia


በዩትዩብ ቻናላችን ሰብስክራይብ ያድርጉ
👉https://www.youtube.com/@Historicalheromedia
ጥቆማ ለመስጠት
👇👇👇
@ethiotemsaletbot

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:26


💚💛 በዘመቻ በሃይሉ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር በአገዛዙ ሰራዊቶና አመራሮች ላይ በወሰደው ድንገተኛ ደፈጣ ጥቃት ከፍተኛ ድል ተቀዳጀ።
ጥቅምት 12/2017 ዓ/ም
ሸዋ አማራ ኢትዮጵያ
በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ዋና ጦር አዛዥ ፊትአውራሪ ኢ/ር ባዩ አለባቸው እና በናደው ክፍለጦር ዋና ጦር አዛዥ ቀኝ አዝማች ይታገስ በተመራ በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን የአገዛዙ አሽከር የሆኑት የመርሃቤቴ ወረዳ የብልፅግና አመራሮች በባህርዳር ስብሰባ ሰንብተው እና በአገዛዙ ሰራዊት ታጅበው ከለሚ ወደ መርሃቤቴ አለም ከተማ ለመቀባበል እንዲሁም በዚህ ሳምንት ከአለም ከተማ ያገታቸውን ባለሃብቶች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች ፣ወጣቶች እና የነቁ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ወደ ሸዋሮቢት ለመውሰድ ጉዞ እያደረገ ባለበት ሁኔታ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር መቅደላ ብርጌድ ሶስተኛ ሻለቃ ዛሬ ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:20 ሰዓት ባደረጉት የደፈጣ ውጊያ በአናብስቶቹ የናደው ክፍለጦር አባላት ከጀማ ድልድዩ አቅራቢያ ልዩ ስሙ አጥበርበር በተባለ አካባቢ መብረቃዊ ጥቃት የተሰነዘረበት ሲሆን ሲሆን ጠላት የአማራን ህዝብ ለመፍጀት ሲጠቀምበት የነበረ አንድ ዙ23 ከጥቅም ውጪ ማድረግ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የወራሪው ብልፅግና ሰራዊት እስረኞቹን ተቀብሎ ወደ ለሚ እየወጣ ባለበት ሰአት ከ9:00 ጀምሮ እስከ 9:40 በቀጠለው ውጊያ በሮቃ መገንጠያ አካባቢ ላይ አይበገሬወቹ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር የራስ አበበ አራጋይ ብርጌድ አንድ ሻለቃ እና የናደው ክፍለጦር ተወርዋሪ ሰራዊት በጠላት ላይ በወሰዱት ፈጣን ምት ሀለት ሲኖትረክ እና ሁለት ኤፍኤሳር የጭነት አይሱዙ ላይ የነበረ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።

በዚህ የተበሳጨው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በየመንገዱ ላይ ያገኘውን የአርሶ የደረሰ ሰብል ሲያቃጥልና በከባድ መሳሪያ አካባቢውን ሲያሸብር ውሏል።
''ድላችን በክንዳችን''
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር የሚዲያና ኮምንኬሽን ተጠሪ ክፍል

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:26


💚💛 አሳዛኝ ዜና ‼️

ተሸናፊው የአብይ ገዳይ ቡድን በአማራ አህዝብ ላይ እያደረገ ያለውን በድሮን እና በጀት የታገዘ ድብደባ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ቀጥሎበታል።

ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም በምስራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ፈለገ ብርሃን ከተማ ንዋዬ ማርያም አንደኛ ደረጃ ትቤት አካባቢ በተደረገ የድሮን ጥቃት ለማክሰኞ ገበያ ወደ ከተማው ሲጓዙ የነበሩ በርካታ ሲቪሊያን የተገደሉ ሲሆን በሌሎች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

#ድል ለፋኖ

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:25


💚💛 የድል ዜና ‼️
/
የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር የስናን አባ ጅሜ እና የንጉስ ተክለሐይማኖት ብርጌድ ባደረጉት የደፈጣ ውጊያ ጠላት እንደ ቅጠል ሲረግፍ ውሏል።

ገና በጠዋቱ ከደብረ ማርቆስ ተነስቶ ወደ ረቡ ገበያ ስንቅ ለማቀበል ሲንቀሳቀስ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ የንጉስ ተክለ ሐይማኖት ብርጌድ የፋኖ አባላት በደፈጣ አስደንብረውት ይወጣሉ።
በዚህ የተደናበረው እና በፍራቻ የተዋጠው ፈርጣጭ የአብይ አህመድ ወንበዴ ቡድን እንደገና ሐይሉን አጠናክሮ ከደብረ ማርቆስ ባለ ጎማውን መድፍ፣ዙ23 እና ሞርታር ብሎም ድሽቃውን ጠምዶ ከደብረ ማርቆስ አስፍቶ ወደ ረቡ ገበያ ወጣ።

ረቡ ገበያ ላይ መሽጎ ስንቅ መቀበል አልችል ብሎ ራብ የሚያነጉደውና ህዝቡን እያስገደደ የእለት ጉርሱን የሚደፍነው የጠላት ኃይል ደግሞ ሞርታሩንና ድሽቃውን ጠምዶ ከከተማው ወጥቶ ስንቁን ለመቀበል ጉዞ ጀመረ።

ይህን ሁሉ ግሳንግስ የሚስበው በጠዎቱ አንድ ቲም የንጉስ ተክለ ሐይማኖት ብርጌድ በተተኮሰበት ጥይት ተደናብሮ በልመታ ነው ፍራቻ ነው።
ዳሩ ግን በነበልባሉ ሺ አለቃ ባለው ጊዜ ወንዴ የሚመራው የስናን አባ ጅሜ ብሮጌድ የፋኖ አባላት ሁለቱን ሻለቃ ግራና ቀኝ ደፈጣ አስይዞ ይጠብቀው ኖሯል።
ያልታሰበ ዱብዳ እንራታ ላይ ጠላት አለ ብሎ ሲጠብቅ የነበረ የአብይ ሽፍታ ቡድን ከረቡ ገበያ በቅርብ እርቀት ሁለቱ ስንቅ ተቀባይና አቀባይ ሳይገናኙ መንገድ ላይ ያላሰበው ዱብዳ ወረደበት።

#የፋኖ_ጥይት እንደ #ዶፍ_ዝናብ ይወርድበት ጀመር።የአብይ ፈርጣጭ ቡድን በየቀኑ ከተወሸቀበት ከተማ ወይም አስፓልት በወጣ ቁጥር ሬሳ እየጫነ መፈርጠጥ ልማዱ ነውና ዛሬም እንደ ትናንቱ ቁጥር ስፍር የሌለው ሬሳና ቁስለኛውን ሬሽን ጭኖበት በመጣው መኪና ጭኖ ተመልሷል።

ይህን ሁሉ ጀብዱ የሚፈፅሙት ሲጥሉ እንጅ ሲዋጉ ለአይን ጥቅሻ የማይታዩት የስናን አባ ጅሜ ብርጌድ የነበልባልና የፋሲካው ሻለቃ የፋኖ አባላት ናቸው።
ከጠዋቱ አራት ሰዓት የጀመረው የደፈጣ ውጊያ ወደ መደበኛ ውጊያ ተሸጋግሮ እስከ እኩለ ቀን ሰባት ሰዓት ድረስ ጠላትን ሲያደባዩት መዋላቸውን የብርጌዱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መለሰ ለክፍለ ጦራችን ቃል አቀባይ አርበኛ መ/ር ታደገ (ሸርብ) ገልጿል።
ድል ቁርሱ የሆነው የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ዛሬም በብርጌዶቹ የእለት ተእለት ተጋድሎ ታሪክ በአምዱ እያስመዘገበ ይገኛል።

አማራነት ዘላለማዊነት
አዲስ አብዮት ፣አዲስ ድል ፣አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ
በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በክንዳችንና በአንደበታችን እንፈጥራለን።

©የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ መ/ር ታደገ ይሁኔ(ሸርብ)

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:24


💚💛 ዘመቻ 100 ተራሮች በድል እንደቀጠለ ነው ‼️
-----------------------------
በዛሬው ዕለት ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በጎጃም ጃዊ መተከል ክ/ጦር ፣ ጣና በለስና መብረቁ ብርጌድ በጥምር ኦፕሬሽን መንደር 24 ከሚባል ቦታ ላይ በጥዋቱ ድል በድል ሁኗል።
1/የተማረከ ብሬን=01
2/የተማረከ ክላሽ=25
3/ምርኮኛ=10
4/የተደመሰሰና ቁስለኛ=ከፍተኛ ቁጥር

#ድል ለፋኖ

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:24


💚💛 አገዛዙ በንፁሃኖች ላይ ግፍ ፈፀመ‼️

የ8 ንፁሀን ወጣቶች የግፍ ሞትና የ450 ወጣቶች እስራት የብልፅግናው አሳፋሪ ተግባር በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም

የሽንፈት ማሳያ ጥጉን ፣የውርደት ካባውን ተከናንቦ የሚደናበረው የብልፅግናው መንግስት የቀን ስራ በመስራት የእለት እንጀራቸውን ለመብላት ከየአቅጣጫው የመጡ ከ1000 በላይ ወጣቶችን ሰብስቦ የጅምላ ግድያ ሙከራ አድርጎ ሳይሳካለት 450 ወጣቶችን በአንድ ክፍል ውስጥ በጅምላ ያሰረው ልጓም የለሹ የብልፅግናው ወንበር ጠባቂ ቡድን ማንነቱን በይፋ ገልፇል።

ራሱን ጥምር ጦር እያለ የሚጠራው የአማራ ሚሊሻ ፣የአማራ ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት በሸዋ ምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ከተማ የሚገኙ ለቀን ስራ የመጡ እና የከተማው ወጣት ነዋሪዎችን ቁጥራቸው ከ1000 በላይ የሚሆኑትን ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ለአስቸኳይ ስብስባ ትፈለጋላችሁ በሚል የማስፈራሪያ ጥሪ በአንድ አዳራሽ ሰብስበው የአገዛዙ አረመኔዎች የጅምላ ጭፍጨፋውን የአፈፃፀም እቅድ በማሴር ላይ ሳሉ በጉዳዩ ግራ የተጋቡት ወጣቶች ባነሱት የግልፀኝነት ጥያቄ "ገድለን ሳንጨርሳችሁ ማን ተንፍሱ አላችሁ?" በሚል የአገዛዙ ሹማምንቶች በሰጡት ትዕዛዝ በተፈፀመ የግድያ ተኩስ 8 ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን 450 ወጣቶች ከሞት አምልጠው በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ በጅምላ ታስረው ይሰቃያሉ። ቀሪዎቹ አምልጠው ከከተማው በመውጣት ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

ይህንን አሳፋሪ ተግባር አይደለም የአንዲት ሉአላዊት አገር መሪ ነኝ ከሚል መንግስት ይቅርና በአለም አቀፍ ደረጃ አሉ የሚባሉ አሸባሪዎች እንኳን ፈፅመውት የማያውቁት ወራዳ ተግባር ነው።

አሁንም እንላለን በየከተማው ቁጭ ብለህ እንደ መስዕዋት በግ ልትታረድ የተዘጋጀህ የማረጃ ቢለዋህ ሲሞረድ ድምፁን እየሰማህ ቁጭ ያልክ የአማራ ወጣት ሆይ በየአካባቢህ የሚገኘውን የአማራ ፋኖ አደረጃጀት በመቀላቀል ይህን ፀረ አማራ ስርዓት በቃኝ ልትል ይገባል።

ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:23


💚💛 የድል ዜናዎች በጎንደር ክፍለ ሃገር የውጊያ ግንባሮች‼️
=================================
ጀግናው ጎንደር የኦህዴድን መንጋ እያራገፈው ነው!

ጀግናው የአማራ ፋኖ በምዕራባዊና የሰሜን ምዕራብ ጎንደር ክፍለ ሃገር ግንባሮች ከፍተኛ ድልን በጠላት ላይ ተቀናጀ:: በመተማና በአርማጭሆ ግንባር የነበረው የፋሽስት ወራሪ ኦህዴድ ሰራዊት ፈራርሶ ከቀጠናው ለቅቆ መውጣቱን ከግንባሩ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል:: በአርማጭሆ ግንባር እስከ ኤርትራ ያለው የጎንደር ክፍለ ሃገር ቀጠና ጀግናው የጎንደር ክፍለ ሃገር ፋኖ ቀጠናውን ሙሉ በሙሉ ከጠላት ማጽዳቱንና ነፃ ቀጠና መፍጠሩን አስታውቋል

እንዲሁም በመተማ ግንባር እስከ አዳኝ አገር ጫቆ ያለው የውጊያ ቀጠና የፋሽስቱ ኦህዴድ መንጋ ተመትቶ መፈራሩስና መፍርጠጥ መጀመሩ ታውቋል:: በዚህ ግንባር በጎንደር አርበኞች ተቀጥቅጦ ሰራዊቱ የተበታተነበት የጠላት ኃይል ከጎጃምና ከደቡባዊ የጎንደር ክፍለ ሃገር ቀጠናዎች መንጋውን ወደ ምዕራብ ጎንደር ግንባር ለማነቃነቅ እየማከረ ይገኛል::

ጥቅም 6 እና 7 ወደ መተማ ግንባር የተንቀሳቀሰው ሰራዊት በጀግናው ደረጀ በላይ በሚመራው የቤጌምድር ክፍለ ጦር ተመቶ ለጊዜው እንቅስቃሴ ተገድቧል::

እንዲህም በማዕከላዊ ጎንደር ጎንደር ክፈለ ሃገር ቆላ ድባ ቀጠና ጠላት በቤጌምድር ክፍለ ጦር በደረሰበት ከባድ ምት መፈራረስ መጀመሩን ከቤጌምድር ክፍለ ጦር ሰራዊት የወታደራዊ ዘመቻ መኮነን ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል!

የድሮን ውጊያ ትግላችን ቅንጣት ታክል አይገታውም! በመኪና ተሳፍረህና በብዛት ተሰባስበህ ለብዙ ሰዓታት እስካልቆየህ ድረስ ድሮን ከዚህ ግባ የሚባል ትርጉም ያለው ትጽህኖ ማምጣት አይችልም!!!

# ድል ፋኖ

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:23


💚💛 አሳዛኝ ዜና ጎንደር የንፁሀን ጭፍጨፋ ‼️

አገዛዙ በንፁሐን ላይ እያደረሰ ያለን ግፍ እና ግድያ ያለ ርህራሄ ቀጥሎበታል።
ዛሬ በዚህ ሰአት ማለትም (10/02/2017) በጎንደር ደንቢያ ስምራ ቀበሌ ላይ አንድ ቤተሰብ ሙሉ በቤታቸው እንዳሉ በረጅም እርቀት ተተኳሽ ከባድ መሳሪያ ተግድለዋል። ቤተ ክርስትያን ወድሟል። አገዛዙ የወንድነት ግጥሚያ አልችል ሲል ንፁሃንን በገፍ ከማሰር አልፎ መረሸን ፣ ሀብት ንብረታቸውን መዝረፍ ፣ ማውደም፣ ማንገላታት ቀጥሎበታል።
ትናንት ደንቢያ ሮቢት በመግባት ቤት ላይ የሚገኙ ሴትና አዝውንት ሽማግሌዎቹን በማገት ወደ ቆላድባ ወስደው እያንገላቷቸው ይገኛል። በዚህም ወይዘሮ ናናየ የሚባሉ እናት ህወታቸው ወዲያኑ ሲያልፍ ሁለቱ ቤተሰብ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ንፁሀን በመረሸን ህዝብን በማንገላታት እሚቆም ትግል የለም።

#ድል ለአማራ ህዝብ

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:23


https://youtu.be/ZvIQX6Gpw-Y

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:23


•"ከግድያ ሙከራ መትረፍ የኦሎምፒክ ውድድር ቢሆን ኖሮ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፍ ነበር።"-
ይህን ያለው ከ 600 ጊዜ በላይ ከግድያ ሙክራዎች እንዳመለጠ የሚነገርለት የቀድሞው የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ ነበር።

የግድያ ዜና በ 2025ቱ ( የፈረንጆች አቆጣጠር) የጃፓን ቶክዮ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አንዱ የውድድር አይነት ከሆነ በሰሞኑ የነ አብይ አህመድ የተስፋ መቁረጥ "የገደልነው ዘመቻ" ብቻ ወርቅ ባላገኝ የብር ሜዳሊያ አላጣም ።የመለያ ቁጥሬም 21-12 ይሆናል።

•በሁሉም ረገድ፣ በሁሉም ሰበብ እና ምክንያት ልትጠልፉኝና ልታጠለሹኝ የሞከራችሁ እና በየቀኑ የምትሞክሩ ሰዎችና ቡድኖች መጨረሻችሁ ውርደት እና የእድሜ ልክ መሸማቀቅ እንደሚሆን ዛሬ ድረስ በጥቂቱ በምታውቁት፣ነገና ከነገ ወዲያ ደግሞ ሰፊውን ማንነቱን በምትረዱት በዘመነ አምላክ ስም እነግራችኋለሁ ።አምላኬ ይቅር ይበለኝና ብዙዎች አይሆን ሞክረውኝ፣ ደጋግመው ሞካክረውኝ መጨረሻቸው የሌባ ጣት ጥፍራቸው ውስጥ መደበቅ ሆነ። (ድንግል ማርያምን ያሳዝኑኛል።)

የቀብሮ ጫጫታ የማያስደነብረኝ፣ጀርባዬ ላይ ሊወጣ የሚሞክረው ሁሉ ቢሳካለት እንኳን የማይከብደኝ "ዝሆን" ነኝ።በቃ እንደዚህ ነው የሰራኝ።

•ከንግስና ዙፋንና ዘውድ ጀምሮ በተለያዩ የህዝብ አስተዳደር እርከኖች እና ሃላፊነቶች እስከ ጦር ሜዳ ውሎዎች በብዙ ፈተና መሃል እያለፈ ሃገር የገነባ ቤተሰባዊ ማንነትና የመከራ ዘመን በቅጡ የገነባኝ ሰው ነኝ።በአለሙ ውስጥ በማንኛውም ሁኔታ እንደ ህፃን በደስታና በሃዘን በእምባ የምሟሟ ተራ ሰው፣ምድራችን በድንገት ጨረቃ ብትሆን እንኳን የማይጨንቀኝ ልበ-ሙሉ "ጨካኝ" ፍጡር ነኝና በጅራፍ ጩኸት ልታስደነብሩኝ የምትሞክሩ የዋሆች አትድከሙ።

•እኔና ጓዶቼ ፣ከትውልድ አጋሮቻችን ጋር እንደምናሸንፍ የተፃፈው የእናቶቻችን ማህፀን ውስጥ እያለን ነው።ወኔና ድል አድራጊነትንም የተጋትነው በእትብት ነው።ይህ ትውልድ አሸናፊ ትውልድ ነው።ልድገመው!ይህ ትውልድ የአሸናፊነት እጣፋንታውን ግንባሩ ላይ ተነቅሶ ወደዚህ ምድር የተላከ ትውልድ ነው።
እየታገለ ነው ፥ድል አድርጎ የአማራን ህዝብ ህልውና በፀሃይ ፊት ያረጋግጣል።

ይህ ትግል ለትግሉ ብቻ የተሰጠ እና የሚሆን ራሱን የቻለ ልዩ ነፍስ ይፈልጋል።እንጨት እንጨት የሚል ሰዋዊና ፖለቲካዊ ስብእና ተይዞ ፥ነፍስን ቅናት፣ምቀኝነትና ተንኮል በሚባሉ የመንፈስ ቆሻሾች መርዞ ታጋይም አታጋይም መሆን አይቻልም።እና "ልፋ ያለው በህልሙ ዳውላ ይሸከማል" እንዲሉ በብዙ የተበከለች ነፍስ ተሸክማችሁ ለ ደካማ ተልእኮ አጉል የምትደክሙ ወገኖች
ከድል ሃውልት ውጭ ከፊታችን መቆም የሚችል ነገር የለምና ነፋስን ለማሰር በመሞከር ጊዚያችሁን አታጥፉ።ይህ ትውልድ እያለ የአማራን ህዝብ ጉልበት መሬት አታስነኩትም።በኩራት ቆሞ ገጥሟችኋል፥ያሸንፋችኋል።

እና በባንዶች ፊታውራሪ በተመስገን ጥሩነህ አገላለፅ "ዘመነን አስወግደነዋል፥ከዚህ በኋላ ድምፁን አትሰሙትም" የሚለውን የሰሞኑን ብልፅግናዊ አዲስ መዝሙር ስቃችሁበት እለፉ።ሌት ተቀን እያቀድንላቸው ነው።ከጠፋሁም ያጠፋኝ የጠላት ስሥ ብልት ልየታ ቢዚ አድርጎኝ ነው።የዘመነ ትውልድ የአለማችን እድለኛና ገድለኛ ትውልድ ነው።መንጋው እንዲበተን እረኛውን ምታው የቆዬ ብሂል በኛ ትግል ውስጥ አይሰራም።ትግሉ ሚሊዮን እረኞች ከበውታል፥መንጋው ራሱ ረኛ ከሆነ አመታት አልፈዋል።

ዘመነ የእናንተን ሞት ቆሞ ለማዬት ለተአምር ተፈጠረ እንጅ በዘመነ መጥፋት ለአንድ ሴኮንድ እንኳን የሚንገራገጭ ትግል የለም።ይህ ትውልድ ከቀደምቶቹም ከነገዎቹም ትውስታና መንፈስ ቀድቶ የትሸከመውና ያጎለበተው ከእድሜውና ተሞክሮው በላይ ያበሰለው አንዳች ነገር አለው።ስለሆነም ያሸንፋል።
ይኸው ነው!!
በአዲሱ ዘመቻ እና ድሎቹ እንገናኛለን!!

አንድ አማራ!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ
ጥቅምት 10 ቀን-2017 ዓ.ም

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:23


💚💛 አስቸኳይ መረጃ ‼️

አራዊት ሠራዊቱ ከመኮድ ባህር ዳር ነቅሎ የወጣ ነው የሚመስለው አመራሮችም በነጭ ፒካፕ መኪና አሉ 2 መድፍ፣ ሮኪት፣ bm toyota ላይ የተጫነ ዙ23 ወደ ጎንደር አቅጣጫ ከበርካታ ሎቤድ ጋር እየወጡ ነው ዘንዘልማ ይደርሳሉ‼️

መረጃዉ ለወገን ጦር ይደርስ!

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:22


💚💛 የድል ዜና‼️

#ደምበጫ
የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር የኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ባደረጉት የደፈጣ ውጊያ ሁለት አድማ ብተና እና ሁለት ሚኒሻ እስከወዲያኛው ሲያሰናብት አራት ቁስለኛ ደግሞ ጠላት  ታቅፎ እንዲሔድ አድርጓል።
ድል ቁርስ የሆኑት የኢንጅነር ክበር ተመስጌን የፋኖ አባላት የነፍስ ወከፍ መሳሪያም ለመማረክ ችለዋል።
በደንበጫ ከተማ ወሽቆ የሚገኘው የጠላት ኃይል በየቀኑ እየከዳ ወደ ፋኖ እየተቀላቀለ ቢሆንም ተርፎ ከጠላት ወገን ተሰልፎ የሚገኘውን ደግሞ ሌትም ቀንም ደፈጣ በመያዝ እረፍት መንሳታቸውን የብርጌዱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ተበጀ ማተቤ ለቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ ገልጸዋል።

#ቁሌች
በየቀኑ ድል መጎናፀፍና የብልፅግናውን ወንበዴ አራዊት ሰራዊት ማስጨነቅ ልማዳቸው የሆኑት የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ የፋኖ አባላት ጠላት በአንድ ኦራል እና በአንድ ሲኖ ተጭኖ ከደብረ ማርቆስ ተነስቶ ወደ አማኑኤል እየበረረ ባለበት ወቅት ቁሌች በምትባል ቦታ ደፈጣ በመጣል በሁለቱም መኪኖች የጥይት በረዶ ሲያወርዱባቸው ከሁለቱም መኪና ላይ ጠላት እንደሚዘራ በቆሎ እየተንጠበጠበ ሲወድቅ መኪኖቹ በፍጥነት ይበራሉ።ማቆም የሚባል ነገር የለም።

ነፍሴ አውጭኝ ያለው ሹፌር ከሁለቱም መኪና ከአውቶማቲክ ጥይት የተረፉ ከሀያ ያልበለጡ አራዊት ሰራዊት ብቻ ነበሩ።ተጭኖ የመጣው የጠላት ሀይል ከፊሉ በፍራቻ ከፊሉ ደግሞ የጥይት እራት በመሆኑ ከሲኖውና ከኦራሉ እየተንጠባጠበ ወድቋል።

በየት ገብተው በየት እንደሚወጡ ለአይን ጥቅሻ እንኳን ለጠላት የማይታዩት የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ የፋኖ አባላት ጠላት በየመንገዱ ሲያንጠባጥቡት ውለዋል።

በሰዓታት ልዩነት ከአማኔል የተነሳው ዙ-23 እና ዲሽቃ የጫነ መኪና ከቦታው ቢደርስም የፋኖ አባላት ግን ከስፍራው የለም።ታሪክ በእጁ መጣፍ ልማዱ የሆነው የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ የፋኖ አባላት ጠላት በየመንደሩ ዙ23 እና ሞርታር ቢወረውርም ዛፍና ሰብል ላይ ከመውደቅ በስተቀር ነበልባሎቹ የፋኖ አባላት ግን ስራቸውን ሰርተው ወጥተዋል።

ጠላት ማርቆስ ይመጣሉ ብሎ ሲያስብ መንገዱ ሁሉ እሾህ የሆነበት የአብይ አህመድ አራዊት ወንበዴ ቡድን ይገባበት ጉድጓድ ይሸሸግበት ቦታ አጥቷል።
ዘመቻ መቶ ተራሮች የተቋረጠ የሚመስለው የብልፅግናው ወንበዴ ቡድን ከማርቆስ ተንደርድሮ አማኑኤል በነፃነት ሊገባ አደለም በሰልፍ መንገዱን አጥሮም መንቀሳቀስ አልቻለም።
አዲስ አብዮት፣አዲስ ድል፣አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በክንዳችን እና በአንደበታችን እንፈጥራለን።

©የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ መ/ር ታደገ ይሁኔ

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:22


💚💛 ሰበር ዜና‼️

በዛሬው ዕለት ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም የአገዛዙ ሰራዊት ከአዲስ ዘመንና ከእብናት ኃይሉን አግተልትሎ በአንቦ ሜዳና አካባቢው ወረራ ለመፈፀም በሌሊት ጀምሮ በተለያዩ አቅጣጫዎች እንቅስቃሴ ቢያደርግም በጀግናው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር አንበሳው ሊቦ ከምከም ብርጌድ ተመክቶ መመለሱን የእቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

ከአዲስ ዘመን አቅጣጫ የተነሳው የጠላት ሀይል በተለያየ አቅጣጫ በማስፋት ከበባ ሊፈፅም ቢሞክርም ብራ በተባለው አካባቢ ደፈጣ ይዞ የቆየው የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር የአንበሳው ሊቦ ከምከም ብርጌድ ነበልባል ሻለቃ ሙትና ቁስለኛ አድርጎ ወደመጣበት አስፈርጥጦ ልኮታል ሲል ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለጣቢያችን ገልጿል።

የጠላት ሀይል ከላይ የጀት ሀይል በማንሳፈፍ በምድር ዲሽቃና ሞርተር አግተልትሎ ቢገባም በአናብስቶቹ የሊቦ ፋኖ ተመትቶ የክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መልካሙ ጣሴ ለኢትዮ 251 ሚዲያ አክሎ ገልጿል።

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:20


💚💛 የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእለቱ መልእክት
(ጥቅምት 08-2017 ዓ.ም)

ለጀግናው የአማራ ህዝብ እና ለክፍለ-ዘመኑ የአፍሪካ ቀንድ ክስተት የአማራ ፋኖ አመራር እና አባላት!!
__________
በዘመቻ መቶ ተራሮች ባለፉት አስራ ስድስት ቀናት እጅግ የበዙ የድል ታምራትን አሳይተናል።በሌላ ድንቅ የዘመቻ እቅድ እስኪተካም ዘመቻ መቶ ተራሮች ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ወገኖቼ! ጓዶች!!
ይህ የህልውና ትግል በፍጥረቱም፥ በፍጥነቱም በባለቤቶችም ብዙ ነገሩ የተለዬ በመሆኑና በሌሎች ብዙ አካባቢያዊና ቀጠናዊ ምክንያቶች ምክንያት አውቆ የተኛ የሚመስለው አለምም ሲያንቀላፋ አንኳን አንድ አይኑን ከፍቶ ያለመዘናጋት የሚከታተለው ትግል ነው።
እና እንደ ሁልጊዚያችን እንበርታ።

ሃገር ሽጠው በሚያገኙት የደም ገንዘብ አሮጌ ተራ ወርደው በሚሸምቱት ድሮንና ተተኳሽ አይደለም ከዋክብት ቦንብ ሆነው የአማራ ህዝብ ላይ ቢዘንቡ እንኳን ጠላቶቻችን ይህን ትግል ማሸነፍ አይችሉም።እምቢ ያለን ህዝብ፥ ለህልናው ላለመጥፋት የሚታገልን ህዝብ ማሸነፍ ፈፅሞ አይቻልም። ከምድረገፅ ላለምጥፋት መሳሪያ ያነሳን ህዝብ ከማሸነፍ የፀሀይን ከምስራቅ ወደ ምእራብ ተፈጥሯዊ የጉዞ ኡደት ከሰሜን ወደ ደቡብ ማዞር ይቀላል። ከፈጣሪ በታች ትልቁ ጉልበት ያለው የአመፀ ህዝብ መዳፍ ላይ ነው። እንበረታ እንፅና ብቻ!! ፅናት ነገ ከነ- ጠዋት ውብ ጀንበሯ የራስ እንደምትሆን በጥልቅ ከነፍስ በማመን የዛሬን ሰው፣ተፈጥሮና ሁኔታዎች ወለድ ወጣ ውረዶችን የማመቅና የገለባ ያክለ እንኳን ለስን ልቦናችን ሳይከብዱን ወደ ግብ የመገስገስ ስነ አእምሯዊ ሁነት ነው።-እንፅና!!

• ለመላው የአማራ ህዝብ!!
_______
አይዞህ በርታ!! ጠላት ከመድረገፅ ሊፍቅህ በሰማይም በምድርም ጭፍጨፋ እየፈፀመብህ ቢሆንም
ከታሪክህ ፣ከማንነትህና ከውብ እሴቶችህ አኳያ ይህን ዘመን በድልና በኩራት እንደምታልፈው የደቂቃ ጆሮ ካዋስከው ተራራውና ሸለቆው በደምህ ደረቱ ላይ ከመዘገበው ወፍራም ታሪክህ ብዙ አብነቶችን መዞ ይነግርሃል።
በመካከለኛው ዘመን ማንነትህን፥ ታሪክህን፥ ግዛትህንና መንግስታዊ አስተዳደርህን አሳለፎ ላለምመሰጠት 15 አመታትን በዱር በገደሉ ኖረሃል፥ ጠላቶችህን ተፋልመሃል፥ በመጨረሻም አሸንፈሃል።
በቅረቡ የታሪክህ አንጓ ላይ የጣሊያን ወረራን ዘመን መለስ ብለህ ብታይ አምስት አመት ዱሩን ቀየህ ዋሻዎችን ቤትህ አድርገህ ከመሬት የሚትኮስን የጠላተትና የባንዳ ጥይት መክተህ፥ ከሰማይ የሚዘንብ የመርዝ ጋዝን በጫካ እና በዋሻ ጥላ ተከላክለህ ታግለሃል፥ በመጨረሻም አሸንፈሃል!!
እና ወገኔ ሆይ ፅና!!ነገ ያንተ ነውና ፅና!!

•ለመላው የአማራ ፋኖ አመራርና አባላት
______
ታሪክ እየሰራን መጥተናል። በቅርቡ በዘመቻ መቶ ተራሮች ተአምር አሳይተናል፥ የጠላትን አንገት ዳግም ቀና በሎ እንዳያይ አድርገን ወደ ግራ ሰብረናል። ከምናውቅበትና ከመጣንበት መደበኛው ፋኖአዊ ውጊያችን ባለፈብ ጠላት ኪሊማንጃሮን ነቅሎ አምጥቶ ምሸግ ቢገነባ እንኳን ማስቆም የማይችለው አንድ ሌላ ድንቅ ዘመቻ በቅርቡ ይኖረናል። እንበርታ! እንፅና!!፥ፅናት የትግላችን ደም ሰር የድላችን ምሰሶ ነው።

•ለአማራ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች
________
ከሰሞኑ የጀመራችሁት የተናበበ እና የተቀናጀ የስርአቱን ግፎች የማጋለጥ ዘመቻ እዚህ መሬት ላይ ያለን ወንድምና እህቶቻችን በእጅጉ አስደስቷል። አኩርቷል።
ከኛ ላልሆኑ፣ ህሌናን ያክል ውብ ፀጋ በአምሳ ሳንቲም ለገዳያቸው የሸጡ፣ ለወደፊቱ ሌላ ነፃ አውጭ በስማቸው የምናቆምላቸውና ነፃ የምናወጣቸው አሳዛኝ ፍጡራን አንድ ደቂቃም ሳታባክኑ ትኩረታችሁ መሰል ትግል ላይ ብቻ ይሁን። ድንቅ ጅምር ነው በርቱ።

•ለአማራ ዲያስፖራዎች
_____
ከሰሞኑ ጥሩ መነቃቃት እያየን ነው። ጥሩ ነው። በእጅጉ ግን ይቀራል። እናቶቻችሁ ከነ ከብቶቻቸው በድሮን በሚጨፈጨፉበት ዘመን ለሰበብ የሚሆን የሚያደናቅፍ የእናት መቀነት የለምና ጥሪያችንን ሰምታችሁ ውጡ!!በሁሉም ዘርፍ ውጡና ታገሉ። ያበቀለው መሬት በእሳት እየተጠበሰ የሌላ ሃገር መሬት ላይ ችሎ እንቅልፍ የሚተኛ ጤነኛ አማራ ካለ የኛ አይደለም።ከነ ጃሪና ኮሎ ጋር አብራ ለምትገደል እናት ሰልፍ መውጣት ያን ያክል ከባድ ነው? አይምስለኝም።እና በርቱ ወገኖቻችን!

•ለጠላት አድራችሁ በጠላት ካምፕ ላላችሁ !
__________
በተለያዬ ጊዜ ያደረግነውን ጥሪ ተቀብለው የተቀላቀሉን መሰሎቻችሁ ከህሌናም፥ ከታሪክም ተጠያቂነት ራሳቸውን አድነው ከሰቀቀን ወጠው ሂወታቸውን እንደ አዲስ መኖር ጀምረዋል።
እነ አብይ ዛሬ ይንቋችኋል፣ ይጠሏችኋል ነገ አውጥተው ጎዳና ላይ ይጥሏችኋል። ጎዳና ላይ የውሻ ሞት ትሞቱና ያሳደጋችሁ ምድር ተከፍቶ ይውጣችኋል። ስለዚህ ያ ከመሆኑ በፊት ኑ!! ኑ ብለናል ኑ!።
እንበርታ!እንፅና ወገን።ይህ ትውልድ የመከራ ሳይሆን የድል ትውልድ ነው። ዘመኑም የአማራ ትንሳኤ የሚበሰርበት ነው።

አንድ አማራ! (አንድ ህዝብ፥ አንድ እጣ- ፋንታ፥አንድ ድል!!)

ድል ለ አማራ ህዝብ
[ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!!]
አዲስ ትውልድ፥አዲስ አስተሳሰብ ፥አዲስ ተስፋ!!

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:20


ከአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ የተላለፈ መልእክት።

1ኛ በዕዙ ወስጥ ያለ የማንኛውም የፋኖ የአመራር ሆነ የፋኖ አባል ፎቶመለጠፍ በእዙ የተከለከለ ነው።

2ኛ) የዕዙን ከዚህ በፊት የወጣ ፎቶ በመጠቀም መረጃ መስጠት ይቻላል።

አዲስ ፎቶ መለጠፍ አቁሙ ከኛ ዉስጥ የሆነና በኛ አካባቢ የሚገኝ ሰው ሆኖ ፎቶ አንስቶ መረጃ የሰጠ ወይም ያወጣ ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን ተብሏል።

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:18


ሰበር ዜና
በአማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ በደፈጣ 5 አድማ ብተና ሲሸኙ ከ10 በላይ ቁስለኛ አድረገውታል።
ድሉ ይቀጥላል።

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:17


ሌላ ቀጠሮ እንዳትይዙ‼️

ከነገ ማታ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን የሚቆይ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ X ላይ ዘመቻ ይኖረናል። ሁሉም ይዘጋጅ። የX አካውንት የሌላችሁ ክፈቱ‼️

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:16


💚💛 መረጃ መተማ‼️
==========
👉የመተማ ከተማ ከንቲባ አዝመራው አማራ ሹፌሩን ጨምሮ ከ8አጃቢዎቹ ጋር ፋኖን ተቀላቀለ።
🔥ድል ለለአማራ ፋኖ

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:16


💚💛 ከድሮን ጭፍጨፋ ለመዳን የሚያስችሉ ዘዴዎች ‼️

1ኛ. በአንድ ወይም በቡድን ሁኖ አለመጓዝ!
2ኛ. ከ5 ሰው በላይ ሁኖ አለመጓዝ!
3ኛ. ራሱን በቅጠል/በጫካ መሸፈን!
4ኛ. ከ25ሜትር በታች ባለ የጎንዮሽ ርቀት አለመጓዝ!
5ኛ. ሲቀመጡ በዛፍ ጥላ ስር መሆን አለብን (ድሮን በጥላ ስር ያለን ብዙ ጊዜ ማንበብ አይችልም)!
6ኛ. የሚያፀባረቁ ምንጣፍ/አንሶላ አለመጠቀም!
7ኛ. ሲቀሳቀሱ በጨለማ/ጧት/በደመና ይጓዙ(በጨለማም ቢሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል)!
8ኛ. ካሉበት ቦታ ጋ የሚመሳሰሉ ልብስ ይልበሱ!
9ኛ. በአንድ መንገድ ሁሌም አለመጓዝ!
10ኛ. ከመሄዳችን/ከመጓዛችን በፊት ጫካ የሆኑ ቦታወችን መምረጥ!
11ኛ. በአንዴ ብዛት ያለው የፋኖዎቻችን ስቅ መጫንና መጓጓዝ የለበትም!
12ኛ. ከድሮውን እይታ ውጭ መሆን ፤ ቦታ ካምፕ መቀየር ፣ ስልጠናና ስብሰባዎችን አለማድረግ ወይም በከፍተኛ ጥንቃቄ ነገሮችን መፈፀም!
13ኛ. በገቢያ, ሰበት ቀን,እቁብ,በመኪና, በጋራ ,በሀዘንና በሌሎች የማህበር አኗኗር አብሮ አለመገኘት(መበትን ያስፈልጋል)!
14ኛ. ሲራመዱና ሲቀሳቀሱ በዝግታ ይሁን ምክንያቱም ሲፈጥኑ በቀላሉ ድሮውን ሰለሚያየን!
15ኛ. ወደ አዲስ ቦታ ሲሄዱ በጥንቃቄ ይሂዱ!
16ኛ. በእንቅስቃሴ ወቅት በደንብ መረጃ መለዋወጥ!
17ኛ. አካባቢውን መቃኘት!
18ኛ. የድሮን እቆስቃሴ መኖሩን ወደ ሰማይ በማየት በደንብ ማረጋገጥና መዘጋጀት ቦታ ለመያዝ!
19ኛ. አንዴ በድሮን ከመታን በኋላ እኛ ቁስለኛ ወይም አስክሬን ለማሳት አለመሄዴ ምክንያቱም ከዛው ላይ እኛን ድጋሜ ሊመታን ስለሚችል!
20ኛ. በከፍተኛ ጥንቃቄ ምቹ ሁኔታ ከተገኘ ድሮኗን መቶ መጣል !.....
ድል ለአማራ ፋኖ 💪
አማራ ያሸንፋል ??
#ሼር በማድረግ ለሁሉም ቀጠና ፋኖዎች አድርሱ።
ከድሮን ጥቃት እራሳችንን እንጠብቅ

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:14


💚💛 ዘመቻ መቶ ተራሮች ‼️

11ኛ ቀን!!

ዛሬ 03/2/2017 ዓ ም የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ኛ ክ/ጦር ልዩ ስሙ ሶሰር ከሚባል ቦታ በጠላት ላይ የቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ልጆች በወሰዱት ርምጃ ሙትና ቁስለኛ ሁኖ ቀሪው ወደ ዳንግላ ፈርጥጦ ተመልሷል።

ዳንግላ ካለው የጠላት ሃይል ሶስት የአድማ ብተና አባላት አንድ ሻለቃ መሪ ከነሙሉ ትጥቃቸው አንድ መገናኛ በመያዝ የቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬን ብርጌድ ተቀላቅለዋል።

ድል ለአማራ ፋኖ !

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:14


💚💛 ሰበር ዜና‼️

የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ደብረብርሃን ከተማ እምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ተከማችቶ በነበረ የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ኃይል ላይ በሞርተር የታገዘ መብረቃዊ ጥቃት ሰነዘረ።
  ጥቅምት 3/2017 ዓ/ም
   ሸዋ አማራ ኢትዮጵያ
ከሰሞኑ የአማራን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጠፋለሁ በሚል ፉከራ ያለ የሌለ ሀይሉን አግተልትሎ  ወደ አማራ ክልል የገባው የብልፅግናው ዙፋን አስጠባቂ ቅጥረኛ አራዊት ሰራዊት ባሰበው ልክ ሳይሆን በግልባጩ እየተቀጠቀጠ ይገኛል።
በትናንትናው አመሻ እለትም የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ኃይል  ደብረብርሃን ከተማን ለመጠበቅ በሚል ከደብረብርሃን ከ5ኪሎሜትር በላይ በማትርቀው ወሻውሽኝ ቀበሌ መሽጎ ህዝብን ለማሰቃየት በተቀመጠ ባንዳ አድማ ብተናና ቅጥረኛ ሚሊሻ  በአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ በካምፑ ላይ በተወሰደ በሞርተር የታገዘ መብረቃዊ ጥቃት ብትንትኑ ወጥቶ ወደ መሀል ደብረብርሃን ፈርጥጧል።
በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽ ሻለቃ ዓለሙ ሀብቱ እና የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ ምኒልክ ሻለቃ መሪ ፊትአውሪሪ ደሳለኝ ሽፈራ በተመራ በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን በርካታ የጠላት ሀይል ሰብዐዊ እና ቁሳዊ ሀብቱን አጥቶ ወደመጣበት የፈረጠጠ ሲሆን የወገን ሀይልም ግዳጁን በሰላም አጠናቆ ወደ መጣበት በሰላም ተመልሷል።
       "ድላችን በክንዳችን"
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኘነት ክፍል

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:14


💚💛 ሰበር ዜና‼️

በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ አሳምነው ክፍለጦር የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ ወደሆነችው ወልደያ ከተማ አስደናቂ ተጋድሎ በማድረግ ወልደያ ከተማ መግባቱን የአማራ ፋኖ በወሎ አሳምነው ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ንጉስ አበራ ገልጿል።

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:12


💚💛 አጋልጥ መረጃ‼️

በደቡብ ሜጫ ገርጨጭ (መሀል ገነት) ከተማ የብልጽግና ሰራዊት የከተማ ነሪዎችንና አርሶ አደሮችን ምርኮኛ በሚል ሰብስቦ ዶክመንታሪ በመስራት ላይ ነው ሲሉ የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል።

ወታደራዊ ኮማንዱ አርሶ አደሮችን ከየቤታቸው በመሰብሰብ "ጽንፈኛው ፋኖ አስገድዶ አሰልፎን ነው፣ ፋኖ ዘራፊ ነው" በሉ በሚል በአንድ በኩል አፈሙዝ፣ በአንድ በኩል ካሜራ ተደቅኖ ለዶክመንታሪ ቀረጻ በመስራት ላይ ናቸው ብለዋል።

ዛሬ ረፋዱን በዚሁ ወረዳ የአብሮ መኖር ገንቦ ማርያም የቅዱስ ዮሐንስ ትምህርት ቤትን በድሮን የመታ ሲሆን፣ ከትናንት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2:00 ድረስ ሙሉ ጦርነት ሲካሄድ ውሏል።

ከአማራ ፋኖ በጎጃም ጋር በተደረገው ከባድ ውጊያ የተመታው ኃይል መሐል ከተማ ላይ የግለሰቦች መኖሪያ ቤት በምሽግነት ሲጠቀም ታይቷል ተብሏል። ዛሬ አርሶ አደሮችንና የከተማዋ ነዋሪዎችን ከየቤታቸው አስገድዶ ሰባስቦ በምርኮ ስም ዶክመንታሪ ሲሰራ ማርፈዱን ተመልክተናል ብለዋል።

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:11


💚💛ባንዳ መጨረሻችሁን ከደጋዳሞት ተማሩ‼️

ደጋ ዳሞት የሆነው እንዲህ ነው

ሰራዊቱ ከደጋዳሞት ለቆ ሲወጣ አብሮት የነበረውን ሚሊሺያ ፖሊስና አድማ ብተና እንዳትከተለኝ ብሎ ጥሏቸው ነው የሄደው። ለመከተል የሞከሩት የብአዴን ሰራዊተቶች ተገድለዎል። ለምሳሌ የወረዳው ፖሊስ ሀለፊ በራሱ መኪና ሲከተላቸው ገለውታል። ፋኖ ደጋ ዳሞትን ሲይዝ ተራግፈው የቀሩትን የወረዳው አመራሮች አስተዳዳሪውን ጨምሮ አንቆ እስር ቤት ከቶታል። ሌሎች ፖሊስና አድማ ብተና እየተፈለጉ ነው። ብዙዎቹን ከተደበቁበትን አውጥተዋቸዋል።

ሌላው ሰራዊቱ ሲወጣ አስሯቸው የነብሩ ሰዎችን በውጭ ቁልፎባቸው ነበር የሄደው። ፋኖ ከተማውን ሲይዝ ቁልፉን ሰብሮ እስረኞችን እንዲወጡ አድርጓል።

የፖሊስ፣ አድማ ብተናና የሚሊሺያ አባላት ከዚህ ምን ትማራላችሁ

#ንቁ...‼️

#ማሳሰቢያ_ለወገን_ሀይል‼️

ህዝብን ከጠላት ነፃ በማድረግ እያስተዳደራችሁ ያላችሁ የፋኖ ሀይሎች ‼️

1ኛ. እንቅስቃሴያችሁ በህዝባችን ፍላጎት መሰረት ይሁን ማለትም እያንዳንዷ ህግ የማስከበር እርምጃ በግል ጥላቻና ቂም ላይ የተመሰረተ እንዳይሆን እያንዳንዱ ከፍተኛ ውሳኔ በህዝብ ድምፅ ይሁን!!

2ኛ. ከጠላተ ነፃ የሆኑ ቀጠናዎች በማንኛውም ሰዓትና ቦታ የአየር ድብደባ ሲለሚኖር የህዝብ መሰባሰብ እንዳይኖር በማድረግ ህዝቡን ከጉዳት ጠብቁ!!

3ኛ. ነፃ ቦታዎችን በመጠቀም ለአየር ሀይል በማያጋልጥ መልኩ ስልጠናዎችና አደረጃጄቶች ይቀጥሉ ዘንድ በርትታችሁ ስሩ!!!

በመጨረሻም የወጣነው ለአማራ ህዝብ ነውና የህዝባችንን ባህል፣ዕምነት እና የአኗኗር አሴት ወዘተ እንጠብቅ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን‼️

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:10


ሰበር ዜና
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ሁለት ክፍለ ጦሮች በጋራ በሻለቃ ዓለሙ ሀብቱ የነጎድጓድ ክፍ ለጦር ምክትል አዛዥ በተመራ ልዩ ኦፕሬሽን በሁለት የተለያዩ ቦታዎች በተመሳሳይ ሰዓት ድል ተቀዳጁ።
ጥቅምት 1/2017ዓ/ም
ሸዋ አማራ ኢትዮጵያ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ ነብሮ ሻለቃ እና የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ፊትአውራሪ አስማረ ዳኜ ብርጌድ በሻለቃ ዓለሙ ሀብቱ የቀድሞው ጋተው ብርጌድ ዋና አዛዥና በአሁኑ ነጎድጓድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን መሪነት በተሰራ በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን ከደብረብርሃን ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ በምትገኘው አንጎለላና ጠራ ወረዳ "ጠገጎ ቀበሌ"ተከማችቶ የነበረውን የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ባንዳ ሚሊሻ በመበታተን ከተለያዩ ቦታዎች የፋኖ ቤተሰብና ደጋፊ ናቸው በሚል የተዘረፋ በርካታ የቀንድ ከብቶች ፣ በጎችና የጋማ ከብቶችን በማስመለስ ለባለቤቶቹ ለማስረከብ የመለየትና የማጣራት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።

ላለፈው አንድ አመት ደብረብርሃን ከተማ ተከማችቶ የህዝባችንን ሰላም ሲያናውጥ የከረመው ይህ አጥፊ እና ወራሪ የኦሮሙማ ቡድን የቀድሞው አማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ጋተው ብርጌድ ዋና አዛዥ የአሁኑ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽንን በተደጋጋሚ የሚወስደውን እርምጃ መቋቋም ስላቃተውና መውጫ መግቢ በመቸገሩ የተነሳ ከሰሞኑ የተለያዩ አካላትን የይተወን ሽምግልና ማቅረቡን ለማወቅ ተችሏል።

ይህ የተጠናና ድንቅ ኦፕሬሽ ከሀሳብ ጀምሮ እስከ ተግባራዊነቱ ድረስ በንቃት በመሳተፍና በመተግበር የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ፊትአውራሪ አስማረ ዳኜ ብርጌ ሻለቃ አንድ መሪ ፋኖ ሀይሉ ተፈራ እንዲሁም የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌ ነብሮ ሻለቃ መሪ ፋኖ መንገሻ አዲሴና የጋተው ብርጌድ ዘመቻ መሪ የሆነው ፋኖ ነገሰ አስበ በጋራ የፈፀሙት ጀብዱ በታሪክ የሚመዘገብ ሆኖ አልፏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተመሳሳይ ሰዓት በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተው ብርጌድ በተሰራ ልዩ ኦፕሬሽን በደብረብርሃን ከተማ ጫጫ ክፍለ ከተማ ለአርሶ አደሩ መከፋፈል የነበረበትን የአፈር ማዳበሪያ ለአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ባንዳ ሚሊሻዎች በዝቅተኛ ዋጋ በማስረከብ እንዲቸረችሩ በመሰጠቱ ሰው በማይኖርበት አሳቻ ሰዓት በከባድ መኪና ተሳቢዎች ሲያንቀሳቅሱ በጀግናው ሻለቃ ዓለሙ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን እና በጋተው ብርጌድ ነብሮ ሻለቃ እይታ ውስጥ በመግባቱ ከነ ከባድ ተሽከርካሪዎቹ በቁጥጥር ስር በማስገባት ለማህበረሰቡ በዝቅተኛ ዋጋ ማከፋፈል ተችሏል።

"ድላችን በክንዳችን"
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኘነት ክፍል

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:09


💚💛ከፍተኛ የመከላከያ አዛዥ ተማረከ‼️

የጎጃም ኮማንድ ፖስት ሎጅስቲክስ ክፍል ኃላፊ የአበባው ታደሰ ቁልፍ ሰው የ6ኛ ዕዝ 75ኛ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ያሬድ በግዮን ብርጌድ አናብስቶች ተማርኳል።

(ወገን በድል ላይ ድል እየተደራረበ ለማብሰርም ተቸገርንኮ)

ድል ለአማራ ሕዝብ!!!
©️ሞገሴ ሽፈራው

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:09


የአማራ ፋኖ በጎጃም ፫ኛ ክፍለጦር ግዮን ብርጌድ በትላንትናው እለት ከጠላት የማረከው የጠላት ሬዲዮ ቋት በቪዲዮ

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:08


🔥#እንደምን_ዋላችሁ_ጓዶች

ዛሬ መስከረም 29-2017 አም በዘመቻ መቶ ተራሮች ሰባተኛ ቀን ላይ እንገኛለን!! አስቀድመን ቃል በገባነው መሰረት ለታሪክ ገፆች እንኳን የሚከብዱና  የሚገርሙ ድሎችን አስመዝግበናል፣እያስመዘገብንም ነው።

ዘመቻ መቶ ተራሮች ይቀጥላል። በትግላችን የሚመጣው ዋናውና ሙሉው ድልም ከፊታችን ይጠብቀናል።

-“ይህን ዘመቻ በትግሉ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነገር እናሳያለን ብለን ጀመርነው  “እግዚአብሄር ይመስገን! በተመኘነው ባቀድነውና ባሰብነው ፍጥነትና ግዝፈት እየተከወነ ነው።
-እንግዲህ የዛሬው ልዩ ክስተት
በጥብቅ ዲሲፕሊን የጠበቅነው የህዝብ ተቋም ባንክ! ዛሬ ውጊያ መሀል ቆሞ ሲተኩስ ተገኝቶ ከበርካታ
የአብይ ወራሪ ሰራዊት አባላት ጋር ምርኮኛ ሆኗል። እናመሰግናለን።

ወንድምና እህቶቼ!
ይህ ድል በፍፁም ወንድማማችነት፣ትብብር እና ፍቅር እየተገኘ ያለ ድል ነው።በጥቅሻ መግባባት የወንድሞች ቅንጂት የወለደው ነው።

-ጓዶች!  በዘመቻ መቶ ተራረ‍ሮች በጣም ብዙ የወራሪው ሰራዊት አባላትን ማርከናል። ይሁን እንጂ የአብይን ወራሪ መማረክ የመጨረሻው ግባችን ነውን?አይደለም። ግባችን የአማራን ህልውና ማረጋገጥ ነው። እደግመዋለሁ
የምንታገለው አማራ የሚባል ህዝብን ከምድረ ገፅ የማጥፋት ግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ አደገኛ ትርክት የወለደው የብልፅግና ስርአትን ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ የአማራን ህልውና ለማረጋገጥ ነው። የአማራ ህልውና በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ደግሞ የአማራ ህዝብ በትክክለኛ ልጆቹ ተወክሎ ስልጣን ይይዛል። ያለ ስልጣን የሚረጋገጥ ህልውና የለምና።ፋኖ ተራ ጠመንጃ ነካሽ ሳይሆን ጥርት ያለ የፓለቲካ ንቅናቄም ነው። ስልጣንን ለማለምም  በአለሙ ፋሽን የግድ በፓርቲ ስም መጠራትም መመዝገብም የለበትም። ከመሰረቱ ፖለቲካ ማለት ህዝብን ለጋራ ዓላማ አንድ ላይ ማንቀሳቀስ እና ማሰለፍ መቻል ነው። ፋኖ ይህንን ተግብሮ ለዓላም አሳይቷል።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ አውድ ውስጥ በህልውና ትግል እና ለስልጣን በሚደረግ ትግል መካከልም ቀጭን ክር የሚያክል መስመር እንኳን አይገኝም። በስልጣን እና በህልውና ትግል መካከል ላይገናኙ የተወገዘ ድንበር የለም። ይህ ፎርሙላ ደግሞ በተለይ ለአማራ ህዝብ የህልውና ጥያቄ በሚገባ ይሰራል።

ፋኖ ስልጣን ይይዛል! መያዝም ይኖርበታል።ስለዚህ ለዚህ ግብ በሚመጥን ልክ እንንቀሳቀስ!!! ጠላትን እየደመሰስን ወደ ዋናው ግባችን ወደ አራት ኪሎ እንገስግስ።

-የአማራ ልሂቃን ወዴት ናችሁ? ምን እየሰራችሁ ነው? እያሸነፍን ነው። የእናንተ ድርሻ እና ሚና ምን ላይ ነው?
የአማራ ምሁራን ደህና ናችሁ? ምን እያደረጋችሁ ነው?
የሀይማኖት አባቶች? በሀገር አላችሁ?ሰላም ለናንተ ይሁን!
የአማራ ዳያስፖራ ላቀረብንላችሁ የትግል ጥሪ ምላሽ ለመስጠት እንቅስቃሴ እንደጀመራችሁ ሰምተናል፥ ግዜ የለንም ፍጥነት እና ቅንነት ያስፈልጋል:: የክብርን እና የአደረጃጀቱን ጉዳይ ለግዜው ተውት እና የክተት አዋጅ አውጁ። ልክ መሬት ላይ እንደሚዋደቁ እንቁ ወንድሞቻችሁ እና ልጆቻችሁ ደማቅ ታሪክ ለመፃፍ ተጣደፉ።

-በጠላት ካምፕ ላላችሁ-አሁንም እንላለን-እጂ ስጡ። ምድራችን እጂ ከመስጠት ህይወት ከመንፈራገጥ ሞትን ያስገኛል። እና እጂ ስጡ።ራሳችሁን አውጡ።
-ህዝባችን አሁንም ነቅሎ  ይውጣ!!-ማርኮ ይታጠቅ። በየአካባቢው አደረጃጀት ስር ሆኖ ጠላት ጋር ይተናነቅ።

-ፋኖ-መሬት ነክሰህ ተዋጋ!-ድል ላንተ ነው። እየከበብህ ደምስሰው።

እንፅና ጓዶች!
ታሪክም፣ዘመንም፣ፈጣሪም ከኛ ጋር ነው።
ድሉ የኛ ነው!
አንድ አማራ!! ድል ለአማራ ህዝብ!
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
[ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም]

©አርበኛ ዘመነ ካሴ

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

21 Jan, 00:08


የተጠቃለለ!
ዘመቻ ፻ ተራሮች

፯ኛ ቀን

የአማራ ፋኖ በጎጃም ፫ኛ ክ/ጦር ዛሬ በማለዳ ከሠከላ እያስሮጠ ያስወጣውን የዘር አጥፊውን ጠላት ኃይል 6ኛ እዝ 75ኛ ክ/ጦር 4ኛ እና 5ኛ ሬጂመንት ቲሊሊ መዳረሻ ከበባ ውስጥ በማስገባት ድሽቃዎችን፣ ብሬንና ስናይፐሮችን፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ክላሾችንና ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም የመገናኛ ሬዲዮኖችን ማርኳል።

በተጨማሪም የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠር የጠላት ኃይል ተማርኳል።
እየተካሄደ ያለው ዘመቻ በየቀኑ አዳዲስ አስደናቂ ድሎችን እያስመዘገበ በፍጥነት አየገሰገሰ ሲሆን በጠላት ሰፈር ሽብርና ጭንቀት ተፈጥሮ እርስ በርስ እስከመመታታት አድርሷቸዋል።

በንፁኃን ደም የተጨማለቀው የብልጽግና ስብስብና ወምበር ጠባቂ ኃይሉ እጅ ከመስጠት የተሻለ አማራጭ የለውም።

ከጠላት የተማረኩ ቁሳቁሶች በቁጥር፦
➣ ሁለት ድሽቃ
➣ ሠባት ብሬን
➣ አራት ስናይፐር
➣ 800 የድሽቃ ጥይት
➣ 7400 የብሬን
➣ 15 ሺህ የክላሽ ጥይት
➣ አምስት መኪና
➣ 115 ምርኮኛ
በወገን በኩል ዘንገና ብርጌድ፣ ግዮን ብርጌድ፣ ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ፣ ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ
ብርጌድ እና ከ፭ ተኛ ክ/ጦር አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ቢተው ሻለቃ ተሳትፈውበታል ።

#ዘመቻ ፻ ተራሮች

አዲስ ትውልድ፤ አዲስ አስተሳሰብ፤ አዲስ ተስፋ!
[ ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም !]

Amhara Fano In Gojjam
በቴሌግራም ያግኙን 👇
https://t.me/amharafanoingojjam2016