Gemenaye ገመናዬ

@gemenaye1


At Gemenaye we are here to help you!
contact us.
To get mentor make sure you have telegram username !
Click on Connect to Mentor button and then Start the bot.

Gemenaye ገመናዬ

18 Dec, 16:01


ስመኘው የነበረው እያንዳንዱ ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ግልጽ በሆኑ ባህሪዎች መተካት ጀመረ። ሁሉም ነገር እየተቀየረ የመጣው ቀስ በቀስ ስለነበር ግንኙነታችን ወደ ወሲባዊ ግንኙነት እየተቀየረ መሆኑን ማስተዋል አልቻልኩም ነበር። ሲያደርጋቸው የነበሩት ነገሮች በሙሉ እኔን ኢላማ አድርጎ ቢሆንም እኔም የድርጊቱ ተባባሪ እንደሆንኩ እንዳምን አድርጎኝ ነበር።
የወሲባዊ ጥቃት ሙከራ ደርሶቦት የሚያውቅ ከሆነ ቁስሎቹ ጥልቅ ናቸው። ጠባሳዎቹ ከባድ ናቸው። ስሜቶቹ ውስብስብ ናቸው። ነገር ግን ብቻዎትን አይደሉም። ልናማክሮት ዝግጁ ነን።
ሙሉውን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/sexual-exploitation
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

15 Dec, 16:43


በሚያሳየኝ ፍቅር እና እንክብካቤ የተለየው ሴት እንደሆንኩ ተሰማኝ። ለእሱ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆንኩ ይነግረኝ ነበር። ምን ያህል ተሰጥኦ እንዳለው እና ለትልቅ ነገር እንደተፈጠረ ግን በጣም ደካማ እንደሆነ እና የሚያግዘው ሰው እንደሚፈልግ ይነግረኛል። ቤተሰቦቹ እንዳልተረዱት ፍቅረኛው ራሱ እንዳልተረዳችው እና በትክክል የተረዳሁት እኔ ብቻ እንደሆንኩ ሲነግረኝ በጣም አዘንኩለት። የምወራውን ነገር በሚስጥር መያዝ እንዳለብኝ ይነግረኝ ነበር። ምክንያቱም ጓደኞቻችን ጥሩ ነገር ላያስቡ ወይም ግንኙነት እንዳለን ሊጠረጥሩ ይችላሉ። ስለዚህ ለወላጆቻችንም ሆነ ለጓደኞቻችን በተለይ ለፍቅረኛው መናገር እንደሌለብን ተስማማን። እንዚህን ነገሮች የተጠቀመው እኔን ለማታለል እንደሆነ የገባኝ አሁን ነው።

የወሲባዊ ጥቃት ሙከራ ደርሶቦት የሚያውቅ ከሆነ ቁስሎቹ ጥልቅ ናቸው። ጠባሳዎቹ ከባድ ናቸው። ስሜቶቹ ውስብስብ ናቸው። ነገር ግን ብቻዎትን አይደሉም። ልናማክሮት ዝግጁ ነን።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ
https://gemenaye.com/sexual-exploitation
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

22 Nov, 16:01


ምናልባት ችግር እንዳለብህ ላታውቅ ትችላለህ። ሁሉም ጓደኞችህ ልክ እንዳንተ ስልኮቻቸው ላይ ተጠምደዋል። የምታውቃቸው ሰዎች ሁሉ በየደቂቃው የinstagram እና የfacebook ገፃቸውን ያያሉ። በየቀኑ በየሰአቱ youtube እና Tiktok በማየት ያሳልፋሉ። አንተም እንደ እነሱ ነህ?
ስኬታማ የሆነ ጤናማ የኢንተርኔት አጠቃቀምን ለመጀመር ተጠያቂነት ዋናው ነገር ነው። የትኛውም አይነት ሱስ ቢኖርቦት ብቻዎን አይደሉም። ድጋፍ የሚያስፈልግዎት ከሆነ፤ እባክዎን ያነጋግሩን።
ሙሉውን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/magazine/addicted-to-screen-time-try-the-digital-diet
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

20 Oct, 16:01


ራስን ለማጥፋት ማሰብ ማለት ስለ ህይወት እና ስለ ወደፊት ውሸትን ማመን ማለት ነው። ከድሮ ጀምሮ ብዙ ሰዎች በድብርት ተሰቃይተዋል ግን ለስሜታቸው አልወደቁም ወይም ስሜታቸውን አላመኑትም። በሱ ፈንታ ለመቀጠል ጽናት ነበራቸው፤ የወደፊት ህይወታቸው የተሻለ እንደሚሆን በማመን ውስጥ ያለ ጽናት። አንተም ይሄ ጽናት ሊኖርህ ይችላል።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/suicide-giving-life-another-chance
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

18 Oct, 16:00


ይሄን የምታነበው ምናልባት ራስህን ለማጥፋት አስበህ ሊሆን ይችላል። ወይም ሊያጠፋ ያሰበ ሰው ታውቅ ይሆናል። ምናልባት ለህይወት ተስፋ ያጣህ ሰው ብትሆን፤ እባክህን ማንበብህን ቀጥል። ህይወትህን ለማጥፋት አስበህ ጨርሰሃል ወይም ሞክረሃል። ልታስብ የምትችለው ሁሉ ህይወትህ ምን ያህል ተስፋ እንደሌለው፤ ይሄን ህይወትህን እንደዚህ መኖር መቀጠል እንደማትችል ይሆናል። ስቃዩ በጣም ከባድ ነው። ማንም የተሸከምከውን ሸክም ወይም ውስጥህ ያለውን የስሜት ብጥብጥ አይረዳህም። ግን አሁን እዚህ ነህ እና እዚህም ስለሆንክ እባክህን የሆነ ተስፋ ላካፍልህ
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/suicide-giving-life-another-chance
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

27 Sep, 16:07


በቤተሰቦቼ መካከል አልፎ አልፎ ይከሰት የነበረው አለመግባባት እየከረረ መጥቶ አሁን ላይ የቀን ተቀን ክስተት መሆን ጀመረ። ይባስ ብሎ አለመግባባታቸው ከከረረ ቃላት መወራወር አልፎ ሆኖ በማያውቅ መልኩ እጅ ወደመሰነዛዘር አደገ። እነርሱ መሆናቸውን እስክጠራጠርና ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ የማላውቃቸው ሰዎች ሆኑ። ትናንት የመልካም ትዳር ምሳሌ የሆኑት እና በብዙ ሰዎች ይወራላቸው የነበሩት ወላጆቼ ዛሬ ላይ ወደ ፍቺ ማቅናት ጀመሩ።
ሁሌም ግን ፤ ምንም እንኳን እነርሱ በራሳቸው ምክንያቶች ባለመግባባት ሁለቱም ለመፋታት ቢወስኑም፤ ትዳራቸው እንዳይፈርስ ከሞከርኩት የበለጠ ምን ማድረግ እችል ነበር? ከሚል ሃሳብ ጋር እታገላለሁ። በተመሳሳይ የህይወት መስመረ ውስጥ እያለፉ ከሆነ እና ታሪክዎን ሊያጋሩን ከፈለጉ ፤ እባክዎን ያነጋግሩን።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/adult-child-of-divorce
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

14 Sep, 15:59


አሁን ላይ ግርምሽ ካለፈ ሶስት አመት ሆኖታል ሃዘኑ ግን ልክ ትናንት እንዳጣሁት አይነት ነው ሚሰማኝ። ብዙ ጊዜም ራሴን በመሪር ሀዘን ውስጥ አገኘዋለው። ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ፤ ያለ ግርምሽ መኖር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ በአርባ አምስት አመቴ በሚገባ ተምሬያለሁ። ብዙ ነገሮች ይናፍቁኛል ብዙ ጊዜ ከስራ ስመለስ የግርምሽ ጠንካራ ክንዶች ውስጥ ተወሽቄ ጭንቀቶቼን ሁሉ ብረሳቸው ብዬ እመኛለው። የሚጠብቀኝ ግን የቀዘቀዘ ባዶ ቤት ብቻ ነው።
የሚወዱትን ማጣት ከባድ እንደሆነ አይቻለው። ግን ደግሞ፣ ተስፋ ቢስ መሆን እንደሌለብኝ እየተማርኩ ነው። በተመሳሳይ የህይወት መስመር እያለፉ ከሆነ ብቻችሁን አይደላችሁም።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/widowhood
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

08 Sep, 16:59


ምንም እንኳን በትዳር ለአስራ ሰባት አመት አብረን ብንኖርም ፍቅራችን ግን ልክ እንደ አዲስ ፍቅረኞች ነበር። አልተሰለቻቸንም ነበር። ከስራ ሰአት ውጪ ያለውን ጊዜ ሁሌም አብረን ነበር ምናሳልፈው። አንዲት ቀን ግን የህይወታችንን ምዕራፍ ላይመለስ ቀይራው አለፈች። ግርምሽ አልፎ አልፎ የሚሰማው ያልተለመደ አይነት የህመም ስሜት ቢኖርም፤ ትንሽ ሲቆይ ይተወኛል በሚል ምክንያት ወደ ህክምና ቦታ አልሄደም ነበር። አንድ ቀን ግን ህመሙ ትንሽ ጠንከር ሲልበት ምንም እንኳን እሱ ደህና ነኝ ቢልም፤ መሄድ አለብን ብዬ በግድ ሆስፒታል ሄድን። ሄደን የሰማነው የህክምና ውጤት ግን ጭራሽ ያልጠበቅነው ጀሮ ጭው የሚያደረግ ነበር።
የሚወዱትን ማጣት ከባድ እንደሆነ አይቻለው። ግን ደግሞ፣ ተስፋ ቢስ መሆን እንደሌለብኝ እየተማርኩ ነው። በተመሳሳይ የህይወት መስመር እያለፉ ከሆነ ብቻችሁን አይደላችሁም።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/widowhood
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

18 Aug, 11:00


ልጅ ሆኜ እናቴ ጥላን እንዳትሄድ ለማድረግ እኔ ብቁ ባለመሆኔ እራሴን እወቅሳለሁ፤በዛን ጊዜ አንድ ሰው አጠገቤ ሆኖ ምን እየተፈጠረ እንዳለ እንድረዳ ቢረዳኝ ኖሮ ጥሩ ነበር ብዬ ተመኘሁ፤ እናቴን ይቅር ማለት በጣም ከበደኝ፤ እንዴት ትታኝ ትሄዳለች? የሚለው ጥያቄ በውስጤ ተብላላ። ልቤ ቆስሎ ነበር እና ቤተሰቦቼን በድጋሚ ለማመን በጣም ከብዶኝ ነበር። ሳድግ ግን በልጅነቴ ምን እንደተፈጠረ ቀስ በቀስ ይገባኝ ጀመር ፤ በመሆኑም የራሴን የማገገሚያ መንገድ ጀመርኩኝ። የቤተሰቦቼን የትዳር ህይወት እኔ ማስተካከል እንደማልችል ገባኝ፤ አሁን እኔም እናት ነኝ፤ እናም ልጆቼን ትቶ የመሄድን ሃሳብ መቋቋም አልችልም።
በአብዛኛው የማገገሚያ መንገድ የሚጀምረው የምናልፍበትን መንገድ ሁሉ በሀዘኔታ እና በጥበብ ሊያዳምጠን ፍቃደኛ የሆነ ሰው ከማግኘት ነው፤ ይህ ነበር በእኔ ህይወት የሆነው እናም ለእናንተም ይህ ሊሰራ ይችላል፤ እዛ ቦታ ላይ ለብቻችሁ መቆም እንደሌለባችሁ እወቁ።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/child-of-divorced-parents
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

15 Aug, 16:33


በአንድ ፀሃያማ ጠዋት ገና ፀሃይዋ መስታወቱ ላይ ስታንፀባርቅ ከእንቅልፌ ተነስቼ በቤት ውስጥ እናቴን መፈለግ ጀመርኩኝ። በኮሪደሩ ላይ ነጠላ ጫማዋን ባገኘውም እርሷን ግን ማግኘት አልቻልኩም። ግራ የመጋባት ስሜት ሲሰማኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። አባቴ ሳሎን ከሚገኘው መደርደሪያ ፊትለፊት ቁጭ ብሎ ከቦርሳው ውስጥ ደብዳቤ መዝዞ በማውጣት ኮስተር ብሎ ሲያነብ ሰማሁት። ልቤ ቀጥ ስትል ተሰማኝ!! በጊዜው የተሰማኝን ስሜት ሊገልጽልኝ የሚችል የማስታውሰው ቃል የለም። እናቴ ትታን ሄዳለች!
በአብዛኛው የማገገሚያ መንገድ የሚጀምረው የምናልፍበትን መንገድ ሁሉ በሀዘኔታ እና በጥበብ ሊያዳምጠን ፍቃደኛ የሆነ ሰው ከማግኘት ነው፤ ይህ ነበር በእኔ ህይወት የሆነው እናም ለእናንተም ይህ ሊሰራ ይችላል፤ እዛ ቦታ ላይ ለብቻችሁ መቆም እንደሌለባችሁ እወቁ።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/child-of-divorced-parents
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

02 Aug, 11:01


አሁን ትልቅ ከሆንኩ በኋላ ሌላ የተማርኩት ነገር አለ። ያኔ እነዛ ጉልበተኛ ልጆች የሰደቡኝን ስድብ እና ድምጻቸውን ከአዕምሮዬ ለማስወጣት በጣም ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ተምሬያለው። ምክኒያቱም አንድን ነገር ተደጋግሞ ስትሰሚው በሃሳብሽ ውስጥ ይቀረጽና ይቀራል። ነገር ግን ጊዜ ቢወስድም ራስን ከዚህ ሃሳብ ነጻ ማድረግ ይቻላል።
ፍርሃት ህይወትን የሚያደክም ነገር ነው። እናንተም ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ አልፋችሁ ከሆነ ወይም ትምህርት ቤት ውስጥ የተናገሩዋችሁመጥፎ ንግግሮች አሁንም የሚሰማችሁ ከሆነ ብቻችሁን አይደላችሁም። እነርሱ የተናገሩዋችሁን አይደላችሁም። ስለእሱ ማውራት ከፈለጋችሁ እኛ አለን።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/bullying
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

31 Jul, 11:59


እነርሱ ስድስት ነበሩ እና እኔ ብቻዬን ስለነበርኩ የዝምታ ቋንቋን በፍጥነት ተማርኩ። “ራስሽን ዝቅ አድርጊ። አንድ ቃል አትናገሪ የማይታይ ለመሆን ሞክሪ ምናልባት እዚህ መሆንሽን ከረሱት ሁሉ ነገር ይቆማል” ነገር ግን አላቆመም። 6ኛ ክፍል ወይም 7ኛ ክፍል ወይም 8ኛ ክፍል ላይ አልቆመም።…
ፍርሃት ህይወትን የሚያደክም ነገር ነው። እናንተም ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ አልፋችሁ ከሆነ ወይም ትምህርት ቤት ውስጥ የተናገሩዋችሁ መጥፎ ንግግሮች አሁንም የሚሰማችሁ ከሆነ ብቻችሁን አይደላችሁም። እነርሱ የተናገሩዋችሁን አይደላችሁም። ስለእሱ ማውራት ከፈለጋችሁ እኛ አለን።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/bullying
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

06 Jul, 16:00


የሶስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ የትምህርት ቤት ጓደኛዬን እኛ ቤት አብረን እንድናድር ጠየኩት። ቤተሰቦቹን ሲያሰፈቅድ ግን ‹እናትህና አባትህ ሰካራሞች ሰለሆኑ እናንተ ቤት እንዳድር ወላጆቼ አልፈቀዱልኝም› አለኝ። በዛን ሰዓት ነበር ነገሮች የተገለጡልኝ። ለካስ ቤተሰቦቼ ጤነኛ ሰዎች አይደሉም። ወላጆቼ የአልኮል ሱሰኞች ናቸው።
እኔ አልኮል አልጠጣም ነገር ግን የአልኮል ተፅዕኖ ገፈት ቀማሽ ነኝ፡፡ ጤነኛ ያልሆነ ቤተሰብ ውስጥ በማደጌ ጤናማ ቤተሰብ ምን እንደሚመስል ማወቅ አቅቶኛል። ያልተፈታ ችግር ተሸመክው እየተንቀሳቀሱ ነው? ለብቻዎትን አይደሉም።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/alcoholic-parents
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታች ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

30 Jun, 16:05


ለአመታት እራሴ ላይ በር ዘግቼ ነበር። በጣም ስሜቴ ተነክቶ ነበር እና የገጠመኝን ነገር ለማንም ባለማካፈሌ እና ለመታደስ ባለመፍቀዴ ያንን ሁሉ ጭንቀት ለብቻዬ መሸከም ነበረብኝ። የሞተውን ግንኙነቴ እንዲሞት ስተወው እንደገና እራሴን በማግኘት አዲስ መንገድ ጀመርኩኝ። በጀመርኩት ችግሬን ለሌሎች የማካፈል መንገድ ይበልጥ ጤነኛ እየሆንኩኝ ነው። ያለፈኩበት መንገድ መሆን ከምችለው በላይ ጠንካራ አድርጎኛል። በተለያየ መልክ ህይወትን ኖሬለሁ፤ ጣፋጭም መራራም። ያሳለፍኩት ህይወት ዛሬ የሆንኩትን አድርጎኛል። አሁን ያለፈው የትግል ህይወቴ አላማ እንደነበረው አምኛለሁ።
ዛሬ ስሜቶት ተቀባይነትን እንዳጣ ከተሰማዎት ይህንን ስሜት ለብቻዎ መጋፈጥ የለቦትም። ከእኛ መካከል ሚስጥር ጠባቂ የሆነ አማካሪ በነፃ
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/emotional-abandonment
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታችኛው ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

29 Jun, 16:01


በጋብቻዬ ውስጥ ለብቻዬ ነበርኩኝ፡፡ ባለቤቴ የእኔን ስሜት አይረዳም ደግሞም አያከብርም። ከሰባት አመት የእጮኝነት እና ከአስራ ሶስት አመት የጋብቻ ጊዜ በኃላ እንደማይተዋወቅ ሰው ሆነናል። አንዳችን አንዳችንን መረዳት ወደማንችልበት እና ግንኙነታችን ወደሻከረበት ደረጃ ደረሰናል። በአንድ ቤት እንደሚኖሩ ነገር ግን እንደማይተዋወቁ እና እንደማይነጋገሩ ሰዎች ሆነናል። አልፎ አልፎ እናወራለን ነገር ግን ካወራን በጭቅጭቅ ነበር የምንቋጨው። ሁሌ እንጨቃጨቃለን። ከእኔ አጠገብ መሆን ስለማይፈልግ በተለያየ ክፍልም እንተኛ ነበር።
ዛሬ ስሜቶት ተቀባይነትን እንዳጣ ከተሰማዎት ይህንን ስሜት ለብቻዎ መጋፈጥ የለቦትም። ከእኛ መካከል ሚስጥር ጠባቂ የሆነ አማካሪ በነፃ ማግኘት ይችላሉ።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/emotional-abandonment
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታችኛው ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

14 Jun, 17:00


ድብርት አስፈሪው ገፅታ ጭንቅላትን ቀስ በቀስ መቆጣጠሩ ነው። የሚታዩብኝን ምልክቶች አላስተውልም ነበር፤ ያለምንም ምክንያት ይደክመኛል፣ ቶሎ እናደዳለሁ፣ መተኛት አልችልም፣ ሁሉን አቀፍ ግራ መጋባት ይሰማኛል እና በሀሳብ እሰጥማለሁ፤ አንድ የማውቀው ነገር በአዲሱ ስራዬ የእኔ ሀላፊነት ምን እንደሆነ ስላልተረዳሁኝ ወደ ቢሮዬ መሄድ በጣም እንደምጠላ ነው። በተደጋጋሚ በፍርሃት ስሜት እዋጣለሁ። ወደ ቤት ስመለስ ከስራዬ የምባረር እና የቤተሰቤን የገቢ ምንጭ የማጣ ስለሚመስለኝ እጨነቃለሁ።
በድብርት ውስጥ እንደሆናችሁ ከተሰማችሁ ብቻችሁን መንገዱን መራመድ የለባችሁም። ወደሚሰሙን ሰዎች ሄደን ስለህመማችን መናገር አለብን። የዛን ጊዜ ሰዎች ሲቀበሉን ትክክለኛውን ዋጋችንን እናውቃለን።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/depression
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታችኛው ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

09 Jun, 16:00


ከጨለማው ባሻገር የብርሃን ጭላንጭል ይታየን ጀምሯል፤ ይሁን እንጂ እስከ አሁን ጨለማውን አልተሻገርንም፤ አሁንም መክፈል ያለብን ሂሳብ እና ብድር አለብን እና አንዳንዴ በየወሩ የምንከፍለውን እዳ በጊዜው መክፈል አንችል ይሆን ብዬ እፈራለሁ። ያ አመት በጣም ከባዱ አመቴ ነበር፤ ግን ባህሪዬን በጥሩ ሁኔታ ቀርፆልኛል፤ ለማወጣው ወጪ በጣም እንድጠነቀቅ እና ሀላፊነት እንዲሰማኝ አድርጎኛል። ምን ያህል ጭንቀትን ጤነኛ ባልሆነ መልኩ እየተጋፈጥኩት እንደነበር አስተውያለሁ።
ስለ ገንዘብ ጭንቀት ተውጣችሁ ከሆነ እኛን ያናግሩን፤ የገንዘብ ጭንቀት በሁሉም ቦታ አብሯችሁ የሚሄድ ጥላችሁ ሊመስላችሁ ይችላል፤ ነገር ግን ለብቻዎት መጋፈጥ የለቦትም። ሚስጥርዎ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/financial-stress
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታችኛው ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

08 Jun, 11:01


የአለማችን ደሀው ሰው እኔ አይደለሁም፤ መቼም አልሆንም። ቤተሰቤ ሳይበላ የሚያልፈው ምግብ የለም፤ ጥሩ ቤት አለን እና አልፎ አልፎ ለመዝናናት የሚያስችለን ገንዘብም አለን። በሀገራችንን ሁኔታ መካከለኛ ገቢ ከሚያገኘው የህብረተሰብ ክፍል እንመደባለን። ነገር ግን ለብዙ ወራት የገንዘብ ሁኔታችን አሳስቦኝ ብዙ የጨለሙ ሌሊቶችን አሳልፌለሁ። የጭንቀቴ ትልቁ ክፍል ገና እየተቋቋመ ባለ ለትርፍ ባልተቋቋመ ድርጅት ውስጥ መስራቴ እና ደሞዜ ድርጅቱ በሚያገኘው ገቢ ላይ የተንጠለጠለ መሆኑ ነው። በተጨማሪም ባለቤቴ አራት ልጆቻችንን የምታሳድግ የቤት እመቤት ናት።
ስለ ገንዘብ ጭንቀት ተውጣችሁ ከሆነ እኛን ያናግሩን፤ የገንዘብ ጭንቀት በሁሉም ቦታ አብሯችሁ የሚሄድ ጥላችሁ ሊመስላችሁ ይችላል፤ ነገር ግን ለብቻዎት መጋፈጥ የለቦትም። ሚስጥርዎ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/financial-stress
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታችኛው ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

02 Jun, 11:37


አሁን የውስጥ ጥንካሬ ይሰማኛል፤ ያሳለፍኩት ስቃይ ምንም ነገር ሊበግረኝ እስካይችል ድረስ ጠንካራ አድርጎኛል። ተስፋ ከሌለው ግንኙነት ነፃ መውጣት እፈልጋለሁ፤ ለአመታት ከኖርኩበት የጭቆና ህይወት ነፃ መሆን አለብኝ። ገደለኝ እንጂ እልጠቀመኝም። ለራሴ ያለኝን ክብር እና በራስ መተማመኔን ገደለው እንጂ ምንም አልፈየደልኝም።
የትኛዋም ሴት አካላዊ ጥቃት ሊደርስባት አይገባም። ጥቃት ከደረሰባት ደግሞ ለብቻዋ አይደለችም። እርዳታ ለማግኝት እና አስፈላጊውን ውሳኔ ለመወሰን ዝግጁ መሆን አለባት።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/domestic-violence
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታችኛው ባለው link ያገኙናል።

Gemenaye ገመናዬ

01 Jun, 11:01


በቤት ውስጥ በሚደረግ ጥቃት ሊያደርስ የሚችለውን አካዊም ሆነ ስነልቦናዊ ጉዳት ካልደረሰብን በስተቀር መገመት የምንችለው አይደለም። በጣም ጥልቅ የሆነ እና አጥንትን ዘልቆ እስኪገባ ድረስ የሚያሳምም ነው። ጥቃቱ የሚደርስባችሁ በምታፈቅሩት ሰው ሲሆን ደግሞ ምድር ትገለበጥባችኋለች እና የሚያስደስታችሁ ነገር ሁሉ ወደ ባህር ልብ ይሰወራል። ህይወትም መኖርም ሁሉም በአንድ ጊዜ ትርጉም ያጣሉ።
የትኛዋም ሴት አካላዊ ጥቃት ሊደርስባት አይገባም። ጥቃት ከደረሰባት ደግሞ ለብቻዋ አይደለችም። እርዳታ ለማግኝት እና አስፈላጊውን ውሳኔ ለመወሰን ዝግጁ መሆን አለባት።
ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ከፈለጉ
https://gemenaye.com/domestic-violence
የግል አማካሪ ከፈለጉ ከታችኛው ባለው link ያገኙናል።