Ethio Psychiatry

@ethiopsychiatry


No Health Without Mental Health!

☎️ +251949114685
📩 [email protected]

Ethio Psychiatry

18 Oct, 06:10


Vacancy Announcements

Addis Ababa University College of Health Sciences, Tiqur Anbessa Specialized Hospital


1 BSc in #Psychiatry professional

3 BSc in #Midwifery

50 BSc in #Nursing

3 BSc in Medical #Laboratory Technology

1 BSc in Medical #Radiology Technology

3 BSc In #pharmacy

3 BSc in #Anesthesiology

1 BSc in #Biomedical Engineering

1 BSc in #Dental Medicine

1 BSc in #Physiotherapy

Minimum Experience: Vary ( #0_year – 7 years)

Deadline: October 25, 2024

Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry

Ethio Psychiatry

14 Oct, 14:52


በሕግ አግባብ እንዲታይ
======================

ከሰሞኑ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት አካዳሚክ ጉዳዮች
ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በሰርኩላር ደብዳቤ የአእምሮ ህክምና  የሙያ ስያሜ በተመለከተ የውሳኔ ደብዳቤ መላኩ ይታወቃል።

በደብዳቤው ለማተት እንደተሞከረው
ሁሉም ጤና የሚያስተምሩ ተቋሟት
BSC IN PSYCHIATRY NURSING
ወይም የባችለር ሳይንስ ዲግሪ በአእምሮ ህክምና ነርሲንግ እንዲጠቀሙ  ገልጿል።

ለዚህ ወሳኔ ዋቢ ያደረገው ደግሞ የሚመለከታቸውን አካላት ማወያየት እና ከ2012_2015 ዓም የተመረቁ ባለሙያዎችን ግራጁየት ፕሮፋይል ነው።

ነገር ግን  ጥያቄው የሙያ ስያሜ መነሻው ምንድን ነው? ዝም ብሎ በአቦ ሰጥ መሰየም ይቻላል ወይ?

በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይህንን ሙያ በዲግሪ ደረጃ ቀላል ለማይባሉ አመታት እያስተማሩ እነደነበረና አሁንም እያሰለጠኑ ይገኛሉ።

በስልጠናው የሚመረቁ ባለሙያዎችም
ተመርቀው ሲወጡ የሰለጠኑበትን አግባብ (Scope of practice) መሠረት ያደረገ የሙያ ስያሜ እንዲሰጣቸውና በተማሩበት ልክ ወደ ስራ መስክ ሲሰማሩ እንዲጠቀሙ የተለያዩ ሰነዶችን እንደሰነዱ ይታወቃል።

ለአብነት ያክል june,2019 ድራፍት ተደረጎ በ Aprile 2021 የጸደቀውን ካሪኩለም መመልከት ይቻላል። በዚህ ካሪካለም ነደፋ ላይ ጤና ጥበቃ፣ወደ ዘጠኝ የሚደርሱ ዩኒቨርስቶች እና Jhpiego ተሳትፈዋል።ሲጸድቅም ወደ 7 ዩኒቨርሲቶች ተሳትፈውበታል።ይህ ካሪኩለም ታዲያ የተመራቂዎች የሙያ ስያሜ ያደረገው "BSC IN PSYCHIATRY PROFESION"  ወይም ደግሞ የባችለር ሳይንስ ዲግሪ በአእምሮ ህክምና ሙያ " ነው።

ይህን የሙያ ስያሜ ሲጠቀም በዋናነት ታሳቢ ያደረገው የሙያው የቀድሞ ተመራቂዎችን ሚና፣የአእምሮ ህመም ጫና እና ሀገሪቷ ባለሙያዎች በምን መልክ ቢሰማሩ አዋጭነት እንዳለው ከግንዛቤ በማስገባት ነው።

በዚህም የተነሳ እስከአሁን በትንሹ ወደ 3000ገደማ የሚገመቱ ባለሙያዎች ተመርቀው አያሌ አገልገሎቶችን እየፈጸሙ ይገኛሉ።

እነዚህን ያህል ቀላል የማይባሉባለሙያዎች ዩኒቨርሲቲዎች ሲያበቁ ወይም ሲያስተምሩ ባለሙያዎች ህመምን ለይተው ተገቢውን ማዳኒት እንዲያዙ የሚያደርግ ክህሎት ኮርሶችን ሲማሩ እንደነበረ ካሪኩለሞቹና ባለሞያዎች የተግባር እማኞች ናቸው (80% diagnosis and treatment role) ።

ለዚህም ሀገሪቷ አያሌ ሀብት አፍስሳለች። አያሌ ባለሙያዎች ራሳቸውን  በክህሎቱ  ለማብቃት ደክመዋል።ከዚህ የዘለለ ሚና (role) ደፍረው ለመሰማራት የሚያስችል ስልጠና እንደለሌላቸው ግልጽ ነው።

ሲጀመር ይህ የሙያ ዘርፍ በድግሪ እንዲሰጥ ገፊ ምክነያቶች ውስጥ ዋናው ምክነያት በዘርፉ የሚመረቅ የሰው ሃይል እጅጉን አናሳ መሆኑና የአእምሮ ህመም ጫና አሳሳቢ በመሆኑ ነው።

በዚህ የተነሳ ሀገሪቷ 1987 ዓም 12/11  ነርሶችን ከተለያዩ ዲስትሪክት ሆስፒታሎች መልምላ የአንድ ዓመት ስለጥና በመስጠት ወደ ነበሩበት ተመልሰው እንዲያገለግሉ በማድረግ ጀምራላች።

ይህም በቂ ሆኖ አልገኝ ሲል በሁለተኛ ዲግሪ ደግም የተለያየ የሙያ ዘርፍ ያላቸውን
ማለትምHO: Comprhensive nursing: Midwifery: Anesthesia ሙያ ያላቸውን በክሊኒካልም በማህበረሰብ የአእምሮ ጤና ስፔሻሊቲ እንዲኖራቸው በማሰልጠን ሙያው እንዲያድግ ጥረት እየተደረገ እንደነበር ይታወቃለ።

ከዚህ ባሻገር የዲግሪው መርሓ ግብር ዘርፈ ብዙ ችግር የሚፈቱ ባለሙያዎችን አፍርቷል እፎይታም እንደሰጠ ግልጽ ነው።

ጥያቄ ሁለት
ታዲያ ይህን ሁሉ ባለሙያ የበለጸገበትን ክህሎቱን እንዳይሰማራ ወደሚያደርግ ወደማያቀው ብቃት እንዲሰማራ የሚያስመስል ስያሜ መስጠቱ ያዋጣል ወይ?

Bsc in psychiatry Nursing
የሚለው ስያሜ የትኛው ካሪኩለም እንደወለደው እና ይህን የሙያ ስያሜ የሚመጥን ካሪኩለም (scope of practice) ዩኒቨርስቲዎች  ነበራቸውወይ? የትምህርት ጥራት ማለት ምን ማለት ነው?

ሲጀመር ጤና ጥበቃ እስካሁን ያለው program አይጠቅምም ብሎ የሚያሳምንበት ሳይንሳዊ መንገድ ካለው በግልጽ ማሳመኛ መንገዶቹን ማስረዳትና ውሳኔ ላይ መድረስ ይቻላል።

አይ ሀገሪቷ የምትፈልገው surgical nursing care for psy pt:፣advanced nursing care for psy pt፣pediatric nursing care for psy pt:adult nursing care for psy pt  Or comprensive psychiatric nursing  ከሆነ የምትፈልገው ካሪኩለም አስቀርጻ ተገቢውን ስልጠና አግኝተው እንዲፈሩ ማድረግ ይቻላል።

ማንም የሙያ ጥላቻ የለበትም ።
ካልሆነ ግን በ8ክሬዲት medical surgical የተማረ አንድ ሳይካትሪን፣በ5 Chr  obs /Gyn  የተማረን አንድ ሳይካትሪን፣በ2chr nursing art የተማረን አንድ ሳይካትሪ፥5 chr pharmacology ስላጠና፣3chr psychotherapy የተማረን አንድ ሳይካትሪ ወዘተ: ግባና __ ሁን፣ ሁን፣ መሆን ትችላለህ ይባላል ወይ?

በዲግሪው መርሓ ግብር የpsychiatryዉን science  100%  diagnosis and treatment ነው የሚያውቁት በተማሩበት ይሰማሩ ማለት ነውር ነወይ።

ካልሆነ
1.ይህ አካሂድ የባለሙያዎችን ሞራል ይጎዳል
2.ለሀገሪቷ ኪሳራ ነው
3.የሙያው ዘርፍ ያቀጭጫል
4.ከሁሉም በላይ ሰው የተማረበትን ሙያ መንጠቅ ነው።ለማንኛው በህግ መታየት አለበት።

በሌላም የጤና ዘርፍም ብንሄድና Nomenclature ብናይ፦

ANSTHESIA: Bachelor of science (BSC) in Anesthesia ነው።
Opthamology:optometry ነው
midwifery: midwife ነዉ።
physiotherapy  እንደዛው ሁሉንም ማየት ይቻላል። እና ነርሲን የሚባል የተከበረ ሙያ ራሱን ችሎ የሚሄድ ትልቅ የጤና ዘርፍ ነው። ነርሲንግ ሙያ በአብዛኛ ዓለም በዲግሪው ጠቅላላ ዕውቀትን የሚፈልግ እና በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ ወደ አንድ ስፔሻሊቲ እያደላ የሚሄድ ነው።
    
ባለሙያዎች
በተማሩበት የስራ ክህሎት ይሰማሩ።


ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!

Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ)
ጥቅምት/ 4 /2017


Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry

Ethio Psychiatry

14 Oct, 05:50


በ'ሰበር ዜና' ምክኒያት የሚመጣ 'Disorder'
===========================

ሰበር ዜና እንዲሁም ተሰባሪ ዜና😂 እጅግ በዝቷል። ዜና ከሰማችሁ በኋላ እስቲ የውጥረት (Stress) መጠናችሁን አስተውሉ። ደስ የሚል ዜና መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ የሰማችሁት?🤔

ዜናን ተከትሎ የሚመጣ የውጥረት ሁኔታ Headline Stress Disorder ይባላል። 'ሰበር' ም ይሁን አል 'ሰበር' 😂  ዜናዎች ሁለት ወሳኝ አሉታዊ ነገሮች ያስከትላሉ።

1) አቅመቢስነት(Powerlessness)- አብዛኞቹ ዜናዎች ተስፋ ያስቆርጣሉ። ሴራ፣ ደባ፣ አሻጥር፣ ተንኮል፣ ጦርነት፣ ክፋት.....ወዘተ ናቸው። ከዛ ደግሞ በግለሰብ አቅም ምንም ማድረግ አንችልም። ሆኖም ስራችን ላይ ጠንክረን እንዳንሰራ ተነሳሽነታችንን ይሰልቡታል።

2) ህይወት ትርጉም የለሽ (Meaningless) እንዲመስለን ያደርጉናል። የሚሰማው ዜና ሁሉ መጥፎ ሲሆን ህይወት ትርጉም የለሽ ይመስለናል። "ሰራሁ አልሰራሁ ምን ለውጥ አለው?" እንድል ያደርገናል። ከራሳችን አቅምና ፍላጎት ይልቅ ትርጉም የለሽ ነገሮችን እንድንመለከት ያደርጉናል። ሰበር ዜናዎችን ስንመለከት ነገሮች ከመጥራት ይልቅ ይወሳሰቡብናል። ይሄኛው ያኛውን እወቀሰ ዜና ይሰራል። ያኛው ይሄኛውን እየከሰሰ ይተነትናል።እኛ በመሀል ተቃ.......ጠልን!

ጥሩ ነገሮች ለምን ዜና እንደማይሆኑ ግራ ይገባኛል።

ለምሳሌ፦
-ስዊዘርላድ ጦርነት ከተደረገ በጣም ቆይቷል።
-60 ሰዎችን ይዞ ሲሄድ የነበረው የህዝብ ማመላሻ አውቶብስ ለተሳፋሪዎቹ ቆሎ በነፃ እያደለ ነበር።
-አንዳንድ ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደነገሩኝ ከሆነ 'ውስጥ አዋቂ ምንጮች' የሚባለው ዜና እነሱን እንደማይወክልና ስም ተጠቅሶ በመረጃ ተደግፎ እንዲቀርብ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።😂

ለማንኛውም ዜና መቀነስ ለአእምሮ ጤና ጥሩ ነው።

በአንድ ሰበር ዜና እንለያይ "ቀላሉን ነገር አታካብድ" 6ኛ እትም ገበያ ላይ ነው!!!

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!

ዶ/ር ዮናስ ላቀው

Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry

Ethio Psychiatry

14 Oct, 04:21


ሰበር ዜና

Ethio Psychiatry

13 Oct, 05:28


Prescribing psychotropics from drug interactions to pharmacogenetics


Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry

Ethio Psychiatry

11 Oct, 03:14


Check in on those around you!!

No Health Without Mental Health!!

        Ethio Psychiatry
🤝 "Together, we can create a world where mental health is a priority"

Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry

Ethio Psychiatry

10 Oct, 16:38


No Health Without Mental Health!!

October 10 is World Mental Health Day!!!

It’s a significant day, but mental health problems aren’t just for a day. We’re going to keep fighting every single day for those of us struggling.

🤝 Together, we can create a world where mental health is a priority

        Ethio Psychiatry
"We Care For Your Mental Health"


Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry

Ethio Psychiatry

09 Oct, 14:58


Tomorrow is World Mental Health Day

It is time to prioritize mental health in the workplace.

👩‍👩‍👦‍👦 Let us prioritize mental health in the workplace and create a brighter future for all

It’s a significant day, but mental health problems aren’t just for a day. We’re going to keep fighting every single day for those of us struggling.

🤝 Together, we can create a world where mental health is a priority

        Ethio Psychiatry
"We Care For Your Mental Health"

#Ethiopsychiatry
#Worldmentalhealthday
#Mentalhealthawareness #Breakthestigma

Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry

Ethio Psychiatry

08 Oct, 05:15


አለም አቀፍ የአእምሮ ጤና ቀን
=====================

በየዓመቱ October 10 ይከበራል፡፡

አለም አቀፍ የአእምሮ ጤና ቀን በየዓመቱ October 10 በተለያዩ መፈክሮች ይከበራል። "በስራ ቦታችን ለአዕምሮ ጤናችንን ቅድሚያ እንስጥ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል::

የበዓሉ ዓላማ ስለ አእምሮ ጤና አስፈላጊነት ግንዛቤ ማሳደግ, ሰዎች ለሌሎች አካላቸው እንደሚያደርጉት ለአእምሯቸው ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው,  ስለ አእምሮ ህመም እና ስለ ሌሎች የአእምሮ ጤና ጉዳዮች እርስ በርስ መማማር, የአእምሮ ጤናን መጠበቂያ መንገዶችን ማስተማር ነው።

በአጠቃላይ ከአእምሮ ህመም ጋር ተያይዞ ያለውን መገለል በመስበር የተሻሻለ የአእምሮ ጤና ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ማበረታታት ነው።  ስለዚህ መረጃ ጠቃሚ ሚና ይጫወታል.

የዚህ የቴሌግራም ፔጅ Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ) አላማ ስለ አእምሮ ጤና፣ የስነ ልቦና እና የአእምሮ ህመም መረጃዎችን በቋንቋችን ማካፈል ነው። ከዚህ ተጠቃሚ እንደሆናችሁ ተስፋ እናደርጋለን።

ይህ ስራ ወደፊት ተጠናክሮ ይቀጥላል!!! በተቻለ መጠን የአዕምሮ/የስነ ልቦና ጤናችንን ለመጠበቅ እንዲረዳን ስለአእምሮ/የስነ ልቦና ሕመሞች እና ህክምናዎቻቸው ሳይንሳዊ መረጃ ማድረሳችንን እንቀጥላለን።

በስራ ቦታችን ለአዕምሮ ጤናችንን ቅድሚያ እንስጥ!!!

Ethio Psychiatry (ኢትዮ ሳይካትሪ)

#ethiopsychiatry
#worldmentalhealthday
#breakthestigma

Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry

Ethio Psychiatry

06 Oct, 17:03


Guyyaa Fayyaa Sammuu Addunyaa 2024
===============================
Guyyaan fayyaa sammuu addunyaa waggaa waggaan, Onkolool
essa 10 A.L.Atti  dhaadannoo gara garaatiin
kabajamee oola. Kan baranaa dhaadannoo "Bakka hojii keenyaatti fayyaa sammuu keenyaaf dursa haa kenninu!” jedhuun Onk  10. 2024Akka addunyaatti kabajamee nii oola.

Kaayyoon kabaja kanaas barbbachisummaa fayyaa sammuu irratti dammaqina uumuu,  namootni  haguma qaama isaanii biro fayyaa sammuu isaaniif xiyyeeffannoo akka kennan, waa’ee dhibee sammuufi waantoota biroo sammuu namaa miidhuu danda’an wal hubachiisuu, maloota fayyaa sammuu eeguuf nama gargaaranirratti namaota quba qabaachisuu, yoo rakkoon fayyaa sammuu nu mudate, aantee keenya mudate akkamitti waldhaansa argachuun akka danda’amu quba walqabsiisuu dha.

Walumaa galatti mogggeeffamuu, safeeffamuu dhibee sammuu waliin walqabatee jiru cabsuun, hawaasa fayyaa sammuu fooyya’e qabu uumuuf sochii godhamu jajjabeessuu dha. Kanaaf ammo odeeffannoon gaheen isaa guddaadha.

Kaayyoon fuula Telegram kanaas, odeeffannoo fayyaa sammuu, qorqalbii , dhibee sammuun walqabatan afaan keenyaan, wal biraan gahuudha.  Fayyadamoo tahaa akka jirtan abdii qabna!

Hojiin kun fuuldurattis jabaatee itti fufa!!! Maloota danda’aman maraan odeeffannoo dhibee sammuu/qorqalbiifi waldhaansa isaanii, fayyaa sammuu/qorqalbii keenya eeggachuuf nugargaaran saayinsawaa tahan isiniif dhiyeessuun itti fufa.

Ethio Psychiatry

Bakka hojii keenyaatti fayyaa sammuu keenyaaf dursa haa kenninu!!!

#ethiopsychiatry
#fayyaasammuu
#worldmentalhealthday

Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry

Ethio Psychiatry

06 Oct, 16:36


Guyyaa Fayyaa Sammuu Addunyaa 2024

Ethio Psychiatry

02 Oct, 17:02


WORLD MENTAL HEALTH DAY 2024
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
World Mental Health Day is coming up on October 10, and it’s a reminder to take a moment for yourself.

We are excited to share with you the upcoming World Mental Health Day on 10th October 2024. This day serves as a global platform to increase awareness about mental health and highlight its immense importance in our lives.

In today's fast-paced world, it is crucial to prioritize our mental well-being just as much as our physical health. Mental health matters because it affects every aspect of our lives - from our relationships to our work performance and overall happiness. Let's break the stigma and start talking openly about it!

This year's theme for World Mental Health Day is "It is time to prioritize mental health in the workplace." It emphasizes the fact that access to quality mental health care should be a fundamental right for everyone, regardless of their background or circumstances. Let us join together in advocating for this essential cause!

Remember, showing compassion and offering support to those struggling with mental health challenges can make a significant difference. Together, we can create safe spaces for open conversations, offer understanding, and extend a helping hand to those in need.

Join us in spreading awareness about mental health by sharing this post and using the hashtag

#Worldmentalhealthday.

Together, let's contribute to creating a more inclusive and supportive world for everyone. 🌍❤️

Let us prioritize mental health in the workplace and create a brighter future for all and  make every day a day to prioritize mental health!Together, we can make a difference.

Yordanos Yihun (Psychiatry Professional)

#Ethiopsychiatry
#Worldmentalhealthday
#Mentalhealthawareness #Breakthestigma

Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry

Ethio Psychiatry

02 Oct, 17:02


WORLD MENTAL HEALTH DAY 2024

Ethio Psychiatry

23 Sep, 14:34


Suicide
***
Sometimes, the most important conversations are the hardest ones to have. September is Suicide Prevention Month, and one of the most powerful things we can do is to learn how to ask someone if they're feeling suicidal. Here's how:

🤔 How to Ask:

1. Choose a Calm Moment: Find a quiet, comfortable place where you can talk without interruptions.
2. Show You Care: Start by expressing your concern. "I've noticed you've been going through a lot lately, and I'm here to support you."
3. Be Direct and Gentle: While it may feel uncomfortable, ask the question directly. "Are you having thoughts of suicide?"
4. Listen Without Judgment: Give them space to share their feelings without jumping to conclusions or offering immediate solutions.
5. Validate Their Emotions: Let them know that their feelings are valid and that you're there to understand.
6. Ask About Their Plan: If they express thoughts of suicide, ask if they've thought about how they might do it. This helps gauge the level of risk.
7. Encourage Professional Help: Suggest speaking with a mental health professional and offer to help them find resources.
8. Stay Connected: Let them know you're committed to supporting them throughout their journey.

Remember, your willingness to ask can provide a lifeline to someone in need. By showing you genuinely care and are there for them, you're taking an essential step toward breaking down stigma and saving lives.

Ethio Psychiatry

We care for your mental health

#ethiopsychiatry
#talkbringshope #askthetoughquestions #suicidepreventionmonth
#youarenotalone 🗣️❤️
#mentalhealthmatters

Join Us
@ethiopsychiatry
@ethiopsychiatry

Ethio Psychiatry

21 Sep, 19:23


🔵 CALL FOR ABSTRACT 🔵

🔸EVENT:- World mental health day.

🔸HOST:- Worabe Comprehensive Specialized Hospital Collaborating with Ministry of Health

🔸DATE: October 10, 2024

🔸THEME:  "It is time to prioritise mental health in the workplace"

Subthemes:

Workplace stress, distress and burnout

➡️ Impact of mental health problems on workplace productivity

➡️ Workplaces mental health interventions

➡️ Others related to main theme

🔶 Important dates

▪️Abstract submission deadline: September 30, 2024

▪️Notification of acceptance date: October 3, 2024

▪️Full paper submission deadline: October 6, 2024

🔸Submit abstract to:

[email protected]
[email protected]

Ethio Psychiatry

21 Sep, 09:39


ዘላቂ ሱስ በአንድ ዛፍ እንዴት ይመሰላል?

ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦች!

ዛሬ አንድ ዘላቂ ሱስ በአንድ ባለ ብዙ ስር፣ ግንድ ፣ቅርንጫፎች፣ ቅጠሎች እና ፍሬዎች ባለው ትልቅ ዛፍ በመመሰል ስለሚያስረዳ አንድ ዘይቤያዊ ሞዴል አስነብባችሁሃለሁ።

"በሱስ ዛፍ" ዘይቤ ውስጥ ሱስ ብዙ ውስብሰብ ስሮች ያሉት፣ እየወፈረ የሚሄድ ግንድ ያለው ፣ እየሰፉ የሚሄዱ ቅርጫፎች፣ እየበዙ በሚሄዱ ቅጠሎች እና ብዙ ጣፋጭ ወይም መራራ ፍሬዎች ያሉት ሕያው ሥርዓት ሆኖ ይመስላል።

ይህ ዘይቤ ሱስ ውስብስብ እና ባለ ብዙ ንብርብር ሽፋን የህይወት ልማድ እንደሆነ ለማሳየት ይሞክራል። ዝርዝሩን እነሆ!

1. የዛፉ ሥሮች ( ስረ-መሰረት መንስኤዎች)

በዚህ ዘይቤያዊ ሞዴል ውስጥ ሥሮቹ ወደ ሱስ የሚሚያመሩትን ጥልቅ እና ብዙውን ጊዜ የተደበቁ ምክንያቶችን ይወክላሉ። እነዚህም በሱስ ለመያዝ አጋላጭ ስነ ልቦናዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሲሆኑ ሥሮቹ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ ።

✍️የዘረመል ቅድመ-ተጋላጭነት:- አንዳንድ ሰዎች በዘር የሚተላለፍ ለሱስ ተጋላጭነት አላቸው። ይህም ከአዕምሮ ንጥረ ነገሮች እስከ ቤተሰብ ታሪክ ሊያካትት ይችላል።

✍️ ያለፉ አሰቃቂ የህይወት ገጠመኞች ወይም ከፍተኛ የየዕለት ጭንቀት፡- ሰዎች ያልተፈቱ የስሜት ቁስሎች ወይም ሥር የሰደደ የህይወት ውጥረትን ለመቋቋም ወደ ሱስ ሊገቡ ይችላሉ።
✍️የአእምሮ ጤና መታወክ፡- የጭንቀት፣ የድብርት፣ ድህረ አደጋ ጭንቀት፣ ወይም ሌሎች የአእምሮ ጤና ህመሞች ካሉ ወደ ሱስ ሊያመሩ ይችላሉ።
✍️አካባቢ እና አስተዳደግ፡- የአደንዛዥ ዕፅ መጠቀም እንደ መደበኛ ነገር በሚቆጠርበት አካባቢ ማደግ ወይም የተበላሽ የቤተሰብ ግንኙነት ለሱስ ለመያዝ መንስኤ ይሆናሉ ።

2. የዛፉ ግንድ (የሱስ እድገት)

በዚህ የሱስ ዛፍ ዘይቤ ውስጥ ግንዱ አንድ ሰው መጀመሪያ ሱስ ሀ ብሎ መጠቀም ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ሙሉ የተወሳሰበ ሱስ የሚሸጋገርበትን ሂደት ይወክላል። ይህ ደረጃ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል:-

✍️ ሙከራ፡- ሰውዬው መጀመሪያ ሱስን የሞከረበትን ጊዜ የሚያሳይ ሲሆን ይህም ሱስ አስያዥ የሆነውን ንጥረ ነገር ለመሞከር ካለን ፅኑ ፍላጐት ወይም ከአቻ ግፊት የተነሳ ሊሆን ይችላል።

✍️ በመደበኛነት መጠቀም:- ከዚያም ቀስ በቀስ ግለሰቡ አዘውትሮ ሱስ አስያዥ የሆነውን ንጥረ ነገር መጠቀም ሲጀምር የዕለት ተዕለት ሕይወቱ አካል ወደ መሆን ይሸጋገራል።

✍️ በጊዜ ሂደት በትንሹ አለመርካት፡- በጊዜ ሂደት አካል እና አእምሮ ሱሱን በመላመድ ተመሳሳይ ከሱሱ የሚገኘውን የእርካታ ውጤት ለማግኘት ብዙ ንጥረ ወደ መፈለግ ደረጃ ያሸጋገራል።

✍️ ሙሉ ጥገኝነት:- በመጨረሻም ግለሰቡ በሱሱ ላይ ሙሉ ጥገኛ በመሆን የየዕለት መደበኛ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ እንኳን ሳይቀር የግድ ሱሱ ወደሚያሰፈልግበት አስከፊ ደረጃ ይሸጋገራል።

3. ቅርንጫፍ (የሱስ ዘርፈ -ብዙ አሉታዊ መዘዞች)

በዚህ ዘይቤያዊ ሞዴል ውስጥ ቅርንጫፎቹ ሱስ የሚያስከትላቸውን መጠነ ሰፊ አሉታዊ ውጤቶች ይወክላሉ። ሱሱ እየቆየ ሲመጣ ተጠቃሚው በተለያዩ የሕይወት ዘርፎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያጋጠመው ይሄዳል። እነዚህም:-

👉የአካላዊ ጤና ጉዳቶች፡- ዘላቂ ሱስ የጉበት ችግሮች፣ የልብ ችግሮች፣ የመተንፈሻ አካላት እና ሌሎች በርካታ የአደንዛዥ እጽ አጠቃቀም የጤና መዘዞች ያስከትላል።

👉 የአእምሮ ጤና መበላሸት፡- ሱስ እንደ ድብርት፣ ጭንቀት፣ እና ሳይኮሲስ ያሉ የአእምሮ ጤና መታወክ እንዲከስቱ ወይም እንዲባባሱ በማድረግ የአዕምሮ ጤናን ወደ ማበላሸት ይሄዳል።

👉 የማህበራዊ የግንኙነት ችግሮች፡- ሱስ ከቤተሰብ፣ ከጓደኞች እና ከ ህይወት አጋር ጋር ያለውን ጤናማ ግንኙነት በማበላሸት የተበላሽ የየዕለት ማህበራዊ ህይወት እንዲኖር ያደርጋል።

👉የገንዘብ ችግሮች፡- ዘላቂ ሱስ ለራሱ ለሱሱ በየቀኑ ገንዘብ በማውጣት ወይም ደግሞ በሱሱ ምክንያት ሥራ በማጣት ወደ ገንዘብ ቀውስ ይመራል።

👉ህጋዊ ጉዳዮች፡ - ሱሱን ለማግኘት ወይም ለመጠቀም በህገ ወጥ ተግባራት ውስጥ መሳተፍ እስራትን ጨምሮ ወደ ሌሎች ህጋዊ ችግሮች ያመራል።

👉ማህበረሰባዊ መገለል፡ - እንዲሁም ሱስ ብዙውን ጊዜ ከማህበራዊ ህይወት ወደ መውጣት ወይም በሌሎች መገለል ወደ መጋለጥ እና ሌሎች በርከታ የሱስ መዘዞችን ያካትታል።

4. የዛፉ ቅጠሎች (ሱስ ያለበት ግለሰብ ለየት ያሉ ባህሪያት)

በዚህ ዘይቤያዊ ሞዴል የዛፉ ቅጠሎቹ ግለሰቡ ሱሱን ለመቀጠል ወይም ለመደበቅ የሚጠቀምባቸውን የሚታዩ እና እና የማይታዩ ባህሪያትን ይወክላሉ። ለምሳሌ፦

👉 ስለ ሱሱ አስከፊነት መዋሸት እና መካድ
👉ማታለል
👉 ተደጋጋሚ ሱስን ለማቆም መቸገር
👉 ማሳበብ
👉 ችግሩን አሳንሶ ማየት
👉 ሱስን ለትንንሽ ችግሮች እንደማምለጫ መጠቀም
👉 ለሱስ ችግራቸው ሳይንሱም እኮ ትንሽ ትንሽ ተጠቀሙ ይላል የሚል ግርድፍ ማብራሪያ መስጠት
👉 ስለ ሱስ ለመነጋገር ፈቃደኛ አለመሆን ወዘተ...

5. የዛፉ ፍሬዎች ( ከሱስ የማገገምን አወንታዊ ውጤቶች ወይም የዘለቂ ሱስ አሉታዊ መዘዞች)

በዚህ የሱስ ዛፍ ዘይቤ ውስጥ የዛፉ ፍሬዎች ከሱስ የማገገምን አወንታዊ ጣፋጭ ውጤቶች ወይም የዘለቂ ሱስ መራራ አሉታዊ መዘዞችን ያመለክታል።

አወንታዊ ጣፋጭ ፍሬዎች
👉ከሱስ የፀዳ መደበኛ ህይወት
👉የተበላሹ ግንኙነቶችን ወደነበሩበት ጤናማነት መመለስ
👉የተሻሻለ ጤና
👉 ዘርፈ-ብዙ ግለሰባዊ እድገት

አሉታዊ መራራ ፍሬዎች
👉 ዘላቂ የጤና ችግሮች
👉 ጥልቅ ማህበራዊ መገለል
👉 ጥልቅ ማህበራዊ ቀውስ
👉 ጥልቅ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ
👉 ዘላቂ የስነ አዕምሮ አክሎች
👉 መንፈሳዊ ቀውሶች
👉 ያለዕድሜ ሞትን ሊያስከትል ይችላል ።

በአጠቃላይ "የሱስ ዛፍ ሞዴል" የሱስን ውስብሰብ ባህሪ ለማሳየት ያለመ ሞዴል ሲሆን ስር የሰደዱ ድብቅ እና ግልፅ መንስኤዎችን፣ የሱስ ዕድገትና ሂደትን እና መጠነ ሰፊ አሉታዊ የሱስ መዘዞችን በአንድ ትልቅ ዛፍ በመመሰል ያስረዳል። እንዲሁም ከሱስ ማገገምም ልክ አንድ የደረቀ ዛፍን ወደነበረበት እንደመመለስ ያለ ውስብስብ የህይወት ጉዞ እንደሆነ ለማሳየት ይሞክራል።

እነዚህን የሱስ ንብርብር ባህሪያት በመረዳት ግለሰቦች እና ባለሙያዎች ሱስን ከላይ ከላይ ማየት ብቻ ሳይሆን ሱስን ከጀርባ ሆነው የሚዘውሩትን ዋና ዋና ጉዳዮችን በተሻለ ሁኔታ መፍታት ይችላሉ።

ከሱስ ማገገምም ልክ እንደ ዛፍ ዘላቂ እድገትን እና ጤናን ለማሳደግ እነዚያን ሥሮች እና ቅርንጫፎች ን በጥልቀት ማየት እና ማከምን ይጠይቃል።

ለወዳጅዎ ማጋራት አይርሱ!

አብረውን ስለሆኑ ከልብ እናመሰግናለን!



"ጤናማ አዕምሮ ለጤናማ ህይወት!!"

ሲደልል አስፋው (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)


Join us:👇👇👇👇👇

Telegram

@Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ)
@Ethiopsychiatry (አትዮ ሳይካትሪ

Facebook

https://www.facebook.com/profile.php?id=61556978168876

LinkedIn

https://www.linkedin.com/in/sidelil-asfaw-72a710217?utm_source=share&utm_campaign=share_via&utm_content=profile&utm_medium=android_app