#KALTUBE

@kaltube


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ። ዩሐ1÷ 14
" Daily Spiritual Feeding"
በዚህ ያገኙናል👉 @Kaltube_bot

የዩቲዩብ ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ👇
https://youtube.com/c/KALTUBEOfficial

ዘጠነኛ ቃልኛ ዲጂታል መፅሔታችን👇
https://t.me/KALTUBE/9618

#KALTUBE

22 Oct, 14:52


92. በጌታና በኃይሉ ብርቱ ነኝ (ኤፌሶን 6፡10)
93. የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ እለብሳለሁ (ኤፌሶን 6፡13)
94. የሰይጣንን ፍላጻዎች ሁሉ ማጥፋት እችላለሁ (ኤፌሶን 6፡16)
95. በእኔ መልካምን ሥራ የጀመረ እርሱ  ይጨርሰዋል (ፊልጵስዩስ 1፡6)
96. በምንም አላፍርም  (ፊልጵስዩስ 1፡20)
97. በክርስቶስ የነበረው አሳብ በእኔ ውስጥ ነው። (ፊልጵስዩስ 2፡5)
98.እግዚአብሔር በጎ ፈቃዱን ልፈልግና ላደርግ በእኔ ይሠራል (ፊልጵስዩስ 2፡13)
99. አገሬ በሰማይ ነው(2ቆሮ 5:1)
100.እኔ ምጽአቱን በናፍቆት የምጠብቅ አማኝ ነው። (ፊልጵስዩስ 3፡20)

ሃሌሉያ!!!
እናንተ ቃሉ ከሚላችሁ ዉጪ ሃይማኖተኞች፣  ሰይጣንና ሁኔታ የሚላችሁን አይደላችሁም።

የእግዘብሔር ቃል ነበራችሁ ያላችሁን ነበራችሁ!
የእግዚአብሔር ቃል ናችሁ ያላችሁን ናችሁ!
ትሆናላችሁ ያላችሁን ትሆናላችሁ !
ትችላላችሁ ያላችሁን ትችላላችሁ !

አሜን!!
መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)

ክፍል 5 ይቀጥላል

👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
            @KALTUBE
            @KALTUBE
            @KALTUBE

#KALTUBE

22 Oct, 14:52


  በክርስቶስ    IN CHRIST
ክፍል 4
        = እኔ በክርስቶስ ማነኝ? =
100 መፅሐፍ ቅዱሳዊ የአማኞች መታወቂያ


እኔ በክርስቶስ:--

1- የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ (ዮሐ. 1፡12)
2. ዳግመኛ ተወልጃለሁ (1ኛ ጴጥሮስ 1:23)
3. እኔ ቅዱስ ነኝ (1ኛ ቆሮንቶስ 1፡2)
4. እኔ የምድር ጨው ነኝ (ማቴ 5፡13)
5. እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ (ማቴ 5፡14)
6.የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነኝ (ዮሐ. 13፡34-35)
7. በስሙ ኃይል የምጠበቅ ሰው ነኝ (ዮሐንስ 17፡11)
8. በእውነት አርነት ወጥቻለሁ (ዮሐንስ 8፡31-33)
9. በክርስቶስ ለዘላለም ተጠብቄአለሁ (ዮሐንስ 10፡27-31)
10. ከክፉ ተጠብቄአለሁ (ዮሐ. 17:15)
11. እኔ የእግዚአብሔር  ቤተሰብ ነኝ (ዮሐ. 17፡23)
12. በክርስቶስ የእግዚአብሔር ስጦታ ነኝ (ዮሐ. 17፡24)
13.ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለኝ (ሮሜ 5፡1)
14. በእምነት ጸድቄአለሁ (ሮሜ 5፡1)
15. ወደ ከበረው  የእግዚአብሔር ጸጋ ስፍራ ገብቻለሁ።  (ሮሜ 5፡2)
16. በመከራ ደስ ይለኛል (ሮሜ 5፡3)
17. የእግዚአብሔር ፍቅር በልቤ ፈሷል (ሮሜ 5፡5)
18. በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ገዢ ነኝ።  (ሮሜ 5፡17)
19. በኢየሱስ ሞት ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅያለሁ። (ሮሜ 5፡10)
20. የዳንኩት በኢየሱስ ሕይወት ነው (ሮሜ 5፡10ለ)
21. ከክርስቶስ ሞት ጋር አንድ እንድሆን ተጠመቅያለሁ። (ሮሜ 6፡3)
22. በአዲስ ሕይወት ለመመላለስ ተነስቻለሁ (ሮሜ 6፡4)
23. በሞቱና በትንሳኤው ከክርስቶስ ጋር አንድ ነኝ (ሮሜ 6፡5)
24. አሮጌው ሰውነቴ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሏል (ሮሜ 6፡6)
25. በክርስቶስ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ሕያው ነኝ (ሮሜ 6፡11)
26. ለእግዚአብሔር ተሰጥቻለሁ (ሮሜ 6፡13)
27. ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደለሁም (ሮሜ 6፡14)
28. በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት አለኝ (ሮሜ 6፡23)
29. ከኃጢአት ኃይል ነፃ ወጥቻለሁ (ሮሜ 6፡18)
30. ከኩነኔ ነጻ ነኝ (ሮሜ 8፡1)
31. የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ (ሮሜ 6፡22)
32. ከኃጢአት ሥልጣን ነፃ ወጥቻለሁ የጽድቅም አገልጋይ ነኝ (ሮሜ 6፡18)
33. ከኃጢአትና ከሞት አዙሪት ነፃ ወጥቻለሁ (ሮሜ 8፡2)
34. የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ነኝ (ሮሜ 8፡9)
35. በእግዚአብሔር መንፈስ እመራለሁ (ሮሜ 8፡14)
36. ከክርስቶስ ጋር የጋራ ወራሽ ነኝ (ሮሜ 8፡17)
37. ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እርግጠኛ ነኝ (ሮሜ 8፡28)
38. የክርስቶስን መልክ እመስል ዘንድ ከክብር ወደክብር እለወጣለሁ።  (ሮሜ 8፡29)
39. መንፈስ ቅዱስ በድካሜ ይረዳኛል (ሮሜ 8፡26)
40. መንፈስ ቅዱስ ስለ እኔ ይማልዳል (ሮሜ 8፡26)
41. እግዚአብሔር አስቀድሞ አውቆኛል (ሮሜ 8፡29)
42.በክርስቶስ ሁሉ ተሰጥቶኛል (ሮሜ 8፡32)
43. ከእግዚአብሔር ፍቅር የሚለየኝ ኃይል የለም።  (ሮሜ 8፡35)
44. በክርስቶስ ከአሸናፊዎች እበልጣለሁ (ሮሜ 8፡37)
45. እኔ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነኝ (1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16-17)
46. ​​በኢየሱስ ደም ታጥቤ፣ ተቀድሼ፣ ጸድቂያለሁ (1ኛ ቆሮንቶስ 6፡11)
47. በዋጋ ተገዝቻለሁ (1ኛ ቆሮንቶስ 6፡20)
48. የእግዚአብሔር መልክና ክብር በእኔ ይገለጣል።  (1ኛ ቆሮንቶስ 11፡7)
49. በክርስቶስ ድል አድራጊ ነኝ (2ኛ ቆሮንቶስ 2፡14)
50. በምሄድበት ሁሉ የእግዚአብሔርን መገኘት የምገልጥ ጣፋጭ መዓዛ ነኝ (2ኛ ቆሮንቶስ 2፡14)
51. እኔ ለማንኛውም ነገር በቂ ነኝ ምክንያቱም የእኔ ብቃት ከእግዚአብሔር ነው።  (2ኛ ቆሮንቶስ 3: 5)
52. እኔ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ነኝ (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17)
53.  በጣም ደካማ ስሆን ያኔ በጣም ኃይለኛ ነኝ (2ኛ ቆሮንቶስ 12፡10)
54. እኔ የክርስቶስ አምባሳደር ነኝ (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡20)
55. ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ፤ አሁን የምኖረው ኑሮ የእርሱ ነው (ገላ 2፡20)
56. ከሕግ እርግማን ነፃ ወጥቻለሁ (ገላ 3፡13)
57. በመንፈስ ፍሬ በፍቅር፥ በደስታ፥ በሰላም፥ በትዕግሥት፥ በበቸርነት፥ በበጎነት፥ በእምነት፥ በየውሃት፥ ራስን በመግዛት መንፈስ የምመላለስ አማኝ ነኝ። (ገላትያ 5፡22-23)

58.እኔ በክርስቶስ ነኝ (ኤፌሶን 1፡1)
59. በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ተባርኬአለሁ (ኤፌሶን 1፡3)
60. ቅዱስና ነውር የሌለኝ እሆን ዘንድ በእግዚአብሔር ተመርጫለሁ (ኤፌሶን 1፡4)
61. በኢየሱስ ልጅ ለመሆን አስቀድሞ ተወስኛለሁ። (ኤፌሶን 1፡5)
62. በአብ ፊት ተቀባይነት አግኝቻለሁ (ኤፌሶን 1፡6)
63. በደሙ የተደረገ ቤዛነት አለኝ (ኤፌሶን 1፡7)
64. ኃጢአቴ ሁሉ ተሰርዮልኛል (ኤፌሶን 1፡7)
65.የፈቃዱን ምሥጢር አውቃለሁ(ኤፌ 1፡9)።
66. ፈቃዱን የማውቅበት ጥበብ አለኝ (ኤፌሶን 1፡8)
67. እንደ ሀሳቡ አስቀድሞ ተወስኛለሁ (ኤፌሶን 1፡11)
68.በክርስቶስ ርስት አግኝቻለሁ (ኤፌሶን 1፡11)
69. በተስፋው በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቻለሁ (ኤፌሶን 1፡13)
70. የእውቀት የጥበብና የመገለጥ መንፈስ ተሰጥቶኛል። (ኤፌሶን 1፡17)
71. ዓይኖቼ በርተዋል (ኤፌሶን 1፡18)
72. የመጠራቴን ተስፋ አውቃለሁ (ኤፌሶን 1፡18)
73. በእኔ ዘንድ ያለውን የኃይሉን ታላቅነት አውቃለሁ (ኤፌሶን 1፡19)
74. በቅዱሳን ያለውን የርስቱን ባለጠግነት አውቃለሁ (ኤፌ 1፡18)።
75. ከክርስቶስ ጋር ሕያው ሆኛለሁ (ኤፌሶን 2፡1)
76. ከክርስቶስ ጋር ተነስቻለሁ በሰማያትም ተቀምጫለሁ (ኤፌሶን 2፡6)
77. በጸጋው  በእምነት ድኛለሁ ኤፌሶን 28)
78. ለበጎ ሥራ ​​በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርኩ የእግዚአብሔር የእጅ ሥራ ነኝ (ኤፌሶን 2፡10)
79. ቀድሞ ርቄ ነበር ፤አሁን ግን በክርስቶስ ደም ቀርብያለሁ (ኤፌሶን 2፡13)
80. በኢየሱስ ወደ አብ የመግባት መብት አግኝቻለሁ (ኤፌሶን 2፡18)
81. እኔ በእግዚአብሔር ቤት ከቅዱሳን ጋር አብሬ ዜጋ ነኝ (ኤፌሶን 2፡19)
82. በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽሁ፣ የማዕዘኑ ራስ የሆነው ክርስቶስ ራስ ሆኖኛል (ኤፌ 2፡20)።
83. በድፍረት ወደ ክርስቶስ መገኘት መሄድ እችላለሁ (ኤፌሶን 3፡12)
84. በውስጥ ሰውነቴ በመንፈሱ በኃይል እበረታለሁ (ኤፌሶን 3፡16)
85. ከምለምነው ወይም ከማስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብዝቼ እቀበላለሁ (ኤፌሶን 3፡20)
86. እውነትን በፍቅር እናገራለሁ (ኤፌሶን 4፡15)
87. በእርሱ ሥር በሁሉም ነገር ማደግ እችላለሁ (ኤፌሶን 4፡15)
88. በአእምሮዬ መንፈስ እታድሳለሁ (ኤፌሶን 4:23)
89. አሮጌውን ሰው አስወግጄዋለሁ (ኤፌሶን 4፡22)
90. እኔ ዱሮ ጨለማ ነበርሁ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ሆኜአለሁ (ኤፌሶን 5፡8)
91.እንደ ብርሃን ልጅ እመላለሳለሁ (ኤፌሶን 5፡8)

#KALTUBE

21 Oct, 19:21


በክርስቶስ   IN CHRIST

ክፍል 3

=በክርስቶስ የተቃኘ አስተሳሰብ=

እኛ አማኞች በክርስቶስ ማንነት፣ተፈጥሮና መታወቂያ ያለን ክቡር ህዝብ እንጂ ተራ ህዝቦች አይደለንም።እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ነን። ይህ 100% የተረጋገጠ እውነት ነው።

➢በክርስቶስ ሆነህ የማልረባ፣ የማልጠቅም፣ ሀጢአተኛ፣ተራ ሰው ነኝ ማለት አጉል ትህትና እንጂ በእግዚአብሔር ፊት የሚያስገኝልህ ሞገስ የለም። ትህትና ማለት እራስህን መራገም ሳይሆን እግዚአብሔር ነህ ያለህን አሜን ነኝ ብለህ ማመንና መቀበል ነው።

እግዚአብሔር ልጄ ሲልህ፣አቤት አባዬ ማለት እንጂ ያለብህ እኔ የማልረባ ሰው ነኝ ማለት
የትህትና ሰው አያሰኝም። ምክንያቱም እግዚአብሔር የማይረባ ልጅ የለውም።

አንደ አማኝ ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ህብረት ማድረግ የምንጀምረው  የልጅነት ተፈጥሯችንን በትክክል በመረዳት እና እንደ ልጅ በመመላለስ ነው።(ዮሐ 1:12) እኛ አማኞች የተቀበልነው የልጅነት መንፈስ እንጂ የባርነት መንፈስ አይደለም።

“አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።”
  — ሮሜ 8፥15


በልጅነትና በባርነት መንፈስ መካከል ሰፊ የሆነ ልዩነት አለ።

የባርነት መንፈስ ሰዎችን በክስና በወቀሳ የሚያጠቃ ሲሆን፤ ይህ የባርነት መንፈስ በክርስቶስ የተደረገውን የጽድቅ ስራ  ትተን በራሳችን ጽድቅ ላይ ለመቆም ስንፍጨረጨር
የሚያጠቃ ከፍተኛ የኩነኔ መንፈስ ነው።

የባርነት መንፈስ ደካማ እንደሆንህ፣ኃጢአተኛ እንደሆንህ፣ ማንም እንዳልሆንህ አምነህ እንድትቀበል ይሰብክሀል።የባርነት መንፈስ ከህግ ጋር አስሮህ ከፀጋ ጋር የሚያጣላህ
የራስ ጽድቅ (self righteousness) የሚያመጣው ውድቀትና የህሊና ወቀሳ ነው።

➢አማኞችን የሚያንኳስስ፣ዋጋ ቢስ አድርጎ የሚሰበኩ ስብከቶችና ትምህርቶች ብዙዎችን በባርነት መንፈስ አስሮ ይዟል።ነገር ግን የክርስቶስ ትምህርት ላይ የተመሰረተ ትምህርት ሲሰበክ የትኛውም አይነት ጨቋኝ እና በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘነውን ልጅነት የሚገዳደር ትምህርት ሁሉ ተረት መሆን ይጀምራል። በአዲስ ኪዳን አማኞችን የኩነኔ መንፈስ ውስጥ የሚከተው በራስ ፅድቅ ላይ ትኩረት ማድረግ መጀመር ነው። ነገር ግን አንድ አማኝ በክርስቶስ ኢየሱስ ፅድቅ ላይ መደገፍ ሲጀምር በውስጡ የክስ መዝገብ እያገላበጠ የሚከሰው ከሳሽ መረታት ይጀምራል። የአዕምሮ ክስም ይቆማል።

➢ሰው የኩነኔን  መንፈስ ሊያሸንፍ የሚችለው በክርስቶስ የጽድቅ ስራ አምኖ ልጅ ሲሆን እና ልጅነቱን በእውቀት ሲረዳው ብቻ ነው። የልጅነት መንፈስ ከአግዚአብሔር ጋር ህብረት ለማድረግ ዋና ቁልፍ ነው። ይህ የልጅነት መንፈስ አባ አባ ብለን የምንጮህብት መንፈስ ነው።

እንደ አማኝ በክርስቶስ የተቃኘ አዕምሮ ሊኖረን ያስፈልጋል። ይህ የሚሆነው ደግሞ አዕምሯችን በቃሉ ሲቃኝ ነው።

በክርስቶስ የተቃኘ አዕምሮ በቃሉ የተቃኘ  አዕምሮ ውጤት ነው።

➢ ስለ አዲሱ ማንነታችንና በመንፈሳዊ አለም ስላለን ስፍራ(POSITION) በቃሉ  ማወቅ፣ ማጥናትና ማሰላሰል ውጤቱ የምስጋናና የድል ህይወት ነው።ሐዋርያው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች ይፀልይ የነበረው አማኞች በክርስቶስ የተቃኘ እይታና አስተሳሰብ ይኖራቸው ዘንድ ነበር።(ኤፌ1:16፤ኤፌ 4)

➢ አንድ አማኝ ለመንፈሳዊ ህይወቱ ያለው ዋጋ እየጨመረ የሚመጣው በክርስቶስ ማንነቱን አጥብቆ ሲረዳ ነው።

➢በክርስትና ህይወታችን የአስተሳሰብ ቅኝታችን ውድ ዋጋ አለው።በክርስቶስ ትምህርት ያልተቃኘ አዕምሮ እንደ አማኝ በስልጣን እና በሙሉ ልብ መመላለስ ይሳነዋል።

➢ሁሉም አማኝ በክርስቶስ እኔ ማነኝ ብሎ እራሱን ሊጠይቅ ይገባል። መልሱን ደግሞ ቃሉን በማንበብና በማጥናት ውስጥ ያገኘዋል። 


ስለ እናንተ እያመሰገንሁ ስጸልይ ስለ እናንተ ማሳሰብን አልተውም፤  የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣች ሁ እለምናለሁ።ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤
  (ኤፌሶን1:16-17)

  መሳይ አለማየሁ(ነቢይ)

ክፍል አራት ይቀጥላል
       = እኔ በክርስቶስ ማነኝ? =
100 መፅሐፍ ቅዱሳዊ የአማኞች መታወቂያ

👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
            @KALTUBE
            @KALTUBE
            @KALTUBE

#KALTUBE

21 Oct, 16:08


በቅቤና በስብ


📖“ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥ ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ።”

           — መዝሙር 63፥5


ምድራችን እርካታን በሚሹ ሰዎች ተሞልታለች። የሰው ልጅ የረካን ሕይወት ለመኖር ስለሚፈልግ እጅግ የበዙ ነገሮችን ያደርጋል። አንዳንዶች እርካታን በትምሕርት ውስጥ የሚያገኙት ይመስላቸውና በምርምር ጊዜያቸውን ያጠፋሉ። ነገር ግን ያሰቡት ቦታ ሲደርሱ አገኘዋለሁ ብለው ያለሙትን እርካታ ከቦታው ያጡታል። ሌሎች ደግሞ የእርካታ ልካቸውን በገንዘብ ላይ ያደርጋሉ። ይህንንም ውጥናቸውን ከግብ ለማድረስ ሌት ተቀን ይደክማሉ። ኪስ በገንዘብ የሞለ ዕለት ግን የጠበቁትን አይነት እርካታን ያጡታል።


አንዳንዶች የእርካታ መሰረቴ ትዳር ነው ብለው ያስባሉ። የትዳር ፍሬ በሆኑት ልጆች መባረክ እርካታዬን ጣራ ያደርሰዋል በማለት ይናገራሉ። ያሰቡት ሁሉ በጊዜ ሂደት ቢሳካ እንኳን አገኘዋለሁ ያሉትን እርካታ ከቤታቸው ያጡታል።


የእርካታ አንፃራችን ምድራዊ ከሆኑ ዘላለም እንደ ረካን አንኖርም። እየቆየን ስንሄድ ያለንበትን ሁኔታ እንለምደውና የጓጓንለት ነገር በሙሉ ጣዕሙን ያጣል። የሕይወት ትርጉሜ ብለው ያሰብነው ህልም ዕውን መሆኑ እንብዛም አያስገርመንም።


የእርካታችን ልክ ግን እግዚአብሔር ከሆነ ሰርክ ደስታችን ነው። እርሱ ዛሬ ቀምሰነው ነገ ላይ የምንለምደው ሳይሆን ዘውትር በየማለዳው አዲስ ነው። የእርካታችን መሰረት እግዚአብሔር ሲሆን በእውነተኛ ደስታ እንባረካለን። ዳዊት ይናገራል፦ “ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥ ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ።” (መዝ 63፥5)


ወንድሜ፣ እርካታን በማጣት እየተቅበዘበዝክ ነውን? እህቴ፣ የረካን ሕይወት መኖር ናፍቆትሽ ነውን? እንግዲያውስ ወደዚህ አምላክ ቅረቡ። እርሱ በእውነተኛ እርካታ ሕይወታችንን ይጎበኘዋልና።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ እውነተኛ እርካታን ሰጪ ስለሆንክ አከብርሃለሁ። “ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ” በመንፈስህ የረካን ሕይወት አጥግበኝ። አሜን።

የህይወት ስንቅ ~ #BT
| KALTUBE
  "Daily Spiritual Feeding"
👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
            @KALTUBE
            @KALTUBE
            @KALTUBE

#KALTUBE

20 Oct, 15:05


በክርስቶስ  IN CHRIST

ክፍል-2
የእግዚአብሔር ቃል በክርስቶስ የተሰራልንን እና የሆነውን ማንነት በተመለከተ እንዲህ ይላል ;---
“ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው። አሮጌው አልፏል፣ አዲሱ መጥቷል!”  በ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17

“ስለዚህ” የሚለው ቃል በቁጥር 14-16 መሰረት  ሁሉም አማኞች ከክርስቶስ ጋር እንደሞቱ እና ከእንግዲህ ለራሳቸው እንደማይኖሩ ይነግረናል።

ሕይወታችን ከአሁን በኋላ ዓለማዊ ሳይሆን  መንፈሳዊ ነው።

'''አሮጌ የተባለው'' ከክርስቶስ ጋር
በመስቀል ላይ በምስማር የተቸነከረው የአሮጌው የኃጢአት ተፈጥሮ ነው።አሮጌው ሰው ከክርስቶስ ጋር ተቀብሯል፤ ክርስቶስ እርሱ ከአብ እንደተነሳ እኛም “በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ” (ሮሜ 6፡4) ተነስተናል።

👉 አዲሱን ፍጥረት ለመረዳት በመጀመሪያ ፍጥረት መሆኑን ማለትም በእግዚአብሔር የተፈጠረ መሆኑን መረዳት አለብን።
ዮሐንስ 1፡13 ላይ ይህ አዲስ ልደት በእግዚአብሔር ፈቃድ መፈጠሩን ይነግረናል። አዲሱ ተፈጥሮ ከወላጆቻችን የወረስነው ተፈጥሮ አይደለም።

በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ሲባል
NEW CREATURE
-BRAND NEW

ከዚህ ቀደም ያልነበረ አዲስ የእግዚአብሔር የፈጠራ ውጤት  ነው።
እግዚአብሔር አዲስ ፍጥረት ናችሁ ሲል ዝም ብሎ እንዲያው  አሮጌውን ተፈጥሮአችንን ጠጋግኖ፣አድሶ ባለበት ቀለም ቀብቶ፣መለስተኛ ማሻሻያ አድርጎበት ሳይሆን ሙሉ በሙሉ አዲስ እና ልዩ የሆነ ሰው እያለ ነው።ሃሌሉያ!!!

ማንም በክርስቶስ ቢሆን ሙሉ በሙሉ አዲስ ነው።ይህ ማለት ልክ አጽናፈ ዓለሙ በሙሉ በእግዚአብሔር  እንደተፈጠረ እንዲሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ያመነ ሰው አዲስ ፍጥረት ሆኖ ተፈጥሯል።

“አሮጌው ነገር አልፏል።

“አሮጌው” የሚያመለክተው የአሮጌው ተፈጥሮአችን አካል የሆኑትን ሁሉ ነው።
ይህም ኃጢአተኝነታችን ፣በደላችንን ሁሉ ማለት ነው። ቃሉ እንደሚለው አሮጌው ሰው ከኃጢአት ተፈጥሮ ጋር በመስቀል ላይ ተቸንክሯል። አሮጌው ባይቸነከር አዲሱ አይመጣም ነበር።

አሮጌው ፍጥረት ተሽሯል፣ከጨዋታ ውጪ እንዲሆን ተደርጓል። ከዚህ በኋላ የስጋ ስርአት ሳይሆን የመንፈስ ስርአት የበላይነቱን ተቆጣጥሯል። የመጀመርያው አዳም ሳይሆን ሁለተኛው አዳም(ክርስቶስ) ንጉስ የሆነለት ሌላ ሰው ተፈጥሯል። የሞቱ ነገሮች በአዲስ ነገር ተተክተዋል፣ በማይጠፋ ህይወት የተሞላ እና የእግዚአብሔር ክብር እለት እለት እያንፀባረቀ የሚኖር አዲስ ሰው በክርስቶስ ተፈብርኳል።

አዲሱ ፍጥረት በእግዚአብሔር ነገር ደስw የሚሰኝ፣ አላማው፣ ስሜቱና ፍላጎቱ የላይኛው የሆነ፣ ከነገድ፣ከቋንቋ፣ከዘር፣ከብሔር የተዋጀ፣በሰማይ ዜግነቱ ኮርቶ፣ተፈርቶ የሚኖር፣ ባንዲራው ኢየሱስ የሆነ የሰማይ ዲያስፖራ እና ለምድር እንግዳ የሆነ ሰው ነው።

“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።”
  — ራእይ 5፥9-10


ቃሉ ሲናገር  “አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር አስወግዳችኋል'' ይላል (ቆላስይስ 3፡9) ስለዚሀ “በእውነተኛ ጽድቅና ቅድስና እግዚአብሔርን ሊመስል የተፈጠረውን አዲሱን ሰውነታችንን እንለብሳለን” (ኤፌሶን 4፡24)።

👉ይህን እያነበብክ ሳለ ኃጢአት የሚሰሩ  ክርስቲያኖችሽ?እንዴት ነው ነገሩ  እያልክ ይሆናል......

አስቀድሞ አንድ ነገር ማወቅ ተገቢ ነው። በኃጢአት ፀንቶ መኖርና እና በኃጢአት መሳሳት  መካከል ልዩነት አለ።

አማኞች አዲሱን ማንነታቸውን አውቀው በዛ መረዳት( CONSCIOUSNESS)ሲመላለሱ
ኃጢአትን እየጠሉ ፅድቅን እየወደዱ ይመጣሉ።ደግነቱ አዲስ ፍጥረት የኃጢአት ባሪያ አለመሆኑ ነው። እኛ አማኞች ከኃጢአት ነፃ ወጥተናል ከዚህ በኋላ ኃጢአት በእኛ ላይ ህጋዊ የሆነ ስልጣን የለውም (ሮሜ 6፡6-7)።

በአሮጌው እና በአዲሱ ፍጥረት መካከል ፀብ አለ። አዲሱ የህይወት ስርዓት ከአሮጌው ስርአት ጋር ይቃረናል። አንድ አማኝ ኃጢአት ሲሰራ የሚወቀሰው ተፈጥሮው ስላልሆነ ነው።

አዲሱ የህይወት ስርአት የነፍሳችንን ክፍል(ስሜት፣ፈቃድ፣እውቀት) መቆጣጠር ሲጀምር አሮጌው አስተሳሰብ እየታደሰ ይመጣል። ሰው አዲስ ፍጥረት ሆኖ በአስተሳሰቡ ባለመታደሱና በቃሉ ባለመብሰሉ ምክንያት እንደ ህፃን ልጅ የኃጢአትን ጭቃ ሊያቦካ ይችላል። ነገር ግን የአንድ ህፃን ልጅ አይምሮ እየበሰለ ሲመጣ ጭቃ ማቡካት እንደሚያስጠላው ሁሉ  አስተሳሰቡ በቃሉ የተቃኘ አማኝም እንደዛው ነው።

መሳይ አለማየሁ (ነቢይ)

ክፍል ሶስት ይቀጥላል

በክርስቶስ የተቃኘ አስተሳሰብ

   👇💐👇💐👇💐👇💐
            @KALTUBE
            @KALTUBE
            @KALTUBE

#KALTUBE

18 Oct, 15:19


ባለጠግነት ቢበዛ
============================

📖“ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት፤ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኵራ።”

         — መዝሙር 62፥10


የአለማችን ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሀብት የሚገኘው ከጠቅላላው የህዝብ ቁጥር አንፃር 1% በሚሆኑት ሰዎች እጅ ላይ ነው። ይህ አሃዝ በሀብታምና በደሃ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ልዩነት ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በጣም ጥቂት ሰዎች በሀብት ላይ ሀብትን በማጋበስ ሲኖሩ እጅግ ሰፊው ማሕበረሰብ ግን እንዴት በልቶ ማደር እንደሚችል በማሰብ በሰቀቀን ያልቃል።


እግዚአብሔር ሀብትን ሲሰጠን ለሌሎች እንድንተርፍ ጭምርም ነው። ምን አልባት እነዛ 1% የሚሆኑት ሰዎች "ያለኝ ይበቃኛል" የሚልን መርህ ቢከተሉና የማካፈል ልምድ ቢኖራቸው የድህነትና የማጣት ችግር በጉልህ ሊቀረፍ ይችል ነበር። ነገር ግን ማካፈል እንደ ማጣት በሰፊው ህዝብ ዘንድ ስለሚቆጠር ይህን ማድረግ ቂል ያስብል ይሆናል።


ብዙውን ጊዜ የገንዘብ ምንነት ትርጉሙን ሲስት ይስተዋላል። ገንዘብ መገልገያ መሆኑ ቀርቶ በተቃራኒው አገልጋይ ከሆነ የጥፋት መንገዳችንን በገዛ እጃችን እያፈጠንን እንደሆነ ይቆጠራል። “ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥” (1ኛ ጢሞ 6፥10) ይሁዳ ጌታውን በባሪያ መልክ የሸጠው፣ የዬሴፍ ወንድሞች አካላቸውን ለባርነት አሳልፈው የሰጡት፣ ኤሳው ብኩርናውን ያቃለላት ጊዜያዊ ጥቅም አይናቸውን አሳውሮት ስለ ነበር ነው። ገንዘብን መውደድ ጌታን ያሸጣል። በንዋይ ፍቅር መነደፍ ቤተሰብን ይበትናል።


ለዚህ ነው ዳዊት እንዲህ በማለት ምክሩን የሚለግሰን፦ “ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት፤ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኵራ።” (መዝ 62፥10) ጌታችንም ተመሳሳይነት ያለውን ሀሳብ እንዲህ በማለት ገልፆታል፦ “ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው። ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ።” (ማቴ 19፥23-24) ወገኖቼ፣ በመጠን መኖርን እንለማመድ። “ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤” (1ኛ ጢሞ 6፥6) ተብሎ እንደ ተፃፈ የረካና የተረጋጋን ሕይወት እንምራ።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ምድርና ሞላዋ የአንተ ናቸውና አከብርሃለሁ። ከአንተ ይልቅ ደግሞ ገንዘብን በመውደድ እንዳልጠፋ ጠብቀኝ። አሜን።

የህይወት ስንቅ ~ #BT
| KALTUBE
  "Daily Spiritual Feeding"
👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
            @KALTUBE
            @KALTUBE
            @KALTUBE

#KALTUBE

16 Oct, 18:32


በክርስቶስ IN CHRIST

ክፍል 1

የእግዚአብሔርን ቃል ስናጠና
በገላቲያ 3:26-28 ላይ 
“በክርስቶስ” ለሚለው ሐረግ እና ምን ማለት እንደሆነ በቂ የሆነ መረዳትና መገለጥ ይሰጠናል።

ገላትያ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤
²⁷ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።
²⁸ አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።

ሐዋርያው ጳውሎስ በገላትያ ላሉ ክርስቲያኖች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት ካደረጉ በኋላ አዲሱን ማንነታቸውን በማሳሰብ እየተናገረ ነው።

"በክርስቶስ" መሆን ማለት ለእኛ ሲል የፍቅር መስዋዕት የሆነውን የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስን በማመን አዲስ ፍጥረት መሆን፣መፅደቅ፣መቀደስ፣የእግዚአብሔር ልጅ መሆን፣የንጉስ ካህን መሆን፣አሸናፊ መሆን፣ መቤዥት፣መወደድ፣መዳን እና የዘላለም ህይወት ተካፋይ መሆን ማለት ነው።

በክርስቶስ የሚለው ቃል በኢየሱስ የተደረገልንን ነገር ሁሉ የሚያጠቃልል ነው።

በ ሮሜ 3፡10-12 መጽሐፍ ቅዱስ በተፈጥሮ ኃጢአተኛ በአኗኗራችን የእግዚአብሔር ጠላቶች መሆናችንን ይናገራል። ነገር ግን እንዲያው በፀጋ እንደምንፀድቅ ደግሞ አበክሮ ይናገራል ።

ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ የተደረገለትን ካላወቀ እና አምኖ ካልተቀበለ ከህይወት ስታንዳርድ በታች ሆኖ እንደ ተራ ሰው ይመላለሳል።

በክርስቶስ ኢየሱስ የተደረገልንን እና በክርስቶስ የሆነውን ካላወቅን በጨለማ ውስጥ እንመላለሳለን። ይህን እውነታ ማወቅ በአሸናፊነት፣በልበ ሙሉነት እና በምስጋና  እንድንመላለስ ያሰችለናል።

ክርስቶስ ለሰራው ስራ ምላሽ ስንሰጥ፣ መንፈስቅዱስ ወደ እግዚአብሔር ቤተሰብ "ያጠምቀናል"። 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡13 "አይሁድ ብንሆን አሕዛብ ብንሆን ባሪያም ብንሆን ጨዋ ሰው ብንሆን አንድ አካል እንድንሆን ሁላችን በአንድ መንፈስ ተጠምቀናልና።"

በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያሉ በርካታ ቦታዎች የአማኙን “በክርስቶስ” የመሆናቸውን እውነታ ያመለክታሉ (1ኛ ጴጥሮስ 5፡14፤ ፊልጵስዩስ 1፡1፤ ሮሜ 8፡1)።

ቆላስይስ 3፡3 " ሞታችኋልና ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና።" ይላል።

እግዚአብሔር በአሰራሩ ፍፁም ነው። ኃጢያታችንን በቀላሉ ሊዘነጋው ​​ወይም ሰበብ ሊያደርገው አይችልም። የኃጢአት ዋጋ መከፈል ስለነበረበት እግዚአብሔር በክፋት ላይ ያለውን ቁጣ ሁሉ በገዛ ልጅ ላይ በማውረድ እኛን አስመልጦናል ፣አድኖናል።

ኢየሱስ በመስቀል ላይ የእኛን ቦታ ሲወስድ፣ ለኃጢአታችን የሚገባውን ቅጣት ሙሉ በሙሉ ወስዶልናል።

የተፈፀመውን መረዳትና ከተፈፀመው መጀመር.........

ጌታ ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት የተናገረው የመጨረሻው ቃል “ተፈጸመ”  (ዮሐ. 19፡30) የሚል ቃል ነበር።
ተፈፀመ የሚለው ቃል በግሪክ ( TETELESTAI ) ሲሆን ይህ ቃል በአብዛኛው ጥቅም ላይ ይውል የነበረው አንድን ትልቅ ገድል፣ተግባር ወይም ተልዕኮ የፈፀመ ሰው በድል ሲያጠናቅቅ ቴቴሌስታይ TETELESTAI ወይም ተፈፀመ IT IS FINISHED ይላል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ተፈፀመ ሲል የተፈፀመው የምድራዊ ሕይወቱ ብቻ አልነበረም። ከሦስት ቀን በኋላ እንዳረጋገጠው በመስቀል ላይ ሆኖ ተፈፀመ ያለው  እግዚአብሔር የወደቀውን አለም ለመቤዠት ያለውን እቅድ በተመለከተ ነው።
(ማቴ 28፡7፤ ማር. 16፡6፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡6)።

ኢየሱስ፣ “ተፈጸመ” ሲል እያንዳንዱን የአመጽ ድርጊት፣ ያለፈውን፣ የአሁኑን እና የወደፊቱን ሙሉ በሙሉ እንደከፈለ እየተናገረ ነው።

በክርስቶስ የመዳን ስራ ተጠናቋል።ይህ ማለት ለመዳን ኢየሱስ አስፈላጊውን ስራ ሁሉ ፈፅሟል ማለት ነው።
ክርስትና የሚጀምረው ከተጠናቀቀው የኢየሱስ ክርስቶስ ስራ እንጂ ከእኛ ጥረትና ልፋት አይደለም።

በዚህ ተከታታይ ትምህርት ከተጠናቀቀው የኢየሱስ የማዳን ስራ ተነስተን የጉዞ አቅጣጫችንን ወደ ፍፁም ሙላት በማድረግ ለህይወት የሚሆን ትምህርት እንማራለን።

✍️ነቢይ መሳይ አለማየሁ
            @KALTUBE
            @KALTUBE
            @KALTUBE

#KALTUBE

16 Oct, 18:30


     @KALTUBE
            @KALTUBE
            @KALTUBE

#KALTUBE

16 Oct, 16:08


Blog ➥ከትዳር በፊት ማወቅ ያሉብኝ ነገሮች

በሀና ኤልያስ #ክፍል-3

በእግዚአብሄር ፈቃድ አግብተው፣ በብዙ የአገልግሎት ፍሬ የተባረኩ፣ ትክክለኛ ጥሪያቸውን ያወቁና በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል እርዳታ ያገኙ ሰዎችንና የትዳር ምሳሌዎችን አውቃለሁ። በአንፃሩ ደግሞ፣ ለትውልድ ሊተርፍ የሚችል የከበረ ሀብታቸውን በትዳር ምክኒያት የጣሉ ሰዎችንም እንዲሁ አውቃለሁ። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ፥ ከማግባታቸው በፊት፥ አላማ ስለሚባለው ነገር ምንም መረዳት ባይኖራቸውም፥ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በመጠየቅና በእርሱ ፈቃድ በመመራት ካገቡ በሁዋላ “ይሄ ሰው ነበር ህይወቴ ላይ የሚያስፈልገኝ” ሲሉ እንሰማቸዋለን። ዋናው ወገኖቼ፥ ማግባት አይደለም። የእግዚአብሄር ሀሳብ ያለበት ህይወት ውስጥ መግባት ነው። ዋናው፥ ሊያገባን የሚችልን አንድ የሆነን ሰው ማግኘት አይደለም። እግዚአብሄር ለህይወታችን ትክክለኛ ረዳት ካለው ሰው ጋር መገናኘት ነው......... .....


➥  ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

#KALTUBE

15 Oct, 17:30


Blog Monday ➥ከትዳር በፊት ማወቅ ያሉብኝ ነገሮች

በሀና ኤልያስ #ክፍል-2

ይሄንን ትልቅ የሆነውን የትዳር አላማ ስንረዳ ታዲያ፣ አመለካከቶቻችንና ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች መለወጥ ይጀምራሉ። ለትዳር የምንፈልገውን ሰው የምንመርጥበት መስፈርት ከመልክ፥ ከገንዘብና ከመሳሰሉት ነገሮች ያልፍና፥ ይሄ ሰው ውስጤ የተቀመጠውን የእግዚአብሄርን ሀሳብ ወይንም ከእግዚአብሄር የተሰጠኝን ስራ በትክክል ለመስራት ይረዳኛል? ወደሚለው ዋና ጥያቄ ውስጥ እንገባለን። ይሄንን ለማለት ታዲያ ከማግባታችን በፊት ማወቅ ያለብን ዋናው ነገር ከእግዚአብሄር የተሰጠንን ስራ ነው። አላማችንን ነው መጀመሪያ ማወቅ ያለብን። እግዚአብሄር በክርስቶስ ኢየሱስ የፈጠረንና አዲስ ፍጥረት የሆነው እግዚአብሄር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን ስራ ለመስራት እንደሆነና ይሄ ለእያንዳንዳችን የተሰጠንን የግል ሀላፊነት ነው መጀመሪያ ማወቅ ያለብን። ከዘላለም አንፃር ስናያት ነጥብ የምታክለው ይህቺ በጣም አጭር የምድር ቆይታ የተሰጠችን፥ እንድንሰራባት ነው......... .....


➥  ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

#KALTUBE

15 Oct, 10:28


Blog Monday ➥ከትዳር በፊት ማወቅ ያሉብኝ ነገሮች

በሀና ኤልያስ #ክፍል-1

ዛሬ በጣም ደክሞኛል። ምን የመሰለ ሰርግ ላይ ውዬ አሁን ቅርብ ጊዜ ነው ወደ ቤቴ የገባሁት። አቤት ሙሽሮቹ እንዴት እንደሚያምሩ! ሚዜዎቹስ ብትሉ፥ የቃልኪዳን ስነስርዓቱ፣ የሰርጉ አዳራሽ ደግሞ ማማሩ! አምልኮውንማ አጠይቁኝ፥ በጣም ቀውጢ ነበር። እስኪያልበን ድረስ መዝለላችን፥ አምልኮ የሚለውን ቃል ባይተካውም፥ ያው እየዘለልን ዘምረናል። ምናለበት ግን የእሁድ እሁድ የቤተክርስቲያን አምልኮአችንም እንዲህ ቢመስል! ማለት፥ ተፈቶ ሲያመልክ አይተነው የማናውቀው ሰው ሁሉ ሰርግ ላይ ሲፈታ እናየዋለን። ይሄን ባህል ግን ከአህዛብ ሰርግ ይሆን እንዴ የወረስነው? ሰርጌ ላይ በደምብ አልጨፈሩም እንዳንባል ይሆን የምንጨፍረው? እኛ ክርስቲያኖች ግን ከዚህ ፍርሀት ነፃ ሆነን ነው ማምለክ ያለብን። መዝለልና መጨፈራችን ምንም ክፋት ባይኖረውም፥ እግዚአብሄር ስላደረገልን ነገር ወይንም በውስጣችን ስለ ፈሰሰው የመንፈስ ቅዱስ ደስታ እንጂ፥ ሰውን የሚለንን ፈርተን መሆን የለበትም። ብቻ ግን በአጠቃላይ ሰርጉን ወድጄዋለሁ። ሁኔታው ሁሉ ደስ ይል ነበር።

የሰርጉን ስርዓት ካጠናቀኩኝ በሁዋላ፥ ወደ ቤቴ እየተመለስኩ፥ ልዩ በሆነ ፀጥታና፥ በሚገርም ተመስጦ ውስጥ ነበርኩ። ስለ ሰርጉ ሁኔታ እያሰብኩ፥ አንድ ጥያቄ እየደጋገመ ወደ ሀሳቤ ይመጣ ነበር። እነዚህ የሚያምሩ ወንድና ሴት ሙሽሮች ግን በአላማ ይሆን የተገናኙት? እኛማ እግዚአብሄር ይስጣቸው በእነሱ ወጪ በልተን ጠጥተን፥ ጨፍረን ወደየቤቶቻችን ሄደናል። ሰርግ ግን ዋናው የአብሮነት ህይወት አንድ ተብሎ የሚጀመርበት የመጀመሪያ ቀን እንጂ ትዳር ማለት አይደለም። በተለይ እኛ ሴቶችማ በጣም የሚከብደን ነገር ቢኖር፥ ሰርግና ትዳርን .....


➥  ሙሉ ለማንበብ  👉  ይጫኑ

#KALTUBE

14 Oct, 18:46


💐ምንም የጥያቄ ገደብ የሌለውን Ai ቦታችንን KAL AI ማንኛውም መንፈሳዊ ጥያቄና መፅሐፍቅዱስ ውስጥ ያልተረዳችሁትን ክፍሎች እንዲያብራራ መጠየቅ ትችላላችሁ።

ለምሳሌ የሮሜ መፅሐፍ ምዕራፍ 12 በስፋት እንዲብራራላችሁ
Explain in detail about apostle paul letter to romans chapter 12
በማለት መጠየቅ።

ይሄን በመጫን Start ብላችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇👇
@Kaltube_aibot
@Kaltube_aibot
@Kaltube_aibot

#KALTUBE

14 Oct, 13:10


https://youtu.be/LKqMjhTcui8?si=zazNYpFUxwAeikMd

#KALTUBE

13 Oct, 16:36


ይሄ ቦት በቃልቲዩብ የተዘጋጀ ማንኛውንም መንፈሳዊና መፅሐፍቅዱሳዊ ጥያቄዎቻችሁን የሚመልስ በ Artificial Intelligence የተሰራ ነው። Start በማለት ጥያቄያችሁን በ እንግሊዝኛ ብቻ ይፃፉ። በተጨማሪም በቀን ውስጥ ለጥያቄ ምንም ገደብ የሌለው ነው። መንፈሳዊ ያልሆኑ ጥያቄዎችን አይቀበልም።
👇👇👇👇👇

@Kaltube_aibot
@Kaltube_aibot
@Kaltube_aibot

#KALTUBE

13 Oct, 15:45


@Kaltube_aibot

#KALTUBE

10 Oct, 18:25


#New #Album #Lealem_Tilahun

መዝሙር ንብረትነቱ የዘማሪው ነው ብዬ አላስብም:: መዝሙር ምንጩ ጌታ ራሱ ቢሆንም ንብረትነቱ ደግሞ የእግዚአብሔር ህዝብ ነው ብዬ አምናለሁ::

መዝሙራችሁን በዚህ ደረጃ በማዘግየቴ ቅዱሳኑ ሆይ ይቅርታ እየጠየቅሁ ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ዓመቱ በገባ በ2ኛው ወር አዲስ ሰንዱቅ ወደ እናንተ ለማድረስ ዝግጅት ላይ እገኛለሁና በፀሎታችሁ ልታሰብ::ተባረኩልኝ!!

@KALTUBE

#KALTUBE

10 Oct, 04:34


💐ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና


📖“ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።”

          መዝሙር 62፥5


ሕይወትን ጣፋጭና ተወዳጅ ከሚያደርጓት ነገሮች አንዱ ተስፋ ነው።  ተስፋ የሌለው ሕይወት ካለመኖር ተለይቶ ሊታይ አይችልም። ይህ ተስፋ አሁናዊ ጨለማችን ነገ ላይ በታላቅ ብርሃን እንደሚለወጥ ለውስጣችን ይነግረዋል። ከዛሬ ነገ የተሻለ እንደሚሆንም ያረጋግጥልናል።


ብዙዎች በተለያዩ ነገሮች ላይ ልባቸውን በመጣል ተስፋ ያደርጋሉ። አንዳንዶች ተስፋቸውን ቁሳዊ ነገር ላይ ይተክሉትና ተስፋ ያደረኩት ነገር አልሆን ሲል ለታላቅ የልብ ስብራት ይዳረጋሉ። ሌሎች ደግሞ "ለእኔ ያለሁት እኔው ራሴ ነኝ" በማለት ራሳቸውን ብቻ ታምነው ተስፋ ያደርጋሉ። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉን ቻይ አይደለምና ያሰቡት ነገር በሙሉ ከመሬት ላይደርስ ይችላል። ታዲያ በዚህን ጊዜ "እኔ ምንም ነገር ማድረግ አልችልም በቃ" በማለት ራሳቸውን ከባድ ጭንቀት ውስጥ ይከትቱታል።


ዳዊት ለነፍሱ እንዲህ ይላታል፦ “ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።” (መዝ 62፥5) እውነተኛውና ዘላቂነት ያለው ተስፋ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው። ማን ነው እርሱን ተስፋ አድርጎ አውላላ ሜዳ ላይ የቀረው? ማንስ ነው በሀዘን ዓይኖቹ የፈዘዘው? ማንም! ስለዚህ ተስፋችንን ከእግዚአብሔር ጋር እናቆራኘው። እርሱ ለተስፋ ቃሉ ታማኝ ነውና።


🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ተስፋዬ ስለሆንክ አከብርሃለሁ። “ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።” አሜን።


የህይወት ስንቅ ~ #BT
| KALTUBE
  "Daily Spiritual Feeding"
👇💐👇💐👇💐👇💐👇💐
            @KALTUBE
            @KALTUBE
            @KALTUBE

#KALTUBE

06 Oct, 06:03


https://youtu.be/eanrBcBFOBk?si=zobmrKcMwoIlLAcU

#KALTUBE

05 Oct, 06:24


Full Album Playlist Aster Abebe

https://youtube.com/playlist?list=PLKNx68410nPXKxLqRbQ5FWHte-cOCN1Lg&si=5N4U74j1eFUW3iBq

#KALTUBE

04 Oct, 17:49


Aster Abebe