Ethio Scholars Info

@ethio_lecturers


Scholarships, call for papers, grants, projects, job vacancies, etc

For any comment @ethiolbot

Ethio Scholars Info

21 Oct, 10:53


የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ባለ 14 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጣ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከጥቅምት 7-9/2017 ዓ.ም ድረስ በአዳማ ከተማ ሲያካሄድ የነበረውን 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን ባለ 14 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ።

👉1. መምህራንን እየተፈታተነ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣

👉2. ረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ እድገት ወይም የእርከን ጭማሪ አለመኖር፣

👉3. በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል፣

👉4. ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደሞዝ መቆረጥ፤ ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት፣

👉5. ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ ያለመሆን

👉6. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የቤት አቅርቦት ጭራሽ አለመጀመሩ፣

👉7. በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣

👉8. የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት፣

👉9. የክረምት መምህራን ስልጠናና ያጋጠሙ ችግሮች እና ሌሎችም ይገኙበታል

በቀረቡት ጥያቄዎች ዙሪያ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚንስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ኮራ ጡሹነ እና በት/ት ሚንስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራሮች ዴስክን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከመምህራን ጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ እየታየ ያለው ጥያቄ የተጀመረው የትምህርት ሴክተር ሪፎርም ተጠናቆ ተግባራዊ ሲሆን ብዙ ጉዳዮች እንደሚፈቱ ገልፀዋል። #አዩዘሀበሻ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethio Scholars Info

19 Oct, 19:09


ይህንን በመፃፌ ተቃዋሚ ብሎ የሚፈርጀኝ ካለ go-ahead

በ [ዳግማዊ ታሪኩ ]

ዛሬ በቀረበውን የሚኒስትሮች ምክርቤት የ100 ቀን ግምገማ ላይ ሚኒስትሮቹ የሚናገሩትን ሰምቼ ዝም ብዬ ላልፈው አልቻልኩም።

በሀገራችን ያለው የኑሮ ውድነት ብዙዋች መኖር የማይችሉበት ደረጃ እንዳደረሳቸው ለመረዳት ከባድ አይደለም።ህዝቡ ኑሮ ከብዶታል ይህንን ከቤተሰብ ከጓደኛ ወዳጅ ዘመድ በየእለቱ የምንሰማው በየሶሻል ሚዲያው የምናየው ነው።ጥቂት እጅግ በጣም ሀብታም የሆኑ ሰዋች ተፈጥረዋል በፖለቲካው አመራርነት ያሉ ችግሩ የማይነካቸው አሉ የተቀረው ህዝብ ግን ኑሮው ፈታኝ ሆኖበታል።

ሚኒስትሮቹ በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ የሚደመጠው ግን ነገር ሁሉ አልጋ በአልጋ እንደሆነ ነው።ችግርን የመስማትና የማስማት የማደናነቅ ሱስ የለብኝም ሆኖም ግን የህዝቡን የእለት ተእለት ኑሮ ተረድቶ ችግሩ መኖሩን ተቀብሎ ለመለወጥ የማይነሳ አመራር ባለበት ሀገርን መለወጥ አይታሰብም።አሁን የምናየው እጦት ከዚህ ቀደም መሀከለኛ ኑሮ ሊባል የሚችል ቦታ ላይ የነበሩትን ከድህነት ወለል በታች ያደረገ ነው።

ችግር መኖሩን መረዳት ተረድቶ ለለውጥ መነሳት የመፍትሄው ግማሽ መንገድ መሄድ  ነው።ችግር አለ ስር የሰደደ ድህነትና ማጣት ተንሰራፍቷል ለውጥ ማምጣት የሚቻለው እውነታውን መቀበል ሲቻል ነው።

የሚገርመው ችግሩ ብሄር ይሁን አካባቢ አይለይም ያለልዩነት
ብዙው ህዝባችን ተጎሳቁሏል።በሌላ በኩል ደግሞ ከየቦታው የተጠራሩ ጥቂት ብልጣብልጦችና የፖለቲካ ነጋዴዋች ህዝቡን አፍነው ይዘው ለራሳቸው "ጥሩ " ይኖራሉ።ይህ ግን ረጅም ርቀት አይሄድም ።

በለፀጉ በሚባሉ ሀገራትም ልናነፃፅረው ባንችልም ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አሉ።የሚለየን ግን በበለፀጉ ሀገራት ተግዳሮቶቹ በሚዲያ ይሁን በሌሎች መንገዶች ውይይት ይደረግባቸዋል ፖለቲከኞች ለህዝብ ቅርብ ናቸው ከአካባቢ ተመራጮች ጀምሮ እስከከፍተኞቹ ወርደው ይሰማሉ በውሸት ሪፖርት መሸፋፈን አይታሰብም።
[ዳግማዊ ታሪኩ ]

Ethio Scholars Info

19 Oct, 12:53


https://www.youtube.com/watch?v=__E1CH2ir6Y

Ethio Scholars Info

19 Oct, 10:28


Bold Visions ET is a non-profit program which focuses on helping Ethiopian students in their application process to various US universities, our main services include:
📌 As an international students emerging from Ethiopia, We understand how hard it is to access most of the information needed in the application process. So we will try our best to reduce such challenges for you by providing well-researched, accurate, and updated information, which we have acquired through deep and detailed research done by our Team members.
📌 More than that, we will be able to provide you with reliable and useful resources to help you achieve good results on your SAT test.
📌 We offer regular voice meetings to address your queries.
📍Join our channel for updates and share with friends planning to study abroad.
https://t.me/Bold_visions

Ethio Scholars Info

17 Oct, 11:14


" በአለም አቀፍ ደረጃ 1.1 ቢሊዮን ሰዎች በአስከፊ ድህነት ውስጥ ይገኛሉ  " - ተመድ

° ኢትዮጵያን ጨምሮ 5 አገራት ግማሽ ያህሉን ደሀ ዜጎች ይዘዋል

° የድህነት መጠን በጦርነት ውስጥ ባሉ አገሮች በሦስት እጥፍ ከፍ ያለ ነው


በዓለም ከ1 ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በአስከፊ ድህነት እንደሚኖሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ባወጣው አዲስ ሪፖርት አመለከተ። ተመድ ከተጎጂዎቹ መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ህጻናት ናቸው ብሏል።

በኦክስፎርድ የድህነት እና የሰብአዊ ልማት ኢኒሼቲቭ (OPHI) ላይ የወጣው ይህ ሪፖርት እንዳመለከተው ህንድ በከፋ ድህነት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ያላት ሀገር ስትሆን ካላት ከ1.4 ቢሊዮን ህዝብ 234 ሚሊዮን ያህሉ ደሆች ናቸው።

አምስቱ ሀገራት ማለትም ህንድ፣ ፓኪስታን፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከ1.1 ቢሊዮን ድሆች መካከል ግማሽ ያህሉን እንደሚሸፍኑ ይህ የ2024 የአለም ሁለገብ የድህነት መረጃ ጠቋሚ (MPI) ሪፖርት አመልክቷል።

በድህነት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አምስት አገሮች ሕንድ (234 ሚሊዮን) ፓኪስታን (93 ሚሊዮን) ፣ ኢትዮጵያ (86 ሚሊዮን) ፣ ናይጄሪያ (74 ሚሊዮን) እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ  ኮንጎ (66 ሚሊዮን) ናቸው።

በ2023 ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በዓለም ላይ ከፍተኛ ግጭቶች የታዩበት መሆኑ ሲገለፅ የድህነት መጠን በጦርነት ውስጥ ባሉ አገሮች በሦስት እጥፍ ከፍ ያለ መሆኑን ተመላክቷል።

የተመድ የእድገት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) እና የኦክስፎርድ የድህነት እና የሰብአዊ ልማት ኢኒሼቲቭ (OPHI) ከ2010 ጀምሮ ሁለገብ የድህነት ምዝባ (ኢንዴክስ) በየአመቱ 6.3 ቢሊየን ህዝብ ካላቸው 112 ሀገራት መረጃ እየሰበሰቡ እንደነበር ተገልጿል።

በዚህም ሪፖርቱ የመኖሪያ ቤት እጥረት፣ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና፣ የኤሌክትሪክ አቅርቦት፣ የምግብ ማገዶ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና የትምህርት ቤት ክትትልን የመሳሰሉትን መስፈርቶች እንደ ድህነት አመላካቾች ተጠቅሟል።

በዚህም 1.1 ቢሊዮን ህዝብ ዘርፈ ብዙ ድህነትን ውስጥ እየኖረ ሲሆን፣ ከነዚህም 455 ሚሊዮን የሚሆኑት በግጭት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው።

የዩኤንዲፒ ዋና የስታቲስቲክስ ባለሙያ ያንቹን ዣንግ " በግጭት በተጠቁ አገሮች ውስጥ ያሉ ድሆች፣ ለመሠረታዊ ፍላጎቶቻቸው የሚያደርጉት ትግል እጅግ የከፋ እና ተስፋ አስቆራጭ ነው " በማለት ተናግረዋል።

ሪፖርቱ ከ18 አመት በታች የሆኑ 584 ሚልዮን ሰዎች ለከፋ ድህነት የተዳረጉ መሆኑን ጨምሮ ያሳየ ሲሆን ከነዚህም 27.9 በመቶ ህጻናት ናቸው። አዋቂዎቹ ደግሞ 13.5 በመቶ እንደሆኑ ተመላክቷል።

በተጨማሪም 83.2 በመቶው የዓለማችን ድሆች ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ እና ደቡብ እስያ እንደሚኖሩም ነው የተገለፀው።

tikvaheth

Ethio Scholars Info

17 Oct, 10:18


" ኑሮን መቋቋም አቃተን ! " - ሰራተኞች

በተለይ በተለይ አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነታቸውን ያደረጉና ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ በተለያዩ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ኑሮን መቋቋም ፈተና እንደሆነባቸው ገልጸዋል።

ቃላቸውን ከሰጡት ውስጥ የልጆች እናት መሆናቸውን የገለጹ አንዲት እናት " መሃል ከተማ ያለውን የማይቀመስ የቤት ኪራይ ሽሽት ከከተማ ጥግ ብገባም በየጊዜው በእያንዳንዱ ነገር ላይ በሚታየው ጭማሪ ኑሮን መቋቋም አልቻልኩም " ብለዋል።

" እኔ የዛሬ አመት ይከፈለኝ የነበረ ደመወዝ ዛሬም እዛው ነው ትምህርት ቤት፣ የምግብ ግብዓት፣ አልባሳት፣ ትራንስፖርት ሌሎችም ነገሮች ጨምረዋል ፤ ነገር ሁሉ ነው ግራ ያጋባኝ " ሲሉ በሃዘን ስሜት ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።

ሌላኛዋ ወጣት በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ የምትሰራ ፥ " ከተመረቅኩ ይኸው 5 ዓመቴ ነው ፤ ደህና ደመወዝ የለኝም። የምሰራው ቀን ሙሉ ነው ደመወዜ እዛው ሆኖ ያልጨመረ ነገር የለም " ብላለች።

" ቤት ኪራይ ብቻዬን መክፈል ስለማልችል ከጓደኛዬ ጋር ነው የምኖረው ፤ እንደዛም ሆኖ የወር ጊቢዬን ምኑን ከምን እንደማደረገው አላውቅም ይኸው ልክ እንደ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ አንዳንዴ ቤተሰቦቼ ገንዘብ ይልኩልኛል ፤ ሁኔታዎች እንዲህ ከሆኑ እዛው ቤተሰቤ ጋር ሄጅ ሻይ ቡናም ቢሆን እየሰራው ብኖር ይሻለኛል " ስትል ተናግራለች።

ሌላ ቃላቸውን የሰጡ አንድ አባት ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየአገልግሎቱ ላይ የሚታዩት ጭማሪዎች እሳቸውና ሌሎችም ሰራተኛ ዜጎች ቼይ ከፍተኛ ጫና እንደሚያሳድር ገልጸዋል።

" አንዳንድ የመንግሥት ተቋማት ሳይቀሩ ለአገልግሎት የሚያስከፍሉትን ጭማሪ አድርገዋል ፤ ትራንስፖርት ዋጋው ጨምሯል እኔም ሆንኩኝ ሌላው ሰራተኛ ወርሃዊ ደመወዙ እዚህ ግባ የማይባል ነው ፤ ታዲያ ኑሮ የሚኖረው  ፤ ልጆችን ማሳደግ የሚቻለው እንዴት ነው ? " ሰሉ ጠይቀዋል።

አዲስ አበባ ከተማ በርካታ ዜጎች የሚኖሩባት ሲሆን የቤት ኪራይ ዋጋ የማይቀመስባት በመሆኑ በርካቶች ከሚሰሩበት ርቀው ከከተማ ዳር ዳር ተከራይተው ለመኖር ይገደዳሉ።

በርካቶች ጥዋት ማታ ለፍተው ተንከራተው የሚያገኙት ገቢም እዚህ ግባ የማይባል ፤ ያሰቡትን ለማሳካት ይቅርና ኑሮን ለመግፋት የማያስችል ነው።

በተለይ ወርሃዊ ደመወዝ የሚያገኙ ዜጎች በኑሮ ውድነቱ እጅግ በጣም ነው የሚፈተኑት።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ወጣቶች በክልል ከተሞች ያለው ብሔር እየመረጡ ፣ በትውውቅ በሙስና ሰዎችን ስራ መቅጠር ፣  አስተማማኝ የሆነ ሰላምና ደህንነት ሁኔታ አለመኖር ፣ ብዙ ድርጅት እና ተቋማት አለመኖር ፣ የሰፋ የስራ እድል አለመኖር ፣ በአንዳንድ ከተሞችም ያለውን እንቅስቃሴ እጅጉን መዳከም ሳቢያ በአንጻራዊነት አዲስ አበባን ለኑሮና ስራ እንዲመርጧት እንዳደረጋቸው ጠቁመዋል።

Credit: Tikvah Ethiopia

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethio Scholars Info

08 Oct, 08:11


ማስተርስ እና ዶክትሬት የሚማሩ ተማሪዎች ጉዳይ በራሱ ከሌሎች የትምህርት አጀንዳዎች ወጣ ብሎ መታየት አለበት

በደንብ ቢታሰብበት፣ የተማሪዎችን እንግልት መቀነስ ይቻላል

ለምሳሌ የሀገራችን ባንኮች እና ፋይናንስ ተቋማት ቢሳተፉ፣ ሌላው አለም የብዙ አመት ልምድ አለ።

ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ተለይቶ ሰዎችን የሚያሰቃይ አሰራር ለምን ይኖረናል ?

አንድ የPhD ተማሪ ትምህርት እና ምርምር ለመጨረስ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከባንክ መበደር ይችላል ?

ሌሎች ሀገሮች ብዙ የተለየ ዘዴ ይጠቀሳሉ፣ ሀገራችን ከሌሎች ሀገሮች የተለየ የሚሆነው ለምንድን ነው?

የፋይናንስ ተቋማት የመጀመሪያው የመፍትሔ ባለቤቶች ናቸው

Fikadu Reta Alemayehu

Ethio Scholars Info

08 Oct, 07:25


PhD ትምህርቱን ጨርሶ Congratulations ብለን ሳናበቃ በ10,000 ብር ደሞዝም ቢሆን ሥራ ፈልግልኝ አለኝ

ትምህርት መማር የዓለምን ምስጢር ማወቂያ እና የችግር መፍቻ መንገድ እንጂ በራሱ ግብ አይደለም:: ችግር የማይፈታ፣ በገበያው የማይፈለግ ትምህርት መማር ጥቅም የለውም። በዚህ ዘመን Lotus 1-2-3 የሚባለውን የSpreadsheet application program ማን ለምን ይማራል? የመማር ግቡ የእውቀትን ዳር ድንበር ማስፋት እና ችግር መፍታት ነው። ትልቅ ደሞዝ አስቦ PhD የሚማር ሰው ቀልፉን ጨለማ ውስጥ ጥሎ መብራት ላይ አገኘዋለሁ ብሎ የሚለፋውን ሰው ይመስለኛል።

እየራበው ንብን ምን ያስደንሳታል? ብሎ የሚመራመረው ሰውዬ ከዚያ በፊት ንብ እንዴት እንምትረባ እና ማር እንዴት እንደሚቆረጥ ቢያውቅና ንብ አርብቶ ማር ቢበላ ይሻለዋል።

የጃፓኖቹ ikigai የህይወት መስመርህን ስትመርጥ 4 ነገሮችን ማሟላቱን ልብ በል ይላሉ።
1) ሥራውን መውደድህን
2) ሥራህ በሌሎች መፈለጉን
3) ሥራውን መቻልህን
4) ለሥራው በቂ ክፍያ የሚከፈልህ መሆኑን

አውቀህ ብትሠራ ለህይወትህ ጥሩ ነው ይላሉ። አብዛኛው የPhD ተማሪ በሌሎች የማይፈለግ ምርምርን፣ በቂ ክፍያ ሳይከፈለው ይማረዋል። እናም በዚያ ላይ ይበሳጭበታል ወይም ቅር ይለዋል። ያ ደግሞ አይወደውም ማለት ነው። ስለሚችለው ነው እንዳይባል ገና እየተማረው ነው። እና ለምን PhD ይማራል? ግራ የገባ ነገር እኮ ነው።

እኔ ወደፊት ጊዜ ሳገኝና ሩጫ ስጨርስ በPhD ደረጃ ምርምር ሠራበታለሁ የምለው ሃሳብ አለኝ። ያኔ ተረጋግቼ የምሠራው በማኔጅመንት ዘርፍ አንድ የአሠራር ሞዴል ለማውጣትና በሌሎች ለማስተቸት ነው እንጂ ልቀጠርበት አይደለም። እስከዚያ Practice እያደረግሁ መረጃ እየያዝኩበት ነው። አንድ የማውቀው ትልቅ ሰው የዛሬ ሁለት ዓመት የPhD ትምህርቱን ጨርሶ Congratulations ብለን ሳናበቃ በ10,000 ብር ደሞዝም ቢሆን ሥራ ፈልግልኝ ሲለኝ የፈጠረብኝ ግርምት ዛሬም ድረስ አለ። ለምን ተማረ? የሁልጊዜ ጥያቄዬ ነው።

አንዱ ልጄ ኮሌጅ ገብቶ፣ ተፈትኖ የአርክቴክቸር ትምህርትን ጀምሮ "አልጣመኝም" ብሎ እንዳቋርጠው ፍቀድልኝና በቀጣዩ ዓመት ሌላ ትምህርት ልማር አለ። ልጁ ትምህርቱን ቢችለውም ሊማረው ደስታ አጣበት እናም እንዲያቋርጥ ፈቀድኩለት። አሁን ሌላ ትምህርት ሊጀምር ዝግጅቱን ጨርሶ እየተጠባበቀ ነው።
መማር በደስታ፣ በፍላጎት ሲሆን ጥሩ ነው። መማር በራሱ ግብ አይደለም። Basic ትምህርት እንኳ በራሱ ግብ አይደለም። ማንበብ፣ መጻፍ፣ ስሌት መስራት እና በምክንያት እና ውጤት ተዛምዶ ስልት ማሰብ እንዲያስችል ነው።

Eng. Getu K.

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethio Scholars Info

08 Oct, 06:05


መምህራን የሚገባቸውን ጥቅምና ክብር እየተሰጣቸው ባለመሆኑ ሀገር እየተጎዳች ነው - ዶክተር ዮሃንስ በንቲ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሃንስ በንቲ ወደ መምህርነት ሙያ የሚቀላቀሉት ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ በመምጣቱ ወደፊት የመምህራን እጥረት ሊኖር ይችላልም ብለዋል። ወደ ሙያው የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ገልፀው፣ ችግሩ እልባት ማግኘት እንዳለበት ተናግረዋል። ከትምህርት ጥራት እና ከመምህራን ጥቅማጥቅሞችና ጥያቄዎች አንፃር ለረጅም ጊዜ ቅሬታዎች ሲነሱ ነበር ብለዋል።

ቢያንስ የመምህራን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት በትምህርት ጥራት ላይ የሚኖረውን ተፅእኖ ይቀንሳል ብለዋል። የመምህራን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ከ50 ዓመታት በላይ በመምህራን ሲቀርብ የቆየ መሆኑን ገልፀው፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተወሰነ ምላሽ ማግኘት ቢጀምረም አሁንም የመምህራን ከባድ ችግርና ፈተና መሆኑን ተናግረዋል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የዋጋ ግሽበት ቀድሞውኑ የነበረውን የመምህራን የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ይበልጥ አባብሶታል ብለዋል። የመምህራን የጥቅማጥቅሞች፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ የደረጃ እድገት ደረጃዎች፣ የስልጠና፣ የደመወዝ ጭማሪ እና የወር ደሞዝ መዘግየትን ጨምሮ ለሌሎች ችግሮች የተጋለጡ በመሆኑ እየታገሉ እንደሆነ ገልፀዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethio Scholars Info

04 Oct, 16:06


የ2ኛ ዲግሪ የሌላቸው ከ300 በላይ መምህራን በዚህ አመት ማስተማር አይችሉም - የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከተቀጠሩ ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው እና የ2ኛ ዲግሪ የሌላቸው ከ300 በላይ መምህራኑን በ2017 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ምንም አይነት ኮርስ እንዳይሰጡ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል።

የዩኒቨርሰቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዲ አህመድ: ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከ1,400 መምህራን በላይ እንዳሉት ፤ ከእነዚህ ውስጥ 800 ገደማው የሁለተኛ ዲግሪ እንዳላቸው ጠቁመዋል።ከአጠቃላይ መምህራን ውስጥ 350 ያህሉ የመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ያላቸው ናቸው ብለዋል።

2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ እና እየተከታተሉ ያሉ መምህራን እንዳሉ የገለጹት ም/ ፕሬዝዳንቱ፤ " አንዳንዶች ለመማር ፈቃደኛ ያልሆኑ ግን እዚያው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የቀጠሉ ናቸው " ብለዋል።

" 2017 ዓ.ም. ሊጀመር ሲል አንደኛ ዲግሪ ያላቸውን መምህራን ብቻ ስብሰባ ጠርተን ነበር። መጀመሪያ ላይ የመጡልን 11 መምህራን ብቻ ናቸው። ሁለተኛ ዕድል እንስጥ ብለን የዛሬ ሳምንት ስብሰባ ጠርተን ነበር። ከ300 በላይ መምህራን ውስጥ 48 መምህራን ነው የመጡት "  ሲሉ ወቅሰዋል።

በዚህም መምህራኑ 2ኛ ዲግሪ ባለመያዛቸውና እና የዩኒቨርሰቲው አመራር በጠራቸው ስብሰባዎች ላይ አለመካፈላቸውን ተከትሎ እየተጀመረ ባለው የ2017 ትምህርት ዘመን " ምንም ዓይነት ኮርስ እንዳይሰጡ " ውሳኔ መተላለፉን አስታውቀዋል።

" እነዚህ መምህራን መማርም ስለማይፈልጉ፤ በአንደኛ ዲግሪ ያለ መምህር አንድም ኮርስ እንዳይሰጥ ወስነናል። " ሲሉ ተናግረዋል።
#ቢቢሲ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethio Scholars Info

03 Oct, 16:58


የደመወዝ ጭማሪው

ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁን የገንዘብ ሚኒስትሩ ገለጹ

ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ፤ ከትላንት በስቲያ በተካሄደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ መጽደቁን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። የደመወዝ ጭማሪው 92 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መጠየቁንም የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት፤ ከሁለት ወራት በፊት መተግበር የጀመረውን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት ለመንግስት ቅርበት ላለው ፋና ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው። አቶ አህመድ በዚሁ ገለጻቸው፤ የፖሊሲ ማሻሻያው “በጎላ መልኩ ማህበራዊ ጫና እንዳያስከትል” በወጣው እቅድ መሰረት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። 

ፌደራል መንግስት “በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለውን ማህበረሰብ የመደገፉ ወይም የመደጎሙን ስራ አጠናክሮ መቀጠል አለበት” የሚለው ከእቅዱ መካከል አንዱ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያው ይፋ በተደረገበት ወቅት፤ ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች “አስፈላጊ የደመወዝ ድጎማ እና ማሻሻያዎች” “ለተወሰኑ ጊዜያት” እንደሚደረግ መገለጹ ይታወሳል።

ይህ የደመወዝ ጭማሪ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ መስከረም 21፤ 2017 ዓ.ም በተካሄደው “የካቢኔ” ስብሰባ ላይ መጽደቁን አቶ አህመድ ተናግረዋል። ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ፤ “ለኑሮ ድጎማ ጭምር እንዲሆን” በማሰብ የተተገበረ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።  
ethiopia insider

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethio Scholars Info

30 Sep, 08:42


“አንሶላችን ከተቀየረ 8 ዓመት ሞላው”

ሙዝ በዳቦ እየበሉ 'ፒኤችዲ' የሚማሩ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰቆቃ
!

አስተማሪን? በጫማው ትለየዋለሁ እኮ። አንድን ጫማ ለብዙ ዓመታት ነው የምንጫማው። ብዙ ሲረገጥ የአቀማመጥ ሚዛኑን ያጣል።“እኛ ግቢ ብትመጣ ትደነግጣለህ። የብዙ መመህር ጫማ ተንሻፎ ነው ያለው። ድምጽ አውጥቶ ‘ጣሉኝ!’ ነው እያለ ያለው። እንዴት ትጥለዋለህ? ግማሽ ደመወዝህ ደህና ጫማ እንደማይገዛ እያወቅክ? “ታች ግቢ ለምሳሌ ኮመን ኮርስ የምንሰጣቸው የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች አሉ። 5 ዓመት ገደማ ዩኒቨርስቲ ይቆያሉ። እና ሸፋፋዋን ጫማህን ያውቋታል። ጃኬትህን ያውቋታል። ገደድ- ሸፈፍ እያልክ ስትመጣ ከርቀት ይለዩሃል። በጫማህ ባይለዩህ፣ በጃኬትህ ይለዩሃል። ደግሞ ይቀልዱብሃል። ባይቀልዱብህም እንደሚቀልዱብህ ታስባለህ። በአጠገባቸው ስታልፍ ትሸማቀቃለህ። ይህ ነገር ስሜትህን ይጎዳዋል።

“አስበው! አንድ የኢንጂነሪንግ ተማሪ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በኬሚካልም ይሁን በመካኒካል ኢንዱስትሪ እስኪመረቅ ድረስ አንተ መምህሩ ጫማ መቀየር አለመቻልህ...አያምም?
“በአጭሩ ቅድም ‘ኑሯችን ጫማችንን ነው የሚመስለው’ ያልኩህ ለዚያ ነው።”

አንዳንድ የሰቆቃ እና የሰቀቀን ታሪኮች

ይህ ጥናታዊ ዘገባ የዩኒቨርስቲ መምህራን ላይ ያጠነጥናል፤ ከእነርሱም ውስጥ ፒኤችዲ የሚማሩት ላይ ያተኩራል። መምህራኑ የበለጠ በተማሩ ቁጥር የበለጠ እየተራቡ እንደሆነ ያወሳሉ። ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በተለይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዲሠሩ ከተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች የተመደቡ መምህራን ለቅሷቸው የእናቱን ሞት ያረዱት ሰው ያህል ነው። “በተመጣጠነ ምግብ እጦት የተነሳ እየቀነጨርን ነው” ብለው ያማርራሉ።

ቢቢሲ በርከት ያሉ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ለወራት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ቆይቷል። ከጉዳዩ ስፋት የተነሳ የብዙዎቹ ኑሮ በአምስት መምህራን ታሪክ ውስጥ ጨምቆ ማስቀመጡ የተሻለ መንገድ ሆኖ አግኝቶታል። ‘ዕጩ ዶክተሮቹ’ የሰቆቃ ሕይወታቸው በቤተሰባቸው ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ሐፍረት ለማስቀረት፣ በተማሪዎቻቸውም ላይ አሉታዊ ስሜት ለማስወገድ ማንነታቸው በፊደል ተወክሏል።

“ቀንም ማታም ቀጭን ሽሮ ነው የምበላው”

“ልጆቼንና ባለቤቴን ገጠር ትቻቸው ነው የመጣሁት።አዲስ አበባ ባመጣቸው የት ያድራሉ? ምንስ ይበላሉ? እኔ ራሴ የማድረው ዶርም ውስጥ ለአራት ተዳብዬ ነው። በስተርጅና እንዲህ እኖራለሁ አላልኩም ነበር። ለዚህ 1500 ብር እከፍላለሁ። ሦስት ልጆች አሉኝ። በየወሩ ለቤተሰብ 7ሺህ እልክላቸዋለሁ። እጄ ላይ ስንት ቀረ? 1ሺህ ቀረችኝ። አንድ ሰው በ1ሺህ ብር አንድ ወር እንዴት ነፍሱን ያቆያል? ሌላም ወጪ አለብኝ። የልጆች የትምህርት ቤት ክፍያ። 2ሺህ ብር ነው። ከየት አምጥቼ ልክፈል? ከዚያም ከዚህም ተበዳድሬ እከፍላለሁ። የሚያቃዠኝ ልጆቼ ቢታመሙስ የሚለው ነው። እንቅልፌን አጣለሁ። እግዜር ረድቶን እስከዛሬ አልታመሙም። በቃ በየወሩ ጸሎቴ ልጆቼ እንዳይታመሙ ብቻ ነው። ምን ይውጠኛል? በምኔ አሳክማቸዋለሁ?
አንዳንዴ ችግር ሲጠናብኝ ወንድሜ አለ፤ በወር በወር እንዲደጉመኝ እለምነዋለሁ። አይጨክንብኝም። በወር 4ሺህ ብር አካባቢ ይቆርጥልኛል። እሱ ባይኖር ምን ይውጠኛል? ይህን ሁሉ ዓመት ተምሬ ራሴን አለመቻሌ ግን የእግር እሳት ይሆንብኛል።

ስለ ልጆቼ ልንገርህ?

የአስተማሪ ልጅ መዝናናት አያውቅም። ልብስ አይቀይርም። ልጆቼ ልብሳቸው ሰውነታቸው ላይ ያልቃል። ባደጉ ቁጥር እደነግጣለሁ። ሱሪው ያጥራቸዋላ። ልብስ መግዛት ሊኖርብኝ ነው። አባት ልጁ ሲያድግ መደንገጥ አለበት? እኔ ግን እደነግጣለሁ። ምንም ማድረግ አልችልም። ከየት አምጥቼ ነው ልብስ የምገዛላቸው? አስተማሪ ነኝ። ሙስና አልሠራ። እዚህ አገር ሙስና ካልሠራህ መኖር ትችላለህ እንዴ? ተወኝ በናትህ። ፒኤችዲ በአብዛኛው 4 ዓመት ነው የሚወስደው። በ6 ዓመት ያልጨረሱ አሉ። አእምሯቸው የተነካ አሉ። ‘ያበዱ’ መአት ልጆች አውቃለሁ። እንዴት ትማራለህ በዚህ ጭንቅ? ከአራት ኪሎ - 6ኪሎ ዞር ዞር በል። ብቻውን የሚያወራ ሰው አታጣም። የፒኤችዲ ተማሪ ነው።”

“ጓደኞቼን ካየሁ መንገድ እቀይራለሁ”

“ስለ ጓደኞቼ ልንገርህ? ድሮ አብረውኝ የተማሩ ጓደኞቼ ብዙዎቹ ባንክ ይሠራሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ናቸው። ይናፍቁኛል - እናፍቃቸዋለሁ። ግን በፍጹም አላገኛቸውም። ከርቀት ካየኋቸው ራሱ መንገድ እቀይራለሁ። ለምን በለኛ? ልጋብዝህ ሲሉኝ ይሰማኛል። ግብዣውን ብፈልገውም ወደ ኋላ መቅረቴ ያንገበግበኛል። አሁን አንድ ጓደኛዬ አለ። የውጭ ድርጅት ውስጥ ነው የሚሠራው። 2500 ዶላር ገደማ ያገኛል። ኑሮው ያስቀናኛል። ከአንዳንዶቹ ጋር መንገድ ካገናኘን፣ ‘ተው እንጂ! አትራቀን፤ እናግዝሃለን’ ይሉኛል። እሸማቀቃለሁ። ‘ምነው አሞህ ነበር እንዴ?’ ይሉኛል። ‘ራስህንማ እንደዚህ አትጣል’ ይሉኛል። ብዙ ሰው ጀዝቦ ቀርቷል እኮ። እኔ እግዜር ረድቶኝ እጅ አልሰጥ ብዬ እንጂ ብዙ ልጆች እኮ አእምሯቸው ተነክቶ መንገድ ወድቀዋል። ቀልዴን መሰለህ? ይሄ ይገርምሃል እንዴ? ፍቺ የፈጸሙ አሉ። ትዳራቸው የፈረሰ አውቃለሁ፤ በጭንቅ። ሱስ ውስጥ የወደቁ አሉ። ያበደ አስተማሪ 2 እና 3 በየዩኒቨርሰቲው አታጣም። ቀልዴን መሰለህ? እኔ ራሴ አንዳንዴ እያበድኩ ይመስለኛል። ቤተሰቤ ይደውላሉ። ባለቤቴ በጣም ስትቸገር ትደውላለች። ‘እስከመቼ ነው በዚህ ድህነት የምታኖረን? ለምንድን ነው ትምህርቱን ትተህ ሥራ የማትፈልግ?’ ትለኛለች። እኔም ነገሩን አስቤበት ነበር። ነገር ግን በማስተማር ላይ ነው ዕድሜዬን የፈጀሁት። እንዴት ነው አሁን ድንገት ልምድ ሳይኖረኝ ኤንጂኦ እና ባንክ የሚቀጥረኝ? ማን አስተማሪን ይቀጥራል ደግሞ? የመረጥነው መንገድ በጣም ጎዳን - ወንድሜ። ከዜሮ መነሳት ይከብዳል።
እንደነገርኩህ ጓደኞቼ አሉ። በጥሩ ጊዜ ኤንጂኦ የገቡ። በትምህርት ብዙም ያልገፉ። ጂፕላስ- 2 ቤት የገነቡ። እኔ በዚህ ዕድሜዬ ፒኤችዲ እየሠራሁ ዶርም ውስጥ ከ4 ሰው ጋር ተዳብዬ እኖራለሁ።

“እናቴ ደውላ አለቀሰች”
“አንሶላችን ከተቀየረ 8 ዓመት ሞላው”
“ምናለ ጎበዝ ተማሪ ባልነበርኩ” እላለሁ“ባለቤቴ ናት ሱሪ የገዛችልኝ”
“የድሃ ድሃ ነን”

“ከሰው አልጨመርም። አብዝቼ እተክዛለሁ። ፊደል ያልቆጠረ ብዙ የማውቀው ሰው ቤት ንብረት አለው። የተሻለ ሕይወት ይመራል። እኔ ለምን ተማርኩ እላለሁ - አንዳንዴ። እንደሱ አይባልም - አውቃለሁ። ግን ምን ላድርግ? ወደ አእምሮዬ የሚመጣውን ነው የምነግርህ።

“አእምሮዬ ልክ አይደለም”
“የፒኤችዲ ትምህርቱ ያን ያህል ከባድ አይደለም። ግን ቀልባችን ተበተነ። በትምህርቴ ላይ ማተኮር ተቸገርኩ። በዚህ የተነሳ መቀጠል አልቻልኩም።
እንዴት አይሰማኝም ታዲያ?”
#ቢቢሲ #BBC

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethio Scholars Info

29 Sep, 18:32


ፖሊሲ አቅጣጫ ጥቆማ
(Aminu Nuru)
==================
ምናልባት የሚመለከተው አካል ግብዓት እንዲያገኝበት በዝርዝር የተፃፈ
.............
ባለፈው ያነሳሁት የሀገራችን ፕሮፌሽናሊዝም እጣ ፈንታ ችግር እንዳለ ሆኖ.. ቢያንስ ተመራቂዎቻችን ባሉበት ሆነው የዓለምን ትሬንድ በመከተል ስራ የሚፈጥሩበትን እና ገቢ የሚያገኙበትን መንገድ በተመለከተ የበኩሌን ልበል...

What is Gig Economy?
=====================
ጊግ ኢኮኖሚ "ፍለሪላንሰሮች" በኮንትራንት ወይም  ለአጭር ጊዜ ከስራ ደንበኞቻቸው ጋር በዲጂታል ፕላት ፎርሞች የሚገናኙበት መስክ ነው።በቅርብ አመታት  እጅግ በፍጥነት እያደገ ያለ ኢንዲስትሪ ነው።  በ2023 ኢንዱስትሪው ከ 452 ቢሊየን ዶላር በላይ አንቀሳቅሷል። 

Freelancing and Outsourcing
===================
አሁን ባለው የዓለም ትሬንድ ተወዳዳሪነት እጅግ እየጨመረ ስለመጣ። ትላልቅ ብሎም ትናንሽ ድርጅቶች በውድ ዋጋ ሰራተኛን ከመቅጠር ታለንቶችን አወዳድሮ ሀፍሪላንሰርነት ማሰራት የብዙዎች ምርጫ ነው።

Upwork እና Fiverr የዘርፉ ግንባር ቀደም ፕላትፎርሞች ናቸው። ሁለቱም በድረገፆቻቸው በይፋ እንደለጠፉት አመታዊ ሪፖርት...

- Upwork እኤአ 2023 የ4.1 ቢሊየን ዶላር ስራ በሚሊየን ለሚቆጠሩ ፍሪላንሰሮች ሰጥቶዋል።  ድርጅቱም እንደ ኮሚሽን 600 ሚሊየን ዶላር በ2023 ብቻ እንዳገኘ ገልፆዋል።

- ፊቨር በድረ ገፁ እንዳስታወቀው በ2023, ከ160 ሀገራት ስራ ላመለከቱ ፍሪላንሰሮች በ550 የስራ መደቦች ከ 4 ሚሊየን በላይ ደንበኞች ስራ እንዳቀረበ  ገልፆዋል። በቀጣሪዎቹ የቀረበው የስራ ጥያቄ ወደ 1 ትሪሊየን ዶላር እንደሆነ አስታውቋል

- በሌላ ሪፖርት አፕወርክ ከተቋቋመ ከ2018 ጀምሮ 20 ቢሊየን ዶላር ለፈፍሪላንሰሮች እንዳስገኘ ተገልፆዋል።

በአጠቃላዩ "ፍሪላንሲንግ" ድንበር ተሻጋሪ የትሪሊየን ዶላር ኢንደስትሪ እየሆነ ነው። ከአሜሪካ ውጭ ህንድ፤ፊሊፒንስ እና ሌሎች የምስራቅ ኤሺያ እና የምስራቅ አውሮፖ ሀገሮች ግንባር ቀደም ተጠቃሚዎች ናቸው።  ሴክተሩ ለፊሊፒን GDP 9.1% እንደሚያበረክት ተገልጿል። ከአፍሪካም ብዙ ሃገሮች እየተቀላቀሉ ነው።

እኛስ ምን እየጠበቅን ነው?
==============================

የሀገራችንን የውጭ ምንዛሪ ክፍተት ሊሞላ ከሚችሉት ኤርያዎች አንዱ ይህ "ሰርቪስ ኤክስፖርት" ነው።  በአጭር ጊዜ በሸቀጥ ኤክስፖርት ተወዳዳሪ ሆኖ ክፍተቱን ለመሙላት አይታሰብም። ዝርዝሩ ብዙ ነው።

ምን አይነት ስራዎች ናቸው።?
=========================

በአሁኑ ጊዜ ፍሪላንስ የማይደረግ የአገልግሎት አይነት የለም። የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙት ከ አይቲ ጋር የተያያዙ ዘርፎች ቢሆንም እንደ Accounting, Data entry & Management, Translation, Virtual assistant, Digital Marketing, Customer service….. ብዙ ስራ ይወጣባቸዋል ከ500 በላይ የስራ ዘርፎች ተዘርዝረዋል።

ምን ይደረግ? በተለይ መንግስት
===========================

፩ ተፈላጊ በሆኑ ዘርፎች ላይ ክህሎት ማዳበር።  የትምህርት ስርአቱ ላይ ማካተት። comparative advantage ያለን ላይ ማተኮር።

፪ Digital Skill ላይ መስራት

፫. የቋንቋ ክህሎት፤ እንግሊዘኛ ቋንቋ የሚጠቀሙ ሀገራት የተሻለ እድል አላቸው።  ለቋንቋው ከስር ጀምሮ ትኩረት መስጠት። (ዳቦ የማይሆነውን የቤር ቤረሰቦች ቋንቋን ጉዳይ ለባህል ሚኒስቴር መስጠት) የትምህርት ስርዐቱን ከፖለቲካ ማራቅ።

፬. መሰረተ ልማት፣ የኢንተርኔት ፋሲሊቲ እና የመስሪያ ቦታዎችን በፖርክ መልክ በነፃ ማቅረብ።

፭. ሰለ ፕላትፎርሞቹ እና አጠቃቀሙ ሙያዊ ድጋፍ መስጠት፤ ሴሚናር እና ስልጠናዎችን ማዘጋጀት።

፮. ፍሪላንሰሮችን የሚደግፍ እና መብታቸውን የሚያስከብር የህግ ማዕቀፍ ማበጀት

፯. ለስታርታፕ የሚሆኑ አነስተኛ ብድሮችን ያለ ኮላተራል መስጠት። "ግራንቶች"  ማፈላለግ።

፰. ዘርፉ ዘላቂነት ያለው የስራ ዋስትና ስለ ሌለው ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች ሊያኙዋቸው የሚችሉ ጥቅማ ጥቅሞች ካሉ ለፍሪላንሰሮች ማቅረብ።

፱. የክፍያ ሲስተምን ማመቻቸት። የዶላር አካውንት በቀላሉ እንዲከፍቱ ማድረግ እንደ PayPal ያሉ የክፍያ ስርአቶች እንዲሰሩ ማድረግ።

፲. የፍሪላንሰሮች ማህበር፤ ባለሞያዎች መረጃ እና ልምድ የሚለዋወጡበት ማህበር እንዲያቋቁሙ እገዛ ማድረግ። ማደራጀት።

፲፩. አገር በቀል ፕላትፎርሞች እንዲፈጠሩ ማገዝ እና ማበረታታት።

፲፪. ሌሎች ሀገሮች ከዘርፉ ለመጠቀም የሄዱባቸውን መንገድ መዳሰስ።

ይህ የመንግስት 5 ሚሊየን ኮደርስ "ኢኒሽየቲቭ" ጥሩ ጅማሮ ነው።  ይሁን እንጂ 6 ሳምንት ኦንላይን ኮርስ ሰርተፍኬት አድሎ እንደ ፀበል ማዳረስ ሳይሆን ዘላቂነት ባለው ድጋፍ ቢታገዝ ጥሩ ነው። ከብዛት ጥራት።

የሌሎች ሀገራት ተመክሮ
==========================

- ህንድ በዘርፉ ተቀዳሚ ናት። ዜጎቿ ከዘርፉ ቢሊየን ዶላርላሮችን ይሰበስባሉ። መንግስት በፖሊሲ ተደግፎ እየሰጠ ያለው ማበረታቻ እዚህ ሊንክ ላይ ማየት ይቻላል። https://financialinsights.in/government-schemes-for-freelancers-and-self-employed-individuals-in-india

- ባንግላዲሽ መንግስት እየሰጠ ባለው ማበረታቻ ከቀዳሚ 10 ሀገሮች መቀላቀል ችላለች።1 ቢሊየን ዶላሩን ወደ 5 ለማሳደግ እየሰራች ነው። https://freelancers.gov.bd/2021/01/02/government-initiatives-to-develop-the-freelancing-sector/

- ፊሊፒንስ ሌላዋ ተቀዳሚ ሀገር ናት።ዘርፉ ኢኮኖሚዋን ደግፎ ይዟል። የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን ከመንግስት የሚሹትን ድጋፍ በጥናት እንዲህ አቅርበዋል። https://www.freiheit.org/philippines/finding-policies-work

- ከአፍሪካም ኬንያ፤ ናይጄሪያ፤ ጋና የመሳሰሉት ሃገራት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩበት ነው።

እኔ የበኩሌን ብያለሁ።

ለመንግስት አድርሱልኝ።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Ethio Scholars Info

29 Sep, 08:44


https://waltajobs.com/call-for-papers-hawassa-university/