ትምህርት 1:- ቅዱሳን መጻሕፍት
========================
ውድ ተማሪዎች:
ይህ የመጀመሪያው ትምህርት በይፋ የሚለቀቅበት ቀን ነው። የዚህ ትምህርት ትኩረት "መጽሐፍ ቅዱስ" ነው።
ቅዱሳን መጻሕፍት በሰብአዊ ሰው ድነት ላይ ያላቸውን ሚና ለማስተዋል እንዴት እንደተጻፉ: ማን እንደጻፋቸው: በአጻጻፋቸው ላይ የሰውን እና የእግዚአብሔርን ሚና በሰፊው ማጥናት ተገቢ ነው።
የእግዚአብሔርን ቃል ተአሚነት ማወቅ ለመንፈሳዊ ሕይወት ጠንካራ መሰረት መጣል ነው::
ይህ ትምህርት በጽሑፍና በድምጽ የታገዘ ነው:: ጽሑፎቹን መጀመሪያ ካነበባችሁ በሁዋላ የድምፅ መልእክቶቹ ይለጠፋሉ:: በመጪው አርብ ሳምንት የመጀመሪያውን ፈተና ትወስዳላችሁ!!
ጥያቄ ካላችሁ በውስጥ መስመር መላክት ትችላላችሁ!