ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

@apostolic_council


እንኳን ወደ ጉባኤ ሐዋርያት በደህና መጣችሁ ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት "ሐዋርያት በሰበሰቧት ከሁሉ በላይ በምትሆን በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን"

ከእግዚአብሔር ቃል የተጣረሱ ሐዋርያዊ ወንጌልን የሚጻረሩ አስተምህሮዎችን ሁሉ እያነሳን በቃሉ ሥልጣን እንለያቸዋለን ከሐዋርያት የተቀበልነውን ቅዱሱን ወንጌል አጽንተን እንቀጥላለን።

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

20 Oct, 06:31


<< ከድንቅም ድንቅ >>
"መንክረ-መንክራት"

የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ባስልዮስ እንዳስተማረው።

የእግዚአብሔር ገቢረ ተኣምራት ሁሉ ግሩማን ናቸው አይመረመሩም። ቅዱስ ዳዊት ሥራህ ግሩምና ድንቅ ነው ይላልና....

ግና ከድንቅም ድንቅ አምላክ በሥጋ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት የተወሰነበት ከሃሊነቱ አይደንቅም..?? አይረቅም..? ኢሳይያስ ስለ ነገረ ትሥጉቱ ሲናገር የተወለደው ሕጻና ድንቅ መካር ኀያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ይለዋልና..(ኢሳይያስ 9፥6)  መንክር(ድንቅ) የሚባል ከሕሊናት ሁሉ የሚያልፍ የማይመረመር ሥራ ነው።

የአንጾክያ ሊቀ ጳጳሳት ባስልዮስ ሲናገር "እስመ ኢሳይያስ ነቢይ ክቡር በውስተ ነቢያት ሰመዮ መንክረ መንክርኒ ውእቱ ግብር ዘኢይትረከብ..." 'ከነቢያት መካከል የከበረ ነቢይ ኢሳይያስ መንክር(ድንቅ) ብሎታልና መንክር(ድንቅ) የሚባልም የማይመረመር ሥራ ነው። (ሃይ-አበው ዘባስልዮስ ም 96 ቍጥር 27)

ዓለማትን በእጁ የያዘ አሕዛብ ሁሉ በፊቱ በገንቦ እንዳሉ የውሃ ጠብታ የሆኑለት ሰማይ ዙፋኑ ምድርም መረገጫው የሆነ አምላክ ሥጋ ሆነ አበው እንደ ተናገሩትም <<ወልደቱሂ ኮነ ብርሃነ መድኀኒትነ>> (ልደቱም የደኅንነታችን መታወቂያ ሆነልን) ሃይ-አበው ዘባስልዮስ ምዕ 96 ቍጥር 23)

መልካም ዕለተ ሰንበት 🙏

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

13 Oct, 06:12


የአምላክን ሰው መሆን ባሰብን ጊዜ ይህ የማይመረመር ታላቅ ደስታ ለዓለሙ ሁሉ የሚሆን እንደሆነ ቅዱሳት መጽሐፍት ያስተምሩናል ይህ ምክንያተ ፍሰሓ ግን ለሰብአውያን ብቻ ሳይሆን ለዓለመ መላእክትም ጭምር እንደሆነ አክለው ይነግሩናል ይህ ፍጹም ደስታ አምላክ በመወለዱ ያመሰገኑበት (ሉቃስ 2፥13) ሊያዩት የሚመኙት (1ጴጥሮስ 1፥12) ኀጥእ ንሰሐ በገባ ጊዜ የሚደሰቱበት ፍሰሐ ነው (ሉቃስ 15፥10) ። ጌታ መድኀኔ ዓለም ከኀጢአት የሚያድን ዕረፍተ ሥጋ ዕረፍተ ነፍስ ነው።


ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ   ገጽ 292 ክፍል 34 ምዕራፍ 75    ቍጥር 24

እፎኑ ኢንመልእ ፡ ፍሥሓ  እንዘ ፡ ንሬእዮ  ለእግዚእነ  መድኃኔ  ዓለም ተወሊዶ እምድንግል ፡ ቅድስት  ወእሙንቱ ዓዲ ፡ ያብዕሉ፡ ሶበ ይሬእዩ ፡ ፩ደ[አሐደ] ፡ ብእሴ ፡ኃጥኣ ፡ እንዘ ይኔስሕ፡ በከመ ይቤ፡ መድኃኒነ ፡ ኵሎሙ ፡ ቅዱሳን ፡ መንፈሳውያን ይሴብሑ ።

እንዲህ  ከሆነ ፡ የዓለም መድኃኒት ጌታችን ፤ ከንጽሕት  ድንግል ' ተወልዶ ፡ ስናየው እንደምን ደስ  አይለን? ዳግመኛ መድኃኒታችን ክርስቶስ ፡ ቅዱሳን መንፈሳውያን መላእክት ደስ ይላቸዋል ፡ እንዳለ እነርሱ ፡ አንድ ኃጥእ ሰው ንስሐ  ሲገባ ፡ ባዩ ፡ ጊዜ ፡ ደስ ፡ ይላቸዋል


መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን🙏

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

08 Oct, 08:24


በከመ መሀረ ፊላታዎስ ሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ ሃይ አበው ምዕራፍ 105 ቍጥር 3 ገጽ 472

ምሥጢረ ፡ ሥላሴ ፡ ይትከፈል ፡ ወኢይትከፈል ፤ ይትከፈሉ ፡ በአካላት ፡ ወበገጻት ፡ ወኢይትከፈሉ በመለኮት ፡ በከመ ፡ መሀሩነ ፡ አበው ንሰግድ ለአብ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አሐተ ፡ ስግደተ..

የሦስትነት ፡ ምሥጢር ፡ ይለያል ፤ አይለይም ፤ በአካላት ፤ በገጻት ፡ ይለያሉ ፤ በመለኮት ፡ ግን ፡ አይለ ዩም ፤ አባቶች ፡ እንደ ፡ አስተማሩን ፡ ለአብ ፡ ለወ ልድ ፡ ለመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አንዲት ፡ ስግደትን ፡ እንሰግዳለን

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

06 Oct, 08:20


አብ ከወልድ ፡ ተለይቶ ፡ የኖረበት ፡ ዘመን ፡ የለም ፥ወልድም ፡ ከመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ተለይቶ ፡ የኖረበት ፡ ዘመን ፡ የለም፤ መንፈስ፡ ቅዱስም ፡ ከአብ ፡ ከወልድ፡ ተለይቶ ፡ የኖረበት ፡ ዘመን ፤ የለም ሥሉስ ቅዱስ በዘመኑ ፡ በቀኑ ፡ ሁሉ ፡ በግብርም ፡ በስምም ፡ ሳይለ ወጥ ፡ ሳይፋለስ ፡ ጸንቶ ፡ ያለ  ነው ፡ እንጂ ።

ጥንት ፡ የሌለው ፡ ቀዳማዊ ፡ ልጅ  ያለው ፡ እግዚአብ ሔር ፡ አብ ፡ ብቻ  ነው ፡ ዳግመኛ ፡ እርሱ ፡ ወልድም፡ አይመረመርም ፡ ማንም  መርምሮ አያገኘውም ።

አብ ፡ ከዘመን፡ በኋላ አልወለደውም ፡እርሱ ቀዳማዊ ወልድ፡፡ ከአብ ፡ ጋር ፡ በቅድምና  የነበረ ፡ ነው ፡ እንጂ የማይሞት  ነው ፡ ከማይሞት ፡ ከአብ ፡ ጋር ፡ ፈጣሪ ፡ ነው ፤ እንደ፡ አብም፡ ሁሉን የፈጠረ ' ነው ።

እንዲሁ መንፈስ ፡ ቅዱስም ፡ ከአብ  ከወልድ ፡ ጋር፡ በቅድምና ፡ የነበረ  ቀዳማዊ ፡ ነው ፤ በሥራውም ሁሉ ከአብ ከወልድ፡ ጋር፡ አንድ፡ ነው ።

ጉባኤ ፡ የቆመለት ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን፡ የተቀበለችው፡ ሐዋርያት ፡ ያስተማሩት ፡ እውነኛ ትምህርት፡ ይህ፡ ነው ።

ሃይማኖተ አበው ዘሠለስቱ ምዕት ምዕራፍ ፲፱ ገጽ ፶፩  ቍጥር ፮ እስከ ፲

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን።🙏

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

29 Sep, 05:55


ዛሬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ለምን ፡ ተውከኝ ፡ ይል ዘንድ ፡ ምን ፡ አተጋው ! እኛስ ፡ ቀድሞ ፡ አዳም ፡ በበደለ ፡ ጊዜ ፣ የተሠራችለትን ፡ ትእዛዝንም ፡ በአፈረሰ ፡ ጊዜ ፤ ከተሠራችለትም ' ሕግ ፡ እርሱ ፡ በተለየ ' ጊዜ ፤ ስለዚህ ፡ ነገር ፡ እግዚአብሔር ፡ የሰውን ፡ ባሕርይ ፡ ከእርሱ ፡ አርቆት ፡ ነበርና ፤ በፍዳም ፡ ተይዞ ፡ ሞትም ፡ ድል ፡ ነሥቶት ፡ ነበርና ፡ ስለዚህ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእኛን ፡ ባሕርይ ፡ ወደ አለመለወጥ ' ሊመልሰው ' ወደደ ። ዘፍጥረት 3፥1-19። ሮሜ 15፥14-20
(ሃይማኖቸ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ ገጽ 323 ምዕራፍ 79 ቍጥር 36)

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን።🙏

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

27 Sep, 06:39


'እልመስጦአግያ"

...ወበመስቀሉ ኮነ

እልመስጦአግያ የሚለው ቃል በግዕዝ ትምህርተ ኅቡዓት ማለት ነው። ትምህርተ ኅቡዓት በሥጋ ሕሊና የማይመረመረውን ነገረ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ በከሠተበት ልክ የምንማርበት ትምህርት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፦“ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።”
(1ቆሮንቶስ 2፥14)
 
መንፈሳዊ ነገር በፈቃደ እግዚአብሔር ካልተገለጠ ዘወትር ኅቡዕ ነው ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ “መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው (1ቆሮንቶስ 2፥10)።” ብሎ እንደ ተናገረው ኅቡዕ የሆነው ነገረ እግዚአብሔር በምንችለው ልክ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ያስተምረናል።

በዚህ በሃይማኖተ አበው በእልመስጦአግያ ክፍል ላይ አበው ስለ ክርስቶስ መስቀል ማተኰር ያለብንን ሀሳብ በዚህ መልክ ያስተመሩናል፦ ተሰቅለ በእንቲአነ ፡ ወበመስቀሉ ፡ ኮነ፡ ሕይወትነ ፡ ጽንዕነ ፡ ቤዛነ።


ትርጓሜውም፦ ስለእኛ ፡ ተሰቀለ ፡ በመስቀሉም ጽናችን ፡ ቤዛችን ፡ ድኅነታችን ፡ ተደረገልን ።  ይኸውም ፥ከእግዚአብሔር ፡ የማትርቅ ፡ መቸም ፡ መች ፡ የማትለይ ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ የማትመጠን  የቸርነቱን ፡ ብዛት ፡ በመናገር ፡ የማይፈጸም ፡ ደስታ ፡ ያለበት ፡ ረቂቅ ፡ ምሥጢር ፡ ነው ።

እልመስጦአግያ ምዕራፍ 2 ቍጥር 2

በዚህ ምንባብ ላይ አበው በ1ጴጥሮስ 2፥24 ላይ ያለውን ምንባብ ዋቢ አድርገዋል እንዲህ ይነበባል፦“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።”

ጌታችን ኢየሱስ ኀጢአታችንን በመስቀሉ በማስወገዱ የጥልን ግድግዳ በመስቀሉ አፈረሰ ነገረ መስቀሉን ስናስብ እጅግ የሚደንቀን እውነት ይህ ነው።

በዚሁ በእልመስጦአግያ ምዕራፍ 2 ቍጥር 2 ላይ
ዘውእቱ ፡ ምሥጢር ፡ ኅቡዕ ፡ ፍሥሓ፡ ዘኢይትዌዳዕ ፡ በነጊር ፡ በዕበየ ፡ ትሩፋት ፡ ኵሎ ፡ ጊዜ ፡ እንተ ኢትትኌለቍ ፡ ወኢትርኅቅ ፡ እም ፡ እግዚአብሔር ፡ ወትረ ፡ ኢትሴስል ።



ይኸውም ፥ከእግዚአብሔር ፡ የማትርቅ ፡ መቸም ፡ መች ፡ የማትለይ ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ የማትመጠን  የቸርነቱን ፡ ብዛት ፡ በመናገር ፡ የማይፈጸም ፡ ደስታ ፡ ያለበት ፡ ረቂቅ ፡ ምሥጢር ፡ ነው ።

ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያይቱ በቆሮንቶስ መልእክቱ ላይ፦“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።”
(1ኛ ቆሮንቶስ 1፥18)

የመስቀሉ ቃል የተባለው በቍጥር 23 ላይ የተሰቀለውን ክርስቶስን መስበክ እንደሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ይናገራል በዚህ በመስቀሉ ቃል በኩል የዘላለም ሕይወት ድኅነት እና የኀጢአት ሥርየት ሁሉ አለ እግዚአብሔር መዳንን ሁሉ በልጁ በክርስቶስ አዘጋጅቶልናልና።
ስለዚህም ነው ዘውእቱ ምሥጢር ኅቡዕ የተባለው።

መልካም የመስቀል በዐል ይሁንልን።

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

22 Sep, 04:47


ወንአምን በእሉ አስማት ዘተጠመቅነ ቦሙ።አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ዘከመ አዘዘነ ቃል ሥግው እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ።

በከበርንባቸው በእሊህ ስሞች በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እንመን ሰው የሆነ ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አዘዘን።

ሃይማኖተ አበው ዘባስልዮስ  ምዕራፍ 32

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን።

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

20 Sep, 05:49


መንክር ውእቱ ልደትከ ኦ ወልደ እግዚአብሔር ከመዝ። የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ መወለድህ እንዲህ ድንቅ ነው።

የሕጻናት ፈጣሪ-ፈጣሬ ሕጻናት በማኅጸነ ብእሲት አጥንትን የሚያገጣጥም ጅማትን የሚያስማማ ሥጋንም የሚያለብሳቸው በየጥቂቱም የሚያሳድጋቸው አምላክ መፍጠሩን በፈጸመ ጊዜ ጌትነቱን የሚገልጥበት አምላክ ለራሱ በድንግል ማኅጸን ሥጋን ፈጠረ ቅዱስ ኤፍሬም ወለሊሁ ፈጠረ ወላዲቶ ወእምኔሃ ነሥአ ሥጋነ ዘውእቱ ፈጣሪ እርሱም እናቱን ፈጠረ ከርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ።

መወለዱ እንዲህ ድንቅ ነው! ማሪ ያዕቆብ እንደ ተናገረው ትንንሽ ሕጻናትን የሚፈጠር ይዋሐደው ዘንድ ሥጋን ካንቺ ፈጠረ ሕጻናትን ልጆችን የፈጠረ እርሱ በማኅጸንሽ አደረ

ድንግል ታዝለው እና ታቅፈው ዘንድ በድንግል ማኅጸን ለራሱ ደረትን ፈጠረ በፍዳ ተይዞ ተጎድቶ የነበረ የአዳምን ባሕርይ ገንዘብ አደረገ የሚወደውን ደቀ መዝሙርንም በደረቱ አስጠጋው።


የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነገረ ክርስቶሳዊ መደነቅ ከሰፊ ማብራሪያ ጋር ይቀጥላል።

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

16 Sep, 21:36


ቃሌ Vs አክሊል።

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

16 Sep, 17:57


https://t.me/Hokhmahstudies?videochat

ሊጀመር ነው ግቡ

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

16 Sep, 08:00


ዛሬ ከምሽቱ 3:00 ላይ በወንድም ቃሌ እና አክሊል Sola Scriptura በሚል ርዕስ ውይይት ይኖራል።

ውይይቱን በቲክቶክ ለመከታተል ፦ https://vm.tiktok.com/ZMhRB4WtD/


ውይይቱን በቴሌግራም ለመከታተል።
https://t.me/Hokhmahstudies

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

15 Sep, 07:50


ወወልደ አብ ዋሕድ ይሰመይ ብርሃነ.. <<የአብ አንድ ያ ልጅ ብርሃን ይባላል>>

ወወልደ አብ ዋሕድ ይሰመይ ብርሃነ እስመ ብርሃን ዘተወልደ እምብርሃን ኡይትበሀል ተወልደ እምድኅረ ብርሃን አላ በጊዜ ዘኮነ ቦቱ ውእቱ ብርሃን ይትረከብ ብርሃን ዘተወልደ እምኔሁ ወኅልው ወትረ ምስሌሁ ወብርሃንሂ ያጤይቀከ አምሳሊሁ ለወልድ ዘውእቱ ህልው ምስለ አብ በኵሉ ጊዜ እምቅድመ ኵሉ ዓለም። ወንነግረከ ወናሌብወከ ዘንተ ስመ ዘውእቱ ወልድ ከመ ውእቱ አሐዱ ህላዌ ምስለ አብ። አሜን።

የአብ አንድ ልጅ ብርሃን ይባላል ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከብርሃን በኋላ የተገኘ ነው አይባልምና ያ ብርሃን በተገኘ ጊዜ ከርሱ የተወለደው ብርሃን ተገኝቶ ከርሱ ጋር ህልው ሆኖ ዘወትር ይኖራል እንጂ ብርሃንም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር በጊዜው ከአብ ጋር ህልው የሚሆን የወልድን ነገር ያስረዳሃል። ይህንንም ስም ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ እንደሆነ እንነግርሃለን እናስረዳሃለን ይኸውም ወልድ መባል ነው።  አሜን። ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቴዎዶስጦስ ምዕራፍ 53 ቍጥር 10-11 ገጽ 172-173

ነአምን በሥላሴ (በሥላሌ እናምናለን)  መልካም ዕለተ ሰንበት

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

11 Sep, 03:47


እስመ ለዓለም ምህረቱ
ምህረቱ ለዘላለም ነውና..(መዝሙር 136)

የብርሃናት አባት የጊዜያት ሁሉ ባለቤት ታላላቅ ብርሃናትን ለጊዜያትና ለዘመናት ያበጃቸው በምህረቱ እና በቸርነቱ ብዛት መሻገርን አድርጎልናል እስመ ለዓለም ምህረቱ ብለን እንናገራለን..

መንገዳችንና ትንፋሻችንን ሁሉ በእጁ የያዘ አምላክ ዐዲሱን ዘመን እንደ ምህረቱ ብዛት ስላሳየን ምስጋና ይገባዋል።

እንኳን ለ2017 ዓም ዐዲስ ዐመት በሰላም አደረሰን።

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

09 Sep, 15:45


@Yeshua_Apologetics_Ministry

➟የሹዋ ዐቅበተ እምነት አገልግሎት አላማ

ከክርስትና እምነት አንጻር ደርዛቸውን የጠበቁ ስነ መለኮታዊ ፍልስፍና፤ አመክንዮአዊና ታሪካዊ ጽሑፎችን ማቅረብ

በክርስትና ላይ የሚነሱ የተቃውሞ ሀሳቦችንና የኑፋቄ ትምህርቶችን መመከት

የሌላውን እምነተ መርህ ከሎጂክና ከታሪካዊ ዳራዎች አንጻር መመርመር።

-----
ቻናሉን በመቀላቀል ከአገልግሎቱ ተካፋይ ይሁኑ።🙏

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

08 Sep, 07:01


አሐቲ ምልክና ወአሐቲ ሥምረት ወአሐቲ መንግሥት አሐቲ ስግደት ወአሐቲ አኰቴት ወአሐዱ ስብሓት ይደሉ  ለሥሉስ ቅዱስ። አሐቲ ምክር ወአሐቲ ሥልጣን ወ፩ዱ[ወአሐዱ] ክብር ወአሐቲ ፅንዕ ወ፩ዱ[ወአሐዱ] ህሉና ወ፩ዱ[ወአሐዱ] ፈቃድ ለሥሉስ ቅዱስ።

አንዲት አገዛዝ አንዲት ፈቃድ አንዲት ኀይል አንዲት መንግሥት አንዲት ስግደት አንዲት ምስጋና አንዲት ክብር አንድ ጽንዕ ለሥላሴ ይገባል፤ አንዲት ምክር አንዲት ሥልጣን አንድ ክብር አንዲት ጽንዕ፤ አንድ አኗኗር አንድ ፈቃድ ለሥሉስ ቅዱስ ነው። (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አግናጥዮስ ገጽ 37 ምዕራፍ 11 ቍጥር 7)

አሜን።

መልካም ዕለተ ሰንበት።

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

07 Sep, 16:16


ቅዱስ ኤራቅሊስ ቶማስ ጌታዬ አምላኬ ያለበትን ቃል እንዲህ ይተረጒመዋል..

አንተ እግዚእየ ወአምላኪየ አንተ እምቅድመ ዓለም ወአንተ ዘይእዜ አንተ ሰማያዊ ወአንተ ምድራዊ።

"ጌታዬ ፈጣሪዬ አንተ ነህ ቅድመ ዓለም የነበርክ አንተ ነህ ዛሬም ያለህ አንተ ነህ ሰማያዊ ነህ ምድራዊም ነህ"
(ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤራቅሊስ ምዕ 48 ገፅ 155 ቍጥር 89)

በምድር የተገለጠው ድኅነተ-ዓለምን የሰራው ዕሩቅ ብእሲ ወይም ሰው ብቻ የሆነ አልነበረም እርሱ ሰማያዊ ነው መስፍነ-መሳፍንት የሆነ መላእክት የሚሰግዱለት ቀዳማዊ፣ ወልድ-ዋሕድ አምላክ የሆነ ነውና እርሱ ሰማያዊ ነው...

ይኸው አምላክ ከክብሩ ሳይወርድ በትረ-ሥልጣኑን ሳይተው ሕያው አምላክ ባሕርያችንን የእርሱ ባሕርይ ገንዘብ አንድርጎ ተዛምዶናልና እርሱን ምድራዊ እንለዋለን።

አንዱን ሥግው ቃል አንተ ሰማያዊ ወአንተ ምድራዊ ብለን እንጠራዋለን። ምሥጋና ይገባዋል

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

02 Sep, 17:03


https://t.me/Apostolic_Council

ሼር በማድረግ ብዙዎችን ተካፋይ አድርጓቸው። ተባረኩ🥰

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

02 Sep, 17:01


እንኳን ወደ ጉባኤ ሐዋርያት በደህና መጣችሁ ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት "ሐዋርያት በሰበሰቧት ከሁሉ በላይ በምትሆን በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን"

►  ይህች ቤተክርስቲያን ብቸኛ ራሷ የቃል እና የስብከት ማዕከሏ የወልደ አብ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደመሆኑ እኛም የሐዋርያትን  መሠረት ሳንለቅ ሌላም መሠረት ሳንመሰርት ሕያው የማዕዘን ራስ ድንጋይ ክርስቶስን የስብከት ማዕከላችን እናደርጋለን ።

➛"ንሕነሰ ንተሉ እምነተ አበዊነ ቅዱሳን እንበለ ተወላውሎ እንዳለው ቄርሎስ እኛም ያለ ማወላወል የደጋጉን የአባቶቻችንን ሃይማኖት እንይዛለን ቅዱሳን አበው ያስተማሩንን ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ትምህርት ሁሉ እያነሳን እንማማራለን። ቃለ መለኮት በሆነው እና ብቻውን በማይሳሳተው  በመጽሐፍ ቅዱስ ሚዛንና የመጨረሻ ሥልጣንነት ተመሥርተን አስተምህሮዋችንን ሁሉ እንቃኛለን በቅዱሳት መጽሐፍት መሠረትነት በተለያዩ መንፈሳዊ ርዕሶች እንማማራለን።

➛ ከእግዚአብሔር ቃል የተጣረሱ ሐዋርያዊ ወንጌልን የሚጻረሩ አስተምህሮዎችን ሁሉ እያነሳን በቃሉ ሥልጣን እንለያቸዋለን ከሐዋርያት የተቀበልነውን ቅዱሱን ወንጌል አጽንተን እንቀጥላለን።

ማዕከላችን ክርስቶስ መሠረታችን የእግዚአብሔር ቃል ነው  ቻናችንን ተቀላቀሉ ወንጌልን እንማር ተባረኩ።

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

02 Sep, 15:55


1K ገብተናል .. አብራችሁን ቅዱስ ወንጌልን የምታገለግሉ ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ.. በቀጣዩ ዘመናችን ከፍ ሊል የሚገባውን የክርስትና ማዕከል ክርስቶስን አድምቀን እንድንሰብክ ሐዋርያዊ ወንጌልን እንድንናገር እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልን።..🤗

ጉባኤ ሐዋርያት እቅበተ እምነት

01 Sep, 07:27


እስመ እግዚአብሔር ውእቱ ወአኮ ገብር ወተለዐለ ኀበ ስብሐተ እግዚአብሔር ወዳእሙ ነሥአ አርአያ ገብር እንዘ ሀሎ በ፩ዱ[በአሐዱ] ዕሪና ምስለ አብ ወኢኮነ ሰብእ ወእምዝ ረከበ ብዕለ መለኮት

እርሱ እግዚአብሔር ነውና ተገዥ ሆኖ ኖሮ ወደ እግዚአብሔርነት ክብር የደረሰ አይደለም ከአብ ጋር በአንድ ትክክልነት ሳለ የተገዥ ባሕርይን ነሣ እንጂ መለኮት ሰው ሆኖ ኖሮ ኋላ ክብር ያገኘ አይደለም። ሃይማኖተ አበው ዘቄርሎስ ምዕ 72 ቍ 9

ፊልጵስዩስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥
⁸ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
⁹ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤




መልካም ዕለተ ሰንበት።