ከገጠምኩ ለኢየሱስ

@kegetemku_leyesus


well come ወደ ቻናላችን በደህና መጣችሁ
ስራችን ሙሽራው ማላቅ ቤተክርስቲያን ማብቃት ነው ለማንኛውም ማስታወቂያ Owner @ErmiyAs_kifle

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:24


ቤተሰዎች ነን


ከተለያየ ዘር ባህል ቋንቋ በደሙ የተገናኘን የአንድ አባት ልጆች ነን ዝምድናችን ጥብቅ ነው የአባቴ ልጆች እወዳችኃለው

ኤፌሶን 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።
¹⁴-¹⁵ እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥
¹⁶ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።
¹⁷ መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤
¹⁸ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።
¹⁹ እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።

ኤርሚያስ ክፍሌ

react And Share
@Kegetemku_leyesus

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:22


የሚረዳ ...ሚረዳኝ....

እኔ እራሱ እኔን ሲዉጥ
ሳለቅስ ሳይ ብዙ ሳምጥ
ስደገፈዉ ጎኔ ሲለምጥ
አለኝያልኩት እንደ ጤዛ
ሸንበቆነዉ ሰዉም ዋዛ።

እንደሆነ ቀድሞ አዉቆ
የሚረዳኝ ከኔጠልቆ
አንዳች የለም ምንም
ማንም!

የሚረዳኝ የሚገባዉ
የዉስጤ ድጥ
አንተዉ ጋርነዉ
ሩጨ ማመልጥ።


ጌታዬ ሆይ...
ይሄነን ሳይ....

ያልተረዳኝ
ልርዳሽ ቢልስ
ቢያለቅስልኝ
እንባን ቢያፈስ

የ ይምሰልነዉ ከላይ ከላይ
ለሱምለሰዉ ሲል እንዲታይ

ካንተበላይ ማን? ሊረዳኝ
ሊረዳኝስ ባለሜ ዉስጥ
አብሮኝ ሚያለቅስ አብሮኝ ሚያምጥ
ያንተ ፍቅር እንዲህ ታይቷል
ጣርህራሱ መስቀል ወጥቷል።

አንተብቻ ....

ምትረዳ ...የምትረዳኝ

ስለዚህም ከኔ አትራቅ🙏
ከፈቃድህ እንድ ጣበቅ
ያንተን በኔ ትቸ እንዳለቅ

ሆዴን ብሶት ባር ባር ሲለኝ
የሚረዳ የሚረዳ ስለሌለኝ!


ገጣሚቱ
ደስታ እሸቱ

react and share
@Kegetemku_leyesus

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:22


..........ቆስቁሰው ፍቅርህን በልቤ
ቆስቁሰው ፍቅርህን በልቤ ይብዛልኝ ፊትህን መፈለጌ
የእጅህን ሳይሆን አንተን ብቻ እንድል የሙጥኝ ብዬ
ዋናዬን እንድሰዋ ያለኝንም ሁሉ ትቼ እንድከተልህ
አው ቆስቁሰው እንደገና ልኑር አንተ እንደወደድህ
ጳውሎስ ተገልጠህለት አንተን ብቻ እንዳለ
ለእኔም ብራልኝ ልኑር ፍቅርህ በልቤ እንዳየለ
ይስሀቄን የሆነውን ላንተ እንድሰዋ
በቤትህ ፀንቼ እንድቆም እንዳላይ የዋላ የዋላ


.....አው እንደገና

በፍቅርህ አጥምቀኝ ልበስብስ ላልደርቅ
በኔ ላይ እስክትታይ ያየኝ ሁሉ በፍቅርህ እስኪደነቅ
ፍቅርህን ቆስቁሰው በልቤ ሁንበት ንጉሱ
ሁሌ እንዲፈልግህ ሆነህ የእለት ተዕለት ሱሱ
አንተን ብቻ እንድል እንድወጣ ፊትህን ፍለጋ
ጥማቴ ናፍቆቴ እንዲበረታ ፊትህን በመፈለግ ሁሌ እንድተጋ
የዚህ አለም ትርምስ ግሳንግስ
እንዳይስበኝ ካንተ አርቆ ኢየሱስ
ቆስቁሰው ፍቅርህን ውረሰው እኔነቴን
ልኑር እንደፍቃድህ በክቡር ደምህ ገዝተህኝ የለምንን🥹
ከቃልህ ልሰፋ ካንተም ልጣበቅህ
ጆሮዬንም ልክፈት ስትፈልገኝ አልታጣ ከቤትህ 🥹
ልትሰራ ስትፈልግ አለውልህ እንድልህ
ቆስቁሰው የሰማዩን ጉዳይ ሀሳህን እንድሰማህ
ካንተ ጋር ውሎ ማደር እንዲሆን በኔ ዘንድ
ጨለማው ላይ እንዳበራ ቃልህን እንድወድድ
ቆስቁሰው ፍቅርህን በልቤ
ኢየሱስ ሁንልኝ የሁሌ የሁሌ 🥰
ፋሲካ ምህረትአብ
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:21


ክፍል 28
የህይወቴ ትውስታ
የልጅነት ጊዜ

እኔም ለመሄድ ወሰንኩ እህትየዋ ተከተለችኝ
እንዴት አረገዝሽ ለማን አረገዝሽ ብለው እንኳን አልጠየቁኝም ይልቁንም አይዞሽ ባንቺ አልተጀመረም እሰይ እንደውም ልጅ ያስፈልገናል ጌታ ልጅ ሊሰጠን ነው ብለው አጨበጨቡ

እውነት ልጅ ፈልገው ወይም ደስ ብሏቸው ሳይሆን እንዳይከፋኝ እና እራሴን እንዳላጠፋ ነው ተገረምኩ

አብራኝ የነበረችዋ እህቴ ስለኔ ለማውራት ብዙ ሞከረች ቤት የሚሰማት ስታጣ ወደ ጎረቤት ሄደች ዲቃላ ይዛ መጣች በሚል
ብዙ አወራች ወደመጣችበት ተመለሰች

እኔም ሴት ልጄን ወለድኩ ወደ አባትዋ ደወልኩ ድምጿን አሰማሁት ሌላ ምንም አልፈልግም አባትነትህ እመን አልኩት አረ እቀበላለሁ የምችለውን አደረጋለሁ አለ እንደውም እመጣለሁ አለ ከዛሬ ነገ እያለ 3ወር ሆነ ያቺ አብረን የነበርነው እህቴ ወታደር አግብታ ቀለበት አድርጎላት አርግዛ ነበረና ወለደች እንደ ገና ወደ እሷ እንደ ሰራተኛ ልጄን ይዤ ወደ ወልቂጤ ሄድኩ

እሷን አረስኳት ግን በፀባይ መቻቻል አልቻልንም አንድ ቀን ብድግ ብዬ ተነስቼ ወጣሁ ማታ ማታ ልጅ የሚይዝልኝ ሰው ፈልጌ ሰጠኋትና የማታ ስራ ጀመርኩ እንደ ምንም እስከ 6ወር ጠባች ለእናቴ ወስጄ ሰጠኋት ጡቴ አበጠ ታመምኩ ናፈቀችኝ ከበደኝ ግን ሁሉም ያልፋል እና አለፈ በየ ሳምንት ወደ ልጄ እመላለሳለሁ የሚያስፈልጋት ነገር አቀርባለሁ አንድ አመት ሆናት ልደቷን አክብሬ አይኖቼ ወደ ማዶ ማየት ጀመሩ እርቄ መሄድ አማረኝ ጨከንኩ አዚያን ጊዜ በኋላ ምንም ነገር አልቸገረኝም
ቢቸግረኝም እንደ ድሮ አልሆንኩም

ለማንኛውም ፓስፖርት አወጣሁ ወደ ወጪ ሱማሌ ሄድኩ ሰራሁ በ1አመቴ በርከት ያለ ብር ይዤ ተመለስኩ ልጄን አየኋት አለበስኳት
አዝናናኋት ሆቴል ከፈትኩ መስራት ጀመርኩ እንደ ገና ከሰርኩ ምንም አልመሰለኝም እቃ ሽጬ ወደመጣሁበት ለመመለስ አሰብኩ
በመሀል ግን አንድ ነገር ትዝ አለኝ

ነገ ልጄ አባት ትፈልጋለች ስልኬን አውጥቼ ወደ አባትዋ ደወልኩ ታላቅ ወንድሙ አነሳው ማን ልበል ሰላም ነኝ የልጄ አባት በረከት ፈልጌ ነበረ አልኩት ምን የምን ልጅ ነው አላወቅሁም ነበረ አለኝ አረ ችግር የለም እኔ አስረዳሀለሁ ከ3አመት በፊት በዚ በዚ ሁኔታ ተገናኘን ድንገት አረገዝኩና ወለድኩ አልኩት
እንደ አጋጣሚ የድሮ ጓደኛዬ እሙ አብራኝ ነበረች ንግግር ትችላለች መንፈሳዊ ቃላት ጠብ እያደረገች ስለ እኔ እና ስለ ሁኔታው ነገረችው አመነ የህፃኗ ፎቶ ላኪ አለኝ አያት ከማመን አልፎ ወሰነ ኢቺማ በልጅነቱ በረከትን ነው የምትመስለው እሱ ባያምን እነረ አምናለሁ አለ አጋጣሚ ስልኩ ጠፍቶ እኔ አውጥቼው ይዤው ነው ብሎኝ የበረከትን ስልክ ቁጥር ሰጠኝ በረከትም ደወለ ደስ አለው እንዲመጣ ተቀጣጠርን አልመጣም

ከለታት አንድ ቀን ልጄን ይዤ ወደ ሆሳና ሄድኩ በራቸው ላይ ቆሚ ደወልኩ ልጁን ይዞ ገባ ለእናቱ አሳያት ተቀበለችው ተመልሰው ወጡ በነጋም ጊዜ እናትየዋ ጠራችኝ ውዬ አደርኩ ልሄድ ብዬ ስነሳ ልጅቷ ስጭኝ አለችኝ
እሺ ብዬ አለማምጃት ላያቷ ሰጥቼ ወደ ወጪ ሱማሌ ተመለስኩ እኔና የልጄ አባት አብረን መሆን እንዳለብን ተነጋገርን ስራ እየሰራሁ 2አመት ቆየሁ እየተጣላን እየታረቅን
በስልክ እያወራን ሰነበትን ከ6ወር በፊት አባቱ ሞተ ደና ገንዘብ አገኘ ሌላ ሰው ሆኖ ተቀይሮ ጥሩ ሆኖ ንስሀ ገብቶ የማላውቀው አይነት ሰው ሆኖ መምጣት አለብሽ እኔ ችላ ያልኩሽ ምንም ገንዘብ ስለሌለኝ ነበረ እያንዳንዱን ቀን እክስሻለሁ እያለ ከልጁ ጋር ሆኖ ያወረኝ ጀመረ ሙሉ ቤተሰቡ በስልክ ተዋወቅን እናትዮ መሬት ሽጣ ወንድምየው ከደቡብ አፍሪካ ገንዘብ ልኮ ምን የመሰለ ግብ ቤት ተሰራ በነገው እለት ከቀኑ 5:00 ኢትዮ እደረሳለሁ የሚል እምነት አለኝ ቀጣይ ሳምንት እንደ ትውውቅ አይነት ፕሮገራም ይዘጋጃል ወደ ቤተሰቦቼ ተያይዘን እንሄዳለን ከዚም ያለፈ እግዚያብሄር ብዙ ነገር አሳክቶልኛል መንገዴን አቀናልኝ ትላንቴን እንዳመሰግንበት አደረገው ክብር ለስሙ ይሁን

እስከ አሁን ድረስ ያለኝ የህየወት ታሪኬ ከልጅነት እስከ 26አመት ያለኝ ኢሄንን ይመስላል በጣም አመሰግናለሁ ተባረኩልኝ ተላንቴን ያስረሳኝ ጌታ አመስግኑልኝ


ተፈፀመ

react And Share
@Kegetemku_leyesus

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:21


ክፍል 27
የህይወቴ ትውስታ
የልጅነት ጊዜ

መቼም በየትኛውም አገር ሴት ልጅ ሳታገባ ስታረግዝ የሚባለው ሁላችንም እናወቀዋለን
ያንን መስማት ስላልፈለግሁ ጽንሴን ይዤ ወደ ወልቂጤ ከተማ ገባሁ

ሆቴል ገብቼ የድሮ ስራኤ ጀመርኩ ጭንቀቱ እንዳለ ነው ቀን ቀን ብሬን ዘግቼ ማልቀስ እንደቀጠለ ነው የልጄ አባት ከነ ጠፋ

እንደ ገና የቤት እቃ ተከራየሁ ልጄን እንዴት ማሳደግ እንዳለብኝ አሰብኩ ወሰንኩ ገና 6ወር
ሳይሞላኝ የሙቅ እህል አዘጋጀሁ ገበያ ስሄድ የህፃናት ልብስ ሳገኝ መገዛዛት ጀመርኩ ኢሄም
ያልፋል ብዬ አሰብኩኝ ቀን ቀን መተኛት እና ማልቀስ እንደቀጠለ ነው

ከለታት አንድ ቀን ከውጪ የመጣችዋ እህቴ ደወለች አነሳሁ አብረን ስራ እንስራ አለችኝ
እሺ በዬ ዘጋሁ ደጋግማ ደወለች ስልክ መዝጋት ጀመርኩ ለምን ብላ በሌላ ሰው አስጠየቀችኝ

ተመልሼ እንዴ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆንም ይችላል ለምን አላወራትም ብዬ አሰብኩ አወራኋት ተቀጣጠርን ተገናኘን መስራት
ጀመርን

የጀመርነው ስራ አዋጪ አልነበረም ከሰርን
እርጉዝ መሆኔ አወቀች አከሰርሽኝ ተጫወትሽብኝ ብላ ነብሴን አስጨነቅችኝ
ከፈለገች ለሊት ተኝቼ ተነሺ ብላ ትሰድበኛለች ስትፈልግ ምግብ ሰርቼ ብዪ ብዬ ሳቀርብላት ለራስሽ ብዪ ትለኛለች ሆዴ እየገፋ ሄደ
አንድ ቀን ከለሊቱ 8:00 ቀስቅሳኝ ስትሰድበኝ ኤሌትሪክ ለመያዝ ሞክሬ መልሼ ነገ እኮ ሌላ ቀን ነው ብዬ ተመልሼ ተኛሁ

አንድ ቀን ግን ወደ እናቴ ደውዬ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ እና ዘጋሁ እናቴና የመጨረሻዋ እህቴ ተደናገጡ ያለ ማቋረጥ ስልክ ደወሉ አላነሳሁም ወደ እህቴ ደወሉ ምን ሆና ነው ሰላም ብለው ጠየቁ ያለውን ነገር ነገረቻቸው
እናቴ እልልል አለች መልሳ ወደ እኔ ደወለችልኝ እህ ስላት ቀጥ ብለሽ ወደ ቤት ነይ ታስፈልጊኛለሽ አለችኝ


ይቀጥላል

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:21


እስክንድር ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ

.................ክፍል 4

ኳየሩ ወደ አዳራሽ ገባ መዝሙር እየተዘመረ የጋወኗ መጥፋት ያላሳመናት ሜርሲ የጓደኞቿን ቦርሳ መፈተሽ ጀመረች  በሚገርም ሁኔታ ጋወኗ ተገኘ...ለብሳ ስትመጣ ግን ኳየሩ መዝሙር ጨርሰው እየወረዱ ነበር ፣ወደ አዳራሹ ሳትገባ ወደ ኋላ አፈገፈገችና ወደ ጥናት ክፍል እንደገባች የሆነ ሰው ከኋላዋ ተከትሏት ገባ <<ይገርምሻል መጀመሪያውኑ እኔ ይቅርብሽ ብዬ ነበረ ፣አንቺን ከፈለኩ አይደለም ከኳየር ከቤተክርስቲያን ጭምር ላስቀርሽ እችላለሁ >>አላት ።{እስክንድር ነበር}
ሜርሲ እንባዋን መቆጣጠር አቃታት <<ቆይ በደሌ ምንድነው በፈጠረህ ንገረኝ ይሄንን ያክል ለምንድነው የምትጠሉኝ፣ደግሞ አንተ ከሁላችንም በተሻለ ምታገለግል ሆነህ እኔ ላይ የምታረገው ነገር ትክክል ይመስ......>>>አላስጨረሳትም ፣....በቃ በቃ እኔ ላይ አታላዝኚ..አለና ጥሏት ወጣ ።
ፕሮግራም አልቆ ሁሉም ወደየቤቱ ሄዶ ነበር ሜርሲ ግን አሁንም እዛው መሪሪር ሀዘን በተሞላ ስሜት ከእግዚአብሔር ጋር ሙግት ገጠመች<<እግዚአብሔር አንተ ታውቃለህ አይደል ፣ምኑ ጋር ነው ጥፋቴ ፣ሲበድሉኝ ይቅር ባልኩ፣ሲጠሉኝ በወደድኩ ፣ሲገፉኝ ባቀፍኩ ቆይ ስህተቴ ምንድነው>>እያለች እዛው ዋለች።
😪😪😪ሜርሲ ቤተክርስቲያን መምጣት ካቆመች ወራቶች አለፉ፣ግን ማንም ሰው አላስተዋለም ነበር ፣...አንድ ቀን የአገልጋዮች ስልጠና ነበረ እና መሪዎች ሁሉ ነበሩበት እና በመሀል አንድ አገልጋይ ከኳየሩ ልጆች አንዷን ጠራትን <<ሜርሲ ለምን ቀረች ዛሬ>>ብሎ ጠየቃት ፣.....ልጅቷም በእንደዚህ አለች ቀለል አድርጋ<<ተዋት ባክህ ፣ተገላገልናት ምኗምኮ አይመቸንአይመቸንም ነበረ፣ለነገሩ ከቸርች ከቀረች ቆይታለች ብቻ የትም ትሁን የት እእንኳን ቀረች>>ስትለው አገልጋዩ ደነገጠ።
ታዲያ አገልግሎታችን ምኑ ጋ ነው፣ አብሮን ያለንን ሰው እንደዚህ እየጠላን መድረክ ላይ ለመቆም ድፍረቱን ከየት አመጣን፣ደግሞስ ቆይ ከማን ነው የተማርነው መሰዊያ ላይ ትኬሻ ለትኬሻ እተለካካን የምንዘምረው፣የምንፀልየው፣የምንሰብከው፣የእውነት አገልግሎታችንን ጌታ ይቀበለዋል፣አይመስለኝም ...እያለ ለብቻው እያወራ እያለ እስክንድር መጣና ከሀሳቡ አነቃው<<ምን አጋጥሞህ ነው እንደዚህ የተጨነከው፣ጭራሽ ብቻህን እያወራህ....ሲለው አገክጋዩ እንደዚህ አለው.....

..............ክፍል 5 ይቀጥላል

Like 👍React 😍&Forward  በማድረግ ለሌሎች አዳርሱ

https://t.me/kegetemku_leyesus

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:19


ሰላም ፀጋና በረከት በያላችሁበት ዓለም ሰዓት አቆጣጠር ይድረሳችሁ

ተወዳጁ <<እስክንድር>> የተሰኘው መንፈሳዊ ልብወለድ ነገ ምሽት 2:00 ሰዓት ይቀጥላል

በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ ስለቆየ ከልብ ይቅርታ ልላችሁ እወዳለሁ

እስካሁን ያላነበባችሁት ከክፍል 1-3 ድረስ ከላይ ስላለ እንድታነቡት እጋብዛችኋለሁ

ፀጋ ይብዛላችሁ

@gechanamo

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:19


ልጨርስ አንተ ላይ

የፍቅሬን በኩር የመጀመሪያውን
ሕይወቴንም ጭምር አለኝ የምለውን
ለራሴ ሳላስቀር ሁሉንም ነገር
ልጨርስ አንተ ላይ አንድም ሳላስቀር.
የሕይወቴ ውዱ ዋጋ የምሰጠው
የቤቴ ድምቀት ዋናዬ የምለው
አይኑረኝ በፍፁም ካንተ ውጪ ሌላ
ውሰደው ሁሉንም እንዳይሆን የሌላ.
ይሰበር አንተ ላይ ያ ውድ ሽቶ
መአዛው ሰፈሩን ቤቱን ሁሉ ሞልቶ
ምንም ዋጋው ቢሆን ሶስት መቶ ዲናር
ላንተ ያንስብሃል ይሄ ሁሉ ነገር.
አባ የኔ ኢየሱስ የሕይወቴ ጀማሪ
ፍቅርን ያሳየኸኝ የታሪኬ ሰሪ
መገኛዬ ምንጩ አንተ ነህና
የዘመኔ መስራች የሕይወቴ ዋና
ፍቅሬን ሕይወቴን ሰብስቤ አንድ ላይ
አንተ ላይ ጀምሬ ልጨርስ አንተ ላይ.
ኢየሱሴ ዘልቀህ ከገባህ ወደ ልቤ ጓዳ
ልትኖር ወደህ የቤቴ እንግዳ
ላንተ ከተባለ ምንም አደርጋለው
አይደለም ሽቶውን ሕይወቴን ጭምር አፈስልሀለው.
ካንተ የጀመረ እያየ ፊትህን
ነፍሱ የተራበች ያን ክብርህን
ካንተ ውጪ ጉዳይ አይኖረውምና
ለሌላ ሚያወራው ትልቅ ዋና ዜና
እግርህ ስር ልሰንብት ልጨርስ አንተ ላይ
ወደ ዋላ ዞሬ ሌላውን እንዳላይ.
ገጣሚ ሃና መኮንን
@kegetemku_leyesus
@kegetemku_leyesus

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:19


ኢሄ ግጥም ሲፖሰት ከእኔ ጋር ሁለት ሜምበር ነበረው ቻናሉ ዛሬ 20 000 ስለ ሁሉ ጌታ ይባረክ

❤️ ለእኔ አባት እኮ ነው👍

ዘማሪው በዜማ ገጣሚው በቅኔ
ሁሉም ወድሀለው ሁሉም ሚለው የኔ

አንተኮ ፍቅር ነህ ቃላት የማይገልጥህ
እሺ ምን ልሁን ስትወደኝ ወደድኩህ

ሁሉም እንዳቅሙ ሁሉም ተራው ደርሶ
ፃድቅነህ የሚለው ትውልድ ፅድቁን ለብሶ
ለኔ አባትኮ ነው

የሰማይ ሰራዊት መላዕክቱ ሁሉ
ቀና ደፋ ብለው ቅዱስ ነህ የሚሉ

ዝቅ ከፍ ሲሉ ክብሩ እየታያቸው
ሌላ ስራ የለ አምልኮ ስራቸው
ሌላ ቃል አያውቁም ቅዱስ ነው ቃላቸው

እንዲህ በመደነቅ ሰማይ የሚያመልከው
ሌላ እንዳይመስላችሁ ለኔአባትኮ ነው

ወፎቹ በጠዋት መዝሙር ሚዘምሩት
ውሆች በአቅሜቸው የሚያሸበሽቡት
ለሱ ክብር ብለው ኮረብቶች ሚዘሉት
ለኔ አባትኮ ነው

ሰማይ አልነበረም ምድር አልነበረም
አልበቀሉም ዕፅዋት ሰውም ሰው አልሆነም
ነገር ግን ከአባቴ ምንም አልጎደለም

የኔ አባትኮ እንደዚ ድንቅ ነው
ሰማይ ወዬ ምድር አቤት ሁን ሲለው የሆነው

ብርሀናትን ፈጥሮ ደግሞ የሚመራ
ከዋክብቶችን በስም የሚጠራ

ለዱር እንስሳቱ ምግብ የሚሰጠው
ሁሉን አስገኝቶ ሁሉን የሚያዘው
የኔ አባትኮ ነው

ሙት ሆኖ የኖረ በሀጥያቱ ምክንያት
በዚ አለም ገዢ በክፋቱ ግዛት

ለሙታኖች ሞቶ ህይወትን የሰጠው
ተወዳጁ አምላክ የኔ አባትኮ ነው

አባቴ በማለት እንዲህ የማደንቀው
የኔ አባትኮ የእናንንተም አባት ነው

ኤርሚያስ ክፍሌ

React and share
t.me/kegetemku_leyesus

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:19


20 000 🙆‍♂🏆🏆 ገብተናል እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላቹ ቤተሰዎቻችን እንወዳችኃለን ተባረኩ ገና 100 000 እንገባለን እንደ ጌታ ፈቃድ

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:17


.......ለእኔ ግን ዋናዬ

ሰው ሀብቱን ያሳያል አለኝ የሚለውን
ዝናውን ያወጋል ዋና የሆነውን
ገደብ አበጅቶ ልኬቱን ለራሱ
ይሄ ከተነካ ይለናል በራሱ
ይቆጥራል ከጎሳ መገኛ አፈርን
ረስቶ ኖሯል ሰሪ እግዚአብሔርን
ለእኔ ግን ዋናዬ አንደኛ የምለው
የናዝሬቱ ኢየሱስ በመስቀል የዋለው
ያላፈረ በእኔ እርቃኑን ሲቀጣ
ውርደትን ተሸክሞ በእንጨት የወጣ
ዋና ነገሬ ነው እሱ ነው ማያዬ
አለኝ ብዬ ምለው ለአለም ማሳያዬ

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:17


ለእኔ ብርቄ የምለው

.ከሰማየ ሰማያት ከዙፋኑ የመጣ
ስልጣኑን ሳይቆጥር ከአሪያም የወጣ
ንጉሰ ነገስቱ በሰው መልክ የኖረ
ጌታ ኢየሱስ ነው ያለና የነበረ
ለኔ ብርቄ ምለው ማከማቸው ሀብቴ
ለክፉ ቀን ደራሽ መከታ ለቤቴ
እሱ ነው ዋናዬ አለኝ የምለው
ዘመን ሲለዋወጥ ፀንቶ የሚኖረው
ብቸኛ ነገር በህይወት እያለሁ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው
ምንም እተዋለሁ እጥላለሁ ከእጄ
ጌታዬን አልችልም ላርቀው ከደጄ

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:16


ኢየሱስ ባይኖርበትስ?

ዛሬ ቀን ከልጅነቴ ጀምር ያለፈብኝ እያሰብኩ ኦ ጌታ ለካ ያሳልፋል ብዬ በምስጋና ተሞላሁ

እናም እንዲህ ብዬ አሰብኩ ባለፍኩበት የህይወት ውጣ ውረድ ተስፋ መቁረጥ ብቸኝነት አለመፈለግ መቸገሬ ውስጥ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ባይሆን ህይወቴ ላይ ኢየሱስ ባይኖር ምን እመስል ነበር ብዬ አሰብኩ

በእርግጥ በህይወት ምኖር አይመስለኝም እሞት ነበር ባልሞት እንኳ ወይ እብድ ሱሰኛ ወይ ጀዝባ ሆኜ እቀር ነበር

ግን ፈተናዬ ላይ ህመሜ ላይ ጌታ ስለነበረበት አስተምሮኝ እና አጠንክሮኝ አለፈ

አይገርምም ኢየሱስ እኮ ሙላታችን ነው

ማንም ያላየው ክፍተት የሞላልን ድቅድቁ ለሊት ያነጋል በቁስል የፈወሰን ድንቅ ወዳጅ ኧረ ስሙ ይባረክ

አባት አለን የሚያስመካ

ልክ ናቸው ዘማሪዎቹ እንደዚህ ያሉት

መዝሙር 124
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፦
² እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
³ ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤
⁴ በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤
⁵ በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።
⁶ ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ።
⁷ ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።
⁸ ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ስም ነው።

ኤርሚያስ ክፍሌ

react And Share
@Kegetemku_leyesus

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:15


የእግዚአብሔር እጅ ያየዘው ነገር እንዳይወድቅ አይፈራም🥰🥰

ኢየሱሴ እጄን ስለያዝከኝ ተባረክ🙏🙏

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:14


ክፍል 26
የህይወቴ ትውስታ
የልጅነት ጌዜ

ምግብ ቤቱ ገበያ የሚባል ነገር ጠፋ
ቤት ክራይ መክፈል አቃተኝ ከአንድ ሰው
3ሺ ብር ተበድሬ ኢንቨርስቲ ወዳለቤት ወደ
አብቾ ከትምህርት ቤቱ ፊት ለፊት ቤት አገኘሁና
ገባሁ አንደኛ ሴሚስተር አልቆ ተማሪዎች ወደ
አገራቸው ገብተው ነበረ

ገና በዚ ሳምንት ይመለሳሉ በሚል ተስፋ ነበር
ቤቱን የተከራየሁት እንደ አጋጣሚ ሆኖ እረብሻ
ነበረ እና መንገድ ዝግ ሆኖ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መመለስ አልቻሉም ቤት የተከራየሁት 2ሺ ብር ነበር እጄ ላይ አንድ ሺ
ብር ቀረ

ስራ ሳልጀምር 1ወር ሆነኝ አሁንም ተማሪዎች ይመጣሉ የሚል ምንም ተስፋ የለም ምንም አይነት ብርከእጄ ጠፋ ምናልባት ብዙ ጊዜ ዞሮብኛል ብዬ
ፅፌ ይሆናል አሁን ግን የመጨረሻ ገራ ገባኝ

እናቱ እንደሞተበት ሰው ቤቴን ዘግቼ ማልቀስ ሆነ ስራዬ እንባዬ ከአይኔ እንደ ምንጭ ይፈሳል
የልጄ አባት ስደውልልት እንኳን ቆይ አንዴ እደውላለሁ እያለ ይዘጋል ከፈለገም ምን ፈለግሽ ይለኛል ከፈለገም ስልክ አያነሳም ሰፈር
ከቀየርኩ በኋላ ጭራሽ አልተገናኘንም

እርግዝናዬ ከ4ወር አለፈ አንድ ጅባስ ሽጬ
ድሮ የማውቃቸው የቡና ቤት ጓደኞቼ ጋርወደ ወሊሶ ሄድኩ በዝያ የማውቃት አንድ ፋርማሴ የምትሰራ የምግባባት የምወዳት ሴት ነበረች

ቀለል አድረጌ እንደዚ አልኳት ገኔ የወር አበባዬ ቀረብኝ መሰለኝ የሆነ መዳኒት እንዳለ አውቃለሁ ሲጭኝ አልኳት ስንት ወር ይሆናል አለችኝ 1ወር አልኳት እድትሰጠኝ ነው እሺ በዚ ሆኔታ አይሰጥም አንድ ወር ከሆነ ብቻ ነው መውሰድ የምትቺ አለችኝ እሺ ብዬ ወደ አንዲቷ
ጓደኛዬ ሄድኩና ተደብቄ መዳኒቱን ወሰድኩ

ወዲያው አስመለሰኝ ሆዴ ተገለባበጠ እንደ ማማጥ አደረገኝ ወገቤ ቀና ብዬ መሄድ አልቻልኩም ጓደኛዬ ማታ ወደ ስራ ሄደች እኔ እንዲሁ እያለቀስኩ እየጮሁኩ አደረኩ ለሊት ተነስቼ ወደ ህክምና መሄድ ጀመርኩ ከነበርኩበት ሰፈር እስከ አስባልት ለመውጣት
ሶስት ጊዜ ቁጭ አልኩ ጤና ጣበያ ደረስኩ ያለውን ነገር አንድ ሳልዋሽ ለዶክተር ነገርኩት ፅንሱ በሆድሽ ሞቷል አሁን ኢሄንን የምትሰራ ዶክተር ዛሬ አልገባችም ወደዛ ወደዚ አትበይ

እንዳትሞቺ ቶሎ ወደትልቅ ሆስፒታል ሂጂ አለኝ ወደ ትልቅ ሆስፒታል ለመሄድ ብር ያስፈልገኛል
ወደ ሆሳዓና እንደ ምንም እእእእእ😭😭 እያልኩ ሄድኩ ቶሎ ብዬ ያለኝን የምግብ ቤት እቃ በ30 ደቂቃ ሸጥኩት የቀረኝ እቃ ወደ እናቴ ቤት ይዤ ሄድኩ እንደ ምንም አደርኩ በነጋም ጊዜ ወደ አጣጥ ሆስፒታል ሄድኩ ራጅ አነሱኝ
ፅንሱ ምንም አልሆነም ሁለተኛ እንደዚ አታድረጊ ብሎ ብዙ አስፈራርቶኝ ወደ እናቴ ሄድኩ እርጉዝ መሆኔ እናቴ አላወቀችም


ይቀጥላል

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:14


ክፍል 25
የህይወቴ ትውስታ
የልጅነት ጊዜ

በነጋታው ወደ አዲስ አበባ ሄጄ የገጠመኝን
ነገርኳት እሷም ጅባሱን ትታው 5 ሺ ብር
ሰጠችኝ

አሁን ምን ልክፈት ብዬ ሰዎችን ሳማክር ጫት
መቃመያ መት ክፈቺ አሉኝ እኔ አስቤ ወስኜ
ጫት መቃመያ ቤት ከፈትኩ

በጣም አሪፍ ገበያ ነበረው በቀን ከወጪ ቀሪ
600 ብር እሰራ ነበር ከነዛ ከሚቅሙት መሀል
አንዱ ጓደኛዬ ሆነ ቀስ በቀስ ፍቅረኛዬ ሆነ

እውነት ለመናገር አፍቅሬው ወይም በሆነ ነገር
ተሸውጄ አይደለም የውሸት አፈቅርሀለሁ አልኩት እሱም እንደዛ አብረን ማሳለፍ ጀመርን
አንድ ወር ሳይሞላን አረገዝኩኝ ማርገዜን ሳላውቅ ልጁን ከኔ እንዲርቅ እኔ እንደማላፈቅረው ነገርኩት ለምን ሲለኝ በቃ
ተወኝ እኔ በሌሎች ወንዶች ተበድያለሁ
ወንድ የተባለ መበቀል ነው የምፈልገው አልኩት

የሆነ ቀን አማላጅ ልኮ አስታርቁኝ እኔ በጣም
ነው የምወዳት አለ ሰው መጥቶ ታረቁ ሲሉኝ
ኸረ በህግ እኔ ሲጀመር ወድጄው አይደለም
ከኔ እራቅ በሉት አልኳቸው ያልኳቸውን ሄደው
ነገሩት

ከዛ የወርአበባዬ ቀረ ስጠብቅ የለም ስጠብቅ የለም ወይኔ ምን ጉድ ነው አረገዝኩ ማለት ነው
ሀኪም ቤት ሄጄ ስመረመር አርግዘሻል በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አሉ🙄 ስደነግጥ አይቶ ማስወጣት ትችያለሽ አለኝ
ኸረ በጭራሽ እኔ ማስወጣት አልፈልግም ብዬ


ወደ ቤቴ ተመለስኩ ማርገዜን ሳስብ ጉጉት አልኩ እጄን ሆዴ ላይ እያደረግሁ መቼ ነው
የምወልደው አንዴ ባየሁት እላለሁ ልጅ በጣም
እወዳለሁ አማላጅ ሲልክ እቢ ያልኩት ልጅ
መልሼ አማላጅ ላኩለት መጣ የተፈጠረው ነገር ነገርኩት አልፈልግም ሲቸግርሽ ነው እንጂ
እኔን ወደሽኝ አይደለም አለ ትቶኝ ሄደ

እንደ ገና እንገናኝ እያልኩ ለመግባባት ሞከረኩ
ይመጣል አብረን እናሳልፋለን ግን ኢሄንን እንዲ
አድርጊ ኢሄንን እንዲ አደረጋለሁ የሚል የሚያግዘኝ አይነት ሰው አይደለም ከጫት መቃመያ ቤት ወደ ምግብ ቤት ቀየርኩ

ጫት ቤቱ በጣም ስራ ነበረው ምግብ ቤቱ ደግሞ ዜሮ ነው ልጁ ሲፈልግ መጥቶ ሰላም
ብሎኝ ይሄዳል ካልፈለገ እያየኝ ትቶኝ ያልፋል
ምግብ ቤቱ ስራ ባዶ ሆነ ግራ ገባኝ በቃ
ኢሄንን ፅንስ ማስወጣት አለብኝ ብዬ አሰብኩ
ግራ ተጋባሁ አልፎ አልፎ ቸርች እሄዳለሁ
ምግብ ቤት ያከራዩኝ ሰዎች በጌታ ናቸው
አገልጋይ ሲጋብዙ ይጠሩኛል

አንድ ቀን እነሱ ቤት አገልጋይ ተጋብዞ ነበረ
ነይ ፀልዪ ብለው ጠሩኝ

በህይወት የማረሳው መልክት ተናገረኝ እንዲ አለኝ አንቺ ልጅ ለክብ ትፈለጊያለሽ አሜን
አልኩ ያቺ ውርንጭላ ታውቅያታለሽ አለኝ
አይ አላቃትም አልኩት እኔ ስለ መፅሀፍ ቅዱስ
ምንም አላውቅም ነበረና ማንም የማይፈልት
የምትራብ ስትጮህ ዝም በይ የሚሏት አንዲት
ውርንጭላ ነበረች ጌታ ኢየሱስ ፈትታቹ አምጡልኝ አለ የሚል መልክት ነገረኝ አሜን
ብዬ ተቀበልኩ

እኔ ለራሴ ግራ ገብቶኛል የምን ክብር ነው ወይ
ክብር እኔ አሁን ኢሄንን ፅንስ እንዴት ላድርገው
ላስወጠው በቃ ብዬ ስወስን በሌላ ቀን አገልጋይ ጋብዘው ጠሩኝ ለሁሉም ከፀለየ በኋላ
እንደዚ አለኝ ሁኔታ አትዪ እኔ በሰራሁት ስራ
እጅሽን አታንሺ ይላል እግዚያብሄር ከእኔና ከልጄ አባት ከእግዚያብሄር በቀር ማርገዜን የሚያውቅ የለም እኔ በሰራሁት ስራ እጅሽን
አታንሺ ምን ማለት ነው ሆሆሆሆ

ይቀጥላል

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:13


የትኛዉ ? ልምዴነዉ።

መታቀፍ በጀታ
እንዲ ሚያስለቅሰኝ
ባይኔ መንታ መንታ።

ጉልበቴን የሚያርድ
ልቤን የሚረታ።

ሰዉ አጣሁኝ ብዬ
ስነፋረቅ እራሴን አዬው
አለማወቅ ከመንገዴ
እንደዘገየዉ

ሲገባኝ....!🙄


ፀሎቴ 🙏 ይሄነዉ
ጌታ የልቤን አይን
እንዲያበራዉ

ያየሁትን ሳይሆ
ያየልኝን ላይነዉ።


ገጣሚቱ
ደስታ እሸቱ

Share And React
@Kegetemku_leyesus

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:10


.......ለመልካም ይሆናል

በሰማዩ ጌታ እምነቴ በርትቶ
ሌላ ሳይታየኝ ጨለማዬ በርቶ
ሰማይ ቤት አለኝ ደስተኛ ነኝ በምድር
የሰላሙ ጌታ ጠበቀኝ እግዚአብሔር
በፅኑ አለት ላይ መሰረትኩ ቤቴ
በማይናወጥ ድንጋይ ታንፆ ህይወቴ
ድንገት ግን አንድ ቀን ነፋስ ተነሳና
ከእጄ በተነው ያንን ሁሉ ዝና
አለኝ ብዬ ያልኩት ደማቁ ኑሮዬ
ከአይኔ ተሰወረ የሳሳሁት ጓዳዬ
መሠረቱ ታወከ ተናጠ አለቱ
ማይበገር መሳይ ከንቱ ነበር በርታቱ
ከራሴ አስበልጬ ልቤን የሰጠሁት
ለስጋ ነብሴ ብዬ ለነገ ያከማቸሁት
ተቀደደ ኪሴ ታምሶ ጣሪያው
እምነቴ ተፈተነ በአብ የነበረው
ልቤን ልብ ከዳው አይሎ ወጀቡ
ይረባኛል ያለው ሲበተን በቅርቡ
.....ለካስ....ለካስ  አሁን ገባኝ🤔🤔🤔

የምድር ባለጠግነት ሀብት ክብር ዝና
አይኔን የጣልኩበት የትምክህት ጎዳና
ሁሉም አላፊ ከንቱ ነው ረጋፊ
መሽቶ እስኪነጋ ብናኝ ነው ጠፊ
ሊወስደኝ የመጣው ያውሎ ነፋስ ክንዱ
ጠራርጎ ሊያጠፋኝ ነበረ መንገዱ
አይኔን አሻቅቤ ከተራራው በስቲያ
ረድኤቴን ሳየው ከአድማስ ወዲያ
ሰማይን የሰራ አለልኝ አባቴ
ንፋሱ ቢያይልልም ፀናችበት ህይወቴ
.......😆😆🤗🤗🤗🤗እህ
እንዳሰበው ቢሆንማ እንደመጣው
መሰረቴን መትቶ አለቱን ሲንጠው
ነበረ ሊያርደኝ ልቤን አሳስቶ
እምነቴን ፈተነ ነብሴን እጅግ ሽቶ
እኔስ ታምኛለሁ በአምባው ላይ
በለስ ባታፈራም እርሱ ነው ኤልሻዳይ
ለመልካም ይሆናል ለድል በረከት
ብኖር ደስታ ብሞትስ እርሱ ነው እውነት
እንዳየው አውቃለሁ በፅዮን ከተማ
ስጋዬ ቢደክምም አለኝ የድል ዜማ
ከትላንት በረታ እምነቴ የዛለው
ክብር በአሪያም ለፀባኦት ገናናው


በጌታሁን አናሞ

Like 👍 React 🥰❤️🔥 Forward🗣🗣↩️ Join@
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/kegetemku_leyesus

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:10


መንፈስ ቅዱስ ሆይ በውስጤ አድረህ ኢየሱስን እንዳውቅ ስለረዳኸኝ አመሰግንሀለው🙏🙏🙏

Join&share
@Ermisitsf

ከገጠምኩ ለኢየሱስ

21 Jan, 00:10


ያዕቆብ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
የምታውቁትን አድርጉ

*
2016 መጨረሻ ጀምሮ እንዲህ ብዬ መፀለይ ጀመርኩ ጌታ ሆይ

📌ቃልህ ለስብከት ሳይሆን ለህይወት (እንድኖርበት) ይግባኝ

📌ብዙ ጊዜ ጌታ የቃሉ መገለጥ ሲሰጥ ለማስተማር አስባለው ስህተት የለውም ኢሄም ልክ ነው ግን እንዳስተምር ብቻ ሳይሆን እንድኖርበትም መገለጥ የሰጠኝ

📌የእግዚአብሔር ቃል በጥልቀት ማወቅ መልካም ነው የእኔም የዘወትር መሻት ነው ግን ማወቅ ብቻ ጥቅም የለውም ባወቅ ነው መኖር እንጂ

📌ክርስትና ወደ ሀገራችን ሲገባ አባቶች የነበራቸው የቃሉ እውቀት ውስን ነበር ግን የተረዱት ጥቂቱ እውነት በህይወታቸው የተገለጠ ነበር ለዚያ ነው ተፅዕኖ ፈጥረው ያለፉት

📌እያንዳንዳችን ምን ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን ማድረግ ያለብን ግን አናደርግም

📌እንዴት ኢየሱስን ላክብር?እንዴት በመንፈስ ልሞላ? እንዴት ተፅዕኖ ፈጣሪ ልሁን? እንዴት በጥበብ ልመላለስ? እንዴት የአገልግሎቴ ፍሬ ማየት እችላለው? የሚል ጥያቄ ባነሳ መልሱ ሁላችንም ጋር አለ ማድረግ ግን ተስኖናል

ወዳጆቼ የተረዳነው የቃሉ እውነት በህይወታችን እንግለጥ የዚያኔ ነፍሳት ወደ ጌታ ይመጣሉ ወደ አለም ብርሀናችን ይወጣል ንግግራችን ብቻ ሳይሆን ህይወታችንም ማርኮአቸው ጌታን ይቀበላሉ።

²¹ ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።
²² ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።

🥰🥰🥰 እወዳችኃለው መልካም ቀን🥰🥰

ኤርሚያስ ክፍሌ

React And Share
@Kegetemku_leyesus