Addis Eyita

@addiseyita


የቢዝነስ ምስረታና ማስፋፊያ፣ የፋይናንስ አጠቃቀም ስልት፣ ሳይንሳዊ የቢዝነስ እቅድ ዝግጅትና የንግድ ስነልቡና ጨምሮ የተለያዩ ከቢዝነስ ጋር የተያያዙ ስልጠናዎችን እንሰጣለን።

አድራሻ:-ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.227
📞 0901842121 / 0978212121

Addis Eyita

23 Oct, 05:59


🔘ሃሳቦቻችንን በማደራጀት እንዴት ወደ ተግባር እንለውጣለን ?| አዲስ እይታ 

ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ👉 https://youtu.be/BMz7HbP29Ig?si=lBP5RkKRfSKRVv_k
አዲስ እይታ
ህልሞን እንተገብራለን!

📍አድራሻ:-ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.227
📞0978212121 / 0901842121

Addis Eyita

22 Oct, 09:28


🏆 ስኬታማ የስራ ፈጣሪ ለመሆን የሚያስፈልጉን ድንቅ ምክሮች
"በዋረን በፌት
"

🧍‍♂️ልዩ ሁን :- ሰው የሚያደርገውን ነገር ተመልከት ፤ ከዛም ከሁሉም ሰው በተለየ መንገድ/ እይታ ነገሮችን አድርግ ።
✍️ ነገሮችን በታጋሽነት አድርግ :- ታላላቅ ነገሮች ጊዜ ይወስዳሉ ለውጦች ጊዜ ይወስዳሉ ስለዚህም በትዕግስት ነገሮችን አድርግ ።
👉 ዙሪያህን ከአንተ በተሻሉ ሰዎች ክበብ :-አብዛኛውን ጊዜህን ከማን ጋር እንደምታሳልፍ አስተውል ።
💪 አይሆንም ማለትን ተለማመድ :-ጊዜህን የሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ አውል :: ፍሬያማ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን አስወግድ ።
🏅ስነ ስርዓት ያለው ሰው መሆን :-በዲሲፕሊን እና በመርህ መመራት ያለህን እውቀት በአግባቡ ለመጠቀም ያስችልሀል::
📚 እውቀትን ፈልግ :-ስለምትፈልገው ነገር በደንብ ሙሉ መረጃ እና እውቀት ሊኖርህ ይገባል ።
🧑‍💻 የምትወደውን ስራ ስራ : -የሚወዱትን ስራ ማግኘትና መስራት አንዱ ለስኬት የሚያበቃን መንገድ ነው ።
👏በአንድ ነገር ላይ ባለሙያ ሁን :-የተለያዩ ነገሮች ላይ ከማተኮር አንድ ነገር ላይ ማተኮር እጅግ ስኬታማ ከሚያደርገን መንገድ ውስጥ አንዱ ነው ።

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
****
አዲስ እይታ
ህልሞን እንተገብራለን!

📍አድራሻ:-ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.227
📞0978212121 / 0901842121

Addis Eyita

21 Oct, 11:31


🧦 ካልሲ የማምረት ቢዝነስ 🧦

👉 ካልሲ በሁሉም ማህበረሰብ ዘንድ ተፈላጊ የሆነ በዋናነት ክርን ተጠቅመን የምንሰራው ምርት ነው:: 
👉 በተለያየ ከለር እና ዲዛይን ማምረት ይቻላል::
👉 በቀን 7, 200 ጥንድ ወይም 600 ደርዘን የሚሆን ጥራት እና ውበት ያላቸው ካልሲዎችን ማምረት ይቻላል ፡፡
👉በወር የተጣራ 283 ሺ ብር💰💰እና ከዚያ በላይ ትርፍ ይገኝበታል::

🎯መነሻ ካፒታሉ 8.9 ሚሊየን ብር ሲሆን የዚህ 20% ማለትም 1.78 ሚለየን ብር ያለው ወደ ቢዝነሱ መግባትና በአጭር ጊዜ ትርፋማ መሆን ይቻላል።

📣ይህን አዋጭ ቢዝነስ ለመጀመር ወደ አዲስ እይታ መጥተው የቲዎሪ እና የተግባር ስልጠና ይውስዱ።
🏆 በተጨማሪም ማንኛውንም ማሽን በአዲስ እይታ በኩል ሲያስመጡ 30% ከደንበኛው ቀሪውን 70% ደግሞ አዲስ እይታ በመሸፈን ማሽኑን አስመጥቶ ያስረክባል፡፡

ለበለጠ መረጃ :
📍አድራሻ:-ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.227

📞0978212121 /0901842121           
🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♀️           
አዲስ እይታ
ህልሞን እንተገብራለን!!

በሁሉም አማራጮች ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ ።
YouTube Facebook
Telegram Tiktok
Instagram Website

Addis Eyita

19 Oct, 10:11


✍️ የቡና ጥራትን በማሻሻል የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።
የቡና ጥራት ደረጃን በማሻሻል ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻፊ ኡመር ገለጹ፡፡

ባለፉት ዓመታት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ቡናን በኩታ-ገጠም የማምረት እና ያረጁ የቡና ተክሎችን የመጎንደል ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸው÷ አሁን ላይ ምርት መስጠት መጀመራቸውን አቶ ሻፊ ገልጸዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመትም 326 ሺህ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ በማቅረብ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ዕቅድ መያዙን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ምርታማነትን ለማሳደግ የተሠራው ሥራ አመርቂ ቢሆንም ከጥራት አንጻር ግን መሻሻል የሚገባው መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው ቡና ጥራት 1ኛ ደረጃ 13 በመቶ ብቻ ሲሆን÷ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው የጥራት ደረጃ 4ኛ እና 5ኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ ለዓለም ገበያ የሚቀርበውን ቡና የጥራት ደረጃ ወደ 1ኛ እና 2ኛ ከፍ በማድረግ የተሻለ ጥቅም ለማግኘት እየተሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ከዚህም አንጻር የቡና አብቃይ አካባቢዎች ከጥራት አንጻር ያሉበትን ደረጃ በመለየት ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

📌 ምንጭ፦ ፋና ቢዝነስ

Addis Eyita

19 Oct, 10:11


✍️የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በሩብ ዓመቱ የተሻለ የኢኮኖሚ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ማድረጉ ተገለጸ።

የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፤ በተያዘው በጀት ዓመት የ8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት የማስመዝገብ ውጥን መያዙን ተናግረዋል፡፡

በ2017 የመጀመሪያው 100 ቀናት ተግባራዊ የተደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተሻለ የኢኮኖሚ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ማድረጉም ነው የተገለጸው፡፡ ይህም የተቀመጠው እድገት እንደሚመዘገብ አመላከች ነው ብለዋል።

በተለይ በወጪ ንግድ፣ በመንግስት ገቢ ፣ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና በውጭ ምንዛሬ ግኝት የተሻለ አፈጻጸም ተመዝግቧል። ከወጪ ንግድ አንጻር በተለይ በወርቅ ወጪ ንግድ እጅግ ስኬታማ ስራ መከናወኑን አብራርተዋል።

ለአብነትም በ2016 በጀት ዓመት ዓመቱን ሙሉ ወደ ብሔራዊ ባንክ የገባው የወርቅ መጠን 4 ቶን ብቻ እንደነበር የተናገሩት ሚኒስትሯ፤ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት ብቻ 7 ቶን ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባቱን ተናግረዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በአጭር ጊዜ ውስጥ ምን ያህል ለውጥ ማምጣቱን አመላካች ስለመሆኑ አብራርተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ በበኩላቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያው ሰፊ ዝግጅት ተደርጎበት በመተግበሩ ስኬታማ ሆኗል። በተለይ የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት የተከናወኑ ስራዎች በዚህ ረገድ ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በትይዩ ገበያና በባንኮች መካከል ያለው የምንዛሬ ተመን አሁን ላይ እጅግ የተቀራረበ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአጠቃላይ ያለፉት ሶስት ወራት አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚመዘገብ ያመላከተ መሆኑን ጠቁመዋል።

አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የኢትዮጵያ የገቢ መሰብሰብ አቅም እያደገ መምጣቱን የተናገሩት የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ናቸው።

በተያዘው በጀት ዓመት ተግባራዊ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እጅግ አበረታች የገቢ አሰባሰብ እንዲመዘገብ እያደረገ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

በዚህም በሩብ ዓመቱ 180 ቢሊዮን ብር ገቢ ከታክስ መሰብሰቡን ጠቅሰው፤ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ71 ቢሊዮን ብር እድገት እንዳለው ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

📌 ምንጭ :- (ኢ.ፕ .ድ)

Addis Eyita

19 Oct, 10:11


✍️ የቻይናው ኢንዱስትሪ ግሩፕ በገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን መሬት ለማልማት ተስማማ ።

የቻይናው ቾንግቺንግ ኩንኋንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ (Chongqing Kunhuang International Industry Group -CKIIG)፣ በስድስት ቢሊዮን ብር (50 ሚሊዮን ዶላር) በገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በንዑስ ተቋራጭነት መሬት ለማልማት ተስማማ፡፡

ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የንዑስ ተቋራጭ አልሚነት ስምምነት የተፈራረመው የቻይና ዓለም አቀፍ ኢንዱስትሪ ግሩፕ፣ በገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ከሚገኘው መሬት 20 ሔክታር የሚሆነውን በማልማት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እንደሚተገብር ታውቋል፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዳስታወቀው ስድስት ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ካፒታል ያለው የቻይናው ሲኬአይአይጂ እንዲያለማ የተፈቀደው 20 ሔክታር መሬት፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ይሁንታ ተሰጥቶታል፡፡

የንዑስ ተቋራጭነት አልሚነት ስምምነት የተፈራረመው የቻይናው ኩባንያ የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረት ኢንቨስትመንት ላይ መዋዕለ ነዋይ ከማፍሰስ ባሻገር፣ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ድርጅቶችን በሥሩ ጋብዞ እንዲያለሙ ማድረግ እንደሚችል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እና የቾንግቺንግ ኩንኋንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ባለድርሻና ተወካይ ቺያዎ ፌንግ ቹ፣ ማክሰኞ እለት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም. የንዑስ ተቋራጭ አልሚነት ስምምነት በኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት መፈራረማቸው ተገልጿል፡፡

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱም ወቅት ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ኅብረተሰብ ዘርፈ ብዙ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር፣ በተኪ ምርት (Import Substitution)፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ከማሳደግ አኳያ፣ እንዲሁም በአገር ውስጥ ምርት ትስስር ረገድ አስተዋጽኦው የጎላ እንደሚሆን ተብራርቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሁለት ሳምንታት አስቀድሞ በኢትዮጵያ በግል ኢንዱስትሪ ፓርክ አልሚነት ከተሰማሩ አልሚዎች ጋር የውይይት መድረክ አሰናድቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ የውይይቱ መድረኩ አንኳር ነጥብ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሚቀየሩበትን ሁኔታ የተመለከተ ነበር፡፡

ሁአጂያን፣ ውዳ፣ ጆርጁ ሹ፣ ኢስት አፍሪካ፣ እንዲሁም ኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርኮች በግል ባለሀብቶች ለምተው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሲሆኑ፣ አልሚዎቹ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ባደረጉት ውይይት የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አስመልክቶ የተቀመጠውን የሕግ ማዕቀፍ ተግባራዊ ለማድረግ የሚጠበቀውን ተፈላጊ ግብዓት እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ለማስገባት ከስምምነት ደርሰው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

📌 ምንጭ፦ ኢትዮጵያን ሪፖርተር

Addis Eyita

19 Oct, 10:11


🗞 🔎ሳምንታዊ የቢዝነስ ዜና🔍🗞

✍️ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከ5 ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን አገበያየ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኝ ነገራ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት አራት የግብርና ምርቶች ወደ ዘመናዊ የገበያ ስርአት እንዲገቡ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከአምስት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶች ማገበያየቱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከጸደይ ባንክ ጋር የክፍያ አጋርነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

ስምምነቱም አርሶ አደሮችና ኤክስፖርተሮች በመጋዘን የሚኖራቸዉን ምርቶች በማስያዝ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችላቸዉ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የግብርና ምርታና ምርታማነት ለማሳደግ ተጨማሪ የግብርና አይነቶች በብዙ አካባቢ እንዲመረቱ እንዲሁም ወደ ዘመናዊ ግብይት እንዲሸጋገሩ እየሰራ ይገኛል።


📌 ምንጭ፦ (ኢ.ፕ .ድ)

Addis Eyita

18 Oct, 12:20


 🧤 የሻወር ጓንት የማምረት ቢዝነስ 🧤

👉 የሻወር ጓንት በሁሉም ማህበረሰብ ዘንድ የሚፈለግ ክርን ተጠቅመን የምንሰራው ምርት ነው:: 
👉 በተለያየ ከለር ማምረት ይቻላል::
👉 በቀን 2,720 ጓንቶችን🧤 ማምረት ይቻላል ፡፡
👉በወር 317ሺ ብር💰💰እና ከዚያ በላይ የተጣራ ትርፍ ይገኝበታል::

🧿መነሻ ካፒታሉ 4.5 ሚሊየን ብር ሲሆን የዚህ 20% ማለትም 900 ሺ ብር ያለው ወደ ቢዝነሱ መግባትና በአጭር ጊዜ ትርፋማ መሆን ይቻላል።

📣ይህን አዋጭ ቢዝነስ ለመጀመር ወደ አዲስ እይታ መጥተው የቲዎሪ እና የተግባር ስልጠና ይውስዱ።
🏆 በተጨማሪም ማንኛውንም ማሽን በአዲስ እይታ በኩል ሲያስመጡ 30% ከደንበኛው ቀሪውን 70% ደግሞ አዲስ እይታ በመሸፈን ማሽኑን አስመጥቶ ያስረክባል፡፡

ለበለጠ መረጃ :
📍አድራሻ:-ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.227
📞0978212121 /0901842121           
🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♀️           
አዲስ እይታ
ህልሞን እንተገብራለን!!
በሁሉም አማራጮች ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ ።
YouTube Facebook Telegram
Tiktok Website

Addis Eyita

18 Oct, 06:45


Addis Eyita pinned «እጅግ አዋጭ በወር 777ሺ ብር💰💰እና ከዚያ በላይ💰💰የተጣራ ትርፍ የሚገኝበት ቢዝነስ..📈!📊  🍅 🍟 ካቻፕ የማምረት ቢዝነስ 🍅 🍟 👉 ካቻፕ በቀላሉ ቲማቲምን ተጠቅመን የምንሰራው የምርት አይነት ነው፡፡  👉 ጥሬ እቃውም በሃገር ውሰጥ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚገኝ በዚህ ቢዝነስ ላይ በመሰማራት ትርፋማ መሆን ይቻላል ። 👉 ካቻፕ በከፍተኛ ካፒታል የሚሰራ ሲሆን በካፌና ሬስቶራንቶች እጅግ ተፈላጊ እና ምግብን…»

Addis Eyita

17 Oct, 13:21


🧹መጥረጊያ የማምረት ቢዝነስ 🧹

ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ👉https://vm.tiktok.com/ZMhPkDLFT/

አዲስ እይታ
ህልሞን እንተገብራለን!

📍አድራሻ:-ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.227
📞0978212121 / 090184212

Addis Eyita

16 Oct, 09:26


እጅግ አዋጭ በወር 777ሺ ብር💰💰እና ከዚያ በላይ💰💰የተጣራ ትርፍ የሚገኝበት ቢዝነስ..📈!📊

 🍅 🍟 ካቻፕ የማምረት ቢዝነስ 🍅 🍟

👉 ካቻፕ በቀላሉ ቲማቲምን ተጠቅመን የምንሰራው የምርት አይነት ነው፡፡ 
👉 ጥሬ እቃውም በሃገር ውሰጥ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚገኝ በዚህ ቢዝነስ ላይ በመሰማራት ትርፋማ መሆን ይቻላል ።
👉 ካቻፕ በከፍተኛ ካፒታል የሚሰራ ሲሆን በካፌና ሬስቶራንቶች እጅግ ተፈላጊ እና ምግብን አጣፍጦ ለመብላት የሚያገለግል ተፈላጊ ምርት ነው ።
👉 በቀን 1 ቶን ካቻፕ ማምረት ይቻላል ፡፡
🔊  ይህን አዋጭ ቢዝነስ ለመጀመር የሚያስፈልገው :-
መብራት ፡ - 3 ፌዝ
ቦታ - 300 ካሬ ሜትር
የሰው ሃይል - 5 ሰው
ጥሬ ዕቃ፦
🍅 ቲማቲም ፣የተፈጨ ስኳር ፣ አቼቶ ፣
🌶ስፓይስ ፣ 📦 ማሸግያ ከነ ሌብል
ማሽኖች :-
✔️ መልቀሚያ ማሽን (sorting machine)
✔️ ማጠብያ ማሽን (bubble cleaning machine)
✔️ ማሞቂያ ማሽን (tubular preheating machine)
✔️ ፐልፒንግ ማሽን (Pulping)
✔️ ማጠራቀሚያ ታንክ (storage tank)
✔️ ፓንፕ (pump)
✔️ ስቴራላይዚንግ ማሽን (sterilization machine)
💡ይህን አዋጭ ቢዝነስ ለመጀመር ወደ አዲስ እይታ መጥተው የቲዎሪ እና የተግባር ስልጠና ይውስዱ።በብቁ ባለሙያዎች ድጋፍ እና ክትትልም በመታገዝ የስኬትዎን መንገድ ይጀምሩ!!!

🔘መነሻ ካፒታሉ 7.6 ሚሊየን ብር ሲሆን የዚህ 20% ማለትም  1.5 ሚሊየን ብር ያለው ወደ ቢዝነሱ መግባትና በአጭር ጊዜ ትርፋማ መሆን ይቻላል።

💡ይህን አዋጭ ቢዝነስ ለመጀመር የሚያስችል በቂ ስልጠና በአዲስ እይታ በመውሰድ በብቁ ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ዛሬውኑ ቢዝነሱን መጀመር ይችላሉ!
🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♀️           
አዲስ እይታ
ህልሞን እንተገብራለን
!!

📍አድራሻ:-ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.227
📞0978212121 / 0901842121
በሁሉም አማራጮች ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ
YouTube Website       
Facebook       Twitter
Telegram       Tiktok
Instagram

Addis Eyita

15 Oct, 09:42


🔑ለስኬት ቁልፉ ምንድነው ?🔑

1) ግልጽ ግቦችን ማውጣት (set clear goals)
2) ጠንካራ የሥራ ሥነ ምግባር (strong work ethic)
3) ቀጣይነት ያለዉ አካሄድ ( consistency)
4) ዲሲፕሊን
5) መስዋዕት ለመሆን መዘጋጀት (willing to sacrifice)
6) የማያቋርጥ እውቀትን ለማሳደግ ጥረት ማድረግ (continuous pursuit of knowledge)
7) የማዳመጥ ችሎታን ማዳበር(the ability to listen)
8) ''በፍፁም አላቆምም'' አመለካከት (''I will never quit'' Attitude)
9) ግልጽ ዓላማ(having a clear purpose in life)
10) አደጋዎችን ለመውሰድ አለመፍራት(not afraid to take risks)


መልካም ቀን ተመኘን 🙏
****************

አዲስ እይታ
ህልሞን እንተገብራለን!

📍አድራሻ:-ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.227
📞0978212121 / 0901842121

Addis Eyita

14 Oct, 12:05


በከፍተኛ ካፒታል በወር 337ሺ ብር💰💰እና ከዚያ በላይ💰💰የተጣራ ትርፍ...📈!📊

     📌ሚስማር የማምረት ቢዝነስ📌

👉አዋጭነቱ በገበያ ፍላጎት ጥናት የተረጋገጠ በከፍተኛ ካፒታል ሊሰራ የሚችል ቢዝነስ
👉ሚስማር  የማምረት ቢዝነስ ከፍላጎት አንጻር ስናየው ገና ያልተነካ የቢዝነስ አይነት ነው ::
👉ሚስማር  ሀገር ውስጥ በሚገኝ ጥሬ እቃ የሚሰራ ነው።
👉ዋና ጥሬ ዕቃው የስታፋ ብረት ሲሆን በቀን ከባለ3- ባለ15 ቁጥር ያላቸው 3000 ኪ.ግ ሚስማሮችን ማምረት ይቻላል ፡፡
🔊  ይህን አዋጭ ቢዝነስ ለመጀመር የሚያስፈልገው :-
መብራት ፡ - 3 ፌዝ
ቦታ - 150 ካሬ ሜትር
የሰው ሃይል - 5 ሰው
ማሽኖች :-
     ✔️ ማቅጠኛ ማሽን
     ✔️ ሚስማር መስርያ ማሽን
     ✔️ ጫፍ ማውጫ እና ዝገት ማስለቀቅያ
     ✔️ መበየጃ መሞረጃ እና ማጠብያ

💡ይህን አዋጭ ቢዝነስ ለመጀመር ወደ አዲስ እይታ መጥተው የቲዎሪ እና የተግባር ስልጠና ይውስዱ።በብቁ ባለሙያዎች ድጋፍ እና ክትትልም በመታገዝ የስኬትዎን መንገድ ይጀምሩ!!!

🔘መነሻ ካፒታሉ 8.5 ሚሊየን ብር ሲሆን የዚህ 20% ማለትም 1.7 ሚሊየን ብር ያለው ወደ ቢዝነሱ መግባትና በአጭር ጊዜ ትርፋማ መሆን ይቻላል።

💡ይህን አዋጭ ቢዝነስ ለመጀመር የሚያስችል በቂ ስልጠና በአዲስ እይታ በመውሰድ በብቁ ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ዛሬውኑ ቢዝነሱን መጀመር ይችላሉ!
🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♀️           
አዲስ እይታ
ህልሞን እንተገብራለን
!!

📍አድራሻ:-ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.227
📞0978212121 / 0901842121
በሁሉም አማራጮች ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ
YouTube Website
Facebook Twitter
Telegram Tiktok
Instagram

Addis Eyita

12 Oct, 10:00


🗞ለጅምላና ለችርቻሮ ንግድ ሥራ 71 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፍላጎት ማሳየታቸው ተነገረ፡፡

የውጭ ባለሀብቶች በአገር ውስጥ የጅምላና የችርቻሮ ንግድ እንዲሰማሩ የሚፈቅድ መመርያ ይፋ ከተደረገ በኋላ፣ ከሐምሌ ወር ጀምሮ 71 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፍላጎት ማሳየታቸውንና 20 ያህሉ ፈቃድ ማውጣታቸው ተገለጸ፡፡
ከሁለት ወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የኢንቨስትመንት ቦርድ፣ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ይፈቀዱ የነበሩ የንግድ ሥራዎች ለውጭ ኩባንያዎች እንዲከፈቱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

የውጭ ባለሀብቶች በጅምላና በችርቻሮ ገበያ እንዲሰማሩ የሚፈቅድ ሕግ ከወጣ በኋላ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምዝገባና ፈቃድ መስጠት ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ 21 ድርጅቶች ፈቃድ ማውጣታቸውን፣ 13 ድርጅቶች በችርቻሮ ገበያ ለመሰማራት፣ ወደ ውጭ ምርቶችን ለመላክ ደግሞ ስምንቱ ድርጅቶች መሆናቸውን የገለጹት፣ በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከፍተኛ የፖሊሲና የሕግ ጉዳይ አማካሪ ሀብታሙ ስማቸው (ዶ/ር) ናቸው፡፡

መስፍን ታፈሰና ጓደኞቹ የሕግ ቢሮ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ቁመና በተመለከተ ሐሙስ መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ጨምሮ የተለያዩ የዘርፉ ባለድርሻዎች በተገኙበት ውይይት ተካሂዶ ነበር፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከፍተኛ የፖሊሲና የሕግ ጉዳይ አማካሪው ፈቃድ ካወጡት ድርጅቶች በርካቶቹ አዳዲስ የገበያ መዳረሻ ከሚባሉ አገሮች የመጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የኩባንያዎቹን ስም ከመጥቅሰ የተቆጠቡት አማካሪው፣ ወደ ውጭ ምርቶችን ለመላክ የተመዘገቡት ኩባንያዎች በአመዛኙ በቡናና ሰሊጥ ላይ ፍላጎት አሳይተዋል ብለዋል፡፡ ወደ አገር ውስጥ ምርቶችን ለማስገባት ከተመዘገቡት ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችና የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን ጨምሮ በበርካታ ዘርፎች በአስመጪነት ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታችውን አስረድተዋል፡፡

የቀድሞው የኢቨስትመንት አዋጅ የውጭ ባለሀብቶችን ገድቦ የነበረ ቢሆንም፣ እ.ኤ.አ. በ2020 ተሻሽሎ የወጣው በመሠረታዊነት በኢንቨስትመንት ላይ ለውጥ አምጥቷል ብለዋል፡፡ አዲሱ የኢንቨስትመንት አዋጅ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ከ150 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን፣ ኩባንያዎቹም ከ2.5 ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2018 እስከ 2023 ባሉት አምስት ዓመታት የተሻለ የቢዝነስ ከባቢ በመፍጠር የሪፎርም ትግበራ፣ በ100 አጀንዳዎች 85 የሪፎርም ሕጎች ይፋ ተደርገዋል ብለዋል፡

የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ እዮብ (ዶ/ር) ባለፉት ሁለት ወራት የውጭ ምንዛሪ ገበያ መር በመደረጉ ለውጭ ገበያ የሚላከውን ምርት ማሳደጉን፣ የሃዋላ ገቢን በመሠረታዊነት እንዲጨምር ማድረጉንና ወደ አገር ውስጥ የሚገባው ምርት ግን እየቀነስ መሄዱን አስረድተዋል፡፡

በቅርቡ በአዳማ በተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የአሥር ቀናት ሥልጠናና ውይይት በፖለቲካ ችግሮች ላይ አልነበረም ያሉት ሚኒስትር ደኤታው፣ በሃርቫርድ ደረጃ የሚሰጥ ከፍተኛ ሥልጠና እንደነበርና ዋና ትኩረቱ አገልጋይ ሠራተኛ የመፍጠር እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ‹‹አገልጋይነት ምን መምሰል አለበት? አገርን እንዴት እናገልግል? በሚል የተሰጠ ሥልጠና ነበር፤›› ብለዋል፡፡


ምንጭ፡ ኢትዮጵያን ሪፖርተር

Addis Eyita

12 Oct, 10:00


🗞የቡና ጥራትን በማሻሻል የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።

የቡና ጥራት ደረጃን በማሻሻል ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻፊ ኡመር ገለጹ፡፡

ባለፉት ዓመታት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ቡናን በኩታ-ገጠም የማምረት እና ያረጁ የቡና ተክሎችን የመጎንደል ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸው አሁን ላይ ምርት መስጠት መጀመራቸውን አቶ ሻፊ ገልጸዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመትም 326 ሺህ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ በማቅረብ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ዕቅድ መያዙን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ምርታማነትን ለማሳደግ የተሠራው ሥራ አመርቂ ቢሆንም ከጥራት አንጻር ግን መሻሻል የሚገባው መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው ቡና ጥራት 1ኛ ደረጃ 13 በመቶ ብቻ ሲሆን÷ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው የጥራት ደረጃ 4ኛ እና 5ኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይ ለዓለም ገበያ የሚቀርበውን ቡና የጥራት ደረጃ ወደ 1ኛ እና 2ኛ ከፍ በማድረግ የተሻለ ጥቅም ለማግኘት እየተሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ከዚህም አንጻር የቡና አብቃይ አካባቢዎች ከጥራት አንጻር ያሉበትን ደረጃ በመለየት ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
ምንጭ፦ ፋና ቢዝነስ(ኤፍ ቢ ሲ)

🗞በቅርቡ በተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ።

👉 ከ3ሺህ 300 በላይ የቻይና ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ፣

👉 ኢስተር ኢንዱስትሪ ዞን 95 በመቶ የሚሆነው በቻይና ባለሀብቶች የተያዘ ነው፣

👉 ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ 72 የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ቀርበዋል፣

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች በዱከም የሚገኘውን ኢስተር ኢንዱስትሪ ዞን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ።

በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ዘለቀ ተመስገን እንደገለፁት፤ ለውጡን ተከትሎ በተሰሩ በርካታ ስራዎች በየጊዜው ወደኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ የሚመጡ ባለሀብቶች ቁጥር ጨምሯል።

የኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን በውስጡ 153 ድርጅቶች አሉት ከእነዚህ መካከል 95 በመቶ የሚሆነው በቻይና ባለሀብቶች የተያዘ መሆኑን የገለፁት ዶክተር ዘለቀ፤ ኢንዱስትሪ ዞኑ ካሉት የግል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

እንደ ዶክተር ዘለቀ ገለፃ፤ ከ3ሺህ 300 በላይ የቻይና ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ። በዚህም ከ325ሺህ በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል።

እንዲሁም የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እየተደረገ መሆኑን በመግለፅ፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከውጭ ለሚመጡ ባለሀብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢን የመፍጠር ስራን እየሰራ መሆኑን ዶክተር ዘለቀ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳገቶ ኩንቤ በበኩላቸው፤ በቅርቡ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ቁጥር ጨምሯል። ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር 12 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል።

ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ 72 የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች መምጣታቸውን ያነሱት አቶ ዳገቶ፤ ከእነዚህ ውስጥ 12ቱ ፍቃድ ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።

ኮሚሽኑ በባለሀብቶች ዘንድ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታትና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን ለመደገፍ በተጨባጭ መሬት ላይ ወርዶ እየሰራ መሆኑን አቶ ዳገቶ ገልጸዋል።
ምንጭ፦(ኢ .ፕ. ድ)

Addis Eyita

12 Oct, 10:00


#ቢዝነስ
       🔎ሳምንታዊ የቢዝነስ ዜና🔍

🗞ኢትዮጵያ 15ኛው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባን ታሰተናግዳለች

ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን 15ኛውን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ማካሄድ የሚያስችል ኮሚቴ ተቋቁሞ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ስብሰባው ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 1 ቀን 2017 ዓም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በ ጥቅምት 1 ቀን የኮሚቴውን የስራ እንቅስቃሴ በመገምገም ስብሰባዉ የሀገሪቱን ገጽታ ለመገንባት ከፍተኛ አበርክቶ እንደሚኖረው በመግለጽ ኮሚቴው በልዩ ትኩረት እንዲንቀሳቀስ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ፈርማ ወደ ትግበራ በመግባት ሂደት ላይ ትገኛለች። ስምምነቱ ለወጪ ንግድ ምርቶች ተገማች የገበያ እድል ለማስፋት፣ አንድ አፍሪካዊ የገበያ ሥርዓተ በመፍጠር የግሉን ዘርፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግና ቀጣናዊ ትስስሩን ለማጠናከር የሚያስችል መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታወቋል።


ምንጭ፦(ኢ ፕ ድ)

Addis Eyita

11 Oct, 09:30


⭐️ የምንወደውን ነገር እንዴት ወደ ቢዝነስ መቀየር እንችላለን ? ⭐️

በትርፍ ጊዜያችን ወይም ብዙ ጊዜያችንን አዘውትረን በደስታ የምንተገብራቸውን ተግባራቶች ወደ አዋጭ ቢዝነስ መቀየር እርስዎ ከሚያደርጉት በጣም ጠቃሚ ጉዞዎች ውስጥ አንዱ ሊሆን ይችላል። ይህን ለማሳካት እነዚህን ጠቃሚ ምክሮች እነሆ:-

1. የሚወዱትን ነገር ለይቶ ማወቅ

ማድረግ የሚወዱትን ነገር በማሰላሰል መጀመር። ይህ ከዕደ ጥበብ ሥራ፣ ምግብ ከማብሰል፣ ከመጻፍ ወይም ከጨዋታም ሊሆን ይችላል። ራስን መጠየቅ፡-
- ምን ዓይነት እንቅስቃሴዎችን እወዳለሁ?
- ምን ችሎታዎች አሉኝ?
- እነዚህ ፍላጎቶች አንድን ችግር እንዴት መፍታት ወይም ፍላጎትን ማሟላት ይችላሉ?

2. ገበያን መመርመር

አንዴ ፍላጎትዎን ካረጋገጡ በኋላ አዋጭነቱን ለመረዳት ገበያውን ይመርምሩ፡
- ደንበኞችዎ እነማን ናቸው?
- በዚህ ቦታ ውስጥ ነባር ንግዶች አሉ ወይ?
- አቀራረብህን ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

3. የቢዝነስ እቅድ መፍጠር

የንግድ እቅድ ማውጣት ግብዎን፣ ደንበኞችን እና የእድገት ስልቶችን ለመዘርዘር ይረዳል።
- ምን አይነት ንግድ መሆን ይችላል።(ለምሳሌ የምርት ሽያጭ፣ አገልግሎት መስጠት)።
- ደንበኞች ጋር ለመድረስ ምን አይነት ስልቶችን እንጠቀም?
- ንግዱን ለመጀመር ወጪዎችን እና የገቢ አቅምን ለመረዳት የፋይናንስ ትንበያዎች ማካሄድ ::

4. በትንሽ ጀምሮ እና ሃሳቦችን ማሳደግ

ሙሉ በሙሉ ከመጀመርዎ በፊት በትንሹ ለመጀመር ያስቡ፡-
- የጎን ፕሮጀክት ወይም የምርት/አገልግሎትዎን የመሞከሪያ ጊዜ።
- ከጓደኞች ከቤተሰብ እና ከቅርብ ደንበኞች የሚገኙ ግብረ መልስ ይሰብስቡ።
- አቅርቦትዎን ለማጣራት ይህንን ግብረመልስ መጠቀም።

🎉. አነቃቂ ታሪኮች. 🎉

ስሜታቸውን በተሳካ ሁኔታ ወደ ትርፋማ ንግዶች የቀየሩ ጥቂት ሥራ ፈጣሪዎች ውስጥ፡-

1. ሶፊያ አሞሩሶ
- ሶፊያ የቀን ስራ እየሰራች በ eBay ላይ የቆዩ ፋሽን ልብሶችን በመሸጥ ጀመረች ። ለፋሽን እና ለቅናሽ ግብይት ያላት ፍቅር ቢዝነስ እንድትጀምር ምክንያት ሆኗታል፣ ይህም ወደ የብዙ ሚሊዮን ዶላር የonline ላይ ስራ ፈጣሪ እንድትሆን አግዟታል ።

2. ፓት ፍሊን - Smart Passive income
- ፓት ፍሊን በሥነ ሕንፃ ላይ ያለውን ፍላጎት ወደ ስኬታማ የመስመር ላይ ንግድ ለውጦታል። ሥራውን ካጣ በኋላ፣ ስለ ኦንላይን ንግድ ሌሎችን በማስተማር Smart Passive ገቢ እንዲፈጠር አድርጓል።

4. ራቸል ሆሊስ - The chic site
- ራቸል የምግብ አሰራር እና የአኗኗር ዘይቤ ፍቅሯን ለመካፈል ብሎግ ጀምረች። በምታቀርባቸው ይዘቶት መጽሃፎችን እና አነቃቂ ንግግሮችን ጨምሮ የተሳካ የምርት ስም አስገኝታለች።ይህ ሁሉ የህይወት ልምዷን ለመካፈል ካላት ፍላጎት የመነጨ ነው።

ፍላጎትህን ወደ ትርፍ መቀየር ትጋትን፣ ጥናትን፣ እና ከተሞክሮ ለመማር ፈቃደኛነትን የሚጠይቅ ጉዞ ነው።
እነዚህን መንገዶች በመከተል እና ስኬታማ ከሆኑ ስራ ፈጣሪዎች መነሳሻን በመቅሰም, የትርፍ ጊዜ ተግባሮችዎን ወደ ትርፋማ የንግድ ስራ መቀየር ይችላሉ።
ዋናው ነገር በመንገዱ ላይ ለመላመድ እና ለማደግ ክፍት በመሆን ለፍላጎትዎ ታማኝ መሆን ነው!!

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
****************

አዲስ እይታ
ህልሞን እንተገብራለን!

📍አድራሻ:-ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.227
📞0978212121 / 0901842121