Pastor John official page🇪🇹🇪🇷 @yekal_sink Channel on Telegram

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

@yekal_sink


በዚህ ቻናል
በየእለቱ የቃል ስንቅ
አዳድስ እና ቆየት ያሉ መዝሙሮች
እናም የተለያዩ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ።



😒አይኔን አንስቼ ከሰው ላይ፣😔 ሀዘኔን ረሳው ኢየሱስን 😳ሳይ😁
ለአስተያየታችሁ http://t.me/hiyaw_kal

በዚህ ቻናል (Amharic)

በዚህ ቻናል የቃል ስንቅ ለበለይ ሀዘኔን ረሳው ኢየሱስን ምንም እንደልን ለመዝሙር እና ፕሮግራም በመላክ መዘናት ስለጠተን እናንተን እናም ታማኝ መዝሙር እናም ፕሮግራም በሰላም እናም ፍቅር ፍቅር በጣም የሚሰጥ ነው። እንቻል። በትግራይ በእናምናለር http://t.me/hiyaw_kal እንበላ።

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

19 Nov, 05:16


https://youtu.be/lWTTkpqk38M?si=aytHyg5tnyvgKp3W

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

05 Nov, 20:50


https://user266117.psee.ly/6nebxc

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

05 Nov, 04:12


https://youtu.be/sbN0nL1rtUQ?si=xdi1QAzx0NS835h4

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

28 Oct, 14:56


https://youtu.be/XTYe7IjX1Eo

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

27 Oct, 10:58


https://user266117.psee.ly/6m32mg

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

19 Oct, 10:54


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🎯 የእግዘብሔር ቃልና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች❗️
"ዋናው የእግዚአብሔር ቃል ነው" ብለው ከመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ከስጦታዎች በተለየ መጽሐፍ ቅዱስ የማስተማር ዕውቀትን በመተንተን ስጦታ ብቻ ከሚደገፉ ከተማሩ አገልጋዮች፤ እንዲሁም "ዋናው የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ስጦታዎች መገለጥ ነው" በማለት በእጃቸው ከሚገለጠው አንዳንድ ምልክቶች የተነሳ ከእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት ጋር ሊያፋቱን ከሚከጅሉ ካልተማሩ አገልጋዮች እጅግ እንጠንቀቀ። ሚዛንን የሳቱ ሚዛን እንዳያስቱን እንጠንቀቅ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ በቁንጽል መረዳትና ልምምድ ላይ ቆመን መጽሐፉንና ደራሲውን የማለያየት እብደት ውስጥ አንዳንገባ እጅግ እንጠንቀቅ። ለራስ ግራ ተጋብተን ትውልዱንም ግራ አናጋባ። በትህትና፣ በፍቅርና በወንጌል ላይ ትኩረት በማድረግ እንጂ በውድድር ሜዳ እግዚአብሔር አይገኝም። በዚህ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ትምህርትና የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ስጦታዎች ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እኩል ስለሚያስፈልጉን ሁሉንም የሰጠን ጌታ ይባረክ። ሚዛናዊነት❗️

✍️ እውነት በቃሉ እንጂ በትፎዞ ብዛት አይጸናም❗️
ወንድማችሁ
ወንጌላዊ ጸጋአብ በቀለ

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

12 Oct, 11:54


https://user266117.psee.ly/6jrsz9

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

09 Oct, 01:11


ይህ ዛሬ በጸጋና በምሕረት ስም ቅይጥነትን (የጣዖት አምልኮ) በቤተ ክርስቲያን እያካሄድን ላለነው ብርቱ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ ቃሉም "አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና" (ሮሜ. 15፡4) ይላልና፡፡ በአዲስ ኪዳንም በቅይጥነት ላይ የእግዚአብሔር አቋም በፍጹም አልተለወጠም፡፡

በምሕረትና በጸጋ ስም በቤቱ ንግድ ላይ የተሰማራን፤ ባሕልና ወንጌል እየቀየጥን ሁሉ 'አማረሽ' የሆን፣ ለመኖር ብለን መንጋውን ማስጠንቀቅ እንቢ ብለን ዳር የያዝን መረን የወጣን መሪዎች፣ አካላችን በቤቱ ልባችን በዓለም እመታ ባለ መንታ ልቦች፣ ነገሮችን እያቀላቀልን ግራ ተጋብትን ግራ እያጋባን ያለን አምቢተኞች ምርጫችን ሁለት ነው፡፡ አንደኛ ንስሐ በመግባት ከእርሱ ጋር መስማማትና ከልብ መመለስ፡፡ ሁለተኛ እንቢ በማት በቅይጥነት መቀጠል። "ለእያንዳንዳም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።"(ራእ.22: 12) ያለው የዘራነውን ልያሳጭደን ፈራጅ በደጅ ቆማዋል፤ ስለዚህ ለእንቢታችን ፍሬ ለሆነው ጥፋትና ቅጣት እንዘጋጅ፡፡ ጌታ ይርዳን!

ከትልቅ ፍቅርና ትህትና ጋር የቀረበ
ወንጌላዊ ጸጋአብ በቀለ
🔥🔥🔥🔥🔥🔥

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

09 Oct, 01:11


🎯 የቅይጥነት መጨረሻ ብሕራዊ ቀውስ ነው❗️
(ዋና ክፍል 2ነገ. ም 17)

🔥 ሃይማኖታዊ ቅይጥነት ምንድነው?
The American Heritage Dictionary ቅይጥነት/syncretism/ የሚለው ቃል ሲፈታው፡- ሁለት በፍጹም የማይታረቁ እምነቶች ወይንም እሳቤዎች አንድ ላይ ለማስኬድ የሚደረግ ጥረት" ይለዋል፡፡ ክራፍት የተባሉ ጸሐፊ ቅይጥነትን ሲገልጹ፡- ከክርስትና ጋር ግንኙነት ከሌላቸው አስተምህሮዎችና እሳቤዎችን ጋር የክርስትና መቀላቀል ሲሆን ውጤቱም ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ሃይማኖት መፍጠር ይሆናል ብሎዋል፡፡ መጋቢ. ጆን ስቶቲ ስለ ሃይማኖት ቅይጥነት ሲናገሩ፡- "የሃይማኖቶች የፍራፍሬ ብፌ" ይለዋል፡፡

አንድ ሆኖ የሁሉ መሆን፣ አቋም ቢስነት፣ አውነትና ውሸትን መቀላቀል፣ ሁሉን ለማስደሰት መጣር፣ በአንደበትና በልብ መለያየት፣ የቀያጭና .... የድህረ ዘመናዊው ትውልድ ባሕርያት ናቸው።

ለክርስቲያኖች፡- ቅይጥነት መንፈሳዊ ግልሙትና ነው፡፡
ቅይትነት በእግዚአብሔር ማንነት ላይ የሚደረግ ክህደት ነው፡፡ ቅይጥነት ለእግዚአብሔር ብቻ የሆነውን አምልኮ ለፍጡር እንድናካፍል የሚያደርገን የጨለማ ሥራ ነው፡፡ ቅይጥነት እግዚአብሔርን የመናቅ ያለማመን ምልክት ነው፡፡ ቅይጥነት በእግዚአብሔር ላይ የማመጽና ለእግዚአብሔር ጀርባ የመስጠት ምልክት ነው፡፡ ቅይጥነት የእግዚአብሔርን ቃል ያለማመንና ያለማወቅ ምልክት ነው፡፡ እግዚአብሔር በቅይጥነት ላይ ይፈርዳል። ወገኖቼ ለመሆኑ በዘመናችን ያልተቀየጠ ነገረ ይኖር ይሆን?

🔥በቅይጥነት የተበከሉ አማኞች ምልክቶች

ቅይጥነት፡- ጥንትም ዛሬም ልብን ያደነድናል፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሳችንን እንድንሰማ ያስተናል፣ መንፈሳዊ ጆሮን ያደነቁራል፣ መንፈሳዊ ዓይንን ያሳውራል፤ ከእግዚአብሔር ጋር እንዳለን እያሰብን ከሕያው እግዚአብሔር ይለየናል፡፡ የቅይጥነት ብዙ ጊዜ እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ እንድንተው ወይንም እንድንክድ አያደርገንም፡፡ ነገርን በእግዚአብሔር ላይ ሌላ ደባል ጣዖት፣ ልማዶች ቀላቅለን እንድናመልክ ያደርገናል፡፡ እስራኤላውያን ስማቸው በእግዚአብሔር እየተጠራና በአንደበታቸው ስሙን እየጠሩ ለበኣል፣ ለፀሐይ፣ ለጨረቃና ለከዋክብት ይሰግዱ ነበር(2ነገ.23፡5)፡፡ ደግሞም ሕያው አምላክ እግዚአብሔርን እየተከተሉ፡- "በረጃጅሙ ኮረብታ ሁሉ ላይ በለመለመውም ዛፍ ሁሉ ታች ሐውልቶችንና የማምለኪያ ዐፀዶችን ተከሉ" (2ነገ.17፡ 10) ይላል፡፡

ዛሬም በቅይጥነት መንፈሳችን ስበከል በመንፈሱ በልባችን የነገሠውን አምላክ ቸል ብለን በፍጡር፣ በማይናገሩ ግዑዛ (ገንዘብ፣ ሥርዓት፣ ተራራ፣ ዛፍ፣ ውሃ፣ ፀሐይ፣…) ፊት እንድንበረከክ ያዋርደናል፡፡ የጣዖት አምልኮ ሲባል ብዙዎች የሆነ የተቀረጸ ምስል ፊት መስገድ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ በአዲስ ኪዳን ጣዖት ሲባል፡- ከፈጣሪ ይልቅ፣ በቁስ፣ በፍጡር ለመሪካት መከጀል በእኛና በእግዚአብሔር መካከል የሚገባ ማንኛውም ነገር ነው፡፡ ክርስቲያኖች በጣዖት አምልኮ ልወሰዱ ይችላሉ። ባይቻል ኖሮ፦ ሐዋርያው ዮሐንስ- "ልጆች ሆይ ከጣዖት ራሳችሁን ጠብቁ "(1ዮሐ.5፡21) ደግሞም ሐዋርያው ጳውሎስ 'ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ('1ቆሮ.10:14) ብለው ባላሳሰቡን ነበር። የጣዖት አምልኮ የቅይጥነት ውጤት ነው።

በዘመናችን ወንጌል ከዝና፣ ከንዋይ፣ ከሥልጣን፣ ...ጋር ተቀይጦ የለም ወይ? ወንጌላውያን በሕገ ፊት መልካችንን ለማሳመርና ድርጅታዊ ጡንቻችንን ለማፈርጠም የአስተምህሮና የልምምድ ዝንፈት ካላቸው ጋር በሕግ ተጋብተን አልተቀየጥንም ወይ? ወንጌል ከፖለቲካ ጋር አልተቀየጠም ወይ? ቤተክርስቲያን ከመቀየጥ አልፋ በብዙ መንገድ በዓለም ተጽዕኖ ሥር አልወደቀችም ወይ? ዘፈንና መዝሙር አልተቀየጠም ወይ?

🔥በቅይጥነት ልቡ የደነደነ ሕዝብ እግዚአብሔርን አይሰማም

የእግዚአብሔርን ቃል የማይሰማ ሕዝብ የሀሳቡን ፍሬ ክፉ ነገር እንደሚያጭድ "ቃሌን ስላልሰሙ ሕጌንም ስለ ጣሉ በዚህ ሕዝብ ላይ የአሳባቸውን ፍሬ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ" (ኤር.6፡19) በማለት የሚደርስባቸውን አደገኛ ነገር ይናገራል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ በቅይጥነት ኃጢአት ስለ ተበከለው የእስራኤል ሕዝብ ሲናገር፡- በ2ነገ 17 እግዚአብሔር "በነቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ" (ቁ.13) ወደ እርሱ እንዲመለሱ ለዘመናት ደጋግሞ ብናገራቸውም "አልሰሙም"(ቁ.14፣ 40) ይላል፡፡

ይህ እጅግ በጣም አሳዛኝ ታሪክ ነው፡፡ በተለይ እግዚአብሔርን አውቆ ይከተል የነበረ ሰው ከእግዚአብሔር ልቡን ስመልስ ሁሉንም ነገር ማምለክ ያምረዋል፡፡ በዚህ ክፍል እስራኤል ልጆች እግዚአብሔርን ማምለክ ሲያቆሙ፡- አጸዶችን መትከል፣ ለሰማይ ሰራዊት መስገድ፣ ልጆቻቸውን በእሳት ማሳለፍ፣ በኣልን ማምለክ፣ ምዋርተኞችና አስማተኞች ሆኑ(2ነገ. 14-17) ይላል፡፡ የዘራነውን ነገር ማጭድ የተፈጥሮም መንፈሳዊም ሕግ ነው፡፡

🔥 የቅይጥነት መጨረሻ፡- የብሔራዊ ቀውስ!

በ2ነገ. ምዕራፍ 17 የእሥራኤል ሰሜን መንግሥት በቅይጥነት ኃጢአት ውስጥ በመውደቃቸውና የእግዚአብሔርን የመታደስና የመመለስ ጥሪን ቸል በማለታቸው የደረሰባቸው፣ ግለሰባዊ፣ ቤተሰባዊ፣ ብሔራዊ፣ መንፈሳዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበረሰባዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሥነ ልቦናዊ፣ … ቀውስና ፍርድ ከዚህ በታች እንመለከታለን፡፡

✍️ ከክ.ል.በፊ በ722 ዓ.ዓ የእሰራኤል የሰሜን መንግሥት በአሦራውያን እጅ ወደቀ፡፡ ፈረሰ፡፡ የመንግሥቱና የሕዝቡም ሕሊውናና ታሪኩም አከተመ፡፡

✍️ እግዚአብሔርን አልሰማ ያለ ንጉሥ ሆሴዕ በአሦር ንጉሥ በስልምናሶር እጅ በኃይል ተማርኮ ገባሪም ሆነ (ቁ.3)፡፡

✍️ በግዞትም ቤት ማቀቀ (ቁ.4) ተዋረደ፡፡

✍️ ሰማርያ ከተማ በጠላት ተከበበች፣ የጦር አውዱማ ሆና ፈራረሰች፣ በጠላት እጅ ወደቀች (ቁ.5)፡፡

✍️ ነቢያቱን አልሰማ ያለ፣ በእግዚአብሔር ላይ ደባል አድርጎ በኣልን ያመለከ፣ በኮረብታ፣ በተራራ፣ በሜዳው ለጣዖት ያጥንና ይሰግድ የነበረው ሕዝብ ተሸነፈ፣ ተዋረደ፣ በምርኮም ከገዛ ምድሩ ተነቅሎ፣ ተበተነ በመጨረሻም ማንነቱን አጣ(ቁ.6፣ 23)

✍️ በመጨረሻም አሦራውያንና እስራኤላውያን ተቀላቅለው(እርስ በርስ ተጋብተው) ሳምራውያን የተባሉ አዲስ ቅይጥ ማንነት ያለው ሕዝብ ተፈጠረ፡፡(ዮሐ.4) ቅይጥነትን የመረጠ ሕዝብ ደብዛው ክምድር ላይ ጠፋ፡፡

ቃሉም፡- "ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፥ ከፊቱም ጣላቸው" (ቁ.18) ይላል፡፡ ደግሞም "እግዚአብሔር የእስራኤልን ዘር ሁሉ ጠላ፥ አስጨነቃቸውም፥ ከፊቱም እስኪጥላቸው ድረስ በበዝባዦች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው" (ቁ.20) ይላል፡፡

እስራኤላውያን ወደውና ፈቅደው በቅይጥነት ኃጢአት በመውደቃቸው፡- (ጣዖትን በማምለካቸው) እግዚአብሔር፡- በእስራኤል ላይ እጅግ ተቆጣ፣ ከፊቱም ጣላቸው፣ የእስራኤልን ዘር ሁሉ ጠላ፣ አስጨነቃቸው፣ አሳልፎ ሰጣቸው ይላል፡፡ ምክንያቱንም፡- ሎችንም አማልክት አምልከው ነበርና" ቁ.7። እግዚአብሔር ጣዖት አምልኮ ላይ ይቆጣል። አምልኮ ለእርሱ ብቻ ስለሆነ። በጣዖት በአምላኪዎች ላይ ደግሞ ይፈርዳል። ለዚህ ነው በቃሉ፦ "የጣዖቶቻችሁን ኃጢአት ትሸከማላችሁ" (ሕዝ. 23:49) ያለው።

🚫 🏴‍☠️ ብርቱ ማስጠንቀቂያ ለቤተክርስቲያ(ለአማኞች)❗️

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

09 Oct, 01:01


https://user266117.psee.ly/6j9py4

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

06 Oct, 12:06


https://youtu.be/oLIKvQkzMvo?si=HyoVlwSDbmgbn4j_

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

02 Oct, 19:58


https://user266117.psee.ly/6hlfzv

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

17 Sep, 18:55


https://user266117.psee.ly/6flj7v

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

14 Sep, 19:04


https://user266117.psee.ly/6fbb9b

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

13 Sep, 06:03


https://user266117.psee.ly/6f79hp

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

10 Sep, 10:19


https://youtu.be/0GofUoP4JVc

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

30 Aug, 18:15


https://user266117.psee.ly/6drwwq

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

18 Aug, 22:25


https://user266117.psee.ly/6cb798

Pastor John official page🇪🇹🇪🇷

16 Aug, 04:21


እግዚአብሔር በስራ ላይ ነው
t.me/yekal_sink