🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹 @ychanut Channel on Telegram

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

@ychanut


ሰላም ለእነዛ 🕊

በዱኣቸው ለሚያስታውሱን...ስማችንን ጠርተው ያ ረቢ ላሉ ሁሉ ይሁን። 💐

ለበጎነት በር ከስር ያለውን ይጫኑ
@ALIFCHARITY123
ሃሳብ ካለ @HASHI41

ለማስታወስ ብቻ !! (Amharic)

እንኳን ደስታ ለማመልከት! ይሁንልን ብቻ !! ሉቃሙን ከምንፈልገው እና ለማታወሳዎት በዚህ አድራሻ ላይ ያግኙ። የምንጉድን ኃሳብ ለማስታውም ምቹን ለክፍል እና ለስራ። የሚለው ይህ ጀርባ በሁለት ግንቦቶች በማገኘት ይበልጥ የሌለውን ቁጥር ለውጥና በዱኣቸው እንገልጻለን። በበጎነት በር ስር ያለው በበጎነት በር ላይ ይጫኑ @ALIFCHARITY123 የሆይ?? እና @HASHE41 ለማስታወስ እንደገና ላይ በማቀላጠፍ ስሪ ይጠቀሙ።

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

13 Jan, 18:45


🌾አብሳሪ ሁን!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿علّموا ويسّروا ولا تعسّروا، وبشّروا ولا تنفّروا﴾

“አስተምሩ፣ አግራሩ፣ አታወሳስቡ፣ አበስሩ፣ አታስደንብሩ።”
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

12 Jan, 18:53


🌾ኃይልም አሸናፊነትም የበላይነትም ሕያው በሆነው አምላክ በአሏህ በቃ..! ጠፊ የሆነው የሰው ልጅ ሰው ነውና የአምላክን ብትር የሚቋቋምበት ሃይል የለውም ። አላሁምመ ዚድድድድ
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

12 Jan, 14:40


🌾የዑለማኦቹ መልስ

**   አንድ ሰው ኢብኑ አልጀውዚ ረሂመሁሏሁ ዘንድ መጣና ‹ተስቢህ ወይንስ ኢስቲግፋር ላድርግ የቱ ይሻለኛል?› አላቸው፡፡
እርሣቸውም ‹ አንድ ሰው ልብሱ የቆሸሸ እንደሆነ ሽቶ ከመቀባት ይልቅ ማጠብ ይሻለዋል፡፡› አሉት፡፡ (ከአላህ ምህረት መጠየቅን አስቀድም፡፡› ማለታቸው ነው፡፡


**    ኢማሙ ሻፊዒይ ‹ዓሊም የማያውቀውን ጥያቄ ይጠየቃል ወይ?› ተብለው ተጠየቁ፡፡
እርሣቸውም ‹ዓሊም የሚያውቀውንም የማያውቀውንም ሊጠየቅ ይችላል፡፡ የሚያውቀውን ይመልሣል፤ የማያውቀውን ይማራል፤ ጃሂል ግን ሲጠየቅ ይቆጣል፤ ለመማርም ዝግጁ አይደለም፡፡› አሉት።

  ***  ኢማም ሻፊዕይ ‹ በእድሜ ወጣት ሆነው ሣለ ለምን ምርኩዝ ይይዛሉ?› ተብለው ተጠየቁ፡፡
እርሣቸውም ‹ መንገደኛ መሆኔን መርሣት እንደሌለብኝ እራሴን ለማስታወስ፡፡› ብለው መለሱ፡፡

**    ኢብኑ ዑመር የሚገዙትም ሆነ የሚሸጡት ነገር ሣይኖር ምን ሊያረጉ ገበያ እንደሚሄዱ ተጠየቁ ‹ ለወንድሞች ሠላምታ ለማቅረብ፡፡› ብለው መለሱ፡፡›
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

09 Jan, 19:09


🌾የሆነ ግዜ ላይ ትረጋጋለህ!! ምንም ነገር እስከማይሰማህ ድረስ።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

07 Jan, 19:57


🌾ይህች እንደ ሕፃን ልጅ የምትነሳ የምትወድቀው ነፍሴ በትዕዛዝህ ላይ መጽናት አቅቷት ባክና ሊሆን ይችላል። ግን እኮ ትወድሃለች ያ ረብ።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

06 Jan, 18:22


🌾ከምትወደው ሰው ጋር
ያለህን ግንኙነት ለመቁረጥ
ስትፈልግ‥.
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

05 Jan, 13:23


🌾ሰው ሁሉ የየዘመኑ ውጤት ነው ከተባለ ነቢዩ ሙሀመድ(ሰ ዐ ወ)ግን አይደሉም ማለት ይቻላል።እሳቸው የተገኙበት ዘመን እሳቸውን መሰል ሰብዕና ለማብቀል" ውኃና አፈሩ" አልነበረውምና።
አማን አሰፋ (ረሒመሁላህ)
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

04 Jan, 20:04


🌾 ነፍስህ በአንተ ላይ ሀቅ አላት
ዋናው እና አንገብጋቢው ዋጋዋን
ከማያውቁ ሁሉ እርቀህ መገኘቱ ነው ።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

04 Jan, 09:04


🌾እንታረቅ🙏

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

02 Jan, 19:54


🌾እንዲህ ነበር ብዬ አውጥቼ ባላወራው፣
እንዲያም ነበር ብዬ ጨርሼ ባልለው፣
ብዙ ነገር አለ ደብቄ ማለቅሰው፣
ደብቄ ሸሽጌ ርቄ የማነባው፣ አማን አሰፋ (ረሒመሁላህ)
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

01 Jan, 18:55


🌾በ 2025 ላይ የሶስተኛው ሴንቸሪ የአክሱም ስልጣኔ ላይ ተቸንክሮ መቅረት ምን ይባላል። ጭንቅላታችሁን ተጠቀሙበትና ከጦርነት የተረፉት ልጆች ይማሩበት!!!
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

29 Dec, 17:08


🌾እናንተ መራቆት መብታችን ነው ካላችሁ እኛ ደግሞ መሸፋፈን መብታችን ነው!

እህቴ ማህበረሰቡ ከሰውነት ይልቅ እንስሳነትን በመረጠበት ግዜ ላይ ነውና ያለሽው ታገሺ።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

27 Dec, 17:54


🌾" ማደግ የሚናፍቀኝ እንደነ ‘እገሊት‘ እንደነ ‘እገሌ‘ ለመሆን ሆነ ። እንደ‘ራሴ‘ መሆን መኖሩን የማውቅበት ስንዝር የሀሳብ ክፍተት አልነበረኝም ። እገሊትና እገሌን ለመሆን ስኳትን ብዙ ስብርባሪ እገሌዎችን ሆንኩ ።   ሁሉንም የምሞክር ፣ ልክና ስህተትን ልክ ሆኜና ተሳስቼ የምፈትን ፣ ቀናና ወልጋዳውን ቀንቼና ተወላግጄ የማረጋግጥ ሆንኩ ። ምክንያቱም ትክክለኛ መንገድ የሚሉትን በዱላና በስድብ ሊያሳምኑኝ ሲሞክሩ እንጂ ሲኖሩት አይቼ የማላውቅ ነኛ ! .. "

ከመጽሐፍት ኣለም
በሜሪ ፈለቀ

@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

26 Dec, 19:40


🌾ከሶላት የምትሰላች ከሆነ አላህ ዒባዳህን አልወደደዉም ማለት ነው። ራስህን ፈትሽ።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

25 Dec, 19:13


🌾 የአራት ክንዷ ቤት የሁላችንም መመለሻ ናት...እንዘጋጅላት🙏
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

24 Dec, 17:34


🌾አንዳንድ ሰዎች ለአንዳንድ ሰዎች ስጦታዎች ናቸው። ጥያቄው ለሰዎች ስጦታ ነን ወይስ ስጦታ ፈላጊዎች ነን??
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

21 Dec, 20:01


🌾<እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ በእርግጥ አስረጅ መጣላችሁ፤ ወደ እናንተም ገላጭ የኾነን ብርሃን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡> ኒሳእ 174
ይህን ብርሃን (ቁርዓን) ለመግለጥ የተሳናቸው እጆች፣ ለማየት ያልፈቀዱ ዓይኖች፣ መስከን የራቀቸው ልቦች ወዮላቸው
አፈር ከለበሱ በኋላ መቆጨት...
ላይቻል ነገር ወደ መሬት ገፅ መመለስን መናፈቅ...
በጊዜ የለኝም ተልከሻ ምክኒያት ያሳለፍነውን ጊዜ መርገም... ከንቱነት እንዳይሆንብን..
ብቻ እኔ እንጃ 😭
በዱዓ❤️
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

20 Dec, 18:29


🌾'ባሪያዉ ባይገባዉም'

እዝነቱ ይቀጥላል !........ያወዱድ
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

19 Dec, 12:29


🌾የማይተውህ አላህ ብቻ ነው ስለ ሰዎች አትጨነቅ።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

18 Dec, 17:58


🌾ሚዛኗን የሳተች የግፍ ምድር!!


አብሽሩ የአላህ እርዳታ ቅርብ ነው።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

17 Dec, 18:01


🌾በአላህ የምታምን ልብ ሀዘን አይገባትምና ፈገግ በል🙏
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

16 Dec, 18:37


🌾"ስታድግ ይገባሃል" ከተባለከው ውስጥ ስንቱ ገብቶሃል?? ካልገባህ ገና አላደክም።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

15 Dec, 19:10


🌾“ጌታዬ! ኃጥያት ባይኖርብኝ ቅጣትህን አልፈራም ነበር። ቸርነትህን ባላውቅ ኖሮ ደግሞ ምንዳህን አልከጅልም ነበር።”
ወደድኩት ይህን ዱዓ…
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

14 Dec, 18:51


🌾ይቅርታው ይፀናል፤ ግና ወዳጅነቱ እንደነበር እንዴት ሊመለስ ይችላል??

#ይቅርታ ቢደረግም ወዳጂነትን ቀድሞ እንደ ነበረ መመለስ ግን አይቻልም!!
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

13 Dec, 19:44


🌾ዓለም ሁሉ የሱ ነች።
እኛም ባሮቹ ነን።
ከቁጣህ አይሁን እንጂ
ጌታዬ እንደሻህ አርገን።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

10 Dec, 20:26


🌾ለሰዎች ጥላቻን ማሳየት ከጀመርክ በቃ ተሸንፈሃል።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

07 Dec, 19:50


🌾“ልብ የልብን ጠረን ያሸታል” ይላሉ ኢብነል ቀይዪም። አንዳንዴ መውደድ የልብ ትውውቅ ነው። ብዙ ያላወራኸውን፣ ብዙም የማታውቀውንና ምንም ያላደረገልህን ሰው እንዲሁ ትወደዋለህ። "ለምን ወደድከኝ?” ብለህ ምክንያት ብትጠይቅ ምክንያት የማይነግርህ ብዙ ወዳጅ አለ።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

07 Dec, 19:34


🌾"ልብህ እንዲለሰልስ ከፈለክ የተቸገሩትን መግብ የየቲሞችን እራስ ዳብስ።" (የውዱ ነብይ መልእክት)
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

02 Dec, 19:47


🌾በቸገረህ ጊዜ ሰዎች ከጎንህ ላለመቆም ምክንያት እየደረደሩ ሲሸሹህ አብሽር እኔ ከጎንህ ነኝ አለሁልህ ያለህን ሰው ፈፅሞ አትርሳ እርሱ እውነተኛ ወዳጅህ ነውና።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

30 Nov, 19:40


🌾 አልሓምዱሊላህ!!
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

29 Nov, 18:41


🌾ከሞት ይልቅ መኖር የሚያስፈራበት ግዜ ላይ ደርሰናል። ግና አብሽሩ መሽቶ አይቀርም ይነጋል።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

28 Nov, 19:47


🌾«ለምትጎነጨው ውሃ እንኳን ቢሆን ከሰዎች ፈላጊ ሆነህ በቀረብካቸው ቁጥር፤እነርሱ ዘንድ የሚኖርህም ክብር በዚያው ልክ ይወርዳል»።

ሸይኩል ኢስላም ኢብን ተይሚያ (ረሂመሁላህ)
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

28 Nov, 18:15


🌾ማጣት ማለት ሙታኖችን ማጣት ነው እንጂ
በህይወት ያሉትማ ይተካካሉ ።
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

26 Nov, 18:12


🌾 አንዳንድ ሰዎች እንደ ሲጋራ ናቸው የወደዳቸውን የሚገሉ። ወዳጅ ተወዳጅ ሁናችሁ ዝለቁልኝ👏
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

25 Nov, 18:00


🌾 አምስት ናቸው!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿حَقُّ المُسْلِمِ على المُسْلِمِ خَمْسٌ: رَدُّ السَّلامِ، وعِيادَةُ المَرِيضِ، واتِّباعُ الجَنائِزِ، وإجابَةُ الدَّعْوَةِ، وتَشْمِيتُ العاطِسِ﴾

“ሙስሊም በሙስሊም ላይ ያሉት መብቶች አምስት ናቸው። ሰላምታ ባቃረበልህ ግዜ ሰላምታውን ልትመልስለት፣ ሲታመም ልትጠይቀው፣ ጀናዛውን ልትሸኝ፣ ለግብዣ ጥሪ ባደረገልህ ግዜ ልትሄድ። አስነጥሶት አላህን ካመሰገነ ‘አልሀምዱሊላህ ካለ’ ምህረት ልትጠይቅለት።”
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

23 Nov, 18:28


🌾 ጀሊሉ ወደ ጀልባው ከመራህ እንዳትሰምጥ መቅዘፉ ያንተ ድርሻ ይሆናል። አስተንትን...
@ychanut

🌷ለማስታወስ ብቻ !!🌹

22 Nov, 19:02


🌾መክፈል የማይቻሉ ብድሮች አሉ!! በህይወት ዘመናችን ፈፅሞ የማንከፍላቸው።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

21 Nov, 18:36


🌾 በድቅድቅ ሌሊት፣
በባህር ጨለማ፣
በዓሳ ሆድ ዉስጥ ተሁኖም ጭምር የተስፋ ጭላንጭል አለ።
ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ።

@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

20 Nov, 19:11


🌾አስተግፊሩሏህ
ሱብሐነላህ
አልሐምዱ ሊላህ
አሏሁ አክበር
ላ ኢላሀ ኢልለሏህ
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

17 Nov, 11:02


🌾 መልካም ሰዎች የቱንም ያህል መጥፎ ለመሆን ቢጥሩ አይሳካላቸውም ምክንያቱም በውስጣቸው ያለው መልካምነት መጥፎ ከመሆን ይከለክላቸዋልና።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

16 Nov, 18:11


🌾 ከኢስላም መርሆች...

﴿أَطْعِمُوا الْجَائِعَ، وَعُودُوا الْمَرِيضَ، وَفُكُّوا الْعَانِيَ﴾

“የተራበን መግቡ፣ የታመመን ጠይቁ፣ እስረኛን ፍቱ።”
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

15 Nov, 18:49


🌾 ሲርበው ብቻ የሚያውቅህ ሲጠግብ ይክድሃል ይላሉ።
ሲቸግረን ብቻ ዘመድን፣ ጓደኛን፣ ወዳጅን  ከማስታወስ አባዜ አላህ ይጠብቀን።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

13 Nov, 18:53


🌾 ወንድ ልጅ እርቃኗን በምትወጣ ሴት ሊፈተን ይችላል ለትዳር የሚመኛት ግን ሂጃብ ጠባቂዋን ነው። በሂጃብሽ ላይ አደራ👏
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

12 Nov, 20:04


🌾አስታውሱ፦ ከእለታት አንድ ቀን ከሙታን መንደር እንቀላቀላለን። መልካም መልካም እናስብ🙏
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

11 Nov, 17:22


🪿የሰው ልጅ የሀዘኑ ክምችት
ስላልታየ ብቻ ድንገት በመጣችለት
ደስታው ላይ አትመቀኝበት ።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

10 Nov, 19:43


አብሽሩ ...ጌትዬ ከጠየኩህ በላይ ነው የሰጠኽኝ የምንልበት አንድ ቀን ይመጣል። ብቻ ሶብር🤌
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

09 Nov, 19:50


ዱንያ ላይ ስትኖሩ ነገ በአኺራ ልታገኙት ከምትናፍቁት ሰው ጋር ተወዳጁ።

የዛሬ መገናኘት ምንም አይደል። የነገው ግን ትልቅ ጥፍጥና አለው።
የምወዳችሁ በምክንያት ነው❤️
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

08 Nov, 17:55


እኔ ገና ነኝ አልደረስኩም ብዬ ከሆነ ቦታ ለመድረስ አልማለሁ። ግና እኔ ካለሁበት ለመድረስ የሚያስቡ ከኋላዬ ብዙ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ።

ጌታዬ በየሕይወት እርከኖቼ ሁሉ አንተን እያስታወስኩ፣ ፀጋህን እያመሰገንኩ የምኖር አድርገኝ።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

07 Nov, 19:58


ሁሉም በጥቅሙ ልክ ነው የሚፈልጋችሁ። አንዳንድ ጊዜ ብልጥ ሁኑ። ለማይነበብ ደብዳቤ፣  ጣቶቻችሁን አታድክሙ፣ መልስ ለማይኖረው ጽሁፍ የሞባይል እስክሪናችሁን ፍቃችሁ አትጨርሱ።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

06 Nov, 17:33


ብልጥና አዋቂ ስለሆንኩ ኢስላምን አልያዝኩም፤
ሞኝና መሃይም ስለሆንኩም አልጠመምኩም።
.
ቅናቻ ከአላህ ነው
እሱ የሻውን ያጠማል
ለሻም ሰው ቅናቻን ይሠጣል።

ያ ረብ

ከሠጠኸን በኋላ አትንሳን
ከመራኸን በኋላ አታንሸራተን
ካስገባኸን በኋላ ከዲንህ አታስወጣን።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

05 Nov, 19:39


"ባለፈው ክፍለ ዘመን ብቻ በጦርነት ያለቀው ሕዝብ ብዛት ከአንድ መቶ ስልሣ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ነበር። አዎ፥ ዕውቀት አምላክን በማያውቁና በማይፈሩ ግለሰቦች እጅ ሲወድቅ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ማመዘኑ አይቀርም።"
.
“ ‘ለውጥ’ ገጽ-49”
#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

03 Nov, 17:25


በተሰበረ ልብና በደከመ ስሜት ከወዳጅ ለወዳጆች የተፃፈ ትውስታን ያዘለ ምስጋና

እነዚህ ቤቶች ላይ...

እንደ ጉርብትና መስተጋብር ብዙ ውጣ ውረዶች እንዲሁም ብዙ ሀዘንና ደስታዎች ታልፎባቸዋል። ጎረቤት ለጎረቤት ሲያዝን (ሲጨልምበት) ብርሃን ሲደሰት ደግሞ የደስታ ተካፋይ በመሆን በአብሮነት ተጋምደውና ተሳስረው ለአመታት ዘልቀውባቸዋል። ግና አሁን ትዝታና ትውስታዎች ሲቀሩ ሌላው ሁሉ ከቤቶቹ ጋር አብሮ ፈርሷል። አላህ ይታረቀን።

አሁን ያለንበት ማንነት በነዚህ ቤቶች ዙሪያ ያሉ የብዙ እናትና አባት እንዲሁም ታላላቅ ወንድምና እህቶች ልፋት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አርፎበታል። አላህ ይቀበላቸው።

ከራስ በላይ ለሌሎች መኖርን እንዲሁም ከራስ ይልቅ ሌላው ማስቀደምን የመሰሉ የኢስላም መርሆችን በተግባር የኖሩና ተግብረው ያሳዩን ድንቅ ወላጆች በነዚህ ደሳሳ ጎጆዎች ውስጥ ነበሩ... ዱኒያ አኺራቸውን አላህ በኑር ያብራው።

ይህ ተወዳጅ ማህበረሰብ በመበተኑ አዝነናል ቃላት የማይገልፁት የሆነ ሀዘን ግና... ጀሊሉ የወሰነው ሁሉ ጀሚል ነውና እንደ ሰውኛ ከማዘን ባለፍ መጥፎን አንናገርም።

ውድ ተወዳጅ ወዳጆች ፣ እናቶች፣ አባቶች፣ እህቶችና ወንድሞች መልካም አሻራችሁና ትውስታችሁ እስከ ህይወት ፍፃሜያችን አብሮን ይቆያልና ልፋታችሁ አላህ ይቀበላችሁ። አላህ ከነበራችሁበት የሄዳችሁበት የተሻለ ያርግላችሁ። ከናንተው ሀሺም !!

ለማስታወስ ብቻ !!

02 Nov, 19:01


"ብድሩን መክፈል አቅቶት የተቸገረን ሰው የእዳውን መክፈያ ያቆየለት ወይም እዳውን ያነሳለት ሰውን በትንሳኤው እለት የእሱ (የአላህ) ጥላ እንጂ ጥላ በሌለበት ቀን በአርሹ ጥላ ስር ያደርገዋል።" ረሱልﷺ
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

31 Oct, 18:24


የእናትህን ፈገግታ ማየት እስከቻልክ ድረስ ህይወትህ ውብ ከመሆኗ ገና አልተወገደችም ።

ረጅም እድሜ ለእናቶች❤️
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

28 Oct, 20:00


በድህነት የመኖርን ልምድ/አቅም (skill) ስታገኝ አትርሳው። ገንዘብ ስታገኝም በፍጥነት አኗኗር ዘይቤህን አትቀይር። NGO ገብተህ በወሩ ሀይላንድ እንጂ አልጠጣም አይባልም። ድንገት መንሸራተትም አለ🙄
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

27 Oct, 16:23


የሩሲያዎች የንባብ ባህል ይለያል ብቻ ሳይሆን ያስቀናል።
ያ ኡመተ ኢቅራእ የት ነን🤔
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

26 Oct, 17:47


ለአንዳንድ ሰው ነገሮችን ለማብራራትና ለማስረዳት ብዙ አትድከሙ። ሰዎች መስማት የሚወዱት የሚፈልጉትን ነገር ብቻ ነዉና።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

24 Oct, 18:25


Never forget your parents who gave you everything. They are the reason why you are and who you are. 🤍
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

23 Oct, 13:43


ብዙ ከዋክብት ፈላጊዎች ጨረቃ ተጽፎላቸው ይሆናል፤ግና ችኩልም አይደለን...ሶብር🤌
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

20 Oct, 17:41


ችግራችሁን እያየን ያልደረስንላችሁ ይቅርታ!
ችግራችንን እያያችሁ ያልደረሳችሁልንም ይቅርታ!
(አሌክስ አብርሃም)

ፍቅር ብቻውን መልስ የሚሆንበት ጊዜ ላይ አይደለንም።
በማንም ላይ መፍረድ ከባድ ነው። ሲቸገሩ መርዳት አለመቻል ከሚፈጥረው ህመም ለመራቅ ከምንወዳቸው ወዳጆቻችን እንርቃለን። ዓይናቸው ውስጥ ያለውን ስቃይ ላለማየት ዓይናችንን እንሰብራለን።የአቅማችንን መደገፍ እንኳን ከአቅም በላይ ሆኗል። የተወለድንበት እና ያደግንበት ስር የሰደደ አብሮነት፣ መረዳዳት አሁን እግር ከወርች ካሰረን ኑሮ ጋር አብሮ አልሄድ ብሎ አስጨንቆናል።

ረስተነው ወደወዳጆቻችን መንገድ ከጀመርን ፣ልንደውል ስልክ ካነሳን በኋላ ባዶ አይናቸው እጃችሁ ከምን ቢለንስ ብለን ተመልሰናል። ከመሄዳችን በላይ ምን ይዛችሁ መጣችሁ የሚለን አንደበታቸው ሳይሆን ኑሯቸው ሁኗል። የተጨነቀ መንፈስ፣ የተጨነቀ አየር። የማንንም እርዳታ የማይፈልጉ መንፈሰ ፅኑ ወዳጆቻችን ነገሮች ከአቅም በላይ ሆነውባቸው በዓይናቸው ባዶ ኪሳችንን ሲቃኙ ብናይ መርዳቱ ቢቀር አንታዘባቸውም። "እንትናም ተቸገረ?" ብለን አናሾካሹክም።

ይገባናል ሰው ወደገደል ቢወድቅ አዳነውም አላዳነውም አጠገቡ ያገኘውን ሳርም ይሁን ቅጠል በደመነፍስ ጨምድዶ እንደሚይዝ። ሁላችንም ገደሉ ውስጥ ነን።ልብሳችንን አንቀው የሚማፀኑን እኛም የሌሎችን ልብስ አንቀን መንጠልጠላችንን ያውቃሉ። የመያያዙ መጨረሻ፣ የገደሉ ጫፍ የት እንደሆነ ማን ያውቃል?! እጃችን እየዛለ ነው። ደመነፍስ ላይ ነን። ማንንም ለመዳን እንይዛለን በማንም እንያዛለን። ችግራችሁን እያየን ያልደረስንላችሁ ይቅርታ። ችግራችንን እያያችሁ ያልደረሳችሁልንም ይቅርታ። ሁላችንም ገደሉ ውስጥ ነን።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

20 Oct, 13:12


ልጆችን ኒቃብ ማልበስ ለእናቶች መዝናኛ ነው። አልፎም ምናልባት እንደማላመጃ ጨዋታም ይቆጥሩታል። ምናልባትም ልጆቹ በጣም ቆንጆ ሲሆኑባቸው መንገድ ሲወጡ እናቲቱ ምን ትመስል ይሆን እያሉ ለሚጨነቁ ዱርየ ወንዶችን ተስፋ ለማስቆረጥ ሊያለብሷቸው ይችላሉ።

ከዚህ በዘለለ ኒቃቢስቶች ልጆቻቸውን በተጽእኖ እንደሚያሳድጉ ለመጻፍ መመሞከር ቂልነት ነው። ልጅነታቸውን ተቀሙ የሚለው ጽንፍ የረገጠ ወቀሳ የሚያቀርቡ ሰዎች ሲፋቁ በኒቃብ መልካምነት አለማመናቸውን ማወቅ ይቻላል። ኮንፊደንስ ሲጎል ደሞ የጠላት አሽከር ያደርጋል።

የትኛዋም ኒቃቢ እናት ህጻን ልጄ ኒቃብ ይወጅብባታል አትልም። ለራሷ ያሰቃያትንም እናት ለልጇ አትቸርም። ከእናቷ በላይ ልጇን እንወዳለን ብላችሁም አታስጠሉን። እህቶቻችንን በመውቀስ ለካፒር ለማሸርገድ እና የራሳችንን ሸክ ለማከም አንሩጥ። ልጆቻቸውን በዋና ልብስ እያወጡ ለ በሽተኛ ወንድ ለሚያጋልጡ እናቶች በመከራችህ።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

19 Oct, 19:01


የአላህ ሚዛን ከፍጥረታት የተለየች ናትና ደረጃህን ጀሊሉ ዘንድ እንጂ የሰው ልጅ ዘንድ አትፈልግ።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

16 Oct, 19:06


⚡️ መጀመሪያ ለራስህ ራስህ መሆን ስትጀምር ለማን ምን መሆን እንዳለብህ ትገነዘባለህ፡፡
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

15 Oct, 19:13


ጨለማ ዉስጥ እያለን መብራት ይዘዉልን የመጡትን ሁሉ አንረሳም። የምክር፣ የአብሽር፣ የፍቅር ...መብራት ።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

15 Oct, 18:28


ሰላም ለእነዛ 🕊

በዱኣቸው ለሚያስታውሱን...ስማችንን ጠርተው ያ ረቢ ላሉ ሁሉ ይሁን። 💐
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

14 Oct, 11:54


ምስጋና ለዛ ወንጀላችንን ደብቆልን ቀና ብለን እንድንሄድ ላደረገን ጌታ።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

13 Oct, 19:48


ማታ የምትተኛው ከህሊናህ ጋር ነው፤ እንቅልፍ የሚነሳህን ስራ አትስራ።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

11 Oct, 19:57


አላህ ጊዜ ጠብቆ ይክሰናል፣ ከኛ የሚጠበቀው ታግሶና መልካም ተስፋ አድርጎ መጠበቅ ብቻ ነው።
ውዶቼ ሶብር👏
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

09 Oct, 20:00


ስንደርስበት ናቅነው እንጂ አሁን ያለንበትን የሆነ ጊዜ ላይ አላህ ጋር አልቅሰንበት ነበር ። አልሐምዱሊላህ 🤍
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

06 Oct, 20:12


የመሬት መንቀጥቀጥም ይሁን የትኛውም ወጣ ያለ ተፈጥሯዊ ክስተት ወደ ልቦናችን እንመለስ ዘንድ ማንቂያ ደወል ነው። በዚህ ዓይነቱ ጊዜ ማሾፍና መቀለድ ተገቢ አይደለም ። ልባችን ትደንግጥ። እንተዛዘን። ምን ያህል ትንሽ እና ደካማ ፍጡሮች እንደሆንን እናስተንትን። ቀልብ ሲደርቅ መዓት ቢወርድ እንኳ ምንም አይመስለውም።
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

06 Oct, 14:04


ተቀበል!

ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿أجيبوا الدّاعيَ، ولا تَردُّوا الهديةَ﴾

“ለጥሪ ምላሽ ስጡ። የተሰጣችሁን ስጦታም አትመልሱ።”
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

05 Oct, 13:40


ኡሙ ሰለማ [ረዲየላሁ ዐንሃ] እንዲህ ብለዋል: ‐
ነቢዩ [ﷺ] በአንድ ቀን ሌሊት ከመኝታቸው ነቁና እንዲህ አሉ: ‐
«ሱብሓነላህ! በዛሬ ሌሊት [አላህ] ያወረደው ፈተና እና የከፈተው ካዝና [የሚደንቅ ነው!] የጎጆዎቹን ሴቶች ቀስቅሷቸው! በዱንያ [የቆዳ ቀለም የሚያሳይ] ልብስ የለበሰች ሁሉ በአኺራ [በሚያዋርድ] ራቁት ትሆናለች!»
:
ሐዲሱን ቡኻሪይ ዘግበውታል። በቅንፍ ያስገባዃቸው ቃላት ከቃል በቃል ትርጉም ሳልወጣ የሐዲሱን መልክት ለማድረስ እንዲጠቅም በማሰብ ነው። "ጎጆዎቹ ሴቶች" የተወዳጃችን ﷺ ባለቤቶች ናቸው።
:
መልክቱ የተጨባጫችንን አደገኝነት ያሳያል። በተለይ በሰርጎቻችን ላይ ሳይለብሱ ለባሽነት በዝቷል። ሴት ልጅ በአባቷ፣ በወንድሞቿ እና በባሏ ፈቃፈኝነት እና እጀባ ሳይቀር ከደረት ጀምሮ ክፍት በሆነ ጨርቅ በአደባባይ እየተሸኘች አለን!
ሌላው ይቅር የሚያገባት የትዳር አጋሯ ሰውነቷ ለመድረክ ሲጋለጥ፣ በባለጌ አይን ሲጠቀስ እያየ ምንም እስከማይሰማው ድረስ እንዴት ሊደርስ ቻለ?!
ኧረ እርቀናል ወዳጆች!💔
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

29 Sep, 18:10


ልብህ አይፍራ
በአላህ ጥበቃ ስር ናትና::!
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

25 Sep, 20:15


{وَلاَ تَنسَوُاْ ٱلْفَضْلَ بَيْنَكُمْ}
«በመካከላችሁም ችሮታን አትርሱ።» አልበቀራ፥ 237
:
ይህ ቁርኣናዊ መልክት ስለ ፍቺ በሚያወሩ አንቀጾች መካከል የተገኘ ድንቅ ሃሳብ ነው። በፍቺ ጭቅጭቅ ውስጥ ላሉ የትዳር አጋሮች የተሰጠ ምክር ነው።

ስነምግባርን የሚዘውር፣ የሰዎችን መስተጋብር የሚያርም ክቡድ የመለኮት መመሪያ ነው። የሰዎች ነፍስ እንዲፀዳ፣ የመልካም ሰዎች ክብር ጥብቅ እና የታፈረ ይሆን ዘንድ የተሰጠ ምክር ነው!

የሰውን ውለታ አትርሳ። አንዲት ጉንጭ ውሃ እንኳን ቢሆን፣ አንድ ሲኒ ቡናም ቢሆን… ከሀዲ አትሁን! የመልካሞችን ችሮታ አትርሳ።

የራሳቸውን ግነት በሌሎች ውድቀት ላይ መመስረት እንደሚሹ ወረዳዎች አትሁን። የሰዎችን ስህተት እያደኑ ታላላቆችን ዝቅ ለማድረግ እንደሚውተረተሩ ኦናዎች አትሁን። የመልካሞችን ገፅታ ለማበላሸት ታሪክ ከሚቀጥፉት፣ ትችት ከሚነዙት በታላላቆች ግርጌ ተንጠልጥለው ካልሆነ በቀር በራሳቸው ከፍ ማለት ከማይችሉ ዝቅተኞች አትሁን!

«በመካከላችሁም ችሮታን አትርሱ።»… የሰውን ነፍስ ከፍታ የሚያንፅ ምጡቅ መልእክት ነው። የቀደመ ተሞክሮን ውበት የሚገልፅ ከፍ ያለ ተግሳፅ ነው። መልካም ንግግር፣ የቀደመ መልካም ሥራ፣ በትዝታ ውስጥ የሚታወስ በጎ አበርክቶ [ውለታ] የሚዘነጋ እንዳልሆነ የሚጠቁም ቅስቀሳ ነው።

ከሁሉም በላይ ስለሌሎች ያለን እይታ ውበት የተሞላ ሰብዕነታቸውን በሚዛናዊነት የሚያስቃኝ እንዲሆን አላህ ይመክራል። የሰብዕ ውበት ስህተቱንም ይጨምራል። በፍትህ ዐይን፣ በሚዛናዊነት፣ በምክንያታዊነት እንዲታይም ያዛል። ስለመጨረሻው ስህተት ሳይሆን ስለቀደመው ከፍታም እንድናስብ ይወተውታል!…
ለዛሬ ህይወታችን መልካም አሻራ ያኖሩ መልካሞቻችንን አላህ ባሉበት በእዝነት ሽፋኑ ይቃኛቸው!
@ychanut

ለማስታወስ ብቻ !!

22 Sep, 18:06


ካንተ የባሱ መጥፎ ለነበሩ ሰዎች፤ አንተ ከሰራሃቸው በላይ የከበዱ ወንጀሎችን ለሰሩ ሰዎች ጌታዬ ይቅር ብሏልና አንተም ተስፋ አትቁረጥ ወደርሱ ተመለስ። إنه ربى
@ychanut