ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ Telegram Posts

This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz- ይህ ገጽ የሚንቀሳቀሰው በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ አይደለም
https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ
“ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 11፥28

30,806 Subscribers
426 Photos
107 Videos
Last Updated 01.03.2025 00:50
Similar Channels

8,985 Subscribers

1,270 Subscribers
The latest content shared by ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ on Telegram
https://www.facebook.com/100089703143482/posts/588128830853883/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
ዜና ድጋሚ ኅትመት !
ሳይንስ እና ሃይማኖት
..✍ሳይንስ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን አዕምሮ ተጠቅሞ ያስገኘውና በዚህ ዓለም ያለውን የኑሮ ድካም ማቅለያው የዕውቀት ዘርፍ ሲሆን ሃይማኖት ደግሞ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘው መንገድ ነው። ነገር ግን የሳይንስን ውሱንነት ያልተረዱ ሰዎች ሃይማኖትን በሳይንሳዊ ዕውቀት ለመተንተን ሲሞክሩና ወደ ተሳሳተ ግንዛቤ ሲያመሩ ይስተዋላል። በሌላ መልኩ ደግሞ ሳይንስ ለመንፈሳዊ ሰዎች እርባና የሌለው ነው ብለው የሚያምኑም አሉ።
ይህንን በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎችና ፍልስፍናዊ አስተያየቶች፣ ጸሐፊው መምህር ያረጋል አበጋዝ፣ በዚህ መጽሐፉ ከሳይንስና ከሃይማኖት ጋር በተገናኙ ፍልስፍናዊ አስተሳሰቦች ዙሪያ ሰፊ ጥናት በማድረግ ከጥልቅ ትንታኔ ጋር አቅርቦልናል። ስለሆነም መጽሐፉን አንብበን የተሻለ ግንዛቤ እንድናገኝና እንድንጠቀምበት እየጠየቅኩ፣ ለመምህር ያረጋል ዕድሜና ጤናን ለእናንተ ለአንባብያን ደግሞ መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ቀሲስ ሰሙ ምትኩ (ፕሮፌሰር)
ቦትስዋና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ
ይህ መንፈሳዊ እና ሳይንሳዊ እሳቤዎችን የተነተነ በግሩማን ሐሳቦች የታጨቀው [የተሞላው] በመምህረ ቤተክርስትያን ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ የቀረበ ጥዑም ማዕድ[መጽሐፍ ] ለ ሁለተኛ ጊዜ የታተመ ሲሆን በግዮን መጻሕፍት ያገኙታል።# ግዮን መጽሐፍት ለመላው ከሀገር ውጪ እና ሀገር ውስጥ ለምትገኙ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲሁም የ Delivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን ።
ይደውሉልን !📞፦0913083816
፦0912198891
https://t.me/GhionBookStore1623

የቤተክርስቲያንን መብትና ጥቅም ለማስከበር እና የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየተሰራ ነው።
ጥንታዊት፣ታሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማስፋፋት በምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሌሎችን መብትና ጥቅም ባለመንካት በትዕግሥትና በማስተዋል የምትጓዝ አገራዊ ኃላፊነት የሚሰማት ሰላምን አብዝታ የምትሰብክ መንፈሳዊት ተቋም መሆኗ ይታወቃል።
ቤተክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮቷን ለማስፋፋት በተጓዘችባቸው አያሌ ዓመታት አገራችን ኢትዮጵያ የራሷ ፊደላትና የራሷ የቀን አቆጣጠር ባለቤት እንድትሆን ያስቻለች፣በሊቃውንቶቿ የመጠቀ እውቀት አማካኝነት የሥነ ጥበብ፣የሥነ ስዕል፣የዕጽዋትና የጠፈር ምርምርና ጥናቶችን በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶችን ለዓለም ያበረከተች ጥንታዊት ተቋም ስለመሆኗም አያሌ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።
ይሁን እንጂ ይህች ለአገረ መንግስት መመስረትና መጽናት፣ለእውቀት መስፋፋት፣ ለአብሮነት መጎልበት፣ ትውልድን በሥነ ምግባር ቀርጻ ፍቅርና አንድነትን በተግባር የሰበከች እናት ቤተክርስቲያን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ፣በአስተምህሮቿ፣በዕምነቷ፣በንዋያተ ቅድሳቶቿ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል።

ስለሆነም በተደጋጋሚ እየተፈጸሙባት የሚገኙትን እነዚህን እኩይ ተግባራት ከዚህ በላይ በዝምታና በትዕግስት ማለፍ መንፈሳዊ ተልዕኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ የሚያደርጋት ከመሆኑም በላይ መብቷን በእጅጉ የሚጋፋ፣ጥንታዊያን አባቶች ለሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ ሲጠቀሙባቸው የነበሩና በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ያለው ትውልድ የተረከባቸው ንዋያተ ቅድሳቶቿን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ በሥርዓተ አምልኮዋ ላይ በማላገጥ በምዕመናን ዘንድ ቁጣ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህ እኩይና ጸብ አጫሪ ተግባራት ሕጋዊ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።
ስለሆነም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ማጥናት፣መከታተልና ሕግን መሰረት ያደረገ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድግ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘችው ወቅታዊ ሁኔታውን በዝርዝር በማጥናት ተቋማዊ እልባት የሚያገኝበትን መንገድ የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ያደረገች ሲሆን የቤተ ክርስቲያናችን የሕግ አገልግሎት መምሪያም በሕግ አግባብ ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ፍትሕ ማግኘት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብና በማደራጀት ክስ መመስረት የሚያስችለውን ሁኔታ በማመቻቸት ወደ ተግባር ለመለወጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ከዚህ ጎን ለጎንም ከፍ ሲል እንደተገለጸው በጠቅላይ ቤተክህነት ከሚገኙ መምሪያዎች መካከል ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን መምሪያዎች በማካተት የተቋቋመው ኮሚቴም ዝርዝር ጥናቶችን በሚገባ በማጥናትና ችግሮቹን ለይቶ ከመፍትሔ ሀሳብ ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ በማቅረብ በቤተክርስቲያኒቱ ማዕከላዊ አስተዳደር አማካኝነት ተቋማዊ አቋም የሚወሰድበትና በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ የማያዳግም መፍትሔ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል ሥራ በመሥራት ላይ መሆኑን እየገለጸች በሁለቱም ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ በተከታታይ ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲገለጽ የምታደርግ መሆኑን ከወዲሁ እያስታወቀች በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ምዕመናንና ምዕመናት በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት የሚደረግላቸውን ጥሪ ተቀብለው ለቤተክርስቲያናችን መብት መከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እናት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ጥር ፲፯ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም

ገድለ አቡነ ጸጋ ዘአብ ወእምነ እግዚእኀረያወገድለ አቡነ ታዴዎስ ጽላልሽ
....ገድላት ኹሉን አቀፍ የመረጃ ምንጮች ናቸው። ዘመን፤ በአንድ አካባቢ፤ በአንድ ተመሳሳይ ሁኔታ የሚጓዙ አለመሆናቸው፤ በተለያዩ የዓለም ክፍል በተለያዩ ዘመናትና ጊዜያት የተነሡ የቅዱሳንን ሕይወት የተመለከቱ፤ ከምእመናን እስከ መዐርገ ጵጵስና ድረስ በተራ ዜግነት ከተሰለፉት እስከ ንጉሥነትና ንግሥትነት ደረጃ እስከ ደረሱት ድረስ ምእመናንንና ምእመናትን በእኩልነት የያዘ በመኾኑ ከሃይማኖት ጥቅሙ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰዎችን እኩልነት በማሳየቱ የበለጠ አጎልቶ ይሳያል።
❞ስለዚኽ ይኸ የካህኑ ጸጋ ዘአብ፣የብፅዕት እግዚእ ኀረያ እና የአቡነ ታዴዎስ ገድል የነፍስና የሥጋ በረከት የምንቀበልበት፤ ኹሉን አቀፍ መረጃ የምናገኝበት በመኾኑ በ፯ቱ ዕለታት በመክፈል በግዕዝና በአማርኛ በመተርጎም ቀርቧል።
❞ይኸም ቅዱሳኑ በሕይወተ ሥጋ እያሉም ኾነ ከዕረፍታቸው በኋላ በዐጸደ ነፍስ ሳሉ ያደረጓቸውን ልዩ ልዩ ድንቅ ተኣምራትን መልክዐቸውንም አካቶ የያዘ የካህኑ ጸጋ ዘአብን፣ የብፅዕት እግዚእ ኀረያንና አቡነ ታዴዎስን ዝክረ ስም የሚናገር የምስጋናጸሎት ስለኾነ በዚኸ የጸሎት መጽሐፍ ተጠቅመን በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እናገኝ ዘንድ ይህን ገድል ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም እነሆ ይለናል ።
❞ይኽን የቅዱሳን ተጋድሎ እና ምስጋና የያዘ ገድል በግዮን መጻሕፍት የሚያገኙት ሲሆን በሀገር ውስጥ እንዲሁም ከሀገር ውጭ ለምትገኙ አንባብያን በDHLእና በEMS በመላክ የ Delivery አገልግሎት በመስጠት ተደራሽ እናደርጋለን።

ጌታችን መጻጉዕን የፈወሰበትን፣ አልዓዛርን ከሞት ያስነሣበትን፣ ዓይን ያበራበትን፣ በአጋንንት እስራት የተያዙትን ነጻ ያወጣበትን፣ ዕለት በክብረ በዓል ደረጃ ሳታከብር የቃናው ተአምር ከጌታችን ንዑሳን በዓላት ውስጥ ተደምሮ እንዲከበር ያደረገችበት ጥልቅ ምሥጢርን ስለያዘና ስላዘለ ነው፡፡ ይህ ሰርግ የሚደረገው ጌታችን ከአእላፋት መላእክቱ ጋር በሚመጣበት በዕለተ ምጽአት ነው፡፡ ዕለተ ምጽአት ሙሽራዪቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅዱሳን ምግባር አጊጣ የምትታይበት፣ የጽድቅ ዘይት ይዘው መገኘት የቻሉ ልባሞች ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሰርጉን የሚታደሙበት፣ እንደ ቃናው ደስታ በሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእከት በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሳት የምንደርስበት ዕለት ነው፡፡ (ዕብ.፲፱፥፳፪)
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ የቃናን ሰርግ ከሰማያዊው ሰርግ ጋር አሰናስሎ ሲያመስግን እንዲህ ይላል፡፡ “ወደ ሰርግ በዓልዋ ዕለት ደስታን ይዘህላት ስለመጣህ ቃና ታመስግንህ! አክብረኸዋልና ሙሽራው የደፋው ዘውድ አንተን ያከብርሃል። የሙሽራዋ አክሊልም የአንተን ድንቅ ሥራ ያደንቃል፡፡ ቤተ ክርስቲያንህን በሙሽራዋ መስለሃታልና በቃና መስታወትነት ምሳሌዎች ሁሉ ትርጒማቸውን አገኙ፡፡ የቃናዎቹ እንግዶች ደግሞ አንተ የመረጥሃቸው (ወደ ሰማያዊው ራት) የጠራሃቸው ናቸው:: ምጽአትህንም በሰርግ ቤቱ ደስታ መሰልከው::”
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደ ሙሽራ አጊጣ፣ ለበጉ ሰርግ ያለ እድፍና ያለ ነውር ውብ ሆና ተዘጋጅታ በምትቀርብበት በዚያ ሰማያዊ ሰርግ ለመገኘትና ወደ በጉ ሰርግ ራት ገብተን፣ ካጌጡ ቅዱሳን ጋር ለመቀመጥና ለመብላት የበቃን ያድርገን!
መልካም በዓል!
ምንጭ፡- ትርጓሜ ወንጌል እና “ቃና ዘገሊላ”
በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

ቃና ዘገሊላ
እንኳን አደረሳችሁ!
በቤተ ክርስቲያናችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካደረጋቸው እጅግ ብዙ ተአምራት መካከል በዓል አድርጋ የምታከብረው የቃና ዘገሊላውን ተአምር ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ተመዝግቦ እናገኘዋለን፡፡ “በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም” አለችው። ኢየሱስም፦ “አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም” አላት። እናቱም “ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” አለቻቸው። አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። ኢየሱስም፦ “ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው” አላቸው። “እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው” አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። “አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት” አላቸው፤ ሰጡትም። አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ ፦ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል” አለው። ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።” (ዮሐ.፪፥፩-፲፩)

በዓለ ጥምቀት
እንኳን አደረሳችሁ!
ጥምቀት ሥርዓቱ ከብሉይ ኪዳን ይጀምራል፡፡ አንድ አይሁድነትን ያልተቀበለ አዲስ ሰው ወደ ይሁዲነት ሲመጣ ከማኅበረ አይሁድ ከመቀላቀሉ አስቀድሞ ግዝረትን እና በውኃ መታጠብን (መጠመቅ) እንዲፈጽም ይደረጋል፡፡ ይህም ለመንጻት ሥርዓት በዘሌዋውያን ካህናት አማካኝነት ይፈፀም ነበር፡፡ ውኃ መንጽኢ ነውና ማንም ሰው በተለያየ ምክንያት ቢረክስ የሚነጻበት (የኅፅበት) ሥርዓት ለእያንዳንዱ ምክንያት ነበረው፡፡ (ዘሌ. ፲፬፥፲፭-፳፪) ይህንንም ተዘርዝሮ እናገኘዋለን፡፡ ይህም በእውነት በውኃ ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳደረበት ያስረዳል፡፡ (ዘፍ.፫፥፪) ተያይዞ እስከ ዘካርያስ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ ደርሷል፡፡
በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራት የተወለደው ጻድቅ፣ ቅዱስ ሐዋርያ ሰማዕት፣ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የዮሐንስ በረሃ በሚባለው እና ከሕፃናቱ ጀምሮ ባደገበትምድረ በዳ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ በብሕትውና ተወስኖ ሲኖር ቆይቶ ለክርስቶስ መንፈቅ ሲቀረው በ፴ ዘመኑ የዮርዳኖስ አውራጃ በምትሆን በይሁዳ ‹‹ነስሑ እስመቀርበት መንግሥተ ሰማያት፤ መንግሥተ ሰማያት በልጅነት፣ ልጅነት በሃይማኖት ልትሰጥ ቀርባለችና በወንጌል አምናችሁ ንስሐ እያለ ሰበከ፤ በነቢይ ‹‹የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ›› እንደ ተባለለት፡፡ (ኢሳ.፵፥፫፣ማቴ.፫፥፫)
ቃሉን የተቀበሉም ስለ ኃጢአት ስርየት ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ በፈለገ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ይጠመቁ ነበር፡፡ ይህም አማኞችን ለክርስቶስ ጥምቀት የሚያዘጋጅና በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ለመሆን የሚያበቃ ነበር፡፡ ‹‹እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸክም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል›› (ማቴ.፫፥፲፩) ክርስቶስም ናዝራዊ ከተባለበት (ማቴ. ፥፳፫) ከናዝሬት ወደ ዮርዳኖስ ጥር ፲፩ ቀን ወረደ፤ ቅዱስ ዮሐንስም ስለ እርሱ መሰከረ ‹‹ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያአትት ወያሴስል ኃጢአተ ዓለም፤ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፡፡›› (ዮሐ.፩፥፳፱)
ዮሐንስም ክርስቶስ በእርሱ እንዲጠመቅ መምጣቱን ባየ ጊዜ ወትሮ ባሪያ ወደ ጌታው ይሄዳል እንጂ እንዴት ይህ ይሆናል? አለው፤ ትሕትናን ከእናቱ ተምሯልና፤ ‹‹የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?›› እንዳለች ቅድስት ኤልሳቤጥ፡፡ (ሉቃ.፩፥፵፫) ደግሞስ ሌላውን ሁሉ በስምህ አጠምቃለሁ፤ አንተን በማን ስም አጠምቃለሁ? ቢለው ‹‹ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሃለነ››፤ ‹‹አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሢመቱ ለመልከ ጼዴቅ›› ብለህ አጥምቀኝ ብሎታል፤ ብርሃንን የምትገልጥ የቡሩክ አብ የባሕርይው ልጅ ይቅር በለን፤ እንደ መልከ ጼዴቅ የዓለም ሁሉ ካህን አንተ ነህ›› እያልክ አጥምቀኝ ብሎታል፤ ከዚያም ዮሐንስ ሊያጠምቀው ወደ ዮርዳኖስ ገብቷል፡፡
ዮርዳኖስ የጥምቀቱ ቦታ እንዲሆን ጌታ የፈቀደው አስቀድሞ ትንቢት አናግሮ ምሳሌ መስሎ ‹‹ባሕርኒ ርእየት ወጎየት ወዮርዳኖስኒ ገብአ ድኅሬሁ ርእዩከ ማያት እግዚኦ ርእዩከ ማያት ወፈርሁ፤ አቤቱ ውኆች አዩህ፤ ውኆችም አይተውህ ፈሩህ፤ ጥልቆችም ተነዋወጡ፤ ውኆችም ጮሁ፡፡›› (መዝ. ፸፮፥፲፮) ‹‹ባሕር አየች፤ ሸሸችም፤ ዮርዳኖስም ወደ ኋላ ተመለሰ፤›› (መዝ.፻፲፫፥፫) ዮርዳኖስ መነሻው ከላይ ነቁ፤ አንድ ነው፤ ዝቅ ብሎ በደሴት ይከፈላል፤ ከታች ወርዶ ይገናኛል፡፡ የሰውም ልጅ አባቱ አንዱ አዳም ሲሆን እስራኤልና አሕዛብ በግዝረት በቁልፈት ተለያይተዋልና፡፡ ከታች ወርዶ እንደገና በወደብ እንዲገናኝ ሕዝብ እና አሕዛብ በክርስቶስ ጥምቀት አንድ ሆነዋል፤ ከዚህም የተነሣ ጌታ የሁለቱ ወንዝ መጋጠሚያ ላይ በመጠመቅ አንድነታችንን መልሶልናል፡፡ ይህንን ውለታ በማሰብ (ይህን የነጻነት በዓል) እናከብራለን፡፡
ከዚህም በላይ የሥላሴ ምሥጢር እኛ በምንረዳው መልኩ ያየንበትን በዓል የዕዳ ደብዳቤያችን የተፋቀበትን ቀን፣ ነጻነታችንን ያወጅንበትን፣ የእግዚአብሔር ልጆች የሆንበትን ዕለት ከበዓልም የሚበልጥ ዐቢይ በዓል አድርገን አናከብረዋለን፡፡ ይህንንም ቀን ቀድሶ የሰጠን ቅዱስ አምላክ ምስጋና ይድረሰው፤ አሜን፡፡
ከበዓሉ በረከት ረድኤት ያሳትፈን!