أحدث المنشورات من የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe (@yahyanuhe) على Telegram

منشورات የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe على Telegram

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |
17,102 مشترك
1,132 صورة
242 فيديو
آخر تحديث 06.03.2025 16:56

أحدث المحتوى الذي تم مشاركته بواسطة የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe على Telegram

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

25 Jan, 17:50

5,545

ይህ ፕሮግራም ወደ ሰኞ ምሽት ተዛውሯል። በአላህ ፍቃድ በዚያው ቀን እንገናኝ። ባለማወቅ ፕሮግራም ያዛባንባችሁ ካለን ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን።
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

25 Jan, 15:52

5,993

በቴሌግራም ቡት አማካኝነት ለላካችሁልን ጥያቄዎች ዛሬ ምሽት በአላህ ﷻ ፍቃድ መልስ መስጠት የምንጀምር ይሆናል። በቲክቶክ በወንድማችን ኢምራን ቤት ይጠብቁን..!

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

23 Jan, 18:37

5,812

📌 ዳዕዋ ቲቪ ከ2 ሺህ በላይ ደርሶች እና ፕሮግራሞች የነበሩት የዩቲዩብ ቻናል በመጠለፉ አዲስ የዩቲዩብ ቻናል ከፍቷል!

የዳዕዋ ቲቪ ቤተሰቦች ከ2ሺ በላይ የሚሆኑ የኪታብ ደርሶች፣ ፈትዋዎች እንዲሁም የሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን የቁርአን ተፍሲርና የተለያዩ ኢስላማዊ እውቀትን የሚያስጨብጡ ትምህርቶችን ሲተላለፉበት የነበረው የዩቲዩብ ገፅ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በመጠለፉ በምትኩ አዲስ ቻናል ተከፍቷል።

ስለሆነም እርስዎም ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን አዲሱን የዳዕዋ ቲቪ የዩቲዩብ ገፅ ሰብስክራይብ እንዲያደርጉና ለሌሎችም እንዲያስተላልፉ ጥሪ ቀርቧል።
https://youtube.com/@daewatv1?si=AyREhvSL0jc-JgSn
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

21 Jan, 08:18

6,945

የትግራይ ህዝበ ሙስሊምና መሪው የክልሉ መጅሊስ የሒጃብ ክልከላውን በተመለከተ ያደረጉት ትግል እጅግ የሚያኮራ ነው። የክልሉ መጅሊስ በዚህ ዙሪያ ያደረገው ትግል ቀላል አይደለም። እኛ ግን እህቶቻችን "ሒጃብ ይልበሱ" ብለን የምንጠይቅበት ዘመን ላይ ደርሰናል፣ ከከልካዮቹ አዳፋነት በላይ እንደ ግል ሁላችንም የሚያሸማቅቅ ነው..!
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

19 Jan, 18:17

7,071

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነት ባለው ድርሳን ውስጥ አንድ ሙስሊም በሰይፍ ክርስቲያን ስለመደረጉ የሚተርከውን ምንባብ አስመልክቶ አጭር ቪዲዮ፦

https://vm.tiktok.com/ZMk9dNc9c/
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

19 Jan, 10:18

7,817

ጺም ያሳደገ ሙስሊምን በክፋት ማየትና አለፍ ሲልም ካልተላጨ ከስራው አልያም ከትምህርቱ ማባረር የተለመደ ክስተት ነው። ይህ ተግባር በሌላው ቢደረግ ላይገርም ይችላል፣ መጽሀፋቸው ጺማቸውን እንዲያሳድጉ በሚያዛቸው ኦርቶዶክሶች ሲሆን ግን ያሳዝናል። አስቡት አንድ ሙስሊም ጸጉሯን የሸፈነች ካቶሊክን ጸጉሯን ካልገለጠች ብሎ ሲያሰቃያት..?! የኦርቶዶክስ ሰማንያ አሀዱ መጽሀፍ ቅዱስ በዚህ ዙሪያ ምን እንደሚል በዚህ አጭር ቪዲዮ አስቀምጨላችኃለው።

https://vm.tiktok.com/ZMkHvvwGs/
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

19 Jan, 08:08

7,273

የስራ ሰው ብርቱ ናት፣ በጀመረችው ስራ ላይም ጽኑ ናት። ለተለያዩ ግልጋሎት የሚውሉ የወረቀት ዘንቢሎችን/Paper Bag/ ታዘጋጃለች። ለድርጅቶቻችሁና ለሱቃችሁ የምትፈልጉ ደውሉና እዘዟት፣ ካሻችሁ በባልሽ በኩል ነው የመጣነው በሉና ዋጋ አስቀንሱ 😀

📌 0910632233
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

18 Jan, 12:53

4,754

ወንድማችን ኡስታዝ ወሒድ ዑመር አዲሱን መጽሀፉን (አልገደሉትም፣ አልሰቀሉትም) ሶስት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ እህቶች ወጭውን እንዲሸፍኑ በማስተባበር 100 መጽሀፍትን ለሒዳያ ላይብረሪ አስረክቦናል። በተጨማሪም በራሱ በኩል የእሱን መጽሀፍ የኦሮምኛ ትርጉም 100 ፍሬ የለገሰን ሲሆን ኡስታዝ ጀማል ደግሞ የአህመዲን ጀበልን "ክርስቶስ ማነው?" መጽሀፍ የኦሮምኛ ትርጉም ስራውን 100 ፍሬ አበርክቶልናል። እያንዳንዳቸው 100 መጽሀፍ በድምሩ 300 መጽሀፍትን ተለግሰውናል። አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው፣ ከዚህ የበለጠ የሚተጉበትን ብርታትም ይወፍቃቸው።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

https://t.me/Hidayaic8212
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

17 Jan, 07:31

7,055

እስልምና ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎችንና በሀይማኖት ንጽጽር ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎችን ጥልቅ በሆነ መልኩ ስራዎችን ለመስራት እንዲያግዝ በማሰብ ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በስሩ የጥናትና ምርምር ዘርፍ አቋቁሟል።

በዚህ ዘርፍ ውስጥ የንጽጽር ዱዓቶችን ጨምሮ ተተኪ ወንድምና እህቶች ሰፊ ጊዜዎችን በመውሰድ ስራዎችን እንዲያጠኑ፣ በየቋንቋቸው የጥናት ውጤታቸውን እንዲያዘጋጁ በማመቻቸት ላይ ይገኛል።

ለስራውም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ አረብኛ እና እንግሊዝኛ የተጻፉ መጽሀፍትን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ሲሆን ለዚህ የሚያግዙ እናንተ ጋር የተቀመጡና ለተቋማችን ይጠቅማል የምትሏቸው መጽሀፍት ካሉ በሚከተለው ስልክ ቁጥር ለአስተባባሪዎች በመደወል መስጠት የምትችሉ ሲሆን ቢሮ መጥቶ መስጠት የሚችሉም ይበረታታሉ።

አድራሻ፦ ቤተል
ስልክ፦ 0910858830
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

15 Jan, 18:49

6,209

ከ464 የግፍ ቀናት በኃላ የጋዛ ንጹሀን ሰላማዊ ሌሊትን በአላህ ፍቃድ ዛሬ ምሽት ያሳልፋሉ። ሰማዕቶቻችሁን አላህ ይቀበል፣ ቅዋችሁንም የበለጠ ኃያል ያድርገው..!