أحدث المنشورات من የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe (@yahyanuhe) على Telegram

منشورات የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe على Telegram

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |
17,102 مشترك
1,132 صورة
242 فيديو
آخر تحديث 06.03.2025 16:56

أحدث المحتوى الذي تم مشاركته بواسطة የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe على Telegram

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

09 Feb, 18:41

5,726

ኪታብ አገላብጠህ፣ ዝቅ ብለህ ተምረህ ካልገባህ በመጨረሻ ህይወት ዘግይቶም ቢሆን ከሚያስተምርህ ነገሮች ውስጥ፤ በስራህና ድካምህ ውስጥ ምን ያክል አብዝተህ ብትደክም ስራህ ኢኽላስ ከሌለው ከጊዜያዊ ብልጭልጭ ውጤት ውጭ እርባና ቢስ መሆኑን ነው። ያ ሁሉ ልፋት አይደለም አኼራ ሊሻገር ይቅርና፣ አመታት ተንፏቆም ዘመን አይሻገርም። ኢኽላስ የዱንያ እና የአኼራ ስኬት ቢሆንም ከእዩልኝ ጋር ልብ ውስጥ የሚያደርገው ተጋድሎ ግን እጅግ ፈታኝና ለጥቂቶች ብቻ የሚሳካላቸው ነው።
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

04 Feb, 10:19

7,729

ስልጠናው አዲስ አበባ የሚሰጥ በመሆኑ የክፍለ ሀገር ወንድምና እህቶች መገኘት የማትችሉ ከሆነ አትመዝገቡ።
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

04 Feb, 08:58

8,466

በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አማካኝነት የተዘጋጀውን ይህንን ስልጠና መውሰድ ለምትሹ ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ መመዝገብ ትችላላችሁ። እያንዳንዱ ስልጠና ለአንድ ቀን በአካል (አዲስ አበባ) የሚሰጥ ሲሆን ከተመዘገባችሁ በኃላ በሚደወልላችሁ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ስልክ ቁጥር አማካኝነት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በቴሌግራም ወይንም በዋትስአፕ ቀድማችሁ መላክ ይኖርባችኃል።

- ለስልጠናው የምንፈልገው 15 ሰልጣኝ ብቻ ስለሆነ ስልጠናውን የመውሰድ እርግጠኛ እቅድ ከሌለዎት አይመዝገቡ።

https://bit.ly/4aK4Pq5
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

31 Jan, 07:55

7,439

ሚዲያ ውስጥ አጀንዳ ፍሬሚንግ ወሳኝ ዘርፍ ነው። የተነሳህለትን አላማ በሚገባ ወደ ተከታይህ ለማስረጽ ከቃላት ጀምሮ እስከ ርዕሰ ጉዳይ በጥንቃቄ የምትመርጥበት መንገድ ነው። በሀገራችን ቋንቋ ከሚሰራጩ ሚዲያዎች ውስጥ የቢቢሲን አላማና የትኩረት ነጥብ ብዙ ሰው ያውቀዋል። ከስሙ ጀምሮ ብዙም ከማይለዩ አፍቃሬ ጽዮናውያን ሚዲያዎች መካከል ግን አል አይንን የሚወዳደር ያለ አይመስለኝም።

በሙስሊሙ አለም ዙሪያ የኢማራት አቋምና አላማ የሚታወቅ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ለተዛቡት መረጃዎች ግን በየሀገሩ ያሉ የተቀጣሪ ሰራተኞችን የግል እምነትና አመለካከትን ምክንያት ማድረግ እመርጥ ነበር። ዜናዎችን የመምረጥ፣ አጀንዳዎችን ፍሬም ማድረግ፣ ለዘገባ የሚወሰነውን የቃላት አጠቃቀም ወዘተ የሚዲያው ፖሊስ እንዳለ ሁኖ የሰራተኞችም የግል ፍላጎት ሊንጸባረቅበት ይችላል።

የጋዛው ኹነት ግን ከብዙው ሚዲያ ጀርባ ያለውን ፍላጎትና ማንነት ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል። ከግለሰቦቹ የግል አመለካከት በተጨማሪ እንደ ሚዲያ የቆመለትን አላማም ጭምር ይኸው መሆኑን ብዙ ሰው የተረዳ ይመስለኛል። ሚዲያዎቹ ሜንትስሪምና በብዙ በጀት የሚደጎሙ ቢሆንም እድሜ ለማኅበራዊ ሚዲያው በጥቂት አቅም የሚሰሩ ተኣማኒ ሚዲያዎች ተቀራራቢ ተደራሽነትን በመፍጠር እኩይ አላማቸውን ማሳየት ችለዋል። ዛሬ ትላንት አይደለም..!

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

30 Jan, 18:50

5,941

إلى رحمة الله ورضوانه

ለጅሀድ የተኖረ ሙሉ ህይወት፣ እስከ ፍጻሜው ድረስ..! ይህ ጋዛ ከከፈለቻቸው ውድ መስዋዕትነቶች ውስጥ ነው።

አላህ ይዘንላችሁ፣ ምትካችሁን ያበርክት።
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

30 Jan, 12:18

5,727

በነገራችን ላይ ሰልዋን ሞሚካ በኢራቅ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የክርስቲያን ሚሊሻ ቡድን መሪ ነበር። በሰራቸው አስከፊ ወንጀሎች ሳቢያ በህግ ሲፈለግ አምልጦ ስዊድን የገባ ሲሆን ጥገኝነት ቢጠይቅም ጥያቄው ተቀባይነት አላገኘም ነበር። በኃላም ከቀናት በፊት አቲየስት መሆኑን አውጆ ነበር።

በስዊድን መንግስት ጥገኝነት ከተከለከለ በኃላ ይህንን ጥያቄየን ያሳካልኛል በሚል የቁርኣን ማቃጠል ስራ ውስጥ በስፋት መንቀሳቀስ ጀመረ። ተግባሩ የስዊድንን ዜግነት ባያስገኝለትም የጀሀነምን ግን አላሳጣውም..!
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

30 Jan, 10:05

5,799

ቁርኣንን በአደባባይ በማቃጠል የሚታወቀው ኢራቃዊው ክርስቲያን (ከ15 ቀን በፊት ኤቲየስት መሆኑን አውጇል) ሰልዋን ሞሚካ በስዊድን በቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት ላይ እያለ በተተኮሰበት ጥይት ተገድሏል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

27 Jan, 09:56

6,839

እስልምና ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎችንና በሀይማኖት ንጽጽር ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎችን ጥልቅ በሆነ መልኩ ስራዎችን ለመስራት እንዲያግዝ በማሰብ ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በስሩ የጥናትና ምርምር ዘርፍ አቋቁሟል።

በዚህ ዘርፍ ውስጥ የንጽጽር ዱዓቶችን ጨምሮ ተተኪ ወንድምና እህቶች ሰፊ ጊዜዎችን በመውሰድ ስራዎችን እንዲያጠኑ፣ በየቋንቋቸው የጥናት ውጤታቸውን እንዲያዘጋጁ በማመቻቸት ላይ ይገኛል።

ለስራውም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ አረብኛ እና እንግሊዝኛ የተጻፉ መጽሀፍትን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ሲሆን ለዚህ የሚያግዙ እናንተ ጋር የተቀመጡና ለተቋማችን ይጠቅማል የምትሏቸው መጽሀፍት ካሉ በሚከተለው ስልክ ቁጥር ለአስተባባሪዎች በመደወል መስጠት የምትችሉ ሲሆን ቢሮ መጥቶ መስጠት የሚችሉም ይበረታታሉ።

አድራሻ፦ ቤተል
ስልክ፦ 0910858830
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

27 Jan, 07:41

5,403

በትግራይ የፋይናል ማጠቃለያ ቢጀመርም የአክሱም ሙስሊሞች መፈተን እንደማይችሉ ተነግሯቸው ከበር ተመልሰዋል። ይህ እምነትን መሠረት ያደረገ አድልኦ ብቻ አይደለም። የህዝብና የመንግስት መገልገያዎችን በእኩልነት እንዳይጠቀም አንድን የህብረተሰብ ክፍል በእምነቱ ምክንያት የመከልከል የአፓርታይድ ስርኣት ነው። ህዝቡ እኩል ግብር በሚከፈልበትና ተወልዶ ባደገበት ቀዮ "እኛ ከፍ ያልን ነን" ባሉ ጥቂት እቡዮች ሳቢያ ባይተዋር የተደረገበት አስቀያሚ ስርኣት ነው። በዚህ የግፍ ሒደት ውስጥ መታገል ከምትችሉት መጠን አፈግፍጋችሁ ከዳር ቁማችሁ በቸልታ የምታዩ "ባለኃላፊነቶች" ሁሉ የዚህ ግፍ ታሪክ አንዱ አካል መሆናችሁን ግን ለሰከንድም እንዳትዘነጉት..!
የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

26 Jan, 12:10

6,286

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ከጉረባዕ ኢስላማዊ ድርጅት ጋር በመተባበር ላለፉት 6 ሳምንታት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል። በስልጠናው መሠረታዊ የንጽጽር አስተምህሮ የተዳሰሰ ሲሆን በቀጣይ በትብብር ስለሚሰሩ ስራዎችም ውይይትና ስምምነት ላይ ተደርሷል። ማዕከሉ ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰጣቸው ስልጠናዎችም በአላህ ፍቃድ ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል