" ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ።"
መዝ. ፹፱፥፫
እመቤታችን ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የማይጠፋ የዘላለም ኪዳን የተቀበለችበት ዕለት መታሰቢያ ነው
እግዚአብሔር ዓለሙን ከፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ፍጥረታቱን ሁሉ በቸርነቱ ይጠብቃል፣ ይመግባል።
ሕግን ተላልፈው ኃጢአት ሰርተው፣ በመንፈሳዊ ህይወታቸው ዝለው ባሳዘኑት ጊዜ ከጥበቃውና ከበረከቱ እንዳይርቁ ስለቧለሟለቹ ቅዱሳን ብሎ በቃል ኪዳኑ ይጠብቃቸዋል።
✍... "እመቤቴ ኪዳነምህረት ሆይ. . .
በአካል ሦስት ሲሆን በመለኮታዊ ባሕርዩ በአንድነቱ ጸንቶ የሚኖር የብርሃን መገኛ እሱ እግዚአብሔር አብ ለቃል ኪዳንሽ የተሰጠውን ልዩ ክብር ብሩህ አድርጎ ያሳየኝ_ዘንድ የቸርነቱ ጸዳለ ብርሃን
ዓይነ ልቡናዬን ይብራልኝ።
የቃል ኪዳኗ እመቤቴ ሆይ ከእግዚአብሔር በታች በሰማይም በምድርም አንቺ የሁሉ እመቤት ነሽ.. "
🖍✥መልክአ ኪዳነምህረት✥
✨✨"እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምሕረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት አመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!"✨✨
◈◈◈ወ▮ዩ▮ግ▮ጉ◈◈◈