ለአዲስ ተማሪዎች ቅዳሜ እና እሁድ ቁርስ ካፌ መግባት ትችላላችሁ።
Посты канала ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

ይህ በወልቂጤ ማዕከል ግቢ ጉባኤ ማሰተባበሪያ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግ.ጉ አባላት መረጃ መለዋወጫ 'የቴሌግራም' ገፅ ነው።
👇👇👇ተከታዮቹን ገጾች ይቀላቀሉ 👇👇👇
Telegram፦
https://t.me/wku_gg_media
YouTube፦ https://www.youtube.com/@Wku_gg
የፎቶ ማኅደራችን
@wku_gg_gallerystore
ለሃሳብና አስትያይቶ @wkugg_bot

3,510 подписчиков
3,117 фото
74 видео
Последнее обновление 01.03.2025 07:20
Похожие каналы

59,738 подписчиков

1,798 подписчиков

1,148 подписчиков
Последний контент, опубликованный в ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ на Telegram
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በዛሬ መርሃግብር የሚዘመሩ መዝሙራት
#1የመድኃኒት_እናት
የመድኃኒት እናት ሕመምተኛ ልጅሽ
ምኅረትን ፍለጋ ቆሜያለሁ ከደጅሽ
ጸሎት ልመናሽን ታምኛለሁና
ከቤትሽ መልሽኝ ዳግም እንደገና
የደካሞች ብርታት የሚስኪናን ተስፋ
ለዓለም አልተውሽኝም በከንቱ እንድጠፋ
የሕይወቴ ጥበብ እረፍቴ ሰላሜ
አማልጂኝ እላለሁ በመቅደስሽ ቆሜ
#አዝ
በፍቅርሽ ብርሃን ነው ልጅሽን ያየሁት
ባዶ ማድጋዬን ጋኔን የሞላሁት
አልጫ ኑሮዬ ዛሬ ተለውጧል
በደልና ኃጢአቴ በምልጃሽ ተፍቋል
#አዝ
ብርሃን ወጥቶለታል ጨለማ ሕይወቴ
ዛሬም ጥላ ሁኚኝ እናቴ እመቤቴ
ፍቅር ውለታሽን ዘውትር አውጃላሁ
ከአእላፍ መካከል እቀኝልሻለሁ
#አዝ
በረከት ረድኤትሽ ይኑር ከኔጋራ
ምሥራቅ ቤተልሔም የሲና ተራራ
መናን ያቀረብሽው ለተራበው ዓለም
ድንግል ዘለዓለም የሚመስልሽ የለም
#2የአብርሃም_አምላክ
የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ቤዛ /፪/
ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ/፪/
የሐስት ምስክር አቁመው ከሰሱት /፪/
በሞት እንዲቀጣ ሁሉም ፈረዱበት/፪/
ጲላጦስ ገረፈው በሰንሰለት አስሮ/፪/
ከሮማዊው መንግሥት እንዲኖር ተፋቅሮ/፪/
ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ /፪/
እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ /፪/
በብርሃን ዙፋን ላይ የቆሙት እግሮቹ /፪/
በችንካር ላይ ቆመው ምንም ሳይሰለቹ /፪/
የብርሃን አክሊልን ለሰማእት ያደለ/፪/
የሾክ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ /፪/
#3የልቤን_በልቤ_ይዤ
የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
ካለኝ ነገር ሁሉ አንቺን መርጫለሁ
እናቴ ሆይ ስሚኝ አማልጂኝ እላለሁ/2/
ግራ ቀኝ ህይወቴ በሾህ ታጥሮብኛል
በፊት በኋላዬ መሰናክል በዝቷል
እኔስ ያለ ምርኩዝ ጉዞዬ ከብዶኛል
እመ አምላክ ደግፊኝ እጄ ተዘርግቷል/2/
ቆሜ ስራመድ ጤነኛ እመስላለሁ
የውስጤን ጎዶሎ እኔ አውቃለሁ
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ አይዞህ ልጄ በይኝ
የጭንቀቴን ካባ አውልቀሽ ጣይልኝ/2/
እናት ያለው ሰው ፍጹም አይተክዝም
አንድ ቀን ይስቃል አልቅሶም አይቀርም
ሀዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ
በደስታ ልዘምር በቀረው ሕይወቴ/2/
አሁንም ጎዶሎ በውስጤ አለና
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ ዛሬም እንደገና
ለዚች ለትንሿ ለጥቂቷ እድሜ
እንደከፋኝ አልኑር ቀና አርጊኝ እናቴ/2/
በዛሬ መርሃግብር የሚዘመሩ መዝሙራት
#1የመድኃኒት_እናት
የመድኃኒት እናት ሕመምተኛ ልጅሽ
ምኅረትን ፍለጋ ቆሜያለሁ ከደጅሽ
ጸሎት ልመናሽን ታምኛለሁና
ከቤትሽ መልሽኝ ዳግም እንደገና
የደካሞች ብርታት የሚስኪናን ተስፋ
ለዓለም አልተውሽኝም በከንቱ እንድጠፋ
የሕይወቴ ጥበብ እረፍቴ ሰላሜ
አማልጂኝ እላለሁ በመቅደስሽ ቆሜ
#አዝ
በፍቅርሽ ብርሃን ነው ልጅሽን ያየሁት
ባዶ ማድጋዬን ጋኔን የሞላሁት
አልጫ ኑሮዬ ዛሬ ተለውጧል
በደልና ኃጢአቴ በምልጃሽ ተፍቋል
#አዝ
ብርሃን ወጥቶለታል ጨለማ ሕይወቴ
ዛሬም ጥላ ሁኚኝ እናቴ እመቤቴ
ፍቅር ውለታሽን ዘውትር አውጃላሁ
ከአእላፍ መካከል እቀኝልሻለሁ
#አዝ
በረከት ረድኤትሽ ይኑር ከኔጋራ
ምሥራቅ ቤተልሔም የሲና ተራራ
መናን ያቀረብሽው ለተራበው ዓለም
ድንግል ዘለዓለም የሚመስልሽ የለም
#2የአብርሃም_አምላክ
የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ቤዛ /፪/
ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ/፪/
የሐስት ምስክር አቁመው ከሰሱት /፪/
በሞት እንዲቀጣ ሁሉም ፈረዱበት/፪/
ጲላጦስ ገረፈው በሰንሰለት አስሮ/፪/
ከሮማዊው መንግሥት እንዲኖር ተፋቅሮ/፪/
ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ /፪/
እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ /፪/
በብርሃን ዙፋን ላይ የቆሙት እግሮቹ /፪/
በችንካር ላይ ቆመው ምንም ሳይሰለቹ /፪/
የብርሃን አክሊልን ለሰማእት ያደለ/፪/
የሾክ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ /፪/
#3የልቤን_በልቤ_ይዤ
የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው
ካለኝ ነገር ሁሉ አንቺን መርጫለሁ
እናቴ ሆይ ስሚኝ አማልጂኝ እላለሁ/2/
ግራ ቀኝ ህይወቴ በሾህ ታጥሮብኛል
በፊት በኋላዬ መሰናክል በዝቷል
እኔስ ያለ ምርኩዝ ጉዞዬ ከብዶኛል
እመ አምላክ ደግፊኝ እጄ ተዘርግቷል/2/
ቆሜ ስራመድ ጤነኛ እመስላለሁ
የውስጤን ጎዶሎ እኔ አውቃለሁ
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ አይዞህ ልጄ በይኝ
የጭንቀቴን ካባ አውልቀሽ ጣይልኝ/2/
እናት ያለው ሰው ፍጹም አይተክዝም
አንድ ቀን ይስቃል አልቅሶም አይቀርም
ሀዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ
በደስታ ልዘምር በቀረው ሕይወቴ/2/
አሁንም ጎዶሎ በውስጤ አለና
ድንግል ሆይ ቅረቢኝ ዛሬም እንደገና
ለዚች ለትንሿ ለጥቂቷ እድሜ
እንደከፋኝ አልኑር ቀና አርጊኝ እናቴ/2/
⭐🌟⭐በጾማችን የነፍሳችንን ክፉ ልማዶች ካላስወገድን ከሥጋ መከልከላችን ብቻውን ምን ይጠቅመናል? ስንጾም ውለን ጾም ከመግባቱ በፊት እንመገበው የነበረውን ምግብ ለውጠን መናኛ የሆነ የጾም ምግብ በማዕዳችን አቀረብን፡ ሆኖም ግን በጸሙ የምንመገበውን ምግብ እንደ ለወጥን ክፉ ግብራችንን እና ሕይወታችንንስ አብረን ለውጠናል ይሆን? በእውነት እኔ ግን እንዲህ ያደረጋችሁ አልመሰለኝም፡፡ እንዲህ ከሆነ መጾማችሁ ጥቅሙ ምንድን ነው? ስለዚህ ከጾማችሁ ጋር ልማዳችሁንና ሕይወታችሁን ወደ መልካምነት ትቀይሩ ዘንድ በተከታታይ እንድታስቡበት አደርጋችሁ ዘንድ ስለዚህ ነገር እናንተን ማስተማርንና መገሠጽን አላቋርጥም፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት 4 ቁ 12)⭐🌟✨
ራሳችንን ፍሬ በሌለው መንገድ በከንቱ እንዳናደክም ጥቂት ነገሮችን እንበል፡፡ በርግጥ አሁን የምታደርጉት ነገር - ጾማችሁና መሬት ላይ መተኛታችሁ - በጣም የተመሰገነ ተግባር ነው፡፡ ሆኖም ከእነዚህ ጋር ሌሎች በጾም ጊዜ ሊፈጸሙ የሚገባቸው ተግባራት ካልተጨመሩ በስተቀር ከጾም የምናገኘውን ዋጋ ያሳጡናል፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአትን እንዴት ይቅር እንደሚል አሳይቶናል፡፡ በጥንት ዘመን የነነዌ ሰዎች ኃጢአትን ባደረጉ ጊዜ በኃጢአት ቁስላቸው ላይ ጽኑ የሆነ የጾምን መድኃኒት አደረጉ፡፡ መሬት ላይ በመተኛት ማቅና ዓመድ ለበሱ፣ ለቅሶንና ሐዘንን በኃጢአት ቁስላቸው ላይ መድኃኒት አድርገው አፈሰሱ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ከዚህ ሁሉ ጋር ደግሞ ሕይወታቸውን ከክፉ ወደ መልካም ለወጡ፡፡ ከዚህ ሁሉ ጋር እግዚአብሔር በምን ምክንያት እንደ ማራቸው ሲናገር እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ ሥራቸውን አየ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም' ይላል። ዮና 3፡10 ስለዚህ ከመጾም ጋር ከክፉ መመለስንና ከክፉ ነገር መጾምንም እንፈጽም ዘንድ መዘንጋት የለብንም፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ትርጓሜ ቆሮንቶስ ቀዳማዊ፣ ክፍለ ትምህርት 4፣ ቁ. 6

✨ርቱዐ ሀይማኖት ስለ ጾም✨
ርቱዐ ሃይማኖት ስለ ጾም በተናገረበት ክፍል የሚጾም ሰው ኹለንተናውን ማስጾም የሚገባው መሆኑን ፣ ማለትም ኃጥያትን እንለያት ዘንድ እንዲህ ሲል ያስተምረናል።
"አፍህ ክፉ ከመናገርን ፣ አንደበትህም ሰውን ከማማት ከመሳደብ ይጹም ፣ ዐይንህም ሴትን ከመመልከት ይጹም ፣ ዦሮህም ዘፈንን ጨዋታን ከመስማት ይጹም ፣ እጅህም የሌላውን ገንዘብ ወስዶ ከመሸጥ ከመማታት ፣ ከመቀማት ይጹም ፣ እግርህም ደምን ለማፍሰስ ከመመላለስ ከመሮጥም ይፁም ፣ ሆድህም ከስስት ጥሉላትንም ከመብላት ይጹም። ጥረስህም ከመሳቅ ይጹም። ልቡናህም ከሽንገላ ፣ ከቂም ከቁጣ ፣ ከመታበይ ፣ከክፉ ነገር ሁሉ ይጹም። ልቡና እንቢ ካላቸው ሌሎቹ አካላት ክፉ ማድረግ አይቻላቸውምና ፣ የብልቶች ( የሕዋሳት) ሁሉ ንጉሣቸው እርሱ ነውና። ሕሊናም ተላላኪው ፣ልብሱ ነው ፣ ናላም የአዕምሮ ፣የጥበብ ፣ የመለኮት ማደሪያቸው ነው። በዚህም አካላትን ሁሉ ይገዛቸዋል። ሁሉንም ወደ መልካምም ይሁን ወደ ክፉ ይመልሳቸዋል። አይሆንም ይሉት ዘንድ አይቻላቸውም ። ከፈለገም በሰማይም በምድርም ሁሉንም ያድናቸዋል። ከፈለገ በሰማይም በምድርም ያጠፋቸዋል። ህሊናህም ከመታወክ ይጹም። ሥጋህም ከዝሙት ይጹም። ሰውነትህም ከስንፍና ፣ ከመቦዘን (ሥራን ከመፍታት) ፣ከዚህና ከመሳሰለው ሀሉ ይጹም። ቅዱስ ጳውሎስ ' እንዲህ ሁነህ በጾምህ ጊዜ ሰውነትህ በሰዎች ሁሉ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ይሆናል። ' አለህ።
✨ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ✨
📥 @wkugg_bot ጻፉልን
🏷 @wku_gg_media ተከታተሉን
📷 @wku_gg_gallerystore ፎቶ ማኅደራችን

✞✟መልዕክት✞✟
ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች።
ዛሬ ማታ ማለትም ሰኞ በ 17/06/2017 ዓ.ም. የሁሉም አመት ተማሪዎች ኮርስ ይኖረናል።
- አንደኛ እና አራተኛኛ ተማሪዎች ነገረ ሀይማኖት ኮርስ
- ሁለተኛ አመት ተማሪዎች ነገረ-ማርያም ኮርስ ይጀመራል።
- አብነት ትምህርት ይቀጥላል። Remedial እና ከ4ኛ አመት በላይ የሆናችሁ ሄዳችሁ አብነት ትምህርት መማር ትችላላችሁ።
- Remedial ተማሪዎች ኮርስ መማር ከፈለጋችሁ ከአንደኛ አመት ተማሪዎች ጋር ነገረ-ሃይማኖት ኮርስ አብራችሁ መማር ትችላላችሁ።
እንዳታረፍዱ እናም እንዳትቀሩ።
ላልሰሙ ጓደኞቻችን በማሳወቅና በመቀሳቀስ ሄደን እንድንማር ይሁን።
ቦታ ፦⛪ ፦ጥምቀተ ባሕር
ሰዓት ፦ 🕤፦ 11:45
✞ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን።✟

ዘወረደ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ነው። ስያሜውም የቅዱስ ያሬድ ነው። ትርጉሙም “ከሰማያት የወረደ” ማለት ነው። ቅድመ ዓለም ከአባቱ ከአብ የተወለደ ፣ድኅረ ዓለም ከድንግል ማርያም የተወለደ ነው። ስም አጠራሩ ያለና የነበረ፣ እግዚአብሔር፣ በፈቃዱ ዓለምን ለማዳን የመምጣቱን ምሥጢር የምንረዳበት ሳምንት ነው። ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹ጾመ ሕርቃል› እየተባለም ይጠራል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊዮስ) በ፮፻፲፬ ዓ.ም የነበረ የቤዛንታይን ንጉሥ ነው፡፡ለክርስቲያኖች ባደረገው ርዳታ ምክንያት አንድ ሳምንት ጾመውለት ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ጾመ ሕርቃል እየተባለ ይጠራል፡፡ ሙሉ ታሪኩ በፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ ፲፭ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጾም ጥቅምና እንዴት መጾም እንዳለብን ታስተምረናለች፡፡ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው “አከለክሙ መዋዕል ዘኃለፈ ዘተቀነይክሙ ለግዕዘ ሥጋክሙ፤ ለሥጋቸሁ ፈቃድ የተገዛችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃችኋል፤ ከአሁን በኋላ ግን ጹሙ፣ ጸልዩ ለእግዚአብሔር ተገዙ” እያለ የጾም አዋጅ ያውጃል። ጾም ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ፣ ፈቃደ ነፍስን ለፈቃደ እግዚአብሔር የምናስገዛበት መንፈሳዊ መሣሪያ ነው፡፡
ጾሙ በሚጀመርበት ሰንበት በሚሰበከው ምስባክ እንዲህ ብሎ ያሳስበናል፤ “ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፣ በረዓድም ደስ ይበላችሁ” ጾም ከምግብና ከመጠጥ እንዲሁም ከሌሎች ምቾቶችና ደስታዎች ከመከልከል ያለፈ ጥልቅ ትርጉም ያለው ተግባር ነው። (መዝ.፪፥፲፩-፲፪) “ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ከመ ያብርህ ብርሃነ ስብሐቲሁ በላዕሌነ፤ (የእግዚአብሔር) የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ ጾምን እንጹም፤ወንድማችንንም እንውደድ” እንዲል። (ጾመ ድጓ)
በዘወረደ እሑድ የሚነበቡት ምንባባትም ይህንን የጾምን ጸጋ የያዙ ናቸው።
“ነገር ግን ፈጣሪያችን የምትበልጠውን ጸጋ ይሰጣል፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ይላል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔርን እሺ በሉት፤ ሰይጣንን ግን እንቢ በሉት፤ ከእናንተም ይሸሻል፡፡ እግዚአብሔርን ቅረቡት፤ ይቀርባችሁማል፤ እናንተ ኃጥኣን እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ ልባችሁን አጥሩ፡፡ እዘኑና አልቅሱ፤ ሳቃችሁን ወደ ልቅሶ÷ ደስታችሁንም ወደ ኀዘን መልሱ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል፡፡” (ያዕ.፬፥፮-፲)
“በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን? ነገር ግን ለድሆች መራራትን፥ ከእነርሱም ጋር መተባበርን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና፡፡” (ዕብ.፲፫፥፲፭-፲፮)
በጾም የተጠቀሙ ቅዱሳንን እያሰብን ለጾም እንድንተጋም ወደ እነርሱ እንድንመለከት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡“ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና።” (ዕብ.፲፫፥፱) ሳምንቱ በሚጀምርበት ሳምንት የሚነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት እንዲህ ይላል፡፡ ጾመ ድጓው አባቶቻችን ያገኙትን በረከት እንደምናገኝበት ሲገልጽ “የእግዚአብሔር የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ ጾምን እንጹም፤ ወንድሞቻችንም እንውደድ፤ ኤልያስ በጾም ወደ ሰማይ አርጓልና፤ዳንኤልም ከአናብስት አፍ ድኗልና፡፡”
ጾም ፈቃደ ነፍስን በፈቃደ ሥጋ ለማሠልጠን የአጋንንት ኃይል ለመቋቋም የሚያስችል የክርስቲያኖች ጋሻ በመሆኑ በሃይማኖት ለሚመሩ ምእመናን እጅግ አስፈላጊና ከምንም በላይ የሕይወታቸው መርሕ መሆን እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ በማለት ያስተምራል፡፡ ” አሁንም ወንድሞቻችን በዚህ በሥጋችን ሳለን ፈቃደ ሥጋችንን ልንሠራ አይገባም፤ ፈቃደ ሥጋቸውን የሚሠሩ ሰዎች በወዲያኛው ዓለም ምውታን ናቸውና፡፡ የሥጋችሁን ፈቃድ በነፍሳችሁ ፈቃድ ድል ከነሣችሁት ለዘለዓለም ሕያዋን ትሆናላችሁ፡፡ የነፍሳቸውን ፈቃድ የሚሠሩ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና፡፡" (ሮሜ ፰፥፲፪-፲፬)
ጾም አበው ቅዱሳን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በጊዜ ቀምረው፣ በበታ ወስነው፣ በሁኔታ ገድበው... ባስቀመጡልን ወቅት ከእህልና ከውኃ በመከልከልና ሰውነትን በማድከም ብቻ ሳይሆን ለስሕተት ከሚዳርጉ ነገሮችና ቦታዎች ተቆጥቦ በጸሎት መትጋትም እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም ይህንን እውነታ በተመለከተ እንዲህ ይላል፡፡ “እኔ ግን እዘንልን፤ ለምንልን ባሉኝ ጊዜ ማቅ ምንጣፍ ለብሼ አዘንኩላቸው፤ ሰውነቴን በጾም አደከምኩዋት፤ ልመናዬም እኔም ወደመጥቀም ተመለሰችልኝ፡፡” (መዝ. ፴፬/፴፭፥፲፫)
ጾም ከሥነ ምግባራት ሕግ አንዱ በመሆኑ እንኳንስ ያልተፈቀደውን የተፈቀደውም ቢሆን የማይጠቅም ከሆነ ፈጽሞ በመተው ለእግዚአብሔር ያለንን ፍጹም ፍቅር የምናስመሰክርበት ምሥጢር ነው፡፡
ጾም ከመብልና ከመጠጥ ጋር የተያያዘም በመሆኑ መብል ጊዜያዊ ስለሆነ ማለትም በዚህ ዓለም እስካለን ብቻ የምንገለገልበት እንጂ ዘለዓለማዊ ስላይደለ ለጊዜያዊ መብልና መጠጥ ምክንያት ከሃይማኖት ሥነ ምግባር እንዳንወጣ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ሲመክሩ “መብል በእግዚአብሔር ዘንድ ግዳጅ አይፈጽምልንም ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ብንበላም አይረባንም፤ አይጠቅመንም፤ ብንተወውም አይጎዳንም” በማለት ሲመክሩን ቅዱስ ጳውሎስም የመብልና የሆድ ጊዜያዊነት አስመልክቶ እንዲህ በማለት አስተምሯል፡፡ (፩ኛቆሮ.፰፥፰)
“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቅመኝም፡፡ ሁሉ ተፈቅዶልኛል በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳን አይሠለጥንብኝም፡፡ መብል ለሆድ ነው ሆድም ለመብል ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያሳልፋቸዋል”፤ (፩ኛቆሮ.፮፥፲፪-፲፫) “ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት ስለሚሆን ምግብ ሥሩ” እንደ ተባለ (ዮሐ. ፮፥፳፯) ካለን ጊዜ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጊዜ በመስጠት ቢበሉት የማያስርበውን፣ ቢጠጡት የማያስጠማውን፣ የዘለዓለም ሕይወት የምናገኝበትን ሥጋ እና ደሙን ተቀብለን መንግሥቱን እንድንወርስ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት
ዘወረደ
በዚህ ሳምንት የቃል ርደት፣ የወልድ ልደት፣ የአዳም ድኅነት ቢነገርም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ፣ በክብር ያረገ በኩረ ትንሣኤ መሆኑ አይዘነጋም፡። ለዚህም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ነገር ግን ምስክርነታችንንም አትቀበሉትም። በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁኝ፥ በሰማይ ያለውን ብነግራችሁ እንዴት ታምኑኛላችሁ? ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው። ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለው የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡ያመነበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዳይጠፋ፣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶታልና” እንዳለ እርሱ ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ነው። (ዮሐ.፫፥፲፩-፲፮) “ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ” ስለ ፍቅሩ በፈጠረው የተጠመቀ ሰማያዊ ነው።
ጾመ ድጓው የሚጀምረውም እንዲህ በማለት ነው፤ “ዘወረደ እምላዕሉ፣ አይሁድ ሰቀሉ…. እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ በቃሉ፤ ….በቃሉ የሚያድነውን ከላይ የወረደውን የሁሉን ጌታ አይሁድ ሰቀሉት…”

✨✨ልዩ መልዕክት✨✨
ሰሞኑን እናት ግቢ ጉባኤ መርቃችሁ የሸኘቻችሁ ውድ ተመራቂ ወንድም እህቶቻችን በምትሄዱበት መንገድ ሁሉ መልካም ነገር ይገጥማችሁ ዘንድ ግቢ ጉባኤ መልሙን ሁሉ ትመኝላችኋለች።
ከተመረቃችሁም በኋሏ እዚህ ያላችሁን መንፈሣዊ አገልግሎት ታስቀጥሉት ዘንድ በአዲስ አበባ ያሉ የግቢ ጉባኤ ወንድም እህቶቻችሁ በጽዋ ማኅበር ተሰባስበው መንፈሣዊ አንድነታቸውን እያስቀጠሉ ስለሆነ በተላይ አድራሻችሁን አዲስ አበባ ያደረጋችሁ ጊዜ ሳትሰጡ ማኅበሩን እንድትቀላቀሉ ይሁን። ወንድም እህቶቻችሁ እናንተን ለመቀበል ዝግጁ ሆነው ይጠብቋችኋል።በድኅረ ግቢ ጉባኤ መርሐግብር የተለያዩ መንፈሣዊ አገልግሎትም እየተካሄደ በመሆኑ ከታች የተቀመጠውን የቴሌግራም ሊንክ በመጫን ተቀላቀሏቸው። ከአዲስ አበባ ውጭ ላላችሁም ጭምር ቴሌግራሙን ተቀላቀሉ። የምትፈልጉትን ጥያቄም እና ትብብርም ለመጠየቅ ያመች ዘንድ ቴሌግራም ቦት ስላላቸው፣በቦቱም በመመዝገብ መንፈሳዊ አንድነታችሁን እንድታጠናክሩ ስትል ግቢ ጉባኤ ታሳስባችኋለች🙏
▮የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ግቢ ጉባኤ
⚪️https://t.me/+VFuzucnDHtEyM2Jk
⚪️https://t.me/WKU_DGG_registered_bot
🏷በየወሩ ቅዱስ ማካኤል በዋለ ዕለተ እሑድ 6:30(በመማሪያ ክፍሎች)
🏷በ6-ኪሎ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ታገኟቸኋላችሁ።