Dernières publications de The Ethiopian Economist View (@wasealpha) sur Telegram

Publications du canal The Ethiopian Economist View

The Ethiopian Economist View
[email protected](0913243956)
23,656 abonnés
293 photos
2 vidéos
Dernière mise à jour 05.03.2025 21:41

Le dernier contenu partagé par The Ethiopian Economist View sur Telegram

The Ethiopian Economist View

23 Feb, 13:07

10,962

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ ህመም እየገጠመው ነው!

ኢኮኖሚው የውጪ ምንዛሬ ቢያከማችም! መልሶ የሚሸጥበት የኢትዮጵያ ብር አቅርቦት እጥረት ገጥሞታል!

ባንኮች የጥሬ ብር አከማችተዋል ብለው ለሚያስቡት ተቋም እና ግለሰብ የጊዜ ገደብ ቁጠባ ከ20 ከመቶ በላይ ወለድ እንደሚያስቡ እየተደራደሩ ነው!

በጊዜ ገደብ ገንዘብ መቆጠብ ያለውን እድል እና ስጋት እንመልከት....

በዝርዝር አዲሱን ህመም እንፈትሽ....https://youtu.be/y6Ug5H6zk2k
The Ethiopian Economist View

22 Feb, 12:18

10,576

አሜሪካ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ልትወጣ ስለማሰቧ እየገለፀች ነው!

ምክንያታቸው UN ባለ ትልቅ በጀት አዋጪዋን ሀገር አሜሪካንን ማስቀደም አልቻለም ነው!

አሜሪካ 28% (በ2022 ብቻ 18 ቢሊየን ዶላር ከፍላለች)፤ ቻይና 15%፤ ጃፓን (8.5%)፤ ጀርመን እና እንግሊዝ በተከታታይ ከፍተኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጀት ድርሻ የያዙ ናቸው።

የድርጅቱ አባል ሆነው የሚጠበቅባቸውን የበጀት መዋጮ የማያደርጉ ሀገራት ጥቂት አይደሉም! ለምሳሌ ኢራን፤ ባርባዶስ፤ ኮሞሮስ፤ ኮንጎ፤ ጊኒ፤ ፓፓዋ ኒው ጊኒ፤ ቬንዙዌላ፤ ሱዳን እና ሳዎቶሜ ናቸው።

ኢትዮጵያ በ2022 (289 ሺ ዶላር)፤ በ2023 (292ሺ ዶላር)፤ በ2024 (315 ሺ ዶላር)፤ 2025 (340ሺ ዶላር) መዋጮ አድርጋለች!

የአሜሪካንን መውጣት እንደ አንድ ሃገር መውጣት ለመመልከት ከባድ ነው!

መግለጫውን ማንበብ ለምትፈልጉ https://www.whitehouse.gov/presidential-actions/2025/02/withdrawing-the-united-states-from-and-ending-funding-to-certain-united-nations-organizations-and-reviewing-united-states-support-to-all-international-organizations/
The Ethiopian Economist View

20 Feb, 17:20

10,261

ዩክሬን ለጦርነት የተሰጣትን 500 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ በተፈጥሮ ሃብት መክፈል አለባት! የማታሸንፉትን ጦርነት ማን ጀምሩ አላችሁ (ትራምፕ!) በራሽያ እና በዩክሬን መካከል የተጀመረው ጦርነት 3 ዓመት ሞላው!

ጦርነቱ እንዲያበቃ አሜሪካ እና ራሽያ ውይይት ቢጀምሩም ዋናዋ የሚመለከታት ሀገር ዩክሬን ለውይይቱ አልተጋበዘችም!

ዩክሬን ለጦርነት የተሰጣትን 500 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ በተፈጥሮ ሃብት መክፈል አለባት! የማታሸንፉትን ጦርነት ማን ጀምሩ አላችሁ (ትራምፕ!) እየተባለ ነው!

የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚ ከጦርነቱ 3 ዓመት በፊት እና ከጦርነቱ ጀምሮ ላለፊት 3 ዓመታት ከፋፍለን እንመልከተው....

ዩክሬን ለውድመት የዳረጋትን የ500 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ እንዴት አድርጋ መክፈል እንደምትችል እንመልከት....https://youtu.be/cyR3sOAkZxM
The Ethiopian Economist View

20 Feb, 10:18

14,061

#መልካም_ዜና: አሊባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ #በኢትዮጵያ_ብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀምር አስታወቀ!

አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም የሆነው አሊ ባባ እንደገለፀው ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ #በአሊ_ኤክስፕረስ የበርካታ አገራትን ገንዘብ ጥቅም ላይ ያውላል፡፡

ከእነዚህ አገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፤ ግብፅ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል፡፡ የክፍያ መፈፀሚያ ገንዘቦችን ማስፋፋት ያስፈለገው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች በስፋት ተደራሽ ለመሆን በማሰብ እንደሆነ የጠቀሰው አሊ ባባ በተጨማሪም በአለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና #የውጭ_ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማስቀረት እንደሆነ አስረድቷል፡፡

የአፍሪካ አገራትን ገንዘብ በግብይቱ ውስጥ ጥቅም ላይ ማዋሉ በአለም አቀፍ የክፍያ ስርአት የተነሳ ለአፍሪካዊያን ትልቅ ማነቆ የሆነውን ችግር ለመቅረፍ ማቀዱንም አስታውቋል፡፡ በዚህም አዳዲስ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎችን እንደሚያገኝ ተስፋ ሰንቋል፡፡

ለዚህ እንዲረዳው በተጠቀሱት አገራት ከሚገኙ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ጥምረት መፍጠሩን የገለፀው አሊ ባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ማለትም #የካቲት_17 ጀምሮ ብርን ጨምሮ የተለያዩ ገንዘቦችን በግብይት ስርአቱ ውስጥ እንደሚያካትት አስታውቋል፡፡

#ለምሳሌ፦ አሊባባ ከቴሌ ብር ጋር ለመስራት ቢስማማ ከአሊ ኤክስፕረስ ላይ ኦንላይን/Online እቃ ለመግዛት ቴሌ ብር ተጠቅሞ መክፈል ይቻላል ማለት ነው!
The Ethiopian Economist View

18 Feb, 17:19

10,514

የንግድ ጦርነት (Trade War)!

በዓለም ላይ ላለፉት 150 ዓመታት የንግድ ጦርነት ልምምዶች አሉ!

በንግድ ጦርነት ደጋፊዎች እና ተቺዎች መካከል ክርክር አለ!

የንግድ ጦርነት ምንነት፤ በዓለም ላይ የነበሩ ጦርነቶች፤ ጦርነት ውስጥ ያሉ እድሎች እና አደጋዎችን በምሳሌ እንመልከት.....https://youtu.be/ZcnRGR9oqpY
The Ethiopian Economist View

18 Feb, 12:41

9,324

#ምን_ማለት_ነው?

"ኢትዮጵያ ለውጭ ባንኮች ፈቃድ የምትሰጠው #ለወዳጅ_አገራት መሆኑን የብሄራዊ ባንክ ገዥ ተናገሩ....

ጥሩ ስም ያላቸው አለም አቀፍ ባንኮች በኢትዮጵያ ውስጥ መሰማራታቸው ጠቃሚ ቢሆንም ፈቃድ ለማግኘት ባንኮቹ የሚገኙበት #አገር ከግምት ውስጥ እንደሚገባ....

የውጭ ባንኮቹ መነሻ አገራት ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸውና ከኢትዮጵያ ጋር ለመተባበር ፈቃደኛ መሆን ይገባቸዋል" ብለዋል።

የፖለቲካ ዓለሙ ዘላቂ ወዳጅም ጠላትም በማያድልበት ምዕዳር ውስጥ የንግድ ግንኙነትን በሚገፋ የፖለቲካ መለኪያ ለመምራት መሞከር ደካማ ምክንያታዊነት ያለው ነው!

አቶ ማሞ ምህረቱ ከመንግስታዊው ዘመን ኢኮኖሚ መጽሔት ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ!
The Ethiopian Economist View

17 Feb, 10:09

12,041

📍 ፒያሳ አድዋ ሙዚየም ፊትለፊት
የንግድ ሱቆች በ 900 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ እንዲሁም ፒያሳ ሊሴ ገ/ማሪያም ት/ቤት አጠገብ የመኖርያ አፓርትመንት በምዝገባ ላይ እንገኛለን።

🎖ለልማት ተነሺዎች አና ለመርካቶ ነጋዴዎች።

🎖መረከቢያ ጊዜ 1 አመት ከ 6ወር

🎖በዶላር ሳይሆን በኢትዮጵያ ብር ይስተናገዳሉ !!!

🎖 የሱቆቹ ስፋታቸው ከ10--- 30ካሬ

📞0974981373

❗️ፒያሳ ሊሴ ገ/ማሪያም ት/ቤት አጠገብ
👉30%ሲከፍሉ 25% ቅናሽ ያገኛሉ
በ18 ዙር ምቹ አከፋፈል 10% ቅድመ ክፍያ  የቤት ባለቤት ይሁኑ።30%ሲከፍሉ 25% ቅናሽ ያገኛሉ
  ስቲዲዮ ,,,
    ♦️46 ካሬ
    ♦️48 ካሬ
ባለ1 መኝታ:
        ♦️64ካሬ
        ♦️66ካሬ
        ♦️71ካሬ
        ♦️75 ካሬዎች
ባለ2 መኝታ:
        ♦️ 71,ካሬ
         ♦️75,ካሬ
         ♦️78,ካሬ
         ♦️91, ካሬ
         ♦️92 እና 99 ካሬ
ባለ3 መኝታ:130 እና 142 ካሬ
NB:100% ለከፈለ 25% Discount.
Nb:ምንም አይነት ዶላር  ጭማሪ አያሳስብዎትም
📣📣📣📣📣
0974981373
The Ethiopian Economist View

14 Feb, 17:25

12,355

በኢትዮጵያ ዋጋ ንረት በአንድ ዓመት ውስጥ በ13.9% ቀነሰ!

የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ወጥቷል! ሪፖርቱ ለማመን የሚከብዱ ቁጥሮችን ይዟል!

ለምሳሌ፡- የዋጋ ንረት በአንድ ዓመት ውስጥ ከ29.4% ወደ 15.5% ቀንሷል! የዋጋ ንረቱ በአንድ ዓመት ውስጥ በ13.9% ቀንሷል! የኢትዮጲያ የዋጋ ንረቱ በአምስት ዓመት ውስጥ ዝቅተኛው ደረጃ ላይ ደርሷል!

የዋጋ ንረት፤ የውጪ ምንዛሬ ግኝት፤ የረሚታንስ ግኝት (በባንኮች የሚደረጉ የግለሰቦች ዝውውር) ፤ የውጪ ንግድ ውጤት (የImport ቅነሳ እና የExport ጭማሪ)፤ የኢንተርባንክ የገንዘብ ገበያ ግብይት፤ ወዘተ፡፡

የመጨረሻውን የኢኮኖሚ ሪፎርም አዝማሚያ ማሳየት ስለሚችል የሪፖርቱን ዋና ዋና የኢኮኖሚ ግኝቶች ከገለልተኛ ተቋማት መረጃ አንጻር በንጽጽር እንመልከተው…..https://youtu.be/N8LUAYfS0Bc
The Ethiopian Economist View

13 Feb, 17:30

11,942

የአፍሪካ ሃገራት እና የብልፅግና እርቀት!

የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወቅት በመሆኑ መታወቅ ያለበት! Legatum Prosperity Index!

ስለ ፖለቲካ ሳይሆን ስለ ኢኮኖሚ እንመልከት...https://youtu.be/RcY_HAmmUbg
The Ethiopian Economist View

12 Feb, 07:09

13,449

የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ 3 የወለድ አይነት/ተመኖች ላይ ያለው ወቅታዊ መረጃ!

#ዝቅተኛ_የተቀማጭ_ገንዘብ_ወለድ_መጠን 7 በመቶ ነው! ይህም ማለት ባንክ ቤት ገንዘብ በቁጠባ ለሚያስቀምጡ የሚታሰበው የወለድ መጠን 7 በመቶ ነው፡፡

#የግምጃ_ቤት_ሰነድ_የወለድ_መጠን 14.51 በመቶ ነው! ይህም ማለት መንግስት የሚያቀርባቸውን የግምጃ ቤት ሰነዶች ለሚገዙ ተቋማት እና ግለሰቦች የክፍያ ወቅቱን ጠብቆ የሚታሰበው የወለድ መጠን 14.51 በመቶ ነው፡፡

#የብሔራዊ_ባንክ_የወለድ_ተመን 15 በመቶ ነው! ይህም ማለት ንግድ ባንኮች ከብሄራዊ ባንክ ብድር በፈለጉ ጊዜ ሲበደሩ ለብሄራዊ ባንኩ የሚከፍሉት ወይም የሚታሰብባቸው የወለድ መጠን 15 በመቶ ነው፡፡  የፖሊሲ ወለድ ተመን በመባል የሚታወቀው ይህ ወለድ የንግድ ባንኮች የብድር ወለድ የመነሻ ተመን ሆኖ ያገለግላል፡፡

#ለማስታወስ፦ የንግድ ባንኮች የብድር ወለድ በባንኮቹ እና በደንበኞች መካከል በድርድር የሚወሰን ነው።