Dernières publications de The Ethiopian Economist View (@wasealpha) sur Telegram

Publications du canal The Ethiopian Economist View

The Ethiopian Economist View
[email protected](0913243956)
23,656 abonnés
293 photos
2 vidéos
Dernière mise à jour 05.03.2025 21:41

Canaux similaires

Jafer Books 📚
27,431 abonnés
Business Info ETH
16,118 abonnés

Le dernier contenu partagé par The Ethiopian Economist View sur Telegram

The Ethiopian Economist View

05 Mar, 12:13

3,604

ባንኮች ካሽ የሚገዙበት ዋጋ #ውድ በመሆኑ #በጣም_ውድ በሆነ ዋጋ እየሸጡት ነው!

የብድር ወለድ ከፍተኛ መሆን እዳው የተበዳሪ ነው!

የባንኮች የስራ ማስኬጃ ወጪ መጨመሩ ከቀጠለ የወለድ መጠን መጨመሩ ይቀጥላል!

ብሄራዊ ባንክ የካሽ እጥረትን እንዴት ሊፈታ ይችላል?

የቁጠባ ወለድ መጠንን መጨመሪያ ትክክለኛ ጊዜ መቼ ነው?

በዝርዝር እንመልከታቸው....https://youtu.be/_H_uBCHgVBE
The Ethiopian Economist View

04 Mar, 13:32

4,855

#ለመረጃ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ወለድ መጠኖች ላይ ማሻሻያ/ጭማሪ ተደረገ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በተለያዩ የብድር ዓይነቶች ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታዉቋል።

ይህ ጭማሪ የመጣው መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት አካል እንደሆነ ባንኩ ገልጿል።

በተደረገው ማስተካከያ መሰረት፦

የግብርና ብድሮች እስከ 15.5%፣

የንግድ ብድሮች እስከ 18%፣

የወጪ ንግድ ብድሮች እስከ 14%፣

የግል ብድሮች ደግሞ እስከ 15% ማሻሻያ ተደርጎባቸዋል።

ይሁን እንጂ ለኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ብድሮች የወለድ ምጣኔ በ12 በመቶ እንደነበረው ይቀጥላል ተብሏል።

የውጭ ምንዛሬ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ሰራተኞች የግል ብድሮች በስምምነቱ ውል ላይ በመመስረት ከ11 በመቶ እስከ 13 በመቶ የሚደርስ ሲሆን፣ ለየት ያለ ከፍተኛ ዋጋ ላላቸው ደንበኞች ሰራተኞች የግል ብድሮች በ12 በመቶ እንደነበረው እንደሚቀጥልም ታውቋል።

ምንጭ :- ካፒታል ጋዜጣ
The Ethiopian Economist View

03 Mar, 16:54

5,825

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ 4 ወሳኝ ወቅታዊ መረጃዎችን እንጠይቃለን!

ባንኩ ተገማች አለመሆኑ ለገበያው አደጋም አለው! https://youtu.be/7pvPOdSw5V4
The Ethiopian Economist View

02 Mar, 15:35

7,572

የራሽያ ኢኮኖሚ 28,000 ማዕቀብ ተቋቁሞ እንዴት አደገ?

ኢኮኖሚው ለ3 ዓመት ጦርነት ውስጥ ሆኖ እጥፍ የGDP እና የፖለቲካ አጋርነት እድገት አስመዝግቧል!

የራሽያ ኢኮኖሚ ( ፑቲን) በጦርነት እና በማዕቀብ ውስጥ ሆኖ ኢኮኖሚን የማሳደግ ምሳሌ ሆነዋል!

ራሽያ ላለፉት 3 ዓመታት 28,000 ማዕቀብ ቢጣልባትም ኢኮኖሚዋ ማዕቀብ ከጣሉባት ሃገራት የተሻለ እድገት ማስመዝገቡን IMF እየመሰከረ ነው!

ጠለቅ አድርገን እንመልከተው.....https://youtu.be/wkH0Ln2QgVE
The Ethiopian Economist View

28 Feb, 16:39

8,101

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ 27 ባንኮች በተሳተፉበት ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ136 ብር ቢሸጥላቸውም ንግድ ባንኮቹ ከ3 ቀን በኋላ አብዛኞቹ የመሸጫ ዋጋ ለውጥ አላደረጉም!

የ10 ባንኮችን የተከታታይ 3 ቀናት የዶላር የመሸጫ ዋጋ ስንመለከት ያደረጉት ለውጥ የሚጠበቅ አይደለም!

ባንኮች ዶላር ከገዙበት በታች እየሸጡ ያሉበት ድራማ መነሻው ምንድን ነው?

ከጨረታው በኋላ እድል የተከፈተላቸው ባንኮች....

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዶላር የሸጠው ገበያው ውስጥ ወርቅ ለመግዛት የበተነውን ብር ለመሰብሰብ ነው ወይስ ለወርቅ ሸመታ ብር አጥሮት ብር ለማግኘት?

በዝርዝር እንመልከተው.....https://youtu.be/LDONqlkHZMs
The Ethiopian Economist View

25 Feb, 17:19

11,262

ብሄራዊ ባንክ ገበያውን አረጋጋለሁ ብሎ ብርን ለምን ከ8-10 ብር ድረስ ለማዳከም ወሰነ?

ብሔራዊ ባንክ በዛሬው የዶላር ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 135.61 ብር ዋጋ መሸጡን አስታወቋል!

ከዛሬው የመደበኛ ባንኮች የምንዛሬ ተመን አንፃር ብር ከ8-10 ብር ተዳክሟል!

የዚህ ጨረታ ዋጋ መጋነን ምክንያት ምንድን ነው?

የብር መዳከም ከነገ ጀምሮ በገበያው ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ምን ሊሆን ይችላል?

ብሄራዊ ባንክ የምንዛሬው ዋጋው መጋነኑን ከተመለከተ በኋላ ጨረታውን ለምን አልሰረዘም?

በፍፁም የጨረታው ዋጋ ብርን በጣም ያዳክማል ብዬ አላሰብኩም ነበር! በዝርዝር እንመልከተው....https://youtu.be/Q0LmEXlEMdU
The Ethiopian Economist View

25 Feb, 13:34

9,184

#ለመረጃ፡ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው የዶላር ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 135.61 ብር ዋጋ መሸጡን አስታወቀ።

ጥያቄው ንግድ ባንኮቹ ለውጪ ምንዛሬ ፈላጊው በስንት ሊሸጡ ነው?
The Ethiopian Economist View

24 Feb, 17:45

9,909

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የ60 ሚሊየን ዶላር ጨረታ አወጣ! የዶላር ጨረታው የዶላር ዋጋን ይወስናል?

የመጀመሪያው የዶላር ጨረታ ከኢኮኖሚ ለውጡ 10 ቀን በኋላ (ነሃሴ 1/2016) ነበር አንድ ዶላር 107.9 ብር ዋጋ ወጥቶለት የነበረው!

ከ6 ወር በኋላ 60 ሚሊየን ዶላር ለጨረታ ቀርቧል! በገበያው ምን አይነት ለውጥ ሊያመጣ ይችላል?

የመጀመሪያው ጨረታ የሚገመት ውጤት አልነበረውም!

ከአሁኑ ጨረታ የውጪ ምንዛሬ ገበያው ለውጥ ሊኖረው ይችላል...https://youtu.be/FUqXEb_oM2c
The Ethiopian Economist View

24 Feb, 12:40

9,288

#ለመረጃ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡

ለጨረታ የሚቀርበው የውጭ ምንዛሪ መጠን 60 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ጨረታው ለሁሉም ባንኮች ክፍት እንደሚሆን ታውቋል።
The Ethiopian Economist View

24 Feb, 11:40


The Ethiopian Economist View pinned «የኢንቨስትመንት አዋጭነት ጥናት (Feasibility Study)፤ የቢዝነስ ፕላን (Business Plan)፤ የአካባቢ ተፅዕኖ ሰነድ ግምገማ (Environmental Impact Assessment )፤ የመመረቂያ ጥናት ወይም Research እየሰራችሁ ድጋፍ (Advice) የምትፈልጉ...... Email:- [email protected] Phone:- 09-13-24-39-56 YouTube፦ https:/…»