ኅዳር 16/2017 (አዲስ ዋልታ) በእስራኤል ሐማስ ጦርነት ምክንያት ካለፈው ዓመት ጀምሮ በጋዛ ሰርጥ በደረሱት ጥቃቶች ከ1 ሺሕ በላይ ዶክተሮች እና ነርሶች መገደላቸውን የጋዛ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ከ310 በላይ ሌሎች የህክምና ባለሙያዎች መታሰራቸው እና በእስር ቤቶች መገደላቸውንም ተናግረዋል።
የህክምና ቁሳቁሶች፣ የጤና ልዑካን ቡድን እና የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ወደ ጋዛ እንዳይገቡ ሁኔታዎች አመቺ ሳይሆኑ መቀጠላቸውን አስረድተዋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።
በጦርነቱ ምክንያት የሟቾች ቁጥር እስካሁን ከ44 ሺሕ አልፏል።