Últimas publicaciones de FMC (Fana Media Corporation) (@waltatveth) en Telegram

Publicaciones de Telegram de FMC (Fana Media Corporation)

FMC (Fana Media Corporation)
This is Fana Media Corporation’s (FMC) official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
49,143 Suscriptores
44,682 Fotos
231 Videos
Última Actualización 06.03.2025 12:53

El contenido más reciente compartido por FMC (Fana Media Corporation) en Telegram

FMC (Fana Media Corporation)

07 Dec, 06:44

20,028

በጂንካ ከተማ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ

ኅዳር 28/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉበት የስምንት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ።

ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከበረውን የአሪ ህዝብ የዘመን መለወጫ “የድሽታ ግና'' በዓልን እና የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተካሄደው የስምንት ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ላይ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች፣ ከተለያየ አካባቢ የመጡ እንግዶች እና አትሌቶች ተሳትፈዋል።

የአሪ ዞን አስተዳደር ከፋን ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጀው የሩጫ ውድድር "ታላቁ ሩጫ ለድሽታ ግና፤ ለሰላም እና አንድነት እሮጣለሁ!" በሚል መሪ ሀሳብ መካሄዱን ኢዜአ ዘግቧል።

በመርኃ ግብሩ ላይ አትሌት ፋንቱ ሚጌሶን ጨምሮ ሌሎች አትሌቶች እና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎች እንዲሁም አርቲስቶች ታድመዋል።
FMC (Fana Media Corporation)

06 Dec, 18:20

13,795

ሀዲያ ሆሳዕና አዳማ ከተማን አሸነፈ

ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሀዲያ ሆሳዕና አዳማ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

በድሬዳዋ ስታዲየም ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ኢዮብ አለማየሁ እና በረከት ወ/ዮሐንስ ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።

በተመሳሳይ ቀን 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው የሊጎ 10ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ስሑል ሽረ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።
FMC (Fana Media Corporation)

06 Dec, 17:39

9,905

የተሰረቁ ሞባይሎችንና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ከሌቦች በመቀበል የተጠረጠረ ግለሰብ ተያዘ

ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተሰረቁ ሞባይሎችንና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ከሌቦች በመቀበል የተጠረጠረ ግለሰብ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ጦር ኃይሎች አካባቢ ጥናትን መነሻ አድርጎ በሞባይል ጥገና ስም በተከፈተ ሱቅ ውስጥ ባደረገው ፍተሻ 29 የተለያዩ መጠን ያላቸው ሞባይል ስልኮች߹ 26 የእጅ ሰዓቶች߹ 6 የእጅ ብራስሌቶችን እና አንድ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ፖሊስ በጀመረው ምርመራ ግለሰቡ ምንም አይነት የንግድ ፈቃድ ሳይኖረው የሞባይል ጥገና አገልገሎት የሚሰጥ በመምሰል የተሰረቁ ሞባይሎችንና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ከሌቦች የሚቀበል መሆኑን አስታወቋል ፡፡

ፖሊስ የተሰረቀ እቃ የሚገዙ ህገ-ወጦች ለወንጀል መስፋፋት መንስኤ በመሆናቸው የሌባ ተቀባዮች ላይ እየተደረገ ያለው ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስቦ ንብረታቸው የተሰረቀባቸው ግለሰቦች ወደ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመሔድ መረከብ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
FMC (Fana Media Corporation)

06 Dec, 16:51

7,579

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሽዊት ሻንካ ከፀረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ማኔጅመንት አባላት ጋር ተወያዩ

ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሽዊት ሻንካ ከፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ማኔጅመንት አባላት ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ተቋሙ የተቋቋመበትን ዓላማ፣ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት እና ትኩረት የሚሸ ጉዳዮችን የሚዳስስ ሰነድ ቀርቧል።

ሚኒስትሯ በውይይቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተጣለበትን ሀላፊነት ከመወጣት አንጻር እየሰራቸው ያሉ ስራዎች አበረታች ናቸው ያሉ ሲሆን በአለም አቀፋ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የበለጠ ቅቡልነት ለማግኘት መስራት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መክዩ መሀመድ በበኩላቸው የላብራቶሪ ስራውን ትኩረት ሰጥተን በመስራት ለምርመራ ወደ ሌላ አገር በመሄድ የምናወጣው ወጭና እንግልት መቀነስ ያስፈልጋል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መኮንን ይደርሳል ጥፋተኛ ሁነው የተገኙ አካላት ተገቢውን አስተዳደራዊና የወንጀልኛ እርምጃ እንዲወስድባቸው ከፍትህና ከጤና ሴክተር ባለድረሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የዋና መስሪያ ቤት ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
FMC (Fana Media Corporation)

06 Dec, 15:52

11,130

የቱሪስት መስህቦችን መጎብኘታችን ለማስተዋወቅ መነቃቃት ፈጥሮብናል- የሚክታ አባል ሀገራት አምባሳደሮች

ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪስት መስህቦችን መጎብኘታችን ለማስተዋወቅ መነቃቃት ፈጥሮብናል ሲሉ የሚክታ አባል ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ።

ከሜክሲኮ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ቱርክ እና አውስትራሊያ (ሚክታ) ያቀፈው የጥምረቱ አምባሳደሮቸ የቱሪዝም ሚኒስቴር ድኤታ ሽለሺ ግርማ ጋር በጋራ መስራት በሚችሉበት ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።

በሚኒስቴሩ ጋባዥነት የተደረገላቸው የሁለት ቀናት የድሬዳዋ እና የሀረሪ ጉብኝት እንዳስደሰታቸው ተናግረው የቱሪስት መስህቦችን መጎብኘታቸው ለማስተዋወቅ መነቃቃት እንደፈጠረላቸውም መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
FMC (Fana Media Corporation)

06 Dec, 15:42

5,707

ሰክሮ አካባቢን ማወክ

#ሕግ_ይዳኘኝ

ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጦችን መውሰድ ለስካር ይዳርጋል፡፡ ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት የሚያስከትለው የጤና ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ ሰዎች በስካር መንፈስ የመኖሪያ አካባቢያቸውን ለረብሻሉ ይችላሉ፡፡

ስካር ድፍረትን የሚሰጥ በመሆኑ የሰከሩ ሰዎች ከአልኮል ግፊት ነጻ በነበሩበት ወቅት ማድረግ የማይደፍሩትን፣ የማይፈልጉትን እና የማይችሉትን ነገሮች ለማድረግ ይደፋፈራሉ፡፡ ይጮሃሉ፤ ይረብሻሉ፡፡

ይህ ድርጊት ግን በስካር መንፈስ ስለተደረገ ብቻ ችላ ተብሎ አይታለፍም፡፡ በሕግ ያስጠይቃል፡፡ ተገቢ እና ተመጣጣኝ ቅጣትም ያስከትላል፡፡

በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 819 መሰረት ማንም ሰው ሰክሮ ወይም አዕምሮ የሚያናውጥ ነገር ቀምሶ በሕዝብ አደባባይ የሚያስነቅፍ እና የሚያስነውር ስራ የፈጸመ፣ የማስፈራራት ንግግርን የተናገረ እንደሆነ ከስምንት ቀን በማይበልጥ በማረፊያ ቤት ይቀጣል፡፡

ይሄም ሰክሮ ሕዝብን ማወክ ሲሆን ምንም እንኳን ለከባድ አደጋ የሚያጋልጥ ባይሆንም በየሰፈራችን፣ በመጠጥ ቤቶች፣ በመንገዶች እና በተለያዩ ቦታዎች ድርጊቱ በተደጋጋሚ ሲፈጸም ይስተዋላል፡፡

በወንጀል ሕግ አንቀጽ 531 በተደነገገው መሰረት ደግሞ አልኮል በመጠጣት የሌላውን ሰው ጤንነት ለአደጋ ያጋለጠ እንደሆነ ከአንድ ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራትና በመቀጮ ይቀጣል፡፡

ይሁን እንጂ አንድ ሰው ጠጥቶ ከባድ ወንጀል ቢፈጽም የፈጸመው ወንጀል በሕግ አግባብ የሚያስቀጣውን ቅጣት ይቀበላል፡፡

በብርሃኑ አበራ
FMC (Fana Media Corporation)

06 Dec, 15:23

5,378

አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ

ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተስፋሁን ጎበዛይ ከህዳር 25/2017 ዓ.ም ጀምረው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እንዲያገለግሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተሹመዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በዛሬው ዕለት በአገልግሎቱ አመራሮችና ሠራተኞች የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ተደርጎላቸው ሥራቸውን መጀመራቸውን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
AddisWalta - AW

30 Nov, 16:56

1,017

የጁባላንዱ ፕሬዝዳንት ማዶቤ የሶማሊያ መንግስት ወታደሮቹን ከግዛቱ በ15 ቀናት ውስጥ እንዲያስወጣ አስጠነቀቁ

ኅዳር 21/2017 (አዲስ ዋልታ) የጁባላንዱ ፕሬዝዳንት አሕመድ ማዶቤ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት ወታደሮቹን ከራስካምቦኒ እንዲያስወጣ ማስጠንቀቂያ ሰጡ።

በሶማሊያ የፌዴራል መንግሥት እና በክልላዊው ጁባላንድ መሪዎች መካከል ያለው ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል።

በኬንያ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ስትራቴጂካዊ ከተማ ራስካምቦኒ የሰፈሩት የሞቃዲሾው መንግስት ወታደሮች በ15 ቀናት ውስጥ ካልወጡ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስዱ አሕመድ ማዶቤ ገልጸዋል።

አርብ እለት በኪስማዩ ከተማ መስጊድ ውስጥ ንግግር ያደረጉት የጁባላንዱ ፕሬዝዳንት ማዶቤ በአካባቢው የሚገኝ ማንኛውም የፌደራል መንግስት ኃይል “ዋጋ ይከፍላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የፌደራል መንግስቱ ወታደሮችን ወደ ራስካምቦኒ ማሰማራቱ በማዶቤ እና በደጋፊዎቹ በኩል የጁባላንድ የራስ ገዝ አስተዳደርን እንደመጣስ ተደርጎ ተቆጥሯል።

በኬንያ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘው ራስካምቦኒ ከተማ ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር በሚደረገው ውጊያ በምትጫወተው ሚና እና የጁባላንድ የኢኮኖሚ ማዕከል ከሆነችው ኪስማዮ ከተማ ጋር በቅርብ ርቀት የምትገኝ መሆኗ ስልታዊ ጠቀሜታ እንዲኖራት አስችሏታል፡፡

የሶማሊያ ፌደራላዊ መንግስት ለማዶቤ ማስጠንቀቂያ እስካሁን ምላሽ አለመስጠቱን ጋሮዌ ኦንላይን ዘግቧል።
AddisWalta - AW

30 Nov, 16:44

1,226

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠ

ኅዳር 21/2017 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል።

በዚህም መሰረት:-

1. ግርማ ሰይፉ - የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. ቆንጂት ደበለ - የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
3. ኒዕመተላህ ከበደ⁠ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
4. ይመኙሻል ታደሰ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ
5. ⁠⁠ሙባረክ ከማል- የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ
6. ሁንዴ ከበደ - የባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
7. ታረቀኝ ገመቹ - የንግድ ቢሮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ⁠ በመሆን መሾማቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
AddisWalta - AW

30 Nov, 15:45

1,684

የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ

ኅዳር 21/2017 (አዲስ ዋልታ) በእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ “Asian Infrastructure Investment Bank” (AIIB) ፕሬዝዳንት ጂን ሊኩ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ

በፕሬዝዳንት ጂን ሊኩ የተመራ የልዑክ ቡድን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እንዲሁም ከአየር መንገዳችን አመራር አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

ልዑክ ቡድኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አጠቃላይ የስራ እስቅስቃሴ ተዘዋውሮ የጎበኙ ሲሆን አየር መንገዱ በአፍሪካ አህጉር በመሪነት የሚጠቀስባቸውንና በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ያስጠበቀባቸውን የስራ ክፍሎችና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎች መመልከታቸውን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።