ኅዳር 21/2017 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት ካላት ቁርጠኝነት አንጻር ብልጽግናን ማረጋገጥ የሁሉም ዜጎች የወል እውነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ብልጽግና ፓርቲም ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እንዲሁም እውነት፣ እውቀትና ጥበብን መለያው አድርጎ ባለፉት አምስት ዓመታት ፈተናዎችን ወደ ድል በመቀየር በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል ብለዋል።
በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ድሎችም የዜጎችን ተጠቃሚነት በተግባር ያረጋገጡ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸውም በቀጣይ አምስት ዓመታት ደግሞ አዳዲስ ድሎችን በማስመዝገብ ከራሷ አልፋ ለሌሎች የምትተርፍ ሀገር ለመገንባት እንሰራለን ብለዋል።