Dernières publications de Tirita 97.6 FM Radio (@tiritaradio) sur Telegram

Publications du canal Tirita 97.6 FM Radio

Tirita 97.6 FM Radio
ትርታ 97.6 ኤፍ ኤም ''ከልብዎ የቀረበ''

ትርታ ሚዲያ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለ የንግድ መዝናኛ፣ ዜና እና ቢዝነስ ጭብጥ ያለው ሚዲያ ነው።
1,271 abonnés
955 photos
7 vidéos
Dernière mise à jour 09.03.2025 15:19

Le dernier contenu partagé par Tirita 97.6 FM Radio sur Telegram

Tirita 97.6 FM Radio

05 Feb, 14:09

154

ድሮንበአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ያለ ፈቃድ ማብረር አይቻልም- ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት
***

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ የሚደረግ የድሮን እና ሌሎች በራሪ አካላት አጠቃቀምን በተመለከተ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ተቋሙ በአዋጅ ቁጥር 1276/2014 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የመሪዎችን፣ የቁልፍ መሠረተ-ልማቶችን እና ብሔራዊ ኩነቶችን ደኅንነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የማስጠበቅ ኃላፊነት አለበት።

ተቋሙ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ የመጡ ድሮኖች እና መሰል ቴክኖሎጂ ወለድ መሣሪያዎች የሚፈጥሯቸውን ስጋቶች ለመከላከል የሚያስችል በቂ የቴክኖሎጂ እና የሰው ኃይል ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።

ሥራው ውጤታማ እንዲሆንም ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እና ጠንካራ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እንደሚፈልግ በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

በተለይ ከመጪው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ጋር ተያይዞ ቅንጅቱን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ማኝናውም አይነት ድሮን ያለ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት ፈቃድ ማስነሳትም ሆነ ማብረር እንደማይቻል መግለጫው አመልክቷል፡፡

በሥራ ምክንያት ድሮኖች መጠቀም አስፈላጊ ከሆነ ጠያቂው አካል የበረራውን ዓላማ፣ የሚበርበትን ቦታ፣ የድሮኑን አይነት እና የሞዴል ቁጥር በመጥቀስ አስቀድሞ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን መጠየቅ እና ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባ መግለጫው አስታውቋል፡፡

ይህ ሳይሆን ቀርቶ በዘፈቀደ የሚኒሱ እና የሚበሩ ድሮኖች ካሉ ተቋሙ አዲስ አበባንና ዙሪያዋን በጸረ-ድሮን ቴክኖሎጂ ያጠረ በመሆኑ በእነዚህ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም በማንኛውም ጊዜ ድሮኖቹን ከአየር ላይ በመለየት፣ በመጥለፍ እና ወደ አስፈላጊው ቦታ በማሳረፍ እንዲሁም የድሮን አብራሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ተጠያቂነት የሚያረጋግጥ መሆኑን አገልግሎቱ አመልክቷል፡፡

ከሥራ ጋር በተያያዘ ድሮኖችን መጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም አካል በ+251 983 00 02 98 እና +251 983 00 04 01 ስልክ ቁጥሮች በመደወል ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት እንደሚችል በመግለጫው አስታውቋል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

02 Feb, 09:06

276

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።

ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) በከፍተኛ ድምፅ መርጧቸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ተመራጩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

በተያያዘ ዜና ጉባኤው ተመስገን ጥሩነህን እና አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንቶች አድርጎ እጅግ መርጧል።

ሁለቱ ምክትል ፕሬዚደንቶች በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

31 Jan, 12:25

299

ብናልፍ አንዷለም የአሜሪካ አምባሳደር ሆኑ
***
አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት አማካኝነት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

30 Jan, 15:17

315

''እንደ ጊዜው'' የድምፃዊ ማሚላ ሉቃስ የሙዚቃ አልበም ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ይለቀቃል።

በሰዋሰው መልቲሚዲያ በኩል ከሚለቀቁ አልበሞች መካከል አንዱ መሆኑን እና ለስድስት አመታት የተለፋበት ስራ እንደሆነ በስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ተጠቅሷል።

በአልበሙ ላይ በግጥምና ዜማ ይልማ ገ/አብ፣ ናትናኤል ግርማቸው ጨምሮ በርካታ ባለሙያዎች እንደተሳተፉበት ተነግሯል።

በጋዜጣዊው መግለጫ ላይ የተገኙት የሰዋሰው መተግበሪያ ማናጀር ሀብቱ ነጋሽ: 13 ትራክ የያዘው አልበም፤ የፊታችን ጥር 30 ጀምሮ በሰዋሰው አፕ እና በሰዋሰው ዩቲዩብ ገፅ ላይ እንደሚለቀቅ ገልፀዋል።

አልበሙ በተለቀቀ በሳምንቱ ደግሞ አንድ የሙዚቃ ክሊፕ ለአድማጭ ተመልካች ለማድረስ በዝግጅት ላይ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል።

(በንጉሱ በሪሁን)

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

27 Jan, 12:15

359

የመጀመሪያው የሰብዓዊ ትምህርት ቤት ተከፈተ
‎***
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰብዓዊ ትምህርት ቤት ማስጀመሪያ መርሀግብር በዛሬው እለት አከናውኗል።

ማህበሩ የሰብዓዊ ትምህርት ቤት ለማስጀመር ያስችለው ዘንድ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎቾንና ተቋማትን በማሳተፍ ጥናት ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጿል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ:- ማህበሩ በሀገሪቱ በተለያዩ ምክንያቶች ለተጎዱ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍን ከማድረጉ ባለፈ የትምህርት ተቋምን በመክፈት የሰብዓዊነት ጽንስ ሀሳብ በሳይንሳዊ መንገድ አስደግፎ ተደራሽ ማድረጉ ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

ማህበሩ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ የመንግስት ድጋፍ እንደማይለየው ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቱ በአዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ የተከፈተ ሲሆን፣ አስፈላጊ ዝግጅቶች ተደርገው መጠናቀቃቸውንም የማህበሩ ፕሬዝዳንት አበራ ቶራ ተናግረዋል።

ትምህርቱ የሚሰጠው በስቴሻል ዲፕሎማ ሲሆን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሆኖ በሁለት ሴሚስቴር የሚሰጥ መሆኑንም ገልጸዋል።

ለትምህርቱ 9 የትምህርት ዓይነቶች የተዘጋጁ ሲሆን በበይነ መረብና በአካል ይሰጣል።

የሰብዓዊ ትምህቱን የሚሰጡ መምህራን የሀገሪቱን እሴት የሚያውቁና ሰብዓዊነትን የተረዱ ታላላቅ ሰዎች መዘጋጀታቸው የተገለጸ ሲሆን ትምህርቱን ለመማር ቢያንስ የማስተርስ ዲግሪ ያስፈልጋል ተብሏል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

27 Jan, 09:50

308

በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ ከ2 ሺህ 300 ሊትር በላይ ቤንዚን ተያዘ
**
በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ 2 ሺህ 360 ሊትር በላይ ቤንዚን መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ስሙ ሰንጋ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን ወንጀል ፈፃሚ ግለሰቦቹ ከመንግስት የግብይት ስርዓት ውጭ ለመሸጥ እና ትርፍ ለማግኘት በማለም ቤንዚኑን እንደደበቁ ተገልጿል።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ቤንዚኑ በህገ-ወጥ መንገድ በአንድ ኮንቴነር ውስጥ በጀሪካን ተሸሽጎ መያዙን የገለጸው ፖሊስ፤ ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ አሳውቋል።

ህብረተሰቡ በመሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

23 Jan, 10:22

247

ምክር ቤቱ ስመኝ ውቤን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ አድርጎ ሾመ
***
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባው ስመኝ ውቤን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ አድርጎ ሾሟል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ዶ/ር የኔነህ ስመኝን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂ፣ እንዲሁም አባይነህ አዴቶን ደግሞ  የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የዘርፍ ዕንባ ጠባቂ አድርጎ በሙሉ ድምጽ ሾሟል፡፡

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

20 Jan, 19:26

466

ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ - መሐላ ፈጽመዋል፡፡

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

20 Jan, 18:26

379

የፊታችን እሁድ ሶስተኛው የየሺህ ጋብቻ ስነ ስርአት በአዲስ አበባ ይከናወናል።
***

የየሺህ ጋብቻ ካርኒቫልና ኤክስፖ ለሶስተኛ ጊዜ እሁድ ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ያሜንት ኢቨንትስ እና የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ይፋ አድርገዋል።

"ቤተሰብን መመስረት ሀገር መገንባት ነው" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የሺህ ጋብቻ ካርነቫልና ኤክስፖ አርብ ጥር 16 ቀን 2017 ዓም በሚሊኒየም አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን፣ ከአንድ ሺህ በላይ ጥንዶች እሁድ ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሞሸሩ አዘጋጆቹ ዛሬ በኃይሌ ግራንድ ሆቴል በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚህ የጋብቻ ስነ-ስርአት ላይ የዓለም ክብረ ወሰንን ለመስበር እና ድንቃድንቅ መዝግብ ላይ ለማስመዝገብ 2017 ኪሎ ግራም የሚመዝን ድፎ ዳቦ ተጋግሮ ለአንድ ሺህ ሙሽሮች ክብር እንደሚቆረስ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከ12 ሺህ በላይ በሚሆኑ የቡና ሲኒዎች ኢትዮጵያዊ የቡና አፈላል ባህልን ለዓለም የማስተዋወቅ ስራ ይሰራል ተብሏል።

የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር  ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ፣ የየሺ ጋብቻ መርሐግብር የኢትዮጵያን ባህልና እሴትን ከአፍሪካ አልፎ ለዓለም የሚያስተዋውቅ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሁሉም አካላት ለስኬታማነቱ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በእሁዱ የሺህ ጋብቻ ስነስርዓት ላይ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ 1 ሺህ ጥንዶችና ከመላው አፍሪካ የሚመጡ 250 ጥንዶች በአንድ ላይ የሚሞሸሩበት ድግስ መሆኑን የገለጹት የያሜንት ትሬዲንግ መስራችና ስራ አስኪያጅ አስናቀ አማኑኤል ናቸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከአፍሪካ አገሮች ለሚመጡ ተጋቢዎች የትኬት ክፍያው ላይ በቂ ማስተካከያ እንዲያደርግና የበኩሉን ድጋፍ እንዲያበረክት እየተነጋገርን ነው ብለዋል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

20 Jan, 15:28

321

ፖሊስ የጥምቀት በዓል በተከበረባቸው የተለያዩ ስፍራዎች ላይ የሥርቆት ወንጀል የፈፀሙ ከ20 በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውንና በተወሰኑት ላይም የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የበዓሉን ሠላማዊነት በቅርበት ለመከታተል በተለያዩ የበዓሉ ማክበሪያ ስፍራዎች ላይ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ በማቋቋም የምርመራ እና የክትትል ቡድን በማዋቀር ከፍትህና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ባከናወነው ተግባር ወንጀልን እና የወንጀል ስጋቶችን መቆጣጠር መቻሉን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ከ20 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና በተወሰኑት ላይም የቅጣት ውሳኔ መተላለፉንም ገልጿል።

ይኸውም ብርሀኑ አበበ የተባለው ተከሳሽ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አበበ ቢቂላ ስታዲዮም በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ በርካታ ሰው መሰባሰቡን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ የስርቆት ወንጀል ፈፅሟል ብሏል፡፡

ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ተከሳሹ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ በግምት 3:00 ሰዓት ገደማ ከሁለት ግለሰቦች ኪስ ውስጥ 2 ሞባይል ስልኮችን ሰርቆ እጅ ከፍንጅ መያዙን ጠቅሷል።

ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ካጠናቀቀና አቃቤ ህግ ክስ ከመሰረተ በኋላ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በበዓሉ ስፍራ በተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት በዚያው ዕለት ተከሳሽ ብርሃኑ አበበ በ2 አመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደተወሰነበት የፖሊስ መምሪያው መረጃ ያመለክታል። 

በተመሳሳይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ በነበረው የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ስፍራ ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በእስራት ተቀጥቷል፡፡

ታዘበው ሞላ የተባለው ይኸው ተከሳሽ በበዓሉ ከታደሙ አንዲት ግለሰብ ላይ ሞባይል ስልክ ሰርቆ በድጋሚ ከሌላ ሰው ላይ ሊሰርቅ ሲሞክር በህብረተሰቡ ትብብር እጅ ከፍንጅ ተይዞ በስፍራው በተቋቋመው ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ ከተጣራበት በኋላ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ዛሬ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም የተከሳሽ ታዘበው ሞላን ጉዳይ የተመለከተው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ  ምድብ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን በተፋጠነ ችሎት በማየት ጥፋተኝነቱን በማስረጃ በማረጋገጥ በ6 ወር እስራት እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል በጃን ሜዳ በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ስነ ስርዓት ላይ የታዳሚውን ብዛት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ተመሳስለው ገብተው ወንጀል የፈፀሙ 21 ተጠርጣሪዎች በፖሊስ እና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ አግባብ እየታየ ይገኛል ሲል ፖሊስ አስታውቋል

ከአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ተጠርጣሪዎቹ የስርቆት፣ የቅሚያ እና የራስ ያልሆነን ንብረት ይዞ መገኘት ወንጀል የፈፀሙ ናቸው ተብሏል፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ  እጅ ላይ የወንጀል ፍሬ የሆኑ እና የተለያየ አይነት ሞዴል ያላቸው ዘጠኝ ሞባይል ስልኮች በኤግዚቢትነት እንደተያዘም ተገልጿል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ