Neueste Beiträge von Tirita 97.6 FM Radio (@tiritaradio) auf Telegram

Tirita 97.6 FM Radio Telegram-Beiträge

Tirita 97.6 FM Radio
ትርታ 97.6 ኤፍ ኤም ''ከልብዎ የቀረበ''

ትርታ ሚዲያ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለ የንግድ መዝናኛ፣ ዜና እና ቢዝነስ ጭብጥ ያለው ሚዲያ ነው።
1,271 Abonnenten
955 Fotos
7 Videos
Zuletzt aktualisiert 09.03.2025 15:19

Der neueste Inhalt, der von Tirita 97.6 FM Radio auf Telegram geteilt wurde.

Tirita 97.6 FM Radio

03 Nov, 13:09

176

ጥሩነሽ ዲባባ በዛሬው የኒው ዮርክ ማራቶን ትሮጣለች።
***

የ39 አመቷ ጥሩነሽ: የዛሬው የኒው ዮርክ ማራቶን ከስድስት አመት በኋላ ወደ ማራቶን ውድድር የተመለሰችበት መድረክ ነው።
ሰንበሬ ተፈሪ በውድድሩ ከፍተኛ ግምት የተሰጣት ስትሆን ፣ የኬንያዎቹ ሄለን ኦቢሪ፣ ሻሮን ሎኬዲ እና ቪቪያን ቺርዮት ከፍተኛ የአሸናፊነት ግምት አግኝተዋል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ

#ትርታ 97.6 FM
Tirita 97.6 FM Radio

03 Nov, 13:01

150

ታምራት ቶላ በኒው ዮርክ ማራቶን ለድል ይጠበቃል!
**
በዛሬው የኒው ዮርክ ከተማ ማራቶን ፉክክር በወንዶች የአምናው አሸናፊ ታምራት ቶላ ድል እንደሚያደርግ ግምት ተሰጥቶታል።

ኬንያዊው ኢቫንስ ቼቤት ሌላኛው ለድል የተገመት አትሌት ነውን

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

03 Nov, 09:30

166

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን አውሮፕላን ከነገ በስቲያ ይረከባል
****

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን የፊታችን ማክሰኞ ይረከባል፡፡

የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት አውሮፕላኑ በአየር መንገዱ ምድረ ቀደምት (Ethiopia land of origins) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው A350-1000 አውሮፕላን 400 መቀመጫዎች አሉት፡፡

አየር መንገዱ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2035 በዓመት 67 ሚሊዮን መንገደኞችን በማጓጓዝ 25 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ለማግኘት እንደሚሰራ አስታውቋል ።

በአሁኑ ወቅትም ባሉት 147 አውሮፕላኖች 139 ዓለም አቀፍ እና 22 የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ነው።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

01 Nov, 17:28

198

የላቀ የሴቶች ፖለቲካዊ ውክልና እና የአመራርነት ተሳትፎ ለምንፈልጋት አፍሪካ እጅጉን አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።

የ2024 የፓን አፍሪካ አመራር ሳውቦና ( Pan - African Leadership Sawubona) ጉባኤ በአዲስ አበባ በዛሬው እለት በራዲሰን ብሉ ሆቴል ተካሒዷል፡፡

ጉባኤውን አኪና ማማ ዋ አፍሪካ (Akina Mama Wa Afrika) የተሰኘው አህጉራዊ ተቋም ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጀው ሲኾን፣ በአፍሪካ ሴቶች ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ ተቋማት ተወካዮችና የመብት ተሟጋቾች ተሳትፈውበታል፡፡

በመድረኩም የሴቶችን የአመራርነት ተሳትፎና የፖለቲካ ውክልና በመጨመር የተሻለች አፍሪካን ለመገንባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

የታንዛኒያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ኒማ ሉጋንጊራ: እየተጠናቀቀ የሚገኘው የፈረንጆቹ 2024 እና መጪው 2025 አመት ብዙ የዐፍሪካ ሀገሮች ምርጫን ያካሔዱና የሚያካሒዱ መሆናቸውን ጠቅሰው: የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎና ውክልና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

"በአፍሪካ እንዲኖር ለምንሻው የአመራር አይነት: ሴቶች በአመራርነትና በፖለቲካ ተሳትፎ የሚኖራቸው ሚና እጅጉን መሰረታዊ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

የአኪና ማማ ዋ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር ኢዩንስ ሙሲሜ በበኩላቸው: አፍሪካ ውስጥ አሁንም ድረስ በአመራር ደረጃ ወንዶች በዝተው የተገኙበት እና የሴቶች የፖለቲካ ውክልና አነስተኛ የሆነበት ምክንያቶች ላይ ጉባኤው ትኩረት ማድረጉን ገልጸውልናል፡፡

"ለምንፈልጋት አፍሪካ እውን መሆን የሴቶች አመራርነት መጨመርና የፖለቲካ ተሳትፎ መኖር አስፈላጊ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

(ቆንጂት ተሾመ)

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

01 Nov, 15:00

129

ከጥራት ደረጃ በታች ምርት በሚያመርቱ 14 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላቸውን ምርቶች የሚያመርቱ 100 ፋብሪካዎች ላይ የኢንስፔክሽን ስራ ተሰርቷል ብሏል። በዚህም የ14 ፋብሪካ ምርቶች ከጥራት ደረጃ በታች ሆኖ በመገኘታቸው ርምጃ እንደተወሰደባቸው አመልክቷል።

እርምጃ የተወሰደባቸው ፋብሪካዎች የቆርቆሮ፣ የዕቃና የልብስ ሳሙናዎች፣ የአርማታ ብረት፣ ዱቄት ሳሙና፣ ዋየር፣ ፈሳሽ ሳሙና ማከፋፈያ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በዚህም ድርጅቶቹ ከማምረት ሂደት እንዲታገዱ፣ ምርትን ወደ ገበያ እንዳያቀርቡ የማሸግ ስራ እንዲሁም ምርታቸውን ከገበያ ላይ እንዲሰበስቡና የማስተካከያ ስራዎችን እንዲሰሩ የሚያደርግ እርምጃ ተወስዷል ብሏል።

በሩብ ዓመቱ ከደረጃ በታች በሆኑ 3 ሺሕ ካርቶን የልብስ ሳሙና፣ 543 ፍሬ ፈሳሽ የዕቃ ማጠቢያ ሳሙናዎች፣ የአሌክትሪክ ገመዶች እና 2 ሺሕ 683 ባለ 14 ዲያሜትር አርማታ ብረት ወደ ገበያ እንዳይወጣና እንዲወገድ መደረጉ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም 77 ሺሕ 356 ሽንሽን ቆርቆሮ ምርት ወደ ገበያ እንዳይወጣ የማድረግ እና 760 ጥቅል የተለያየ መጠን ያላቸው ዋየር ምርቶች ለገበያ እንዳይቀርቡና ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ በማደረግ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል ነው የተባለው፡፡

በዚህም ሸማቹ ጥራታቸውና ደህንነታቸው ካልተረጋገጡ ምርቶች በመከላከል የማህበረሰቡን ጤናና ደህንነት ማስጠበቅ መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

01 Nov, 14:58

121

የአፄ ቴዎድሮስ ጋሻ ከ150 አመታት በኃላ ወደ ሀገሩ ተመልሷል።
****
በመቅደላ ጦርነት ወቅት ከኢትዮጵያ ተዘርፎ እንግሊዝ  የተወሰደ  የአፄ ቴዎድሮስ ጋሻ ከ150 ዓመታት በኋላ ወደ ሀገሩ  ተመለሰ፡፡

ጋሻው እ.ኤ.አ በ1868 በተደረገው የመቅደላ ጦርነት በእንግሊዝ ወታደሮች ተዘርፎ የተወሰደና  አንደርሰን ኤንድ ጋርላንድ በተባለ የጨረታ ኩባንያ  አማካኝነት በኒውካስል ለጨረታ ሽያጭ ለመቅረብ የካቲት 21/2016 ዓ.ም  በእቅድ ተይዞ ነበር።

ይሁንና በባለስልጣኑ ፣ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሜቴ አባላት ፣ በልዑል ኤርሚያስ ሣህለ ስላሴ ኃይለ ስላሴ ፣ በዶ/ር አሉላ ፓንክረስት እንዲሁም የኢትዮጵያ ጥንታዊ አርበኞች ማህበር ባደረጉት ጥረት ጨረታው እንዲሰረዝና  ተደርጎ  በግዥ ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡

በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው: አፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ በ1868 ዓ.ም ከእንግሊዝ ወታደሮች ጋር ተዋግተው ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ተከትሎ በሀገሪቷ ላይ ብዙ ዘረፋ እንደተፈጸመ ገልፀው፣ ከተዘረፉት ቅርሶች መካከልም የተመለሰው ጋሻ አንዱ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ጋሻው ለኢትዮጵያ ትልቅ ፋይዳ ያለው ቅርስ እንደሆነ ጠቅሰው፣ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል ።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

31 Oct, 19:09

147

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች እርስ በእርሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ገበያ ይፋ አድርጓል።

ሙሉ ማብራሪያው ተያይዞ ቀርቧል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

31 Oct, 18:52

148

ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን በደቡብ ሪጅን፣ ሐዋሳ ከተማ አስጀመረ
*

አምስተኛ ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ዓለም የደረሰችበት የመጨረሻው ፈጣኑ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት መሆኑ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

ይህም ለተቋሟት እና ግለሰቦች ፈጣን የኔትዎርክ አገልሎት በመስጠት የስራ ክንውናቸውን ለማቀላጠፍ ሚናው ከፍተኛ ነው ተብሏል።

የግብርና፣ ማዕድን፣ ትምህርት፣ ጤና እና አገልግሎት ዘርፎች የመረጃ ልውውጥን በማሳደግ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማዳበርም ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተጠቅሷል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፥ ኩባንያው ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ያለ ተቋም ስለመሆኑ ተናግረዋል።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፥ ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም በደረሰበት ዲጂታል ቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ ሀገር እና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ እያበረከተው ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ስለመሆኑ አንስተዋል።

በዘንድሮው በጀት ዓመት የአምስተኛው ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን በ15 የሀገሪቱ ከተሞች ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

ኩባንያው የአምስተኛው ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን ከሐዋሳ አስቀድሞም በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ጂግጂጋ እና ባሕርዳር ማስጀመሩ ይታወቃል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

23 Oct, 18:47

85

ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አዲሱ ገበያ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

አደጋው በሸገር የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ መድረሱን ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ የገለጸው። በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ገልጿል።

"የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ነው" ብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በሰጡት ቃል ፥ ከሰሜን ሆቴል ወደ አዲሱ ገበያ ይሄድ የነበረ ኮድ 3 43994 ሸገር ባስ ላይ ነው አደጋው የደረሰው።

እስካሁን የ1 ሰው ህይወት አልፏል። እድሜውም ከ36 እስከ 40 የሚገመት ነው።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ህክምና ተቋም ተልከዋል ብለዋል።


#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

23 Oct, 14:05

116

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጨዋታ በጁባ ይካሄዳል።
***
በአፍሪካ ሀገሮች ዋንጫ (ቻን) የማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታዋን በደቡብ ሱዳን ጁባ እንደምታደርግ ተገለጸ፡፡

በዚሁ መሠረት የሀገራቱ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ጥቅምት 21 ቀን 2017 እና ጥቅምት 24 ቀን 2017 እንደሚከናወኑ መገለጹን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ለጨዋታውም ዛሬ ሹመታቸው የተሰማው አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ