Neueste Beiträge von Tirita 97.6 FM Radio (@tiritaradio) auf Telegram

Tirita 97.6 FM Radio Telegram-Beiträge

Tirita 97.6 FM Radio
ትርታ 97.6 ኤፍ ኤም ''ከልብዎ የቀረበ''

ትርታ ሚዲያ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለ የንግድ መዝናኛ፣ ዜና እና ቢዝነስ ጭብጥ ያለው ሚዲያ ነው።
1,271 Abonnenten
955 Fotos
7 Videos
Zuletzt aktualisiert 09.03.2025 15:19

Ähnliche Kanäle

Wazema Media / Radio
48,253 Abonnenten
Addis Standard
19,972 Abonnenten
FIDEL POST NEWS
18,229 Abonnenten

Der neueste Inhalt, der von Tirita 97.6 FM Radio auf Telegram geteilt wurde.

Tirita 97.6 FM Radio

10 Jan, 06:12

162

ኦቪድ ሪል እስቴት የጫካ ፕሮጀክት አካል የሆነ የመኖሪያ ቤት ግንባታን ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለፀ።

በ9.46 ሄክታር ጠቅላላ ስፋት ላይ የሚገነቡት ቤቶቹ በሁሉም መስመሮች ለከተማዋ መግቢያ የተመቹ መንገዶች ያሉት ነዉ ተብሏል።

ኦቪድ ሪል እስቴት በአዲስ አበባ የሚስተዋለዉን የቤት ችግር ለመቅረፍ ለዝቅተኛና ለመካከለኛ ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ መኖሪያ ቤቶችን እያቀረበ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ፣ ይህ ፕሮጀክትም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረዉ የጫካ ፕሮጀክት አንዱ አካል እንደሆነ ነዉ የተነገረዉ።

መሠረቱን የካ ተራራ ላይ ያደረገዉ ፕሮጀክቱ እስከ መሀል ከተማዋ የሚዘረጋ እንዲሁም ከእንጦጦ አንስቶ እስከ የካ አባዶ የሚደርስ ሲኾን፣ በ5 አመት ለማጠናቀቅም ዕቅድ እንደተያዘ ተነግሯል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

08 Jan, 18:58

213

6 ነጥብ 2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ልጅ ተወለደ
***
በጅማ ዞን ኦሞ ናዳ ወረዳ አንዲት እናት 6 ነጥብ 2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ልጅ ተገላግላለች፡፡

ህጻኑ በናዳ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና መወለዱን በሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ዶክተር ደሳለኝ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ህጻኑ እና ወላጅ እናት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ጤናማ አዲስ የሚወለድ የህጻን ልጅ አማካኝ ክብደት 3 ነጥብ 4 ኪሎ ግራም መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

07 Jan, 18:33

252

ጤና ሚኒስቴር ለመቄዶኒያ የአምቡላስ፣ የመድሃኒትና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
***

ጤና ሚኒስቴር የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር የአምቡላስ እንዲሁም 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የመድኃኒት እና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የጤና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ እና ሌሎችም የተቋሙ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የገና በዓልን ምክንያት በመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር ለሚኖሩ ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል።

የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ፥ ድርጅቱ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በ44 ቅርንጫፎች ከ8 ሺህ በላይ ወገኖችን እየደገፈ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይ የሚደግፋቸውን ወገኖች ቁጥር 20 ሺህ የማድረስ ዕቅድ እንዳለው ገልፀው፤ ማህበሩ በ15 ከተሞች የቅርንጫፍ ማዕከላት ግንባታ እያካሄደ መሆኑን ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

07 Jan, 15:17

246

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ!
***

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ተወስኗል።

በዚሁ መሰረት ፦

አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር፣

አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር፣

አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር፣

የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር፣

አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር

አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር ሆኖ እንዲሸጥ ተወስኗል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

06 Jan, 18:40

255

የአእላፋት ዝማሬ የምስጋና መርሐ ግብር በድምቀት ተካሂዷል።
***
ለሁለተኛ ግዜ የተዘጋጀው የአእላፋት ዝማሬ የምስጋና መርሐ ግብር በቦሌ ደብረ ሳሌም መድሃኒዓለም ካቴድራል በድምቀት ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ እና ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም ምእመናን ተገኝተዋል፡፡

የጃንደረባው ትውልድ ማኅበር ባዘጋጀው የአእላፋት ዝማሬ የምስጋና መርሐ ግብር ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናንና ምዕመናት ተሳትፈዋል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

06 Jan, 18:29

167

መልካም የገና በአል!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ:-
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል አደረሳችሁ!

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

06 Jan, 08:48

197

ፖለቲከኛና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቡልቻ ደመቅሳ በዛሬው ዕለት በ94 ዓመታቸው በሞት አርፈዋል።

ቡልቻ ደመቅሳ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ስፍራ አላቸው። በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የገንዘብ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር እንዲሁም የዓለም ባንክ የአፍሪካ ተወካይ በመሆን ሠርተዋል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቀጥረው በተለያዩ ሀገራት አገልግለዋል።

በምዕራብ ወለጋ ዞን ቦጂ ቢርመጂ ወረዳ ከአባታቸው ደመቅሳ ሰንበቶ እና ከእናታቸው ናሲሴ ሰርዳ በ1923 ዓ.ም ተወለዱ።
የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸውን በጊምቢ አድቬንቲስት እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በኩየራ አድቬንቲስት ተምረዋል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ እና በሕግ ዲግሪዎች ተመርቀዋል። በወቅቱም በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ከተመረቁ 10 ተማሪዎች መካከል አንዱ በመሆን ወደ አሜሪካ በመሄድ በሲራኪዩዝ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ቡልቻ ደመቅሳ በዘመናዊ የግል ንግድ ባንኮች ምሥረታ ታሪክ ተጠቃሽ የሆነው የአዋሽ ባንክ መሥራች ናቸው።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

04 Jan, 20:18

233

ፋብሪካው በመሬት መንቀጥቀጡ ስራ አቁሟል!
***
በአፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው ከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል። ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ስራ እንዳቆመም ተገልጿል።

በክልሉ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ በስኳር ፋብሪካው አስተዳደር ህንፃ፣ በኃይል ማስተላለፊያ ክፍል፣ የላብራቶሪ እና ኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱን የፋብካው ስራ አስኪያጅ አሊ ሁሴን ኡመር ለመንግስት መገናኛ ብዙሀን ተናግረዋል።

ጉዳት በደረሰባቸው ህንፃዎች ውስጥ የሚገኙትን ሌሎች ንብረቶችን ለማዳን የመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነባቸው ገልፀዋል።

የፋብሪካው ሰራተኞች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስቀድሞ እንዲለቁ መደረጉን ጠቅሰው፣ በፋብሪካው ንብረት ላይ ስርቆት እንዳይፈጸም ከመከላከያ፣ ፌዴራል ፖሊስ እና ከዞን ፖሊስ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያለው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆሙ ተጠቅሷል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

04 Jan, 19:55

208

በመሬት መንቀጥቀጥ ዙሪያ በባለሙያ የሚሰጡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ህብረተሰቡ እንዲከታተልና በጥብቅ እንዲተገብር የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳሰበ። የመሬት መንቀጥቀጡ እስካሁን በከተሞች ምንም ጉዳት አለማድረሱንም አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ እንዳስታወቀው፣ በአፋር፤ ኦሮሚያ እና አማራ ከልል አዋሳኝ አካባቢዎች ማዕከላቸውን አድርገው የተለያየ መጠን ያላቸው የርዕደ መሬት ክሥተቶች በተደጋጋሚ ተከስተዋል፡፡

ክሥተቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠን እና በድግግሞሽ እያደጉ ይገኛሉ። በተለይም በዚህ ሳምንት በርዕደ መሬት መለኪያ እስከ 5.8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ መንቀጥቀጥ መከሠቱን መረጃዎች ያሳያሉ።

መንግሥት የርዕደ መሬቱ ማዕከል (epicenter) የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሌዎች ላይ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረገ ይገኛል ብሏል።

በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሷል።

በተጨማሪም ርዕደቱ በማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት፤ በኢኮኖሚ ተቋማት እና በመሠረተ ልማት ላይ ሊኖረው የሚችሰውን ተጽዕኖ በመከታተል ላይ ነው ብሏል።

እስካሁን ባለው ሁኔታ በዋና ዋና ከተሞች የጎላ ተጽዕኖ ያላደረሰ ቢሆንም ዜጎች በባለሞያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መልእከቶችን እንዲከታተሉና በጥብቅ አንዲተገብሩ አሳስቧል፡፡

በቀጣይም ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል አስፈላጊ መረጃዎችን በሚመስከታቸው ተቋማት አማካይነት የሚያደርስ መሆኑን አስታውቋል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

02 Jan, 14:11

265

ኃይሌ ሪዞርት በጅማ ተመረቀ
***
ኃይሌና ዓለም ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር 10ኛውን ባለ አራት ኮኮብ ሪዞርት በጅማ ከተማ በዛሬው እለት አስመርቋል።

ሪዞርቱ በ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የተሰራ ሲሆን ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥም የተጠናቀቀ ነው።

ሪዞርቱ የእንግዶች ማረፊያ ክፍሎች፣ የምግብ አዳራሾች፣ የተለያዩ ባሮች፣ የመዋኛ ገንዳ፣ ስፓ፣ ጂምናዚየም አሉት።

ሆቴሉ ኦዲዮ ቪዥዋል መሳሪያዎች የተሟሉላቸው 5 የስብሰባ አዳራሾችና አራት ዘመናዊና ባህላዊ ምግቦችን የሚያቀርቡ ሬስቶራንቶች እንዳሉት ተነግሯል።

ሆቴሉ ከ210 በላይ ቋሚ የሥራ እድል የፈጠረ ሲኾን፣ በቀጣይ በሙሉ አቅም ሥራ ሲጀምር 400 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል እንደሚፈጥርም ተገልጿል።

በአጠቃላይ ሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ባሉት ሁሉም መዳረሻዎች ላይ ከ2 ሺህ 500 ሰራተኞች የሥራ እድል በመፍጠር እየሰራ ይገኛል ተብሏል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ