Latest Posts from TenaSeb - ጤና ሠብ (@tenaseb) on Telegram

TenaSeb - ጤና ሠብ Telegram Posts

TenaSeb - ጤና ሠብ
ሠላም- 👋
ይህ በጤና ዙርያ መረጃ የምታገኙበት ቻናል ነው::
ለበለጠ መረጃ 👉🏽 https://youtube.com/@tenaseb-?si=TAxp4fhX-YijtoJn
4,843 Subscribers
307 Photos
55 Videos
Last Updated 06.03.2025 21:36

The latest content shared by TenaSeb - ጤና ሠብ on Telegram

TenaSeb - ጤና ሠብ

03 Mar, 17:27

625

በ እርግዝና ወቅት የሚከሰት ከፍተኛ የሆነ  ማቅለሽለሽ እና ትውከት ክፍል ፩ (Hyper emesis gravidarum)

📌በእርግዝና ወቅት ሰውነት ላይ በሚፈጠሩ የሆርሞን ለውጦች ምክንያት 90% በላይ የሚሆኑ እናቶች ላይ በተለይም ከ 5 ኛ የእርግዝና ሳምንት ጀምሮ ማቅለሽለሽ እና ትውከት ይከሰታል። ይህም ቀለል ያለና ሌላ ችግር የማያደርስ ነው። 

📌 ነገር ግን ከበድ ሲል፣ ክብደት መቀነስ ሲያመጣ እና አመጋገብን በማስተካከል የማይሻል ከሆነ ህክምና የሚያስፈልገው ችግር ይሆናል።

📌ብዙጊዜ ከ አምስት ወር በኋላ በራሱ ጊዜ ይቆማል።


አጋላጭ ምክንያቶች

* መንታ እርግዝና

* ቀደም ሲል የቃር ህመም(GERD) ያለባቸው ሴቶች

* ጂቲዲ(Gestational trophoblastic disease)

* ከዚህ በፊት ወልደው የማያውቁ ሴቶች

ምልክቶቹ

🚨በቀላሉ የማይቆም ተደጋጋሚ የማቅለሽለሽ ስሜት እና ማስመለስ 

🚨 የክብደት መቀነስ: ከእርግዝና በፊት ከነበረው ክብደት 5% እና ከዛ በላይ መቀነስ

🚨የሰውነት ፈሳሽ ማነስ ጋር ተያይዘው የሚታዩ ምልክቶች: የአፍ መድረቅ፣ ቆዳ መሸብሸብ፣ 

🚨የልብ ትርታ መጨመር፣ ከፍተኛ የድካም ስሜት

🚨ምግብ ለመመገብ መቸገር፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ

🚨 የምራቅ መብዛት

ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
TenaSeb - ጤና ሠብ

01 Mar, 10:01

857

ፖሊዳክቲሊ (ትርፍ ጣቶች) (Polydactyly) ማለት አንድ ሰው ከአምስት በላይ ጣቶች በእጅ ወይም በእግር ላይ የሚኖሩበት የትውልድ ችግር ነው።

ይህ ተጨማሪ ጣት ሙሉ በሙሉ የተሰራ ወይም በቆዳ ብቻ የተያያዘ ትንሽ እጢ ሊሆን ይችላል።

ፖሊዳክቲሊ በዘር የሚተላለፍ ወይም በድንገት የሚከሰት የጄኔቲክ ለውጥ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ከሌሎች የጄኔቲክ ሲንድረምስ ጋር ሊያያዝም ይችላል።

የፖሊዳክቲሊ ሕክምና በፕላስቲክ ቀዶ ጥገና ሲሆን ይህም ተጨማሪውን ጣት ማስወገድን ያካትታል። የሕክምናው ዓላማ የእጅን ወይም የእግርን ተግባር እና ገጽታ ማሻሻል ነው።

ስለ ፖሊዳክቲሊ ወይም ስለማንኛውም የፕላስቲክ እና የመልሶ ግንባታ ቀዶ ጥገና ጤና ሁኔታ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ቀጠሮ ለማስያዝ፣ ከበታች ባሉት የማህበራዊ ገፃችን እንዲሁም በ ስልኮቻችን ያግኙን።

Dr.Abdurezak

0911416955
0907222228
Dr Abdurezak Facebook

Lucy a center for plastic reconstructive and micro surgery
Facebook
TenaSeb - ጤና ሠብ

28 Feb, 09:51

978

ጤናማ የሆነ የወር አበባ ኡደት

የአንድ ለአቅመ ሄዋን የደረሰች ሴት ሰውነቷ ላይ በሚፈጠሩ ሆርሞኖች ምክንያት በየወሩ የወር አበባ ታያለች።

ይህም ሂደት ተፈጥሯዊ የሆነ እና ለእርግዝና ብቁ መሆኗን ማሳያ ነው።

መደበኛ የወር አበባ

* በአማካኝ 5 ቀን ይቆያል።

* ከ21-35 ቀናትን በአማካኝ ደግሞ በየ28 ቀኑ ይመጣል።

* መጠኑ ከ 10-80 ሚ.ሊ ወይም በአማካኝ 50 ሚ.ሊ ደም ነው።

* የሚፈሰዉም ደም ጠቆር ያለ እና የማይረጋ ነዉ።

* የወር አበባ ዑደት ተዛባ የምንለው አንዲት ሴት ወትሮ ከምታየው የተለየ ጠባይ ሲገጥማት ነው፡፡

* በመሆኑም የሚመጣበትን ጊዜው የሚያዛባ ከሆነ፣ ከወትሮው የተለየ ብዙ ደም ፍሰት፣ መጓጎል ካለ ወይም በጣም አነስተኛ ከሆነ፣ እርግዝና ሳይፈጠር ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሳትጠቀሚ የወር አበባሽ በጊዜው ካልመጣ በተለያዩ የማህፀን ፣እንቁልጢ(Ovary)ችግሮች ምክንያት የሚከሰት የወርአበባ መዛባት ሊሆን ስለሚችል ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው።
TenaSeb - ጤና ሠብ

25 Feb, 11:28

1,212

የጆሮ መልሶ ግንባታ ሰርጀሪ በብዛት በተፈጥሮ ወይም በአደጋ ምክንያት ለሚፈጠሩ የጆሮ ቅርፅ፣ መጠን ወይም ገፅታ እክሎች ወሳኝ መፍትሄ ነው።

የፕላስቲክ እና መልሶ ግንባታ ሰርጀሪ በእኛ ማህበረሰብ የቅንጦት ተደርጎ ቢወሰድም እሄ ግን ከእውነታው የራቀ ሲሆን ለብዙሀን ሁነኛ መፍትሄ እና ሙሉ የአካላዊ እንዲሁም የስነልቦናዊ ጤንነትን የሚሰጥ ነው።



To Book appointment with Dr.Abdurezak 0911416955
0907222228
TenaSeb - ጤና ሠብ

24 Feb, 07:39

1,270

ጥያቄ: ሰላም ዶ/ር ጥያቄ አለኝ ፣ ከወለድኩ 20 ቀን ሆኖኛል ነገርግን ከአሁን በፊት አይቼ የማላዉቀዉ፡ ከማሕፅን የሚወጣ ቢጫ ፈሳሽ አለ ጠረኑም ብዙም ጥሩ ያልሆነ በፈሣሹ ምክንያት እየተረበሽኩ ነው ። ምን ማድረግ አለብኝ?

መልስ: የማህፀን ፈሳሽ ከማህፀን ጫፍ እና በዙሪያው ከሚገኙ ህዋሳት የሚሰራ በውስጡ ውሃ፣ የተለያዩ ባክቴሪያዎች እንዲሁም ዝልግልግ(mucus) የሚይዝ ፈሳሽ ነው።

📌ጤናማ የሆነ ወይም ጤናማ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ አለ።

📌ጤናማ የሆነ የማህፀን ፈሳሽ መጠኑ ትንሽ እና ነጣ ያለ መልክ ያለው፣ እንዲሁም ሽታ የሌለው አይነት ፈሳሽ ነው። ይህም የወር አበባ በየወሩ የሚያዪ ሴቶች ላይ፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች፣ የሆርሞን የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚጠቀሙ ሴቶች ላይ ይታያል። 

📌ብዙ ጊዜ ጤናማ የማህፀን ፈሳሽ ከማረጥ (menopause) በዃላ አይታይም። 

እንዴት ነው ጤናማ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽን መለየት የምንችለው?

በተለያዩ የጤና ችግሮች ምክንያት ለምሳሌ እንደ የማህፀን ኢንፌክሽን፣ የአባላዘር በሽታዎች፣ የፈንገስ ኢንፌክሽኖች እንዲሁም በማህፀን ጫፍ ካንሰር ምክንያት ተፈጥሯዊ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ ሊከሰት ይችላል።

🚨 ከወትሮው የተለየ መጠኑ የበዛ የማህፀን ፈሳሽ

🚨 መጥፎ ጠረን ያለው ፈሳሽ

🚨 ቀለሙ አረንጓዴ፣ ቢጫ ወይም እርጎ የሚመስል ነጭ የማህፀን ፈሳሽ

🚨 ከማህፀን ፈሳሹ በተጓዳኝ የሚኖር ሽንት ቶሎ የመምጣት፣ ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል ስሜት እንዲሁም የህመም ስሜት

🚨 ደም የቀላቀለ የማህፀን ፈሳሽ 

🚨 ከወር አበባ ውጭ የሆነ ወይም በግንኙነት ወቅት የሚከሰት ደም መፍሰስ ካለ 

ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶችን ካስተዋልሽ ጤናማ ያልሆነ የማህፀን ፈሳሽ ምልክት ስሆኑ ችላ ሳትይ ምርመራ ማድረግ እና ህክምና ማግኘት አስፈላጊ ነው።
TenaSeb - ጤና ሠብ

21 Feb, 15:06

1,375

📌በተደጋጋሚ ከሚደርሱን ጥያቄዎች ውስጥ📌


ጥያቄ: ልጄን ከተወለደ በኋላ እትብቱ ሳይወድቅ ሰውነቱን ማጠብ እችላለሁ?

መልስ: ህፃናት እንደተወለዱ ሰውነታቸውን ከቅዝቃዜ እና ኢንፌክሽን ለመከላከል በተፈጥሮ ቆዳቸው አይብ በሚመስል ነገር(Vernix caseosa) የተሸፈነ ነው። ይህም ቆዳቸውን የሸፈነው ነገር ቀስበቀስ በራሱ ጊዜ እየረገፈ ይመጣል።

ሌላው ጨቅላ ህፃናት ላይ መታወቅ ያለበት እና ጥንቃቄ መደረግ ያለበት ነገር እነዚህ ህፃናት የሰውነትን ሙቀት ለመጠበቅ የሚያስችሉ ተፈጥሯዊ ዘዴዎች አላዳበሩም ስለዚህ ለአነስተኛ ቅዝቃዜ በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ናቸው። ለዚህም ነው ቅዝቃዜ አንዱ ለጨቅላ ህፃናት ሞት ምክንያት ሆኖ የሚጠቀሰው።

ስለዚህ ጨቅላ ህፃናት ወዲያው እንደተወለዱ መታጠብ የለባቸውም ነገር ግን ከ24 ሰዓታት በኋላ ውሃ ላይ ነክረን እንደ ሌሎች ህፃናት ሳይሆን የምናጥባቸው፣ ለብ ባለ ውሃ እርጥብ ጨርቅ ወይም ስፖንጅ በመንከር መጠራረግ ይቻላል። እትብታቸው ከወደቀ በኋላም እንደሌሎች ህፃናት በውሃ እና ለቆዳቸው በሚስማማ ሳሙና ማጠብ እንችላለን።

ነገር ግን ሁሌም ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ለቅዝቃዜ እንዳይጋለጡ ከታጠቡ በኋላ ሙቀት እንዲያገኙ በደምብ መሸፋፈን እና ጡት ማጥባት ያስፈልጋል።
TenaSeb - ጤና ሠብ

19 Feb, 12:31

1,317

ጨቅላ ህፃናት ላይ የሚከሰት የአንጀት ቁስለት(Necrotizing Enterocolitis)

ካለ ጊዜያቸው የተወለዱ ጨቅላ ህፃናት ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ ናቸው ከነዚህም ችግሮች ውስጥ አንዱ
የአንጀት ቁስለት ነው።
ይህ ችግር በብዛት የሚከሰተው ከጊዜያቸው ቀድመው የተወለዱ ህፃናት ላይ ከተወለዱ በኋላ ከ 2 እስከ 4
ሳምንታት ውስጥ ነው።
እነዚህ ህፃናት ተገቢውን ህክምና ቀድመው ካላገኙ እስከሞት ሊያደርስ ይችላል።

ምልክቶቹ
ምልክቶቹ እንደየደረጃው ይለያያል።
*ማስለስ
*የሆድ መነፋት
*የአቅም ማጣት
*ተቅማጥ፣
*ደም የቀላቀለ ካካ
* ሆድ ሲነካ ከፍተኛ የሆነ ህመም
*ሲቆይም የአንጀት መበሳት

ምርመራው
ምርመራው በዋነኝነት አጋላጭ ምክንያቶቹን እና የህመም ምልክቶቹን በማየት ሲሆን የሆድ ራጅ እንዲሁም
አልትራሳውንድ ምርመራ ይታዘዛል።

ህክምናው
* ይህ ችግር ያለባቸው ህፃናት ምንም ምግብ በአፋቸው እንዳይወስዱ፣ ጡት እንዳይጠቡ ይደረጋል።
* በደም የሚሰጡ ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች ይሰጣቸዋል።
* እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ ቀዶ ጥገና ሊደረግ ይችላል።

ቅድመ መከላከያ ዘዴዎች
ዋናው አጋላጭ ምክንያት ካለጊዜ መወለድ ስለሆነ በእርግዝና ወቅት ጤና ተቋም ክትትል ማድረግ፣ የእንሽርት
ውሃ ቀድሞ ከፈሰሰ እንዲሁም ካለጊዜው ምጥ ከጀመረ ወዲያው የጤና ተቋም በመሄድ ጨቅላ ህፃናት
ያለጊዜያቸው እንዳይወለዱ መከላከል እና ተያይዘው ከሚመጡ ችግሮች መከላከል ይቻላል።
***
TenaSeb - ጤና ሠብ

15 Feb, 07:53

1,853

⚡️ከምጥ በፊት የእንሽርት ውሀ መፍሰስ

⚫️አንድ ነፍሰጡር እናት የእንሽርት ዉሃዋ ይፈሳል ተብሎ የሚታሰበው ምጥ ከጀመራት በኋላ ነዉ።

⚫️ነገርግን ከ 37 ሳምንት በፊት ምጥ ሳይመጣ የእንሽርት ዉሃ ከፈሰሰ ህክምና የሚያስፈልገዉ ችግር ይሆናል።

⚡️እንዴት ነዉ የእንሽርት ዉሃ መሆኑን ማረጋገጥ የሚቻለዉ?

⚫️እንደ ድንገት ሿ ብሎ የሚፈስ አይነት ዉሃ የመሰለ ፈሳሽ ካየሽ የእንሽርት ዉሃ መፍሰስ ሊሆን ይችላል።

⚫️ከዚህም በተጨማሪ ሃኪምሽ በተለያዩ ምርመራ መንገዶች የእንሽርት ዉሃ መሆኑን ያረጋግጣል።

⚡️ሕክምናዉ ምንድን ነዉ?

⚫️ከምጥ በፊት የእንሽርት ዉሃ መፍሰስ ካጋጠመ ቶሎ ወደ ሃኪም ቤት መሄድ ያስፈልጋል።

⚫️እንዲሁም ከ 8 ሰአት በላይ ካለፈዉ የኢንፌክሽን መድሃኒቶችን እንድትወስጂ ሊደረግ ይችላል።

⚡️ካልታከመ ምንአይነት ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል?

⚫️ የፅንሱ መታፈን እስከሞት ሊያደርስ የሚችል

⚫️የእትብት ከማህፀን መውጣት( cord prolapse)

⚫️የማህፀን ውስጥ ኢንፌክሽን( chorioamnionitis)

⚫️ ፅንሱ ካለጊዜው መወለድ

⚫️የእንሽርት ውሃ መጠን ማነስ እና ከዚህ ጋር ተያይዘው ፅንሱ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች

‼️ስለዚህ ምጥ ሳይጀምርሽ የእንሽርት ዉሃ ከፈሰሰ አንችም ላይ፣ጽንሱም ላይ ከሚደርስ ችግር ለመከላከል ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።
TenaSeb - ጤና ሠብ

11 Feb, 11:56

1,875

⚡️ጨቅላ ህፃናት ላይ የሚታዩ ህክምና የሚፈልጉ አደገኛ ምልክቶች

⚫️የጨቅላ ህፃናት መታመም ለቤተሰብ ከባድ ነገር ነው። ጨቅላ ህፃናት ሲታመሙ እንደ ሌላ እድሜ ላይ እንዳለ ሰው ያመማቸውን ስለማይናገሩ ሁኔታውን የበለጠ ከባድ ያደርገዋል።

⚫️ስለዚህ የህፃኑን መታመም ቀድሞ ለይቶ ማወቅ የ የወላጅ ሃላፊነት ይሆናል።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ምልክቶችን ልጅሽ ላይ ካስተዋልሽ ቶሎ ወደህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል።

⚪️ጡት በደንብ የማይጠባ ከሆነ፣ በሆነ ባልሆነው የሚነጫነጭ ከሆነ እንዲሁም እያባበልሽውም ካለማቋረጥ የሚያለቅስ ከሆነ

⚪️በተደጋጋሚ የሚያስመልሰው ከሆነ እንዲሁም ምንም ነገር ባፉ አልወስድ ካለ።

⚪️ቆዳው እንዲሁም ነጭ የአይኑ ክፍል ቢጫ እንደሆነ ካስተዋልሽ።

⚪️ ከተወለደ በ 2 ቀናት ውስጥ ምንም ካካ ነገር ከሌለው፣ ሆዱ እየተነፋ የሚሄድ ከሆነ

⚪️እትብቱ የተቆረጠበት ቦታ የሚደማ ከሆነ እንዲሁም ሌላ ፈሳሽ የሚወጣው ከሆነ

⚪️ጡት ሲጠባ የሚያቆራርጥ ከሆነ፣ ከንፈሩ እንዲሁም እጆቹ የሚጠቁሩ ከሆነ
እነዚህን ምልክቶች ካስተዋልሽ ቶሎ ልጅሽን ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል።


ለበለጡ የቪድዮ መረጃዎች👉🏼 https://youtube.com/@tenaseb-?si=amsElXsqA2PN3KGE
TenaSeb - ጤና ሠብ

09 Feb, 13:26

2,091

ጤናማ የሆነ የወር አበባ ኡደት

የአንድ ለአቅመ ሄዋን የደረሰች ሴት ሰውነቷ ላይ በሚፈጠሩ ሆርሞኖች ምክንያት በየወሩ የወር አበባ ታያለች።

ይህም ሂደት ተፈጥሯዊ የሆነ እና ለእርግዝና ብቁ መሆኗን ማሳያ ነው።

መደበኛ የወር አበባ

* በአማካኝ 5 ቀን ይቆያል።

* ከ21-35 ቀናትን በአማካኝ ደግሞ በየ28 ቀኑ ይመጣል።

* መጠኑ ከ 10-80 ሚ.ሊ ወይም በአማካኝ 50 ሚ.ሊ ደም ነው።

* የሚፈሰዉም ደም ጠቆር ያለ እና የማይረጋ ነዉ።

* የወር አበባ ዑደት ተዛባ የምንለው አንዲት ሴት ወትሮ ከምታየው የተለየ ጠባይ ሲገጥማት ነው፡፡

* በመሆኑም የሚመጣበትን ጊዜው የሚያዛባ ከሆነ፣ ከወትሮው የተለየ ብዙ ደም ፍሰት፣ መጓጎል ካለ ወይም በጣም አነስተኛ ከሆነ፣ እርግዝና ሳይፈጠር ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሳትጠቀሚ የወር አበባሽ በጊዜው ካልመጣ በተለያዩ የማህፀን ፣እንቁልጢ(Ovary)ችግሮች ምክንያት የሚከሰት የወርአበባ መዛባት ሊሆን ስለሚችል ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው።