STEM with Murad 🇪🇹 (@stemwithmurad) के नवीनतम पोस्ट टेलीग्राम पर

STEM with Murad 🇪🇹 टेलीग्राम पोस्ट

STEM with Murad 🇪🇹
Welcome to STEM with Murad! This is your one-stop destination for all things related to Science, Technology, Engineering, and Mathematics (STEM). I will share updates and insights from the exciting world of STEM. You'll also get a sneak peek into my works
11,308 सदस्य
410 तस्वीरें
14 वीडियो
अंतिम अपडेट 09.03.2025 17:55

समान चैनल

AAU MEREJA
25,005 सदस्य

STEM with Murad 🇪🇹 द्वारा टेलीग्राम पर साझा की गई नवीनतम सामग्री

STEM with Murad 🇪🇹

13 Feb, 04:31

2,999

«Sundar Pichai of Google was on AI summit in Paris ላይ በ2-4 አመታት ውስጥ AI ላይ ምን ለውጥ እናያለን? - ካላያችሁት ምናልባት ብትከታተሉት ታተርፋላችሁ::

አንድን ፕሮቲን ስትራክቸር አንፎልድ (መረዳት) ለማድረግ የ1 PhD - ከ4-5 አመት ሙሉ ግዜን የሚወስደውን አሁን 1 AI በሶስት ወር ውስጥ ብቻ 200 ሚሊየን ፕሮቲንን አንፎልድ ማድረግ ችሏል - ለማወዳደር እንኳን ይከብዳል::
3000 000 000 Ie = 3 ቢሊየን እጥፍ!

ባለፈው ወሎ ዩኒቨርስቲ AI Enhancing Diagnostic and Prognostic ዙሪያ ስናቀርብ ዶር ሰይድ ሙሄ ከሀምቡርግ ዩኒቨርስቲ Prompt Engineering የሚል ላይ ግዜ ወስዶ አውርቶ ነበር - How important it is now!

አሁን ያለው AI ለምሳሌ Programing ላይ ያግዛል more of a giving a suggestion and you can accept it! In 2-4 years ግን ከማገዝ አልፎ Agent Tech ሙሉ በሙሉ ይገባል ነው የሚለን - ትእዛዝ ብቻ መስጠት እና ሙሉ ፕሮግራሙን ይፅፈዋል ይሰራዋል! በሌላውም ዘርፍም እንደዛው!

People who don’t adopt it will be left behind!
If you are not paying for a product, you are the product»

ዶ/ር ሙሐመድ ሳኒ
STEM with Murad 🇪🇹

13 Feb, 04:20

2,756

ይሄን ነገር መስፈርቱን የምታሟሉ ተመዝገቡ።


#ማስታወቂያ

#PhDOpportunities 🎓

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለፒ.ኤች.ዲ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመሆን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የፒ.ኤች.ዲኘሮግራም ለ2ዐ17 ዓ.ም 2ኛ ሴሚስተር በመደበኛ መርሓ ግብር አመልካቾችን ተቀብለው ማስተማር ይፈልጋሉ፡፡

የኘሮግራሙ ዓላማ በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የተመራማሪዎች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች እጥረት መቅረፍ ነው፡፡ ለኘሮግራሙም ስኬት ሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የሆነ ትኩረት ሰጥተው የሚከታተሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል፡-

🟠የኮርስ መምህራንን እና አማካሪ ኘሮፌሰሮችን በወቅቱ መመደብ፣

🟠ለምርምር የሚሆኑ ሀገራዊ “Themes” መለየት፣

🟠የምርምር “Dataset” ማቅረብ፣

🟠ለምርምር የሚያስፈልጉ “Computational Resources” ማቅረብ፣

🟠ለምርምር የሚያስፈልገውን በጀት ማፈላለግ ይገኙበታል፡፡

የመመዝገቢያ መስፈርቶች

🟠ሁለተኛ ዲግሪ በተያያዥ የትምህርት ዘርፍ ከታወቀ የትምህርት ተቋም ያጠናቀቀ/ ያጠናቀቀች፣

🟠በሁለተኛ ዲግሪ “CGPA” ለሴቶች 3.ዐዐ እና ከዚያ በላይ ለወንዶች 3.25 እና ከዚያ በላይ፣

🟠የሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ጽሁፍ ውጤት “Good” እና ከዚያ በላይ የሆነ፣

🟠ሀገራዊ የድህረ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና (National Graduate Admission Test) ያለፈ/ ያለፈች፣

🟠አመልካቾች ከ1ዐ ገጽ ያልበለጠ “Synopsis” ማዘጋጀት እና ሁለት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

🟠በተጨማሪም የመመዝገቢያ ክፍያ ሁለት መቶ /200/ ብር እና የመግቢያ ፈተና (Entrance exam administration) ወጪዎች 300 ብር (ሦስት መቶ) በድምሩ 500 (አምስት መቶ) ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971544 የተከፈለበት ደረሰኝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የማመልከቻ ሁኔታ
አመልካቾች ከየካቲት 6 እስከ 20፤2017 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን ማመልከት ይችላሉ፡፡

ማንኛውም አመልካች በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገፅ ላይ ለዚሁ መመዝገቢያ ተብሎ የተዘጋጀውን ሊንክ www.aastu.edu.et/Application በመከተል መመዝገብ ይችላል፡፡

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ በቀጣይ ማስታወቂያዎች የሚገለፅ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-

+251-118-89-86-27/ +251-114-6241-78/+251-993-80-71-78

ወይም

በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ www.aastu.edu.et ገብተው ማግኘት ይችላሉ፡፡


#EAII #AASTU #PhD #PhDLife #Research #GradSchool #HigherEducation
STEM with Murad 🇪🇹

13 Feb, 04:01

2,520

GPT-5 ሊመጣ ነው!
o3ም ብቻውን አይለቀቅም።
STEM with Murad 🇪🇹

12 Feb, 12:11

3,291

አሜሪካ እና እንግሊዝ ውድቅ ያደረጉት የዓለም ዓቀፍ ስምምነት

አሜሪካ እና እንግሊዝ ዓለም አቀፍ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ስምምነት አለመፈረማቸው ተገልጿል።

ሁለቱ ሀገራት አቋማቸውን ያስታወቁት በቅርቡ በፓሪስ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዙሪያ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ሲሆን ፈረንሳይ፣ ቻይና እና ህንድን ጨምሮ 60 ሀገራት ስምምነቱ ላይ መፈረማቸው ተመላክቷል።

ስምምነቱ በዲጂታሉ ዘርፍ ያለውን መከፋፈል ለመቀነስ፣ የAI እድገትን፣ ግልፅ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና እምነት የሚጣልበት መሆኑን ለማረጋገጥ ያለመ ነው ተብሏል።

ይሁን እንጂ በጉባኤው የተሳተፉት የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ላይ የሚደረገው ከልክ ያለፈ ቁጥጥር ኢንዱስትሪውን ሊጎዳ እንደሚችል በመግለጽ የትራምፕ አስተዳደር ስምምነቱን እንደማይቀበል አስታውቀዋል።

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ ከደህንነት ይልቅ ለእድገት ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል።

በተመሳሳይ የእንግሊዝ መንግስት በብሄራዊ ደህንነት እና በዓለም አቀፍ አስተዳደር ስጋት ምክንያት መፈረም እንደማይችል አስታውቋል።

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በበኩላቸው ስምምነቱ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዕድገት አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ጥብቅ የኤአይ ደንቦችን መደገፋቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።

በዮናስ ጌትነት
STEM with Murad 🇪🇹

12 Feb, 08:05

3,222

China is making waves!
ByteDance just released OmniHuman-1
It can create ultra-realistic human videos from just a single image and audio.
STEM with Murad 🇪🇹

12 Feb, 08:01

3,352

Don't let the fear of losing be greater than the excitement of winning.
STEM with Murad 🇪🇹

11 Feb, 20:09

4,009

እኔ ብቻ ልብላው! ማንም አይቀናቀነኝ!
STEM with Murad 🇪🇹

11 Feb, 11:37

4,159

ቢሊየነሩ የማይክሮሶፍት ባለቤት ቢልጌት ካምፓኒው እንዳያሽቆለቁል በሳምንት ለ80 ሰዓት ያክል ኮዲንግ ላይ ያሳልፋል።

አንተ 1000 ብር በቅጡ የሌለህ እንቅልፍህን ስትነካ እደር አሉህ¡
STEM with Murad 🇪🇹

11 Feb, 07:06

3,960

ወትሮም ባይስማሙም ሳም አልትማንና ኤለን መስክ ተጣልተዋል በቻትጂፒቲ ባለቤት ኦፕንኤይ ዙሪያ። መስክ ቀድሞም ኦፕንኤአይ ውስጥ ያለውን ክፍተት ስለሚያውቅ፤ ኦፕንኤአይ አቅሙን ለማሳደግ ፈንድ ራይዚንግ ላይ ባለበት ወቅት በ97.4 ቢሊዮን ብር እንግዛችሁ ብሎ ከባለሃብት አጋሮቹ ጋር በመሆን ለኦፕንኤአይ ቦርድ ጥያቄ አቅርቧል። ሥራ አስኪያጁ ሳም አልትማን አንፈልግም፤ ከፈለግክ ቲዊተርን በ9.74 ቢሊዮን ዶላር እንግዛህ ብሏል። ቁጥሮቹን ልብ በሉ፤ ሲቀጥል ኤክስ ሳይሆን መስክ የሚጠላውን ቃል ትዊተርን ነው የተጠቀመው። መስክም ኮመንት ላይ «አጭበርባሪ» ብሎ መልሷል።😁

Sam Altman የሚለውንም Scam Altman እያለ ነበር¡

የት እንደሚዳረሱ እስኪ እናያለን።
STEM with Murad 🇪🇹

10 Feb, 20:06

3,952

Since DeepSeek R1's release, very quickly AWS, Azure, Fireworks AI, Groq, Hugging Face, SambaNova and Together AI all started to host R1 variants. What's the "best" model changes frequently, and so developers often want to try out new ones. The aisuite package, which helps developers do this quickly with minimal code changes.

Thanks Rohit Prsad & team for working with me on this!

https://github.com/andrewyng/aisuite


Andrew Ng