መንፈሳዊ ግጥሞች @spritualpoem Channel on Telegram

መንፈሳዊ ግጥሞች

@spritualpoem


በዚህ ቻናል እግዚአብሔር እንደ ፈቀደ መንፈሳዊ ወኔያችንን የሚቀሰቅሱና ዕውቀት የሚያስጨብጡ መንፈሳዊ ግጥሞችን እናስተላልፋለን፡፡
ለአስተያየት @atnatioss
ቻናሉ@spritualpoem

መንፈሳዊ ግጥሞች (Amharic)

ምሳሌዎች አብቃዎችን ለመጠቆም እና ሃሰተኛ ስሜትን ከእኛ ጋር የተገኘነው መንፈሳዊ ግጥሞች፡፡ ይህን ግጥም በዚህ አፕ እንደሚገለጽው እባኮት አንድም ማለት አልነበረም፡፡ አሁንም ኖርበራዊ ገጽን እያካበበ በመንፈሳዊ ግጥሞች ስብሰባና ምልክቶች በትክክሉ እንዲሰራሩ በመጠን እርዳን አገልግሎታችንን ሊግኝቷችን አረከቡ፡፡ እንደምንለዋወጥ ስለፈለገ ያልታወሰ ማንኛውም ሰዎች መንፈሳዊ ግጥሞችን በመጠቀም የምንሚያቀርብ ትክክለኛ መግለጫን በማወቅ የሚከተለው መረጃ እንዲሰጥ ነው፡፡ ይህን ግጥሞች የ 'አቡነ ቱጉለይም' ባለቤቴሳ ከሆኑ ስምሮች ይፈልጋሉ፡፡

መንፈሳዊ ግጥሞች

20 Jul, 01:24


የቀጠለ

መንፈሳዊ ግጥሞች

20 May, 04:21


፨መልክአ ሚካኤል አማርኛ በግጥም ፨
መልክ በግዕዝ ሲጻፍ 5 ስንኞች ሁሉም ቤት የሚመቱ ሆነው ነው። ይኼን ታሳቢ በማድረግ የተጻፈ ነው። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይቀጥላል።

መንፈሳዊ ግጥሞች

24 Apr, 17:24


ጠዋት- ማታ
፨፨፨

ጠዋት ቁርስ: ቤተመቅደስ
ጭፈራ ቤት:  መክሰስ

ጠዋት ጠዋት መዝሙር
ማታ ላይ መጨፈር

ስታደርግ አያለሁ: ማለዳ ላይ ጸሎት
ለምንድነው ታዲያ: ወደ ማታ ጸጸት

ጨክን አንዱን ምረጥ: ምንድነው ነገሩ
አትደበላልቀው: ክፉውን ከጥሩ

"በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር እንዲሁም ለብ ስላልክ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንክ ከአፌ ልተፋህ ነው" ራዕ 3:15-16

ለማስታወስ ጾሙ የተፈታው ከምግብ አይነትና የምንበላበት ሰዓት እንጅ ሌሎች ይቀጥላሉ።

ምናልባትም በተለይ የበዓል ሰሞን የአብዛኛው ክርስቲያን ሕይወት እንደዚህ ነው 😓

ጠዋት ቤተመቅደስ በረገጠ እግራችን ማታ በየጭፈራ ቤቱ የምንዞር
እግዚአብሔርን ባመሰገነ አንደበታችን ሰውን መዝለፍ

ጠዋት ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን በቀመሰ ምላሳችን ማታ የአልኮል መጠጥ በየአይነት እስከ ስካር የምናጣጥም

ጠዋት ለእግዚአብሔር ክብር በተንበረከኩ እግሮቻችን ማታ ለዳንኪራ የምንበረከክ የሁለት አለም ሰዎች አንሁን።

ምን እናድርግ ለሚሉ
እግዚአብሔርን በእውነት ለመከተል ቆርጦ መነሳት እና ወደ አምላክ መቅረብ  እንደ ፈቃዱ እንኖር ዘንድ መጸለይ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
መልካም በዓል🙏
© @spritualpoem
@spritualpoem
@spritualpoem

መንፈሳዊ ግጥሞች

03 Mar, 20:27


፨እንዴት በሀይማኖቴ ተደስቸ ልኑር? ፨
፨፨፨
1) ምስጋና
ባለህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግን።
ምንም ባይኖርህ እንኳን ወደ በጎው ሁሉ እንዲመራህ እየጸለይክ አመስግን ። ያንተን ያህል  ጤና ያንተን ያህል ከጎንህ የሚሆኑ ቤተሰቦች ፣ ስራ ካለህ ያንተን ያህል ስራ የሌላቸው ብዙዎች ናቸው፣
እግዚአብሔር ያደረገልህን ውለታ (ተዓምር ሊሆን ይችላል) አስታውስ በርሱ ደስ ይበልህ አመስግነውም።እግዚአብሔር ከመፈጠራችን ጀምሮ እስከ እድገታችን እኛ ባናስተውለውም ያደረገልን ተዓምር ብዙ ነው።
• ለምሳሌ እኛ እኮ የተወለድነው በየቦታው እንደአሁኑ ክሊኒክም ሆነ  የጨቅላ ህፃናት ህክምና ባልነበረበት ዘመን ነው።
• ብዙዎቻችን ክትባት ባንከተብም ከተለያዩ የልጅነት በሽታዎች ተርፈን አድገናል።
•  ብዙዎቻችን የውሀ እጦት ቢያሰቃየንም ከትራኮማ አምልጠናል
• ብዙዎቻችን ስንት ጊዜ ነው ከመኪና አደጋ የተረፍነው
•  ብዙዎቻችን በየሀገሩ ከነበሩ አለመረጋጋቶች ከጥይትና ከቦንብ ፍንዳታ አምልጠናል።
እንዲህም አመስግነው መድሀኒታችን  ሆይ ምን ውለታ  መመለስ ይቻለኛል? ላንተ እዘምራለሁ እንጅ


2) ሰዎችን አትውቀስ
ሰዎች ሁሌም በሁሉም መልኩ ፍፁም አይደሉም ጥሩ ነገር እንዳላቸው ሁሉ አንተ ክፉ የምትለው(ለእነርሱ እንደ ጥሩ የሆነ) ባህሪም ሊኖራቸው ይችላል
ሰዎች መልካም እንደሆኑ አስብ ዓሉታዊነትን አስወግድ

3) መልካም መልካሙን ማሰብ
ስለራስህም ሆነ ሌሎች በአዕምሮህ መልካም ነገር አስብ
የስበት ህግ በሁሉም ቦታ ይሰራል አንተ ስለራስህ የምታስበውን ነው የምትሆነው በራስህ ደስተኛ መሆን አለብህ። እኔ መልካም አይደለሁም ከሚለው ሐሳብ ይልቅ እራስክን መልካም ለማድረግ መጣር ላይ አተኩር።ጥሩ አርአያ ይኑርህ የእነርሱን ለመከተል ወስነህ ተጓዝ ነገር ግን ለምን እርሱን አልሆንኩም ብለህ ራስክን አትውቀስ አታወዳድርም። አርአያህ ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ሆነ አስተውል እርሱ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ እንዳለን።

4) መዝሙርና የመዝሙር መሣሪያ
መዝሙር ያሬዳዊ የሆኑ ዜማውችን ማዳመጥ ልብን ይመስጣል እግዚአብሔርን አመስጋኝ ያደርጋሉ።
የመዝሙር መሣሪያን መለማመድም ሆነ መተግበር በሀይማኖትህ ከምትደሰትበት አንዱ ነው።

5) ግዕዝን ማወቅ
የኢኦተቤ ከግዕዝ ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላት ግዕዝን ማወቅ እጅግ ደስታን ይሰጣል ቅዳሴዋ ውዳሴዋ ቅኔዋ  አብዛኛው በግዕዝ ነው ግዕዝን ለመማር ባትችል እንኳን በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችሉ መጽሀፍት በሶፍት ኮፒም ይሁን በሀርድ ይገኛሉ። እነሱን በመጠቀም በቤክ ውስጥ ሲዘመር ሲቀደስ ማህሌት ሲቆም ላለመደናገር ቀደም ብሎ ሊዘመሩና ሊቀደሱ የሚችሉ ዜማዎችን እስከ ትርጉሙ አውቆ እየገቡ መሳተፍ፤ እነግርሃለሁ ከዚህ ዓለም ውጪ የሆነ ነገር ነው የሚሰማህ ደስታ።

6) ጸሎት
ከልጅነትህ ጀምሮ እየተንከባከበ ካሳደገህ ከሚሳሳልህ ከስጋ አባትህ ጋር ስታወራ ደስ ይልሃል።
ጸሎት ደግሞ ከሰማዩ አባትህ ጋር በኑሮህ ሁሉ ከሚረዳህ ሰላምን ከሚሰጥህ፣ ቸርነትን ከሚያደርግልህ ምንም ስትሆን አባ አባት ብለህ እንድትጠራው የልጅነትን መንፈስ ከሰጠህ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ስትነጋገር እንዴት ደስ አይልህ። በጸሎት ከጻድቃን ቅዱሳን ማህበር ከመላአክት ጋር ስትነጋገር እንዴት ደስ አይልህ።
በዕለት ከዕለት እንቅስቃሴህ እግዚአብሔር እንዲረዳህ ፀሎት አድርግ እንደሚረዳህም እየተገነዘብክ ደስ ይበልህ
በጸሎት አንተ የምትፈልገውን አስበህ መጠየቅ ነው ሚጠበቅብህ ሐሳብህን እግዚአብሔር ላይ ተማምነህ መጣል ነው ስራህን እግዚአብሔር ያከናውንልሀል ደስ አይልም።

7) መጽሐፍትን አንበብ
ቅዱሳን መጽሐፍት የነፍስ ምግብ ናቸው ያረጋጋሉ፣ ተስፋ ይሰጣሉ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኛሉ፣ ወደ ንስሀ ይመራሉ።
8) ከሀጢአት መራቅ ንሰሀ መግባት
ብዙ ማብራሪያ መስጠት ይቻላል ባጭሩ ግን ሰውነትህ ቆሽሾ ሻወር ወስደህ ለስጋህ ምን እንደሚሰማህ አስበው የነፍስህንም ሀጢአት ሲወገድላት ስጋህ ይደሰታል ነፍስህ ሐሴት ታደርጋለች
9)  ተሰፋ
ከዚህ ሁሉ በላይ በተስፋ ደስ ይበልህ ተስፋችን መንግስተ ሰማያት ናት። በዚህ ዓለም ምንም መከራ ቢፈራረቅብን ኃላፊ ነው የዚህ ዓለም ደስታም እንደዚሁ አንተ ደግሞ በጠበቧ መንገድ ስለምትጓዝ በብዙ ፈተና መካከል እንኳን ደስ ይበልህ። በሚመጣው አለም የዘላለም ህይወት እንዳለህ እያሰብክ በክርስቶስ ደስ ይበልህ። እግዚአብሔር ለቅዱሳን በሰጠው ቃል ኪዳን ደስ ይበልህ። በሐሳብህ የመላአክትን ማህበር የጻድቃንን ማህበር እያየህ ደስ ይበልህ።
10) ስጋወ ደሙን መቀበል
የደስታ መጨረሻ ከክርስቶስ ጋር ህብረት መፍጠር ነው። ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ ወደዚህ ማማ መድረሻዎች ናቸው እውነተኛ የደስታ ምንጭ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
እነዚህና ሌሎች በሐይማኖት ተደስተን እንድንኖር ያስችለናል። ከዚህ በተጨማሪ አንተ ራስህ ምን እንደሚያስደስትህ በማሰብና በመመርመር ማግኘት ይቻላል።
© @Spritualpoem
    @Spritualpoem
    @Spritualpoem

መንፈሳዊ ግጥሞች

03 Jan, 03:46


ላለማመን ወስኖ ከመጣ ሰው ጋር አትከራከር
፨፨
በተለያዩ ጉዳዮች ሃይማኖትን ጨምሮ ሐሳባችን ስንገልጽ/ስንወያይ  ልዩነት ሊኖር ይችላል
አንዳንድ ሰዎች ከራሳቸው ሐሳብ ውጪ ምንም ያህል ማስረጃ ብታቀርብ አይቀበሉትም። ይህ ሰው ላለማመን ወስኖ ስለመጣ ከእርሱ ላይ ጊዜ መጨረስ አያስፈልግም።

ላለማመን ወስኖ የመጣ መሆኑን በምን ታውቃለህ የሚል ሰው ይኖራል
1ኛ ሲናገር ጮክ ብሎ /በቁጣም ሊሆን ይችላል  ይሆናል።
2. እርሱን ሊያሸንፍ በሚችል በማስረጃ እየተናገርክ እየገባው እያለ unconciously /ሳያስበው ንግግርህን ያቋርጥሃል
3. ከርዕሱ ወይም ጭብጡ ውጭ ያወራል።

ይህ ሰው ለምን ላለማመን ወስኖ  ይመጣል? የሚል ሰውም ይኖራል።
ይሄ ከባድ ጥያቄ ነው ነገር ግን መልስ አይጠፋውም
ምክንያቱ
1) ይህ ሰው ሃሳቡን እንደ ዶግማ/የማይለወጥ አድርጎ ይዞታል ያን ዶግማ ሊሸረሽር የሚችል ነገር አይቀበልም።
2) ከግል ስብዕናው ጋር የተያያዘ ችግር ሊሆን ይችላል
3) ሀሳብክን በህሊናው ሊቀበል ይችላል ነገር ግን ተሸነፈ ላለመባል ብቻ በቃል ደረጃ የማይቀበል ሊሆን ይችላል። ስለዚህም እንደማንም ብሎ የሰማውን ሐሳብ suppress/በጭንቅላቱ ሊደብቀው ብሎም ረፍት ስለሚነሳው ለመርሳት ይሞክራል።
ባጠቃላይ ይህ ሰው የሚቀበለው እውነቱን ሳይሆን እርሱ እውነት እንዲሆን የሚፈልገውን ነገር ነው ።
ምንም ያክል ልዩነት ቢኖርም  ክርክሩን መተውና ልዩነትን መቀበል እንጅ በእርሱ ላይ መፍረድ አያስፈልግም

©@spritualpoem
@spritualpoem
@spritulapoem

መንፈሳዊ ግጥሞች

02 Jan, 19:34


https://t.me/Ortodoxe19

መንፈሳዊ ግጥሞች

02 Jan, 19:26


መልኬ ያምር ይሆን
፨፨፨
ታበጥራለህ ትታጠባለህ ትቀባለህ
ትስተካከላለህ
ከዛ በመስታውት ታያለህ
አንተው ራስህ ብትሆንም ግን ጽድት ታረገዋለህ።
እንዴት ነኝ አምራለሁ ? ብለህም ለሰዎች ራስክን አስተያየት እንዲሰጡህ ትጠይቅም ይሆናል

መልክህን እንዳሳመርከው እንዳስዋብከው
በመስታወት እንዳየኸው
በሰው እንዳሰገመገምከው
አንተነትክንስ? አስተሳሰብህንስ እንዴት ነው ውብ ምታደርገው?
ምታስገመግመውስ?

መጽሐፍት የአንተን ሚዛን ይነግሩሃል የአንተነትህን ሚዛን ይነግሩኻል።

የራስን መልክ ለማየት መስታውት እንደሚያስፈልግ ሁሉ....
የራስህን አስተሳሰብ ለመገምገም መጽሐፍት ያስፈልጋሉ
©@spritualpoem
    @spritualpoem
    @spritualpoem

መንፈሳዊ ግጥሞች

07 Oct, 22:48


ጠይቅ
፨፨፨
ሐሳብ ሲለዋወጥ፡ሰው ከሰው ሲመክር
ቤተሰብ ይጸናል: ትቆማለች ሀገር
ሲጠያየቅ ሰዉ: የማያውቅ ከሚያውቀው
ፍቅርንም ይጨምራል,  ይበልጥ ተዋውቀው።

እንዲሁ ቢቀመጥ,  አውቃለሁ እያሉ
በሰው ፊት ያፍራሉ፡  የታለ ቢባሉ

አንብብ ለምን ብለህ ጠይቅ
በጎውን ቁምነገር : አብጠርጥረህ እወቅ
ትደርሳለህ አንተም: ከደቂቅ ወደ ሊቅ።

ካላወቁ አይሰሩ: ይሄነን ጠንቅቁ
ትሩፋት ደግነትን: ካልሰሩም አይጸድቁ

ከተሰወረችው ለማግኘት: ጥበብን
አምላክን ጠይቀው: እንደ ሰሎሞን።

ስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
#Orthodox #Christianity #Inspiration-towards-the-heaven , #Jusus-is-God, #St.Mary-God's-Mother
#ኦርቶዶክስ-ክርስቲያን
#ወደ-አባቶቻችን-ርስት-አይናችን-እናቅና
#ክርስቶስ-እግዚአብሔር-ነው
#ቅድስት-ማርያም-የአምላክ-እናት ናት።
©@spritualpoem
    @spritualpoem
    @spritualpoem

መንፈሳዊ ግጥሞች

03 Oct, 16:39


How to have 7 times per day prayer easily
፨፨፨

As you all know Prayer is basic to every Christian,
But many of us are not giving credit for this
As we are in battle place we need to refill the equipments for our day to day war against devil,
Praying 7 times per day is not as much difficult as you assume,
As you know Our God teach as how to pray,
The so called Oh Our father,
If you can do it, it will take only 15 sec in Geez or amharic,
Oh St. Mary prayer only 15 sec in Geez,
If you add both prayers it takes only 30 sec,,

Even if you can't do this prayer for 30 sec , you can say "prayer of Jusus" which takes only 3 sec,

"የዳዊት(የእግዚአብሔር ) ልጅ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ" (3 Seconds)
ወይም "ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ምህረትህ በእኔ በኃጢአተኛው ላይ ትሁን።" 4 seconds
ወይም "ጌታ ኢየሱስ ሆይ ምህረትህ በእኔ ላይ ትሁን"
3 seconds
So how can I act with
Have an Alarm with only vibration once or Beep sound you will set for sunday to Monday in your clock app, at 12:00 Am  3፡00 Am 6:00Am , 9:00Am, 11:00Am, 3:00 PM and immediately before you sleep according to your experience of sleeping, all in local time
but if you are really devoted you can set the  last two as a cannon at 4:00 Pm before sleep and get up at middle of night,( unfortunately it may be difficult for most of us so you can try the above)

God will give you more if you have some, as his word says so


ስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
#Orthodox #Christianity #Inspiration-towards-the-heaven , #Jusus-is-God, #St.Mary-God's-Mother
#ኦርቶዶክስ-ክርስቲያን
#ወደ-አባቶቻችን-ርስት-አይናችን-እናቅና
#ክርስቶስ-እግዚአብሔር-ነው
#ቅድስት-ማርያም-የአምላክ-እናት ናት።
©@spritualpoem
    @spritualpoem
    @spritualpoem

መንፈሳዊ ግጥሞች

02 Oct, 22:56


፨ተዘክሮ ሞትን ተስፋ መጻእያትን ካልያዙ ትሩፋትን ማድረግ አይቻልም።

፨አብዝቶ መመገብ  ሐልዮ ኃጢዓትን ከእግዚአብሔር የምትገኝ ጥበብን ከሰውነትህ ይሰውራታል።

፨አባት ለልጅ እንደሚያዝን ክርስቶስም በትሩፋት ለደከመ ሰውነት ያዝናል ፈጥኖም ይሰማዋል።

፨ነፍስህ ከመከራ ከድንቁርና የምትለይበት ጊዜ እንደደረሰ ይህ ምልክት ይሁንህ በዕንብ ትሰለጥናለህ

፨መከራ ሳይቀበል ጸጋ ላንዱ ስንኳን አትሰጥም።

ከ ማርይስሐቅ የተወሰደ

ስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
#Orthodox #Christianity #Inspiration-towards-the-heaven , #Jusus-is-God, #St.Mary-God's-Mother
#ኦርቶዶክስ-ክርስቲያን
#ወደ-አባቶቻችን-ርስት-አይናችን-እናቅና
#ክርስቶስ-እግዚአብሔር-ነው
#ቅድስት-ማርያም-የአምላክ-እናት ናት።
©@spritualpoem
    @spritualpoem
    @spritualpoem

መንፈሳዊ ግጥሞች

10 Sep, 10:12


🌻🌻🌻
" ዘመን አትሻገር !"
🌻🌻🌻
የወራት ማግ ፥ የዕለታት ድር
በአንድ መታታት ፥ውሕደት - የቁጥር ድምር
ከተፈጥሮ ዑደት ፥ ተስማምቶ
በዘመንነት ተለይቶ ፥ ተበጅቶ
ተቆጥሮ - ተቀምሮ
ቀናትን ሠፍሮ
ዘመን ዘመንን ፥ ሊያስረጅ
አዲስነት ሲታወጅ ...

ተራሮች በልምላሜ መቀነት - ታጥቀው
አበቦች በደስታ ቦርቀው - ፈንድቀው
የፀሐይ ጸዳል ፥ ደመናውን ሲገፍ
ኃጢአት አትሻገር ፥ ሞት ሆይ ከእኛ እለፍ።

ከህዝብ ልብ ፥ ከኢትዮጵያ ምድር
ጥላቻ ተሰደድ ፥ ጥላቻ ተቀበር
ዘመን ስንሻገር ፥ ዘመን አትሻገር።
05/13/2013 ዓ.ም
©ዮሴፍ ጌትነት

መንፈሳዊ ግጥሞች

08 Sep, 16:43


ምስጢረ -ማይ
"ለኖኅ ዘመን ትውልድ" ፥ የጥፋት ምክንያት
"የኖኅ" የከፍታ ምስጢር ፥ ምክንያተ ዕርገት
"ምስጢረ-ማይ"
"ምስጢረ-ሰማይ"
ለምስጉን ሲሳይ
ምክንያተ ኃሳር ፥ ለዕቡይ።
03/13/2013 ዓ.ም
©ዮሴፍ ጌትነት
https://t.me/bieteyoseph

መንፈሳዊ ግጥሞች

05 Sep, 17:06


+++ ስማኝማ ዳዊት ? ! +++
መዝ 64፥11
በቸርነትህ ፥ ዓመትን ታቀዳጃለህ
ምድረ በዳውን ፥ ስብን ታጠግባለህ
የምድረ በዳ ተራሮችን ፥ አንተ ታረካለህ
ኮረብቶችህንም በልምላሜ ደስታ ፥ የምታስታጥቅ ነህ
ሸለቆችም ከቶ ፥ በእህል ተሸፈኑ
ማሰማሪያዎችህ ፥ በመንጎች ተሞሉ
ሁሉም በአንድነት ፥ በደስታ ይጨሃሉ
የምስጋና ቃልን ፥ የዝማሬ ድምፅን ላንተ ያቀርባሉ
የምትል ዳዊት ሆይ ፥ እስኪ ልጠይቅህ
ከቶ ይህንን ምስጢር ፥ ስለ ማን ተናገርህ ?

ተራራው ኮረብታው ምድረ በዳው ማነው ?

ማሰማሪያ ያልከው ፥ የሸለቆው ምስጢር
በደስታ የሚጮሁት ...፥ የመንጋውና የእህሉ ነገር
እውን ለግዑዛኑ ፍጥረታት ፥ ለደመ ነፍሳዊያን
ምስክር መሆንህ መናገርህ ይሆን ?

ወይስ ተራራና ኮረብታ ያልካቸው
ከምድር ከፍ ያሉ ቅዱሳንህ ናቸው
ሸለቆ ፥ ምድረ በዳን የማንሳትህ ጉዳይ
ራሳቸውን በፈቃዳቸው ላደሩጉት ነዳይ
ያለበስካቸውን ጸጋ ፥ የመንፈስ ርካታ ፥
ያስታጠቅሃቸውን ልምላሜ ፥ የደስታ ገበታ ፤
መናገርህ ይሆን ?
መዝሙረኛው ዳዊት ፥ ጻድቁ አባቴ
ይህን የመናገርህ ነገር ፥ ለእኔ ለሕይዎቴ
ትርጉሙ ይህ ይሁን ፥ ብዬ እለምናለሁ
በፍፁም ተማፅኖ ፥ ፊትህ እቆማለሁ...

እንዲህ እንደነርሱ ፥ ዓመትን በመቀዳጀት ፥ ኅብረትን ካገኘሁ
በዕድሜ ከባረከኝ ፥ ዘመንን አልፌ ፥ ለዘመን ከበቃሁ
ምድረ በዳው ፥ “ልቤ” ፥ በኃጢአት በረሃ ዋዕይ የሚነደው ፤
ምድረበዳ እኔነት ፥ ልምላሜ ምግባር ፍፁም የተለዬው
ተራራው ... ፥ ኮረብታውም "እኔ" ፥ ዕቡይ እኔነቴ በስጋ መክበሩ ፍፁም የሚገደው
ሸለቆውም እኔ ፥ በዓለም ማዕበል ፥ ጎርፍና ውሽንፍር
ልቤ ተሸርሽሮ ፥ ተስፋን የቆረጥኩኝ በመዳኔ ነገር ...
የነፍሴ ጥም ሊቆረጥ በነፍሴ ልፈወስ ፥
በደስታ ልዘምር ልቤ ሊረሰርስ
የጊዜውን መቅረብ የጊዜውን መድረስ
ላንተ ሳበስርህ ነው ብለህ አስደስተኝ ፥ ብልዬቴን አድስ...

አወ ትርጉሙ ይህ ይሁን፤ ስለ ፀሎትህ ኃይል ፥ ስል እማፀናለሁ
የምድረ በዳ እኔነቴን መርካት ፥ በደስታ መታጠቅ ፥ በምናብ እያየሁ
የዕቡይ ልቡናዬን ፥ በአንተ ፊት መንበርከክ
የሸለቆ እኔነቴን ፥ በፍሬ መባረክ
ፍፁም ስለ መሻት
ይህን እልሃለሁ
ቅዱሱ አባቴ ፥ ስማኝማ ዳዊት
አሁን ይህን ሰዓት
አብዝቸ ስቃትት ፥ ...
የዝማሬህ ምስጢር ፥ የትንቢትህ ነገር
ለእኔ ይሁንና በደስታ ልታጠቅ ፥ በደስታ ልዘምር
4/1/2013

መንፈሳዊ ግጥሞች

05 Sep, 15:19


+++ ይደንቀኛል ጌታ ! +++
ሉቃ 13፥ 7
በወይን ማሳህ ላይ ፥ በለሙ መሬትህ
ዘመንን ሰጥተኸኝ ፥ እንድኖር መፍቀድህ
አንዴም ብቻ ያይደል ፥ ብዙ ጊዜ መጥተህ
ፍሬዬን ፍለጋ ፥ እኔን መጎበኝተህ
ይደንቀኛል ጌታ ...
የኔ ፍሬ ላንተ አውቃለሁ ፥ ምንም ነው
ፍሬህ የታል ያልከኝ ፥ እኔን ልትባርክ ነው
ይደንቀኛል ጌታ ...
ደጋግመህ መምጣትህ እኔን መፈለግህ
ትቢያነቴን ሳትንቅ ፍሬዬን መሻትህ
አክሊል ልታቀዳጅ እንዲህ መናፈቅህ
ከቃላት የሚያልፈውን ይሄን ልዩ ፍቅር
አድንቄ ሳልጨርስ ስልህ ዕፁብ መንክር...
ልትቆርጠኝ ስትችል ፥ ቃል ብቻ ተናግረህ
የመጥፋቴ ነገር ፥ ፈፅሞ ቢገድህ
የእኔን ፍሬ አልባነት ፥
የእኔን መካንነት
ከሰራተኞችህ ላንዱ ፥ የመንገርህ ነገር ፥
የያዘው ልዩ አሳብ ፥ የገለጠው ምስጢር
ራራለት ብለህ ጣት እንደመጠቆም ፥ በአፍ እንደመናገር
እዘንለት ባክህ ፥ አርመው ኮትኩተው
በፀሎትህ ቅጥር ከማይረባ አዕምሮ ፥ ከመጥፎ ሃሳቦች ፥ ከአራዊት ጠብቀው
ስለ ነፍሱ መዳን ፥ ፍሬን ስለ ማፍራት ዕንባን አፍስስለት ፥ መግበው አጠጣው
ያሊያ ሊጠፋ ነው ብሎ እንደመናገር
እንደሆነ ስረዳ ፥ይህ ያንተ ማማከር
ይደንቀኛል ጌታ ለእኔ ያለህ ፍቅር ...

አውቃለሁ ጌታዬ ፥ ብዙ ... እንደበደልኩ
ለሙን መሬትህን ፥ ብዙ እንዳጎሳቆልኩ
ይህን ዓመት ተወው ፥ የሚልህን ቅዱስ ፥ የሚልህን መልአክ
ከአንዴም ብዙ ጊዜ ፥ ለእኔ ብታዘጋጅ ፥ በምስጢር ብትልክ
እኔ ግን አሁንም ፥ በመካንነት ግብር ፀንቸ ኖሬያለሁ
ውሃን ማፍሰስህን ፥ በድንጋዩ ልቤ ፥ አብዝቸ ሽሪያለሁ
ያደረግህልኝን ሁሉ ከምንም ሳልቆጥር
ይደንቀኛል ጌታ ...
ይህ ፍሬ አልባነቴ ፥ አልገድህ ብሎኝ ለዘመናት ስኖር ...
ከቆዬሁ በኋላ ፥ ቆም ብዬ ሳስብ ፥ አሁን ስመረምር
ስለ እኔ መዳን ፥ ፍሬን ስለ ማፍራት
የአንተን ልዩ ፍቅር ፥ ያንተን ልዩ ትጋት
የአንተን ስስትና ፥ ጥልቅ የሆነ መሻት
እኔ ስለ ራሴ ፥ የመዳኔ ነገር
ከሰጠሁት ቦታ ፥ ካሳየሁት ፍቅር
አንፃር ስመዝነው ...
ይደንቀኛል ጌታ ...
የእኔ ታካችነት ፥ ያንተ ታጋሽነት...!
ዘወትር የማይወድቅ የመውደድህ ፅናት
እናም...
ይሄ ቸርነትህ ፥ በዕድሜዬ ላይ ፥ ዕድሜን ጨምሮልኝ
ፍሬን ላፈራበት የሚቆጠር ዕለት ፥ ዘመንን ስለ ሰጠኝ
ለእኔ ያለህን በጎ ሃሳብ እንዲህ መመልከቴ
የተስፋ ጭላንጭል ሆኖኝ በማግኘቴ
ልለምንህ ወደድኩ ለቀሪው ፥ ዘመኔ ለቀሪው ሕይዎቴ...

እባክህን ተለመነኝ ፥ እኔም ልለምንህ ፥
እዘንለት ባልከው ፥ በጻድቁ አባት ፣ በቅዱስ መልአክህ
መልዕልተ ፍጡራን የፍጥረታት ደስታ ፥ በሆነች እናትህ

የእኔን ርኩሰት ፥ ስለ ርሱ ፥ ስለርሷ ንፅሕና ፥ ከምንም ሳትቆጥር
በፍቅርህ ደግፈህ ፥ ኃጢአቴን ሁሉ ሻር ፥ በደሌን ይቅር በል
ዘመነ ዮሐንስን ፥ አዲስ ዓመት ብላ ፤ እናቴ ስታውጅ
ለእኔም አዲስ ልብን ፤ በእኔ ውስጥ ስራ ፥ በእኔ ውስጥ አብጅ
አንተን የሚያሳውቅ ፥ ብሩህ ህሊና
ለቤትህ የሚተጋ ፥ የቀና ልቡና
ፍሬን የሚያፈራ ትሁት ስብዕና
እባክህ አድለኝ ስል እማፀናለሁ ፥ም
ደጅ እጠናሃለሁ...

ያኔ ወደ እኔ ስትመጣ ፥ ፍሬዬን ለማዬት
ደስ ላሰኝህ ጌታ ፥ ይብቃኝ መካንነት
©ዮሴፍ ጌትነት
03/01/2013 ዓ.ም የተፃፈ
በድጋሜ የተለጠፈ።

መንፈሳዊ ግጥሞች

22 Aug, 05:05


በረከት ይድረሰን
ፍቅርሽን ተርበን
ፍልሰትሽን አስበን
ውዳሴሽን ደግመን
ቅዳሴሽን ሰምተን
ጸበልሽን ጠጥተን
እምነት ተቀብተን
በረከትን ሽተን
ከልጅ እስከ አዋቂ ፥ ከሊቅ እስከ ደቂቅ
በፊትሽ ለምንሰግድ ፥ በፊትሽ ለምንወድቅ...
...ለእኛ ለልጆሽ...
ከጉስቁልና አኗኗር ፥ ፍልሰትሽ ያፍልሰን
የትንሣኤሽ በረከት ፥ ከኃጢአት ሞት ያንሣን
ከምድራዊ ሃሳብ ፥ ፍፁም ተለይተን
በዕርገትሽ እናርግ ፥ በረከት ይድረሰን።
©ዮሴፍ ጌትነት
15/12/13 ዓ.ም
በዓለን የሰላም የፍቅር የፅድቅና የበረከት ያድርግልን።
በትንሣኤዋ ፥ በዕርገቷ ፤ ትንሣኤ ልቡና ዕርገተ ህሊናን ያድለን።
አሜን።