Dernières publications de ኢማን መልቲሚዲያ (@sineislam) sur Telegram

Publications du canal ኢማን መልቲሚዲያ

ኢማን መልቲሚዲያ
<< `በጊዜያቱ እምላለሁ ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው ፤ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ፥ በእውነትም አደራ የተባባሉት ፥ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።` >>
ሱረቱል ዐስር፦(1፥3)


https://telega.io/c/sineislam
29,411 abonnés
462 photos
97 vidéos
Dernière mise à jour 01.03.2025 10:21

Le dernier contenu partagé par ኢማን መልቲሚዲያ sur Telegram


ፆም የሚያበላሹ ነገሮች
~
1- የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም፣

2- የዘር ፈሳሽን ሆን ብሎ ማውጣት፣

3- መብላትና መጠጣት፣

4- በአፍ መድሃኒት መዋጥ፣

5- ሲጋራና መሰል ነገሮችን ማጨስ፣

6- የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም መምጣት፣

7- ፆምን የማቋረጥ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ (ባይበላም ባይጠጣም)

እነዚህ ነገሮችን ፆምን የሚያበላሹት የሚያፈርሱ እንደሆነ እያወቀ፣ አስታውሶ እና በምርጫው በቀኑ ክፍለ ጊዜ ከፈፀማቸው ነው።

* የሚያፈርሱ መሆናቸውን ሳያውቅ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም። ልክ እንደዚሁ ያልነጋ መስሎት ወይም ፀሐይ የገባ መስሎት ቢፈፅምም ፆሙ አይበላሻም።

* የሚያፈርሱ መሆናቸውን እያወቀ ነገር ግን ረስቶ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም።

* የሚያፈርሱ መሆናቸውን እየወቀ ግን ተገዶ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም።

@sineislam
@sineislam

በረመዳን ቁርኣንን ለማክተም‼️
========================
1) አንድ ግዜ ለማክተም፥
~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣

2) ሁለት ግዜ ለማክተም፥
~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣

3) ሶስት ግዜ ለማክተም፥
~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣

4) አራት ግዜ ለማክተም፥
~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ ገጽ 16  መቅራት፣

5) አምስት ግዜ ለማክተም፥
~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 20  ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 20  ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 20  ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 20  ገጽ መቅራት!!
||


ረመዳን የቁርኣን ወር ነው።
ከአምስት ግዜ በላይ ብናከትምም በጣም ተወዳጅ ነው።

ምናልባት ይህ ፕሮግራማችን አንድ ቀን ወይም በሆነ ሰአት ላይ በተለያዬ ምክንያት ቢያልፈን፣
ከሌላኛው ቀን ወይም ግዜ ማካካስ መቻል አለብን።

"ረመዳን ገጥሞት ሳይጠቀምበት ምህረት ሳያገኝ የሄደበት ሰው በአፍጢሙ ጀሀነም ይደፋ!"፡ ጂብሪል(ዐሰ)፤ አሚን በል ሲላቸው
ነብዩ(ሰዐወ) "አሚን"ብለዋል! ጠንቀቅ እንበል አደራ!!

@sineislam
@sineislam

🚨🌙 በሳውዲ አረቢያ ጨረቃ መታየቷን ተከተሎ የታላቁ የረመዳን ፆም ነገ ይጀመራል።

ለመላው ሙስሊሞች ከወዲሁ መልካም ፆም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን 🙏

ረመዳን ሙባረክ 🌙

#RAMADAN1446

#ለበጎ_ነው

በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ለፈጣሪው ፀሎት ለማድረስ ራቅ ወዳለ ስፍራ ይሄዳል ፣

በዚህም ወቅት ወደ ፀሎት ቦታ የሚሄዱት ተሳፋሪዎች በጉዞ መሀል ምሳ ለመብላት ወደ አንድ ካፌ ይወርዳሉ ።

ወጣቱም ከነሱ ጋር አብሮ በመውረድ ምግብ አዞ መመገብ ይጀምራል ።

ተመግቦም ከጨረሰ በኃላ ሂሳብ ለመክፈል ወደ ኪሱ ሲገባ ዋሌቱን ያጣዋል

ለ ሆቴሉ ማናጀርም ዋሌቱ እና ብሩ በሌባ መሰረቁን ያስረዳዋል ፣

ከዛም ከተማ ላለው ጓደኛው ደዉሎ የሆነውን ይነግረዋል ።

ጓደኛውም ገንዘብ ይልክለትና አመስግኖ ሂሳቡን ከፍሎ ሲወጣ ባሱ ስለቆየበት ጥሎት ይሄዳል ።

ከዛም በጣም አዝኖ ወደ ጓደኛው ዘመድ ቤት ያቀናል፣

እነሱም ጋር ለ 2 ቀን አድሮ ወደ ፀሎት ቦታው እንዲሸኙት ይጠይቃቸዋል ፣

እነሱም ያሳፍሩታል! ፀሎት ቦታውም ጋር ለ 2 ቀን አድሮ ወደ ቤቱ ወዳጁ ያሳፍረዋል ፣

ወደ ቤቱም ሲገባ እያለቀሱ ከቤቱ የሚወጡ ሰዎች ችን ይመለከታል ። ከዛም ፈጠን ብሎ ወደ ቤት ሲገባ ሰዎቹ እንዳለ በፍርሀት እና ድንጋጤ ይጮሀሉ።

እሱም ማን እንደሞተ እያለቀሰ ይጠይቃቸዋል ፣

ከጎረቤቱም አንዱ ጠጋ ይልና << አንተን ያሳፈርንህ ባስ መንገድ ላይ ተገልብጦ ማንም የተረፈ ሰው የለም> > ይለዋል፣

ወጣቱም ስላጋጠመው ችግር በሰከነ መልኩ ያስረዳቸዋል ።

በአደጋውም ከባድነት የሰዎች መልክ ባለመለየቱ ያንተን ዋሌት በኪሱ ይዞ ስናይ አንተ መስለከን ከቀበርነው ዛሬ 4ኛ ቀናችን ነው ይለዋል🥹🥹

ለካ በወጣቱ ቦታ የተሳፈረው የወጣቱን ዋሌት የሰረቀው ሰው ነበር -


#ረመዳን_4_ቀናቶች_ይቀሩታል።

@sineislam

በዚህ#ረመዳንአላህ🥰 ያላሰባችሁትንሪዝቅይስጣችሁ


#ረመዳን_13_ቀናቶች_ይቀሩታል። 9/6/2017

@sineislam
@sineislam

ሰላትን መስጂድ ሄዶ

የመስገድ ጠቀሜታዎች

1. የበለጠ አጅር እናገኛለን

ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡-

''በጀማዓ የሚሰገደው ሰላት አንድ ሰው ብቻውን ከሚሰግደው ሶላት ሃያ ሰባት እጥፍ ይበልጣል።''

(ቡኻሪና ሙስሊም)

2. አላህ ጀነትን ያዘጋጅልናል


ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡-

''በጧትም ሆነ በማታ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው አላህ በሄደበት ቁጥርጀነት ነት ውስጥ ቦታ ያዘጋጅለታል።''

(ቡኻሪና ሙስሊም)

3. ወደ መስጂድ በተራመድንበት እርምጃ ልክ አጅር እናገኛለን

ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡-

''በቤቱ ውስጥ (ውዱእ በማድረግ) ራሱን ያነፃና ከዚያም ወደ አላህ ቤቶች የግዴታ ሰላት ለመስገድ የሄደ ሰው እያንዳንዱ እርምጃ ወንጀሉን ያብስለታል እና በጀነት ያለውን ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።''

(ሙስሊም)

4. የአላህን ትእዛዝ አክባሪ እንሆናለን

''ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም (ግዴታ ምጽዋትን) ስጡ፡፡ (ለጌታችሁ) ከአጎንባሾች ጋርም አጎንብሱ፡፡''

ሱራቱ አል-በቀራ 2:43

''አላህ እንድትከበርና ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ (አወድሱት)። በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ።''

ሱራቱ አን-ኑር 24:36

5. መላኢካዎች ዱዓ ያደርጉልናል

ነቢዩ

صلى الله እንዲህ ብለዋል፡-

''አንድ ሰው መስጂድ ውስጥ በሚሰግደው ቦታ ላይ እስካለ ድረስ (ከመስጂድ እስካልወጣ ድረስ) መላኢካዎች አላህን ምህረትን ይለምኑለታል። ''አላህ ሆይ ይቅር በለው አላህ ሆይ እዘንለት'' (በማለት ይለምኑለታል)

(አል-ቡኻሪ)

6. ፈጅር እና ዒሻን በመስጂድ ውስጥ መስገድ ከሙናፊቅነት ይጠብቀናል

ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡-

''በሙናፊቆች ላይ በጣም የከበደችው ሰላት ፈጅር እና ኢሻእ ናቸው። በነሱ ውስጥ ያለውን (ምንዳቸውን) ቢያውቁ ኖሮ (በደረት) መሳብ ቢገባቸው እንኳን ይመጡ ነበር።''

(ቡኻሪና ሙስሊም)


@sineislam
@sineislam

አስራሚ እውነተኛ ታሪክ
የታሪኩ ረእስ የተቅዋ ጠቀሜታ

አንድ እውቀት ፈላጊ ተማሪ እና እርሱን የሚያስተምሩት አንድ አሊም ነበሩ። እኝህ አሊም ከለታት አንድ ቀን ለዚህ ተማሪና ለጎደኞቹ የሚከተለውን ምክር መከሯቸው ከሰው ዘንድ ለማኝ ከጃይ እንዳትሆኑ። አሊም የሆነ ሰው እሲ ስጡኝ ብሎ እጁን ወደሰው የሚዘረጋ ከሆነ ምንም ኸይር አያገኝም። ለራሱም ለድኑም ውርደት ነው የሚከናነበው። ስለዚህ እናነተ ወዳባቶቻችሁ ሂዱና አባቶቻችሁ የሚሰሩትን ስራ ስሩ ወይም አግዞቸው። ታዳ በምትሰሩት ስራ ሁሉ አላህን ፍሩ። ከዚህ ቡሀላ ተማሪወቹን ወደ የጉዳያቸው አሰናበቱአቸው።
ይህ ወጣት ተማሪ ወደ እናቱ ሄደና አባቴ የሚሰራው ምን አይነት ስራ ነበር ብሎ ጠየቃት። እናቲቱም የአባቱን ስራ ለመንገር በጣም ተቸገረች። እንደገና ቡሀላ አባት ወደ አኼራ ሂዲአል የእርሱ ስራ ላንተ ምን ያደርግልሀል አለችው። ልጁ ካልነገርሽኝ ብሎ አስጨነቃት። ጥያቄ ሲያበዛባት አባትህ ሌባ ነበር አለችው።

ልጅየውም ሸይኻችን አባታችን የሚሰራውን ስራ እንድንሰራ ነገር ግን አላህ መፍራት እንዳለብን መክረውናል አላት። እናቲቱም ምን ማለትህ ነው? እየሰረክ እንዴት ነው አላህን የምትፈራው? ስትል የግርምት ጥያቄዋን ጠየቀችው። እናትና ልጅ በሀሳብ ሳይግባቡ ተለያዩ። ልጁ ግን ወደ አንድ ቦታ ሂዶ የአሰራረቅ ዘደወችን ተማር።

በሌብነት ስልቶች ከተካነ ቡሀላ ትምህርቱንም የሸህየውን ምክርም ተግባራዊ ለማድረግ ወሰነ። የኢንሻን ሶላት ሰግዶ ሰው እስኪተኘ ድረስ አድፍጦ ጠበቀ። ከዚያም ከቤቱ ወጣ በቅድሚያ ወደአንድ ጎረቢት ቤት ወስጥ ገብቶ ለመስረቅ ነበር ያሰበው። ነገር ግን የሸህየውን አላህ ፍሩ ተግሳጽ  አስታወሰ ጎረቢትን ማስቸገር አላህ ከመፍራት አይደለም አለና ይህንን ቤት አልፎ ወደሌላ ቤት ተሻገረ። ይህ ቤት ደግሞ የየቲሞች ነው ለነፍሱም ይህ ቤት የየቲሞች ቤት ነው። አላህ ደግሞ የየቲሞችን ገንዘብ መብላት እርም ( ሀራም) አድርጎታል አለ።

ይህንኛውንም ቤት ትቶ ወደቀጣዩ ቤት አለፈ። እንድህ እንድህ እያለ ወደ አንድ ሀብታም ነጋደ ቤት ደረሰ ቤቱም ዘበኛ አልነበርውም ።  ይህ ሀብታም ብዙ ገንዘብ እንዳለው ሰው ሁሉ ያውቃል ከአስፈላጊ በላይ ትርፍ ገንዘብ እንዳለው ይታወቃል እዚህ ቤት ነው መግባት ያለብኝ ብሎ በተመሳሳይ ቁልፍ በሩን ከፍቶ ወደ ቤት ውስጥ ገባ።
ሰፊ ግቢና ብዙ ክፍሎች ያሉት ቤት ነው። ወደዋናው ቤትም ገብቶ ካዝናውን ከፍቶ ሲመለከት,,,,,


ወርቅ እና አልማዝ እንድሁም ብዙ ገንዘብ አገኘ። ያገኘውን እቃ ይዞ ለመውጣት ሲል ሁሉንም መውሰድ የለብኝም ምክንያቱም ሽይሀችን አላህ ፍሩ ብለውናልና ምን አልባት ይህ ነጋዴ ዘካ ያላወጣ ከሆነ መጀመሪያ ከገንዘቡ ዘካ ማውጣት አለበት አለ ።

ካዝናው አጠገብ ተቀምጦ ያገኘውን መዝገብ ፊኖስ አብርቶ መመርመር ጀመረ። እንዳጋጣሚ በሂሳብ ጎበዝ ነበርና ገንዘቡን ቆጥሮ ዘካውን አሰበ። ሂሳቡን ሲያሰላ ብዙ ሰአት ወስዶበት ኖሮ የፈጅር (የሱብሂ) ሶላት ደርሷል። አላህን የመፍራት መጀመርያው ሶላት መስገድ ነውና ወደመታጠቢያ ክፍል ውስጥ በመግባት ውዱእ አደረገ። ለሶላት አዛን አደረገ።

የቤቱ ባለቤት አዛን በቤቱ ውስጥ ሲሰማ ግራ በተጋባ ስሜት እና ድንጋጤ ተነሳ ሚስቱም ተከትላዋለች። የሚያስገርም ነገር ነበር የተመለከተው ፋኖሱ በርቱአል የገንዘብ ማስቀመጫው ሳጥኑ ወለል ብሎ ተከፍቷል በአቅራቢአው አንድ ሰው አዛን ይላል። ሚስቱ በአላህ እምላለሁ እየሆነ ያለው ነገር ምንም አልገባኝ አለች። አዛኑን ከጨረሰ ቡሀላ ሰውየው ወደልጁ ቀርቦ ሰውየው ምን አይነት ጉደኛ ነህ ማነህ አንተ ሌባ አለው።

ልጁም ፈርጠም ብሎ መጀመርያ ሶላት እንስገድና ከዛ ቡሀላ እናወራለን ይለዋል። ባለቤቱም ውዱእ አደረገ ልጁም ለባለቤቱ በል ቅደም ቅደምና አሰግደን ኢማምነት ለባለቤት ነውና አለው። ባለቤቱም ምን አልባት መሳርያ ይኖረዋል ብሎ ስለፈራ ኢማም ሁኖ አሰገደ። እንደት እንደሰገደ ግን አላህ ብቻ  ነው የሚያውቀው። ሶላት ሰግደው እንደጨረሱ ባለቤቱ ወደልጁ በመዞር ማነህ ምን እያደረክ ነው ያለኸው? ጉዳይህ ምንድነው ሲል የጥያቄ ውረጅብኝ አወረደበት። ልጁም,,,,,,,,,,


ልጁም ያላወጣኸውን የዘካ ገንዘብ ሂሳብ እያሰላሁልህ ነበር የስድስት አመት ዘካህን አስቤ ጨርሸልሀለሁ ይህን የዘካ ገንዘብ ለሚገባቸው ሰወች እንድትሰጣቸው ለብቻ አስቀምጨልሀለሁ አለው።

ባለቤቱም በመገረም ሌላ ጥያቄ ጠየቀ ለመሆኑ አንተ እብድ ነህ? ልጁም ይህን ያደረገበትን ምክንያት ከመጀመርያው ጀምሮ ለባለቤቱ አጫወተው። ነጋደውም የልጁን ታሪክ ካደመጠ ቡሀላ ሂሳቡ ትክክል እና ምንመ ያልጎደለው መሆኑን አረጋግጦ ወደሚስቱ ሄደ። የልጁንም ታሪክ በዝርዝር አጫወታት።

ይህ ነጋዴ አንድት ልጃገረድ ልጅ ነበረችውና ወደሌባው ልጅ ተመልሶ እንድህ አለው : ልጀን ብደርህና  እና የሂሳብ ሰራተኛየና ፀሀፊየ ባደርግህ እናትህንም ደግሞ እኔ ጋር ባስቀምጣት እንድሁም አንተን በተጨማሪ በንግድ ሽርክና ባስገባህ ደስ ይልሀል? ልጁም እሽ እቀበላለሁ አለ። እንደነጋም ነጋዴው ምስክሮችን ጠራና ኒካሁን አሰር የጋብቻ ስነስረአት ተደረገ። የነጋደው ሴት ልጅና ሌባው ተጋቡ።

አላህን በቁረአኑ አላህን የፈራ እሱ መውጫ ያበጅለታል። እርዚቅም ካላሰበበት ያመጣለታል ይለናል። ለዚህም ነው ይህ ወጣት አላህን ፈራ ካላሰበበት እርዚቅ አመጣለት። በማጭበርበር በስርቆት በማታለል እሚመጣ ነገር የለም ቢመጣም ለግዜው ይመስለናል እንጅ መጨረሻው ውርደት ነው አላህ የተቅዋ ሰወች ያድርገን


ፀሀፊ አረቡ ዩሱፍ

       ምንጭ ቀሶስ ኢማኒያት ከሚለው
                     መፅሀፍ የተወሰደ

@sineislam
@sineislam

.                ምዝገባ ተጀመረ
        
                اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎
    አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
=============================
🕌*ሂዳያ ኦንላይን የቁርአን እና የተጅዊድ ማእከል*

ማእከላችን በኦን-ላይን ከ አሊፍ ጀምሮ እስከ ተጅዊድ ትምህርት ድረስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ መቆየቱ ይታወቃል። ብዙዎችንም ቃኢዳን በትንሽ ጊዜ በማስጨረስ የሰርተፍኬት ሽልማት አበርክቷል

ብዙ ተማሪዎችን ቁርአንን እንዲያነቡ ሰበብ የሆነው እና ብዙ ሂፍዝ ተማሪዎችን ያፈራው ይህ ማእከላችን እነሆ ረመዳንን ለለውጥ በሚል መርሀ ግብር ለ 1ወር ብቻ የሚቆይ አዳዲስ ደርሶች ማዘጋጀቱን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው

      🌟 የቃኢዳ እና የቁርአን ትምህርት
      🌟 የሩቃ ኮርስ
      🌟 የተጅዊድ ትምህርት
      🌟 ኡሉም አለ-ቁርአን

🔸 በመሆኑም በዚህ የ 1ወር የኦንላይን ፕሮግራም ላይ መሳተፍና መመዝገብ #የምትፈልጉ በሙሉ ከታች በሚገኘው የውስጥ መስመር ሊንኩን ተጭነው በመግባት መመዝገብና ሙሉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ!!!

የውስጥ መስመር ሊንክ
👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
         ☞︎︎︎  @hidaya254

ይህ የቴሌግረም ግሩፓችን ነው ይቀላቀሉ
ተጨማሪ መረጃዎችን ያገኛሉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/hidaya4241

*ሂዳያ ኦንላይን የቁርአን እና የተጅዊድ ማእከል*

#በጣም_ልብ_የሚነካ_ታሪክ_ነው

☞በአረብ አለም የሚኖር አንድ የአሥር አመት ታዳጊ ነው

ይህ ታዳጊ የሰራው ነገር ግን ሠውን አጃኢብ አስኝቷል።

ነገሩ እንዲህ ነው: ይህ የአስር አመት ህፃን ዘውትር በሠላት ወቅቶች ከመሥጂድ ይታደማል

ሠላቱም በጀመዓ ይሠግዳል ድምፅ ከፍ ተደርጎ በሚሰገድባቸው ሦስት ሠላቶች ላይ ታዲያ ኢማሙ ፋቲሀን ቀርቶ ሲጨርስ ማለትም ወለዷ ሊን ሲል ሠጋጁ በአንድነት አሚን ሢል ይህ ልጅ ድምፁን ከፍ አድርጎ ከጀመዓው ተነጥሎ ብቻውን አሚን ይላል....

ይህ ነገር በመደጋገሙ ኢማሙን እጅግ ያበሳጨው ነበር ቢያየው ቢያየው ልጁ ሊያቆም ስላልቻለ አንድ ቀን ከመግሪብ ሠላት በኃላ ንዴቱን መቆጣጠር ያቃተው ኢማም ይህን ልጅ እንቅ አድርጎ አንጠልጥሎ ያምባርቅበታል!

ለምንድነው ምትረብሸው ከጀመዓው ጋር አብረህ ለምን አሚን አትልም እና መሰል ነገሮችን ይህን ህፃን ልጅ ተናገረው😡😡

ይህ ታዳጊ በፍርሃት በተሸበሸቡት ልብሶቹና
ቲማቲም በሚመሥሉ ጉንጮቹ እምባ ያቀረሩ አይኖቹ ያንን ኢማም በሥሥት እየተመለከቱ...

«እኔ ምጮህው አለ......
እኔ ምጮህው እቤታችን መስጂዱ አጠገብ ነው አባቴ ደሞ ሠላት አይሰግድም ምናልባት የኔን ድምፅ ሢሠማ ደስ ብሎት አልያም ተደንቆ ከመጣና ከሠገደ ብዬ ነው ያ ኢማም» ብሎ መለሰለት🥺🥺

ይህን ጊዜ ኢማሙ ሚናገረው ጠፋው ሠውነቱ ተርገፈገፈ😔😔

የአከባቢውን ሠው አፈላልጎ ይህን ለአባቱ አደረሠው አባቱም በልጁ ተግባር እጅግ ተደንቆ ወደ ጌታው እያለቀሰ ተውበት በማድረግ ሠላቱን ጀመረ።

ሰዎችን አይተን ብቻ በችኮላ አንፍረድ። ይህን ለመስራት ያበቃቸው ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል ብለን ኡዝር እንፈልግላቸው ምናልባት መጥፎ ሥራ የሚሰሩ መስሎን ሲፈተሽ ግን በጣም የሚደንቅ ሊሆን ይችላል!!   

ሱብሃን አላህ

@sineislam
@sineislam

ከእለታት አንድ ቀን የአላህ መላክተኛ (ሰ ዐ ወ) መንገድ ላይ ሳሉ አንዲት በእድሜ የገፉ ሴት እቃ ተሸከመው ይመልከቱና፤ወደሴትዬዋ ጠጋ በማለት እናቴ እቃውን ላግዞት በማለት ይጠይቃሉ?!

ሴትዮዋም የአላህ መላክተኛ ስለመሆናቸው የሚያቁት ነገር አልነበረም፤እቃው ከራሳቸው ላይ አውርደው ሰጧቸው፤የ አላህ መላክተኛም
(ሰ ዐ ወ) እቃውንም ተሸክመው እስከ በር ድረስም አደረሱላቸው።

ሴትዮዋ ትንሽ ጠብቀኝ ብላቸው ወደቤት ገቡ፤
የአላህ መላክተኛ (ሰ ዐ ወ) ሴትዮዋ እስኪመጡም ጠበቁ፤ ሴትዮዋም ከቤት በመውጣት እንዲህም አሉ፦
ሊጄ ምክር ብሰጥህ ትቀበለኛለህ አሉ?የአላህ መላክተኛም (ሰ ዐ ወ) እንዴት አልቀበልም ሲሉ መለሱ፤ሴትዮዋም ልጄ እኔ አደራ የምልህ
የሙሀመድን እምነት እንዳትከተል ነው አሉ፤
የአላህ መላክተኛም(ሰ ዐ ወ) እንዲህም አሉ እኔ ሙሀመድ ከሆንኩኝስ አሉ?!ሲሉ ጠየቋቸው!

ሴትዮዋም አንተ ሙሀመድ ከሆንክማ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም ሙሐመድም የአላህ መላክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለው አሉ፤

እንዲህ ነበር የአላህ መላክተኛ (ሰ ዐ ወ)አለምን በፀባያቸው የገዙት!!!

እህት ወንድሞቼ እኛስ እውን ባህሪያችን ስራችን ምን ይመስላል?!!

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ ዐ ወ) ለአለም የበሩ ብርሃን ናቸዉ!!

@sineislam
@sineislam