Latest Posts from አማራ ፋኖ በሸዋ (@shewaamharafano) on Telegram

አማራ ፋኖ በሸዋ Telegram Posts

አማራ ፋኖ በሸዋ
1,668 Subscribers
263 Photos
43 Videos
Last Updated 06.03.2025 12:29

The latest content shared by አማራ ፋኖ በሸዋ on Telegram

አማራ ፋኖ በሸዋ

07 Sep, 17:11

1,797

ይህ ሰው ከስድቡ በላይ ቁምነገር ያወራል በእውነት ስሙት .. "ግብፅ ልትወረን ነው ይላል ወረሞ ..እና እኛ አማሮች ምን አገባን " "..ትክክል ነው
አማራ ፋኖ በሸዋ

31 Aug, 16:16

1,863

የ ሸዋ አማራ
ሸዋ የ ንጉስ ሚኒሊክ የ ፕሮፌሰር አስራት ሀገር፡፡ሸዋ የ አክሊሉ ሀብተወልድ ሀገር ድንበር እና ካርታ ስሎ ኢትዮጵያን የ ፈጠረ ምጡቁ የ ሸዋ ህዝብ የ ራሱን መሪ ማዉጣት መቻል እንዴት አቃተዉ ፡፡ ሁሉም አማራ በ የሰፈሩ የ ራሱን መሪ ይዞ ሲወጣ ሸዋ ግን እራሱን በራሱ እንዳይቆም ለምን ተፈለገ ? ሸዋ ተሸካሚ፣መራጭ እንጂ ተመራጭ እንዳይሆን ለምን ተሰራበት ይህንን ሁሉ ስትመረምሩ የ ሸዋ አማራን ደግመን አናነግስም ከ ሸዋ አማራ ትግሬ ይግዛን ብለዉ አማራን አንገቱን አስደፍተዉ እነሱም መሬታቸዉን ተቀምተዉ ሲማቅቁ የኖሩት ወደጭንቅላቴ ይመጣሉ አሁንም በዚህ ህልዉና ትግል ዉስጥ የ ሸዋ አማራ ላይ ሴራ እየጎነጎኑ ያሉ እነኚህ ሆዳም ሀይሎች ናቸዉ፡፡ ሸዋ የ አማራ መዳኛ !!!
አማራ ፋኖ በሸዋ

27 Aug, 21:37

2,245

ሼር

ከደራ በረኸኞች ለአርበኛ ሽመልስ ንጉሴ(ዳግማዊ ምንሊክ ) እና ለቀስተንህብ ብርጌድ ጓዶቹ የተላለፈ ጥሪ
                                     21''12''16 አ.ም

    ወንድማችን በቅድሚያ እንደምን አለህ ?
  ከከበረው ኑሮ ያስመነነህ የግፉአን ትግል እንዴት ይዞሃል ?
          እኛ ደህና ነን አምክ ይመስገን።
  ጠላት በወረረው ግዛት ከንደ ብርቱ ሆነን የገፋንን አረመኔ ስርዓት እንዳመጣጡ አየሸኘነው አለን ።

ፈለጋቸውን ተከትላችሁ የወጣችሁህችለው የነ በፍቃዱ በላይ የነ ባልፈው አበይ የነ ማሙሽ ያዘው የነ ሽፈራው ደም  በወኔ ላይ ወኔ በድፍረት ላይ ድፍረት አስታጥቆን ሃሞታቸውን እንደውሃ ጠጥተን ከአላማችን ውልፍት ሳንል የዚህን መከረኛ ህዝብ እንባ በብረት ለማበስ ቆርጠን ተነስተናል ። 
ትግሉንና የናንተን ናፍቆት እንኳን አታንሱት መንታ ናቸው ።

ክንዳለም ሽሜ እኛማ ------ አምስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የቱቲ አውደ ውጊያ ላይ ሆነን ከወደ ወለቃ ተኩስ በሰማን ቁጥር ጀግናው ጦሩን ይዞ ከተተ እያልን ብናማትርም የለህም  ።
  ነጋ ጠባ የናንተን  መምጣት እየጠበቅን እንገኛለን  ።
አስችሏችሁ  ይሆን ? ወይስ የትግል ጓዶቻችሁ ወገኔ ተደፍሯል እንዝመትለት ስትለበቸው ለገሙ?

ጀግኖቼ ቢሆን ይከተሏችሁ ታልሆነ ግን እናንተ ብቻ ኑ!
   ተቃላችን ከወጣችሁ ብረቱን አምጡ ያሉ እንደሆን ወርውሩላቸውና ኑ ። በማይመስሏችሁ  ስብስብ ውስጥ በይሉኝታ ሰንሰለት ታጥራችሁ እሰከመቼ ?
እኛ ወንድሞቻችሁ ከጠላት የማረክነው ክላሽ  ያጥር መገርገሪያ ሆኗል  ኑልን ።

  ስትሏቸው ግን ★
በሉ ደህና ሁኑ እኛ ለወጣንለት ህዝብ ሄደናል ብንሰዋ ተሰዋልን የሚለን ህዝብ አለን ።
ብንኖርም በርታ የምንለው ከአለት የፀና ወታደር አለን ። 
ሳንኖር በስማችን ይዋጋሉ ስለዚህ አናስፈልጋቸዋለን በሏቸውና ኑ ቶሎ ክንዶቼ ።

  እኔ አርማዬ ወለቃ ወንዝን ተሻግሬ እቀበልሃሁ ። 

ጀግናው ስለሺ ደግሞ እንዳለህ★
[ ሽሜዋ ጓዶችህን ይዘህ ናልኝ ቀኝ እጄ ሌሎቹ የሽዋን ትግል የመሰረተችውን ደራን ረስተው ለይፋት ሆኗል የሚዋጉት ናና ጠላትን እንደቀድሟችን እንቅጣው ]  ብሎሃል ።

   አርማዬ ነኝ ወለቃ ወንዝ ስር ።  💪
አማራ ፋኖ በሸዋ

20 Aug, 12:01

2,109

በእነዋሪው ውጊያ 387 የገዢው ቡድን ወታደሮች መገደላቸው ተገለፀ!

የሞረትና ጅሩ ወረዳ ዋና መቀመጫ በሆነችው እነዋሪ ከተማ ላይ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ እስከ አመሻሹ በተደረገ ውጊያ በቁጥር 387 የገዢው ቡድን ወታደሮች ሲገደሉ ከዘጠኝ ተሽከርካሪ በላይ ቁስለኛ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን የአማራ ፋኖ በሸዋ ዕዝ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የአገዛዙ ጦር የፋኖ አባላትን ገደልኩ በሚል ከባሕልና ከእሴት ባፈነገጠ መልኩ የሟቾችን አስከሬን አውራ ጎዳና ላይ እየጎተተ ተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረፅ በሚዲያ ማሰራጨቱ ይታወቃል።

ለዚህ ምላሽ የሰጠው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ አገዛዙ የደረሰበትን ከባድ የሆነ የሰውና የንብረት ኪሳራን ለማካካስ በሚል በማሕበረሰቡ ላይ የግፍ በትሩን በጭካኔ እያሳረፈ ነው ያለ ሲሆን፡ ሰራዊታችንም ዘመቻ ሰማዕታት በማወጅ ይሄንን ወራሪ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ከባድ ትንቅንቅ እያደረገ ነው ብሏል።

ነሐሴ 11/2016 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ እስከ አመሻሹ በተደረገ ውጊያ 336 የኮማንዶ አባላት፣ ሁለት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሦስት የፖሊስ አባላት፣ 48 ሚኒሻ፡ በድምሩ 387 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ ከዘጠኝ ተሽከርካሪ በላይ ቁስለኛ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ዕዙ በላከው መግለጫው ገልጿል።

እኛ ብንወድቅ፣ ብንሰዋ እንኳን እልፍ ጠላት ይዘን ነው ሲል በመግለጫው የጠቀሰው ዕዙ፡ ስለዚህ ሕዝቡ በውጊያ በሚሰው ጀግኖች ስነ ልቦናው እንዳይጎዳና ማዘንም እንደለለበት አሳስቧል።

ሰራዊታችን ከትናንት የተሻለ ቁመና ላይ የሚገኝ ሲሆን ለቀጣይ ግዳጅ የተዘጋጀ አስተማማኝ አቅም ያለው ነው ሲል የጠቀሰው መግለጫው፡ በማሕበረሰባችን ላይ የበቀል ዱላ ያነሳውን የገዢው ቡድን ወታደርን በዘመቻ ሰማዕታት አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ነው ብሏል።

በመጨረሻም ዕዙ በመግለጫው፡ የሰማዕታቱን ሞት የግል ፖለቲካ ፍላጎታቸው ማሟያ ለማድረግ ከፋፋይ ሃሳቦችን ሚያናፍሱ አካላትን ተመልክተናል ያለ ሲሆን፡ እነዚህ ከፋፋይ ያላቸውና በሰማዕት ጓዶቻችን ነፍስ ላይ ቁማር ለመጫዎች ሙከራ እያደረጉ ነው ላላቸው አካላት በአስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
አማራ ፋኖ በሸዋ

19 Aug, 21:16

1,864

ሸዋ ውስጥ በዚህ መጠን ፋኖ ሞቶ አያውቅም እነዚህ ጀግኖች በዚህ ሰው በላ ስርአት እንዲጨፈጨፉ ያደረጋችሁ ሰዎች ልትጠየቁ ይገባል ። ሸዋ በጊዜ መሪህን አርቅ መሪ ነው ለሁሉም መሰረቱ ዝርክርክ አመራር ጀግና ያስበላል ጦር ይበትናል እና እቅድ የሌለው ጦርነት ኪሳራ ነው። የሰውም መሳለቂያ ነው የሚያደርገን ቆም ብለን መክረን በቶሎ ወደ አንድነት መጥተን የጀግኖቹን ደም በፍጥነት እንመልስ። ሸዋ የጀግኖች ምድር ናት በቶሎ ቅስሙን እና ልቡን የሰበርነውን ህዝብ መካስ ይኖርብናል።

ሼር በማድረግ አድርሷቸው
አማራ ፋኖ በሸዋ

18 Aug, 21:41

1,904

በትናንትናው ዕለት እነዋሪ የተደረገው ውጊያ የጨበጣ(እጅ ለእጅ) ውጊያ ነበር ። የፋሺስቱ የብልፅግና አፈቀላጤዎች በእነሱ ላይ የደረሰውን ሽንፈት ለመደበቅ ሲሉ ለፋኖ አዛኝ መስለው ታይተዋል ። ነገር ግን ጠላት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ። ሞቱ ተብሎ ከተሰራጨው መረጃ ውስጥ አብዛኛው ሚሊሻና የአድማ ብተና ፓሊሶች ናቸው ።

እርካሽ የፓለቲካ ትርፈ ለማግኘት ሲባል አብረዋቸው ተሰልፈው የተገደሉትን ጭምር ፋኖ እንደገደሉ አሰራጭተዋል ። ከዚህ በተጨማሪ የቆሰሉ ፋኖዎችን ደማቸው እየፈሰሰ ፎቶ አንስተው ለቀዋል ። እንግዲህ ስርዓቱ ወርዶ ወርዶ በሞተ ሰው ፎቶ መነገድ ጀምሯል ።

በዚህ የተነሳ በሚሊሻና በመከላከያ መካከል አለመግባባት ተደርሷል ። ምክንያቱ ደግሞ በትላንትናው እለት በተደረገ ውጊያ ላይ ተገደለ ከተባለው ውስጥ 50% በላይ የሚሊሻ አባላት እና አድማ ብተና ፖሊሶች ናቸው ።

ለሚዲያ ፍጆታ በፋኖ የተገደሉ የሚሊሻ አባላትን አስኬረን በጥይት ሁሉንም ግንባራቸው እንዳይታወቁ ተመተዋል ። በቀብር ወቅት ህዝቡ ሚሊሻዎቹ አብረው አሉ ግን እንዳይታወቁ ሁሉም ግንባራቸው ተመትቷል ብለው ነበር ።

ይህ ጉዳይ አሁን ላይ የሚሊሻ ቤተሰብ መጠየቅ ሲጀምር የወረዳው ሚሊሻ ቀድሞም ተናግረን ነበር አሁን ላይም ቢሆን እውነቱን እንናገር እና ቤተሰብም ካሳ ያግኝ በሚለው ሀሳብ ባለመስማማት እርስ በርሳቸው ተፋጠዋል ።