أحدث المنشورات من አማራ ፋኖ በሸዋ (@shewaamharafano) على Telegram

منشورات አማራ ፋኖ በሸዋ على Telegram

አማራ ፋኖ በሸዋ
1,668 مشترك
263 صورة
43 فيديو
آخر تحديث 06.03.2025 12:29

قنوات مشابهة

Sheger Times Media️
4,619 مشترك
Walia bookstore gallery
4,054 مشترك

أحدث المحتوى الذي تم مشاركته بواسطة አማራ ፋኖ በሸዋ على Telegram

አማራ ፋኖ በሸዋ

31 Dec, 18:23

904

ከመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ሰሞኑናዊ ንግግሮች

<<ወንድም ወንድሙን መሸከም የሚችል ትክሻ ከሌለው ታጋይ አይደለም። አንዳችሁ የሌላኛችሁን ክፍተት ለመሙላት ስሩ። ማንም ሰው ሙሉ አይደለም፤ የሰው ልጅ ትምህርት ከአንቀልባ እስከ መቃብር ይቀጥላል።>>

<<የሃሳብ ልዮነቶች ትናንት የነበሩ፣ ዛሬም ያሉ፣ ነገም የሚኖሩና የሚጠበቁ ናቸው።>>

<<በአመራሩ መካከል ልዮነት ለመፍጠር የብልጽግና ቡድን ቢሊዮን ይመድባል፤ ብልጽግናን እቃወማለሁ የሚለው ምቀኛም ቢሊዮን ይመድባል። ትግላችንን እንጠብቅ! ወሬ እገሌ የመንደር ወሬኛ ነው በሚል ብቻ የሚበተን ሳይሆን የጠላቶቻችን የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ነው። ግን አይሳካም!>>

<<በተለያየ አሰላለፍ ላሉ ወንድሞች ሽምግልናን እናስቀድም። ወንድሞቻችሁንም በመሰረተቢስና የማጥቂያ የግንባር ወገብ ምናምን ፍረጃን አቁሙ።>>

<<ፋኖን የአማራ ሕዝብ ብቻም ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አዳኝ በተስፋ እየጠበቀው ይገኛል፤ እናም ከሌሎች አካላት ጋር አብረን እየሰራን እንገኛለን። ምናልባትም በቅርቡ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የምንሰማው ብስራት ይኖራል። ከሃገራት ጋርም በጎ ነገሮች አሉ።>>

<<እኛ የአማራ ሕዝብ መሪዎች ነን፤ ማንም የመንደር መሪዎች ሆኖ አይቀጥልም። ከአንድነት ማግስት ብዙ ነገሮች ይቀየራሉ።>>
አማራ ፋኖ በሸዋ

08 Dec, 19:25

1,517

#ሰበርዜና!

#Amhara

የጎንደር ፋኖዎቻችን ወደ አንድ መጥተዋል። የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ በጎንደር እዝ በአንድ መዋቅር ተደራጅተዋል።

አርበኛ ባዬ ቀናው፣ ሻለቃ ሐብቴ ወልዴ እና አባት አርበኞች የአማራ ሕዝብ አለኝታነታቸውን አሳይተዋል።

አንድነታችን መዳኛ መንገዳችን ነው!

ድል ለሕዝባችን!
አማራ ፋኖ በሸዋ

26 Nov, 19:02

1,876

የሌሊት ወፍ

"የሌት ወፍ እንደ ዓይጥ ጥርስ አላት፤ እንደ ወፍም ከንፍ አላት፡፡ አንድ ጊዜ የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊቶች ተጣልተው አራት ቀን ሙሉ ጦርነት አደረጉ፡፡

የሌት ወፍ ግን በዳር ሁና ትመለከትና የዱር አራዊቶች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ ትሔድና እኔ እኮቁጥሬ ወደናንተ ነው እዩት ጥርሴን! እዩት ጡቴን እስቲ ከሰማይ ወፎች እንደኔ ጥርስና ጡት ያለው ማነው ትላቸዋለች፡፡

ደግሞ የሰማይ ወፎች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ
ትሔድና እኔ እኮ ቁጥሬ ወደናንተ ነው! እዩት ክንፌን እስቲ ከዱር አራዊት ወገን እንደኔ በከንፍ እየበረረ በአየር ላይ የሚሔድ ማነው ትላቸዋለች፡፡

ወደ ጦርነቱ ግን ምንም ቢሆን አትገባም፡፡

ከጥቂት ቀን በኋላ ዕርቅ ተደረገና ጦርነቱ ቆመ፡፡ ስለዚሁም የሰማይ ወፎችና አራዊቶች ትልቅ በዓል አደረጉ፡፡

የሌት ወፍም ወደ ወፎች ድግስ ብትሔድ እኛ እንደ አውሬ ጥርስ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡ ወደ ዱር አራዊትም ብትሔድ እኛ እንደወፍ ክንፍ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡

ከዚህ በኋላ አፈረችና ወፎችም አራዊትም እንዳያይዋት ቀን ቀን እየተደበቀኝ እየዋለች፤ ማታ ማታ ምግብዋን ለመፈለግ ጀመረች። ቀን ወፎችም ቢያገኝዋት! አራዊትም ቢያገኝዋት አይተዋትም ይገድልዋታል እንጂ

የሌት ወፍ የተባለችውም ከዚያ ወዲህ ነው ይባላል፡፡" (ብላቴን ጌታ ኅሩይ)

አንዳንዶች እንዲህ ናቸው፤ያጠቃ ያሸነፈ ከመሰላቸው ጋር ቦርጫቸውን ያስተካክላሉ፤ላጠቃው መወድስ ለተጠቃው ተረት አያጡም። ጥርሳቸውንና ክንፋቸውን እያቀያየሩ እያሳዩ "እኔ ያንተ አሽከር ያንተ ቡችላ" ይላሉ።

እንደ ንሥርም እንደ አንበሳም ኮራ ብሎ መብረር ወይም መንጎማለል የሚቻለው ወይ ወፍነትን ወይ አውሬነትን መምረጥ ሲቻል ነው!

ጦርነትም ሆነ ጠብ በእርቅ አልያም በመሸናነፍ ይጠናቀቃል። ያኔ እንደ ሌት ወፍ ሌት መጓዝ ይመጣል።

የባንዳም ነገር ይህ ነው መጨረሻው ላኩላቸው ምንአልባት ቢገባቸው ያው ሆዳም አይገባውም እንጂ
አማራ ፋኖ በሸዋ

21 Nov, 21:53

1,591

~ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል!

አማራን ለመጨ*ፍጨፍ በአገዛዙ የተላከን የኦሮሞ ልጅ ማርኮ ተንከባክቦ ወደቤተሰቦቹ የሚልከው የፋኖ ሠራዊት  ሰላሌ ድረስ መጥቶ አንድ ምስኪን ታዳጊ የሚገ*ድልበት ምድራዊ አመክንዮ የለም።

ይልቅስ እነ በቴ ኡርጌሳን የበላው አገዛዝ ፣ ሐጫሉንም የገደለው ሥርዓት፣ የከረዩ አባገዳዎችን የጨፈ*ጨፈው አገዛዝ ፣ በኦሮሚያ የሚታፈሱ ወጣቶች የፈጠረውን የሕዝብ ቁጣ ለማስታገስ የፈፀመው ርካሽ ተግባር ነው።

አለሁ የሚል "መንግስት" ካለ የሰላሌ ሕዝብ ቀንበር ተሸክሞ የጠየቀው ጥያቄ  ቢኖር "አርሰን እንድንበላ የሚያሠማራውን ታጣቂ ያስታግስልን" የሚል ነው።

ፋሽስቱ አብይ ሆይ፥ በእንደዚህ አይነት እንጭጭ ድራማ በፍፁም አትድንም!

@ከአዲሱ ደረበ
አማራ ፋኖ በሸዋ

03 Nov, 21:12

1,716

የአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ

አንረሳውም !!!
ህዝቤ ሆይ እንዳትረሳው በሀዘንህ ግዜ ማን ከጎንህ እንደነበረ ማን እንደጨፈጨፈህ ስትሞት የተሳለቀብህ: ቆሞ ማን እንዳየህ እንዳትረሳው !! ይህ ቀን ያልፋል ,ባንዳ ያንተን መቼም አንረሳውም .. መቼም
አንረሳውም በብዙ ሺህ እጥፍ እሳት ተበቃይ ልጆች አሉት አማራዬ ዛሬ ብዙዎች ሀዘኑ እቤታቸው ስላልገባ ያንተ ደም ምንም መስሎ አይታየውም ግን የአማራ እናት ብቻ አልቅሳ አንብታ አትቀርም አትቀርም
አንረሳውም መቼም።
አማራ ፋኖ በሸዋ

24 Oct, 17:23

2,315

ጀግኖች
አማራ ፋኖ በሸዋ

23 Oct, 15:27

1,912

እባካችሁ - እንደ ዐዲስ እንሠራ

ከነገ ዛሬ ይቀድማልና፣ ከመቅረትም መዘግየት ይሻላልና

፩. አሳማኝ በምንላቸው ማስረጃዎቻችን እና ምክንያቶቻችን ጎራ ለይተን የቆምን፣

፪. ግራ ገብቶን መኻል ላይ የቀረን፣

፫. በቲክ ቶክ፣ በትዊተር፣ በፌስቡክ እና በዩቱብ ደግሞም በሳተላይት ቴቪ የምንጎሻሸም፣

ግን አንድ cause (መግፍኤነገር) - እርሱም የዐማራ ሕዝብ ሕልውና አደጋ ውስጥ መግባቱ የሚያዋሕደን፤ ፈጽሞ ያልተለያየን:-

እባካችሁ የሕዝባችን የመከራ ቀናት ያጥሩ ዘንድ የምንገፋፋባቸውን ትተን ወይም ቆም አድርገን ወደ አንድ እንምጣ።

ለሕዝባችን ስንል ልዩነቶቻችንን ለጊዜው እናምቃቸው። ከዚያም በዐደባባይ ሳይኾን ለብቻ በጓዳ እየመከርን እየተገሳጸጽን እየተማማርን ወደ አንድ ለማምጣት ቃል እንግባ።


የታናሻችሁ ጥሪ!

ከዲን ዓባይነህ ካሴ
አማራ ፋኖ በሸዋ

20 Oct, 18:03

1,780

የእነዚያ ዘር!

ቀዳሚ ምኞታችን ተቋማዊ ውህደት ካልሆነ ደግሞ በህብረት የሚያቆም አንድነትን ማየት ነው። የዓላማ ልዮነት ሳይኖረን፣ የአካሄድ ልዮነቶች ግን ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ነገር ደግሞ ህዝባችን እየጨፈጨፈ ባለው በጨቅላው አብይ አህመድ ላይ ከመተባበር ሊያግደን ፈፅሞ አይችልም።

ዛሬ በሸዋ የሰማነውም ይህንን በግልጽ የሚያስረዳ ነው። ሁለቱ በሸዋ የከተሙ የአማራ እዞቻችን አራዊት ሰራዊቱን አበራይተው፣ ከክተው፣ ፈጭተውታል። ገና ይቀጥላል!

ሸዋ የትግላችን መስፈንጠሪያ ስፕሪንግ ቦርድ ነው፤ በዚህም ትይዮ ደግሞ የፍጥነታችን መቆጣጠሪያ ቫልቭና rate limiting ነውና ብዙ የምንጠብቅበት እናም ትኩረት የምንሰጠው ብሌናችን ነው።
አማራ ፋኖ በሸዋ

20 Oct, 06:29

1,318

ሁለት መቶ ተራሮችን የፈጠረ የተራሮች ዘመቻ!

"ዘመቻ መቶ ተራሮች" ይፋ ሲደረግ የሩቅ ጠላቶችም የቅርብ የኮንዶም ትራፊዎችም ተሳልቀው ነበር። ነገር ግን ይህ ትውልድ ከምድር ፈልቆ እንደወጣ ገሞራ ተራራን ማንቀጥቀጥ ይቅርና ተራራን መናድ የሚችል፣ ሲያሻውም ተራራን በአረንጓዴ ለባሽ ምርኮኞች መሸፈን የሚችል ክንደ ነበልባል ትውልድ መሆኑን በዘመቻ መቶ ተራሮች አስመስክሯል።

አሁን ተራሮቹ 200 ደርሰዋል - ገሚሱ የዘመቻችን ስያሜ ሲሆን ገሚሱ ደግሞ የአራዊት ሰራዊቱ የአስክሬን ቁልል ነው። የአማራ ህዝብን ለማጥፋት ልጃችሁን መርቃችሁም ሆነ አልቅሳችሁ ለውትድርና የላካችሁ እናቶች፣ ልጃችሁ መንገድ ላይ ቀርቷል - አትጠብቁት። ቀሪዎቹም የተለየ እጣፈንታ የላቸውም።

በታሪክ መዛግብት ፊት በኩራት የሚያቆም ታሪክን እየጻፈ ያለው ይህ ትውልድ፣ ጥቂት ክላሽ ይዞ ተነስቶ፣ በሃገር ሃብት አሰሱንም ገሰሱንም የታጠቀውን የግለሰብ ወታደራዊ ተቋምና ሰራዊትን ብትንትኑ እያወጣው ነው። እንኳንም የእናንተ ሆን።

#የመውጫ_መልዕክት፦ አሁንም የድል ቀናችን የሚረዝመው በእኛ ድክመት እንጅ በጠላታችን ጥንካሬ አይደለም። የጎተተንን ድክመት ደግሞ በቅርብ የምናርመው ይሆናል።
አማራ ፋኖ በሸዋ

18 Oct, 07:17

1,532

የብርቱ አርበኛ ቃል

+ + + + +

"ሀገር ሽጠው በሚያገኙት የደም ገንዘብ አሮጌ ተራ ወርደው በሚሸምቱት ድሮንና ተተኳሽ አይደለም ከዋክብት ቦንብ ኾነው የዐማራ ሕዝብ ላይ ቢዘንቡ እንኳን ጠላቶቻችን ይኽን ትግል ማሸነፍ አይችሉም።

እምቢ ያለን ሕዝብ፥ ለህልውናው ላለመጥፋት የሚታገልን ሕዝብ ማሸነፍ ፈጽሞ አይቻልም። ከገፀ ምድር ላለመጥፋት መሣሪያ ያነሣን ሕዝብ ከማሸነፍ የፀሐይን ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ተፈጥሯዊ የጉዞ ዑደት ከሰሜን ወደ ደቡብ ማዞር ይቀላል። ከፈጣሪ በታች ትልቁ ጉልበት ያለው የአመፀ ሕዝብ መዳፍ ላይ ነው።

እንበርታ እንጽና ብቻ!! ጽናት ነገ ከነ- ጠዋት ውብ ጀንበሯ የራስ እንደምትኾን በጥልቅ ከነፍስ በማመን የዛሬን ሰው፣ ተፈጥሮና ሁኔታዎች ወለድ ውጣ ውረዶችን የማመቅና የገለባ ያክል እንኳን ለሥነ ልቦናችን ሳይከብዱን ወደ ግብ የመገስገስ ሥነ አዕምሯዊ ኹነት ነው። እንጽና!!"


#አርበኛ_ዘመነ_ካሤ