https://youtu.be/BGTPiGgqmOA?si=4jf0TiCWWHfJhNrV
Sheger Times Media️ टेलीग्राम पोस्ट

በማትሪክስ ኢንተርቴይመንትና የፕሬስ ስራዎች ኃ.የተ.የግ.ማ እየታተመ በየ15 ቀኑ ለአንባቢያን የሚደርሰው የ #ሸገር_ታይምስ መፅሄት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
4,614 सदस्य
6,689 तस्वीरें
112 वीडियो
अंतिम अपडेट 01.03.2025 03:50
समान चैनल

29,456 सदस्य

11,069 सदस्य

2,980 सदस्य
Sheger Times Media️ द्वारा टेलीग्राम पर साझा की गई नवीनतम सामग्री
https://youtu.be/BGTPiGgqmOA?si=4jf0TiCWWHfJhNrV
👉🏽“በህይወቴ እንደዚህ አይነት ጋዜጣዊ መግለጫ አይቼ አላውቅም!”
***
በህይወቴ እንደዚህ አይነት ጋዜጣዊ መግለጫ አይቼ አላውቅም ትላለች - የABC News የዜና ክፍል አለቃ እና የነጩ ቤተመንግስት correspondent Mary Bruce.
በጭንቅ ውስጥ ያሉት ዘለንስኪ በትራምፕ እና ምክትላቸው ጄዲ ቫንስ ቁጣ እና ማስፈራርያ ሲዋከብ ታይቷል።
“እዚህ የመጣሠ ዉ ሀገርህን ከጦርነት ማውጣት ስለሚችል ዲፕሎማሲ ለመምከር ነው። አንተ የመከራከርም ሆነ - የመጮህ መብት የለህም። እየተጫወትክ ያለህው በሶስተኛው የአለም ጦርነት ነው ካርድ ነው።”
“አነገጋገርህ - አቀራረብህ የሀገራችንን ክብር ይነካል።
እናም ስምምነቱ እንዲፈረም ከፈለግክ - እኛ የምንልህን ስማ። ካልሆነ ግን ብቻህን ትዋጋለህ” ሲሉም አጣደፋት።
ለዚህም ነው - የABC News አለቃ እና የነጩ ቤተመንግስት correspondent Mary Bruce - በህይወቴ እንደዚህ አይነት ጋዜጣዊ መግለጫ አይቼ አላውቅም ያለችው።
በዚህም ምክንያት - ታቅዶ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰርዟል።
እንደሚታወቀው በትላንትናው አመሻሽ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬኑ አቻቸው ቪላድሚር ዘለንስኪ በነጩ ቤተመንግስት ቀጠሮ ነበራቸው።
ቀጠሮው አሜሪካ የዩክሬንን ማእድናት ልትቆጣጠር - በምላሹ ለዩክሬን የደህንነት መተማመኛ ለመስጠት ነበር።
ያም ሆኖ - በ Oval Office የተደረገውን በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ፍጥጫ ተከትሎ - ዘለንስኪ ጋዜጣዊ መግለጫውን ሳይሰጡ ውይይቱን አቋርጠው ለመውጣት ተገደዋል።
https://youtu.be/14xFBw19JwE?si=Sk-RXwjFs0Dv8Q6C
"የዶክተር ሙላቱ አቋም የኔ አይደለም.!” መንግስት
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
ቃል አቀባዩ በመግለጫው ላይ ከጋዜጠኞች ከቀረበላቸው ጥያቄዎች መካከል የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ተሾመ ሙላቱ (ዶ/ር) ኤርትራን አስመልክቶ ያጋሩት ጽሁፍ ነው።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከሁለት ሳምንትት በፊት አልጀዚራ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ "የኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ለመቀስቀስ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ በምስራቅ አፍሪካ አዲስ ግጭት እንዳይከፈት ለማስቆም ጊዜው አሁን ነው" ማለታቸው ይታወሳል።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የተነሱትን ነጥቦች አጣጥለዋል።
ስለ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጽሁፍ ምላሽ የተጠየቁት አምባሳደር ነቢያት "የቀድሞው ፕሬዝዳንት አስተያየት የግላቸው እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም አይደለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
👀 https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
ቃል አቀባዩ በመግለጫው ላይ ከጋዜጠኞች ከቀረበላቸው ጥያቄዎች መካከል የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ተሾመ ሙላቱ (ዶ/ር) ኤርትራን አስመልክቶ ያጋሩት ጽሁፍ ነው።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከሁለት ሳምንትት በፊት አልጀዚራ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ "የኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ለመቀስቀስ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ በምስራቅ አፍሪካ አዲስ ግጭት እንዳይከፈት ለማስቆም ጊዜው አሁን ነው" ማለታቸው ይታወሳል።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የተነሱትን ነጥቦች አጣጥለዋል።
ስለ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጽሁፍ ምላሽ የተጠየቁት አምባሳደር ነቢያት "የቀድሞው ፕሬዝዳንት አስተያየት የግላቸው እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም አይደለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
https://youtu.be/x-b9GguzPgQ?si=g99edh8Xp1b9U-89
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም፣ ተመራማሪ እና መምህር እንዲሁም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታወቀ።
የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው፤ የዶ/ር አንዷለም ዳኘ ግድያን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ገድያውን የፈጸመው በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ኃይል ነው።
ኮማንደሩ እንዳሉት ፖሊስ የሟችን ግድያ በተመለከተ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱንና ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ማዋሉን መናገራቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው።
165 ሚሊየን ብር ደርሷት መደበቋ አልበቃ ብሏት የ25 አመት የትዳር አጋሯን ፍ/ቤት ስለገተረችውና እሱን በመፍታት ያገኘችውን ገንዘብ ብቻዋን ልትሽሞነሞንበት ተዘጋጅታ ከነበረችው ሴት ፣ መታከሚያ አጥቶ ስምንት አመታት በካንሰር ሲሰቃይ የነበረና እድል ፊቷን እስካዞረችለት የ1.1 ቢሊየን ዶላር አሸናፊ…
#ይመልከቱት
https://youtu.be/x-b9GguzPgQ?si=g99edh8Xp1b9U-89
#ይመልከቱት
https://youtu.be/x-b9GguzPgQ?si=g99edh8Xp1b9U-89
Dubartoonni magaalaa Madliin fedhii isaanii malee daldala saal quunnamtii irratti hirmaatanii bulguuwwan gareen gurma’aanii magaalattii bulchaniif madda galii ta’aaniiru.
Mootummaan kolombiyaas gareewwan kunneen to’achuu dadhabee haadholiin halkanii guyyaa imimaan dhangalaasaa jiru.
Dhiironni addunyaa irraa miliyoona 1.5 ta’an dubaroota xoxobbee waggaa 12 fi 12 olii waliin ciisuuf waggaatti gara magaalaa kanaatti ni yaa’u.
wanti sammuu namaa adoochus ifaan waan gurguramuuf ijoollee xoxobbee kunneen dogoggorsuuf gareen bulguu kun itti fayyadama.
Guutuu viidiyoo isaa ilaaluuf liinkii gadii tuqa.
https://youtu.be/fjRKHtgTFaw?si=2VluUjRgdmfEloud
አየር መንገዱ የአፍሪካ ምርጥ የፋርማ ዕቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ እና የአፍሪካ ምርጥ የዕቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ በሚሉ ዘርፎች ነው የአቬሽን አቺቭመንት አዋርድን ያሸነፈው፡፡
ሽልማቶቹ አየር መንገዱ ለልህቀት፣ ፈጠራ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክቱ ሲሆን አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ የዕቃ ጭነት በረራ አድማሱን እያሰፋ መሄዱን ተከትሎ በዓለም ደረጃ ያለውን ተፎካካሪነት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚያስችለውም ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ “አሸናፊዎች እንድንሆን ላበቁን የምንጊዜም አጋሮቻችን እና ታታሪ ሰራተኞቻችን ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን” ብሏል፡፡
አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መዳረሻዎቹንና አገልግሎቶቹን በማስፋፋት የመሪነት ሚናውን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡