**********
ይህ ምስል ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና የሶማሊያው ፕሬዘዳንት ሀሴን ሼክ ሞሀመድ በሞቋዲሹ ባሀረ ገብ መሬት የህንድ ውቂያኖስን ሲጎበኙ የሚያሳይ ነው፡፡
ዛሬ በሶማሊያ መዲና ሞጋዲሹ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉት አብይ - ከጎበኟቸው ስፍራዎች መካከል በተለምዶ “Somalia Beach” እየተባለ የሚጠራው የባህር ዳርቻ ይገኝበታል፡፡
በቀይ ባህር አሊያም በህንድ ውቂያኖስ ለኢትዮጵያ ወደብ ብቻ ሳይሆን የባህር በር ለማጎናፀፍ እየሰሩ እንደሆነ የሚናገሩት አብይ - ውቡን ህንድ ውቂያኖስ በቅርበት ጎብኝተውታል - በሶማሊያው መሪ ሼክ ሞሀመድ አማካኝነት፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለአንድ ዓመት የቆየውን ውዝግባቸውን በድርድር ከፈቱ በኋላ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ለይፋዊ ጉብኝት ሞቋዲሾ የተገኙት፡፡
ሶማሊያ ከአንደ አመት በፊት ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የባህር በር አጠቃቀም ስምምነት ሉአላዊነቴን የሚጥስ ነው በማለት ስትቃም እና የጦርነት ነጋሪት ስትመታ ቆይታለች፡፡ “የአንካራው ዲክላሬሽን” ግን ሞቃዲሾ እና አዲስ አበባ በዚህ መልኩ ወዳጅነታቸው እንዲታደስ ምክንያት ሆኗል፡፡
ለዚህም ይመስላል የጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊው ሳንዶካን ደበበ “እሩቅ አስበን ጀምረናል - የኢትዮጵያ መፃኢ ዘመን ብሩህ ነው” ሲሉ በኤክስ ገፃቸው የፃፉት፡፡