አእምሮአችን በምድራዊው አስተሳሰብና ጥንቃቄ እንዲሞላ የመፍቀዱን አደጋ ጌታ አሳይቶኛል።
👉አንዳንድ አእምሮዎች አስደሳች ያሏቸውን ሌሎች መጻሕፍትን በማንበብ ከወቅታዊው እውነትና ከመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር ተነድተው ሲወጡ የተመለከትኩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ምን እንደሚበሉ፣ ምን እንደሚጠጡና ምን እንደሚለብሉ ሲጨነቁ አይቻ ለሁ። ጥቂቶች ጌታ ዳግም ይገለጣል ብለው ከጠበቁት ጊዜ ተጨማሪ ጥቂት ዓመታት በማለፋቸው ዳግም ምጽአቱ ገና ብዙ ጊዜያት እንደሚወስድ በማሰብ እሩቅ አድርገው ይመለከቱ ነበር።
ነገር ግን በመሃል አእምሮአቸው ከወቅታዊው እውነት በማፈንገጥ ዓለምን ተከትሎ ነጎደ: በዚህ ዙሪያ ታላቅ አደጋ የተመለከትኩ ሲሆን ይኸውም አእምሮ በሌሎች ነገሮች ከተሞላ ለወቅታዊው እውነት የተጋ ይሆናል ይህን ተከትሎ የሕያው እግዚአብሔርን ማኅተም በግንባሮታችን ላይ የምንታተምበ ቦታ አይኖርም።
የሱስ በቅድስተቅዳሳኑ ክፍል የሚቆይበት ጊዜ እያለቀ መሆኑን ተመልክቻለሁ: ባሉን ትርፍ ጊያቶች ሁሉ
በመጨረሻው ቀን የምንዳኝበት መጽሐፍ ቅዱስ በማንበብ ልናጠፋ
ይገባል።👉የተወደዳችሁ ወንድምና እህቶቼ የእግዚአብሔር ትእዛትና የየሱስ ክርስቶስ ምስክር ያለማቋረጥ በአእምሮቸችሁ ውስጥ በመሆን ዓለማዊ አስተሳቦችንና ጥንቃቄ ዎችን ጠራርገው ያውጧቸው:: ስትተኙም ሆነስትነሱ ጸሎታችሁ ይኸው ይሁን::
አኗኗራችሁና ድርጊቶቻችሁ የሚመጣውን የሰው ልጅ የተቀደሰ ማንት ምሳሌ ያደረገ ይሁን።
የምንታተምበት ጊዜ በጣም ኣጭርና በቅርቡ የሚያበቃ ነው::
የተጠራንበትንና የተመረጥንበትን የምንተገብረው አራቱ መላእክት አራቱን ነፋሳት በያዙበት እነሆ በአሁኑ ወቅት ነው::
EWAmh 40.1 - EWAmh 40.3
(ቀደምት ጽሑፎች)
መልካም የእረፍት ቀን