أحدث المنشورات من ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . . (@samuel_dereje) على Telegram

منشورات ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . . على Telegram

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .
ሽ ራ ፊ : ቃ ላ ት

ስ ባ ሪ ፡ ተ ረ ኮ ች

😊 - @Samvocado




https://linktr.ee/samueldereje
2,329 مشترك
386 صورة
23 فيديو
آخر تحديث 09.03.2025 05:54

قنوات مشابهة

LeEgna / ለእኛ
5,581 مشترك
Design Weg
1,502 مشترك

أحدث المحتوى الذي تم مشاركته بواسطة ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . . على Telegram

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

01 Mar, 18:19

735

ድሮ ድሮ ሁሉም ሰዉ ለጀብዱ ተፈጥሯል እል ነበር። ቢወድቅ ለቀናም "ቀን" አለዉ እያልኩ።

ሲገባኝ በጉድጓድ የተጣለ ሁሉ በክብር ዙፋን አይሾምም። ለካ ገድለ ዮሴፍ የጥቂቶች እድል ነበር። በየተጣለበት ጉድጓድ ጊንጥ የነደፈዉ ፥ የሌት አዉሬ የገደለዉ እልፍ አለ ።

በጎሊያድ የተቀሉ ብዙ ዳዊቶች ተረስተዋል። አንበሳ ስለበላቸዉ እልፍ ዳንኤሎች ያላፈሰስነዉ እንባ አለ። ተራራዉ ስለለገመበት ስሞኦን ማን ዘመረ?

ለስኬት ነዉ የተፈጠርከዉ ያሉህን መካሪዎች ቂል በልልኝ።

አትሞኝ! ለሞከረ ፥ ለጣረ ሁሉ ይብራል ይሉት ተረት ተረት ነዉ። ከጣረዉ ፥ ከሞከረዉ ለቀናለት ለጥቂቱ "ምንአልባት" ይበራል። ግን ላልጣረ ፥ ላልሞከረ በርግጠኝነት ይጨልማል።


@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

25 Feb, 20:29

1,228

ያሰላዉ ሂሳብ ይጎድልበታል። እሱ ቢያጥር ፥ እሱ ቢከልል ሲነጋ ይፍርሳል።
ምሁር ነዉ ሰዉየዉ!
አለም ግን ለቀመሩ አልተደለለም። ንዋዩ ቢፈስ ፥ ቀለሙ ቢሞላ እሱን ግን ፅልመት ያድነዋል።
___

ያላየዉ እጅ እግሩ ስር ጥሬ ዘራለት ፤ ያለመነዉ ልብ ለጥሙ ምንጭ አፈለቀ ።
እዉር ነዉ አሞራዉ! አለም ግን ለእዉርነቱ አልተወዉም። ብሌኑ ብርሃን ባይጠራ ፣ አይኑ ወጋገን ባያይ ፥ እሱ ግን አልተራበም።

___

እድል እንደጨለማ ጥላ አይደል - ባታየዉስ መች ይተዉሃል?
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

10 Feb, 18:46

2,096

.



@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

19 Jan, 06:42

3,132

ነግሬሽ ነበር?

ደመና ቀን እንደማልወድ? ካፊያ እንደሚጨንቀኝ ፣ ዝናብ ድብርቴ እንደነበር? ደሞም ተራ ሁነት – ተጠልዬ ፣ ኮት ደርቤ የማሳልፈዉ።  

ይግረምህ ሲል ጥላ ጨብጠሽ ፥  ዝናብ ላይ አጊጠሽ ካየሁ ወዲህ ክረምት ናፋቂ ሆኛለሁ። 

ተስፋ አይሰንፍ .  .  . ሃምሌ መሃል ወለም ላለኝ ልብ — ይኀዉ ጥር መሃል እታሻለሁ።


.

@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

25 Dec, 18:59

3,834

“Believe me, I know what it's like to feel all alone... the worst kind of loneliness in the world is isolation that comes from being misunderstood, it can make people lose their grasp on reality." ― Dan Brown, Inferno

And I wish you also knew this state of isolation. Sadly you don't. Or maybe that's good? But you won't ever be able to get too close. You'll always be on the periphery. I wish I could share more today.

I wish I could tell you more. Why I'm the way I'm. Why I say the things I say. And above all where all the anger & resentment comes from. I wish I could spell it out for you. The damages of the past became the builders of tomorrow's misery.

Someone else did the harm and someone else has to pay for it. How is that even fair you asked me? And I obviously had no answer. The silence between us is not due to lack of conversation. This silence has my screams in every fold.

I wish you could hear that. I wish you knew. My reality has now become your misery.

I'm now your inferno.

I'm extremely sorry.

Because I have a lot of unfulfilled wishes.

And Sorry about that...

Photo: Sosina Mengistu
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

18 Dec, 07:25

3,450

ደስታ! ከረሜላ ብቻ አይደለም።



"ልጅ ሆኜ የሆነ ቀን ደስታ ከርሜላ ገዛሁ።  እንደልጅነቴ የኔ በሆነዉ ከረሜላ ያለቅጥ ደስ ብሎኝ ነበር . . ."

ሳዉቃት ልጅ ሆኜ ነዉ። አብሮ አድጌ ነበረች።  ቤቴ ቤቷ አጠገብ ፥ እናቴ የእናቷ ወዳጅ ነበሩ። አብሮ የተሰፋ ልጅነት አለን። ብዙ የሱዚ ገመዶች ቀምቼያት አልቅሳለች ፥ ብዙ  የዉሸት "መታኝ"ኞች ለእናቴ አቃጥራ ተገርፊያለሁ። 

ሰኞ ፥ ማክሰኞ ስትዘል የተደበቀ ፥ ጠጠር ስትለቅም ያልታየኝ ፥ አኩኩሉ ስትል ያልጎላ  ጡት አጎጥጉጣ  አይን ስትገባ  በለስ እንደበላ አዳም ዉበቷ ለአይኔ ተገለጠ።  ( ለእኔ ብቻ አይደለም - ለሃገሩም)

እንደሌላ ቁንጅናዋን ፥ ሴትነቷን ብቻ ሳይሆን ሳቋን ፥ እንባዋን እንዳየ። ሥሥ ጎኗን እንደፈተሸ ( በልጅ ልብም ቢሆን)።  ልጅ ሳለን በልፊያ ከፍም ካልን በጥልቅ ወሬ  ልብ ምቷን እንደመዘነ ፥ ቀድሞ ከንፈሮቿን እንደቀመሰ ፥ በሄደችበት እንዳጀበ  (በዚህ በእኩዮቼ ቢቀለድብኝም) ፥ ከእናት ከአባቷ በፊት ተጠሪዋ እንደሚባል አንድ ሰዉ ፤ ልመስክር። አመሏ ከመልኳ ይረቃል ። ከገጿ እኩል ግብሯ ያምራል። 

ላይወዷት ትከብዳለች!

፪ 

" ከረሜላዬ በእጄ እንዳለች ልጣጯን ብዙ ጊዜ ፈትቼ ብዙ ጊዜ አስሬያታለሁ። ልበላት አልቸኮልኩም! የኔ አይደለች?" 

"የምኞት አስኳል አለመጨበጡ ነዉ ፤ ሰዉ ለያዘዉ አይጓጓዋም?" ይሉት ፍልስፍና አለ።*  እዉነት ይመስላል። ግን አንዳንዴ የጨበጡትም ያጓጓል። አንዳንዴ!

እናም ባደግን ቁጥር መላመዳችን ጎላ! ሳቋ የቀን ማጀብያዬ ሆነ። እቅፏን ብቻ ሳይሆን ኩርፊያዋን እናፍቅ ነበር። አብረን ዉለን ሲመሽ መግቢያችን ያባባናል። እልፍ ጊዜ ቻዉ እያለች ዳግም ከንፈሮቿ ወይ በወሬ ወይ በእኔ ከንፈር ይጠመዳሉ። ሰባ ጊዜ ቻዉ ብላኝ በሰባኛዉ ትሄዳለች። እያመናታች። የሸኘኋትን ልጅ እያናፈኩ ቤቴ እገባለሁ።  

የሆነ የሆነ ቀን የምናወራዉ የለንም። ጋደም ባልችበት ወደ ደረቷ እጠጋና ልብ ምቷን እሰማለሁ። የረጋ ፥ ጊዜ የጠበቀ ነዉ። ወደ ከንፈሯ ስጠጋ ግን ይፈጥናል። ስስማት ከልጅ ልቧ እኩል ትንፋሿ ይፈጥናል። ረግረግ ነበረች። የሆነ እድሜዬ ስሯ ሰርጓል። 

በዚህ ሁሉ ግለታችን ዉስጥ ጭኗን ከፍቼ አላውቅም። የሆነ የሆነ ቀን በእጄ የታፋዎቿን ግለት ለክቻለሁ። አልክድም! ግለቱ ይጋባ ነበር። ግን ቃሏ ይቆይ ስለነበር መሻቷን አልገፋሁም። ገና ዘመናት አብረን አይደለን?።

"የኔ ናት!" ፥ እንደዛ ብዬ ነበር።



"ጉጉቴ ሥሥቴን ሲያሸንፍ  የከረሜላዬን ልጣጭ በእርጋታ ገፍፌ ወደ አፌ ልከት ሳስጠጋ  ከእጄ ወድቃ እግሬ ስር  ያለ አፍር ላይ ወደቀች።  ላነሳት ያየኝ መኖሩን ልቃኝ ቀና ስል ከእናቴ ጋር ተያየን።
 " በል አንሳና ጣል"  ትዛዝ ነበር።


 ከነሥሥቴ ሳላጣጥማት ሄደች - ከረሜላዬ! " 

እድል ፍትህ የላትም። ተስፋ ከጤዛ ያጥራል። ሰዉ ስለፈልገ ብቻ አያገኝም። ሰዉ ስላልጠየቀም አያጣም። ይጠማል ፥ ሲለዉ ሳይደግስም ይጣላል።

እንዲህ ሆነ . . . አደገች ፥ አደኩ። ለዉጥ አሻች። እንደትናንት  በመሳም ልቧ አይመታ ፥  ከሆዷ መሳቅ ተወች።  ሁሉ ቀልድ ለዘዘባት ፥ ወሬችን ወደ ቅጽበቶች አጠረ።  መጣበቃችን ላላ። እኔ እና እሷ እንዳልነበርን። በወራት እኔ እሷን እና ብዙ ወንዶች ሆንን። 

በጊዜ እንደሸረሪቷ ቀስ በቀስ ሸረተት እያልን ከእኔ እጅ እሷ ፥ ከእሷ ልብ እኔ ሾለክን።

የሆነ እለት ምን ጆሮ ለባልቤቱ ባዳ ነዉ ቢሉ ከርሞም ቢሆን ሰማሁት። "ይቆይን ለሌላ እንዳላለች። ብዙ አንዳቀፈች ፥ ብዙ እንዳላበች። ዝግ ጭኗ ፥ ዛሬ መንገድ እንደሆነ።" እና ሌላም ያመመኝ ብዙ ነገር . . 

 ግን ምስክር ነኝ።  ሰናይ እንደነበረች። ጸደይ ነፍስ እንደነበራት!

ከእሷ ወዲህ "መልክ ይረግፋል። አመል እንጂ ዉበት አላፊ ነዉ" ሲባል ሳቅ ያፍነኛል። የቱ ፈላስፋ ነዉ የአመልን ዘላለማዊነት የሰበከን?  የቱ አዋቂ ይሆን ጸባይን ከመልክ በላይ ያነገሰዉ? መልክም ፥ ጸባይም አላፊ ነዉ።  ጊዜ አይለዉጠዉ የለም። 

"ትወደኝ ነበር!"  ነበር እንኳ ይለወጣል።


.

@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

13 Dec, 18:46

4,447

.



@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

05 Dec, 18:00

3,701

ከዝቅ ይልቅ ፣ ከፍ ያድጣል። ማጣት ከወሰደዉ ምቾት የነጠቀዉ ይበልጣል።  

ሃገሬዉ " ችግር ነዉ ጌትነት ካላወቁበት" እንዲል!


@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

03 Dec, 19:00

3,917

ቀይዋ ወፍ ፥ ቀይዋ ወፍ . . .

መልከኛ አይደለችም። ወይ ዉብ የሚሉት አይነት። በልክ ግን አይን ትገባለች። ሰዉ ቀን ቢሆን ለበዓል ብታንስ ቆንጆ ቅዳሜ ይወጣታል። ረዥም ናት። ከፊቷ እኩል የጎሉ ጥርሶች ፣ የሚያስቅ ደሞም የሚያጓጓ የከንፈር ቅርጽ አላት።  ቀይ ናት። ጸጉሯ የሆነ ማንነቷን ያሳብቃል። ችኩል አትባልም። እንደዛዉ የረጋች አይደለችም። በአንዴ ሁለቱንም ያልሆነች አይነት. . . 

ሳገኛት ቦሌ መጨላለሙ ነበር። ተቀምጣ ከጠበቀችኝ ካፌ ፍሪዝ ባረገችዉ ጸጉር ጎልታለች። 

 ተነስተን አንድ ቅያስ አልፎ የነበር ባር ገባን።  እንደተቀመጥን "የመጀመሪያ ወንድ ነህ። በስልክ አዉርቼ ያገኘሁት" አለች። ያወራሁትን ሁሉ አላገኝም ልትል። ድምጿ አዘቦት አይነት ነዉ። ዞር ብል የምረሳዉ።

"ልዩ ነኝ ኣ!"

" አይደል" ፈገግ አለች። ስላቅም ፥ ጨዋታም  ያለዉ አይነት። 

 እናወራለን ፥  ስለምን እንደምናወራ ግድ አላለንም። ስለምንም ብናወራ ወሬው አይጠነክርም ፥ አይሳሳምም። አይደብርም ፥ አይደንቅምም። ትንሽ ትስቃለች ፥ ትንሽ እስቃለሁ። ትንሽ ትቀልዳለች ፥ ትንሽ እቀልዳለሁ።

 በመሃል ዝም ይዉጠናል። በደበዘዘዉ ብርሃን አይኗን ፍልጌ አያለሁ። አትረበሽም።  በሃሳቧ ትጠፋለች ፥ እኔ ደግሞ በአይኗ።  እንደወሬያችን ዝምታችንም ያዉ ነዉ። አይቀዘቅዝ አብዝቶ አይሞቅ። ለብ ያለ።

ድንገት ድንገት የሆነ የጠጠረ ጥያቄ ትወረዉራለች። ቀልድ ይመስል። መልሰን በጥያቄዋ ወደ ለዘብተኛ ወሬያችን እንገባለን።  
ሳናዉቀዉ ( ወይ እኔ ብቻ ) ተላመድን። እጆቿ እጄ ላይ ከረሙ። አካሏ ሲቀላት ፥ ሳቋ ነጻ ሲወጣ። 

በመስኮቴ ገባች. . .

የሳምኳት ቅጽበት እንደልጅ የሃሴት እለት ያለ ነዉ። ዛሬ ድረስ ትዝ የሚል . . .

 ሥስማት አይኗን የከደነችበት ዝግታ ፈጥኖ  ፥  ከንፈሬ ከንፈሯ ደጅ እስኪደርስ የዘላለም ያህል ራቀብኝ። ሩቅ ሆኖ.  . . ሲደርስ የጠበኩት እረፍት አለዉ። የሆነ አይነት መመረጥ። 

ከዛ ወዲህ የዝምታ ልዋጭ አገኘን።  መሳም የሚሉት ምትሃት . . .

ከአካሏ ተላመድኩ። በህይወት በብዙ ምርጫ ግራ ፥ ቀኝ ማትሪያለሁ። እሱን ያቀፍኩ ቀን " የምፈልገዉ ይህ ነዉ አልኩ"

በመስኮቴ ወጣች

የሆነ ቀን ድንገት ጠፋች።  እንዲያ ለምጄ። ብደዉል ብደዉል ምላሽ ጠፋ።  ጠብኩ አልደወለችም።  ደገምኩ ፥ ሰለስኩ። አይነሳም። ተዉኩት። 

ረሳኋት። ወይ እንደረስኋት አሰብኩና ህይወት ቀጠለ . . .

ከቀናት ወዲያ እለት እለት ይባስ አስታዉሳት ጀመር። እንዴት? እንጃ! ግን ዘመን አብሬ የከረምኳቸዉን በሳምንት እንዳልረሳሁ በአንድ ጣት ቢቆጠር የማያልቅ ቀን ያገኘኋት እሷ እንዲ ልቤን መርገጫ አሳጣች። 

አላስቻለኝም። መልዕክት ላኩ "ምነዉ" የሚል። የሆነም ቀን እንዲ ጠፍታ መመለሷ ትዝ ሲለኝ። ረጅም ምክንያት ያልሆነ ምክንያት አወራችኝ። " ባንተ አይደለም ፥ ያልፈታሁት ነገር አለ አይነት"  ቃል በቃልም ባይሆን እንደዛ። ልቤ አመነ ፥ ቀልቤ በሞኝ ልቤ ሳቀ . . . 

ደወልኩ። አነሳች።  ረጅም ወሬ ሳወራት መሸ። እንደድሮ ሞቅም ያለለ ፥ ያለዘዘም። ልቤ ዳጋም ተስፋ ጣለ. . .

ዉይ በራ ሄደች! . . .

ከዛ .  . .  ከዛማ ዳግም ጠፈች። ዳግም ደወልኩ ፥  አይነሳም። አሁን ገባኝ ፥ ተዉኩትም። 

ለምን ቀረች? ጥያቄ አይደለም። ምክንያቱ አይገድም መቅረቷ እንጂ  .  . .

ሳስብ ብዙ ሰዉ ገብቶ በሚወጣበት ህይወታችን ጥቂት ናቸዉ  እንዲ ልብን አከዉ የሚያልፉት። ቀናት መተዉ ፥ ወራት የሚናፈቁት።  ስለተለዩ  ፥ ስላማሩ ፥ ወይ ስላወቁበት ሳይሆን እንዲዉ እድል ፥ ምርጫ ሆኖ . . . 

ብቻ ዛሬ ሲገባኝ ያ ቀን ሸረተት ብያለሁ። ከወደ ልቤ . . .


@samuel_dereje
ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

22 Nov, 08:47

3,652

ዘመኑ ከብዶናል። ኑሮዉ ብቻ ሳይሆን ከጊዜዉ ጋር መግባባቱም።  

ለአንዳንዶች ዘመን ኋላ ቀርታለች። ሃገሩም ፥ ባህሉም አልፎበታል።  ሊጎትቱት ይታገላሉ ፥ እነሱን እንዲመስል። ኋላ ቀር ወይ ያልነቃ እያሉት። አፍ አዉጥተዉም ባይሆን . . . በመብት ወይ በመሰልጠን ስም።

አንዳንዶች ነፍሳችው ገና ነች። ወጉንም ፥ ስርአቱንም እናጥብቅ ባይ ናቸዉ። ቸኩሏል ይላሉ — ትዉልዱ። ሰይጥኗል ፥ ዘምኖ ሞቷል አይነት። ከፊሉ እምነቱን ሙጥኝ ብሎ ፥ ሌላዉ መጪዉ ባህል እሱን አልመስል ሲለዉ። 

ገሚሱ ግራ ገብቶታል። ቢዘምን ቢዘገይ ግድ ያለዉ አይመስልም። ወይ ይሄን ለማሰብ ኑሮዉ ቀና አላረገዉም። የሚከንፍ ባቡር መንጠላጠል ሆኖበት ሰርክ ሊሳፈር ያደገድጋል። አጀንዳዉ እንደ ንፋስ ነዉ። አንዱን አንስቶ ሳያመነዥግ ደግሞ ሌላዉ ያፉጫል። ሃሳብ ይሰጠዋል እንዲያስበዉ ግን ጊዜ የለዉም። 

ደሞም ቅንጦት አይደል? ደህንነት ፣ መጥገብ ይጠይቃል — ስለሚሰማን ለማሰብ።  

ተመሰገን ነዉ! እንዲህ ምን እንደሚሰማን  ለማሰብ ጊዜም ፥ ህይወትም ቅንጦት ለሰጠን። እልፉ ቢጤያችን ያንን አልታደለምና።

.

.

Like Dave says in his special Stick and Stones " I did something most people didn't have the time or the luxury to do, I think about how I feel"


@samuel_dereje