Latest Posts from ራስን ማግኘት!!! (@rasenmagyet3679) on Telegram

ራስን ማግኘት!!! Telegram Posts

ራስን ማግኘት!!!
ወዳጄ፥ ሕይወት አጭር ናት።ዛሬን እንጂ ነገን ስለመኖርህ እርግጠኛ መሆን አትችልም። ስለዚህ ዛሬን መልካም አስብ፤ለሌሎች መልካም አድርግ።በሙሉ ልብህ እመን።ስላለህ ነገር አመስግን።ሰው አትበድል ነገር ግን ብትበድል ይቅርታን ጠይቅ፤ቢበድሉህም ይቅርታ እስኪጠይቁህ ሳትጠብቅ ይቅርታን አድርግ። የዋህ ሁን ነገር ግን ይቅርታ ያደረክለት ሰው ዳግም ይበድልህ ዘንድ ሞኝ አትሁን።

መልካም ዛሬ(ከዛሬም አሁን)!?
2,512 Subscribers
192 Photos
9 Videos
Last Updated 12.03.2025 04:03

The latest content shared by ራስን ማግኘት!!! on Telegram

ራስን ማግኘት!!!

05 Mar, 17:07

287

6.  "If you really want to do something, you'll find a way. If you don't, you'll find an excuse."

"አንድን ነገር ከልብህ ስትፈልገው መንገድ ትፈልጋለህ ካልሆነ ግን ሰበብ"

7. "Don't wish it were easier. Wish you were better."

"ቀላል በሆነ ብለህ አትመኝ ይልቅስ እኔ ጠንካራ ብሆን በል!"

8. "Time is more valuable than money. You can get more money, but you cannot get more time."

"ጊዜ ከገንዘብ በላይ ውድ ነው ተጨማሪ ገንዘብ መስራት ትችላለህ ተጨማሪ ጊዜ ማግኘት ግን አትችልም"

9. "For things to change, you have to change."

"ነገሮች እንዲለወጡ አንተ መለወጥ አለብህ!"

10. "Take care of your body. It's the only place you have to live."

"ሰውነትህን ተንከባከበው ብቸኛው የነፍስህ መኖሪያ ቦታ ነው።"


https://t.me/RasenMagyet3679
ራስን ማግኘት!!!

27 Feb, 00:51

550

ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ እጅግ ይበልጣል።

መመጽሐፈ ሲራክ(25:8)
ራስን ማግኘት!!!

25 Feb, 16:32

579

ያለኸው አሁን ላይ ነው?!
ራስን ማግኘት!!!

11 Feb, 19:50

816

https://vm.tiktok.com/ZMkG5FWsc/
ራስን ማግኘት!!!

04 Feb, 01:54

994

ሁሉም ሠው የራሡ የሆነ ታሪክ አለው…ሁሉም
ደግሞ የራሡ ታሪክ ጸሀፊ ነው፡፡ እስካሁን ያለው
ታሪክህ ካልጣመህ ሠርዘህ እንደገና ጻፈው!!
በራስህ የምትተማመን ከሆነ የፈለከውን አይነት
ኑሮ ለመኖር አቅሙ አለህ፡፡
ራስን ማግኘት!!!

03 Feb, 19:29

993

በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ባህሪህን ይወስናል

ባህሪይህን ተመልከተውና በራስህ ላይ ያለህን አመለካከት በግለጽ ይጠቁምሃል፡፡ ከሰዎች ጋር ስትሆን የምትገልጠው ባህሪይ በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ነጸብራቅ ነው፡፡ ብቻህን ስትሆን፣ ስለራስህ ስታስብ፣ ራስህን በመስታወት ስትመለከተው ስለራስህ የምታስበውን ትክክለኛውን ሃሳብ አግኘውና ከሰዎች ጋር ስትሆን የምታንጸባርቀውን የባህሪህን ፍቺ ይነግርሃል፡፡

ለምሳሌ፣ ጤናማ የሆነ በራስ መተማመን አመለካከት ያለው ሰው የሚገልጠው ባህሪይና የዝቅተኝነት ስሜት ያለው የሚገልጠው ባህሪይ አንድ አይደለም፡፡

እንደተገፋና እንደተናቀ፣ ዝቅተኛ እንደሆነ የሚያስብ ሰው ማንም ሳይነካው ሰውን የሚነካና የሚተናኮስ ባህሪይ ያዳብራል፡፡ ማንም ገፋው አልገፋው ምንም ለውጥ እንደማያመጣበት የሚያስብ ሰው የተረጋጋና አላማው ላይ የሚያተኩር ባህሪይ ይታይበታል፡፡

ለምንም ነገር ያለመመጠን ስሜት ያለበት ሰው የፍርሃትና የአይን አፋርነት ባህሪ ይወርሰዋል፡፡ የሚመጥን ማንነትና አመለካከት እንዳለው የሚያስብ ሰው ደፋርነትና ተግባቢነት ይኖረዋል፡፡

ሰዎች አይፈልጉኝም የሚል ስሜት ያለበት ሰው ለሁሉም ሰውና ለሁሉም ነገር እሺ ባይነት ያጠቃዋል፡፡ ተፈለገም አልተፈለገም ተረጋግቶ የሚኖር ሰው ያመነበትንና ያላመነበትን በመለየት ሃሳቡን መግለጽ ችግር የለበትም፡፡

ተወዳድሮ ለማሸነፍ እንደማይበቃ የሚያስብ ሰው አታላይና አጭበርባሪ ባህሪይን ያዳብራል፡፡ ምንም ነገር ቢሆን ራሱን አሰልጥኖ መወዳደር እንደሚችል የሚያምን ሰው ደግሞ ቀጥተኛና እውነተኛ ይሆናል፡፡
በራስህ ላይ ያለህ አመለካከት ጤናማ ሲሆን ማሕበራዊ ግንኙነትህም እንደዚያው ጤናማ ይሆናል፡፡

ስለዚህ ማሕበራዊ ሕይወትህ እንዲስተካከል ከፈለክ በቅድሚያ በራስህ ላይ ያለህን ምልከታ አስተካክለው፡፡

ዶክተር ኢዮብ ማሞ

ራስን ማግኘት!!!
ራስን ማግኘት!!!

14 Jan, 00:46

1,148

ዛሬ ደግሞ ትንሽ ወንድሞችን እንቀጥቅጥ ለምን እህቶችን ብቻ ሎል


መጽሐፈ ምሳሌ 6
32፤ ከሴት ጋር የሚያመነዝር ግን አእምሮው የጐደለ ነው፤
እንዲሁም የሚያደርግ ነፍሱን ያጠፋል።
33፤ ቍስልንና ውርደትን ያገኛል፥
ስድቡም አይደመሰስም።


ካላገባሃት ሴት ጋር ምታመነዝር ከሆነ አእምሮ የጎደለህ ነህ እያለህ ነው ቃሉ.. ኧረ ወራዳም ብሎሃል እና ደግሞ ለዘላለም ማይደመሰስ ስድብ ነው በአንተ ላይ ያለው.. በዚህም ነፍስህን ታጠፋለህ ይልሃል..

እንዲህ የጎደለ አእምሮ ይዘን እንዳንኖርና ነፍሳችንንም እንዳናጠፋ ጌታ ይጠብቀን.. የሳትንም ጌታ በምህርቱ ይቀበለን ዘንድ ንስሐ እንግባ..

@Apostolic_Answers
ራስን ማግኘት!!!

10 Jan, 12:29

1,278

ፍቅር የሞተበት
ግሩም ዘነበ

https://t.me/RasenMagyet3679
ራስን ማግኘት!!!

07 Jan, 17:09

1,313

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን!🕊

መልካም በዓል!
ራስን ማግኘት!!!

20 Dec, 10:28

1,507

Merxute sewohe👏