RADA College HO

@rada_college


RADA College HO

21 Oct, 12:06


የ 2017 የቴ/ሙያ የመቁረጫ ነጥብ

RADA College HO

21 Oct, 12:06


የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።
የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።
@rada_college

RADA College HO

01 Jul, 13:00


@ትምህርት_ ሚኒስቴር

የ2016 የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT)  ሐምሌ ወር መጨረሻ ሳምንት እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

@rada_college

RADA College HO

07 Jun, 09:03


ለሬሜዲያል ተፈታኞች በሙሉ
የትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናን ከሰኔ 3-10/ 2016 ዓ.ም ድረስ ለመስጠት የፈተና ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ ሰኔ 9/ 2016 ዓ.ም የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ስለሆነ በዕለቱ ይሰጥ የነበረው ፈተና ሰኔ 11/2016 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ @MOE

RADA College HO

21 May, 06:00


#ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የመውጫ ፈተና Re-exam የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ

በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አመልካቾች በሙሉ፣ ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 – 21/2016 መሆኑን አውቃችሁ የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፤
1.ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የምታካሂዱት እና የአገልግሎት ክፍያ የምትፈፅሙት በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊው የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።

2.የ ድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ (500.00 ብር) በቴሌ ብር ብቻ የሚከናወን ይሆናል።
MOE

@rada_college

RADA College HO

29 Apr, 13:46


#የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና
ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።
@rada_college

RADA College HO

26 Feb, 12:37


ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ2016  ዓ .ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ውጤት ከየካቲት 18/2016 ዓ/ም ጀምሮ መለቀቁን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ፤ ለሁሉም የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ ባስተላለፈው መልዕክት ነው።

ተፈታኞች ውጤታችሁን በ https://result.ethernet.edu.et ሊንክ ማየት ትችላላችሁ!!
MOE
@rada_college

RADA College HO

08 Feb, 06:03


ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች

ለድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ
የካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የ ድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ የመፈተኛ የይለፍቃል (Password) ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. በምዝገባ ወቅት በሞላችሁት email በኩል

2. https://exam.ethernet.edu.et ላይ በመግባት የከፈላችሁበትን Transaction Number በማስገባት እንዲሁም

3. ከተመደባብችሁብት የመፈተኛ ተቋም ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ
• ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች የይለፍ ቃል (Password) የምታገኙት ከምትማሩበት ወይም ከተመደባብችሁበት የመፈተኛ ተቋም ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።

• ሁሉም ተፈታኞች የሞዴል ፈተናን እስከ የካቲት 5/2016 ዓ.ም መውሰድ ይኖርባቸዋል።

MOE
@rada_college

RADA College HO

31 Jan, 18:33


የመውጫ ፈተና ተራዘመ።

የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ

ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም ሲሆን

ለአዲስ ተፈታኞች ሞዴል ፈተና ከጥር 27 እስከ 30/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

የተፈታኞች ዝርዝር እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን እንደደረሰን  የምናሳውቅ ይሆናል።

@rada_college

RADA College HO

24 Jan, 18:55


" የመውጫ ፈተና ምዝገባ ጊዜ ተራዝሟል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ መራዘሙን አስታወቀ።

በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመፈተን የምዝገባ ጊዜው ጥር 08/2016 ዓ.ም ጀምሮ ጥር 15/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ መጠቀሱ የሚታወሰ ነው።

ይሁን እንጂ ትምህርት ሚኒስቴር በተፈታኞች ጥያቄ መሰረት የምዝገባ ጊዜው እስከ ጥር 20/2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ሌሎች ሁኔታዎች ግን ቀደም ሲል በተገለጸው አግባብ የሚከናወኑ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል
@rada_college

RADA College HO

21 Jan, 03:49


#መረጃ፦ እንደ ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች

የተፈጥሮ ሣይንስ ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ፊዚክስ፣
ኬሚስትሪ፣
ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት


የማኅበራዊ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ታሪክ፣
ጂኦግራፊ፣
ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት


በዚህም #የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።

የሥነምግባር እና ሥነ ዜጋ ትምህርት (Civics and Ethical Education) ፈተና በሁለቱም የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች አልተካተተም።

MOE
@rada_college

RADA College HO

17 Jan, 07:45


ማስታወቂያ
የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለምትፈተኑ አመልካቾች በሙሉ

ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የመውጫ ፈተናን ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ከጥር 27- የካቲት 1/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስለሆነም በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ተፈትናችሁ ያላለፋችሁ እና ከጥር 27 - የካቲት 1/ 2016 ዓ.ም ድረስ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተፈታኞች በሙሉ ምዝገባ የምታካሂዱትና የመፈተኛ ተቋም (የመንግስት ዩኒቨርሲቲ) የምትመርጡት ከታች በተገለጸው ማስፈንጠሪያ (Link)
(https://exam.ethernet.edu.et)
ስለሆነ፣ ከጥር 08 እስከ ጥር 15/ 2016 ዓ.ም ድረስ የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በቴሌ ብር ብቻ በመክፈል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

አመልካቾች ተጨማሪ ድጋፍ የምትፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር +251 118 13 21 76 ወይም በኢሜይል [email protected] በኩል ድጋፍ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ
1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የምታካሂዱት እና የአገልግሎት ክፍያ የምትፈፅሙት በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊው የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል። @MOE @rada_college

RADA College HO

03 Nov, 16:40


የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል!

#Ethiopia | የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 255 ያመጡ

የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ700 -234 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ600- 218 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 200 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 224 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 - 192 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 180 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 - 180 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 180 ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ500 -150 ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ500 -150 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።
MOE
@rada_college

RADA College HO

09 Oct, 19:26


ውጤት እንዴት መመልከት ይቻላል ?

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች መገ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

በዌብ ሳይት 👉 https://eaes.edu.et/

በአጭር የጽሑፍ መልዕክት 👉 6284

በቴሌግራም 👉 https://t.me/eaesbot

#MoE

@rada_college

1,283

subscribers

43

photos

1

videos