BMW በቻይና ፈጣን የሆኑ የሚኒ ኩፐር ኤሌክትሪክ ሞዴል መኪኖች ማምረት ጀምሯል።
BMW ቡድን በቻይና ዣንግጂያጋንግ በሚገኘው ፋሲሊቲ ውስጥ የኤሌክትሪክ ከፍተኛ ጉልበት እና ፍጥነት ያላቸውን ሞዴሎች በሚኒ ኩፐር ስር (JCW) ኤሌክትሪክ እና ሚኒ JCW Aceman ሞዴሎች ማምረት ጀምሯል። ሁለቱም ሞዴሎች 258 የፈረስ ጉልበት እና 350 Nm የማሽከርከር ኃይል የሚያቀርቡ ሲሆን የ Boost ተግባር ለፍጥነት ደግሞ ተጨማሪ 27 የፈረስ ጉልበት ይጨምራል። JCW ኤሌክትሪክ በ 5.9 ሰከንድ ውስጥ ከ0-100 ኪሜ በሰዓት ይደርሳል, JCW Aceman በ 6.4 ሰከንድ ውስጥ ይከተላል:: ሁለቱም በሰአት 200 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ከፍተኛ ፍጥነት አላቸው። በ 54.2 Kwh ባትሪ ሲኖራቸው በአንድ ቻርጅ 355 ኪሎ ሜትር ርቀት ይጟዛሉ። የአገር ውስጥ ምርት፣ በ BMW እና በ Great Wall Motors መካከል በተደረገው ትብብር፣ እነዚህን ሞዴሎች እንደ Zeekr X ካሉ ሌሎች ኤሌክትሪክ መኪኖች ጋር እንዲወዳደሩ በማድረግ ተወዳዳሪ ዋጋን እንዲኖር ያስችላልም ተብሏል ::
@OnlyAboutCarsEthiopia