ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች @mzmur_ortodox Channel on Telegram

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

@mzmur_ortodox


በአይነቱ ልዩ እና ኦርቶዶክሳዊ ለዛና አስተምህሮ የጠበቁ ቀደም ያሉ ዝማሬዎች እምያገኙብት

እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን እሚያገኙበት

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች (Amharic)

ከዚህ በኋላ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች በተባሉ በቅርብ ወሬዎች እና ፈተናዎች መካከል ዓምዲ አርቲስት በተባለው ቶኪሎጂ ጨካኞችን የትምህርት ምንጭ ይዞታል። የሚከተለውን መዝሙር በአስቸጋሪዎች በመከላከል ወሰን ማዘጋጃ እንዲሰራ መሸመጊያ አስገምግሰዋል። ይህን ቦታ ከሚካሄዱ ኦዲዴን ቅንብሮች በመሆኑ አማካኝ ተኮርተዋል። ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች በማንኛውም ኦንላይን በቀናት ትልቅ ማስገንቱ ተወግዷል። የሚሆን እራሱን እናምዳለ።

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

02 Oct, 09:15


#እንኳን #ለፆመ_ጽጌ በሳላም አደረሳቹህ

✤ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው (ከሰዓትም ቅዳሴ የሚቀደሰስባቸው አካባቢዎች አሉ (ጎንደር )፡፡
በግዕዝ ጸገየ ማለት   አበበ ፤ አፈራ ፣ በውበት ተንቆጠቆጠ ማለት ነው፡፡ 
በማኀሌቱም ወቅትን እመቤታቸንን 3 ዓመት ከ6 ወር እስከ ግብፅ ከዚያም የአሥራት ሀገሯ  በሆነችው በኢትዮጵያ የተሰደደችበትን ወቅት በማሰብ  በጽጌና በአበባ እመቤታቸንን እና ጌታቸንን በመመሰል ሲያመሰግኗት ፣  ከልጇ ጋር ያየችውን መከራ  እያሰቡ  እና  ምልጃዋን ሲለምኑ ያድራሉ ፡፡

✤እምግብጽ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን፤ ለቅዱሳን ክብር ልጄን ከግብጽ ጠራሁት››
በማለት ነቢዩ ሆሴዕ በምዕራፍ ፲፩ ቍጥር ፩ እና ፪ ላይ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልጅነቱ ወደ ምድረ #ግብጽ (ምስር) የተሰደደው የነቢያት ትንቢት ይፈጽም ዘንድ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕፃናትን በመፍጀት ከሚታወቀው ከአረመኔው ንጉሥ ከሄሮድስ ለማምለጥ ነው፡፡ አምላካችን ክርስቶስ ያለጊዜው (ዕለተ ዓርብ) #ደሙ #አይፈስምና፡፡ ስለዚህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ለመግደል ይፈልጋልና›› ብሎ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ለዮሴፍ በነገረው ቃል መሠረት ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ምድር ተሰደደ፡፡ ይህንን ስደት አስመልክቶ #ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር ካህናቱ በሚያሳዝን ዜማ ያደርሳሉ፤ ያቀርባሉ፡፡

#በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሕፃናትን ሄሮድስ አስፈጅቷል፡፡ ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ለቅሶና ብዙ ዋይታ፡፡ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፡፡ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና›› የሚለው ትንቢትም ተፈጸሟል፡፡

#ከሦስት ዓመት ከመንፈቅ የግብጽ ስደት በኋላ ሊቃውንቱ፡- ‹‹ተመየጢ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፣ በላዕሌኪ አልቦ ዘያበጽሕ ሁከተ፣ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፣ ዘየኀሥሦ ለወልድኪ ይእዜሰ ሞተ፣ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ›› እያሉ ከስደት መመለሷን ያበሥራሉ፡፡ ትርጉሙም፡- ‹‹ማርያም ሆይ! ወደ ሀገርሽ ወደ ናዝሬት ተመለሺ፡፡ በአንቺ ላይ ሁከት የሚያመጣ ማንም የለም፡፡ ቤት እንደሌለሽ ሁሉ በግብጽ አትቆይ፡፡ ለዮሴፍ በሕልሙ መልአክ እንደ ነገረው የሕፃኑን ነፍስ የፈለገው (ጠላት ሄሮድስ) ሞቷልና›› ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በዐርባው ቀን (በዘመነ ጽጌ) ወቅት የማርያምን የሽሽትና የመመለስ (የሚጠት) ታሪክ እያነሡ ውዳሴ የሚያቀርቡትና ማኅሌት የሚቆሙት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ለእመቤታችን ክብር ሲባል የፈቃድ ጾም የሚጾሙ ምዕመናንና ምዕመናትም ብዙዎች ናቸው በመሃል ኢትዮጵያ  በፈቃድ ጾምነት ሲጾም ; በሰሜኑ አካባቢ ተጹሞ ከሰዓት ይቀደሳል ሌሎች ጋር ግን ጠዋት ያበቃል፡፡

የእመቤታችን ምልጃ ና ጸሎት አይለየን

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

14 Aug, 08:32


ጠቢቡ ሰሎሞን ከመዝሙር በሚበልጠው  መዝሙሩ “በዓለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ፥ ቃልሽ መልካም ፊትሽም ያማረ ነውና መልክሽን አሳዪኝ፥ ድምጽሽንም አሰሚኝ።” መኃ 2፥14 እያለ ይዘምራል። ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንም የዚህን ጠቢብ ዝማሬ ተቀብላ አብራው ታዜማለች። ለመሆኑ ይህች ርግብ ማን ናት?

ስለ ርግብ ስናነሳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውስታችን ወደ ኦሪት ዘፍጥረት ይወስደናል። በዘፍጥረት ምዕራፍ 8 ላይ እንደምናነበው  ዓለም በበደል ኃጢአት በንፍር ውሃ ስትጠፋ የእግዚአብሔርን ወገን ከያዘችው መርከብ አካባቢውን እንድትቃኝ ተልካ ነበር። ርግቢቷም የሰላም የምስራች ለምለም ቀጤማን ይዛ ወደ ኖኅና ቤተሰቡ ተመለሰች።

የርግቧ ከለምለም ሳር ይዞ መመለስ ለኖኅና ቤተሰቡ ደስታ ነበር። ከጠፋው ዓለም ጋር አብረው ላለመጥፋታቸው፤ ከመርከቡ ጋር ላለመዋጣቸው ከመርከብ በኋላ ያለው ሕይወታቸው መልካም መሆኑን ማሳያ ነበር። የርግቧና የለምለም ቀጤማው መመለስ የአዲስ ዘመን፣ የሰላም ዘመን፣ የደኅንነት ዘመን የመምጣት ምልክት ነበር። ለምለም ቀጤማውን የያዘችው ርግብ ዛሬም ድረስ የምድራዊ ሰላም ምልክት ናት።

ከዚህች ርግብ የተሻለችውን ምልክት፤ ከለምለሙ ቀጤማ የተሻለ የልምላሜ ምንጭ የሆነውን ክርስቶስን የያዘችው ቤተክርስቲያን ጌታ ራሱ በሠራት መርከብ (ቤተክርስቲያን) ከዓለም ጥፋት ለሚከለሉ ሁሉ ምልክት ያደረጋትን ድንግል ማርያምን ከፊት አድርጋ በመግቢያው ላይ ያስቀመጥነውን የሰለሞንን ዝማሬ ትቀኛለች።

በርግጥም የሰላሙ አምላክ የሆነው ክርስቶስን ካሳየችን፣ ካመጣችልን፣ ለቃሉ ማደሪያነት በተገባ መልክ ከተዘጋጀችው ከድንግል ማርያም በስተቀር ማን ርግብየ ሊባል ይችላል?

በርግብ የሚመሰል የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም በስተቀር ማን በርግብ ይመሠል ዘንድ ይችላል?

መካን የነበሩት ጴጥርቃና ቴክታ በህልማቸው ካዩት የትንቢት ርዕይ ከሰባት የነጫጭ ርግቦች የዘር ሐረግ ከተገኘችው ጨረቃ በስተቀር ማን ርግቧን ይመስልልናል?

የወለደች ርግብ ከልጇ ጋር ስትጫወት በተመለከቱ ጊዜ የተከዙ የሐናና የእያቄም ፍሬ ከሆነች ከድንግል በስተቀር ያቺ ርግብ ማንን ትሆናለች?

ሐና በራዕይዋ ያየቻት በክንፎቿ በርራ በራሷ ካደረች በጆሮዋም ገብታ በማህፀንዋ ከተቀመጠች ከፀዐዳዋ የሐናና የእያቄም ፍሬ በስተቀር ያቺን የምሕረት፣ የበረከት፣ የሰላም ርግብ ማን ይመስልልናል?

ስለዚህ ሁሉ ቅድስት ቤተክርስቲያን ከሰለሞን ጋር በመሆን ንዒ ርግብየ እያለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ትጠራለች።

ከቅዱስ ኤፍሬም ጋራ ሆና "አካላዊ ቃልን ያስገኘሽልን መልካሟ ርግብ ሆይ ደስ ይበልሽ" ትላለች።

ከማኅሌተ ጽጌ ጸሐፊያን ከአባ ጽጌ ድንግልና ከአባ ገብረ ማርያም ጋር በመሆን "አንዲቷ ርግብ ማርያም ሆይ አንቺ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ሆነሻልና ተዓምርሽን አደንቃለሁ" እያለች ለዓለም ሁሉ የመጣውን መድኃኒት ያስገኘችውን ድንግል ማርያም ታከብራታለች።

እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ "መንፈሳዊው ርግብ መንፈስ ቅዱስ በየዋኅነቷ በርግብ ስለተመሰለችው የእመቤታችንን የምስጋና ኃይለ ቃሉን ያሳስበኝ ዘንድ እንዲገባ የልቦናዬን ደጅ ክፈት" በማለት እየለመነች መጽንዒ ወመንጽዒ ወደ ሆነው ወደ መንፈስ ቅዱስ ትጸልያለች።

ጾመ ፍልሰታውን የዋኅ ርግብ እናታችን ማርያምን ንዒ ብለን የምንጠራበት፣ ፍቅሯና እናትነቷ የልጇም ጌትነት በጸሎታችን ምላሽ፣ በረድኤትና በቸርነት የሚገለጡበት ጊዜ ያድርግልን።
https://t.me/mzmur_ortodox

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

14 Aug, 08:15


ደቀ መዝሙርህ ነኝ
ገጣሚ_ህሊና

https://t.me/mzmur_ortodox

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

05 Sep, 05:20


📢 : ጳጉሜ ማለት ምን ማለት ነው ?
📢 : የጳጉሜን ጾም ለምን እንጾማለን ?
በ ኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ጳጉሜ የምትባልአምስት(ስድስት)ቀን አለች።ይቺ
ጳጉሜን ወር እንዳንላት 25 ቀን ይጎላታል።ሳምንትም
እንዳንላት 2 ቀን ያንሳታል። ለወርም ለሳምንትም አቅም
የሚያንሳት ጳጉሜ በአመቱ መጨረሿ ላይ ትገኛለች።

ጳጉሜ የሚለው ስያሜ '' ኤፓጉሜኔ ''ከሚለው የግሪክ
ቃል የመጣ ሲሆን ትርጓሜው "ተጨማሪ" ማለት ነው።
በመሆኑም ጳጉሜ የአመቱ ምራቂ ቀናት እንጂ ወር ወይም ሳምንት አትባልም። አውሮፓውያን በአመቱ ወራ
ት ውስጥ በታትነዋታል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ሊቃው
ንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የአመት ተጨማሪ
በማድረግ የአመቱን ቀን 365 ወይም 366 ቀን ብለው
ደምረውታል።
ጳጉሜ በየአመቱ አምስት ወይም ስድስት ቀን ሆና የም
ትመጣ ናት።በአራት አመት አንዴ ጳጉሜ ስድስት ሆና ት
መጣለች በዚህም የአመቱ በዓላት ቀናትን ትቀይረዋለች
ለምሳሌ የገና በዓል በአራት አመት አንዴ ታህሳስ 28 ቀን ሲውል ሌላውን ግን 29ኝን አይለቅም። በዚህም ኢ
ትዮጵያ የ 13ወር ፀጋ ባለቤት እና ከአፍሪካም ከአለም
ም ብቸኛ የሯሷ አቆጣጠር ያላት ሀገር ያደርጋታል።

እስካሁን ሳይንስ ያልደረሰበት ነገርግን የቤተክርስቲያን
ሊቃውንት በሚገባ የሚያውቁት ጳጉሜ በ 700 አመት
አንዴ ሰባት ትሆናለች።ለዚህም ብቸኛዋ ማስረጃ ተዋህ
ዶ ሐይማኖትና ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተክርስቲያን
ናት።
የጳጉሜ ፆም(ፆመ ዮዲት)
ይህች ፆም ከሁለቱ የፈቃድ ፆም አንዷ ናት አንዱ ፆመ
ፅጌ ሲሆን ሁለተኛዋ ይህች የጳጉሜ ፆም ናት።በብዙ ሀን ዘንድ ባትታወቅም ታላቅ የበረከት እና እራስን የም
ናድስባት ጾም ነች።

የጰጉሜ ጾም ጾመ ዮዲት በመባልም ትታወቃለች ይህም
ዮዲት እረሷ ስለፆመችው ነው። ዮዲት ስላችሁ የቤተክር
ስቲያን አጥፊየሆነችው የዲት ጉዲት እንዳልሆነ አሰምሩ
ልኝ። ታሪኩም እንዲህ ነው።

የፋርስ ንጉስ ናቡከደነ ፆር በሰራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀ
በልክ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለ
ሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ መ ዮዲት 2:2-7።

እርሱም እንደታዘዘው በሀይላቸው የሚመኩትን 12ሺ
እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡትን 12ሺ ጦረኞችን እየ
መራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን
እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሄድ ከ አይሁድ ከተ
ማ ደረሰ በዚያም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ል
ጆች አለቀሱ።

ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ እርቃ ንፅህናዋን ጠብቃ
በፆም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች።በተፈጠረው
ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራሷ
ላይ ትቢያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች።የፍጥረ
ቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር ህዝቡን የሚያድንበት
ን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሶስተኛው ቀን
መለሰላት ዮዲ 8 :2

ከዚህም በሁዋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤልያዊያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋ
ቸዋል። ዮዲት ጠላቷን ማጥፋት የቻለችው በፆም እና
በፀሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ሀይልን አግኝታ ነው።

ጳጉሜ የአመቱ መገባደጃና መሸጋገሪያ እንመሆኗ መጠን እጅግ ድንቅ ቀናት ናት።ይህች ወር የዳግም ም
ፃት መታሰቢያ ናት,የዘመነ ፍዳ መገባደጃ ከ ቁር ብርዱ
መላቀቂያ በመሆኗ ብዙ እና አያሌ ጥቅም አላት።

ስለዚህ ምዕመና በየ አመቱ ጳጉሜን የቻለ በመፆም በ
በመፀለይ መጪውን አመት የተሻለ እንዲሆን እራስን በ
ማዘጋጀት ፀበል በመጠመቅ በልዩ ዝግጅት ያሳልፋሉ።

አሜን

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

27 Jul, 17:27


ወቅቱን በደንብ የሚገልፅ ስዕል፤ ይህ ስዕል ከተቻለ በደንብ ተስሎ ለታሪክም ለትውልድም በየ ቤተክርስቲያናቱ መቀመጥ ያለበት የጥበብ ስራ ነው።
እስኪ የገባው? በኮሜንት፤

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

24 Jul, 16:36


የአራቱ ኪሩቤልን ስም ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ይላቸዋል
፩) ባራማራ
፪) እግረማጣ
፫) ሱርትዮን
፬) መሊጦን
ይላቸዋል። ሃይማኖተ አበው ላይ ስለዚህ ኪሩቤል ሲናገር መናብርት ነባብያን ይላቸዋል። የሚናገሩ መናብርት ይላቸዋል። ከሱራፌል ነገድና ከኪሩቤል ነገድ ሁለት ሁለት ተመርጠው በጠቅላላው አራት ኪሩቤል አሉ። እንደገና በኢዮር ከሚገኙት አርባ ነገዶች አሥሩ ነገድ ኪሩቤል ይባላል።

ሰአሉ ለነ ኀበ እግዚአብሔር ጸባዖት___ቅ. ያሬድ
(ኪሩቤል ሆይ ወደአሸናፊ እግዚአብሔር ለምኑልን)

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

15 Jul, 02:38


ከጲላጦስ ወደ ሔሮድስ ፥ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ ፥ ከሔሮድስ ወደ ቀያፋ አመላለሱት፨

ሥርዓቱን ፥ ቀኖናውን ፥ ዶግማውን የሚያውቁትም የማያውቁትም ጮኾበት፥ በሩን ዘጉበት ፨

በየጊዜው የሚፈስሰው የአረጋዊ አባት ዕንባ ምን ያመጣ ይኹን?

ብጹዕ አባታችን በረከትዎ ትድረሰን፨

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

10 Jul, 17:18


👉👉የቅዱስ አባታችን ጉዞ (ሁሉም ያየው ሀቅ )

በህገ ቤተክርስቲያን እንኳን ፓትርያርክ? አንድ ሊቀጳጳስ ሲመጣ ቄሰገበዙ የቤተመቅደሱን በር ይከፍታል ሊቀጳጳሱ ገብቶ ቅዱስ ብሎ ጸሎት አድርጎ ባርኮ ተከትለው የመጡትን አባታዊ ምክር ሰጥቶ ያሰናብታል

ዛሬ ግን ያየነው ይህን አይደለም

በየትኛውም ቦታ በስርዓት በህግ በምንም ቤተክርስቲያን አሐቲ ናት የእነገሌ የምትባል ቤተክርስቲያን የለችም አሁን ግን በአንዳንድ ግለሰቦች የእኛ የእነሱ የሚል ነገር ሲያነሱ ይሰማሉ ይህ ትክክል አይደለም

እንኳን በአንድ ሲኖዶስ ስር ያለች ቤተክርስቲያን በባለፈው ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የቀኖና ጥሰት ተፈጸመ ሲባል የግብጽ ሲኖዶስ መግለጫ አውጥቷል የህንድ ሲኖዶስ ትክክል አይደለም እኛ ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ይህን አንጠብቅም ወደነበራችሁበት ክብር ተመለሱ በማለት መግለጫ አውጥቷል ጉዳዩን ተቃውመዋል

ይህ የሚያሳየው ቤተክርስቲያን አሐቲ መሆንዋን ነው

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የምትገለገለው የግብጽ እና የግሪክ የእስክንድር ሊቃነ ጳጳሳት ባወጡት ህግ በሰሩት ስርዓት ነው የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጳጳሳት ካልሆኑ አልፈልግም አላለችም ሃይማኖተ አበው የእነሱ ነው ቅዳሴው የእነሱ ነው ቀኖናው ዶክማው የእነሱ ነው ስርዓተ ምንኩስናው የእነሱ ነው

ይህን ተቀብላ የምትገለገለው በቤተክርስቲያን የእኛ የእነሱ የሚባል ስሌለለ ነው

እንዲያውም እንናገር ካልንማ ግብጻዊው ሊቀጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስን አባቴ ትላለች ዮሐንስ አፈወርቅ አባቴ ቅዱስ አትናቴዎስ አባቴ ትላለች ከዚህ በላይ ምን ትምህርት አለ

👉👉ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ

ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ የበለጠ በሊቃውንቶችዋ በቅዱስ ያሬድ ዜማ አብባ አሸብርቃ በዓለም ከፍ ብላ ትታያለች ተብሎ ሲጠበቅ እየሆነ ያለው ተቃራኒ ነው

ሊቃነ ጳጳሳትን በጎጥ መሾም ጀምራለች ወዘተ ሌላም ሌላም

ሐምሌ ሁለት ቀን ቅዱስ አባታችን ለተፈጠረው ክፍተት ሽማግሌ አልክም እራሴ መሄድ አለብኝ ብለው ሊቃነጳጳሳት አስከትለው ልጆቻቸውን ለመባረክ ይቅርታ ለመጠየቅ መሄዳቸው ይታወቃል

አሁን በፎቶ አስደግፌ የላኩላችሁ ፎቶ ላይ እንደምናየው ከኤርፖርት ጀምሮ የክፍሉ ጳጳሳት አልነበሩም ካህናት አልተገኙም ሲቀጥል አካባቢው ወደአለው ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ዝግ ነው እንደማንኛውም በውጭ ተሳልመው ፓትርያርኩ ሲመለሱ አየን ይህ ትልቅ ስህተት ነው ከዚህ በላይ ስህተት የለም

በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የነውር ነውር ነው በፓትርያርኩ ላይ በርዋን የዘጋጅ ቤተክርስቲያን ለማን እንደምትከፈት አላውቅም

በመግቢያዬ ላይ እንደተናገርኩት በትግራይ ያሉ አቢያተ ክርስቲያናት ችግር ደርሶባቸዋል አወ በሚገባ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው ነገር ግን ይህ ችግር በትግራይ ብቻ ያቆመ አይደለም ወደ ወሎ ሂዱ የወደሙ አቢያተ ክርስቲያናት በአቡነ ኤርምያስ በዝርዝር ተነግሯል በሺዎች የሚቆጠሩ አቢያተ ክርስቲያናት ወድመዋል ጎንደርም እንደዚያም ባይሆን በተመሳሳይ

ነገር ግን የትኛውን ሲኖዶስ አኮረፉ በየትኛው ጳጳስ ላይ በር ዘጉ ለቤተክርስቲያን ከሲኖዶስ ከፓትርያርኩ በላይ እኔን ይመለከተኛል ማለት ጉም መጨበጥ አይሆንም ወይ

እንደማይመለከተን እያየን እየሰማን ዝም ያልናቸው ብዙ ነገሮች አሉ በሲኖዶስ አድርጎ ስርዓቱን ጠብቆ ይምጣ ብለን ዝም ያልናቸው ብዙ ናቸው እረ ስንቱ

አሁንም በእውነት እግዚአብሔር ያስተካክለን 🙏🙏🙏

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

08 Jul, 21:49


ሰንበተ ክርስቲያን

" ወዮ ይህች ዕለት አብ የቀደሳት ወልደ የባረካት መንፈስ ቅዱስ ከፍ ከፍ ያደረጋት ናት፡፡ በርሷ ደስ ይበለን፡፡ በርስዋም ኀሤት እናደርጋግ ትከብሩባት ዘንድ አክብሯት
ዘመን ወር ለመባል በርሷ የታወቃችሁ ሌሎች ዕለታት ሆይ የበዓላትን በኩር ኑ አመስግኗት ይህችውም የከበረች ሰንበተ ክርስቲያን ናት፡፡ "

     ቅዳሴ አትናቴዎስ
            https://t.me/mzmur_ortodox  

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

27 Jun, 17:14


‹‹ወይእዜኒ አንትሙ ከመዝ ግበሩ፤ ከእንግዲህ እናንተም እንዲሁ አድርጉ›› (መጽሐፈ ስንክሳር)

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕንጸተ ቤታ እና ቅዳሴ ቤታ የሚዘከርባቸው ሰኔ ሃያ እና ሃያ አንድ ቀን የከበሩ በዓላት ናቸው፡፡

እመቤታችን ባረገች በአራኛው ዓመት ጳውሎስና በርናባስ በፊልጵስዩስ ወንጌልን እያስተማሩ ነበር፡፡ ሕዝቡም አምነው ተጠመቁ፤ ነገር ግን ከእንግዲህ ጣዖት እንዳያመልኩና ወደ ጣዖት ቤትም እንዳይሄዱ ቢከለክሏቸው ‹‹የለመድነውን ከከለከላችሁንማ መካነ ጸሎት ስጡን›› ብለው አስገደዷቸው፡፡ ይህንንም ለመንገር ወደ ቅዱስ ጴጥሮስና ዮሐንስ ‹‹አልቦ ዘትገብሩ ወኢምንተኒ ዘእንበለ ትእዛዙ ወምክሩ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባም፤ እናንተም ጸልዩ፤ እኛም እንጸልያለን›› ብለው መልእክት ላኩባቸው፡፡ ሱባኤያቸውንም ሲጨርሱ ክብር ይግባውና ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ (ስንክሳሩ በሀገረ ቂሳርያ ዘኬልቄዶን ይላል መዝገበ ታሪክ ደግሞ በፊልጵስዩስ ይላል) ሰበሰባቸው፡፡

ዮሐንስ ‹‹ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን?›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹በእናቴ ስም ጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፋቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሳያችሁና ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው›› አለው፡፡ ይህንን ብሎ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው፤ ተራርቀው የነበሩ ሦስት ደንጊያዎች ነበሩ፤ በገቢረ ተአምራቱም አቀራርቦ ቁመቱንና ወርዱን መጥኖ ሰጣቸው፡፡ እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ /እየተሳቡ/ ቁመቱን ፳፬ ወርዱን ፲፪ ክንድ አድርገው ሠርተውታል፡፡ ‹‹ወአዕባንኒ ይለመልሙ በእዴሆሙ፤ ደንጊያዎችም በእጆቻቸው ይለመልሙ ነበር›› እንዲል፤ ከዚያም ‹‹ወይእዜኒ አንትሙ ከመዝ ግበሩ፤ ከእንግዲህ እናንተም እንዲሁ አድርጉ›› ብሏቸው ዐርጓል፤ ይህ የሆነው ሰኔ ፳ ቀን በ፶፫ ዓመተ ምሕረት ነው፡፡

በማግሥቱ ሰኔ ፳፩ ቀንም ጌታ እመቤታችንን ታቦት፣ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ዳግመኛም እጁን ጭኖ ቅዱስ ጴጥሮስን ፓትርያሪክ አድርጎ የሾመውም በዚህች ዕለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜም የሰማይ መላእክትና የምድር ሰዎች (ሐዋርያት) አንድ ሆነው አመስግነዋል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

https://t.me/mzmur_ortodox

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

07 Jun, 17:15


የክርስቶስ እስሩ የኔታ በመጨረሻም ከ27 ቀን በኋላ ለጊዜው ተለቀዋል ።

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

04 Jun, 18:02


+++ ለሐዋሪያት.. ፆም.. አደረሳችሁ+++
ፆመ ሐዋሪያት ወይም ሰኔ ፆም፣" ግንቦት 28 ይገባል(ይጀምራል)" ሐምሌ 5 ቀን ይፈታል።

ይህ ፆም ከቤተክርሰቲያናችን የአዋጅ አጿሞች ውሰጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋሪያት ጌታችንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ፆም ነው።

የሰኔ ፆም፦ ይህ ፆም የሐዋሪያት ፆም በመባል ይታወቃል፣ ሰለምን የሐዋሪያት ፆም ተባለ ቢሉ በበዓለ ዼራቅሪጦሰ ሐዋሪያት መንፈሰ ቅዱሰን ከተቀበሉ በጛላ የፆሙት ፆም ሰለሆነ ነው።

የሰኔ ፆም የሚፆምበት ጊዜያት፣ ቢያንሰ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይፆማል፣ የሰኔ ፆምን እሰከ 9 ሰአት እንድንፆም ቤተክርስቲያናችን አውጃለች።

የሚገባበት ቀን በየአመቱ የተለያየ ቢሆንም የፆሙ ማብቂያ ዕለት ግን ሐምሌ 5 ድረሰ ነው።

2015'ዓ'ም ግንቦት 28 ሰኞ ይጀመራል።👉ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት ፆም ነው።

💒 የሰኔ ፆም :- ይህ ፆም የሀዋርያት ፆም በመባል ይታወቃል ስለ ምን የሐዋርያት ፆም ተባለ ቢሉ በበአለ ጴራቅሪጦስ ሀዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በዉሀላ የፆሙት ፆም ስለሆነ ነው።

👉የሰኔ ዖም የሚፆምበት ጊዜያት
የሰኔ ፆም ቢያንስ 15 ቢበዛ 45 ቀናት ያህል ይፆማል የሰኔ ፆምን እስከ 9 ሰአት እንድንፆም ቤተክርስቲያን አውጃለች ።

💒 የሚገባበት ቀን በየአመቱ የተለያየ ቢሆንም የፆሙ ማብቂያ ዕለት ግን ሐምሌ 5 ድረስ ነው ። ሐምሌ 5 ሁለቱ ሀዋርያት ጴጥሮስ እና ጳዉሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉበት እለት ነው ።

💒 ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን አድርገዋል፡፡

👉ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ ጌታችን አስቀድሞ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹ እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው? አሉት ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ›› ማቴ 9፥15-16

💒 እኛም ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ‹‹መሣሪያ›› አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ ነው። አንድ አንዶች እንደሚሉት የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡

ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን በሰላም ያድርሰን!!!
ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን በሠላም ያድርሰን!!

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

04 Jun, 03:13


ሰንበት ት/ቤት ያልገባ ወጣትና ያልተተኮሰ ሸክላ አንድ ናቸው።
ሁለቱም ሲነኳቸው ይፈርሳሉና
አቡነ ሰላማ

እንኳን ለ12ኛው ዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች ቀን አደረሳችሁ አደረሰን

https://t.me/mzmur_ortodox

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

04 Jun, 03:12


መልካም በዓለ ጰራቅሊጦስ እና የሰንበት ት/ቤቶች ቀን 🙏

["የሕይወትን ቃል የተመገብንባት መሶባችን ናት "]

" አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤"(2ኛጢሞ3:14)
#እኔም_ሰንበት_ተማሪ_ነኝ

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

04 Jun, 02:15


"ርደተ መንፈስ ቅዱስ"
በዓለ ጰራቅሊጦስ

+++ቅድስት በምትሆን በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የአብ በረከት የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እና አንድነት በሁላችሁም ላይ ይውረድ ዕጽፍ ድርብም ይሁን! አሜን!+++

**ሥርዓተ ቅዳሴ***

🌷እንኳን ለቅድስት ቤተክርስቲያን ልደት በሰላም አደረሳችሁ🌷

ጰራቅሊጦስ› የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ሲኾን፣ ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በወረደበት ዕለት በቤተ ክርስቲያን የሚከበረው ይህ በዓል ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ወይም ‹በዓለ ጰንጠቆስጤ› በመባል ይታወቃል፡፡ ‹ጰንጠቆስጤ› በግሪክ ቋንቋ በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲካ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣ የመከር በዓል) ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፱፻፮-፱፻፯)፡፡

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች

01 Jun, 06:02


ምህረት ይዘንማል ከሰማይ
በአንድ እግርህ ቆመህ ስትጸልይ
ብዙ ተጋድለህ አትርፈሀል
ያገለገልከው አክብሮሀል
ከቅዱሱ አባት ከተክለሃይማኖት በረከት ይክፈለን። አባታችን ሆይ በፀሎትህ አትርሳን።